Professional Documents
Culture Documents
Construction Project Price Analysis Report
Construction Project Price Analysis Report
ማህበራችን የቢዝነስ ተቋማትን ለማስፋፋት የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የደብረ ማርቆስ ባለ አስር ፎቅ
(B+G+10) ሁለገብ ህንጻ፣ የዋንዛየ ሎጅ እና የጢስ አባሊማ ውሃ ፋብሪካ ፕሮጀክቶችን ደረጃ 3 እና
በላይ የሆኑ የመንግስት የልማት ድርጅት ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማስገንባት በአወጣነው
የውስን ጨረታ የተሳተፉት የስራ ተቋራጮች ባቀረቡት ዋጋ፣ ባንክ ለፕሮጀክቶቹ በገመተው ዋጋ እና
በአማካሪ ድርጅቱ በቀረበው የዋጋ ግምት መካከል ልዩነቶች በመፈጠራቸው ልዩነቱ የተፈጠረበትን
ምክንያት ተለይቶ ሪፖርት እንዲቀርብ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት፤ በቴክኒክ ዳይሬክቶሬት የስራ
ክፍላችን በኩል ሁሉንም ሰነዶች በዝርዝር ታይተው ልዩነቶችን እና የልዩነቶቹን ምክንያቶች
በመለየት፣ የተገኜውን ውጤት ከአማከሪ ድርጅቶቹ ጋር ሰፊ ወይይት እና ምክክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡
በዚሁ መሰረት ለሦስቱም ፕሮጀክቶች ቀደም ሲል የነበረው አማካሪ ድርጅት ለባንክ ያቀረበውን ስራ
ዝርዝር እና የዋጋ ግምት፣ አዲስ የተቀጠረው አማካሪ ድርጅት ያዘጋጀውን የስራ ዝርዝርና የዋጋ
ግምት፣ የስራ ተቋራጮች ያቀረቡትን ዋጋ በማየት የዋጋ ልዩነት ለምን እንደተፈጠረ እና
ምክንያቶችን ለመለየት ጥረት ተደርጓል፡፡
አማራ ህንፃ
2 ዋንዛየ ሎጅ 167,147,827.12 239,000,000.00 791,639,478.00 824,584,809.35
ስራዎች
2
2. በሦስቱም ፕሮጀክቶች የዋጋ ልዩነት ያስከተሉ ምክንያቶች
በቀደመው አማካሪ Detail Design እና በዲዛይኑ መሰረት የስራ ዝርዝር ያልተሰራባቸው
ስራዎች በመገኜታቸው ምክንያት በአዲሱ አማካሪ ዲዛይኖች ተገምግመው ለስራው አስፈላጊ
የሆኑ ዲዛይኖች እና የስራ ዝርዝሮች በመካተታቸው፡፡
በቀደመው አማካሪ በኩል ተዘጋጅቶ ለባንክ በቀረበው የስራ ዝርዝር ላይ የተካተቱ የስራ
ዝርዝሮች የመስሪያ የዋጋ ግምት ግምት ያልተቀመጠላቸው ስራዎች በመኖራቸው፡፡
ባንኩ የፕሮጀክት ግንባታዎችን ግምት ሲያሰላ የቀደመው አማካሪ በሰራው ዲዛይን እና የስራ
ዝርዝር መሰረት በመሆኑ፡፡
በቀደመው አማካሪ እና በባንኩ የተገመተው የግንባታ መስሪያ ነጠላ ዋጋ አሁን ካለው የገበያ
ዋጋ ጋር ሲነፃፃር አነስተኛ በመሆኑ፡፡
በአዲሱ አማካሪ የቀረበ ግምታዊ የመስሪያ ዋጋ እና በስራ ተቋራጮች የቀረበ የመስሪያ ዋጋ
ላይ በነጠላ ዋጋ አሞሞል ላይ ልዩነቶች መኖር ማለትም በስራ ተቋራጮች በኩል የቀረበ
የነጠላ መስሪያ ዋጋ በአንዳንድ ስራዎች ላይ ምክንያታዊ ባልሆነ እና ግነት ያለበት በመሆኑ
የሚሉት በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
3. በእያንዳንዱ ፕሮጀክት የተፈጠረው የዋጋ ልዩነት፣ ማብራሪያ እና ዝርዝር መረጃ
3.1. ጢስ አባ ሊማ ውሀ ፋብሪካ
3
DRAINAGE SYSTEM & ACCESSORIES፣ Sanitary Manholes፣ Electrical installation
for production hall Partially missed(Fire fitting፣ Conduits and Pipes conduits and
Pipes፣ Electric Manholes፣ Feeder Line፣ Low Voltage System Earthling፣ Distribution
Board Panels፣ EMERGENCY LIGHTING FITTINGS AND LAMPS፣ Socket Outlet
Points 20A, 25A፣Lighting preventer system፣ COMMUNICATION TELEPHON
