You are on page 1of 42

ገለፃው የሚያተኩርባቸው ነጥቦች

1. መግቢያ
2. የማዕድን ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ስልጣን ተግባር
3. የማዕድን ሥራዎች ህግጋት
4. የማዕድን ሥራዎች ህግጋት ዓላማዎች
5. ዋና ዋና የማዕድን ሀብት አስተዳደር ህጎች አዋጅ ቁጥር 678/2002 የተመሰረተ
6. ጥፋቶችና ቅጣቶች ( በደንብ ቁጥር 423/ 2010 ላይ የተመሰረተ )
7. መመሪያ ቁጥር 27/2009 ዓ.ም
8. የማዕድን ሃብት ልማቱ ያለበት ሁኔታ
1. መግቢያ

ማዕድን
 የተፈጥሮ ሀብት ወይም ፀጋ ነው፣
 አንድ አገር ለማደግ ብቻ ሳይሆን ለመኖር የተፈጥሮ ሀብቷን በአግባቡ መጠቀም አለባት፣
 ማዕድን ከሰው ልጅ ህይወት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው
 ለኮንስትራክሽን ልማቱ የጀርባ አጥንት ነው
 ለኢንዱሰትሪ ወሳኝ ግብአት ነው
 የገቢ የስራእድልና የውበት ምንጭ ነው

 ስለሆነም በተቋማዊና ህጋዊ አሰራር መሰረት መመራት ይኖርበታል


የቀጠለ

 በዚህ መሰረት ይህ ገለፃ በየደረጀው የሚገኙ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ አመራሮች ስለ


ስለማዕድን ሃብት ልማትና አስተዳደር ስራ ተቋማዊና ህጋዊ አሰራር በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በተወሰነ
ደረጃ ትውውቅ እንዲፈጥሩ ለማድረግና ለቀጣይ ስራ ለማዘጋጀት በማለም የቀረበ ነው
2. የማዕድን ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ስልጣን ተግባር

2.1 በአዋጅ 678/2002 ላይ የተመሰረተ የማዕድን ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ስልጣን

ሀ) ባህላዊ የማዕድን ማምረት ሥራ ፈቃድ፣


ለ) ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች፡-

 የግንባታና የኢንዱስትሪ ማዕድናትን በሚመለከት የቅኝት፣ የምርመራና ይዞ የመቆየት ፈቃዶች፣

 የአነስተኛ ደረጃ የኢንዱስትሪ ማዕድናት ማምረት ስራ ፈቃዶች እንዲሁም የአነስተኛ እና የከፍተኛ

ደረጃ የግንባታ ማዕድናት ማምረት ሥራ ፈቃዶች፣

 ልዩ አነስተኛ ደረጃ የማዕድን ማምረት ስራ ፈቃድ፣


ሐ)ከስትራቴጂካዊ ማዕድናት ውጪ ለሆኑ ማዕድናት የግኝት የምስክር ወረቀት የመስጠት፣
2 .2 በአዋጅ ቁጥር 238/2008ዓ/ም መሰረትየማዕድን ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ስልጣን ተግባር

 በክልሉ ውስጥ የማዕድን ሀብት ልማት እንዲስፋፋ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ በሌሎች እንዲካሄድ ያደርጋል በነዚሁ ጥናቶች
አማካኝነት የክልሉን ዕምቅ የማዕድን ሃብቶች በአይነትና በመጠን ይለያል፤

 በክልሉ ውስጥ የስነ-ምድር ጥናትና ምርምሮችን ያካሄዳል ወይም እነዚህኑ የመሳሰሉ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ ረገድ አግባብ
ካላቸው የፌደራሉ መንግስት አካላት ጋር ተባብሮ ይሰራል፤

 የግል ባለሀብቶች በማዕድን ሀብት ልማት ስራዎች በስፋት እንዲሳተፉ ያነሳሳል ፤ የተለያዩ የፕሮሞሽን ስራዎችን በማከናውን
ያበረታታል፤

 ዘርፉ ለላቀ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውጤታማ አስተዋጾኦ እንዲያበረክት አደረጃጀቱን በማሻሻል አቅሙን በመገንባት ረገድ ተገቢውን
ጥረት ያደርጋል፤
የቀጠለ
 ማዕድንን አስመልክቶ በሀገሪቱ የወጡ ህጎችን በክልሉ ውስጥ በስራ ላይ ስለመዋላቸው ያረጋግጣል፤ ይቆጣጠራል፤

 ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በባህላዊ በአንስተኛ ፤ በልዩ አንስተኛና በከፍተኛ ደረጃ የሚካሄደውን የማዕድን ሀብት ፍለጋ፣
ምርምር፣ ግኝት፣ ምርትና ይዞ የመቆየት ፈቃዶችን ይሰጣል፣ያድሳል፣ይሰርዛል፤

