You are on page 1of 97

የትምህርቱ መመሪያ

የ Microsoft Digital Literacy የማስተማሪያ ተጨማሪ መርጃ መሣሪያ


በonline ለደኅንነት አስተማማኝ በሆነ
መንገድ እና በኃላፊነት ተሳትፎ ያድርጉ

Digital ትምህርት
በዚህ የትምህርት ጉዞ ላይ internet
በሚጠቀሙበት ጊዜ ሊያጋጥምዎት የሚችሉ
የደኅንነት ስጋቶች ምን እንዲሆኑ እንዲተዋወቁ
ይደረጋሉ። ስለ online ቅጥፈቶች እና እንዴት
ሊያስቀሯቸው እንደሚችሉ ይማራሉ። online
መረጃን ለማጋራት ምርጥ ስለሆኑ የአሠራር
ልማዶች በተጨማሪ ይማራሉ። በተጨማሪ፣
ሳይበር ዱለኝነት ምን እንደሆነ እንዲያውቁ
ይደርጋሉ።
የኮርስ ሞጁል አጭር ማጠቃለያ

▪ internet እና ድሩን በመጠቀም ወቅት ያሉ አንዳንድ አደጋዎች ምንድን ናቸው?


▪ የደኅንነት ስጋቶች እና online ቅጥፈቶች አንዳንድ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
▪ internet በሚጠቀሙበት ጊዜ ደኅንነትዎ እንደተጠበቀ ለመቆየት ምን እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ?
▪ የእርስዎን digital የእግር አሻራ እንዴት መቆጣጠር ይችላሉ?
internet ብዙ ዕድሎችን
ያመጣልናል። ከሌሎች ጋር
ማውራት፣ በቀጥታ online
ግዢዎችን መፈጸም እና የግል
ሥራዎችን ከአንድ ቦታ ላይ
ሆነን መሥራት እንችላለን።
ነገር ግን እነዚህ የ online
መስተጋብሮች ደኅንነታቸው
ሁልጊዜ የተጠበቀ አይደለም።
እርስዎ ሊያውቁት ስለሚገባ
የታወቀ የ online
የማጭበርበር ድርጊት
እንነጋገር።
አጠራጣሪ የሆኑ መልእክቶችን
በጥንቃቄ ይመልከቱ። እርስዎ
እንዲያምኗቸው አጭበርባሪዎች
መልእክቶቻቸው ኦፊሴል እና
የተለመዱ ዓይነት መልእክቶች
እንዲመስሉ ለማድረግ ይሞክራሉ።
አጠራጣሪ መልእክት ሲደርስዎት ቆም
ብለው ሁለት ጊዜ ያስቡ እና
በመልእክት ወይም በemail የግል
መረጃን ከማጋራት ይቆጠቡ። ይህ
የእርስዎን የቤት አድራሻ፣ የባንክ
መረጃ፣ ፓስዎርዶች እና ተጨማሪ
ነገሮችን ያካትታል። ላኪውን
የማያውቁት ወይም የማያምኑት
ከሆነ ሊንክ ላይ click አያድርጉ
ወይም ፋይል download አያድርጉ።
የ credit card መረጃ ከመስጠትዎ፣ ፓስዎርድ
ከማስገባትዎ ወይም ሌላ የግል መረጃ
ከመስጠትዎ በፊት፣ በሚታመን ለደኅንነት
አስተማማኝ በሆነ የድር ጣቢያ ላይ ያሉ
መሆንዎትን ያረጋግጡ። አብዛኛዎቹ ለደኅንነት
አስተማማኝ የሆኑ የድር ጣቢያዎች በ
browser የአድራሻ bar ውስጥ ከ URL
መጀመሪያ ላይ prefix https ይኖራቸዋል።
በተጨማሪም ትክክለኛው ድረ ገጽ ላይ
መሆንዎን ያረጋግጡ። አጭበርባሪዎች
አብዛኛውን ጊዜ ወደ ትክክለኛ የሚመስሉ ደረ
ገጾች ይመርዎታል እና የተሳሳቱ የድርጅቶችን
ስም ፊደላትን በመጠቀም ሊያታልሉ
ይሞክራሉ። www.microsoft.net ከ
Microsoft ኦፊሴላዊ የድር ጣቢይ ከሆነው
www.microsoft.com የተለየ ነው።
የእርስዎን የድር browser እና
operating system
እንደተዘመኑ ያቆዩዋቸው።
የቅርብ ጊዜ የ software ልቀቶች
በራስ ሰር በኮምፒውተርዎ ላይ
መጫናችውን ለማረጋገጥ
ራስሰር ዝማኔዎችን ማብራት
ይችላሉ። የእርስዎን መሣሪያ
software እንደተዘመነ ማቆየት
ማለት የእርስዎን ኮምፒውተር
ደኅንነት ለመጠበቅ
የሚያስችልዎትን የቅርብ ጊዜ
