Professional Documents
Culture Documents
123
123
i
ሰንጠረዠ ማውጫ
ii
ምስል ማውጫ
ምስል 8፡ የመሬት መሰንጠቅ እና የመሬት መንሸራተት የጀመረበት ቦታ ∕Starting point of fault and Land slide∕ 10
ምስል 9፡ የመሬት ስብራት ያቆመበት ቦታ/Fault ending point/ 10
ምስል 10፡ አስጊ የውሃ ተቋም እና መኖሪያ ቤት ∕Peril water point and house∕ 10
ምስል 11፡ ከሃያ ዓመት በፊት የተፈጠረ የመሬት መንሸራተት 12
ምስል 12፡ የተጉዱ መሰረተ ልማቶች በከፊል 14
ምስል 13፡ የወደሙ ቤቶች በከፊል 15
ምስል 14፡ በከፍተኛ ስጋት ላይ ያሉ ቤቶች በከፊል 15
ምስል 15፡ የተጉዳ መሬትና በስጋት ላይ ያለ መሬት መጠን 16
iii
አጭር መግለጫ
የአምባሰል ወረዳ በአማራ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ መስተዳደር ዞን ስር ከሚገኙት የምስራቅ አማራ ወረዳዎች ወስጥ አንዱ
ነው፡፡ አምባሰል ወረዳ በጥቅሉ የመሬቱ አቀማመጥ ተራራማና ወጣ ገባ የበዛበት፣ የአፈር ለምነቱም ዝቅተኛ የሆነ፣ የአፈር
መሸርሸር ያለበት፣ በጎርፍ የሚጠቃ ወረዳ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ለመሬት መንሸራተት ዋነኛ መንስኤ ነው ተብሎ ይወሰዳል፡፡
በአካባቢውም የመሬት መንሸራተት አደጋ አልፎ አልፎ የተከሰተ ሲሆን አሁንም በ01 ሊሞ ቀበሌ የተፈጠረው መሬት መንሸራተት
አደጋ ያደረሰው ጉዳት እጅግ የከፋ በቀላልና ባጭር ጊዜ ሊካካስ የሚችል አይደለም፡፡ አደገጋው በስነልቦናም ሆነ በኢኮኖሚ ላይ
ደረስው እንድሁም የደቀነው ስጋት ከፍተኛ ትኩረት ሊቸረው የሚገባ መሆኑን መረዳት ይቻለል፡፡ ስለዚህም በደረሳው አደጋ ስነ
ልቦናዊም ሳናነሳ በቅሳዊ ጉዳት ብቻ 35782500 ብር ሙሉ ለሙሉ አሳጥቷል፡፡ 81 ወንድ 86 ሴት 166 ማህበረሰብን ከመኖሪያ
ቦታቸው ሙሉ በሙሉ እንድፈናቀሉ አድርጓል፡፡ ለ137 አባዋራ ለ178 እመዋራ በድምሩ ለ315 ህብረተሰብ ለስጋት አጋልጧል፡፡
መሰረተ ልማቶችን አውደሟል፤108 ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንድስተጓጎሉ ሁነዋል፡፡ የችግሩ ጥልቅት ለአካባቢው
ህብረተሰብ ብቻ ሳይሆን ለውጫሌ ከተማም ቢሆን አስጊ በመሆኑ ከተማውን መታደግ የሚቻለው ለችግሩ ትኩረት ተሰጥቶ ዘላቄ
መፍትሄ በማበጀት መሆኑን ያመለክታል፡፡ በመጨረሻም መሬትን በአግባቡ አለመያዛችንና ከመሸከም አቅም በላይ አላግባብ የምን
ጠቀምባት ከሆነ በቃኝ ብላ አራግፋ አንደምትጥለን ማሳያ መሆኑን ያስረዳል፡፡ ስለዚህ ይህ አደጋ ብቸኛና ተተኪ የማይገኝለትን
የተፈጥሮ ሃብት የሆነውን መሬትን ተንከባክበንና ትኩረት ሰጥተን ካለይዝ በቀላሉ ማጣት አንደምንችል የሚያሳይ የደወል ጥሪ
መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ ስለዚህ አደገው የተከሰተባቸው ማህበረሰቦች ሆኑ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን አደጋ
ከመድረሱ በፊት በአፋጣኝ ቦታውን ለቀው እንድ ወጡና በጊዜያውይ መጠለያ የሚሰፍሩበት መንገድ ቢመቻች፡፡ በዘለቄተው
ሊሰፍሩበት የሚችሉ ቦታ በማዘጋጀት በእጃቸው ያለ ሃብትና ንብረት ሳይጠፋ በቋሜነት እንድቋቋሙ ቢደረግ፡፡ አካባቢው ጥለቅ
ጥናት ቢደረግበትና አካባቢው ከሰውና ከእንሰሳት ንኪኪ ተጠብቆ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራዎች ቢሰሩበት እንድሁም ወደ ቋሚ ደን
ልማት ቢሸጋገር፡፡ በጥቅሉ የተደረገው የዳሰሳ ጥናት ችግሩ ፈጣን ምላሽ ከልተሰጠው ችግሩ ቀጣይንት እንደሚኖረውና ተጨማሪ
ጉዳት እንደሚያደረስ ያመልክታል፡፡
iv
1. መግቢያ
አባሰል ወረዳ አባዛሃኛው የመሬት ክፍል ገደላማ በመሆኑ የጉርፍና የመሬት መንሸራተት ችግሮች
