You are on page 1of 3

መደመር ወይስ መከባበር፡ እያሸነፈ ያለው የትኛው መርህ ነው?

--------------------------------

(ዘመንፈስ አክሱማዊ)

ድምጺ ወያነ፡ ጥሪ፡3/2011 ዓ/ም

መግቢያ

--------------

ዶር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ዛሬ የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት በነበራቸው የትግል ተሞክሮ ግን
በርካታ ውጣ-ውረዶችን አሳልፈዋል፡፡ ዶር ደብረፅዮን አምባገነኑን የደርግ ስርዓት ለማስወገድ የተጀመረውን የትጥቅ
ትግል የተቀላቀሉት በወጣትነታቸው ነው፡፡ በእነዚህ መራራ የትግል ጊዜያት ዶር ደብረፅዮን ያላሳለፉት ስቃይ አልነበረም፡፡
ለየት የሚያደርገው ታሪካቸው በትጥቅ ትግሉ ወቅት ከገደል አፋፍ ወድቀው በተዓምር የተረፉበት አጋጣሚ ነው፡፡ ከዚህ
አንፃር ዶሩ ዛሬ የደረሱበት ደረጃ የደረሱት ከውድቀት እየነጠሩ ተነስተው ነው ማለት ይቻላል፡፡

በከተማ የፖለቲካ ትግላቸውም በድርጅታቸው ውሳኔ በወረዳ ደረጃ በሚገኙ የታችኛው እርከን ላይ አንዲሰሩ
የተጣለባቸውን ግዴታ ያለምንም ቅሬታ በአግባቡ ተወጥተዋል፡፡ ዶር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ዛሬ የትግራይ ክልል ርዕሰ
መስተዳደር የሆኑትም ከወረዳና ከቀበሌ አመራርነት ተነስተው ነው ፡፡ ዶር ደብረፅዮን ወደ መቀሌ መጥተው ክልሉን
መምራት የጀመሩት በመደመር ፖለቲካ ዋዜማ ነው፡፡

የመደመር ፖለቲካ ለውጡን ተከትሎ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች የሰላም ችግር እየተስተዋለ ባለበት በአሁኑ ወቅት ዶር
ደብረፅዮን በሚመሯት የትግራይ ክፍል በማይታመን መልኩ አስተማማኝ ሰላም ተፈጥሯል፡፡ የዛሬው ለውይይት
የመረጡኩት ጉዳይም ከዚህ ጋር በተያያዘ ጥያቄ ላይ ያተኩራል፡፡ ለመሆኑ አሁን አገሪቱ በእርስ-በእርስ ግጭት
በምትናጥበት በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል ለተፈጠረው የሰላም የአመራሩ የፖለቲካ አቅጣጫ ምንድን ነው?

