You are on page 1of 17

1

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የመጋዘን ኦፕሬሽን


ክፍል

2013 ዓ.ም
2

አገልግሎት የሚሰጥባቸዉ ቅርንጫፎች


• በ11 የቡና ፤ በ12 የጥራጥሬ እና ቅባት እህሎች በጠቅላላ በሀያ ሁለት
(23) ቅርንጫፎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
የቡና ቅርንጫፎች የጥራጥሬ እና ቅባት እህሎች ቅርንጫፎች
1 በደሌ 1 አብርሃ ጅራ
2 ቡሌ ሆራ 2 አዳማ
3 ቦንጋ 3 አሶሳ
4 ዲላ 4 ቡሬ
5 ድሬዳዋ 5 ዳንሻ
6 ጊንቢ 6 ጎንደር
7 ሐዋሳ 7 ሁመራ
8 ጅማ 8 ኮምቦልቻ
9 ሳሪስ (በሁለቱ) 9 መተማ
10 ሶዶ 10 ነቀምት
11 መቱ 11 ፓዌ
12 ሽራሮ
3

የቅርንጫፍ ኦፕሬሽን ክፍል ዕይታ በከፊል….


የናሙና አወሳሰድ

የቡና ላብራቶሪ የቅባትና ጥራጥሬ እህሎች ላብራቶሪ

መጋዘን
4

የኦፕሬሽን ክፍል ስራ ሂደት

• የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በሁሉም ቅርንጫፎቹ (23)


በዋናነት የሚከተሉትን አገልግሎቶችን ይሰጣል፡
1. ከአቅራቢዎች ምርት በመረከብ የመጋዘን አገልግሎት
ይሰጣል፤
2. የጥራት ሰርተፊኬት የመስጠት ሂደት ያከናውናል
(ለማህበራት፤ ለቀጥታ ላኪዎች እና የቀጥታ ገበያ ትስስር
ላላቸው)፤
3. ለገዢዎች በገዙት ምርት መጠን እና ደረጃ ምርቱን
ያስረክባል፡፡
5

የእያንዳዱን አገልግሎት አሰጣጥ የስራ ሂደቶች በከፊል…


1. ምርት መረከብ አገልግሎት አሰጣጥ

• በቅድሚያ አቅራቢዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ምርት ይዘው ወደ


ቅርንጫፎች በሚመጡበት ጊዜ የሚከተሉትን ነገሮች አሟልው መቅረብ
ይኖርባቸዋል፡፡
1. ዲስፓች ( መረጃዉ በዞኑ ግብርና/ንግድ ቢሮ የተሞላና ማህተም ያለበት
መሆን አለበት)
2. ህጋዊ ውክልና እና ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ ፤ የንብረቱ ወይም
የድርጅቱ ባለቤት ከሆኑ የባለቤትነትን የሚገልጽ መታወቂያ
3. የሹፌር መንጃ ፈቃድ/መታወቂያ
6

የቀጠለ…..

• ወደ ምርት ገበያው ግቢ በሚገቡበት ወቅት የሚከናወኑ የሥራ ሂደቶች

1. መኪኖች በገቡበት አግባብ እንዲስተናገዱ የመግቢያ ትኬት መስጠት


(Get Ticket )
2. በምርት ገበያው የቀረበውን ዕለታዊ የደንበኞች መመዝገቢያ ቅጽ በሰዓቱ
በሚገባ መሙላት እና ማስገባት ይኖርበቸዋል፡፡
3. ይዘውት የቀረቡትን መኪና በማቆያ ስፍራ በማቆም ከአካባቢው ሳይርቁ
ተራቸውን መጠባበቅ ይኖርባቸዋል፡፡
7

የቀጠለ…..

• ምርት ገበያው ምርትን ከአቅራቢዎች በሚረከብበት ጊዜ ከሚያከናውናቸው


ተግባራት በጥቂቱ በቀደም ተከተል ፡፡
1. የምዝገባ ሂደት ማከናወን (Arrival registrations)
2. ሚስጥር ቁጥር በመስጠት ናሙና መውሰድ (Sampling)
3. የላብራቶሪ ሚስጥር ቁጥር መስጠት (Coding)
4. ደረጃ መስጠት (Grading)
5. የሚስጥር ቁጥር መተርጎም (Decoding)
6. ደረጃ የወጣለቸውን ምርቶች ለደንበኛው ወይም ለህጋዊ ወኪል ማሳወቅ፤
7. ደንበኞች በደረጃው ከተሰማሙ ምርቱን ደንበኛው ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኘበት
በመመዘን (Weighing) መረከብ እና ማቆየት፡፡
8. ደንበኞች በደረጃ ካልተስማሙ የቅሬታ ፎርም እንዲሞሉ በማድረግ ህግን
በመከተል ለተጨማሪ ምርመራ ማዘጋጀት፡፡
8