ከሚስተዋልባቸው አካባቢዎች አንዱ ሲሆን ለነዚህ አደጋዎች እንዲጋለጥ መነሻ ከሆኑት
ምክንያቶች ውስጥ ዋነኛው ተስማሚ ያልሆነ የመሬት አጠቃቀምና አያያዝ መኖር ነው፡፡ ይህም
በመሆኑ የመሬት የአፈር መሸርሸርና የመሬት መንሸራተት አደጋ በአካባቢው ሊሞ (01) ቀበሌ ልዩ
ስሙ ግራር ገንዳ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የመሬት መንሸራተት ተከስቷል፡፡ በዚህም መሰረት
የችግሩ አሳሳቢነት መገለጫ የሆኑት ጉዳቶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
1. አካባቢው ከሰውም ሆነ ከእንስሳት ንክኪ ሙሉ በሙሉ የተጠበቀ ባለመሆኑ የመሬት
መረበሽ ወይም እረፍት ማጣት መኖሩ
2. ህጋዊም ሆነ ህገወጥ ግንባታ በቦታው ላይ እየተካሄደ በመሆኑ መሬት ከሚሸከመው በላይ
በመሆኑ አሁንም እንቅስቃሴው ያልቆመ በመሆኑ
3. የአካባቢው ስሪት አፈር ቀላል እና በውኃ በቀላሉ የሚሸረሸር በመሆን
1
1.2. የጥናቱ አስፈላጊነት /ጠቀሜታ/
1.4.2. የጥናቱ ግብ
2
2. የጥናቱ የአጠናን ዘዴ (Methods of Study)
የወረዳው አየር ንብረት ወይና ደጋ ሲሆን የህዝቡ ኑሮ የተመሰረተው በግብርና ስራ ሲሆን በዚህ
መስክ ከተለያዩ ሰብሎች በተጨማሪ አትክልትና ፍራፍሬ ይመረትባታል፡፡ ወረዳዉ በ25 ቀበሌ
የሚለማ መሬት 14360ሄ/ር እና 91217 ሄ/ር የቆዳ ስፍት ያላት ሲሆን ወረዳዉ ከባህል ወለል
በላይ 1450—3600 ሜትር ከፍታ አለዉ የመሬት አቀማመጡ 92.5% ተራራማና ወጣ ገባ 7.5%
ሜዳማ የሆነ ተፈጥሮአዊ የመሬት አቀማመጥ አለው፡፡ እንደ ዳንኤል (1997) ከሆነ የአየር ፅባይ
ሁኔታ በረሃ (<800 ሜትር)፣ ቆላ (800-1500 ሜትር)፣ ወይና ደጋ (1500-2300 ሜትር)፣ ደጋ
(2300-3300 ሜትር) እና ውርጭ (>3300 ሜትር) ተብሎ ሊከፈል ይችላል፡፡ በዚህም መሰረት
የመሬት መንሸራተት የተፈጠረበት ቦታ በወይና ደጋ የአየር ፅባይ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል
3
ምክንያቱም ቦታው ከ1786-1884 ከፍታ ውስጥ ሰለሚገኝ፡፡ አደጋው ከደረሰበት ቦታ ቅርብ የሆነው
የሜትሮሎጂ ጣቢያ የውጫሌ ሜትሮሎጂ ጣቢያ ነው ፡፡ ከጣቢያው ከተገኘው መረጃ (2000-2005
ዓ.ም) እንደሚያሳየው የአካባቢው አማካኝ የዝናብ መጠን 922 ሚሊሜትር እንደሆነና ዝቅተኛው
የሙቀት መጠን 90C ከፍተኛው ደግሞ 330C መሆኑን ያመለክታል (2000-2009 ዓ.ም)፡፡
በቀበሌው ወንድ 1080 ሴት 283 ድምድ 1303 የሚገመት ህዝብ የሚገኝ ሲሆን የመሬት
መንሸራት በደረሰበት ጎጥ ወንድ 176 ሴት 231 ድምር 407 ህዝብ የኖራል፡፡ ዋነኛ
መተዳደሪያውም የግብርና ሥራ ነው፡፡ በእርሻ ስራው በዝናብ ውሃ በመታገዝ ስንዴ፣ ጤፍ፣
በቆሎ፣ ዘንጋዳና ማሽላ ያመርታሉ፡፡ በግብርና ስራው የሰብል ምርት ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል፡፡
የፍራፍሬ ዛፎች እንደ ብረቱካን፣ ማንጎ፣ ግራቪሊያ፣ አቡካዶ ወዘተ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም
ከአትክልት ደግሞ ጎመን በብዛት ይመረታል፡፡ ከዚሁ ጋር አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን የቤት እንስሳት
በማርባት ተጠቃሚ መሆን ችሏል፡፡
የመሬት መንሸራተት በደረሰበት ቀበሌ በጎጧ ውስጥ የሚገኝ የእንስሳት ሃብት የቀንድ ከብት 66
በግና ፍየል 132፣ ዶሮ 220፣ የንብ ቀፎ 6 ይገኛል፡፡
ቦታዎችን በአካል በመስክ ተገኝቶ የምልከታ ስራ መስራት /Observation/ አንዱ ሲሆን በዚህም
ስለአካባቢው የደረሰው የመሬቱ መንሸራተት በአካባቢው ላይ እያደረሰ ያለውን ችግር ደረጃ እና
ስፋት ለማስተዋል ተችሏል፡፡ ሌላው በዚህም የቅኝት ወቅት በየመሬት አጠቃቀሙ ሊሰሩ የሚችሉ
