You are on page 1of 2

❤❤❤❤❤የሌላም ብትሆኝ❤❤❤❤❤

ፍቅሬን ንቀሽ ገፍተሽ፣ ብትሄጂም ርቀሽ፣

ሆዴን ከፋኝ እንጂ መቼ ተቀየምኩሽ፣

የቤቴን ገመና ዘክዝኬ ነግሬሽ፣

በየዋህ አፍሪቃሽ ምነው መጨከንሽ፣

መልካም መልካም ነገር ዘላለም ይግጠምሽ፣

ዛሬ ብትለይኝ የበለጠ አይተሽ፣

ሁሉም ጊዜያዊ ነው በኋላ እንዳይቆጭሽ።

አንቺ መቼ አወቅሽልኝ ይህን ሁሉ ጉዴን፣

አሰብሽው በመጥፎ በባዶ መውደዴን።

ብየሽ ነበር ያኔ፣ ማጣሽ ይመስለኛል እኔ፣

ባዶነት ተሰማኝ ስትጠፊ ከጎኔ።

ለበጎ ነው ብዬ በራሴ ስፅናና፣

ስትርቂኝ ስቀርብሽ በመልካም ስብዕና።

ራሴን ጥዬ ሁልጊዜ ስወድሽ፣

እኔም ተስፋ ቆረጥኩ አንቺም አልተመለስሽ።

ምነው በቀረብሽ ያ! ሁሉ መሀላ፣

ቃልኪዳን ከማፍረስ ምነው ባይበላ።

ሀዘንሽ ሀዘኔ ህመምሽ ህመሜ፣

ሳቅሽ ሳቄ ቢሆን ድካምሽ ድካሜ።

ደጋደግነትሽ ፈገግታሽ ውበቴ፣

ስለይሽ በድንገት ዛለ ሰውነቴ።

ገራገሩን ልቤን አይተሽ ደግነቴን፣

ራቅሽኝ በድንገት ሳትነግሪኝ ጥፋቴን።


ሌሊቱን በሀሳብ ቀኑን በትካዜ፣

አዪ ከንቱ ፍቅር አዬ ከንቱ ጊዜ።

"አንተ ጥሩ ሰው ነህ እኔ ደግሞ አይደለሁም"፣

ብለሽ የፃፍሽልኝ ልቤን ቢያስከፋውም፣

ያንን ጣፋጭ ጊዜ መቼም አልረሳውም።

አንቺ ጋር ያለውን ልቤን ሳትመልሽው፣

በንቀት ብታይው ስታልፊ ረግጠሽው፣

በአይኖችሽ ቁጣ ስትጥይው ገፍተሽው፣

ስትርቂኝ ስትሸሺኝ ልቤን አሳዘንሽው፣

በደልሽ ሲበዛ አንጀቴን ቆረጥሽው።

ግን ምን ያደርጋል? ትዕግስት ያስፈልጋል።

የሙዚቃው ግብዣ መቼ ይረሳኛል፣

የፎቶወቹ ጥራት ዛሬም ትዝ ይሉኛል።

በመጥፎ አጋጣሚ ልብሽ ቢተወኝም፣

እኔ እያሰብኩሽ አንቺ ብትረሺኝም።

ደብቀሽ በውስጥሽ እውነት ባትነግሪኝ፣

ዛሬም እወድሻለሁ የሌላም ብትሆኝ።

You might also like