የቀጠለ……

• ደረጃ የወጣላቸውን እና ተመዝነው ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን


በሚከተሉት የመረከቢያ አይነቶች መረከብ እና ማቆየት(Deposit)
 ቡና:- ሁለት (2) አይነት ማቆያ ዘዴዎች አሉ
1. ጥብቅ ማቆያ ስፍራ (Bonded Yard)፡- በጥብቅ ማቆያ ስፍራ በማቆየት
ምርታቸውን መሸጥ ለሚፈልጉ ደንበኞች ደንበኛው ወይም ህጋዊ ወኪሉ
በተገኘበት ፕሎንፕ በሚገባ በማሸግ በጥብቅ ማቆያ ስፍራ ማቆየት ፡፡
2. ዱካን በመከተል ስርዓት በመጋዘን በማራገፍ ማቆየት፡፡
 ለጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች፡-
በደረጃው ዓይነት እና መጠን በመጋዘን በማረገፍ ማቆየት፡፡
9
የቀጠለ……

• የምርት መረከቢያ ደረሰኝ በማዘጋጀት ለደንበኛው መስጠት GRN (Good


Received Note) ፡፡
• አቅራቢው ወይም ህጋዊ ወኪሉ የመረከቢያ ደረሰኝ GRN (Good
Received Notes) በጊዜው በመቅረብ የመረጃውን ትክክለኛነት
በማረጋገጥ ፈርሞ መረከብ ይኖርበታል፡፡
2. የጥራት ደረጃ ሰርተፍኬት መስጠት (Grade Certificate)
• ከላይ የተጠቀሰውን የምርት ጥራት ደረጃ አሰጣጥ ሂደት ተከትሎ የጥራት
ደረጃ ሰርተፍኬት አገልግሎትን ለሚፈልጉ ደንበኞች (ለማህበራት፤ ለቀጥታ
ላኪዎች እና የቀጥታ ገበያ ትስስር ላላቸው) አገልግሎቱን መሰጠት (Grade
Certificate)፡፡
10

የቀጠለ……

3. ምርት ማስረከብ (ወጪ ማድረግ)


• በቅድሚያ ገዢዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የገዙትን ምርት ለመረከብ
በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚከተሉትን ነገሮች አሟልተው ምርቱን
ወደየገዙበት ቅርንጫፍ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
1. የምርት ገበያውን ምርት መረከቢያ ደረሰኝ DN(Delivery Note)
(ደንበኞች ግብይት ከፈጸሙ በኃላ የገዙትን ምርት ለማንሳት ከምርት ገበያው
የሚሰጥ ደረሰኝ)
2. ህጋዊ ውክልና እና ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ ፤ የንብረቱ (የድርጅቱ)
ባለቤት ከሆኑ ባለቤትነትን የሚገልጽ መታወቂያ፤
3. ከመጋዘን ለሚነሱ ምርቶች DTW & TTW (Direct To
Warehouse & Truck To Warehouse) ለሆኑ ምርቱን
የሚያነሱበት መኪና ይዘው መቅረብ፤
4. የሹፌር መታወቂያ
11

የቀጠለ…..
 ምርት ገበያው ለደንበኞች ምርትን በሚያስረክብበት ጊዜ
ከሚያከናውናቸው ተግባራት በጥቂቱ ፤
• ደንበኛው ይዞት የቀረበው የምርት መረከቢያ ደረሰኝ DN(Delivery
Note) ህጋዊ እና የመረከቢያ ጊዜው ያላለፈበት እንዲሁም ካሁን
በፊት በቀረበው ደረሰኝ ቁጥር ምርቱ ወጪ አለመደረጉን በሲሰተም
ያረጋግጣል::
• ደንበኛው ይዞት በቀረበው ምርት መረከቢያ ደረሰኝ ቁጥር መሰረት
የምርት ማንሻ ደረሰኝ PUN (Pick Up Notes) ማዘጋጀት፡፡
• በምርት መረከቢያ እና ማንሻ (DN&PUN) ደረሰኝ ላይ ባለው መረጃ
አማካኝነት ደንበኞች በገዙት የምርት አይነት፣ መጠን እና የጥራት ደረጃ
ምርቱን ማስረከብ፡፡
12

የቀጠለ…..
 ምርት የማስረከቢያ ዘዴዎች፡-
1. ከጥብቅ ማቆያ ስፍራ (Bonded Yard)፡- ደንበኛው ወይም
ህጋዊ ወኪሉ በተገኘበት የመኪናው ፕሎንፕ በሚገባ የታሸገ መሆኑን
በማረጋገጥ ማስረከብ፡፡
2. ከመጋዘን (Warehouse)፡- ደንበኛው ወይም ህጋዊ ወኪሉ
በተገኘበት ምርቱን በመመዘን እና ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ማስረከብ፡፡
• የወጪ ደረሰኝ GIN (Good Issued Note) በማዘጋጀት
ለደንበኛው ወይም ለህጋዊ ወኪሉ መስጠት፡፡
• የመውጫ ትኬት በማዘጋጀት ለደንበኛው ወይም ለህጋዊ ወኪል (Get
Pass) መስጠት፡፡
13
የገቢ ደረሰኝ
• የቡና የምርት መረከቢያ ደረሰኝ GRN (Good Received Note)
14
የቀጠለ…….
• ለጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች የምርት መረከቢያ ደረሰኝ GRN (Good
Received Note)
15
የወጪ ደረሰኝ
• የቡና ወጪ ደረሰኝ GIN (Good Issued Note)
16

የቀጠለ…..
• ለጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች ወጪ ደረሰኝ GIN (Good Issued Note)
17

አመሰግናለሁ!
“የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የሁላችንም
ገበያ”

You might also like