You are on page 1of 37

የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/የቴ/ክ/ሙ/ሥ ቢሮ

በሀዉስ ሆለድ ሙያ
የአጫጭር ጊዜ ሥልጠና ማሰልጠኛ የተዘጋጀ
ማንዋል

2008 ዓ.ም
ሀዋሳ

ማዉጫ ገጽ

1 መግቢያ ………………………………………………………………………3
1
2 የብቃት አሀድ ሰንጠረዥ……………………………………………………………………………………4

3. የማሰልጠኛ ግብአት…………………………………………………………………………………………...5
4. የብቃት አሀድ የቤት ጸዳት እና አያያዝ አገልግሎት
4.1 የቤት አያያዝ በለሙያ ሊኖረዉ የሚገባ ባሀሪ እና የስራ ሀላፊነት…………11
4.2 የመኝታ እና መኝታ ክፍል አዘገጃጀት…………………………………………………….13
4.3 የአጸዳድ ቅደም ተከተል ……………………………………………………………………..14
5 የብቃት አሀድ ሁለት የልብስ እጥበት አገልግሎት
5.1 የሚታጠቡ ልብሶችና ጨርቆች……………………………………………………………….17
5.2 የጽዳት ኬሚካሎች……………………………………………………………………………….18
5.3 የልብስ ንጽህና መጠበቂያ ዘዴዎች…………………………………………………......22
5.4 ልብስ ከመታጠቡ በፊት የሚደረግ ቅድመ ዝግጅት………………………..……27
5.5 የልብስ ማጠብ መመሪያ ምልክቶች ………………………………………………….. 31
5.6 የታጠቡ ልብሶችን መተኮስ ፣ማጠፍእና ማሸግ ተግባራት ………….36
6.የብቃት አሀድ ሶስት የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት

6.1 የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት ባለሙያ ባህሪያት ……………………………..……. 37

6.2 የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት አሰጣጥ ቅደም ተከተል……………….. ..38


7 የሙያ ስነ ምግባር………………………………………………………………………………………………………40

ማጠቃለያ

መግቢያ
2
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/የቴ/ክ/ሙ/ሥ ቢሮ በሀዉስ ሆልዲንግ ሰርቪስ ተደራጅተዉ የራሳቸዉን ስራ
ፈጥረዉ ወደ ስራ አለም ለሚገቡ ዜጎች የብቃት አሀድን መሰረት ያደረገ የአጭር ጊዜ ስልጠና መስጫ
ማኑዋል ነዉ፤፤
ይህ ማኑዋል የተዘጋጀዉ ሶስት የተለያዩ የብቃት አሀዶችን ወይም የተለያዩ የሙያ
ዘርፎችን በዉሰጡ የያዘ ሲሆን እነሱም የቤት አጸዳድ እና አያዝዝን ፣ የልብስ እጥበት
እና የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት ነዉ

በነዚህ ሙያዎች መስራት የሚፈልግ ማንኛዉም ሰዉ የሙያዉ በለቤት ከመሆን ባሸገር


የሚሰራዉ ስራ

ሳይንሳዊ መሰረት ፣አለም አቀፍ የዘት የለዉ እና ተወዳዳሪ ሚያደርግ ሲሆን ከዚህ
በተጨማሪ የሙያ ስነ ምገባርን የስራ ፍቅረን እና ጠንካራ የስራ መንፈስን እንዲያዳብሩ
ሆኖ ተዘጋጅቷል

የብቃት አሀዶች

የብቃት አሀድ ስም የብቃት አሀድ ኮድ የተሰጠ ሰአት ምርመራ


Nominal

3
Unit of competence UC code duration

Clean House LSA DOM 01 0812


55hr

Provide Food and


LSA DOM 02 0812 35hr
Beverage Service

Wash and Iron Clothes, 30hr


LSA DOM 03 0812
Linen and Fabric

Total hours = 160hr

4
የብቃት አሀድ 1-(አንድ) clean house

የቤት ጸዳት እና አያያዝ አገልግሎት

ኮድ LSA DOM O10816

የቤት አያያዝ፡- ማለት የመኖርያ አካባቢ፣ የመስሪያ አካባቢዎችንእና የመሳሰሉት ቦታዎች


ንፁህ ምቹና ማራኪ የሚስቡ ማድረግ ሲሆን በተጨማሪም በውስጡ የሚገኙ ዕቃዎችን
ንፅህና በአግባብ መጠበቅ ነው፡፡

የቤት አያያዝ በለሙያ ሊኖረው የሚገባ ባህሪ

 ሚዛናዊ እና አስተዋይ
 ተግባቢ
 ትሁት
 ታጋሽ
 ቅን በመሆን ተገልጋዮቹን ማርካትና ማስደሰት የሚችል መሆን ይገባዋል፡፡

የቤት አያያዝ ሰራተኛ ኃላፊነትን ተግባር

 ንፁህና ለስራው ምቹ የሆነ የስራ ልብስ መልበስ


 ከፍታ የሌለውና የማያንሸራትት ጫማ መጫማት
 ከሌሎች አብረዉት ከሚሰሩ ጋር ተግባብቶ መሥራት
 የመገልገያ ክፍሎችን በማፅዳት ዝግጁ ማድረግ
 የእንግዳውን መኝታ በተገቢው ሁኔታ ማፅዳትን
 አላቂ የሆኑ የእንግዳውን መጠቀሚያ ዕቃዎች ማሟላት
 የጎደለ ወይም የተሰበረ ዕቃ ካለ ለቅርብ አላቃ ማሳወቅ
 የተበላሹ ዕቃዎች ካሉ ለጥገና ክፍል በማሳወቅ ማሰራት

5
 ወንበር ፤ጠረጴዛ የመሳሰሉትን በተገቢ ሁኔታ ማጽደት
 የኤሌትሪክ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በተገቢ ሁኔታ ማጽዳት
 የመታጠቢያና የመጸዳጃ ቤት በተገቢ ሁኔታ ማጽዳት
 መንጣፎችን፤ሶፋዎችን፤የመይወርዱ መጋረጃዎችን እና ከእስፖንጅ
የተሰሩ ወንበሮች አና በረጩማዎችን በማጽጀ ማሽን ማጽዳት
የተጠቀሙባቸውን የማፅጃ መሳሪያዎች ማጠብ መወልወልና አድርቆ በተገቢው ቦታ
 የተጠቀሙባቸውን ጥንተ ንጥር (Cleaning agents and Chemicals)
ለፅዳት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች በጋራ ላይ ማዘጋጀት
ጋሪ (Trolley) ማለትም የክፍል ዕቃዎችን ሊይዝ የሚችል ተንቀሳቃሽ መሳሪያ
ነው፡፡ጋሪው ሊይዛቸው ሚችለው የፅዳት ዕቃዎችን የመኝታ ክፍል ዕቃዎችን
ነው፡፡
 የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦርሳ (Refuse bag)
 ጥንት ንጥር ( Cleaning agent and detergent)
 አሚኒቲ (Amenity)
 ሳሙያ
 ሻምፖ
 ሶፍት ወዘተ
 ንፁህና ለአልጋ ማዘጋጃ የሚያገለግሉ ዕቃዎች
 አንሶላ
 ትራስ ጨርቅ
 የተለያዩ ፎጣዎች፣ የእጅ ፣ የፊት፣ የገላ
 የተለያዩ መጠን ያላቸው
 ብናኝ የሌላቸው ጨርቆች
 ስፖንጅ