 በክልሉ ውስጥ የከበሩ ውይም በከፊል የከበሩ ማዕድናትን አመራረት ፤ግብይትና አስተዳደር ይከታተላል ፤ይቆጣጥራል፤

 ባህላዊና አንስተኛ የማዕድን ማምረት ስራዎችን ይደግፋል፣ በክልሉ ውስጥ ዜጎች በጥቃቅንና አንስተኛ ተቋማት ተደራጅተው በዚሁ ተግባር ላይ ለመሰማራት
የሚያስችል የስራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ያበረታታል፣ ፈቃድ ይሰጣል፣ይቆጣጠራል፤

 ህገ- ወጥ በሆነ መንገድ የሚከናውን ማናቸውም የማዕድናት ምርትና ዝውውር እንዲገታ አስፈላጊውን የቁጥጥር ስርዓት ይዘረጋል፣ይቆጣጠራል፣በህገ-ወጥ
መንገድ ተይዘው የተገኙ ማዕድናት በአግባቡ ተጠብቀው ህጋዊ ውሳኔ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
የቀጠለ

 በማዕድን ሃብት ልማት ሂደት የሚገኝ የሮያሊቲ፣ የመሬት ኪራይና ሌሎች ተዛማጅ አገልግሎቶች ክፍያዎችን
ይሰበስባል፤

 ማዕድንን የሚመለከቱ መረጃዎችን ይሰበስባል፣ይተነትናል፣ያደራጃል፣ ለተጠቃሚዎች ያሰራጫል፤

 አግባብ ባላቸው የማዕድን ሀብት ልማት ማስፋፊያ ህጎች ከተፈቀደው ወሰን ሳያልፍ በባለ አክሲዎንነት ሊሳተፍ ይችላል፤

 የንብረት ባለቤትነት ይሆናል፣ውሎችን ይዋዋላል፣ በስሙ ይከሳል፣ ይከሰሳል፤

 ዓላመዎቹን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፤


3.የማዕድን ሥራዎች ህግጋት

3.1 ህግ የማውጣት ስልጣን

ሕግ የማውጣት ስልጣን የሚወሰነው በኢ.ፌ.ዲ. ሪ ሕግ መንግስት ድንጋጌ መሰረት ይሆናል፡፡ ( (51. 5) ፣
(52 .2.መ) ፣ (55.2 ሀ) ፣ ( 97. 8 ) ( 98. 3 )

በአንቀፅ 51 . 5 መሰረት የፈደራል መንግስት የመሬት ፣ የተፈጥሮ ሀብትና የታሪክ ቅርሶችን


አጠቃቀምና ጥበቃን በተመለከተ ህግ የማውጣት ስልጣን እንዳለው ተደንግጓል

በአንቀፅ 52 . 2 / መ ላይ ደግሞ የክልል …………… ስልጣንና ተግባር ስር የፌደራሉ


መንግስት በሚያወጣው ህግ መሰረት መሬትና የተፈጥሮ ሀብትን ያስተዳድራል ተብሎ
ተቀምጧል ፡፡
የቀጠለ
 በኢፊዲሪ ህግ መንግስት አንቀጽ ፹፱ ንኡስ አንቀጽ ፭ ላይ መንግስት መሬትና የተፈጥሮ ሀብትን በህዝብ ስም በይዞታው ስር
በማድረግ ለህዝቡ የጋራ ጥቅምና እድገት የማዋል ኃላፊነት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ በሀገሪቱ ከሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች መካከል
አንዱ የማዕድን ሀብት በመሆኑ ህገ መንግስቱ ለሀገሪቱ ህዝቦች የጋራ ጥቅም እንዲውል ደግፎታል፡፡

 በአንቀጽ ፺፯ ንኡስ አንቀጽ ፰ የክልል መስተዳደሮች የታክስና የግብር ስልጣን የከፍተኛ ደረጃ የማዕድን ስራዎችን ሳይጨምር
በማዕድን ስራዎች ላይ የማዕድን ገቢ ግብር የሮያሊቲና የመሬት ኪራይ ክፍያዎችን ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ በማለት ህገ መንግስቱ
ይደነግጋል፡፡

 በአንቀጽ ፺፷ ንኡስ አንቀጽ ፫ የማዕድን ሀብት አስተዳደርን አስመልክቶ የፌደራልና ክልል መንግስታት የጋራ ታክስና ግብር
ስልጣንን ሲዘረዝር ከፍተኛ ማዕድን ስራዎችና በማናቸውም የፔትሮለየምና የጋዝ ስራዎች ላይ የገቢ ግብርና ሮያሊቲ ክፍያዎች
በጋራ ይጣላሉ፣ ይሰበሰባሉ ይላል፡፡
3. 2 የማዕድን ሥራዎች ህግጋት

