Professional Documents
Culture Documents
ኦወ 2015 ዓ.ም
የስሙ ትርጉም
በንጉሡ እና በሊቀ ካህናቱ መሃከል በተነሳ ጸብ ንጉሡ የበላይነቱን ለማሳየት ሃብተ ክህነት ሳይኖረው
ቤተመቅደስ ለማጠን ገብቶ ነበር።
ኢሳይያስም ሊገስጸው ሲገባ ዝም በማለቱ እግዚኣብሔር ከንፈሩ ላይ በለምጽ መትቶታል።
ዖዝያንንም በለምጽ መትቶታል።
እርሱንም ወስደው ጨለማ ቤት ዘጉበት:: ሃብተ ትንቢቱንም ተቀማ::
በዚያው ሆኖ ንስሃ ገባ: ጾመ: ጸለየ::
እግዚአብሔርም ንስሓውን ተመለከተለት:: ከዚያም ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት ኢሳይያስ
እግዚአብሔርን በረዥም [ልዑል] ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ: ኪሩቤል ተሸክመውት: 24ቱ ካህናተ ሰማይ
"ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ሲያመሰግኑት ተመለከተ:: ኢሳ (6:1)
ያን ጊዜ እግዚአብሔር "ወደ ሕዝቤ ማንን እልካለሁ?" አለ:: ኢሳይያስም "ጌታዬ! እኔ ከንፈሮቼ የረከሱ
አለሁ" አለው:: እግዚአብሔርም ሱራፊን ላከለት:: መልአኩም ፍሕም [እሳት] በጉጠት አምጥቶ ከንፈሩን
ቢዳስሰው ነጻ:: ሃብተ ትንቢቱም ተመለሰለት:: ይኸውም የሥጋ ወደሙ ምሳሌ ነው::
ከዚህች ቀን በኋላ ግን ኢሳይያስ የተለየ ሰው ሆነ:: ማንንም የማይፈራ እውነተኛ የልዑል ወታደር ሆነ::
ከዖዝያን በሁዋላ በየዘመናቸው 4ቱንም ነገሥታት ገሰጸ:: እነዚህም ኢዮአታም: አካዝ: ሕዝቅያስና ምናሴ
ናቸው::
ትንቢት ወ ተአምራት
ልዑለ ቃል ቅዱስ ኢሳይያስ ለ 70 ዘመናት ሕዝቡን አስተምሮ: ነገሥታቱን ገስጾ: 68 ምዕራፎች ያሉትን
ሐረገ ትንቢት ጽፎ አረጀ::
በዘመኑ የነበረው ንጉሥ ምናሴ ግን ይባስ ብሎ ጣዖትን አቆመ: ለጣዖትም ሰገደ:: ቅዱሱ ይህንን
ሲያደርግ ዝም አላለውም:: በአደባባይ ገሰጸው እንጂ::
በዚህ የተበሳጨ ምናሴም ሽማግሌውን ነቢይ በእንጨት መጋዝ ለሁለት አሰነጠቀው:: ቅዱስ ኢሳይያስ
በዚህ ዓይነት በጐ ሕይወት መስከረም ፮ [6] ቀን ሩጫውን ፈጸመ::
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይኹን፤ እኛንም በጸሎቱ ይማረን፤ በረከቱም ከኹላችን ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ
አሜን!!!