የደኅንነት ዝማኔዎችን ያገኛሉ
እንደ ማለት ነው።
በመሣሪያዎችዎ ላይ ትክክለኛነቱ
የተረጋገጠ አንታይ-ማልዌር ሶፍትዌር
ይጫኑ። ይህ የእርስዎን ኮምፒውተር
ከጎጂ software እና ጠላፊዎች
ለመጠበቅ የተዘጋጀ ልዩ software ነው።
በጠላፊዎች የሚጠመደው ቀጣዩ ዓሣ
አይሁኑ። Internet ን ሲጠቀሙ፣
ራስዎትን ከ online የማጭበርበር
ድርጊቶች ለመጠበቅ click ከማድረግዎ፣
download ከማድረግዎ ወይም
ከማጋራትዎ በፊት ማሰብ እንዳለብዎት
ያስታውሱ።
internet በአዳዲስ መንገዶች
ከሌሎች ሰዎች ጋር መልእክት
መለዋወጥ እንድንችል
ያደርገናል። ሆኖም ግን፣
online ከሌሎች ሰዎች ጋር
መልእክት መለዋወጥ ሁልጊዜ
ለደኅንነት አስተማማኝ
አይደለም። internet ላይ
ሲሆኑ ከማን ጋር እየተነጋገሩ
እንዳሉ ሁልጊዜ እርግጠኛ
መሆን አይችሉም ስለዚህ
ደኅንነትዎ እንደተጠበቀ
ለመቆየት ጥንቃቄ ማድረግ
ይኖርብዎታል።
የእርስዎን ደመነፍሳዊ ጥንቃቄ
አደራረግ ይጠቀሙ። የሆነ ሰው
ካስፈራዎት ወይም ምቾት
ከነሳዎት፣ ከግለሰቡ ጋር መልእክት
መለዋወጥን ያቁሙ እና ይህንን
ጉዳይ ለሚያምኑት የሆነ ሰው
ይንገሩት። አብዛኛዎቹ የድር
ጣቢያዎች እና ማኅበራዊ
የግንኙነት አውታሮች አጠራጣሪ
እንቅስቃሴን ሪፖርት ማድረግ
የሚችሉባቸው መሣሪያዎች
አሏቸው።
የሚያጋሩትን ነገር መጠን
ይገድቡ። Online ጥቃት
አድራሾች ብዙውን ጊዜ
በemails ወይም
በመልእክቶች የእርስዎን
የግል መረጃ እንዲያጋሯቸው
ለማድረግ ይሞክራሉ።
Online ላለ የማያውቁት
እንግዳ ሰው የግል መረጃን
ከማጋራት ይቆጠቡ።
የእርስዎን ርቀት ይጠብቁ። Online ላይ
ብቻ ካነጋገሩት ሰው ጋር በአካል
ከመገናኘትዎ በፊት ሁለቴ ያስቡበት።
Online ጥቃት ፈጻሚዎች ብዙውን ጊዜ
የሌሎችን ሥዕሎች ተጠቅመው የውሸት
ፕሮፋይሎችን በማቀናበር የሆነ ሌላ ሰው
እንደሆኑ ለማስመሰል ይሞክራሉ።
የሆነ የማያውቁት ሰው ጥሩ ጓደኛ
ለመምሰል እንኳ ቢሞክርም፣ ከማን ጋር
online እየተነጋገሩ እንዳሉ በእርግጠኝነት
ማወቅ አስቸጋሪ ነው። አንድ online
የሚያውቁት እንግዳ የሆነ ሰው በአካል
እንድትገናኙ ጥያቄ ሲያቀርብልዎት በአደገኛ
ሁኔታ ውስጥ ራሳችሁን ላለመክተት
ሁልጊዜ ለወላጅ ወይም ሌላ ለምታምኑት
ሰው ስለ ጉዳዩ ተናገሩ። አብዛኛዎቹ የ
online ጥቃት ፈጻሚዎች ወደ አደገኛ
ሁኔታ እናንተን ለማስገባት የሚያማልሉ
ብልጠት የተሞሉ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፣
ሆኖም እርስዎ ከእነርሱ የበለጥ ብልጥ
መሆን ይችላሉ።
Online ደኅንነትን ጠብቆ
ለመቆየት እና የእርስዎን
መረጃ የግልዎ እንደሆነ
እንዲቆይ ለማድረግ
የሚደረገው ጥንቃቄ
ትልቁ ክፍል የእርስዎ
accounts እና የእርስዎ
ኮምፒውተር ጠንካራ
ፓስዎርዶች መጠቀም
መቻላቸው ነው።
የፊደላት፣ የቁጥሮች እና
የምልክቶች ጥምረት ያለውን
ፓስዎርድ ይጠቀሙ። የዐቢይ
ሆሄ እና የንኡስ ሆሄ እንዲሁም
characters ጥምረት መጠቀም
እንዲሁም ቁጥሮችን ማከል
የእርስዎን ፓስዎርድ ጥንካሬ
ለማሻሻል ሊያግዝ ይችላል።
ፓስዎርድ ውስጥ የተለመዱ
ቃላትን ከመጠቀም ይቆጠቡ።
ይህ እንደ ፓስዎርድ ወይም የድር
ጣቢያ የመሳሰሉ እንዲሁም
የእርስዎ የልደት ቀን፣ የእርስዎ
ስም ወይም ትውልድ ከተማ
የመሳሰሉ የተለመዱ ቃላትን
ያካትታል። ጠላፊዎች እነዚህን
ሐረጎች በእርስዎ ፓስዎርድ ላይ
በቀላሉ ሊገምቷቸው ይችላሉ።