የአካባቢ ጥበቃ፣ የተፈጥሮ ኃብትና የመሰረተ ልማት ሥራዎች በምን ያህል መጠን እንደተሰሩ
4
ጭምር፣ ምን ያህል ጉዳት እንደደርሰም ለማየት ተችሏል፡፡ ደረሱ ጉዳቶችን በምስልም ሆነ
በተንቀሳቃሽ ምስል ለመያዝ ተችሏል፡፡
5
2.5. የመረጃ አተናተን ዘዴ (ስልት)
ጥናቱ በሚካሄድበት ወቅት ጥቅም ላይ የዋሉ ቁሳቁሶች ጂ.ፒ.ኤስ፣ ሞባይል፣ ሜትር፣ ኮፒተርና
ጅ.አይ.ኤስ ሶፍትዌር ናቸው፡፡
6
3. የጥናት ውጤቶችና ማብራሪያዎቹ
የከርሰ ምድር ውሃ (ground water table approach to the surface) በዚያ ቦታ ላይ መኖሩ
አንዱ ለፎልት መፈጠር እንዴ ምክንያት ይጠቀሳለ፡፡ በዚህም በቡድን ውይይት የተገኘው መረጃ
በዚሁ አካባቢ የተለያዩ ምንጮች የገፀ መድረ ውኃ ያሉና እንዴነበሩ እንደሁም እንዴተደፈኑ
ያሳያል፡፡ ሌላኛው ምክንያት ደግሞ የውስጠኛው የመሬት ክፍል የአፈሩ ወይም የአለቱ ጥንካሬ
ከመሬት ስበት ጋር ሲነፃፀፃ አናሳ ሆኖ ከተገኘ የመሬት መሰበርና መታጠፍ (fault or fould)
7
ሊፈጠር ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት የመሬት መንሸራተት (Land slide) ይፈጠራል፡፡ በተደረገው
የዳሰሳ ጥናትና በቡድን ውይይቱ በተገኘው መረጃ መሰረት መሬት መንሸራተት የገጠመው አካባቢ
ከፍተኛ ወጣገባ የሆነ፣ ሸለቆ የበዛበት፣ ከፍተኛ ተዳፋትነት ያለው የመሬት ክፍል በመሆኑ ይህ
ደግሞ የመሬት መንቀጥቀጥ (Earthquick) በአካባቢው ለሰከንድ ወይም ለማይክሮ ሰከንድ
በአጋጣሚ ከተፈጠረ ወጣ ገባ የመሬት ክፍል (undulated land surface) ይህንን አደጋ ተቋቁሞ
የመቆየት እድል የለውም፡፡ በዚህም ምክንያት የመሬት መሰበር ወይም የመሬት መታጠፍ (fault
or fould) አደጋ ስለሚያጋጥም ለመሬት መንሸራተት እንደ ምክንያት ይጠቀሳል፡፡ በዚህ የተነሳ
በአካባቢው ያሉ የሰው ልጆች፤ እፅዋቶች፤ መጠለያ እና መሰረተ-ልማቶች በከፊል እና ሙሉ
በሙሉ የመጥፋት አደጋ ይከሰታል፡፡ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድም ችግሩ እንድባባስ በማድረግ
ለሞት እና ለንብረት መውደም አደጋ ያጋልጣል፡፡
መሬት መንሸራተት በተለያዩ ዓይነቶች ሊከፈል ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡- በቁስ አይነቱ በስድስት
ሊከፈል ይችላል፡፡ ይኽውም መውደቅ፣ መገንደስ፣ የመሬት መምታታት ፣ መውረድ፣ መዘርጋት
እንዲሁም ሁለትና ከዚያ በላይ ዓይነቶችን ሊይዝ ይችላል፡፡ በዚህም መሰረት በአምባሰል ወረዳ
ሊሙ ቀበሌ የተከሰቱውን የመሬት መንሸራተት በሚከተለው ምስል ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡
8
ምስል 5፡ የመሬት መስመጥ ∕Normql fault∕
9
ምስል 8፡ የመሬት መሰንጠቅ እና የመሬት መንሸራተት የጀመረበት ቦታ ∕Starting point of fault and Land slide∕
ምስል 10፡ አስጊ የውሃ ተቋም እና መኖሪያ ቤት ∕Peril water point and house∕
10
3.2.3. የገፀ-ምድር እና የውሃ መውረጃ ሁኔታ
በአካባቢው የተለያዩ የአገርና የውጭ ዝርያ ዛፎች በጓሮ ዙሪያ ለምተው ይገኛሉ፡፡ ከአገር በቀል
ዝርያዎች የአባሻ ግራር፣ ወይራና ዋንዛ በብዛት ሲገኙ ደደሆና ሌሎች ቋጥቋጦች በሸለቆ ቦታዎች
ይገኛሉ፡፡ ከውጭ ዝርያዎች ደግሞ የተለያዩ የባህር ዛፍ ዝሪያዎችና የፍራፍሬ ዛፎች እንደ
ብረቱካን፣ ማንጎ፣ ግራቪሊያ፣ አቡካዶ ወዘተ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ማሽላ፣ በቆሎ፣ ጤፍ እና
ዘንጋዳ በአካባቢው ይመረታል፡፡ ከአትክልት ደግሞ ጎመን በብዛት ይመረታል፡፡
የመንሸራተት አደጋ የደረሰበት አካባቢ አፈር ደለል ሆኖ የፍርስራሽ ክምር፣ ቀር አፈርና የደለል
