You are on page 1of 2

ለፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ክፍል

አዲስ አበባ

ጉዳዩ ፤ ለፐብሊክ ባስ ኪራይ ስለ መጠየቅ

የአዲስ አበባና አካባቢዋ ቀጠና ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በሰኔ 17-18 ቀን 2015 ዓ.ም
በሚሊኒየም አዳራሽ የሁለት ቀን ኮንፍራንስ የምናደርግ ስለሆነ ሕዝባችንን ካሉበት አካባቢ
በማንሳት ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ አድርሶ ለመመለስ በእናንተ በድርጅታችሁ 60
አወቶብሶችን ለመከራየት አስበናል ይህም ታውቆ የዘወትር ትብብራችሁን እንድታደርጉልን
በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ከመንፈሳዊ ሠላምታ ጋር

ለዲጅታል ወንጌል ሠራተኞች በሙሉ

አዲስ አበባ

አስቀድመን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሠላታችንን እየቀረብን በሙያቹ ተጠቅማችሁ ለወንጌል ሥራ


ስለምታደርጉት እንቅስቃሴዎች ታላቅ አድናቆትና ልንገልጽ እንወዳለን፡፡

በመሆኑም የአዲስ አበባና አካባቢዋ ቀጠና ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በ 2015 ዓ.ም ካቀደችው አንዱ
የተሃድሶ ወንጌል ስርጭት ኮንፍራንስ በመሆኑ የ 52 ቀናት የወንጌል ሥርጭት ኮንፍራንስ ማለትም ከሚያዝያ
24 ቀን አስከ ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ለአንድ ሚሊየን ሰዎችን በወንጌል ለመድረስ የቻሉ ሲሆኑ በዚህም
ምስክርነት እንቅስቃሴ ጀምርን አንድ ለአንድ የመመስከር ዘዴ ሁለት መቶ ሺህ ሰዎችን በመድረስ 2238 ሰዎች
ወደ ጌታ ሲመጡ 503 ሰዎች በንስሃ ተመልሰዋል፡፡

በተጨማሪም በዲጂታል ኢቫንጄሊዝም ስትራቴጂ አምስት መቶ ሺህ ሰዎች ለመድረስ እንቅስቃሴ የተጀመረ


ሲሆን፤ ከዚህም በመቀጠል ሰኔ 17-18 ቀን 2015 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የሁለት ቀን ኮንፍራንስ ስለምናደርግ
በእናንተ በኩል ይህንን ራዕይ በመደገፍ ወንጌል በመስበክና መልካም ፍቃዳቸሁ ቢሆን የዚህን ኮንፍራንስ
ማስታወቂያ በድረ ገጻቸሁ ላይ በመልቀቅ በአብሮነት የእግዚአብሔርን ሥራ በጋራ በመስራት መንግስቱንም
በማስፋት እንድትተባበሩን በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን፡፡

ከመንፈሳዊ ሠላምታ ጋር

You might also like