የ መኝታ እና የመኝታክፍል አዘገጃጀት


6
ለፅዳት ወደ እንግዳው ክፍል ለመግባት በጥንቃቄ መታየት ያለባቸው ነገሮች

 በሩ ላይ ምልክት መኖሩን ማረጋገጥ


ለምሳሌ አትረብሹ (Do not disturb)
 ወደ ክፍሉ ለመግባት በሚቻልበት አጋጣሚ በሩን “3” ጊዜ ማንኳኳትና ራስን
ማስተዋወቅ ይሆናል
ለምሳሌ፡- የቤት አያያዝ አባል እንደሆኑ በመግለፅ ማንኳኳት

የአልጋ አነጣጠፍ

 በቅድሚያ አልጋ ልብስ፣ብርድ ፣ልብስ፣ አንሶላና ትራስ ጨርቆችን ተራ በተራ


እያራገፉ ማንሳት (Strip the bed)
 ፍራሹን ማገላበጥ ወይም ማዟዟር ( ካስፈለገ)
 በፍራሹ ላይ የፍራሽ መከላከያ (Mattress protector) ማንጠፍ
 የመጀመሪያዉ አንሶላ ፈራሽ መጠቅለል ወይም መሸፈን አለበት
 አንሶላውን በመዘርጋት በ 4 ቱም ማዕዘን በ 900 ከራስጌም በሚያምር መልኩ
ማስገባት
 ሁለተኛዉ አንሶላ ገልብጠን ወደ ትራስጌው በማስረዘም ማንጠፍ
 ብርድልብሱን ከትራስጌው “አራት እንች ” ወረድ ብለን ማንጠፍ (እስከ አልጋ
ኮሜዲኖ ድረስ ማንጠፍ)
 የላኛውን አንሶላ ብርድ ልብስ ላይ ማንጠፍና ዙሪያውን ወደ ውስጥ ማስገባት
በግርጌው በኩል የሚገኙትን ሁለት ማዕዘኞች ወደ ውስጥ በ 900 ወይም በማዕዘን
ማንጠፍ
 ትራሶችን ማስቀመጥ

የመኝታ ክፍል አፀዳድ በሆቴል

7
 የእንግዳ ክፍል ዝግጅት የሚካሄደው በሆቴል ውስጥ ከሆነ የመኝታ
ክፍሉ የሚዘጋጅው በቤት አያያዝ ዲፖርትመንት ነው

የየቤት አፀዳድ ቅድመ ተከተል

 የክፍል ዕቃዎችንና የፅዳት እቃዎችን በሚይዝ ጋሪ (Trolley) ላይ


የሚያስፈልጉትን መሙላት (Stock Trolley)
 የሚሠራበት ክፍል አጠገብ እንግዳን በማያደናቅፍ መልኩ ጥግ ላይ ማቆም
 መኝታ ክፍል ለማፅዳት ከመግባታችን በፊት በሩ ላይ የአትረብሹን ምልክጽ
ከሌለ እንግዳ ቢኖርም ባይኖርም ማንኳኳት
 መብራቶች ከበሩ ማጥፋትና መጋረጃዎችን መግለጥና አየር እንዲገባ መስኮት
መክፈት (Ventilate the room)
 የመፀዳጃ ሳህን ውስጥ ውሃ መልቀቅ (Flush the toilet)
 ከመኝታ ቤት እና ከመታጠቢያ ቤት የተጠቀሙበትን አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅና
ፎጣ የመሳሰሉትን ነገሮች አንድ በአንድ በማራገፍ የእንግዳው ዕቃ አብሮ
እንዳይወጣ ተጠንቅቆ ማውጣትና በተዘጋጀው ጋሪ ( Trolley) ላይ ማደረግ
 መኝታ ቤት እና መታጠቢያ ቤት ያሉትን ቆሻሽዎች ማውጣት
 እንግዶች የተጠቀሙባቸውን ትሪዎች ወይም ሌሎች ዕቃዎች ካሉ ለክፍል
አገልግሎት (Room Service) በመደወል ማስወገድ ወይም ማስቀመጫ
ከተዘጋጀለት አውጥቶ ማስቀመጥ
 አልጋውን በተገቢው መንገድ ካነጠፍን በኋላ የእንግዳውን ልብስ አጣጥፈን
መቀመጥ ያለባቸውን ማስቀመጥን መሰቀል ያለበትን መስቀል
 የእንግዳው ዕቃ በተገቢው ቦታ ማስቀመጥ
 በክፍሉ ውስጥ የሚገኙትን የማንበቢያና የማረፊያ ክፍሎች መጥረግን ማፅዳት
 አቧራ ማንሳት ከበር ከጠረጴዛ ከቁም ሳጥንና ከዕቃ መስቀያ ከመሳሰሉት

8
 መታጠቢያ ቤቱን በተገቢው መንገድ ማፅዳት እና የጎደሉ የእንግዳ መጠቀሚያ
ዕቃዎችን ማሟላት፡-ለምሳሌ ሶፍት ፣ሳሙና የመሳሰሉት
 በረንዳና ደረጃዎች ማፅዳት
 መስኮቶቹን መዝጋትን መጋረጃውን በትክክል መጋረድ
 ኤርፍሬሽነር መርጨት
 በመጨረሻም ክፍሉን በጸገባ መንገድ ማዘጋጀታችንን ካረጋገጥን በኋላ ክፍሉን
መቃኘትን ዘግቶ መውጣ
የእንግዳ መኝታ ክፍል የሚገቡ ዕቃዎች
 የውሃ ብርጭቆ
 አሸትሬ
 የስልክ ማውጫ
 የአትረብሹኝ ካርድ
 የላውንደሪ ቦርሳ
 የልብስ መስቀያ
 የቁርስ መጠየቂያ የአስተያየት መፃፊያ ወረቀትእና እስክሪፕቶ

መታጠቢያ ቤት የሚገቡ እቃዎች

 ሳሙና
 ሻምፖ

9
 ሻወር ኬፕ
 የገላ ፎጣ
 የፊት ፎጣ
 የገላ መታሻ
 ሶፍት
 የመጉጥመጫ ብርጭቆ
 የቆሻሻ መጣያ
 ምንጣፍ (ትንሽ ለእግር መቆሚያ (Bata mat

የብቃት አሀድ 2 (ሁለት)