አፈር አይነት ነው ፡፡ የአፈር ቅንጣት ሁኔታው ደግሞ ዋልካማ (100%) ነው፡፡
በዚህ ቀበሌ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ቢሰራለትም በመሬት ላይ የተሰሩ ሰራዎች የሉም፡፡ በዚህም
መሬቱን ከዕለት ከዕለት እራፍት የሚያሳጡ፣ የሚረብሹ ተግባራት ያሉ ሲሆን የተፈጥሮ ሃብት
ስራዎችም በአካባቢው መሬት ላይ የተሰሩ ስራዎች ማገኘት አልተቻለም፡፡ አካባቢው ከሰውና
ከእንስሳት ንክኪ የተጠበቀ አይደለም፡፡ በዚህም አካባቢው ከሚሸከመው በላይ የተለያዩ ህጋዊና
11
ህገወጥ ግንባታዎች ይገነባሉ ተገንብተዋልም፡፡ ነገር ግን የላይኛው የአፈር ንጣፍ ጥቁር አፈር
በመሆኑ ለግንባታ የማይመከር በቀላሉ ሊንሸራተት የሚችል መሆኑን መረዳት ተችሏል፡፡ የአፈር
ሲሪትም ቢሆን በቀላሉ በውኃ ሊቦረቦር የሚችል፤ እርጥበት ሲነካው በወሀ የሚቀልጥ፣ በፀሀይ
የሚሰነጣጠቅ ጥቁር አፈር የአካባቢው መሬቱ የተሸፈነ በመሆኑ አደጋው በቀላሉ ለፈጠር
እንደሚችል መረዳት ይቻላል፡፡ በዚህ ቦታ የአፈር እና የውኃ ጥበቃ ሊሆኑ የሚችሉ ስራዎች
አልተሰሩም፡፡ እንድሁም መሬተ አቃፊ ስር ያላቸው ዕፅዋቶች (ቀርቀሃ፣ ዝሆኔ ሳር ወዘተ) በሆኑ
ተክሎች መሬቱ ያልተሸፈ በመሆኑ እና ከጉርፍ የሚከላከሉ ስራዎች ያልተሰሩ በመሆናቸው
ለተፈጠረው የመሬት መንሸራተት አድጋ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ነጥቦች ናቸው፡፡
12
3.3. የችግሩ መንሰኤ
በጥቅሉ የመሬት ምንሸራተት ክስተት ውጫዊ እና ውስጣዊ ምክንያቶች አሉት፡፡ በዚህም መሰረት
በአምባሰል ወረዳ ልዩ ስሙ ግራር ገንዳ በተበለው ቦታ የተከሰተውን የመሬት መንሸራተት ችግር
መንሰኤዎች ከላይ በተዘረዘሩት መንስኤዎች በመነሳት እደሚከተሉት ቀርቧል፡-
13
በተደረገው የዳሰሳ ጥናት መሰረት በዚህ አደጋ በሰውም ላይ ሆነ በእንስሳት የሞትን የመቁሰል አደጋ
ያልደረሰ ቢሆንም 166 ማህበረሰብን የተፈናቀሉ መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ ነገር ግን በንብረት ላይ ያደረሰውን
አደጋ እንደሚከተለው ይቀርባል፡-
ሶስት ኪሎ ሜትር የእግር መንገዶች፣ የውኃ መስመሮች፣ አራት የስልክ ፖሎች መውደቅና የሁለት ኪሎ
ሜትር የመብራት ገመዶች በመበጣጠስ ጉዳት ደርሷል፡፡ በዚህም ዘጠኝ የግለሰብ ቆጣሪ፣ አንድ የውኃ
ቦኖና 2000 ሜትር የውኃ ቧንቧ መስመር ከጥቅም ውጭ ሲሆን 58 የግለሰብ ቆጣሪ፣ አንድ የውኃ ቦኖና
4430 ሜትር የውኃ ቧንቧ መስመር በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ሁኗል፡፡ በጥቅሉ የ38 አባዋራ የ46 እማዋራ
በድምሩ የ84 ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ያወደመ ሲሆን ለ137 አባዋራ ለ178 እመዋራ በድምሩ ለ315
ህብረተሰብ ለስጋት ተጋልጧል፡፡
በይዞታ መሬት ላይ የተገነቡ 12 ቤቶች እንደሁም 26 የመገንባት ፍቃድ የሌላቸው ቤቶች ሙሉ በሙሉ
በመሬት መንሸራተቱ አደጋ ተጎድተዋል (ፈርሰዋል)፡፡ በዚህም 25 አባዋረዎች 13 እማዋረዎች በድምሩ 38
የማህበረሰብ ክፍሎች ቤት በመፍረሱ ምክንያት 33.6ሚሊየን ብር እንድያጡና ከኑሮው እንደፈናቀል
ሁኖል፡፡ በውስጡም የነበሩ ህፃናት፣ ተማሪዎችና አቅመድካማ ለጭንቀት፣ ለተስፋ መቁረጥ ተጋልጠዋል፡፡
14
ምስል 13፡ የወደሙ ቤቶች በከፊል
በስጋት ላይ የሚገኙ መልቀቅ ያለባቸው ማህበረሰብ ያሉም ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በይዞታ መሬት
ላይ የተገነቡ 17 ቤቶች እንደሁም 3 የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸው ቤቶች ሙሉ በሙሉ በመሬት
መንሸራተቱ ለአደጋ ተጋላጭ መሆናቸው አይተናል፡፡ በዚህም 10 አባዋረዎች 10 እማዋረዎች
