You are on page 1of 13

አዲስ ሰማይና ምድር

ለአዲሱ ሰው!

"New Sky and Earth for Newborn Man!"

ፍቃዱ ካሣ አይቼው (ዶ/ር)


"አዲስ ሰማይና ምድር ለአዲሱ ሰው!"
ኮፒ መብት 2014 ዓ. ም ፍቃዱ ካሣ አይቼው
መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ

"New sky and earth for newborn man!"


Copyright 2022 by Fekadu K. Ayichew
All rights reserved
United States of America

ለማንኛውም አስተያየት
Email: Fkdu2003@gmail.com
Or
Phone: +17636002079

ይህንን መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያለ አሳታሚው ፈቃድ


ማባዛት በሕግ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።

ii
መቅድም
ከሁሉ በማስቀደም ለአንድ በምድር የሚኖር ሰው በሰማይ ላይ
የሆኑና የሚሆኑ ነገሮችን በተመለከተ ለመጻፍ፣ ለመስበክ፣
ለማስተማር ወዘተ… መነሳቱ ሁኔታውን በሰውኛ ከባድ ያደርገዋል።
ምክንያቱም የሰው እውቀቱ፣ አቅሙ፣ ጥበቡ፣ ወዘተ ውስን
ስለሆነ። የሰው እውቀት ውስንነት ሳስብ ሰው በዚህቺ ጥቂት
አዕምሮ እርሱ ራሱ ካልገለጠለት በስተቀር ስለ ሰማያዊ ነገርና ስለ
እግዚአብሔር ሊረዳ ይቸገራል።
የሰው (ልቀት ወይም የማሰብ ችሎታ) ምን ያህል ይሆን ብዬ
ማሰብ ሲጀምር እግዚአብሔር ለሰው የሰጠውን IQ መጠን ምን
ያህል ጥቂት እንደሆነ ማንበብ ጀመርኩ። እስቲ የሰውን የIQ መጠን
ላስታውሳችሁ።
ብዙ የመስኩ ተመራማሪዎች (ሳይኮሎጂስት ወይም ህዋሰ
ነርቭ(nerve) ሳይንስ (neuroscience) እንደሚናገሩት የሰው
ጭንቅላት ነገሮችን የመያዝ አቅም በአማካይ ወደ 1,000 ጊጋባይት
(gigabytes) አከባቢ እንደሆነ ይስማማሉ። የአንዳንድ ሰዎች
አዕምሮ በተወሰነ ደረጃ የተለየ ሊሆን ይችላል ይላሉ። ልክ እንደ
አልበርት አንስታይን።
የአንስታይ አዕምሮ ላይ ጥናት ያካሄዱት ለአዕምሮ ምርመራ
የሚረዳ ማሽንን ተጠቅመው ነው። የእርሱ አንጎል ከተለመደው
የሰው የማሰብ ችሎታ 15 በመቶ ይበልጥ እንደነበረ ለአለም
አበሰሩ። ግኝቱ የሚያሳየው የእርሱ እዕምሮ የማሰብ አቅሙ 1150

iii
ጊጋባይት ገደማ እንደሆነ ገመቱ። እንግዲህ ለአዕምሮ 1 ጊጋባይት
ቀላል አይደለም። ስልካችን እንኳ በ3 እና በ4 ጊጋባይት መካከል
ከፍተኛ ልዩነት አለው። የአንስታይን አዕምሮ በ150 ጊጋባይት
ከሌላው ሰው መብለጡ የተለየ መሆኑን እንድንቀበል ያደርገናል።
ይህ ስለ አንስታይን ያነሳሁት የሰው አማካይ የማሰብ መጠን
ይህን ያህል ቢሆንም ስለ ሰማያዊው ነገር ማለትም ስለ አዲስ
ሰማይና ምድር ለመጻፍ ይቅርና ስለ ምድሩንም ለማወቅ ውስንነት
አለበት። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ነገሮችን ሲገልጥልን ግን
ሰማያዊውን ነገሮች ለመረዳትም ቀላል ይሆናል። የአዲስ ሰማይና
ምድር ጉዳይ ከሰው እውቀት በላይ ነው። ብቻ እግዚአብሔር ራርቶ
ካልገለጠልን በስተቀር የእርሱ ነገር ለሥጋ ለባሽ አይገባውም።
እንደ ሙሴ፣ ኢሳይያስ እና ዮሐንስ ያሉ የእምነት አባቶች
እግዚአብሔር የገለጠላቸው ለእነርሱ በገባቸው መንገድ ነገሩን።
ኢሳይያስ ከዘመናት በፊት እግዚአብሔር ገና ሊፈጥረው ያለውን
አዲስ ሰማይና ምድርን ለትውልድ አሳወቀ። ‘’እነሆ፥ አዲስ ሰማይና
አዲስ ምድር እፈጥራለሁ’’ ይላል ብሎ። አዲስ ሰማይና ምድር
መፈጠርም እንደ መጀመሪያው ሰማይና ምድር እግዚአብሔር
‘’ይሁን ወይም ሁን’’ ብሎ እንደፈጠረው ዓይነት ይሆንን?
በማለት ራሴን ደጋግሜ ጠየኩ። ብቻ ይህ አሰራር ከሰው አዕምሮ
በላይ ስለሆነ ለራሱ ለሰሪው ተውኩት። በተጨማሪ ኢሳይያስ
አሁን ያለውን ሰማይ (አሮጌው ሰማይም) እንዴት ባለ መንገድ
እንደሚጠፋ ጭምር ተረከልን።