የልብስ እጥበት አገልግሎት

ኮድ LSA DOM 030816

Introduction
10
Laundry-(ላውንደሪ) ማለት የሚለሱ ልብሶችን እና ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ
ጨርቆችን በውሃና ሳሙና ማፅዳትየልብስ እጥበት አገልግሎት ማለት ማንኛዉም የቆሸሹ
የሚለበሱ የስራ ልብሶች፤የመኝታ ልብሶች እና ለተለያየ አገልግሎት የሚዉሉ ጨርቆችን
የእንግዳም ሆነ የድርጅቱን ሊታጠቡ የሚችሉ የልብስ አይነቶችን የእጥበት አገልግሎት
መስጠት ነው፡፡

Laundry service /የለውንደሪ አገልግሎት

የሚለበሱ ልብሶችና የማይለበሱ ጨርቆችን በውሃና በሳሙና በእጅ ወይም በማሽን አፅድቶ

አድርቆ ከዛም ተኩሶና አጥፎ ማቅረብ ማለት ነው፡፡

የሚለበሱ ልብሶች

የህፃናት የቀንና የሌልት ልብሶች

የሴቶች- የሥራ ልብሶች፣የበአል ልብሶች፣የባህል ልብሶች

የወንዶች-የሥራ ልብሶች፣የበአል ልብሶች፣የባህል ልብሶች የውስጥ ልብሶች

- የማይለበሱ ልብሶች /Linen/ -- አልጋልብስ (/ኮንፎርት)


- የመኝታ ልብሶች - ብርድልብስ
- አንሶላ

 የመታጠቢያ ቤት ፎጣዎች
- ፎጣ-የገላ ፎጣ- bath towel
- የፊት ፎጣ- face towel
- የእጅ ፎጣ- hand towel

የእግር መርገጫ - bath mat

11
የእግር መርገጫ- foot mat

የሳሎን- Living room ማቴሪያልስ - የሶፋ ጌጦች ከጨርቅ የተሰሩ

- መጋረጃዎች ጨርቆች

- የኩሽን ኬዞች- ኩሽን ኬዝ


- የሶፋ ትራስ ልብስ

Dining Room/የመመገቢያ ክፍል ጨርቆች

- ናብኪን
- የጠረጴዛ ልብስ
- የጠረጴዛ ቀሚሶች
- የወንበር ቀሚሶች

የፅዳት ኮሚካሎች

- የፅዳት ኬሚካል ለፅዳት ዋንኛውና ተቀዳሚ መሪ ተዋናይ ነው /Cleaning agent/


- ፅዳት የሚፋጠነውና የሚሳካው የፅዳት ኬሚካሎችን በመጠቀማችን ብቻ ነው፡፡
ያለፅዳት ኬሚካል እጥበት የሚባል የለም አይኖርም በውሃ ብቻ ፅዳትን ማከናወን
አይቻልም ማፅጃ ከሚካሎች ከሌሉ በውሃ ብቻ ጽዳት የለም

የፅዳት ኬሚካሎችና የሚሰጡት አገልግሎት

1. መምቻ ሳሙና- ደረቅ ሳሙና- Bar sop


2. ፈሳሽ ሳሙና- Liquid soap
3. በረኪና/ማንጫ - ብለች/white sprit
4. ሶፍትነር- fabric softener/ማለቅለቅያ/
5. እስቴን/Stain remover የመነቸከ እና ምልክቶች ከልብስ ጨርቅ ለላይ ማስወገጃ
/ማስለቀቂያ
6. Color remover- ከልብስ/ከጨርቅ ላይ ቀለም ማስለቀቂያ

12
መምቻ ሳሙና

ይህ የልብስ ፅዳት መጠበቂያ ኬሚካል በእጅ ለሚታጠብ እጥበት/ፅዳት ብቻ የሚሆነው


ማለትም በማሽን ለሚታጠብ ልብስ ይህንን ሳሙና መጠቀም አይቻልም በተጨማሪ
ደረቅ/መምቻ ሳሙና አረፋማ እና ሲነኩት ለስላሳ መሆን አለበት Eg B-29, Popular…

2. ፈሳሽ ሳሙና- በገበያ ላይ የሚገኘው በተለያየ ስም እና የንግድ ምልክት ሲሆን


የሚመረጠው ለአፍንጫ የሚጣፍጥ እና ጥሩ ሽታ ያለውም ወፍራም ፈሳሽ የሆነ የፈሳሽ
ሳሙና ተመራጭ ነው ይህ በዋናት ለማሽን እጥበት ሲሆን ለእጅ እጥበትም ይሆናል፡፡

3. ዱቄት ሳሙና

በገበያ ላይ የሚገኘው በተለያየ አይነት የንግደ ምልክት ሲሆን ጥሩ ሽታ ያለውና አረፋማ


የሆነው ለልብስ ፅዳትና እጥበት በጣም ተመራጭ ነው

Eg. Omo, Bright

4. በረኪና ( BLEACH)

ይህ ኬሚካል በቀጥታ ለማጠቢያ የሚያገለግል ሳይሆን ዋናው ስራው ነጭ የሆኑ ልብሶችን እና


ጨርቆችን የበለጠ ማንጣት ነው ወይም ነጭነታቸውን ሳይበልዝ ሳይቀየር እንዲኖር እና
አገልግሎታቸውን እስከሚጨርሱ ንጣታቸው አብሮአቸው እንዲቆይ የሚያደርግ ነው፡፡

የበረኪና አጠቃቀም

በረኪና ቀጥታ ልብስ ላይ አይደረገም/አይጨመርም

13
አጠቃቀሙ 1 ሊትር ውሃ ውስጥ አንድ የቡና ስኒ በረኪና ግማሽ ስኒ ፈሻ ወይም የዱቄት ሳሙና
ጨምሮ ወዲያው የሚፈለገውን ነጭ ልብስ /ጨርቅ 15-20 ደቂቃ ብቻ መዘፍዘፍ /ማቆየት/

ተጠንቀቁ ቀለም ያለው ልብስ ማለት ነጭ ያልሆን ልብስ/ጨርቅ በሙሉ

በረኪና መጠቀም አይቻልም ምክንያቱም በረኪና ቀለም ያስለቅቃል ምሳሌ-ጥቁር ጨርቅ


በረኪና ከነከው ቢጫ ይሆናል.