በድምሩ 20 የማህበረሰብ ክፍሎች ቤት ቤታቸው ለአደጋ የተጋለጠ በመሆኑ የቤቶቹም የዋጋ
ግምት 21.7 ሚሊየን ብር እንደሚደርስ ተገምተዋል ፡፡
በ500 ሜትር ውስጥ ያሉ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰብ ያሉም ሲሆን ከነዚህም ውስጥ
በይዞታ መሬት ላይ የተገነቡ 8 ካርታና ፕላን ያላቸው ቤቶች እንደሁም 112 የይዞታ ማረጋገጫ
የሌላቸው ቤቶች ሙሉ በሙሉ በመሬት መንሸራተቱ ለአደጋ ተጋላጭ መሆናቸው አይተናል፡፡
በዚህም 70 አባዋረዎች 51 እማዋረዎች በድምሩ 121 የማህበረሰብ ክፍሎች ቤት ቤታቸው ለአደጋ
15
የተጋለጡ በመሆናቸው የቤቶቹም የዋጋ ግምት ጠቅላላ ሀብት 133.1 ሚሊየን ብር እንደሚደርስ
ተገምተዋል፡፡
በመሬት መንሸራተቱ 0.1875ሄ/ር የእርሻ መሬት፣ 0.7ሄ/ር የግጦሽ መሬት፣ 2.557ሄ/ር የደን
መረት እንድሁም 6.2155ሄ/ር መንደር በድምሩ 9.66ሄ/ር መሬት የአደጋው ሰለባ ሲሆን 3.67ሄ/ር
ሙሌ በሙሉ የወደመና 5.99ሄ/ር በከፍተኛ ስጋት ላይ ያለ መሆኑን ተረጋጧል፡፡ 30 አባዋራ፣ 19
እማዋራ በድምሩ 49 የመሬት ባለይዞታዎች ሙሉ በሙሉ የመኖሪያና መሬታቸውን ተጉጅ
ሁነዋል፡፡ 10 አባዋራ፣ 10 እማዋራ በድምሩ 20 የመሬት ባለይዞታዎች በከፊል መሬታቸው ተጉጅ
ሁኗል፡፡
16
3.4.4. በአትክልትና በእፅዋት ላይ የደረሰ አደጋ
በዚህ አደጋ በምግብ እህሎች ላይ የደረሰ አደጋ ባኖርም በቋሜ አትክልቶች ላይ ከፍተኛ አደጋ ደርሷል፡፡
8720 ባህርዛፍ፣ 21 ዋንዛ፣ 25 ግራርና 8 ወይራ በጥቅሉ በወቅቱ የገባያ ዋጋ 1483400 ብር አሳጥቷል፡፡
በተጨማሪም ቋሜ ፍራፍሬ አትክልቶች ማለትም 32 ፓፐየ፣ 34 ማንጎ፣ 5 አቡካዶ፣ 119 ሙዝ፣ 391
ቡና እና 19 ብርትኳን በመጎዳታቸው በወቅቱ የገባያ ዋጋ 699100 ብር አሳጥቷል፡፡
የዞንና የወረዳ ቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሞ የተጎጅዎችን መረጃ በጥራት በማጥናት መጠይቆችን
አዘጋጅቶ መረጃዎችን እያሰባሰቡ መሆኑ፡፡ ተጎጅዎች ከአደጋው ቦታ እንድርቁ /እንድለቁ የጥንቃቄ
ምክር ሃሳቡን አሰቀምጧል፡፡ ተጎጅዎች በአደጋው ውስጥ ያሉ መኖሪያ ቤቶችን እንድፈርሱ ንብረት
እንዳነሱ ማድረግ፡፡ አደጋው እየተስፋፋ በመሆኑ እና የት ላይ እንደሚቆም ስላልታወቀ ከአደጋው
መጨረሻ ነጥብ ጀምሮ በ500 ሜትር ራድየስ ስንት ማህበረሰብ እንደሚኖር መረጃ መያዝ ስራ
ተሰርቷል፡፡ አጠቃላይ መሰረታዊ መረጃ በሁሉም በአደጋ መከላከል፣ በጤና፣ በወሃ፣ በከተማ
ልማት መረጃዎችን በመጠይቆቹ መሰረት መረጃ መሰብሰብ ስራ ተሰርቷል፡፡ የተፈናቃይ ጊዜያዊ
መጠለያ የቤት ኪራይ እንድሁም እንዳስፈላጊነቱ በድንኳን እንድሰፍሩ ምክር ሃሳቡን ተቀምጧል፡፡
የተፈናቀሉ ሰዎችን የእለት ድጋፍ ማለትም በአደጋው የአቅመ ደካሞችን ተጎጅዎችን ጊዜያዊ
የመኖሪያ ቤት ማስፈረሻ፣ የማቴሪያል ማጓጓዣ የመኖሪያ ቤት ግንባታና መስፈሪያ ቦታ ከዞንና
ከወረዳ አመራር ጋር በመሆን ማመቻቸት እንድሁም የተራዓድኦ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን
ድጋፍ እንዳደርጉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ስራ መስራት ተጀምሯል፡፡
በዚህ በተከሰተው የመሬት ምንሸራተት ምክንያት የተስተጓጎሉ ተማሪዎች ያሉ ሲሆን አጸደ ህጻናት 34 ከ1
እስከ 8ኛ ክፍል የሚማሩ 51 ከ8 እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ 23 ተማሪዎች በጠቅላላ 108 ተማሪዎች
ትምህርታቸውን በተረጋጋ ሁኔታ ባለመከታተላቸው ምክንያት የስነ ልቦና ጫና እንደደረሰባቸው ለማየት
ተችሏል ፡፡
17
4. ማጠቃለያና ምክረ-ሐሳብ
4.1. ማጠቃሊያ
18
4.2. ምክረ ሃሳብ
ከአጭር ጊዜ
ከላይ ከተቀመጡት ሃሳብ በመነሳት አደጋው ከዕለት ዕለት እየጨወረ የመጣ በመሆኑ
