You are on page 1of 2

በአዲስ አበባ ከተማ የ 2009 ዓ.ም.

አማካይ የቀን ገቢ ግምት መሰራቱን ተከትሎ የግምቱ ውጤት ለግብር ከፋዮች መገለፅ
ተጀምሯል፡፡ የግብር ከፋዮች የቀን ገቢ ግምት እና ዓመታዊ የሽያጭ መጠናቸው እንዲሁም ዓመታዊ ሽያጫቸውን መሰረት
አድርጎ የግብር ከፋዮች ደረጃ እየተገለፀ ይገኛል፡፡ ነገር ግን የተገለፀውን መረጃ ማለትም የቀን ገቢ ግምቱንና ዓመታዊ የሽያጭ
መጠኑን በማየት ብቻ ያን ያህል ግብር ክፈሉ እንደተባሉ ቆጥረው የመደናገጥና የማማረር ሁኔታዎች መስተዋላቸውን
ተከትሎ የግብር ከፋዮች ዓመታዊ የቀን ገቢ ግምቱንና ዓመታዊ ሽያጩን መሰረት አድርጎ ገቢ ግብር እንዴት እንደሚሰላ ከዚህ
ቀጥሎ በምሳሌ እናቀርባለን፡፡
ምሳሌ 1፡-በርበሬቅመማቅመምንግድ
የቀን ገቢ ግምት መጠን፡-ብር 1,500 ብር 1500 * በ 365 ቀናት = ብር 547,500 /ዓመታዊ ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ/
የዘርፉትርፍመተመኛ 10%=547,500 ግብርየሚከፈልበትገቢ=54,750 ግብር መጣኔ 20% = 10,950
ተቀናሽ - 3,630
ተከፋይ ግብር = 7,320
ምሳሌ 2፡- የባህል ዕቃዎች
የቀን ገቢ ግምት መጠን፡- ብር 2000
ብር 2000 * በ 300 ቀናት = ብር 600,000 /ዓመታዊ ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ/
የዘርፉ ትርፍ መተመኛ 14% = 600,000*14% = 84,000
ግብር የሚከፈልበት ገቢ =84,000
ግብርመጣኔ 25%=84,000*25%=21,000
ተቀናሽ = 6780
ተከፋይ ግብር = 14,220
ምሳሌ 3፡- ፀጉር ቤት
የቀን ገቢ ግምት መጠን = ብር 2,800
ብር 2,800 * በ 365 ቀናት = ብር 1,022,000 /ዓመታዊ ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ/
ዓመታዊ ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ ብር = 1,022000
የዘርፉ ትርፍ መተመኛ 10% = - 102,200
ጠቅላላ ወጪ = 919,800
ጠቅላላ ግብር የሚከፈልበት ገቢ = 102,200
ግብር ምጣኔ 30% = 30,660
ተቀናሽ - 11,460
ተከፋይ ግብር = 19,200
ማሳሰቢያ፡- ከምሳሌው እንደምንረዳው ግብር ከፋዮች የቀን ገቢ ግምቱን ተከትሎ እንዲከፍሉ የሚጠየቁት ዓመታዊ ግብር
እንደሚባለው በአብዛኛዎቹ ላይ የተጋነነ አይደለም፡፡ የተመደበላቸው ግብር አንድ ተቀጣሪ ከደመወዙ ላይ ከሚከፍለው ግብር
አነስተኛ ነው፡፡ ከላይ የተገለጹት ምሰሰሌዎች ለደረጃ “ሀ” እና “ለ” ግብር ከፋዮች የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡- የ 10 ሺ ብር ደመወዝተኛ በወር 2 ሺ 45 ብር፤ በዓመት ከሚከፈለው 120 ሺ ብር ደግሞ 24 ሺ 540 ብር ግብር
ይከፍላል፡፡ 120 ሺ ብር ዓመታዊ ገቢ ያለው ነጋዴ ግን የትርፍ መተመኛ መቶኛው 10 በመቶ ላይ ካረፈ ግብር የሚጠየቅበት
ገቢው 10 በመቶ ወይም 12 ሺ ብር ይሆናል፡፡ ቀሪው 90 በመቶ ወይም 108 ሺ ብር እንደ ወጪ ይታይለትና ከግብር ውጪ
ይሆናል፡፡ 12 ሺውን ደግሞ በግብር ማስከፈያ መጣኔ ሲሰላለት 10 በመቶ ላይ ያርፍና 1 ሺ 200 ብር ብቻ ዓመታዊ ግብር
ይጠየቃል፡፡ ስለዚህ የነጋዴውን 1 ሺ 200 ብር ከደመወዝተኛው 24 ሺ 540 ጋር ማነጻጸር በቂ ነው፡፡

You might also like