3.1 አዋጆች

 የማዕድን ሥራዎች አዋጅ ቁጥር 678/2002፣

 የማዕድን ሥራዎች (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 816/2006፣

 የማዕድን ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 53/1985(እንደተሻሻለዉ)፣

 የማዕድን ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 238/2008

3.2 ደንቦች

 የማዕድን ሥራዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 423/2010፣

 የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለማዕድን ሥራዎች የሚዉል የመሬት ኪራይ፣ የሮያሊቲና የማዕድን ገቢ ግብር

አከፋፈል ለመወሰን የወጣ ደንብ ቁጥር14/1992፣


የቀጠለ
3.3 መመሪያዎች

የማዕድን ሥራዎች ክትትልና ቁጥጥር ድጋፍ ሰጪ ግብረሃይል ማቋቋሚያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት
መመሪያ ቁጥር 27/2006 ዓ.ም.

በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ ወጣቶች የሥራ ዕድል አማራጮችን ማስፋፊያና ማበረታቻ
መመሪያ ቁጥር 27/2009 ዓ.ም.(እንደተሻሻለዉ)

የግንባታ ማዕድናት ቁርጥ ዋጋ አፈጻጸም መመሪያ ጥቅምት/2009 ዓ.ም


4. የማዕድን ሥራዎች ህግጋት ዓላማዎች

 መንግስት የሀገሪቱን ማዕድን ሃብት ለመጠበቅ የተጣለበትን ኃላፊነት ተግባራዊ ማድረግ፣

 የሀገሪቱን ኢኮኖማያዊና ማህበራዊ ልማት ማስፋፋት፣

 የኢትዮጵየዊያንን የስራ ዕድል ማስፋፋትና ማህበራዊና ኢኮኖማያዊ ጥቅም ማሳደግ፣

 በማዕድን ምርመራና ማምረት ስራ የተሰማሩትን ባለሀብቶች የስራ ዋስትና ማረጋገጥ፣

 የሀገሪቱ የማዕድን ሀብት ሥርዓትና ዘላቂነት ባለው ሁኔታ መልማቱን ማረጋገጥ


5. ዋና ዋና የማዕድን ሀብት አስተዳደር ህጎች አዋጅ ቁጥር 678/2002 የተመሰረተ

5.1 ማዕድን” ማለት ማናቸውም ዋጋ ያለው በጠጣር፣በፈሳሽ ወይም በጋዝ መልክ በተፈጥሮ በመሬት ላይ ወይም

ውስጥ፣በውሃ ውስጥ ወይም ስር የሚገኝ በጂኦሎጂ ሂደት ወይም ሁኔታዎች የተፈጠረ ሲሆን ቀደም ሲል ተቆፍሮ

በወጣና ተራፊ የተቆለለ ማዕድን አዘል አፈር ወይም በቀሪ የማዕድን ክምችት ውስጥ የሚገኝ ማዕድንን ያካትታል

 ሆኖም የሚከተሉትን አይጨምርም፦

 ከዉስጡ ማዕድን ለማዉጣት ከሚዉል እንደ ብራይን(የጨዉ ዉሃ) በስተቀር ሌላ ዉሃን፣

 አግባብ ባለዉ የነዳጅ ህግ ትርጓሜ የሚካተቱ የተፈጥሮ ዘይትና ጋዝን፣

 ለም አፈርን(ላይኛዉ አፈር) እና ነዳጅ አዘል አለትን (ነዳጅ አዘል ሸል)፣


5. 2 የማዕድን አይነቶች በአዋጅ ቁ. 678/2002 መሰረት፤

-
 የኮንስትራክሺን ማዕድናት …………2(3)

 የኢንዱስትሪ ማዕድናት ……………2(11)

 ብረት ነክ ማዕድናት ……………….2(17)


-
 የከበሩ ማዕድናት …………………..2(24)
-
 በከፊል የከበሩ ማዕድናት …………..2(34)
-
 ስትራቴጂክ ማዕድናት ……………..2(37)
5. 3 በማዕድን አዋጅ 678/2002 መሠረት ስለ ማዕድን ሀብት ጠባቂነት በአንቀጽ 5 ከንኡስ አንቀጽ 1-3 ሲደነግግ

 በኢትዮጵያ ወሰን ውስጥ በገጸ ምድርም ሆነ በከርሰ ምድር በተፈጥሮአዊ ሁኔታው የሚገኝ የማዕድን ሀብት የመንግስትና የሁሉም

ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ የተፈጥሮ ፀጋ ነው፣

 መንግስት የማዕድን ሀብትን በህዝብ ስም በይዞታው ስር በማድረግ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ጥቅምና ዕድገት መዋሉን

የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት፣

 መንግስት ኃላፊነት በሚሰጠው አካል አማካይነት የማዕድን ሀብትን ይቆጣጠራል፣ ያስተዳደራል፣ ፈቃድ ይሰጣል፣ ይከለክላል፣

ፈቃዶችን ያስተዳደራል፡፡
5.4 ከማዕድን ልማቱ መንግስት የሚያገኛቸው ገቢዎችና ጥቅሞች ፤

 ሮያሊቲ ከ2-7 % ከከፍተኛ ማዕድን ማምረት ፈቃድ፣ ( ባህላዊ፤ በልዩ አነስተኛ እና በአነስተኛ ደረጃ
ማ/ማምረት ሮያሊቲ መጠን በክልል ሕጎች የሚወሰን)
 የገቢ ግብር 25 % ከከፍተኛ ደረጃ ማዕድን ማምረት፣
 የመንግስት ነፃ አክሲዮን ድርሻ 5 % ከከፍተኛ ደረጃ ፈቃድ ፣(የአነስተኛ ደረጃ ባለፈቃድ የሚከፈለው
መጠኑ በክልል ሕግ ይወሰናል)
 ዲቪደንድ ታክስ 10%፤
 የመሬት ኪራይ በክልሎች ሕግ መሰረት የሚከፈል፣
 የሀገር ውስጥ ምርቶች ሽያጭ፤
 የውጭ ምንዛሪ ማግኝት፤
 የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር፤
 የስራ እድልና ለስራው ለምዶችን ማካበት
5. 5 የማዕድን ስራዎች የፈቃድ አይነቶች እና የምስክር ወረቀቶች
ሀ/ ፈቃዶች፤

 የማዕድን ቅኝት ፈቃድ፤(ለ18 ወር የሚሰጥ እድሳት የሌለው፡፡)


 የማዕድን ምርመራ ፈቃድ፤(ለ3 አመት የሚሰጥ ሆኖ ለ2 እና ለ5 ጊዜ በእያንዳንዱ አመት የሚታደስ)
 የይዞ መቆየት ፈቃድ፤(ለ3 አመት የሚሰጥ ሆኖ ሶስት አመት ለማይበልጥ ጊዜ አንዴ የሚታደስ)
 የማዕድን ማምረትፈቃድ፤-
• የባሕላዊ
• የልዩአነስተኛ
• የአነስተኛ
 የከፍተኛ ደረጃ ማዕድን ማምረት

ለ/ የምስክር ወረቀቶች፤

 የግኝት የምስክር ወረቀት፣ ( ለ18 ወር የሚሰጥ የማይታደስ)


 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፤
 የቴክኒክ አገልግሎት የምስክር ወረቀት
5. 6 የፈቃድ አስፈላጊነት ፤ ( 7)

 ማንኛውም ሰው የፀና ፈቃድ ሳይኖረው ማንኛውንም ማዕድን በተፈጥሮአዊ ሁኔታ መያዝ፣ ማዘዋዋር ወይም መሸጥ አይችልም፡፡

 በተለየ መልኩ ሕጉ የፈቀዳላቸው፤

 ሕጋዊ ባለይዞታ የኮንስትራክሺን ማዕድናት የለፈቃድና ክፍያ ለንግድ ላልሆነ አላማ መጠቀም ይችላል፡፡ -ለህዝብ
አገልግሎት፤መንገዶችንግድቦችን…ለመስራት የመጠቀም፡፡

 የቅኝት ስራ ለኢትዮጲያዊ ዜጋ ያለፈቃድ ተፈቅዷል፤


 - ለግል መጠቀሚያ ለምሳሌ ወርቅ ከ 100 ግራም የተፈቀደ ነው፡፡
5. 7 በጨረታ የፈቃድ አሰጣጥ

1/ በጨረታ ፈቃድ የሚሰጠው፣


ሀ) በዚህ ደንብ አንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የተረጋገጠ መረጃና የማዕድን
ክምችት ምልክት እንዳላቸው ተለይተው የታወቁ የከበሩ፣ የብረት ነክና እንደ አስፈላጊነቱ የሌሎች ማዕድናት
ቦታዎች የማዕድን ምርመራ እና ማምረት ሥራ ፈቃድ በአዋጁ አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 4 መሠረት በጨረታ
ሊሰጥ ይችላል፡፡

ለ) በጨረታ ፈቃድ ለመስጠት የማዕድኑ ዓይነትና ቦታው ተለይቶ በፈቃድ ሰጪው


ባለስልጣን ሲወሰን፣ እና

ሐ) ፈቃድ ሰጪው ባለሥልጣን በጨረታ አወዳድሮ ፈቃድ ለመስጠት የጨረታ ማስታወቂያ ሲያወጣ
እና ከአንድ በላይ አመልካቾች በተወሰነው የጊዜ ገደብ ማመልከቻዎች ሲያቀርቡ፡፡
የቀጠለ
2/ ለጨረታ የሚቀርብ ሰነድ የሚከተሉትን መያዝ አለበት፤