አደገው የተከሰተባቸው ማህበረሰቦች ሆኑ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን
አደጋ ከመድረሱ በፊት በአፋጣኝ ቦታውን ለቀው እንድ ወጡና በጊዜያውይ መጠለያ
ቢሰፍሩ፡፡
በዘለቄተው ሊሰፍሩበት የሚችሉ ቦታ በማዘጋጀት በእጃቸው ያለ ሃብትና ንብረት ሳይጠፋ
በቋሜነት እንድቋቋሙ ቢደረግ፡፡
ጉዳት የደረሰበት መሬት መልሶ እጥቅም ላይ እድውል ህገወጥ እንቅስቃሴ ማስቆም ቢቻል፡፡
የረጅም ጊዜ የመፍትሔ ሃሳብ
የስነ ምህዳር ጥናት ጥልቅ የሆነ ጥናት ያስፈልገዋል፡፡ ማለትም ለችግሩ መንስኤ ቅርብ
የሆነ የከርሰ ምድር ውሃ መኖር ተብሎ የተቀመጥው የከርሰ-ምድር ውሃ መኖሩን የሚገልፅ
ከቡድን ውይይት መረጃ በተጨማሪ የጅኦፊዚክስ መሳሪያ በመጠቀም ውሃ በአካባቢው
መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ በሁለተኛነት እንደመንስኤ የተቀመጠው የአፈሩ ወይም
አለቱ ጥንካሬ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት አፈር ምርምር ተቋም ወይም አማራ ውሃ ጥናትና
ድዛይን የአፈርን ጥንካሬ ላቦራቶሪ በመውሰድ ማረጋገጥ ይገባል፡፡ በሶስተኛነት የተቀመጥው
የመሬት መንቀጥቀጥ ሲሆን በዚህ ቦታ ላይ የበላይ ባለሙያዎች ከትልቅ የምርምር ተቋም
በመጋበዝ ጥልቅ የሆነ ጥናት ያስፈልጋል፡፡ በዚህም የተነሳ ከተማውን መታደግ የሚቻለው
ጅኦሎጅስቶች የተሳተፉበት የምርምር ጥናት የሚካሄደው ለስራው የሚያግዝ ወይም ለጥናቱ
የሚያግዙ የመመርመሪያ መሳሪዎች፤ የሰው ሀይል፤ በጀት እና ጊዜ ይፈልጋል፡፡ እነዚህን
አጣምሮ ስራው ካልተሰራ በስተቀር ከተማውንና የዚያን አካባቢ ኗሪ ማህበረሰብ መታደግ
ላይቻል ይችላል፡፡ በዚህም የተነሳ የሚመለከተው አካል ጥናት እንድጠናለት ከትልልቅ
ተቋማት ባለሙያዎችን በመጋበዝ በጀት እና ጊዜ መድቦ ማስጠናት እና ለወረዳውም
ጭምር ዘላቂ መፍትሄ ቢቀመጥ፡፡
አካባቢው ከሰውና ከእንሰሳት ንኪኪ ተጠብቆ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራዎች ቢሰሩበት
እንድሁም ወደ ቋሚ ደን ልማት ቢሸጋገር፡፡
19
ዋቢ መጻሐፍት
Daniel Gemechu. (1977). Aspect of climate and water balance in Ethiopia. Addis Ababa
University press, Addis Ababa, 79pp.
Getnet Mewa and Filagot Mengistu (2021).Institute of Geophysics, Space Science and Astronomy,
Addis Ababa University, Ethiopia.
World Bank (2019). The international Bank for reconstruction and Development, theWorld Bank
Group 1818 H Street, NW, Washington, D.C.20433, USA.
20
ዕዝል
.የመረጃ መሰብሰቢያ ፎርማቶች
I. የመሬት መንሸራተት ጉዳት መረጃ መስብሰቢያ ፎርም
1.አጠቃላይ መረጃ
1.1 የወረዳ ስም----------------
1.2 የተከሰተበት ቀበሌ-------------
1.3 የተከሰተበት ጎጥ ስም---------------
1.4 የተከሰተበት ቦታ የመሬት ከፍታ ከፍተኛ---------------------- ዝቅተኛ-----------
1.5 አመታዊ የዝናብ መጠን------------ሚሚ
2.የመሬት ሁኔታ
2.1 ችግሩ የተከሰተበት ቦታ የአፈር ዓይነት
ተ/ቁ የአፈር ዓይነት ስፋት (ሄ/ር) ስፋት ከጠቅላላው (%)
1 አሻዋማ
2 ዋልካማ አሸዋማ
3 ደለላማ ዋልካ
4 ዋልካ
5 ሸክላማ ዋልካ
6 ሸክላማ
7 ከባድ ሽክላ
21
ተ/ቁ የመሬት አጠቃቀም ሁኔታ ስፋት (ሄ/ር) ስፋት ከጠቅላላው (%)
1 የታረሰ መሬት
2 የሳር/ ግጦሽ መሬት
3 የደን መሬት
4 ቁጥቋጦ መሬት
5 በመንደር
6 ሌላ (ይገለጽ)……………….
