You are on page 1of 1

ታኦዶኮስ(ዳሰሳ በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ) ለዘመነ ጽጌ ንባብ የተመረጠች መጽሐፍ፡፡

A capacity and taste for reading gives access to what ever has
already been discovered by others. It is the key, or one of the key, to the already solved problems. And not
only so, it gives a relish and facility for successfully persuing the yet unsolved ones (Abraham Lincoln).

የንባብ ፍቅርና ችሎታ በሌሎች ዘንድ ቀድሞ የታወቀውን ሁሉ ለማወቅ ዕድል ይሰጣል፡፡ መፍትሔ
የተገኘላቸውን ችግሮች ለማወቅም መክፈቻ ነው፤ ወይም ከመክፈቻወች አንዱ ነው፡፡ ይህም ብቻ ግን
አይደለም፤ ገና መፍትሔ ያልተገኘላቸውን ችግሮች በስኬት ለመቅረፍም ብርታት የሚሰጥና ነገሮችን በራስ
አቅም ለማከናወንም የሚያስችል ነው እንጅ(አብርሃም ሊንከን ትርጉም የራሴ)
ታኦዶደኮስ በሚል ርእስ ተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ በበቂ መጠን መልስ አልተሰጣቸውም ብየ ከማስባቸው
ጉዳዮች ቢያንስ አንዱ ላይ ጠንከር ያለ አቋምን አስቀድሞ በሌሎች በዳሰሳቸውም ጉዳዮች ላይ እስካሁን
ካነበብናቸው በተጨማሪ ልናውቃቸው የሚገባንን አካትቶ የተዘጋጀ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡ በጎንደር መንበረ
መንግስት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት የትርጓሜ መምህር የሆኑት የሊቀ
ሊቃውንት ዕዝራ ደቀ መዝሙርና የጉባኤ ቤቱ ምክትል መምህር በሆኑት በመምህር በጽሐ ዓለሙ የተዘጋጀው
ይህ መጽሐፍ እንደቀደሙት ሁሉ የራሱ አቀራረብና ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ቢኖረውም በዘመናችን
መናፍቃኑን ብቻ ሳይሆን አማኞችንም ሳይቀር የሚያነታርከውን እመቤታችን ጥንተ አብሶ አለባት የለባትም
የሚለውን ጥያቄ ከቤተ ክርስቲያናችን ነባር አስተምህሮ አንጻር መልስ የሚሰጥ ግሩም መጽሐፍ ነው፡፡ ምንም
እንኳን ጉዳዩን ቀደም ብየ ከጠቀስኳቸው መጻሕፍት አንዷ በሆነችው ወልታ ጽድቅ በተባለች መጽሐፍ
በዘመናዊ ክርክራዊ አቀራረብ የዲስኮርስ ትንተና (discourse Analysis) ዘዴን ተጠቅሞ ወይም ደግሞ የቀደሙ
ሃሳቦች ጨመቅ(Synthesis) ዘዴን ተጠቅሞ ከሁሉም ተቃርኖአዊ አቅጣጫ የተባሉትን በተመለከተ የተሸለ
ንጽጽርና ተቃርኖአዊ ትችት (critics) አዘጋጁ ቢያቀርብልንም አጠቃላይ የቤተክርስቲያኒቱ ትምህርት ምን
ይመስላል የሚለውን ሙሉ በሙሉ የዳሰሰ ነው ለማለት ግን የሚያስቸግር ነው፡፡ በእኔ እምነት ይህን ክፍተት
የሚሞላው ይህ የመምህር በጽሐ ዓለሙ መጽሐፍ ይመስለኛል፡፡ አዘጋጅ፡-መምህር በጽሐ ዓለሙ
ዋጋ፡-121 ብር የገጽ ብዛት፡-292

You might also like