You are on page 1of 10

በለሚ

ኩራ

የ2016 ዓ.ም ቀጣይ 100


ቀናት(ከጥቅምት 01,

ጥቅምት 2016 ዓ.ም

አዲስ አበባ

በለሚኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ፅ/ቤት


የተቋሙ ራዕይ፤ ተልዕኮና እሴቶች

የተቋሙ ራዕይ /Vision

በ 2022 ወሳኝ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ ለነዋሪዎቿ እና ለጎብኚዎቿ ምቹ የሆነች ፤ ዘላቂ እና

ችግሮችን መቋቋም የምትችል አዲስ አበባን ማየት፡፡

የተቋሙ ተልዕኮ /Mission

በጥናትና ምርምር የተደገፈ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን በማልማትና ደህንነቱ

የተጠበቀ ሲስተሞችን በማበልጸግ እና ዲጂታል አገልግሎት በማስፋፋት የአዲስ አበባን ከተማ

ነዋሪዎች እና የጎብኚዎቿን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፡፡

የተቋሙ እሴቶች /Values

 በጎ ሕሊናና ቅን ልቦና

 የላቀ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት

 አዳዲስ ፈጠራዎችን ማመንጨት

 የስራ ፍቅርና ትጋት

 ተጠያቂነት

 ግልፅኝነት

 በትብብር መስራት

 ቀልጣፋና ውጤታማ አግልግሎት


የተቋሙ ተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላት

ተገልጋዩች

 የክ/ከተማ አስተዳደሩ ተቋማት

 መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት

 ቴክኖሎጂ አቅራቢና አምራች ድርጅቶች

 የክ/ከተማዋ ማኅበረሰብ

 የክ/ከተማዋ ነዋሪዎች

 የጥናትና ምርምር ተቋማት

 የፈጠራ ባለሙያዎች

ባለድርሻ አካላት

 ኢትዮ-ቴሌኮም

 የመረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር

 ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ

 የግል ሴክተርና ኢንዱስትሪዎች

 የለሚ ኩራ ክ/ከተማ መንግስታዊ ተቋማት

 የቴክኖሎጂ አቅራቢ ድርጅቶች፣

 መብራት ኃይል፣

 አርቴፊሽል እንተለጀንስ ማዕከል

 ትምህርት ቤቶች እና ቴክኒክ ሙያ ኮሌጆች


ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች

1. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት

 ዉጤት፡- ትራትና ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማተና ሲስተም


ማሳደግ
2. ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኦፕሬሽንና አገልግሎት

 ዉጤት፡- ቀልጣፋና ቀጣይነት ያለዉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ተደራሽነት


3. ስማርት ሲቲ
 ዉጤት፡- በጥናትና ምርምር የተለወጠ እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የዘመነ ከተማ
ተግባር ዝርዝር ተግባራት የሚከናወንበት ወር ፈፃሚ አካል
ከጥቅምት 1 እስከ 30, 2016 ዓ.ም ከህዳር 1 ከታህሳስ ከጥር 1
እስከ 30, 1 እስከ 30, እስከ
10, 2016
2016 ዓ.ም 2016 ዓ.ም
ዓ.ም

ተግባር 1፡- ሶስት የቴክኖሎጂ ስልጠናዎችን መስጠት     የስልጠና ቡድን

   
ተግባር 2፡- ለ 89 ሰልጣኞች የቴክኖሎጂ ስልጠና መስጠት የስልጠነ ቡድን

 
ተግባር 3፡- 2 ፅ/ቤቶችን አገልግሎታቸዉን ወደ ዲጂታል የሶፍትዌር ቡድን
ሲስተም እንዲቀይሩ አስፈላጊዉን የሶፍትዌርና
የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ማከናወን
 
ተግባር 4፡- የክ/ከተማዉን ዌብ-ሳይት ማበልፀግ የሶፍትዌር ቡድን

  
ተግባር 5፡- ለ 2 ወረዳዎች የኔትወርክ ዝርጋታ ጥናት የመሰረተ ልማት ቡድን እና
በማጠናቀቅ ዝርጋታዉን ማጠናቀቅ የጥናት ኮሚቴ
  
ተግባር 6፡- በቀጣይ 100 ቀናት ሁሉንም ሴክተሮች የመሰረተ ልማት ቡድን
የብሮድባንድ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ማድረግ
 
ተግባር 7፡- የአዲሱን ህንፃ ደህንነት መከታተያ ካሜራ ስራ የመሰረ ልማት ቡድን
ማስጀመር
   
ተግባር 8፡- ለ 144 ኤሌክትሮኒክስ ማቴሪያሎች የጥገና ቡድን
የመጀመሪያ ደረጃ ጥገና(Priventive
Maintainance) ማድረግ
   