Fabric softness- ፋብሪክ ሶፍትነር የልብስ/ጨርቅ/ማለቅለቂያ ነው

አገልግሎቱ/ጥቅሙ

ፋብሪክ ሶፍትነር ሽታው የሚጣፍጥ የልብስ ኬሚካል ነው በዋናነት የሚጠቀመው


ለልብስ/ጨርቅ ማጠቢያ ወይም ማፅጃ ሳይሆን ታጥቦ የበቃው የመጨረሻውን የእጥበት ደረጃ
የደረሰ ለማስጣት የተዘጋጀ ልብስ/የተለቀለቀ ማለት ነው በሶፍትነር ለማለቅለቅ ነው
ልብስ/ጨርቅ/በሶፍትነር ከተለቀለቀ በኋላ የሚገኘው ጥቅም እንደሚከተለው

የፋብሪክ ሶፍትነር fabric softener ዝርዝረ ጥቅም

1. ልብሶች/ጨርቆች ጥሩ ሽታ ወይም ጠረን እንዲኖር ያደርጋል


2. ውሃ ሲነካቸው የሚኮማተሩ/የሚሰበሰቡ ልብሶችን/ጨርቆችን ይዘርጋጋል
3. ልብስ/ጨርቅ ውስጥ ያለ ኤለክትሪክ/በማታ ብልጭታ በቀን ድምጽ
የሚያሰማውን/ሁኔታ ከልብስ/ጨርቅ ላይ ያጠፋል፡

Stain Remover- እስቴን ሪሙቨር

- እስቴን ማለት- ልብስ/ጨርቅ ላይ የሚገኝ ምልክት/ባዕድ ነገር በከለር የማይመሳሰል ለአይን


የማይወደድ ምልክት ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ፡-

14
ቡና የተንጠባጠበት ልብስ/ጨርቅ
ሻይ » » »
ወተት » » »
ጥላሸት » » »

ወጥ/አልጫ/ቀይ ወዘተ ሲሆኑ

እነዚህ ምልክቶች ልብስ ላይ ከተገኙ ከመታጠቡ በፊት Stain remover ማለቅለቅ ይቻላል

Color remover- ከለር ሪሙቨር


ይህም እንደ እስቴን ሪሙቨር ቀለም እና የተለያየ ከለር ልብሶች/ጨርቆች ላይ ሲገኝ ማስወገጃ
ነው

- የእስክሪፕቶ ቀለም
- የቤት ቀለም

የልብስ ንፅህና መጠበቂያ ዘዴዎች Methods of Laundring

1. የእጅ እጥበት - Hand washing


2. የማሽን እጥበት - machine washing
3. ደረቅ እጥበት - dry clearing

Hand washing - በእጅ የልብስ/ጨርቅ እጥበት በአራት ሳፋዎች (basin) በማድረግ ሁሉንም
የፅዳት ኬሚካሎች እንደ አስፈላጊነታቸው በመጠቀም ልብሶች/የማጠብ ዘዴ ነው

የሚያስፈልጉ እቃዎች

- 4 ሳፋዎች/ basin/

15
- መዘፍዘፊያ
- ማጠቢያ
- ማለቅለቂያ (አረፋ አለው)
- ደግሞ ማለቅለቂያ (አረፋ የለውም)
- በዚህ እጥበት ሁሉንም አይነት የፅዳት ኬሚካል እና እንደ አስፈላጊነቱ መምቻ ሳሙና
መጠቀም ይቻላል፡፡

Machin washing- የማሽን እጥበት

ይህ- በማጠቢያ ማሽን ልብሶችን/ጨርቆችን ማጠብ ሲሆን ከመምቻ ወይም ከደረቅ


ሳሙና በስተቀር ሌሎች የጽዳት ኬሚካሎች እንደአስፈላጊነታቸው በመጠቀም በማሽን
የማጠብ ሥራ ነው

- ደረቅ እጥበት/ፅዳት Dry cleaning

ይህ የልብሶች/ጨርቆችን የማፅዳት ሥራ ውሃ እና ማንኛውንም የልብስ ፅዳት መጠበቂያ


ኬሚካል መጠቀም አይቻልም

በደረቅ እጥበት ጊዜ

- ልብሶች/ጨርቆች የሚጸዱት በደረቅ ኬሚካል ብቻ ነው- የማፅጃው ማሽን ንፁህ ውሃ


ተቀብሎ የቆሸሸ ውሃ የሚያስወጣ ሳሆን በደረቅ ኬሚካል ብቻ ነው የሚያጸዳው በዚህ
የሚፀዱ ልብሶች፡
- ሱፍ ልብሶች
- ፀጉር ያላቸው ልብሶች
- ጌጣጌጥ የበዛባቸው ልብሶች
- ብርድልብሶች ናቸው የሚጠቀመው ኬሚካል የሚተን ኬሚካል ነው ልብስ
አያረጥብም

16
የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች አይነት

1. Mannual- በእጅ የሚታገዝ እጥበት


2. Automatic- ምንም እገዛ የማያስፈልግ
1. ማኑዋል/household/ የቤት፣የቤተሰብ የንግድ ያልሆነ

ይህ ማሽን 6-10kg ያለ ሲሆን ለመጭመቅ ከማጠቢያ ገንዳ ወደ መጭመቂያ በእጅ ይታገዛል


ኬሚካሎች 2-3 ጊዜ ይጨመራሉ ውሃ ማስወጣትና ማስገባት የሚቻለው በተራ ነው በእጅ
እየታየ ነው 4 ቱ የማጠቢያ ዙሮች መዘፍዘፍ፣ማጠብ፣ማለቅለቅ፣መጭመቅ የሚሰሩት
እጅን በመጠቀም ስለሆነ ነው

ማሽን በእጅ ስለሚታገዝ Manual ይባላል ለቤትና ለቤተሰብ ብቻ ስለሆነ ለንግድ ሥራ


ስለማይሆን house hold ይባላል፡፡

Automatic washaing machin


ይህ-4 ቱንዙሮች በራሱ የሚጨርስ ነው መዘፍዘፍ ፣ማጠብ፣ማለቅለቅ፣መጭመቅን
የሚጨርሰው ባስነበበው/በፃፈው ሰ 0 ት /ጊዜ /ነው

- ልብሶችን/ጨርቆችን እና የማጠቢያ ኬሚካሎችን አስገብተን መምረጥና ማዘዝ ብቻ ነው


ሁሉንም ጨርሶ ያስረክበናል ሥራ ከጀመረ በኋላ ማሽኑን መክፈት መዝጋት እጅን ወደ
ማጠቢያ ገንዳ ማስገባት አደጋ አለው አይቻልም እስከሚጨርስ ሌላ ሥራ መስራት
ሲጨርስ ሦስት ዜሮዎችን (000) ያሳያል ከዚያ መብራት አጥፍቶ መክፈት ነው፡፡
ለስራ የሚነኩ button- ቁልፎቹ
- መብራት፡- የምርጫ ቁልፎች ልብሱ ምን እንደሆነ ለመምረጥ ከተደረደሩት ቁልፎች
ለማጠብ የሚፈለጉ የምንፈልገውን ቁልፍ መጫን start button መጫን

17
ምንአልባት- የመንገጫገጭ ሁኔታ እና ማሽኑ የማይፈልግ ድምጽና እንቅስቃሴ ሲኖረው
hold/Pause የሚለውን ቁልፍ/button መጫን ሲስተካከል start button መጫን ከቆመበት
እንዲጀምር ይረዳል

 እንዳትረሱ- ችግር ሲኖር ማሽን ለማስቆም የ power button አይነካም/አትጫን


የሚነካው/የምትጫነው hold/pause button/ቁልፍ/ነው ምክንያቱም የ”power” ቁልፍ
ከተነካ ከተጫንክ ወደ መጀመሪያ ይመለሳል የ hold ቁልፍ ከተጫንክ ካቆምክበት ይቀጥላል