ለየት ያሉ የ characters እና
የቁጥሮች ጥምረት ጠንካራ የሆነ
ፓስዎርድ ይፈጥራል።
የተለያዩ ፓስዎርዶች
ለተለያዩ accounts
ይጠቀሙ። አንድ ሰው
የእርስዎን የ email
ፓስዎርድ መገመት ከቻለ፣
ለባንክ ሒሳብዎ ተመሳሳይ
ፓስዎርድ የሚጠቀሙ
ከሆነ የእርስዎ ደኅንነት እና
ግላዊነት አደጋ ውስጥ
ይገባል ማለት ነው።
በምትኩ ለእያንዳንዱ
እርስዎ ያልዎት የ online
account የተለያዩ
ፓስዎርዶች ይጠቀሙ።
የእርስዎ ፓስዎርድ ለእርስዎ ብቻ
የሚያገለግል ነው። ከጓደኞች እና
ከቤተሰብ ጋርም ቢሆን እንኳ
ከሌላ ሰው ጋር ካጋሩት፣ የሆነ ሌላ
ሰው ሊጠቀምበት መቻሉ ወይም
ደኅንነቱን በሚገባ ለመጠበቅ
ያለመቻሉ ዕድል ከፍተኛ ነው።
የእርስዎን ፓስዎርድ ለራስዎ ብቻ
ይያዙ። ወደ accounts ሲገቡ፣
በሚጨርሱበት ጊዜ ዘግተው
መውጣትዎን ያረጋግጡ
እንዲሁም በሕዝብ ኮምፒውተር
ላይ የእርስዎን በ account
መግቢያ መረጃ አያስቀምጡ።
online በምንሆንበት
ጊዜ፣ ስለ ነገሩ ብዙም
ሳናስብበት የእኛን ደኅንነት
አደጋ ውስጥ ሊከቱ
የሚችሉ በርካታ
ተግባራትን እናደርጋለን።
online ምን እንደሚያጋሩ
ሁለቴ ማሰብ እና ስለ
የእርስዎ ደኅንነት ማሰብ
አስፈላጊ ነው።
ድርን ከማሰስ ጀምሮ
በማኅበራዊ ግንኙነት
አውታሮች ላይ ዝማኔዎችን
ማጋራት ብሎም የ online
ግዢዎችን መፈጸም ድረስ
online ማድረግ
የምንችላቸው በርካታ ነገሮች
አሉ። ማናቸውም online
የሚያደርጉት ነገር በሙሉ
የእርስዎ የ online ታሪክ
አንድ አካል ወይም የእርስዎ
digital አሻራ እንደሚሆን
ሁልጊዜ ያስታውሱ።
52
የእርስዎ አሻራ ስለ እርስዎ ምን እንደሚናገር ይወቁ።
ሌሎች ሰዎች ስለ እርስዎ online የራሳቸውን ግምት
ለመስጠት የእርስዎን digital አሻራ ይጠቀማሉ። ይህ
ሥራ ለመቀጠር ሲያመለክቱ የሚያገኟቸውን ሥራ
ቀጣሪዎች ወይም ለአካዳሚያዊ ፕሮግራሞች
ሲያመለክቱ የሚያጋጥምዎትን መራጮች ያካትታል።

