You are on page 1of 2

እንኳን ለ 2015 ዓ.ም የት/ት ዘመን ቀን፡ 11/12/14 ዓ.


በሰላም አደረሳችሁ!!

ማስታወቂያ
ለደራርቱ ቱሉ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነባር አዲስ ተማሪዎች በሙሉ
ት/ቤታችን ለ 2015 ዓ.ም የት/ት ዘመን ነባር ተማሪዎችን ምዝገባ ለማከናወን ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጉዳዮች በሟሟላት በሠንጠረዥ በተቀመጠው መርሐ -
ግብር መሰረት ምዝገባ እንድታከናወኑ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

1. ማንኛውም ወንድ ተማሪ ፀጉሩን ከ 1 ሴ.ሜ በላይ ያላሳደገ እና ማንኛውም ሴት ተማሪ የከንፈር ቀለም ያልተቀባች እና ዊግ ያልቀጠለች
2. የተማሪነት መታወቂያ
3. 3X3 የሆነ 1 የወላጅ እና 1 የተማሪ ጉርድ ፎቶግራፍ ለነባር ተማሪዎች፡፡ ለአዲስ ተማሪዎች 3X3 የሆነ 2 የወላጅ እና 3 የተማሪ ጉርድ ፎቶግራፍ
4. ወደ ቀጣይ ክፍል የተዘዋወራችሁበትን የውጤት ማመሳከሪያ ካርድ
5. ያስመዝጋቢ ወላጅ/አሳዳጊ የነዋሪነት መታወቂያ ዋናውና ኮፒ
6. በ 2014 ዓ.ም የነበራችሁበትን የመማሪያ መፅሃፍት በዕለቱ በማስረከብ ከንብረት ክፍል ማረጋገጫ ወረቀት
7. አስመዝጋቢ ወላጅ/አሳዳጊ በአካል መገኘት አለበት
8. የመመዝገቢያ ሠዓት ጠዋት ከ 3፡00 ሠዓት እስከ 6፡30 ሠዓት እና ከሰዓት ከ 7፡30 እስከ 10፡30 ሠዓት

ተ.ቁ ክፍል የምዝገባ ቀን ምርመራ


1 ወደ 12 ኛ ክፍል የተዘዋወሩ በ 17/12/14 ዓ.ም እና በ 18/12/14 ዓ.ም
2 ወደ 11 ኛ ክፍል የተዘዋወሩ በ 19/12/14 ዓ.ም እና በ 20/12/14 ዓ.ም
3 ወደ 10 ኛ ክፍል የተዘዋወሩ በ 23/12/14 እና በ 24/12/14
4 በሁሉም የክፍል ደረጃ ያልተዘዋወራችሁ የት/ቤቱ መደበኛ ተማሪዎች 25/12/14 ዓ.ምእስከ 27/12/14 ዓ.ም
(የ 9 ኛ፣ 10 ኛ እና 11 ኛ ክፍል ብቻ)
5 አዲስ የሰርጢ እና በሰቃ 1 ኛ ደረጃ ት/ቤት ወደ 9 ኛ ክፍል ከ 30/12/14 ዓ.ም አስከ 03/13/14 ዓ.ም
የተዘዋወራችሁ እና የወረዳ 08 ነዋሪዎች ብቻ

6 አዲስ የኖላዊ 1 ኛ ደረጃ ት/ቤት ወደ 9 ኛ ክፍል የተዘዋወራችሁ 04/13/14 ዓ.ም


የወረዳ 08 ነዋሪዋች ብቻ
ማሳሰቢያ፡ ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ አይስተናገድም፡፡ የነበረበትን የክፍል ደረጃ የመማሪያ መፅሃፍትን ይዞ ያልመጣ አይስተናገድም፡፡ አስመዝጋቢ
ወላጅ/አሳዳጊ በአካል ካልተገኘ ምዝገባ ማከናወን አይቻልም፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ የማይስተናገድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

You might also like