7 ድምር
3. የሶሾ-ኢኮኖሚክ መረጃ
3.1. የተጋላጭ ህዝብ መረጃ
የቤተሰብ ተጠሪ ጠቅላላ ህዝብ በአማካኝ የዕድሜ ሁኔታ
የቤተሰብ
መጠን
አባወራ እማወራ ድምር ወንድ ሴት ድምር እስከ 14- 18- 36- ከ 55 አመት
13 17 35 55 በላይ
በቁጥር
(%)
22
1 0-14
2 15-64
3 > 64
ድምር
ተ/ቁ የቤት አንስሳት ዓይነት መጠን (በቁጥር) አማካኝ ይዞታ በአባወራ ከጠቅላላው ያለው
ድርሻ በፐርሰንት
1 በሬ
2 ላም
3 ጥጃ
4 ጊደር
5 ፈረስ
6 በቅሎ
7 አህያ
8 ፍየል
9 በግ
10 ዶሮ
ሌላ ካለ ይገለጽ……
ድምር
23
3 ጥጃ
4 ጊደር
5 ፈረስ
6 በቅሎ
7 አህያ
8 ፍየል
9 በግ
10 ዶሮ
ሌላ ካለ ይገለጽ……
24
1 የምግብ እህል ኩ/ል
ጤፍ
ማሽላ
ዘንጋዳ
ሌላ (ይገለጽ)
2 የፍራፍሬ ዛፍ ቁጥር
ፓፓያ
ጊሽጣ
ሌላ (ይገለጽ)
3 አትክልት
ጎመን
ሰላጣ
4 የደን ዛፍ
ባህር ዛፍ
ዋንዛ
5 ቅመማ ቅመም
6 ሌሎች (ይጠቀስ)
25
ዓይነት ዋጋ ወንድ ሴት ድምር
5 ሌላ ካለ ይካተት
4) መሰረተ ልማት
4.1)የውሃ ተቋማት ሁኔታ
የወደሙ የውኃ ተቋማት አይነትና ብዛት በዝርዘር ይገለጽ?
የተበላሹና የወደመ የውኃ መስመሮች አሉ ወይ? 1) አለ 2)የለም
ከለይ ለተገለታ ጥያቄ መልሱ አዎ ከሆነ በመጠን ይገለጽ
የተበላሸ አንዲሁም የተሰበረ የውሃ ቆጣሪ ብዛት ይገለጽ? ምን ያህል ቆጣሪ ከቦታው ይነሳል?
የባከነ ወሃ መጠን እና በከተማ ታሪፍ በገንዘብ ሲተመን ስንት ይሆናል?
በኤሌክትሮ መካኒካል ፣የጥበቃ ቤት፣ጀነረተሮች፣ የውሃ መለዋጫና ጥገና መሳሪዎች የደረሰ ጉዳት
ካለ ቢገለጽ
26
በቦታው ምን ያህል የውሃ ማዳያ (ቦኖ) አለ? የውሃ ማጣራቀሚያ ጋን በቦታው አለ? የሚያዝ
መጠኑ ስንት ነው?
በጉዳቱ ሰለባ የሆነ አባወራና እማወራ ብዛት ቢገለጽ
ጉዳት የደረሰበት የመስኖ ተቋም አይነትና ብዛት በዝርዘር ቢገለጽ
ጉዳት የደረሰበት የእንስሳት ውሃ ማጠጫ ገንዳ ብዛት--------------------
4.2መንገድ
የተጎዳ የእግር መንገድ-------------ኪ/ሚ
የተጎዳ የመኪና መንገድ---------ከ/ሚ
4.3 የመብራት መስመር
የተጎዳ የመብራት ፖል ብዛት--------
የተጎዳ የመብራት መስመር----------------ኪ/ሚ
4.4 ባዪ ጋዝ
በአካባቢው ባየጋዝ አለ? በተቋሙ ላይ የደረሰ ጉዳትስ አለ? የጉዳቱ መጠን ይገለጽ…………..
4.5 መኖሪያ ቤት
1/ የግንባታው ባለቤት ሙሉ ስም አቶ/ወ/ሮ
2/ ግንባታው የሚገኝበት አድራሻ ከተማ ……. ቀበሌ …. ልዩ ሰፈር …………………………..
3 / የግንባታው አይነት …………………………………….. አገልግሎት …………………………...
4/ የግንባታ ካርታና ፕላን ሀ/ ያለው ለ/የሌለው ሐ/ ሌላ ማስረጃ ካለ ይጠቀስ……
5/ ግንባታው በአሁኑ ሰዓት ያለበት ደረጃ …ሀ/ የፈረሰ ለ/ ያልፈረሰ ሐ/ በከፊል ተጎዳ
6/ የግንባታው ልኬታ በሜትር ርዝምት……….. ወርድ…………... ቁመት ……….የቤቱ /የግንባታው
ወለል ስፋት በካ/ሜ……
7/ የቤቱ ዙሪያ በድንጋይ ግንብ ሀ/የታሰረ ለ/ያልታሰራ ሐ/ በደረቅ ካብ የታሰራ መ/ ምንም
የሌለው
8/የተሰራ ከሆነ ልኬታ ይቀመጥ ………………………………………………..