iv
ብቻ አዲስ ሰማይና ምድርን እንዴት እንደሚፈጠሩ
እግዚአብሔር ያውቃል። ይህ መለኮታዊ አሰራሩን ከሰው እውቀት
በላይ ስለሆነ እኛም ከአዕምሮአችን በላይ የሆኑ ነገሮች ሲገጥሙን
እንደ ሕዝቅኤል ‘’አንተ ታውቃለህ’’ ብለን ልንተው እንገደዳለን።
ጳውሎስም ያደረገው ይሄንኑ ነው። ‘’ከእውቀትም ከፍለን
እናውቃለን’’ ብሎ የተገለጠለትን ብቻ ነገረን ወይም ጻፈልን።
ሰዎች እግዚአብሔር ካልገለጠለት ምንም አናውቅም። ሙሴ፣
ኢሳይያስና ዮሐንስም የገለጠላቸውን ጻፉት።
በኢሳይያስ አንደበት ይፈጠራሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩትን
አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ሐዋርያው ዮሐንስ ደግሞ በ(ራዕይ 21፡
1) ተሰርተው አልቀው እርሱ ‘’አዲስ ሰማይንና ምድርን አየሁ’’
ብሎ ልክ እንደ አዲስቷ ኢየሩሳሌም ከሰማይ እንደሚወርድ አይነት
ያለቀ ጉዳይ ያወራናል።
ሙሴ በዘፍጥረት 1፡1 ‘’ሰማይና ምድርን ፈጠረ’’ ብሎ
እንደጻፈልን የሰማይና የምድርን ፍጻሜ አልነገረንም። ምክንያቱም
አልገለጠለትምና። ካልገለጠለት ኢሳይያስም ሆነ ሙሴ በዚያ
መኖራቸው ምንም አይደለም።
እንግዲህ እኔም ማን ከማን ያንሳል ብዬ ይህን መጽሐፍ
ለመጻፍ እግዚአብሔር ይህን የከበረውን አሳብ በውስጤ
ሲያስቀምጥ ጊዜ ዝም ብዬ ሳልተው ይልቁን በተቻለኝ መጠን እንደ
አባቶች በጥንቃቄ ጻፍኩት። እግዚአብሔርም ረዳኝና ይሄው
ለአንባቢያን ደረሰ። ክብር ለእርሱ ይሁን!