• ሀ) የአመልካቹን የቴክኒክ ሥራ ዕቅድ፣ ለሥራው ሊያወጣ ያሰበው የገንዘብ መጠን፣


የፋይናንስ ሁኔታ መግለጫ፣ የሥራ ልምድና ብቃት፤

• ለ) አመልካቹ ለግዴታዎቹ መፈጸም ማረጋገጫ የሚሆን ለመጀመሪያው ዓመት ከመደበው


በጀት 25% የሚሆነውን ስለማስያዙ ከፋይናነስ ተቋማት ዋስትና ማቅረብ፡፡

3/ ለጨረታ የቀረቡ ማመልከቻዎች ምርጫ የሚካሄደው በመመሪያ በሚወሰነው መስፈርት መሠረት


ሆኖ ፈቃድ ሰጪው ባለስልጣን ከፍተኛ ውጤት ላገኘው አመልካች ፈቃድ ይሰጣል፡፡

4/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) (ለ) መሰረት በባንክ የተያዘው የዋስትና ገንዘብ በጨረታው
ለተሸነፉ አመልካቾች ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን ጨረታውን ላሸነፈው አመልካች የመጀመሪያ ዓመት
የሥራና የወጪ ግዴታውን መወጣቱ በፈቃድ ሰጪው ባለሥልጣን ሲረጋገጥ ይመለሳል፡፡
የቀጠለ

5/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) ድንጋጌ ቢኖርም ባለፈቃዱ ግዴታውን ካልተወጣ
ያስያዘው የዋስትና ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡

6/ በጨረታ ማስታወቂያው መሠረት የቀረበው አንድ ተጫራች ብቻ ከሆነ፣ በድጋሚ


ጨረታ እንዲወጣ በፈቃድ ሰጪው ባለሥልጣን ካልተወሰነ በስተቀር ጨረታው ተሰርዞ
የፈቃድ አሰጣጡ በዚህ ደንብ አንቀጽ 9 እስከ 11 በተመለከቱት መሠረት የሚፈጸም
ይሆናል፡፡
5. 8 ስለ ቁጥጥር ስራ

 በማዕድን አወጅ አንቀጽ 54 ማንኛውም ስልጣን የተሰጠው የፈቃድ ሰጪው ባለስልጣን ተቆጣጣሪ በስራ
ሰዓት ወደ ማናቸውም የፈቃድ ክልል በመግባት፡-

 በፈቃድ ክልሉ በመካሄድ ላይ ያለውን ማናቸውንም እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር፣

 ማናቸውንም መዝገብ፣ ሪኮርድ፣ መግለጫ ወይም ሰነድ ለመመርመርና ሰነዱን ወይም የሰነዱን ክፍል
ቅጅ ለመውሰድ፣

 በስፍራው የሚገኙ ማተሪያሎችንና መሳሪያዎችን ለመመርመር፣


የቀጠለ
 ማናቸውንም ናሙና ለመውሰድና ለመፈተሸ፣ ለመመርመር፣ ለመተንተንና በዓይነት በዓይነቱ ለመለየት፣

 በአወጅ፣ ደንብና መመሪያ መጣስ ምክንያት ክስ ለመመስረት አስፈላጊ የሆኑ ማተሪያሎችን፣ ዕቃዎችን፣ መሳሪያዎችን፣
መዝገቦችን፣ መግለጫዎችን ወይም ሰነዶችን ለመያዝና በፈቃድ ሰጪው ባለስልጣን ጥበቃ ስር ለማቆየት፣

 ከላይ የተመለከቱ ተግባራትን ለመፈጸም እንዲችል የሚያስፈልጉ ድጋፎች እንዲሰጠው ትዕዛዝ ለመስጠት ይችላል፣

 ተቆጣጣሪው ምርመራውን እንዲያካሄድ በፈቃድ ሰጪው ባለስልጣን የተሰጠውን ደብዳቤ አግባብ ላለው የባለፈቃዱ
ሠራተኛ የማሳየት ግዴታ አለበት፣
6.ጥፋቶችና ቅጣቶች ( በደንብ ቁጥር 423/ 2010 ላይ የተመሰረተ )

አንደኛ ደረጃ ጥፋቶችችና ቅጣቶች

1. ማንኛውም ሰው፣

• ሀ) የአዋጁ አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ (3) እና (5) ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው በቅድሚያ
ተገቢውን ፈቃድ ሳይዝ በማዕድን ሥራ ላይ ከተሠማራ እና ማዕድናትን ሲያዘዋውር ከተገኘ፣

• ለ) ከፈቃድ ማመልከቻ፣ ከግኝት ማስታወቂያ ወይም ከብቃት ማረጋገጫ የምስክር


ወረቀት ጥያቄ እና ዕድሳት ጋር በተያያዘ ሁኔታ ሀሰተኛ መረጃ ከሰጠ ወይም ካጭበረበረ፣ከብር
300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) እስከ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ
ይቀጣል፤ ያለፈቃድ ያመረተው ማዕድንም ይወረሳል፡፡
የቀጠለ
2 ማንኛውም ባለፈቃድ፤