የልብስ ማጠቢያ ውሃ አይነት(ለልብስ እጥበት የሚመረጥ የውሃ


አይነት)
የልብስ ማጠቢያ ውሃ እንደየልብሱ አይነት ቆሻሻው መጠን የተለያየ ነው

1. ቀዝቃዛ ውህ፡- በቀዝቃዛ ውሃ የሚታጠብ Cold water ልብስ ቀለሙ የሚለቅ ልብስ
ነው በሞቀ ከታጠበ የበለጠ ቀለሙ ይለቃል
2. የሞቀ ውሃ በጣም የቆሸሸ እና እስቴን የበዛበት ልብስ መታጠብ ያለበት በሞቀ ውሃ ነው
በቀላሉ ይለቃል፡፡
3. የፈጀ ውሃ - በፈጀ የሚታጠብ ልብስ የጥጥ ልብሶች ነጭ ልብሶች በአብዛኛው ነጭ
አንሶላ፣ ፎጣ ወዘተ.

የልብሶች/ጨርቆች የመቆሸሽ ደረጃ

እንደሚታወቀው ልብሶች/ጨርቆች የመቆሸሽ መጠናቸው ይለያያል ይህም በሦስት ይመደባል


በትንሹ የቆሸሸ/ጠረኑ ብቻ የሚጠላ Delicat soil

በመካከለኛ የቆሸሸ- የተለበሰ የሥራ ልብስ - Regular so

በጣም የቆሸሸ- stain/እስቴን ያለው heavey soil.

ማብራሪያ

18
1. በትንሹ የቆሸሸ ልብስ- በተለያየ ምክንያት ጠረኑ የተጠላ የማይፈለግ ሽታ፣ ወይም
ለረጅም ጊዜ የተቀመጠ- ያልተጠቀመበት ወይም መታጠብ የተፈለገ
አዲስ ልብስ ሲሆን ለማፅዳት የሚፈልገው ጊዜ ከ 5-10 ደቂቃ ብቻ ነው፡፡
2. በመካከለኛ የቆሸሸ Regolar soil ለሥራ 2-3 ቀን የተለበሰ ነገር ግን እስቴን ባዕድ ነገር
ያልነካው ሲሆን የሚወስደው ጊዜ 10-20 ደቂቃ
3. በጣም የቆሸሸ /heavy/soil/
- በተለያ ምክንያት በጣም የቆሸሸ ልብስ/ጨርቅ
- እስቴን ያለው ወይም የበዛበት
Eg. የወጥ ቤት ልብሶች-
ወጥ የተረጨባጨው - የሬስቶራንት የጠረጴዛ ልብሶች
o አልኮል
o ምግብ የፈሰሰባቸው

የልብስ አይነቶች ጠቅላላ ምድብ

ይህ ከላይ ለቆሻሻ አይነቶች የተጠቀምንበት ስያሜ ለልብስ አይነቶችም በሚከተለው


መሰረት መጠቀም ይቻላል

- Delirat- ልብሶችየህፃናት ልብስ/የእቅፍ ህፃናቶች


- Regular የአዋቂ የውስጥ ልብሶች/ከነቴራ ጡት ማስያዣ፣ፓንትልብሶች- ከጥጥ የተሰሩ
ልብሶች ፖሊስተር የጨርቅ ሱሪ፣ሸሚዝ፣ቲ-ሸርት ቀሚስ

-Heavey ልብሶች - ሹራብ እና ጅንስ ልብሶች

ቅድመ ዝግጅት procedure

19
ልብሶችከማጠብ ወይም ከማፅዳት በፊት የሚደረግ አለም አቀፍ ስርአት ነዉ
ልብሶች/ጨርቆች በሦስቱም አይነት የልብስ/ጨርቅ እጥበት ዘዴ የሚፀዱ/የሚታጠቡ ከሆነ
በመጀመሪያ የሚደረግ ቅድመ ዝግጀት

1. መለየት-Sortingq
2. ኪስ መፈተሸ- Check/inspect pocket
3. እንከን ማስተካከል - Correct damage
4. ታግ ማንበብ -Read tag
5. ባዕድ ነገሮችን/ምልክቶች ማስወገድ- stain removing
6. የቀለም ምልክትን ማስወገድ- Color remover
7. መመዘን-weighting
8. መዘፍዘፍ- Soak

1. መለየት - Sorting

ልብሶችም ይሁኑ ጨርቆች ከመታጠባቸው በፊት ይለያሉ ሲለዩ /selecting/በሦስት


መንገድ ነው

ሀ. በተሠሩበት ክር - ይህ ማለት ከአንድ አይነት ክር የተሰሩት አንድ ላይ ይታጠባሉ ከሌላው ክር


አይደባለቁም

ምሳሌ- ከጥጥ የተሰሩት አንድላይ ይታጠባሉ ከፕላስተርና ናይለንጋር አይቀላቀሉም

ለ. በቆሻሻቸው መጠን ይለያዩ/በመቆሸሽ ደረጃቸው በትንሽ ብቻ የቆሸሸ (ጠረኑ የማይፈለግ)


Delicat soil ለብቻ ይታጠባል

በመካከለኛ የቆሸሸው- Regular soil

ብቻውን ይታጠባል - በጣም የቆሸሸ

20
ከሌላው ይለያል heary soil

ሐ. ቀለሙ የሚለቅ ቀለሙ ከማይለቅ ተሌቶ ይታጠባል፡፡

2. ኪስ መፈተሽ- check/inspect pocket

ብዙ ጊዜ ሰዎች በኪሳቸው ውስጥ ጠቃሚ/Valuable እቃዎች አስቀምጠው ይረሳሉ


ከዚያም እንደተረሳ ውሃ ላወንደሪ/ መታጠብ ይሄዳል በዚህ ጊዜ የላውንደሪ ባለሙያው
ልብስ ከማጠቡ በፊት ኪሶችን መፈተሽ አለበት
- በኪስ ውስጥ ለኖሩ የሚችሉ ነገሮች ጠቃሚ ወረቀት የሆኑ ነገሮች
ለምሳሌ
- መታወቂያ
- ቼክ
- ቪዛ ካርድ
- ደረሰኝ
- የወረቀት ብር

ሌላው የሚዋጋ ወይም የሚቆርጥ ትንንሽ ነገሮች

- እስፒል- Pin
- መርፌ- needle
- መርፌ ቁልፍ- saffey pin
- ምላጭ- bland

ይህንን ጥፋት ለማዳን ከመታጠቡ በፊት ኪስ መፈተሸ አለበት

3 እንከን ያለበትን ማስተካከል Correct damages

ኪሶች ወይም ጨርቆች ላይ የሚገኝ እንከን ወይም ብልሽት ወይም ጎዶሎ የሚሆነው

1. የዚፕ አለመስራት/መበላሸት damaged zips


2. የቁልፎች መነቀል -Dropbutton

21
3. የተቀደደ/ስፌቱ የተፈታ- teard part

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ እንከኖች/ጎደሎዎች /ብልሽቶች/ልብሱ ከመታጠቡ በፊት