የእርስዎ digital አሻራ ስለ እርስዎ ምን እንደሚናገር


ማወቅ እና የእርስዎ መረጃ በምን ዓይነት መልኩ
ጥቅም ላይ እንደሚውል ማወቅ አስፈላጊ ነው።
የእርስዎ online ያለው brand ለማየት እርስዎ
ራስዎ መፈለግ ይችላሉ። በ Bing search engine
ውስጥ የእርስዎን ስም ይፈልጉ እና ምን ዓይነት
ውጤቶች እንደሚታዩ ይመልከቱ። እነዚህ ውጤቶች
እርስዎ የሚፈልጉትን ውጤት የማያሳዩ ከሆነ፣
online ምን እንደሚያጋሩ እና ምን ዓይነት መረጃ
ሌሎች እንዲያዩ እንደሚፈቅዱ ያስቡበት።
54
የእርስዎን የግላዊነት
ቅንብሮች ያስተዳድሩ።
የአብዛኛዎቹን የማኅበራዊ
ግንኙነት አውታሮች እና
እርስዎ የሚጠቀሙባቸው የ
online መተግበሪያዎች
የግላዊነት ቅንብሮችን
መለወጥ ይችላሉ። ይህ ማን
እርስዎ የሚያጋሩትን ማየት
እንደሚችል እና የሆነ ሰው
እርስዎን online ሲፈልግዎት
ምን ዓይነት መረጃን ማየት
እንደሚችል ለመቆጣጠር
እንዲችሉ ያግዞታል።
56
የእርስዎን ኩኪዎች ያስተዳድሩ። ኩኪዎች እርስዎ
ድሩን በሚያስሱበት ወቅት ለእርስዎ የድር browser
የሚሰጡ ማስታወሻዎች ናቸው።