SYSTEM፣MAIN ANTENNA TV)
በቀደመው የስራ ዝርዝር ላይ የግንባታ የስራ አይነቱ ተቀምጦ የመስሪያ ዋጋ
ያልተቀመጠላቸው የስራ አይነቶች (Fiber glass water tanker፣ Pump፣ GRP 55 m3 water
tanker፣ Water proofing material፣ Fire protection pump፣ Fire fitting water supply
syatem፣ Garden tap፣ Water meter) ዋጋ ተሰርቶላቸዋል፡፡
በቀደመው ዲዛይን ያልተካተቱ ስራዎች ነገር ግን በተሻሻለው ዲዛይን የተካተቱ የስራ
ለውጦች፤ ሳይት ፕላን ላይ Layout ኖሮት Detail Design የሌላቸዉ፣ ዲዛይን ኖሮት ደግሞ
የስራ ዝርዝር የሌላቸዉ ብሎኮች በመገኜታቸው ዝርዝር መረጃ ከነማብራረያው
እንደሚከተለው በንፅፅር ቀርቧል፣
ሰንጠረዥ 2፡- ዲዛይን ስለሚያስፈልግ እንደ አዲስ ዲዛይን የተሰራላቸዉ ብሎኮች እና የተጨመሩ
የስራ ዝርዝሮች፡-
4
10 200m3 water resiorver 2 2 6,808,406.73 እንደ አዲስ ዲይዛን የተሰራላቸዉ
Total 231,802,144.01
15% Vat 34,770,321.60
Total Including 15% Vat 266,572,465.61
5
ከመረጃው መረዳት የተቻለው ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረበው ስራ ተቋራጭ በኩል ምክንያታዊ ያልሆነ
እና የተጋነነ ዋጋ በማቅረቡ ከላይ ለተዘረዘሩት ስራዎች አመካሪው ካቀረበው ግምታዊ ዋጋ
በላይ የብር 207,494,519.02 ልዩነት አስከትሏል፡፡ ይህ መረጃ የሚያሳየው ዝቅተኛ ዋጋ
ያቀረበው ድርጅት ያስገባው ዋጋ ምክንያታዊ ያልሆነና የተጋነነ መሆኑ ታይቷል፡፡
3.2. ዋንዛዬ ሎጅ
ለስራው አስፈላጊ የሆኑ በቀደመው ዲዛይን ያልተካተቱ ስራዎች እና በተሻሻለው ዲዛይን የተካተቱ
የስራ ለውጦች፤ ሳይት ፕላን ላይ Layout ኖሮት Detail Design የሌላቸዉ፣ ዲዛይን ኖሮት ደግሞ
የስራ ዝርዝር የሌላቸዉ ብሎኮች ተግኝተዋል፡፡
ሰንጠረዥ 4፡- ዲዛይን ስለሚያስፈልግ እንደ አዲስ ዲዛይን የተሰራላቸዉ ብሎኮች እና የተጨመሩ
የስራ ዝርዝሮች፡-
10 Sanitory Work For Site Work 1 34,655,268.02 እንደ አዲስ ዲይዛን የተሰራላቸዉ
11 Electrical work For Site work 1 33,535,519.07 የስራ ዝርዝር ሙሉ በሙሉ የሌለዉ
Total 205,958,828.14
15% Vat 30,893,824.22
Grand Total 236,852,652.36
6
ከላይ ከተገለፀው መረጃ መረዳት የተቻለው፡-
አዲስ በተጨመሩ የግንባታ ስራዎች ምክንያት ቫትን ጨምሮ ብር 236,852,652.36 በስራ
ተቋራጩ የቀረበ ሲሆን፤ ይህም የፕሮጀክቱን ዋጋ ከፍ እንዲል አድርጎታል፡፡
በስራ ተቋራጩ በኩል ለግንባታ ስራዎች የቀረበ ነጠላ ዋጋ በአብዛኛው ወቅታዊውን የገበያ ዋጋ
ያማከለ በመሆኑ ብዙም ግነት ያልታየበት ሲሆን በአልሙኒየም መስኮት እና በሮች ላይ የቀረበው
ዋጋ ግን መከለስ እንዳለበት ለማየት ተችሏል፡፡
3.3. የደብረ ማርቆስ ባለ 10 ፎቅ (B+G+10) ሁለገብ ህንጻ
ለስራው አስፈላጊ የሆኑ በቀደመው ዲዛይን ላይ ያልተካተቱ የግንባታ የስራ አይነቶች እና በአዲሱ
ዲዛይን እና የስራ ዝርዝር ላይ የተካተቱ የግንባታ ስራዎች Demolishing work፣ Excavation
above 4.5m ፣Excavation for soft, boulder and hard rock፣ Lintels፣ Expansion joints
፣brick wall ፣roof cover changes G-28 to EGA፣ Strainer ፣Skylight roof፣ Fire escape
exit/staircase፣ Ceiling changes Chip wood to Others፣ Ceiling for toilet፣ Corner
protection፣ Acrylic type water proof፣ Wooden door፣ Toilet partition ፣Cladding for