1. የተሳሳተ ስሌት

------------

የመደመር መርህ ለዶር ደብረፅዮን ከሁለት ጉዳዮች አንፃር የተሳሳተ ስሌት ሳይሆንባቸው አልቀረም፡፡ ከንድፈ-አሳብ
አንፃር እና ከተግባራዊ ውጤቱ አንፃር። በእርግጥም የመደመር ለውጡ ግልፅነት የሚጎድለው ነው፡፡ አንደኛ ከንድፈ-አሳብ
አንፃር የየመደመር ፖለቲካ ይዞት የመጣው አዲስ የተደራጀ የፖለቲካ ፍልስፍና የለውም፡፡ አመጣጡ በልማታዊ መንግስት
የፖለቲካ አቅጣጫ ላይ ጥገኛ ሆኖ የመጣ ነው፡፡ በሂደት አቅም እያገኘ ሲሄድ በጥገኝነት የመጣበትን የልማታዊ መንግስት
መስመር እየጋጠ አመነመነው፡፡ በአንድ በኩል የመደመር ፖለቲካ የፖለቲካ ለውጥ ነው አንዳይባል የራሱ የሆነ እና ነባሩን
የፖለቲካ አቅጣጫ ሊተካ የሚችል የተደራጀ መስመር ይዞ አልመጣም፡፡ በሌላ በኩል ነባሩ የልማታዊ መንግስት መስመር
እንዳይቀጥል በመደመር ፖለቲካ እየተሸረሸረ ነው፡፡ በእርግጥም ለውጡ ምን አንደሆነ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡
ሁለተኛ ከተግባራዊ ውጤቱ አንፃር የመደመር ፖለቲካ ለውጥ በነውጥ እየተተካ መሆኑ ሌላኛው አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡
የመደመር ፖለቲካ በአገሪቱ የሚገኙ የፖለቲካ ሃይሎችን የተደመረና ያልተደመረ በሚል ድብቅ ስሌት የሚከፋፍል በመሆኑ
ብዙሀንነትን ማስተናገድ አልቻለም፡፡ የመደመር ፖለቲካ ትልቁ የፖለቲካ አቅም የጠራ መስመር ሳይሆን የመንጋ ድጋፍ
ሆኖ ቀጥለዋል፡፡ በዚህ የተነሳ ከጀርባው ያለውን መንጋ ድጋፍ ለማግኘት ተግባራዊ ሊሆኑ በማይችሉ ነገር ግን
በሚያማልሉ አጀንዳዎችን በማራገብ ተወጠረ፡፡ ፍቅር... አንድነት.... መደመር ወዘተ የሚሉ ቃላቶች አሸዋ ላይ
የመገንባት ስራ ቀጠለ። ከልማት ፣ ዴሞክራሲ እና ከሰላምም አንፃር አንደሚፈለገው ለውጥ ማምጣት አልቻለም ብቻ
ሳይሆን በየቀኑ በሚባል ደረጃ የሞትና እንግልት ዜና መውጣት ቀጠለ፡፡ ይህ ጉዳይ አሳሳቢ የምያደርገው ደግሞ ጉዳዩን
በጥልቀት ማየት እየተገባ "ኤክስተርናላይዝ" የማደርጉ ጉዳይ ነው። በመሆኑም በአገሪቱ የህግ የበላይነት ተሸርሽሮ ስርዓት
አልበኝነት ሰፈነ፡፡ እዚህም እዛም ዜጎች በብሔራቸው የመንጋ ጥቃት ሰለባ ሲሆኑ ከዚህ የተረፉት ስርዓቱ እየተከታተለ
ያድናቸው ጀመር፡፡ በተግባር በአገሪቱ እየታዬ ያለው የእርስ በእርስ ግጭቶችና የህግ ጥሰቶች ከተግባር አንፃር የመደመር
ፖለቲካ ከፖለቲካ ለውጥ ወደ ነውጥ መቀየሩ መደመር የተሳሳተ ስሌት እንደሆነ መታየት ጀመረ፡፡

2. መደመር ወይስ መከባበር?

----------------

ከላይ ለማሳየት አንደተሞከረው የመደመር ፖለቲካ ከንድፈ-አሳብም በተግባርም አንፃር የተሳሳተ ስሌት አንደሆነ እየታዬ
ነው፡፡ ከንድፈ-አሳብ አንፃር የመደመር ፖለቲካ አዲስም አሮጌም የፖለቲካ መስመር አይደለም፡፡ ከተግባር አንፃር ከታየም
የመደመር ፖለቲካ የአገሪቱን የልማትና የሰላም ችግሮች ከማባበስ ውጪ የፈየደው ነገር የለም፡፡ ስለዚህ በመርህ ደረጃ
ችግር አለበት ማለት ነው፡፡ የመርሁ ችግር የሚነሳው መርሁ የሚሰራው ለተደመረ መሆኑ ነው፡፡ ያልተደመረ ምን ይሁን
የሚለው ጥያቄ የሚመለሰው በመቀነስ ነው፡፡ የተደመረው ይጨፈለቃል፡፡ ያልተደመረው ተቀንሶ አንዲገለል ይደረጋል፡፡
በዚህ የተነሳ መደመር ብዙሀንነትን የማስተናገድ ብቃት ስሌለው የብዙ ብሔር-ብሔረሰቦች እና ህዝቦች አገር ለሆነችው
ኢትዮጵያ የሚያዋጣ መርህ ሆኖ አልተገኘም፡፡ ብዙሀንነትን በብቃት ማስተናገድ ያልቻለ የፖለቲካ መርህ ደግሞ ውድቀቱ
የሚገለፀው በእርስ-እርስ ግጭትና በሰላም መደፍረስ ነው፡፡ ስለዚህ ሌላ የተሻለ የፖለቲካ አማራጭ ያስፈልጋል ማለት
ነው፡፡ ስለዚህ የተሻለው አማራጭ ምንድን ነው?