እነዚህ ኩኪዎች መተግበሪያውን እርስዎ


በሚጠቀሙበት ጊዜ መተግበሪያዎቹ የሚፈልጉትን
መረጃ ዱካ እንዲከታተሉ ያስችላቸዋል። ይህ
መተግበሪያው ለእርስዎ በተሻለ ደረጃ እንዲሠራ
ሊያግዘው ይችላል። ነገር ግን ይህ መረጃ የእርስዎን
digital አሻራ በመቅረጽም ላይ አስተዋፅኦ ያደርጋል።
በተወሰኑ የድር ጣቢያዎች ላይ የኩኪዎችን ጠቀሜታ
ለመገደብ ወይም ለማገድ በእርስዎ browser
ውስጥ ያሉትን ቅንብሮች መጠቀም ይችላሉ።
58
ከማጋራትዎ በፊት ያስቡበት።
የሆነ ነገር አንዴ online ካጋሩ
በኋላ፣ መልሰው ሊወስዱት
አይችሉም። ከማጋራትዎ በፊት
በእርስዎ ለሕዝብ የሚታይ
digital አሻራ አንድ አካል ቢሆን
ምንም ችግር እንደሌለው
ያረጋግጡ። የ digital አሻራዎ
ዘላለም ሊቆይ ይችላል።
በእርስዎ digital አሻራ እና
እንዴት ጥቅም ላይ
እንደሚውል ደስተኛ
መሆንዎትን ለማረጋገጥ
እነዚህን ጠቃሚ ምክሮች ልብ
ብለው ይመልከቷቸው።
60
ጠቃሚ ምክሮች፦ ለደኅንነት አስተማማኝ
በሆነ መንገድ online መልእክት መለዋወጥ
1. ጠቃሚ ምክር አንድ፣ ደመነፍስዎ የሚነግርዎትን ያዳምጡ።
የሆነ ሰው ካስፈራዎት ወይም ምቾት ከነሳዎት፣ ከግለሰቡ ጋር
መልእክት መለዋወጥን ያቁሙ እና ይህንን ጉዳይ
ለሚያምኑት የሆነ ሰው ይንገሩት።
2. ጠቃሚ ምክር ሁለት፣ የሚያጋሩትን ነገር መጠን ይገድቡ።
Online ጥቃት አድራሾች ብዙውን ጊዜ በemails ወይም
በመልእክቶች የእርስዎን የግል መረጃ እንዲያጋሯቸው
ለማድረግ ይሞክራሉ።
3. ጠቃሚ ምክር ሦስት፣ የራስዎትን ርቀት ይጠብቁ። Online
ላይ ብቻ ካነጋገሩት ሰው ጋር በአካል ከመገናኘትዎ በፊት
ሁለቴ ያስቡበት።
ጠቃሚ ምክሮች፦ ጠንካራ የሆኑ
ፓስዎርዶች ይፍጠሩ
1. ጠቃሚ ምክር አንድ፣ የፊደላት፣ የቁጥሮች እና የምልክቶች
ጥምረት ያለውን ፓስዎርድ ይጠቀሙ።
2. ጠቃሚ ምክር ሁለት፣ ፓስዎርድ ውስጥ የተለመዱ ቃላትን
ከመጠቀም ይቆጠቡ።
3. ጠቃሚ ምክር ሦስት፣ የተለያዩ ፓስዎርዶች ለተለያዩ
accounts ይጠቀሙ።
4. ጠቃሚ ምክር አራት፣ የእርስዎ ፓስዎርድ ለእርስዎ ብቻ
ነው።
5. በተጨማሪ የግል ሥራዎት በሕዝብ ኮምፒውተሮች እና
የሕዝብ networks ላይ ከመሥራት ይቆጠቡ፣ ይህ
ለጠላፊዎች የእርስዎን መረጃ እንዲደርሱበት ቀላል
ያደርግላቸዋል።
ይሞክሩት፦ online መረጃን ለማጋራት
ምርጥ የሆኑ የአሠራር ልማዶች
ከዚህ video ምን ተማሩ?
የግል መረጃ online በሚያጋሩበት ጊዜ ልብ ሊሏቸው የሚገቡ
1-3 ነገሮችን ይጻፉ።
የእርስዎን digital አሻራ ለማስተዳደር
የሚጠቀሙ ምርጥ የአሠራር ልማዶች
internet የሚጠቀሙ ከሆነ፣ ስለ የእርስዎ digital አሻራ ማወቅ