ሀ) የማዕድን ሥራዎችን በግዴለሽነት ወይም ሆን ብሎ አግባብ ባልሆነ መንገድ ከአካሄደ ወይም የፈቃዱን መሠረታዊ
ስምምነቶች ወይም ግዴታዎች ከጣሰ፣

ለ) በአዋጁ አንቀጽ 69 መሠረት የተሰጠውን ትእዛዝ ካልፈጸመና መከፈል ያለበትን ክፍያ ካልፈጸመ፣

ሐ) ከፈቃድ መብቱ በተያያዘ ማናቸውንም የማጭበርበር ድርጊት ከፈጸመ፣ ወይም ከማዕድን ሥራው ጋር በተያያዘ
ሀሰተኛ መረጃ ከሰጠ፣ በፈቃድ ስምምነቱ ከተመለከተው ውጪ ሌላ የማዕድን ሥራ ሲያከናውን ከተገኘ፣

መ) የተፈጥሮ አካባቢን፣ ጤንነትንና ደህንነትን፣ ወይም ሌሎች የማዕድን ሥራዎችን የሚመለከቱ ግዴታዎችን
ከጣሰ፣ወይም

ሠ) በተጨባጭ ሁኔታ የማዕድን ሥራዎችን የሚመለከቱ አስተዳደራዊና የፋይናንስ ግዴታዎችን ካልተወጣ፤

 የማዕድን ፈቃዱ ተሰርዞ ከብር 150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ) እስከ 2ዐዐ,000 (ሁለት መቶ ሺህ) በሚደርስ የገንዘብ
መቀጮ ይቀጣል፡፡
የቀጠለ

ሁለተኛ ደረጃ ጥፋቶችና ቅጣቶች

ማንኛውም ባለፈቃድ፤

1/ እንደአግባቡ በዚህ ደንብ አንቀጽ 42 ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ የተመለከቱትን መዝገቦችና ሪኮርዶችን
ወይም ሌሎች ሰነዶችን ወይም ማቴሪያሎችን ካልያዘ ወይም መሠረታዊ በሆኑ ነጥቦች ላይ ትክክለኛ ያልሆኑ
ወይም ያልተሟሉ መዝገቦችና ሪኮርዶችን ከያዘ፣

2/ የማዕድን ሥራዎችን በቸልተኝነት ወይም የማንኛውንም ሰው ጤንነት ወይም ደህንነት፣ የተፈጥሮ


አካባቢን ወይም ስለ ማህበረሰብ ልማት የሚጠበቅበትን ግዴታ ካልተወጣ ወይም የማዕድን ክምችቱን አደጋ ላይ
በሚጥል ሁኔታ ካካሄደ፣ በአጠቃላይ ተገቢ የማዕድን አሰራር ልምዶችን ካልተከተለ ወይም ፈቃዱ
የሚያስከትልበትን ግዴታ ካልተወጣ፣
የቀጠለ
3/ ሥልጣን የተሰጠው የፈቃድ ሰጪው ባለሥልጣን ተቆጣጣሪ ወይም ሠራተኛ በፈቃድ ወደ ተያዘው ክልል
እንዳይገባ ወይም የማዕድን ሥራዎች የሚካሄዱባቸውን ቦታዎች ወይም ተቋሞች ወይም የባለፈቃዱን መዝገቦች፣
ሪኮርዶች ወይም ሌሎች ሰነዶች ወይም ማቴሪያሎች እንዳያይ ካደረገ ወይም በሠራተኛው የተሰጠውን ሕጋዊ
ትዕዛዝ ወይም መመሪያ ካልፈጸመ፣

4/ የማማከር እና የቴክኒክ አገልግሎት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባለቤት የማዕድን ኢንዱስትሪው
የሚጠይቀውን ወቅታዊ የሙያ ብቃትና ቴክኖሎጂ ያገናዘበ እንዲሁም ሙያዊ ሥነ ምግባርን ያሟላ አገልግሎት መስጠት ካልቻለ፣

• የፈጸመውን የጥፋት ድርጊት ለማረም ወዲያውኑ እርምጃ ከወሰደ ከብር 5ዐ,000 (ሀምሳ ሺህ) እስከ 70,000 (ሰባ
ሺህ) በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፤ ጥፋቱን ለማረም ወዲያውኑ የእርምት እርምጃ ካልወሰደ የገንዘብ ቅጣቱ
እጥፍ ይሆናል፤

• ጥፋቱ በማንኛውም ሰው ጤንነት ወይም ደህንነት በተፈጥሮ አካባቢ ወይም በማዕድን ላይ ሊደርስ የተቃረበ ወይም
ቀጣይነት ያለው ጉዳት ካስከተለ፣ ፈቃድ ሰጪው ባለሥልጣን ባለፈቃዱ ጥፋቱን እስከሚያስተካክል ድረስ የማዕድን
ሥራዎቹን ወዲያውኑ እንዲያቆም ያደርጋል፤ የጥፋቱ ድርጊት ወይም ሁኔታ እስኪስተካከል ፈቃዱ ታግዶ ይቆያል፡፡
የቀጠለ
ሦስተኛ ደረጃ ጥፋቶችና ቅጣቶች