ካልተስተካከለ ከታጠበ በኋላ ለማስተካከል ቢሞከር ብዙ ብክነት ይፈጥራል

4 ባዕድ ምልክቶችን ማስወገድ - Remove stain ልብሶች/ጨርቆች ባዕድ ምልክት


ሊኖራቸው ይችላል ለምሳሌ- የቡና፣ሻይ፣የወጥ፣ወተት…. ጠብታዎች ልብስን ያበላሻሉ
ይህ ምልክት ያለበት ልብስ መልበስ የልብስን ውበት ያበላሻል
ስለዚህ ከታጠበ በኋላ ይህንን ለማስወገድ ቢሞከር የታጠበው ልብስ ተመልሶ ይቆሽሻል
በዚህ ምክንያት ባዕድ ነጠብጣቦች/የልብስ ላይ ባዕድ ምልክቶች ልብስ ከመታጠቡ በፊት
መወገድ አለባቸው፡፡
5 .Color removed- ይህም እንደ “stain remover” ተመሳሳይ ሲሆን ልዩነቱ የቀለም
ምልክቶች ልብሰ/ጨርቅ ላይ ካሉ ልብስ ከመታጠቡ በፊት ይወገዳሉ
ምሳሌ
- የእስክርፕቶ ቀለም
- የሚጠጣ ቀለም
- የማርከር ቀለም
- የቤት የግድግዳ ቀለም
6 ታግ ማንበብ የልብስ/ጨርቅ ማፅዳት መመሪያ መስጫ ምልክቶችን ማንበብ እነዚህም
ከዚህ በሚቀጥለው የተለያየ ስም ይጠራሉ
- Washing instruction ፣Tag Lawandery care gorde symbols
- Textile labbling lode በመባል ይታወቃሉ እነዚህ ኮዶች/ምልክቶች የሚገኙት በልብስ
የውስጠኛው ክፍል wrong side በማጅራት ላይ እና በጎን በኩል ነው

Washing code የልብስ ማጠቢያ ምልክቶች

በእጅ ይታጠብ

22
በማሽን ይታጠብ
400

በደረቅ እጥበት ይታጠብ

አትጠብ ወይም do’Not

በእጅ አትጠብ

በማሽን አትጠብ

የማድረቅ/Drying symbols

በፀሐይ አድርቅ sun drying

በማድረቂያ ማሽን አድርቅ Machine drying tumble drying

በገመድ ላይ አስጣ/በፀሐይ

23
በመቆንጠጫ አስጣ በፀሐይ

በማድረቂያ ልክ አንጥፈህ አስጣ

Do not do አታድርግ

በማሽን እንዳይደርቅ

Bleaching symbol
የበረኪና ምልክቶች

በረኪና ተጠቀም

በረኪና አትጠቀም

24
Ironing symbol /code
የካውያ አጠቃቀም

ለብያለ ካውያ ተጠቀም ( Cold/ Luck- iron )

- የሞቀ ካውያ ተጠቀም ( Warm Iron)

..

25
- በጋለ ካውያ ተጠቀም (Hot Iron )

...

ካዉያ አትጠቀም

መመዘን- Weighting

በተለይ በማሽን የሚታጠብ ልብስ መመዘን አለበት ምክንያቱም ማሽኑ ከውሃ ጋር


ተደምሮ የተመዘነ ልብስ ማጠብ አለበት

ለምሳሌ- የማጠቢያው ገንዳ የሚይዘው መጠን 10 ኪ.ግ የሚመዝን ከሆነ ወደ


ማጠቢያ ማሽኑ ገንዳ ክፍል የሚገባው ልብስ 8 ኪ.ግ ነው ምክንያቱም ከእያንዳንዱ
የማጠቢያ ማሽን -2 (2 ኪሎ ቀንስ) ፎርሙላ አለው፡፡ ይህ የሚቀነሰው የውሃ ቦታ
ነው፡፡ የሆነበት ምክንያት በገንዳው መጠን ወይም ልክ ልብስ ቢጨመር ውሃ ሲጨመርና ማሽኑ
ማጠብ ሲጀምር ውሃ ወደ ውጭ ይፈሳል አከባቢው በሙሉ በውሃው ይጥለቀለቃል አልፎም
ልብሶች ከማጠቢያ ውስጥ ወጥቶ ይወድቃል ይህ እንዳይሆን ልብስ ከመታጠቡ በፊት
ከማጠቢያው ገንዳው 2 ኪ.ም ለመቀነስ መመዘን አለበት፡፡

26
ልብሶች ታጠቡ እና ከደረቁ በሁዋላ የሚደረጉ ተግባራት

መተኮስ

 ልብሶቹ ላይ ባለው መመሪያ መሰረት


 በቅሚያ መተኮስ የሚችሉትንና የማይችሉትን እንደልብሱ አይነታቸው ልብሱ ላይ
ባለው መመሪያ (Reading Labels) በመመልከት መለየት

ማጠፍ የልብ ስ ማጠፍ አይነት የተለያየ ነዉ

Folding ማጠፍ - ሱሪ ፤ሸሚዝ

Rolling መጠቅለል- የዉስጥ ልብሶች

Hang -በመስቀያ መስቀል -ሙሉ ልብስ

ማሽግና ማስቀመጥ

 ከተጣጠፈ በኋላ እንደየልብሱ አይነት የላውንደሪ ቦርሳ በመጠቀም መስቀል የሚገባቸውን


መስቀያ በመጠቀም መስቀል
 ታጥፈው የሚቀመጡትን በመደርደሪያ ቁምሳጥን ውስጥ በአግባቡ ማስቀመጥ ይኖርብናል፡፡

27
የብቃት አሀድ ሶስት

LSA DOM 03 0816

የምግብና የመጠጥ መስተንገዶ አገልግሎት


(Food and beverage service)

የምግብና የመጠጥ ፤አገልግሎት በሁለት ይከፈላል


1. ለንግድ ስራ የሚውል አገልግሎት
2. የቤት ውስጥ አገልግሎት አሰጣጥ ይሆናል ፡፡
በመኖሪያ ቤት ውስጥ የሚሰጠው የምግብና የመጠጥ አገልግሎት ለትርፍ ስራ የሚውል
ባለመሆኑ ሜኑ የምግብና የመጠጥ ዝርዝር ከነዋጋው የያዘ መረጃ ለተጠቃሚው አይቀርብም
ነገር ግን የሚሰጠው አገልግሎት ደረጃውን የጠበቀና አለም አቀፍ ይዘት ያለዉ ሆኖ ባለሙያው
የሚያከናውነው ተግባር ተመሳሳይ ነው

