You are on page 1of 1

↪''እውነተኛ ታሪክ ✅

አንድ #የቆሎ__ተማሪ ነበር ይህ ተማሪ ከሌሎች እሱን መሰል ተማሪዎች የሚለየው ስለ ማርያም ስለ እመብርሃን ብሎ
ከለመነ በኋላ ያገሬው ሰው ሲሰጡት

" ♥ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ♥"

ብሎ መርቆ ይሄዳል፡፡

እናም ይህ የቆሎ ተማሪ ትምህርቱን እየተማረ የተዘከሩትንም '♥ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ' ♥

እያለ ሲኖር ባንድወቅት ወደ አንዷ ሴትዮ ቤት ገብቶ "ስለ ማርያም ስለ ወላዲተ አምላክ ተዘከሩኝ" ብሎ ሲለምን የቤቱ
ባለቤት ቁራሽ እንጀራ አውጥታ ተዘከረችው እሱም የለመደው ነውና

↩ "ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ" ↩ብሎ መርቆ ይሄዳል በዚህ ግዜ ሴትዮዋ "እንዴት ስዘከረው እግዚአብሔር ይስጥልኝ
ብሎ መመረቅ ሲገባው

♥ 'ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ' ይለኛል" ብላ ትናደዳለች፡፡ "እንዲህ ከሆነማ ጥሩ ብላ ነገ ሲመጣ አሳየዋለሁ" ብላ
ትፎክርበታለች በነገታውም ወደ አመሻሹ ለእራት የሚሆነውን ሊለምን ወደ መንደሮቹ እንደለመደው "ስለ ማርያም"
እያለ ሲሄድ ሴትዮዋም በጎማ ጠላ አዘጋጅታ ጠላው ውስጥ መርዝ ጨምራ ጠበቀችው ተማሪውም እሷ ቤት እንደደረሰ
ስለ ማርያም ስለ እመብርሃን ብሎ ደምፁን እንዳሰማት ወዲያውኑ ያዘጋጀችውን ጠላ የያዘውን ጎማ አውጥታ ሰጠችውና
ከዛው ቁጭ ብሎ ከጠጣው መርዙ ሊገለው ስለሚችል "በል እዚህ ቁጭ ብለህ ከጠጣኸው ስለሚመሽብህ ከቤትህ ሄደህ
አረፍ እንዳልክ ጠጣት፡፡ እንዴት ያለች ጠላ መሰለችህ" ብላ ትልከዋለች፡፡ "እሱም ♥ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ♥" ብሏት
ይሄዳል "እስኪ ደግም ሆነ ክፋት ለራስ ከሆነ እናያለን"

ብላ በውስጧ ሞቱን አስባ ተሳለቀችበት፡፡ እሱም የተዘከሩትን ምግብም ሆነ መጠጥ ይዞ ወደ ማደርያው ጉዞውን ጀመረ
በመንገድ ላይ የሴትዮዋ ልጆች በረሃ ቆይተው በጣም ደከሟቸው ከተማሪው ጋር ተገናኙ ወደ ተማሪው ቀረብ ብለው
"እባክህን በርሃ ቆይተን በጣም ደክሞን መግባታችን ነውና እቤት እስክንደርስ የውሃ ጥማችንን ቢያስታግስልን ከያዝከው
መጠጥ ትንሽም ቢሆን አጠጣን" ብለው ሲለምኑት "እኔም ለምኜው ነው ደግነትም ለራስ ነው" ብሎ ከያዘት ጎማ
እንዲጠጡ ፈቀደላቸው ሁለቱም ልጆች ከጎማዋ እንደጠጡ ወደያው ይሞታሉ ይህን ጊዜ እሪታው ቀልጦ ⚂የመንደሩ ሰው
በሙሉ ይሰበሰቡና ግማሹ ዱላ ይዞ ደብድበን ካልገደልነው

⚂ገሚሱም በድንጋይ መወገር አለበት

⚂የተቀሩት ደግሞ ለህግ መቅረብ አለበት ሲባባሉ ሴትዮዋ የመንደሩን ግርግር ሰምታ ስትመጣ ሁለቱም ልጆቿ ሞተው
መርዝ ከጠላ ጋር ቀላቅላ የሰጠችውም ተማሪ ሰዎች እያመናጨቁ ይዘውት ወደ ህግ እናቅርበው ብለው ሲወስዱት
ታያለች ይሄኔ ነበር♥ 'ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ'♥ የሚለው ነገሩ ትዝ ያላት ሴትዮዋም "በሉ የያዛችሁትን ተማሪ
ልቀቁት የዚህ ሁሉ ችግር ምክንያት እኔው እራሴው ነኝ" በማለት የሆነውን ነገር ሁሉ ተናግራ "በገዛ ክፋቴ የገዛ ልጆቼን
የገደልኩት እኔው እራሴው ነኝ እናም ይሄ ሰው ንፁህ ሰው ነው ልቀቁት" ብላ እራሷን ለህግ ሰጠች፡፡

እውነትም ደግም ሆነ ክፉ መሆን ለራስ ነው ክፉ መሆን በቅድሚያ የሚጎዳው እራስን ነውና ደግ እንሁን ከደግነት በላይ
መልካም ነገር የለምና የዛሬው መለክታችን ነው፡፡

You might also like