Professional Documents
Culture Documents
WPS Office
WPS Office
አያያዥ
አያያዥ ማለት ቃልን ከቃል፣ሐረግን ከሐረግ፣ዐ.ነገርን ከዐ.ነገር የሚያያይዝ ማለት ነዉ።አያያዥ ቃላት
ከአገልግሎታቸዉ አንፃር ሲታዩ በተለያዩ ክፍሎች ልንመድባቸዉ እንችላለን።
1.አማራጭ ወይም አጠራጣሪ አያያዥ፦ይህ የአያያዥ አይነት የቸፈለገዉ እንድመረጥ ወይም እርግጠኛ
ያልሆንበት ነገር በምንናገርበት ጊዜ ለማያያዝ የምንጠቀምበት አያያዥ ነዉ።
ምሳሌ፦ጧት ወይም ማታ እመጣለሁ።
ዛሬ ይሁን ነገ እንገናኛለን ብለናል።
ሻይ ወይስ ወተት ይምጣልሽ?
2.አፍራሽ ወይም ተቃራኒ አያያዥ፦ይህ የአያያዥ አይነት በመጀመሪያ የተነገረዉን ሀሳብ ለማፍረስ ወይም
ለመቃረን የሚቀርብ አያያዥ ነዉ።
ለምሳሌ፦እናቴን እወዳታለሁ ይሁን እንጂ አባቴ ይበልጥብኛል።
ፈተናውን ተፈትኛለሁ ነገር ግን የማልፍ አይመስለኝም።
ብዙ ብር አለዉ ግን የተቸገረ አይረዳም።
3.የምክንያትና ዉጤት አያያዥ፦ይህ የአያያዥ አይነት መጀመሪያ ለቀረበው ምክንያት ዉጤት በማስከተል
ወይም ለዉጤቱ ምክንያት በማቅረብ የሚያገለግል አያያዥ ነዉ።
ለምሳሌ፦ትምህርቱን አያጠናም ስለዚህ ጥሩ ዉጤት አያመጣም።
በአካባቢው መጥፎ ሽታ አለ ምክንያቱም ቆሻሻ ይጣላል።
4.ሐሳብ ሠጭ አያያዥ፦ይህ የአያያዥ አይነት የተሰነዘረውን ሃሳብ ተንተርሶ ሃሳብ ለማቅረብ የሚያስችል
የአያያዥ አይነት ነዉ።
ለምሳሌ፦እቃው ተጓጉዞ አልቋል ታድያ ለምን አናስተካክለዉም?
እራታችሁን አቅርቤያለሁ እንግዲህ አርፋችሁ ብሉ።