የመግብና የመጠጥ አገልግሎት የሚሰጥ ባለሙያ የሚከተለው ባህሪያት

1. 1 አጠቃላይ የግል ንፅህናውን መጠበቅ ይሄውም


1.1 ገላውን መታጠብ
1.2 ጥፍሮቹን ማሳጠርና ቆሻሻ እንዳይኖረው ማድረግ
1.3 የፀጉሩን ንፅህና መጠበቅ
- ሴት ከሆነች ፀጉሯን ወደ ኋላ ማሲያዝ
- ወንድ ከሆነ በአጭሩ መቁረጥ
1.4 ሀይለኛ ሽታያለው ሽቶ /ዶድራንት / አለመጠቀም
1.5 ለእንቅስቃሴ እንዲመች ተረከዝ የሌለው ጫማ ማድረግ
1.6 ንፁህ የሰራ ልብስ መልበስ

28
2 የምየግብና የመጠጥ አገልግሎት የአሰራር ቅድመ ተከተል እነዚህም ቅደም ተከተሎች
የሚከተሉት ናቸው
2.1 የመመገቢያውን አካባቢ ማስተካከል / prepare dining area /
2.2 ጠረጴዛን ለመመገቢያነት ማዘጋጀት / set up table /
2.3 ምግብና መጠጥ ማቅረብ / serve food and beverage/
2.4 ከምግብ በኋላ ጠረጴዛውን ማፅዳት / clear table /

2.1 የመመገቢያውን አከባቢ ማስተካከል / prepare dining area /


የመመገቢያውን አከባቢ ለተመጋው ምቹ ማድረግ ማለት ነው ይሀው ለአገልግሎት የሚውሉት
ጠረጴዛ ወንበር በትክክል ጥቅም ላይ የሚውል /ብልሽት /የለላቸው መሆናቸውን መፈተሸ
- የመመገቢያውን ክፍል ማፅዳት
- ለአገልግት የሚውሉ ዕቃዎችን ማተካከል ንፅሁ መሆናቸውንና ካሆኑም ማፅዳት
- በዕለቱ ለሚቀርበው ምግብ አስፈላጊ የሆኑትን ዕቃዎች ለይቶ ማወቅ
- ጠረጴዛውና ወንበሮች በትክክል መቀመጣቸውን ማረጋገጥ
የመመገቢያውን ጠረጴዛ ማስተካከል በዕለቱ /በግዜው የተዘጋጀውን ምግብ መመገቢያ
ዕቃዎችን መለየት ለምሳሌ ቢላ ፤ማንኪያ ፤ ሹካ ፤ሳህን ---- እነዚህን ማስተካከል
- ጠረጴዛ በትክክል መቀመጡን /አለመነቃነቁን ማየት /
- የጠረጴዛን ጨርቅ በትክክል ላይዛነፍና ላይጨማደድ ማልበስ
- ከጠረጴዛው ጨርቅ ላይ ተጨማሪ ሌላ መተኑ አነስተኛ የሆነ ምግብ ወይም
መጠጥ ቢንጠባጠብ እንዳይበላሽ ማልበስ
- በጨርቅ ሆነ በወረቀት ማዘጋጀት
- የጠረጴዛ ፎጣ ጥቅሙ ከምግብ በፊት የራስን ንጽህና ለመጠበቅ ከምግብ በኋላ
እጅና አፍን ለማፅዳት ሲጠቀም በተጨማሪ በተለያየመንገድ የሚታጠፍና
የሚዘጋጁ የጨርቅ ናፒኪዮች የመመገቢያ ቦታውን ያሳምራሉ ለምግብ
አገልግሎት የሚውሉትን እቃዎች ተገቢ ቦታቸውን ይዘው እንዲቀመጡ
ማድረግ
ለመመገቢያ ቢላ ማንኪያ ሹካ የሚያስፈልጉ ከሆነ ቢላ ከተመጋው በስተቀኝ ከጠረጴዛ ጫፍ
ሁለት ጣት ገባ በማለት ማስቀመጥ ሹካ በስተግራ
በመቀመጥ አለባቸው ብርጭቆ በስተቀኝ
በመጨረሻ ያስተካከልነውን ጠረጴዛ ትክክል መሆኑን አገልግሎት ከመጀመሪያችን በፊት
ማረጋገጥ ፡፡

29
2.3 ምግብ እናመጠጥ ማቅረብ
ምግብ በሚቀርብት ጊዜ የራሱ የሆነ ቅደመ ተከተል አለው ይሀውም
የመጀመሪያው - ከሳቴ ከርስ / አፕታይዘር /
ሁለተኛው ዋናው ምግብ /main dish /
ሶስተኛው ጣፋጭ በመባል ይታወቃሉ - /dessert /
እነዚህን የምግብ አየረነቶች ቅደም ተከተላቸውን ላናዛባና እንዲሁም መጠቀሚያ ዕቃዎችን
ለይተን በተገቢው ዕቃ ይቀርባሉ ፡፡
ምግብ ፡- በሚቀርብበት ጊዜ ምንግዜም ከተመጋቢው በስተ ግራ ይቀርባል
መጠጥ ከተመጋቢው በስተቀኝ ይቀርባል
መጠጥ ሲባል ማንኛውም ሊጠጣ የሚችል ትኩል /ቀዝቃዛ / አልኮል ያለው ወይም የሌለው
ማለት ነው ፡፡
ከምግብ በኋላ ጠረጴዛውን ማፅዳት
ለመግብና ለመጠጥ አገልግሎት የዋሉትን ዕቃዎች ማንሳትና ጠረጰየዛውን ማፅዳት ይህ
የሚሆነው እንግዳው /ተመጋቢው /
በራሱ ጨርሶ በሚሄዱበት ጊዜ ነው
አከባቢው ላይ የሚገኘውን የማንኛውምነገር ወደ ቦታ መመለስ

የሙያ ሥነ-ምግባር

30
ስነ-ምግባር ስንል የሰዎችን ባህርይ የሚቆጣጠር ወይም በሰዎች ባህሪይ ላይ
ተፅዕኖ የሚያድግ አንድ ህብረተሰብ የተቀበለው ትክክለኛና ትክክለኛ ያልሆነ
ባህርይ መለኪያ ነው፡፡

የሥራ ሥነ-ምግባር

የሥራ ስነ-ምግባር ስንል አንድን ስራ ለማከናወን የሚያስችል ከአንድ ባለሙያ የሚጠበቅ


ባህሪ ነው ፡፡ ሁሉም የሙያ መስኮች የራሳቸው የሆኑና የተለያዩ የሙያ ስነ-ምግባሮች
አሏቸው ይሁን እንጂ በሁሉም ሙያዎች የመናገኛቸው የጋራ የሆኑ የሙያ ስነ-
ምግባሮች አሉ፡፡

በሁሉም ባለሙያ ዘንድ ሊኖሩ የሚገቡ የሙያ ስነ-ምግባሮች፡

 ሰዓት ማክበር
 ሥራን ማክበር
 ሙያን ማክበር
 የሥራ ፍቅር
 ታማኝነት
 ቅንነት
 ትህትና
 መረዳዳት
 ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት
 ለሥራ መስዋትነት መክፈል
 ለሥራ ተነሳሽነት
 ብቃት፣ ክህሎትና የመሳሰሉት ናቸው፡