ይኖርብዎታል። Dirt path ላይ የሆነ ሰውን ዱካ እንደሚያሳይ
የእግር ዱካ ወይም አሻራ ሁሉ የእርስዎ digital አሻራ እርስዎ
online የሚያደርጉት እንቅስቃሴን በሙሉ የሚያሳይ ታሪክ
ነው።
1. ጠቃሚ ምክር አንድ፣ አሻራዎ ስለ እርስዎ ምን
እንደሚናገር ይወቁ።
2. ጠቃሚ ምክር ሁለት፣ የእርስዎን የግላዊነት ቅንብሮች
ያስተዳድሩ።
3. ጠቃሚ ምክር ሦስት፣ የእርስዎን ኩኪዎች ያስተዳድሩ።
4. ጠቃሚ ምክር አራት፣ ከማጋራትዎ በፊት ያስቡ።
የ digital አሻራዎ ዘላለም ሊቆይ ይችላል። በእርስዎ digital
አሻራ እና እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ደስተኛ መሆንዎትን
ለማረጋገጥ እነዚህን ጠቃሚ ምክሮች ልብ ብለው
ይመልከቷቸው።
ለደኅንነት አስተማማኝ በሆነ ጣቢያ ላይ መሆንዎትን ለማረጋገጥ ከሚከተሉት ክፍለ አካላት መካከል የትኛውን በድረገጽ
URL ውስጥ ማየት ይኖርብዎታል?
a) http
b) ለደኅንነተ አስተማማኝ
c) https
d) ssh
ለደኅንነት አስተማማኝ በሆነ ጣቢያ ላይ መሆንዎትን ለማረጋገጥ ከሚከተሉት ክፍለ አካላት መካከል የትኛውን በድረገጽ
URL ውስጥ ማየት ይኖርብዎታል?
a) http
b) ለደኅንነተ አስተማማኝ
c) https - ትክክል! "https" ማለት ድረገጹ ለደኅንነት አስተማማኝ ነው።
d) ssh
የዕውቀት ፍተሻ ጥያቄ - የ online ደኅንነት እና ግላዊነት
ከእነዚህ ፓስዎርዶች መካከል የትኛው በጣም ጠንካራ ነው?
a) John@453
b) John500
c) JoHn300
d) 125893
የዕውቀት ፍተሻ ጥያቄ - የ online ደኅንነት እና ግላዊነት
ከእነዚህ ፓስዎርዶች መካከል የትኛው በጣም ጠንካራ ነው?
a) John@453 - ትክክል! ይህ ፓስዎርድ ዐቢይ ሆሄ፣ ንኡስ ሆሄ፣ ልዩ character እና ቁጥሮችን ይዟል።
b) John500
c) JoHn300
d) 125893
የእርስዎ digital አሻራ ማለት፦
a) በእርስዎ online accounts ላይ ያለው መረጃ መጠን።
b) online የሚገናኟቸው ሰዎች ብዛት።
c) online የሚያደርጉት እና የሚናገሩት ነገር ሁሉ ሪኮርድ።
d) የእርስዎ የ online ስም።
የእርስዎ digital አሻራ ማለት፦
a) በእርስዎ online accounts ላይ ያለው መረጃ መጠን።
b) online የሚገናኟቸው ሰዎች ብዛት።
c) online የሚያደርጉት እና የሚናገሩት ነገር ሁሉ ሪኮርድ። - ትክክል። የእርስዎ digital አሻራ የእርስዎን
online ያልዎትን ድርጊቶች ዱካ መከታተልን ቀላል ያደርገዋል።
d) የእርስዎ የ online ስም።
የኮርስ ሞጁል አጭር ማጠቃለያ