v
መግቢያ
ይህን መጻፍ ለመጻፍ ስነሳሳ ለአንድ በሁኔታዎች ተወስኖ
በምድር ላይ ለሚኖር ሰው ስለ ሰማይ መጻፍ ከባድ ነው። ጭራሽ
ስለ ሰማይ ለመጻፍ እኔ ማን ነኝ? ሁሉ አስባለኝ። ነገር ግን ሰዎች
ሁሉ ይህን ሰማያዊ እውነት እንድረዱትና ሰማይን በዘመናቸው
እንዲናፍቁ ለማስቻል ሲባል ስለ ሰማይ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው
እውነት ለትውልድ እንዲደርስ ፈልጌ ይሄው በተቻለኝ መጠን
እኔም እንደ እምነት አባቶች በጥንቃቄ ጻፍኩት።
ስለ ሰማይ ለማወቅ መጓጓት ምናልባት በብዙ ሰዎች ውስጥ
የሚኖር ጥያቄ ይመስለኛል። እነዚህም ጥያቄዎች ሰማይ ማለት
ምንድነው? ሰማያዊ ሕይወትስ ምንድነው? ሰማይ የሚባለው ምንን
የሚያሳይ አሳብ ይሆን? ይህ በአይናችን የሚታየው ሰማይ
በትክክል አለ ወይ? ሰማያት ሲባል ምን ማለት ነው? ስንት ሰማይ
አለ? ወዘተ የሚሉ አሳቦችን በመጀመሪያው ጥቂት ምዕራፎች
ውስጥ ይተነትናል። እኔም በዚህ መጽሐፍ ስለ አሮጌው ሰማይ ብቻ
ሳይሆን ስለ አዲሱ ሰማይና ምድር ጭምር በዝርዝር አቅርቤያለሁ።
ይህ መጽሐፍ ‘’አዲሱ ሰማይና ምድር የአዲሱ ሰው’’ የሚል
ቢሆንም ከአዲሱ ሰማይና ምድር በፊት ስለ ግዑዙ ሰማይ ወይም
አሮጌው ሰማይም ምንነት በስፋት ተተንትኗል። በትንሹ የዚህ
መጽሐፍ አራት ምዕራፎች ስለ አሮጌው ሰማይና ምድር ያወራሉ።
በስፋት ደግሞ ስለ አዲስቱ ኢየሩሳሌም ማንናት? ስለ አዲሱ ሰው
ማንነት፣ ስለ አዲሱ ሰማይና ምድር ወዘተ አሳቦችም በስፋት
ተብራርተዋል።
vi
ይህን መጽሐፍ እስከ መጨረሻው አንብባችሁ ስትጨርሱ ስለ
"አዲሱ ሰማይና ምድር ለአዲሱ ሰው!’’ መሆኑን ፍንትው ብሎ
ይገለጽላችኋል። ስለዚህ በእኔ አስተሳሰብ ይህን መጽሐፍ
በየትኛውም የእምነት ተቋም ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ማንበብ
ይችላሉ። ሰው ሁሉ ይህን መጽሐፍ በማንበብ ትውልዱን በሰማይ
የሚጠብቀውን ታላቅ ተስፋ ምን እንደሆነ ተረድተው በምድር ላይ
ሰማያዊ ኑሮን እንዲለማመዱ ያደርጋል። መልካም ንባብ። ደግሜ
እላለሁ። እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ።

vii
ማውጫ
መቅድም .................................................................................................... ii
መግቢያ .................................................................................................... iii
የቃላትና የአህጽሮተ ቃላት ትርጉም -------------------------------------v
ማውጫ .................................................................................................... vi
1. ሰማይ ምድንነው?
ሰማይ ምንድነው ........................................................................ 1
ሰማይ የመኖሩ መላ ምቶች ..................................................... 4
የሰማይ ምንነት በሳይንስ.......................................................... 4
የሰማይ ሐሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ........................................... 9
ማጠቃለያ ................................................................................. 11

2. የሰማያት ሃሳብ በእምነት አባቶች

የሰማያት ሃሳብ ----------------------------------------------12


ሰሎሞን ስለ ሰማያት ............................................................. 14
ሙሴም ስለ ሰማያት ............................................................... 18
ኢሳያስ ስለ ሰማያት................................................................. 21
ዳዊት ስለ ሰማያት .................................................................. 24
ማቴዎስ ስለ ሰማያት .............................................................. 27
ማጠቃለያ ............................................................................... 29

viii
3. የሰማያት ሶስትነት ሲተነተን
ሰማያት ስንት ናቸው? ........................................................... 31
የሰማያት ክፍፍል ግልጽ አይደለም ........................................36
የሶስቱም ሰማያት ተግባራቸው ............................................ 33
አንደኛው ሰማይና ተግባራቶቹ -----------------------------34
ሁለተኛው ሰማይና ተግባራቶቹ ----------------------------36
ሶስተኛው ሰማይና ተግባራቶቹ -----------------------------39
ማጠቃለያ ............................................................................... 46

4. የሰማያት አንኳር ተግባራት


የሰማይ ተግባራት ምንድናቸው? ---------------------------48
የእግዚአብሔር መኖሪያ ነው ............................................... 49
ሰማይ የእግዚአብሔር ዙፋን አለበት ................................... 54
ሰማይ የቅዱሳን (የዳኑት) የአሁንና የዘላለም መኖሪያ ነው-56
ሰማይ የአግልግሎት ሽልማት መገኛና መቀበያም ነው-------63
ማጠቃለያ-------------------------------------------------- 69

5. በውስጡ ያሉ ፍጥረታትን ጨምሮ የአሮጌው ሰማይና ምድር ፍጻሜ 70


አሮጌው ሰማይና ምድር መጨረሻው መጥፋት ነው-----------------70
ሰማይና ምድር ለመጥፋት ወሰን ተደርጎበታል ------------------------73

ix
የፍጥረትና የሰው አወሳሰድ ምን ይመስላል? --------------------------75
ፍጥረት ይጠፋሉ፥ ሰዎች ግን አይጠፉም ----------------------------- 76
ሰዎች ከሰማይና ከምድር በፊት ይሰበሰባሉ ---------------------------77
ማጠቃለያ -------------------------------------------------------------78