9/ ግንባታው የተሰራበት ማቴሪያል ሀ/ በብሎኬት ለ/ በጭቃ ሐ/ በቆርቆሮ መ/ በሌላ
ከሆነ ይጠቀስ ……………….
10/ ግንባታው የውጭ ግድግዳው በአሽዋና ስሚንቶ ሀ/ ሽምብራ ግርፍ የተገረፈ ለ/ የተለሰነ
መ/ያልተለሰነ ሠ /ሀ እና ለ
11/ ግንባታው የውጭና የውስጥ ግድግዳ በተቦካ ጭቃ ሀ/ የተለሰነ ለ/ የተመረገ መ/በምንም
ጭቃ ያልተመረገ
12/ ግንባታው የውስጥ የግድግዳ ቀለም ሀ/ የተቀባ ለ/ ያልተቀባ ሐ/ በጂብሰም
የተሰራ
27
13/ግንባታው የውጭ ግድግዳ ቀለም ሀ/ የተቀባ ለ/ ያልተቀባ ሐ/ በኳርቲዝ የተሰራ
14/ግንባታው የወለል ስራ በስሚንቶና አሽዋ ማንኪያ ሊሾ ሀ/የተሰራ ለ/ ያልተሰራ
15/ ወለሉ በሌላ የግንባታ አቃ የተሰራ ከሆነ ይጠቀስ …………………………….
16/ለግንባታው ኮርኒስ ሀ/ የተሰራ ለ/ ያልተሰራ
17/የተሰራ ከሆነ ኮርኒሱ የተሰራበት የእቃው አይነት ይጠቀስ……………………
18/ ግንባታው / በር ሀ/ የተገጠመ ለ / ያልተገጠመ የተገጠመ ከሆነ የበሩ ብዛት
በቁጥር ………………………
19/ የበሩ አይነት ይጠቀስ ……………………………………….በካሬ………………………
20/የበሩ አይነት ይጠቀስ …………………………………….በካሬ……………………
21/መስታወት የተገጠመ ከሆነ ስፋቱ በካ/ሜ ይገለጽ ……………………….
22/ መስኮት ሀ/ የተገጠመ ለ / ያልተገጠመ የተገጠመ ከሆነ የመስኮቱ ብዛት ……
23/የመስኮቱ አይነት ይጠቀስ……………………………………………በካሬ……………
24/ የመስኮት አይነት ይጠቀስ ………………………….በካሬ………………………
25/መስታወት የተገጠመ ከሆነ ስፋቱ በካ/ሜ ይገለጽ ……………………….
26/ ግንባታው ዙሪያ የእግር መረማመጃና የውሀ መፋሰሻ ሀ/ የተሰራ / ለ/ ያልተሰራ ሐ/ የተሰራ
ከሆነ በምን ……………
27/ የኤሌክትሪክ መብራት የተሰራ ከሆነ በቁጥር ………… ሶኬት የተገጠመ ከሆነ በቁጥር ……
ማሳሰቢያ ፡- 1/ የፎቶ ግራፍ ማስረጃ መያዝ አለበት
2/እያንዳንዱ ግንባታ መረጃው መሞላት አለበት
3/ተጨማሪ ስለግንባታው ከተዘረዘረው ሌላ ማብራሪያ ካለ ይጠቀስ
28
5. የጤና መረጃ መሰብሰቢያ
29
ማደረግ
10 የተሰባሰበውን መረጃ መሰረት በማድረግ የማጣቃሊያ ሪፖርት ማዘጋጀት 09/04/2015 ዓ.ም
11 ከማጣቃሊያው ሪፖርት በመነሳት የአጭርና የረጀም ጊዜ መፍተሄ ማስቀመጥ 10/04/2015 ዓ.ም
12 የተጠቃለለውን ሪፖርት ለወረዳ አመራሩ ማቅረብ 10/04/2015 ዓ.ም
13 የተጠቃለለውን ሪፖርት ለዞን አመራሩ ማቅረብ 11/04/2015 ዓ.ም
ቁ ጥር ደብተር
እማ አባወ ወን ሴ ብር ሳ ብር ያለ የለለ
ዎራ ራ ድ ት ው ው
1 ሙሉ ለሙሉ ቤታቸው 12 26
30
ውሀ ልክ የታሰራ 884,210 33,600,000
የተለሰነ ጭቃ
የውስጥ ወለል ሊሾ
የተደረገ ከውስጥም
የተቀባ ሙሉ ቤት
ኮርኒስ ያለው
ሙሉ ቤት
ኮርኒስ ያለው
ማህበረሰብ
በአማካኝ የቤቶቹ ሁኔታ 121 51 70
112
ውሀ ልክ የታሰረ 1,100,000 133,100,000 8
በጭቃ የተለሰነ፣
ፕላን
ኳርቲዝ የተቀባ
ያላቸ
ከውጭም ከውስጥም ቀለም ው
የተቀባ
ሙሉ ቤት ኮርኒስ ያለው
ሊሾ የተሰራ የተሟላ ቤት
31