ሀ. የልብሰ እጥበት የተግባር ጥቃቄዎች

የሚከተሉት ጥያቄዎች በተግባር ሰርተህ/ሽ አሳይ

31
1 ልብስ ከመታጠቡ በፊት መደረግ የለበት ቅድመ ዝግጅት በቅደም ተከተል አሳይ
2 የታጠቡ ልብሶችን መተኮስ፣ ማጠፍና ማስቀመጥ በቀደም ተከተል አሳይ

ለ .የቤት ጸዳት እና አያያዝ የተግባር ጥቃቄዎች

1. የቤት ጸዳት ቅደም ተከተል እና ለየጸዳቶቹ የኬሚካል አጠቃቀም አሳይ


2. የአልጋ ማንጠፍ ቅድም ተከተልን አሳይ

ሐ. የምግብ አና መጠጥ አገልግሎት የተግባር ጥቃቄዎች

የእለቱ ምሳ ፓስታ ቢሆን

1. ለምግቡ መገልገያ የሚሆኑ እቃዎችን ግለጽ


2. ለምገቡ መገልገያ የሚሆኑ እቃዎችን በመመገቢያ ጠረጴዛ አስቀምጥ
3. ለመጠጥ የሚያስፈልጉ ብርጭቆዎቸን በቦታቸዉ አስቀምጥ

በሆቴልና ቱሪዝም የቤት ጽዳትእና አያያዝ የማሰልጠኛ ግብዓት

ተ.ቁ የዕቃው ዓይነት መለኪያ


1 ፈሳሽ ሳሙና ሊትር

32
2 ደረቅ ሳሙና በቁጥር
3 ዱቄጽ ሳሙና በኪ.ግ
4 ስፖንጅ በቁጥር
5 አጃክስ በቁጥር
6 የገላ ሳሙና በቁጥር
7 በረኪና በቁጥር
8 ዲቶል በቁጥር
9 የመስታወት ማፅጃ በቁጥር
10 የጣራ ማጸጃ በቁጥር

11 አቡጀዲ በሜትር
12 ብናኝ የሌላቸው ጨርቆች በሜትር
13 እሰፖንጅ በቁጥር
14 አንሶላ በጥንድ
15 ብርድ ልብስ በቁጥር

16 የአልጋ ልብስ በቁጥር


17 ትራስ በቁጥር
18 የትራስ ጨርቅ በቁጥር
19 የገላ ፎጣ በቁጥር
20 የፊት ፎጣ በቁጥር
21 የእጅ ፎጣ በቁጥር
22 ሻምፖ በቁጥር
23 ኮንድሽነር በቁጥር
24 ሶፍት በቁጥር
25 ኤር ፍሬሽነር በቁጥር
26 ምንጣፍ በካሬ
27 የአቧራ ማራገፊያ በቁጥር
28 መስተዋት በቁጥር
29 አሽትሬ በቁጥር
30 ኮልጌትና ብሩሽ በቁጥር
33
31 አበባ በቁጥር

32 ነጠላ ጫማ በቁጥር
33 የተለያዩ ብርጭቆዎች በደርዘን
34 የአቧራ ማንሻ ከነቡርሹ በቁጥር
35 መጥረጊያ በቁጥር
36 መወልወያ በቁጥር
37 ወረቀት በደስጣ
38 እስክሪቢቶ በፓኬት
39 ጓንት በቁጥር
40 የሸረሪት ማንሻ በቁጥር
41 መቆንጠጫ በደርዘን
42 የልብስ ማስቀመጫ ፕላስቲክ በቁጥር
43 ባልዲ በቁጥር
44 የጠረጴዛ ጌጥ በቁጥር
45 የግድግዳ ጌጥ በሜትር
46 መጋረጃ በሜትር
47 የጠረጴዛ ልብስ በቁጥር

48 የልብስ መስቀያ በቁጥር

የምግብ እና መጠጥ አገልግሎት የማሰልጠኛ ግብዓት

ተ.ቁ የዕቃው ዓይነት መለኪያ


1 ቢላዋዎቸ በቁጥር
2 ማንኪያዎች በደርዘን
3 ሹካዎች በቁጥር

34
4 ብርጭቆዎች በቁጥር
5 ሳህኖች በቁጥር
6 ሲኒ የቡና እና ሻይ በደስጣ
7 የጠርሙዝ መክፈቻ በፓኬት
8 የበረዶ ማሰቀመጫ በቁጥር
9 የወይን ማቀዝቀዣ በቁጥር
10 የጠረጰየዛ ና የወንበር በሜትር
ጨረቆቸ
11 የናፕኪን ጨርቆች በሜትር
12 ሰርቪስ ትሪ በቁጥር
13 ማጽጃ ፎጣ በደርዘን
14 ኮንዳምነት በቁጥር

የልብስ እጥበት አገልግሎት ማሰልጠኛ ግብአት

ተ.ቁ የዕቃው ዓይነት መለኪያ


1 ፈሳሰሽ ሳሙና በሊትር
2 ዱቄት ሳሙና በፓኮ
3 መምቻ ሳሙና በቁጥር
4 በረኪና በቁጥር
5 እስቴን ሪሙቨር በቁጥር
6 ከለር ሪሙቨር በቁጥር
7 ፋበሪክ ሶፈትነር በቁጥር

35
8 ካዉያ የልብስ መተኮሻ በቁጥር
9 የልብስ መቆንጠጫ በፓኮ
10 የልብስ ማስጫ ገመድ በሜትር

11 የላዉነደሬ ባሰኬት በቁጥር


12 የባለሙያ ሽርጥ በቁጥር
13 ዉሀ መርጫ በቁጥር
ዲቫይደር በቁጥር
መመዝገቢያ ደብተር በቁጥር

ማጠቃለያ

ይህ ማንዋል በግልም ሆነ በቡድን ተደራጅተው ለሚመጡ ሰልጣኞች በቂ የሆነ


ዕውቀት፣ክህሎትና አመለካከት እንዲኖራቸው በማድረግ ከስልጠና በኋላ ስልጣኞች
ደረጃውን የጠበቀና ሳይንሳዊ ዘዴን በተከተለ መንገድ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ

ሲሆን በተጨማሪ በሙያዉ ከሰለጠኑ በኋላ በቃት አሀዱ መሰረት በምዘና ብቁ


ከሆኑ በኋላ ተደራጅተዉ ስራ በመፍጠር ገቢ ሰለሚየገኙ ለሀገራቸዉ ኢኮኖሚያዊ፤
ማህበራዊ አስተዋጽኦ እንዲየደርጉ የረዳቸዋል

36
አዘጋጆች

1. አሰልጣኝ አልማዝ ሀይሉ mob 0924443672


2 .አሰልጠኝ መስታወት አየለ mob 0931378901
3. አሰልጣኝ አልማዝ በድሉ mob 0960907800

37

You might also like