3. መከባበር

---------------

አዲሱ የዶር አብይ አስተዳደርና ዶር ደብረፅዮን የሚመሯት የትግራይ ክልል በአንድ አገር የሚገኙ ቢሆኑም የሚከተሉት
የፖለቲካ መርህ ግን ተመሳሳይ ነው ማለት አይቻልም፡፡ የዶር አብይ አስተዳደር የሚከተለው የፖለቲካ መርህ "መደመር"
የሚባል መጤ አካሄድን ነው፡፡ በአንፃሩ የዶር ደብረፅዮን የፖለቲካ መርህ "መከባበር" የሚባለውን የፖለቲካ መርህ ነው፡፡
ዶር ደብረፅዮን "መከባበር" እንደ ፖለቲካ መርህ መከተላቸውን ለማረጋገጥ በአንድ ወቅት "መከባበር ወይም መበታተን"
በሚል ከሰጡት አሳብ መነሳት አንችላለን፡፡ ይሁንና ይህን የዶሩን መርህ በተሳሳተ ስሜት የተረዱ በርካታ ሰዎች ነበሩ፡፡
በተጨባጭ እየታዬ ያለው ግን የመደመር ፖለቲካ በፖለቲካ ትርምስ ሲናጥ የመከባበር ፖለቲካን የሚከተለው የደብረፅዮን
አመራር በትግራይ ክልል አስተማማኝ ሰላም መፍጠሩ ነው፡፡

በእርግጥም የዶር ደብረፅዮን የመከባበር አማራጭ ውጤቱ አመርቂ እየሆነ ነው፡፡ ከልማት አንፃር በክልሉ የተጀመሩት
የልማት ስራዎች ሳይቋረጡ ተጠናክረው አንደቀጠሉ ነው፡፡ መከባበር በባህሪው ልዩነትን የማስተናገድ ባህሪ አለው፡፡
ምክንያቱም መከባበር ያስፈለገው ልዩነት ስላለው ነው፡፡ አንድ የሆነ አይከባበርም፡፡ ከዚህ አንፃር የክልሉን ሰላም እና
መረጋጋት ለማስቀጠል የጎላ አስተዋፅኦ አለው፡፡

ከዴሞክራሲ አንፃርም ቢሆን የመከባበር መርህ በትግራይ ክልል ሁሉም ሰዎች ያለምንም የብሔር የሀይማኖትና የፆታ
ልዩነት በእኩልነት የሚታዩበትን ሁኔታ እየፈጠረ ነው፡፡ አንደሌሎቹ የአገሪቷ አካባቢዎች በትግራይ ክልል በብሔሩ የተገደለ
ሰው የለም፡፡ (የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ አንደታዘበው በትግራይ ክልል ከአካባቢው ተወላጆች በላይ የሌላ ብሔር ተወላጆች ልዩ
አንክብካቤ ይደረግላቸዋል፡፡) እውነትም የትግራይ ክልል ሰላም ዋናው መሰረት መከባበር ነው፡፡

ከምንም በላይ የመከባበር መርህ በትግራይ ክልል ስርዓትና የህግ የበላይነት አንዲከበር አድርጓል፡፡ በአሁኑ ወቅት የትግራይ
ህዝብ እና አስተዳደር ህግና ስርዓትን እያከበረ መሆኑን በተግባር እያስመሰከረ ነው፡፡ ስርዓት ማክበር ህግና መመሪያዎችን
በትክክል ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ከተወሰደ በአገሪቱ የሚወጡት ህጎችና መመሪያዎች መቶ በመቶ በሚባል
ደረጃ ተግባራዊ የሚሆኑት በትግራይ ክልል ውስጥ ነው፡፡በትግራይ የህግ የበላይነት እየተከበረ ነው፡፡ በትግራይ የኤኮኖሚ
ስርዓቱ አንደነበረ ነው፡፡ ለአብነት ያህል ባሳለፍነው አመት ከሌሎች ክልሎች በተሻለ መልኩ የግብር ስርዓቱ ተግባራዊ
እየተደረገ ያለው (ብዙ ግብር የተሰበሰበው) በትግራይ ክልል ነው፡፡ የትምህርትና የጤና ስርዓት ሳይደናቀፍ እንደቀጠለ
ነው፡፡

ሌላው ቀርቶ በትግራይ ክልል ህዝብ የሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ሲጋራ ማጨስ የሚከለክለው ህግ ተከብሮ ተግባራዊ
እየሆነ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር በአመራር ደረጃ የሚከተለው የመከባበር ፖለቲካዊ መርህ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል
ለተፈጠረው አስተማማኝ ሰላም የራሱ ድርሻ አንዳለው መውሰድ አንችላለን ማለት ነው፡፡ ዛሬ ላይ ትግራይንና ሌላውን
የአገሪቱ ክፍሎች ያለውን ሁኔታ በንፅፅር ከወሰድን በእርግጥም ከአብይ አስተዳደር የመደመር መርህ በላይ የዶር ደብፅዮን
የመከባበር መርህ እያሸነፈ መምጣቱን የሚያመላክት ነው፡፡

ከድወአ fb ገፅ የተወሰደ

You might also like