down pipe፣ Cladding for duct (EL & SN)፣Floor finish፣ Aluminum internal partition፣
Rollup metal door፣ Epoxy flooring፣ Coping ፣External stone cladding፣ Granite tile
for lift wall፣ Plaque at the top of the building፣ Meeting hall stage work፣ Parquet
for stage flooring፣ Audition chair፣ Gypsum board ceiling፣ Paint for external wall
፣ Traffic signage፣ Pavement around the building፣ Fire fitting፣ Cctv፣ Heater፣
Pumps፣ Ground reservoir፣ Submersible pump፣ Site work፣ Generator ሲሆኑ፤
እነዚህ አዲስ የግንባታ ስራዎች በመጨመራቸው ምክንያት የፕሮጀክቱን ዋጋ ከፍ እንዲል
አድርጎታል፡፡
በስራ ተቋራጩ በኩል በተወሰኑ የግንባታ ስራዎች ላይ ያቀረበው ዋጋ ወቅታዊውን የገበያ ዋጋ
ያላማከለ እና ግነት ያለበት መሆኑ ታይቷል፡፡
ሰንጠረዥ 5፡- በአማካሪ ድርጀቱ እና በስራ ተቋራጩ የቀረበ ዋጋና የልዩነት መጠን
7
4 Openings 9,913,830.13 35,550,335.80 25,636,505.68
5 Specialties 622,888.00 2,671,560.00 2,048,672.00
6 Plumbing 24,863,112.80 35,686,785.00 10,823,672.20
Heating Ventilating
7 11,580,800.00 57,938,540.00 46,357,740.00
and Air Conditioning
8 Electrical 32,828,682.80 67,676,289.00 34,847,606.20
Total 103,389,025.82 230,880,498.08 127,491,472.26
15% vat 15,508,353.87 34,632,074.71 19,123,720.84
GRAND SUMMARY 118,897,379.69 265,512,572.79 146,615,193.10
4.1. በቀደመው አማካሪ የተሰራው ዲዛይን እና የስራ ዝርዝር መጎደሎች ስለነበሩበት፤ በአዲሱ አማካሪ
ዲዛይኖቹ እና የስራ ዝርዝሮቹ ተገምግመው በነባሩ ዲዛይን እና የስራ ዝርዝር ላይ ማስተካከያ
ተደርጎ ለግንባታ ፕሮጀክቶቹ አስፈላጊ የሆኑ አዳዲስ የስራ ዝርዝሮች ስለተጨመሩ ነው፡፡
4.2. ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረቡት የስራ ተቋራጮች በኩል በአንድ አንድ ስራዎች ላይ የቀረበው የግንባታ
መስሪያ ዋጋ የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያማከለ ባለመሆኑ በምህንድስና ግምቱ እና ዝቅተኛ ዋጋ
ባቀረቡ ስራ ተቋራጮች መካከል የዋጋ ልዩነት ተፈጥሯል፡፡
4.3. የባንኩ የግንባታ ፕሮጀክቶች ግምታዊ ዋጋ የቆየ የገበያ ዋጋ ግምት በመሆኑ አማካሪ ድርጀቱ
እና የስራ ተቋራጮች ካቀረቡት ዋጋ ጋር ሲነፃፀር ሰፊ ልዩነት ታይቷል፡፡
5. የመፍትሄ ሀሳቦች
5.1. የስራ ተቋራጮች በአንድ አንድ ስራዎች ላይ ያቀረቡት ዋጋ ወቅታዊውን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበና
የተጋነነ በመሆኑ ከሀብት ስራ አመራር ዘርፍ ጋር በመሆን አሰራሩን በመከተል ከስራ ተቋራጮች
ጋር ድርድር በማድረግ የፕሮጀክቶቹ ዋጋ እንዲቀንስ ጥረት ማድረግ፡፡
5.2. የማህበሩን አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት ለጊዜው ሊቆዩ/ከስራ ዝርዝር ሊወጡ የሚችሉ
ስራዎች ካሉ አሁንም ተጨማሪ ቴክኒካል አስተያየት ቀርቦ የጋራ መግባባት በመፍጠር በቀጣይ
እንዲሰሩ የማድረግ አሰራርን መከተል ቢቻል፡፡
5.3. ዳሽን ባንክ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ለተፈጠረው የዋጋ ልዩነት ተጨማሪ ብድር
እንዲፈቅድልን በማድረግ ግንባታዎቹን ማስቀጠል የሚሉት ናቸው፡፡