6. የአሮጌው ሰማይና ምድር አጠፋፍ----------------------------------28


ሰማያት እንደ ጢስ በንነው ይጠፋሉ-----------------------------------29
ሰማይና ምድር ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ--------------------------31
ሰማያት እንደ ጥቅልል ተጠቅልለው ያልፋሉ---------------------------35
ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ በትኵሳትም ይቀልጣል -------------36
የነገሮች በቅጽበት መለወጥ --------------------------------------------39
ማጠቃለያ ..............................................................................................41

7. አዲስ ሰማይና ምድር -----------------------------------------------42


አዲስ ሰማይና ምድር ምንነት ------------------------------------------42
ማጠቃለያ--------------------------------------------------------------45

8. አዲስትዋ ኢየሩሳሌም ምንነት ----------------------------------46


አዲስቱ ኢየሩሳሌም መሰረትዋ ከምን ተሰራ?---------------------- 47
የከተማዋ በሮችና ቅጥሮች ----------------------------------------48
የከተማዋ መንገዶችና አደባባዮች---------------------------------------52
የከተማዋ ስፋት -------------------------------------------------53
ለከተማዋ በጉ ብርሃንዋ ------------------------------------------55
አዲስትዋ ኢየሩሳሌም ከሰማይ ትወርዳለች ---------------------------58

x
ማጠቃለያ -------------------------------------------------------------60

9. የአዲስቱ ኢየሩሳሌም ተግባራት-------------------------------------62


የበጉ ሰርግ ይደረግባታል -----------------------------------------62
አዲሱ ሰው ይኖርባታል ----------------------------------------- 67
ሰው እንዴት አዲስ ይሆናል? -------------------------------------67
በአዲስትዋ ኢየሩሳሌም የሚኖሩባትና የማይኖሩባት-----------------71
ማጠቃለያ .............................................................................................74

10. አዲስትዋ ኢየሩሳሌም የታመነና እውነተኛ ናትና አጻፈው ………..140


ሐዋርያው ዮሐንስ ራዕይን እንዴት ጻፈው? ----------------------140
ከተማዋ መውረድዋ የታመነና እውነተኛ ነው ---------------------143
ማጠቃለያ ........................................................................................... 145
ዋቢ መጽሐፍት .................................................................................. 146
ምስጋና .................................................................................................. 147

xi
የቃላትና የአህጽሮተ ቃላት ትርጉም
በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱት ቃላትና ሐረጎች አሻሚዎች
ሊሆኑ ስለሚችሉ ከዚህ በታች ለአንባቢያን ግልጽ ለማድረግ
ተብራርተዋል።
ቤተ ክርስቲያን፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ በማመን
በደሙ ቤዛነትን ያገኙ ሰዎች (ቅዱሳን) ጥርቅም ያመለክታል።
አባቶች፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስማቸው የተጠቀሱና ከዚህ
ትውልድ በፊት ለወንጌል መስፋፋት ዋጋ የከፈሉ የእምነት አባቶችን
ያሳያል።
ሰማይ፡ ይህ ለእኛ በአይናችን የሚታይ የሚመሰለን ተፈጥሮአዊ
ግዑዝ ሰማይንና መንፈሳዊ ሰማይን ያመላክታል።
ሰማያት፡ ሰማይ ከሁለት በላይ እንደሆኑ የሚያመለክት ስም
ነው።
አንደኛው ሰማይ፡ ሰዎች በዚህ ምድር ላይ በእንግድነት በሥጋ
የሚኖርበትን የምድር ከባቢ አየርን የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። ይህ
ሰውና ፍጥረታት ማለትም ወፎች እና ደመናት የሚገኙበት የአየር
ግዛትን ይገልጻል።
ሁለተኛው ሰማይ፡ በተለምዶ በመጀመሪያውና በሶስተኛው
ሰማያት መካከል የሚገኘው ሰማይ ነው። ይህ ሰማይ ብዙ ጊዜ
የሰይጣን መገኛ ተደርጎ ይወሰዳል።
ሶስተኛው ሰማይ፡ የእግዚአብሔር ዙፋኑና ማደሪያው መገኛ፣
በክርስቶስ ኢየሱስ ያመኑ ቅዱሳንም የዘላለም መኖሪያ፣ ወዘተ
ነው።
xii
ምህጻረ-ቃላት
እ ኤ አ፡ እንደ አውሮፓ ዘመን አቆጣጠር
ዓ.ዓ. ዓመተ ዓለም
ዓ.ም. ዓመተ ምሕረት
ክ/ዘመን፡ ክፍለ ዘመን

ማሳሰቢያ
በዚህ መጽሐፍ በወንድ ጾታ የተጠቀሱት አሳቦች ለሴቶችም
ይሰራሉ። በዚህ መጽሐፍ የተካተቱ የዘመን አቆጣጠሮች ልዩ
ማብራሪያ ካልተሰጠው በስተቀር የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር
ነው።

xiii

You might also like