•ማንኛውም ባለፈቃድ፣

• 1/ መሠረታዊ በሆኑ ነጥቦች ላይ ትክክለኛ ያልሆኑ ወይም ያልተሟሉ መዝገቦችንና ሪኮርዶችን የመያዝ
ጉድለቶችን ሳይጨምር፣ የተሟሉ ትክክለኛ የሆኑና ወቅታዊውን ሁኔታ የሚያሣዩ መዝገቦችንና ሪከርዶችን
ካልያዘ፤
• 2/ ተፈላጊ ሪፖርቶችንና ሌሎች ሰነዶችን በወቅቱ ካላቀረበ ወይም ተፈላጊ መግለጫዎችን በወቅቱ
ካልሰጠ፣
• 3/ ጥፋቱ የማንኛውም ሰው ጤንነት ወይም ደህንነት፣ የተፈጥሮ አካባቢን ወይም የማዕድኑን ክምችት
አደጋ ላይ የማይጥል ቢሆንም የማዕድን ሥራዎቹን ተገቢ በሆነ መንገድና በጥንቃቄ ካልፈፀመ ወይም
ደንቦችንና መመሪያዎችን ካላከበረ፣
• 4/ ከማዕድን ሥራ ፈቃድ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በሀገሪቱ የሥራ ቋንቋ ወይም በእንግሊዝኛ ካልያዘ፣

ማስጠንቀቂያ እንደደረሰው ወዲያውኑ የእርምት እርምጃ ካልወሰደ ወይም የጥፋት ድርጊቱ ሊታረም የማይችል ከሆነ
ከብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ) እስከ 50,000 (ሀምሳ ሺህ) በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡
7. መመሪያ ቁጥር 27/2009 ዓ.ም

በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ ወጣቶች የሥራ ዕድል


አማራጮችን ለማስፋትና ለማበረታት የተዘጋጀ መመሪያ ቁጥር 27/2009
የቀጠለ
ክፍል አምስት
የባህላዊ አነስተኛ ማዕድን ልማት በተመለከተ

5.1 የባህላዊ አነስተኛ ማእድን ልማት የስራ መስኮች የስራ እድል መፋጠሪያ በመሆን የቅድመ ካፒታል
አቅም መፋጠርያ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ በዚህ ይስራ መስክ የሥራ እድል የተፈጠረላቸው
ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች ቢበዛ ለሁለት አመት ብቻ የሚቆዩ መሆናቸው አውቀው ወደ ዘላቂ
ስራ እንዲሰማሩ አስቀድመው እንዲዘጋጁ መደረግ ይኖርበታል፡፡

5.2 በባህላዊ አነስተኛ የማዕድን የስራ መስኮች ከዚህ በፊት ውል የተሰጣቸው ባለሀብቶች የፈቃድ
ጊዜያቸው ሲጠናቀቅ የፈቃድ እድሳትና ማረዘም አይደረግላቸውም፡፡ በእነዚህ ዘርፎች ባለሀብት አዲስ
ፈቃድ አይሰጥም፡፡ ሆኖም በድንጋይ መፍጨት ስራ ፈቃድ ተሰጥቷቸው በተሰጣቸው ሳይት ላይ ያለው
ሀብት በፈቃድ ጊዜው ያላለቀ ከሆነ በ2009 ዓ/ም የፈቃድ ጊዜው አልቆ እድሳት ለሚጠይቁ ለአንድ ጊዜ ብቻ
በያዙት ቦታ ላይ እንዲሰሩ ፈቃድ ሊታደስላቸው ይችላል ሆኖም ማስፋፊያ ወይም አዲስ ቦታ መስጠት
የተከለከለ ነው፡፡

5.3 በንኡስ አንቀጽ 5.2 የተገለጸው እንሰተጠበቀ ሆኖ ፈቃድ የወሰዱበት ሳይት ድንጋዩ ያለቀ ከሆነ በህጋዊ
መንገድ ከተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ድንጋይ እየገዙ ጠጠር የማምረት ስራውን ሊቀጥሉ ይችላሉ፡፡
8. የማዕድን ሃብት ልማቱ ያለበት ሁኔታ
8.1. ክልላዊ የማዕድን ሀብት አለኝታ ስርጭት
የቀጠለ
የቀጠለ
የቀጠለ
8.2. የማዕድን ሃብት ልማቱ ያለበት ሁኔታ

8.2.1 ከጥናት ስራ አኳያ

 በሰፊ ክልል ካርታ ስራ(1፡250000 መስፈርት) የተፈሸፈነ ቦታ ስፋት = 161828.4 ካሬ ኪሎ ሜትር

 አዲስ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር የተሰራና በመሰራት ላይ የሚገኝ የስነምድር ጥናት ስራ ፡ -

 የኦፓል መገኛ ቦታዎችን ማዕከል በ ማድርግ የተሰራ ( 8000 ካሬ ኪሎ ሜ.)