   
ተግባር 9፡- ለ 500 ኤሌክትሮኒክስ ማቴሪያሎች ጥገና የጥገና ቡድን
ማድረግ
   
ተግባር 10፡- የኤሌክትሮኒክስ ማቴሪያሎችን በመጠገን የጥገና ቡድን
300,000 የመንግስት ወጪን ማዳን
 
ተግባር 11፡- 20 ሴቶችን ልዩ የቴክኖሎጂ ስልጠና ተጠቃሚ የስልጠና ቡድን
ማድረግ
   
ተግባር 12፡- በበጎ አድራጎትና ማህበረሰብ አገልግሎት ክ/ከተማ ኢ/ቴ/ል/ፅ/ቤት

ለአንድ ህፃን 3000 ብር ድጋፍ ማድረግ


  
ተግባር 13፡- 72 የሚገኙ የኔትወርክ መሰረተ ልማቶችና የመሰረተ ልማት ቡድን
ሰርቨር ወደ አያት በማምጣት የኔትወርክ
ዝርጋታ ማከናወን
  
ተግባር 14፡- 72 የሚገኘዉን የቪዲዮ ኮንፍረንስ አገልግሎት የመሰረተ ልማት ቡድን
ወደ አያት በማዘዋወር አገልግሎት ማስጀመር
 
ተግባር 15፡- ለክ/ከተማችን ት/ቤቶችና ጤና ጣቢያዎች ክ/ከተማ ኢ/ቴ/ል/ፅ/ቤት
የኔትወርክ ዝርጋታ ጥናት ማከናወን
 
ተግባር 16፡- በክ/ከተማችን ስር ተበላሽቶ የሚገኙ የጥገና ቡድን
ኤሌክትሮኒክስ ማቴሪያሎችን በመለየት
የሚጠገኑትን ጠግኖ ወደ ስራ ማስገባትና
መወገድ ያለባቸዉን ማስወገድ
  
ተግባር 17፡- የዲጂታል ሳይን ኤጅ አገልግሎት እንዲጀምር የመሰረተ ልማት ቡድን እና
ቴክኒካል ድጋፍ ማድረግ የሶፍትዌር ቡድን

ተግባር 18፡- ለአንድ ፅ/ቤት የወረፋ መጠበቂያ ሲስተም የመሰረተ ልማት ቡድን እና
አገልግሎት እንዲጀምር ቴክኒካል ድጋፍ የሶፍትዌር ቡድን
ማድረግ
ማስፈጸሚያ አቅጣጫዎችና ስልቶች

የማስፈጸሚያ አቅጣጫዎች

የቀጣይ 100 ቀናት እቅድ ለማስፈጸም ቀጣዮቹን የአፈጻጸም አቅጣጫዎች የምንጠቀም ይሆናል፡፡

 ዕቅዱ እንዲሳካ የተቀናጀ የአመራር አሰጣጥ ሂደትን እንከተላለን፡፡


 እቅዳችን የተግባራቶቻችን ሁሉ መነሻ በመሆኑ ይህን የተገነዘበ የአፈጻጸም አቅጣቻዎች እንከተላለን፡፡
 የክ/ከተማችን የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተገልጋዩን ማህበረሰብ ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት አባካኝ
ከሆኑ ልማዳዊ አሠራሮች ወጥተዉ ወደ ፈጣን የቴክኖሎጂ አገልግሎት አሰጣጥ ዘዴ እንዲገቡ
የአገልግሎቶቹን ተደራሽነት ማስፋትን የትኩረት አቅጣጫችን ይሆናል፡
 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የፈጠራ ማህበረሰብ የሚበረታቱበትና የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ምርት
በማስፋፋት የህዝቡን ችግር ለመፍታት ሀገር በቀል የፈጠራ ባለሙያዎች በጥራትና በብዛት ለማፍራት
እንሰራለን፡፡
 በየደረጃው የሚገኘውን የሰው ኃብት ልማት ስራዎች ጥራትና ውጤታማነትን ማዕከል በማድረግ
ተጠናክረው የሚሰሩበትን አቅጣጫ እንከተላለን፡፡
 የሪፎርም ስራዎች በአግባቡ እንዲሰሩ የለውጡን መንፈስ መሠረት በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡ
እንዲሻሻልና የሚሰጡት አገልግሎቶች የህዝቡን ፍላጎትና ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረጉ እንዲሆኑ በጥብቅ
ይሰራል፡፡
 ከላይ የተቀመጡ ተግባራት ግብ ለማሳካት ዋነኛው አቅጣጫ የዘርፉ አመራር እና ፈፃሚ የተስተካከለ
አመለካከት፣ ስራውን በተቀመጠው አግባብ መፈፀም የሚያስችል በቂ ክህሎት እና የስራ ተነሳሽነትና
ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም በየደረጃው ያሉ የዘርፉ አመራርና ፈፃሚ ሰራተኛ እቅዱን አውቀው
ተግባራዊ እንዲያደርጉ ይደረጋል፡፡
 ሁሉም ዘርፎች፣ ከአስተባበሪ እስከ ፈፃሚዎች ድረስ የራሳቸውን እቅድና የድርጊት መርሃ ግብር አዘጋጅተው
ስራው በእውቀትና በተነሳሽነት እንዲፈፅሙ የማድረግ አቅጣጫዎችን እንከተላለን፡፡
 ተግባርን ማዕከል ያደረገ ግምገማ በየደረጃው ይደረጋል፣ ግምገማው በእቅድ አፈፃፀሙ ያጋጠሙ
የአመለካከት፣ የክህሎትና የግብዓት ችግሮች፣ መንስዔ ፣ የመለየት አቅጣጫ በመከተል እንዲፈፀሙ ማድረግ
እና መልካም ልምዶችን የማስፋት ስራ ላይ እንዲያተኩር የማድረግ አቅጣጫ እንከተላለን፡፡