▪ online የሚያገኙትን መረጃ ለመጠቀም ሲፈልጉ ምን ማድረግ አለብዎት?


▪ የሳይበር ዱለኝነትን ለመከላከል ወይም ለማስቆም ምን ማድረግ ይችላሉ?
ምንም እንኳ በ digital
ዓለም ውስጥ መረጃን
መድረስ ቀላል ቢሆንም፣
online የሚያገኙትን
መረጃ ለመጠቀም
ሲፈልጉ ማክበር ያሉብዎት
አንዳንድ ደንቦች አሉ።
የሳይበር ዱለኝነት በ
internet የሚያጋጥም
የዱለኝነት ወይም
የጉልበተኝነት ዓይነት
ነው። ስለ ሌሎች ሰዎች
ሥርዓት የጎደላቸውን
መልእክቶች መላክ ወይም
አሉታዊ አሉባልታን
ማሰራጨት ቀላል ሊሆን
ይችላል ሆኖም ግን ይህ
ዒላማ ለተደረገው ግለሰብ
አደገኛ ሊሆን ይችላል።
online የተገኘን መረጃን ለመጠቀም
ምርጥ የሆኑ የአሠራር ልማዶች
▪ በእርስዎ ሥራ ላይ የሆነ ሌላ ሰውን ይዘት ለመጠቀም
ከፈለጉ፣ ለሥራው ተገቢውን ዕውቅና ለመስጠት የግለሰቡን
ስም ዋቢ መጥቀስዎትን ያረጋግጡ።
▪ በሚሸጡት ምርት ላይ የሌላ ሰውን ሥራ የሚጠቀሙ ከሆነ፣
ከደራሲው በመጀመሪያ ፈቃድ ማግኘት አለብዎት።
▪ internet ሲጠቀሙ እና መረጃን online ሲያገኙ፣
በፍትሐዊነት እና በኃላፊነት እንደሚጠቀሙበት ያረጋግጡ።
digital ሲቪሊቲ online
ለማበረታታት የሚያስችሉ
ምርጥ የአሠራር ልማዶች
▪ ወርቃማውን ደንብ በማክበር ይኑሩ። ልክ እርስዎ በአካል ከሰው
ሲገናኙ እንደሚያደርጉት ሌሎችን ያስተናግዱ።
▪ አሉታዊ መልእክቶችን ከመላክ እና ሌላ ሰው ላይ ጉዳት ሊያደርስ
በሚችል እንቅስቃሴ ላይ ከመሳተፍ ይቆጠቡ።
▪ ልዩነቶችን ያክብሩ። ሁላችንም በተለያዩ መንገዶች የተለያየን ነን።
▪ መልስ ከመስጠትዎ በፊት ላፍታ ቆም ይበሉ። ምን መዘዞች
ሊኖሩት እንደሚችሉ ሁልጊዜ ላፍታ ቆም ብለው ያስቡ።
▪ Online ከማጋራትዎ በፊት ሁለቴ ያስቡ። ለሌሎች እና ለራስዎ
መብት መከበር ይቁሙ።
▪ Online ጨካኝ ወይም አደገኛ የሆነ እንቅስቃሴን ሲመለከቱ፣
ጉዳት እየደረሰባቸው ላሉ እገዛ ለመስጠት ይሞክሩ እንዲሁም
አደጋውን ለሌላ ለሚያምኑት ሰው ይንገሩት።
▪ የራስዎን ግዴታ ይወጡ፣ online ላይ ኃላፊነት የሚሰማው
digital ዜጋ ይሁኑ።
ከሚከተሉት ድርጊቶች መካከል የትኛው የቅጂ መብቶችን አይጥስም?
a) ያለ ፈቃዱ የሆነ ሌላ ሰውን ሥዕሎች እርስዎ በሚያሳትሙት መጽሐፍ ላይ መጠቀም።
b) ከሆነ ሰው መጽሐፍ ላይ አንድን አንቀጽ ዋቢ መጥቀስ እና የግለሰቡን ስም መጥቀስ።
c) የሌላ ሰውን video በስምዎት መሸጥ።
d) ያለ ፈቃድ የሆነ ሰውን መጽሐፍ መሸጥ
ከሚከተሉት ድርጊቶች መካከል የትኛው የቅጂ መብቶችን አይጥስም?
a) ያለ ፈቃዱ የሆነ ሌላ ሰውን ሥዕሎች እርስዎ በሚያሳትሙት መጽሐፍ ላይ መጠቀም።
b) ከሆነ ሰው መጽሐፍ ላይ አንድን አንቀጽ ዋቢ መጥቀስ እና የግለሰቡን ስም መጥቀስ - ትክክል! ባለቤቱን
ሲጠቅሱ የቅጂ መብቶችን ያከብራሉ።
c) የሌላ ሰውን video በስምዎት መሸጥ።
d) ያለ ፈቃድ የሆነ ሰውን መጽሐፍ መሸጥ
የሳይበር ዱለኝነት በዚህ መንገድ ሊከናወን ይችላል፦
a) በማኅበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች ላይ ብቻ።
b) በemails ብቻ።
c) በኤስኤምኤስ ብቻ።
d) በማኅበራዊ ግንኙነት አውታረ መረቦች እና ኤስኤምኤስ እንዲሁም በemails በኩል።
የሳይበር ዱለኝነት በዚህ መንገድ ሊከናወን ይችላል፦
a) በማኅበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች ላይ ብቻ።
b) በemails ብቻ።
c) በኤስኤምኤስ ብቻ።
d) በማኅበራዊ ግንኙነት አውታረ መረቦች እና ኤስኤምኤስ እንዲሁም በemails በኩል። - ትክክል! የሳይበር
ዱለኝነት በማናቸውም የ online ተግባቦት መንገዶች ላይ ሊከናወን ይችላል።

You might also like