 ቋራ-ጃዊ ስነምድር ጥናት( 11458.26 ካሬ ኪሎ ሜትር)፣

 ጓንጓ-ዚገም-ሺንዲና ቡሬ ስነምድር ጥናት(4398.5ካሬ ኪሎ ሜት)፣

 ጠለምት-ሳህላ-አበርገሌና ዝቋላ ስነምድር ጥናት(5515.14 ካሬ ኪሎ ሜት)፣

 ለገሂዳ-ጃማ-ሚዳወራሞ-ወግዲና ቦረና ስነምድር ጥናት(5,937.75 ካሬ ኪሎ ሜት)፣

ከላይ በተዘረዘሩት ፕሮጀክቶች እንዲሸፈን በዕቅድ የተያዘዉ የስነምድርና ማዕድን ፍለጋ ጥናት ቦታ ስፋት ድምር = 35000 ~ 35300 ካሬ ኪሎ

ሜት፣
አዲስ ፕሮጀክት(Outsource)
የቀጠለ

8.2.2 የተሰጡ ፍቃዶች ፡

 ከ1997 እስከ 2010 ዓ/ም ባለው ጊዜ 432 የአንስተኛና የከፍተኛ የማዕድን ስራ ፈቃድ፣ 10,299 ባህላዊ የማዕድን ማምረት ስራ፣ 69

የከበሩ ማዕድናት አዘዋዋሪ ስራ ፈቃድ፣ 81 የከበሩ ማዕድናት ዕደጥበብ ፈቃድ ተሰጥቷል

8.2.3 የተሰበሰበ ገቢን በተመለከተ

 እስካሁን ባለው ጊዜ 111 589 257 ብር የተሰበሰበ ሲሆን ይህም በ GTP -2 ይሰበሰባል ተብሎ ከታቀደው 150 000 000 ብር
ውስጥ 74 ፐርሰንቱን ይሸፍናል
የቀጠለ

ለክልል የተሰበሰበ ገቢ ብር
40100000

35100000

30100000

25100000

20100000

15100000

10100000

5100000

100000
1997 1998 1999 2000 2001 2002 2003 2004 2005 2006 2007 2008 2009 2010
የውጭ ምንዛሪ ግኝት በተመለከተ
እስካሁን ባለው ጊዜ 31 114 000 የአሜሪካ ዶላር የተሰበሰበ ሲሆን ይህም በ GTP -2 ይሰበሰባል ተብሎ ከታቀደው 140 000 000 ዶላር ውስጥ
22 ፐርሰንቱን ብቻ ይሸፍናል
8.2.4 የተፈጠረ የስራ ዕድል
በ GTP -2 ከሚጠበቀው 200 000 የስራ እድል ፈጠራ ውስጥ 162 000 ( 81 ፐርሰንት ነው

55000

50000

45000

40000

35000

30000

25000

20000

15000

10000

5000

0
1998
የስራ ዕድል 1999
ፈጠራ ወንድ 2000 2001የስራ ዕድል
2002 2003
ፈጠራ ሴት 2004 2005 የስራ 2006 2007
ዕድል ፈጠራ ድምር 2008 2009 2010
9. በቀሪ ጊዜ ትኩረት የሚያስፈልገው

 ኤጀንሲያችን ለኢንዱስትሪና ኢንቨስትመነት ቢሮ ተጠሪ እንዲሆን ተደረጎል ፡፡ስለሆነም በቀሪ ጊዚያት ውህድ የሆነ

አደረጃጀት ለመፍጠር መስራት ያስፈልጋል፡፡

 ከክልል በታች ያለው አደረጃጀትና የሰው ሀይል ።

 በዞን ቴክኒክ 3 የሰዉ ሃይል ያለዉ አንድ ቡድን፣

 በሜትሮፖሊታን 3 የሰዉ ሃይል ያለዉ አንድ ቡድን፣

 በመካከለኛ ከተሞች 4 የሰዉ ሃይል ያለዉ አንድ ቡድን፣

 በወረዳ ስር 3 የሰዉ ሃይል ያለዉ አንድ ቡድን እና .

 አነስተኛ ከተሞች 2 የሰዉ ሃይል ያለዉ አንድ በድን፣

 በየደረጀው ያለውን የስራ እንቅስቃሴ መገምገምና ከአሰራሮች ጋራ ለመሄድ ህጎችን ማወቅ ይሆናል
አ መ ሰ ግ ና ለ ሁ !!

You might also like