የማስፈጸሚያ ስልቶች

በ 2016 ዓ.ም ቀጣይ 100 ቀናት(ጥቅምት፤ህዳርና ታህሳስ) የተያዘውን ተግባራቶች ለማስፈጸም ቀጥሎ
ያሉትን መሰረታዊ የማስፈጸሚያ ስልቶች ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት የምናደርግ ይሆናል፡፡

1) የተለያዩ አካላትን አቅም መጠቀም፡፡

 ከግልና ከቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በትትብር መስራት የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት፣


2) ስትራቴጂክ እቅዳችንን ማእከል ማድረግ፡፡

 የተቋሙ የዕለት ከዕለት የስራ እንቅስቃሴዎች ከስትራቴጂ ጋር እዲተሳሳሩ ማድረግና ስትራቴጂያዊ


ፋይዳቸውን በመረዳት መተግበር፣
 የዕቅድ አፈጻጸምን በሚመለከት ራሱን አስችሎ መምራትና መከታተል፣

3) ፕሮጀክቶችን በትኩረት መምራት፡፡

በእቅዳችን ለመፈጸም ከያዝናቸው ተግባራቶች መካከል በርካታ ፕሮጀክቶች ያሉ በመሆኑ ፕሮጀክቶችን


በተገቢው መንገድ ለማጠናቀቅ የሚያስችል አካሄድ መከተል አስፈላጊ ነው፡፡

የክትትል ድጋፍ ግምገማና ሪፖርት ስርዓት

የክትትልና ግምገማ ስራችን በቁልፍ ግቦች ላይ በማተኮር ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ኢኮቴ ቡድን ጋር
ተመጋጋቢነት ባለው አግባብ ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን የተሟላ ጥራት ያለውና ወቅቱን የጠበቀ
ድጋፍ በማድረግ የእቅዱን አፈፃፀም ለማሳደግ የሚረዳ መሳሪያ ነው፡፡

በውስን ሃብትና ባልተሟላ የማስፈፀም አቅም ለሚካሄዱ ስራዎች ውጤታማነት፣ ስኬትና በሂደት
የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታትና በሌላ በኩል ደግሞ ያለው ውስን ሃብት በስራ ላይ መዋሉ፣
አለመዋሉን በማወቅ ወቅታዊ እርምጃ ለመውሰድ እንዲቻል የልማት ፕላን አፈፃፀም ክትትል፣
ግምገማና ግብረ መልስ ስራ ማከናወን ተገቢ ነው።

የክትትልና ድጋፍ ሥርዓት

ክትትልና ድጋፍ በማያቋርጥ ሁኔታ በማጠናከር ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃን የማሰባሰብ፣


የማጠናቀር፣ የመተንተን፣ የመረጃ ልውውጥን የማከናወንና የመፍትሄ ሀሳብ የማመንጨት ሂደት
ነው፡፡ የተዘጋጀውን እቅድ አፈፃፀም ውጤትን ለመከታተልና ለመደገፍ የሚያስችል ጠንካራና
ቀጣይነት ያለው ክትትልና ድጋፍ ስርዐት ይዘረጋል፡፡ ከለሚ ኩራ ክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ
ልማት ፅ/ቤት በተዋረድ ከሚገኙ የሴክተር ፅ/ቤቶች የኢንፎርሜሽን ዳይሬክቶሬቶችና ወረዳዎች
በየጊዜው በሪፖርት፣ በስልክና በአካል ግንኙነት በማድረግ የእቅድ አፈፃፀም ሂደቱን በመከታተል
አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

የግምገማ ስርዓት

ግምገማ የተግባር አፈፃፀምን እየፈተሹ፣ መረጃ በማሰባሰብ ጥንካሬና ድክመቱን እየለዩ የአፈፃፀም
ማሳለጫ ውሳኔ የሚወሰንበት ሂደት ነው፡፡ ግምገማው በእቅዱ ጊዜ የነበሩ አፈፃፀሞች፣ ያጋጠሙ
ችግሮችን የተገኙ ተሞክሮዎችንና ውጤቶችን እንዲሁም የታየውን ለውጥ በዝርዝር በመመልከት
ተገቢ የውሳኔ ማስተላለፊያ ተግባር ነው። በመሆኑም ተግባራችንን ውጤታማ የሚያደርግ
የግምገማ ስርአት ተዘርግቶ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ በዚህም የባለ ድርሻ አካላትን በማሳተፍ የእቅድ
አተገባበርና የውጤት መሻሻል ሪፖርት ቀርቦ በዝርዝር እየተገመገመ አፈፃፀሙ እንዲጎለብት
ይደረጋል፡፡

You might also like