You are on page 1of 2

የ2012 ዓ.

ም የ3ኛ ሩብ ዓመት ለ9ኛ ክፍል የተዘጋጀ አጭር የዕለት


ት/ት

 ውድ ተማሪዎች፡- ይህን ማስታወሻ በደብተራችሁ ከገለበጣችሁ በኋላ መልመጃዎችን ስሩ፡፡

ወር ፡- መጋቢት 28/2012 ዓ.ም


የትምህርት ዓይነት፡- አማርኛ ለ9ኛ A- F ክፍል
ምዕራፍ፡- 7
ርዕስ ፡- ስነ-ፅሁፍ
ንዑስ ርዕስ ፡- ምሳሌኣዊ አነጋገር

ሰኞ 28/2012 ዓ/ም
 ምሳሌአዊ አነጋገሮች ለአንድ ቋንቋ ለዛ ይሰጣሉ ተብለው ከሚጠቀሱ መካከል የሚገኙ ሲሆኑ በሚገባን እና በተመረጡ
የቃላት አጠቃቀሞች መሰረት ጠንከር ያሉ እና የተለዩ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ የምንጠቀምባቸው የስነ-ፅሁፍ
ዘርፎች ናቸው፡፡
 የቋንቋ ለዛ ሰጭ የሚባሉት ምሳሌአዊ አነገጋሮች፣ ፈሊጣዊ አነገጋገሮች እና ዘይቤአዊ አገላለፆች ናቸው፡፡
ምሳሌ፡- የመተባበርን አስፈላጊነት የሚያስተምሩ ምሳሌአዊ አነጋገሮች
- ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
- በአንድ እጅ አይጨበጨብም
- አንዱ አይነድ አንዱ አይፈርዱ
- ከላይ በምሳሌው በተሰጣችሁ አቅጣጫዎች መሰረት የሚከተሉትን ጥያቄዎች አንብቡ እና በአጠያየቃቸው
መሰረት መልስ ስጭ/ስጥ፡፡
1. ስንፍናን የሚወቅሱ ታታሪን የሚሞግሱ ም/አነጋገሮች(2) ጥቀሱ፡፡
2. የችኮላን ጎጅነት የማስተዋልን ጠቃሚነት የሚያሳዩ ም/አነጋገሮች(3) ጥቀሱ፡፡
3. ጀግንነትን የሚሞግሱ ፈሪን የሚነቅፉ ም/አነጋገሮች በዓ/ነገር ግለፁ፡፡
4. አስነዋሪ ባህሪያቶችን የሚቃወሙ፣ መልካም ስነ-ምግባርን የሚደግፉ ምሳሌአዊ አነጋገሮችን በዓ/ነገር አደረጅታችሁ
ግለፁ፡፡
5. የሚጠነቀቅና አስፈላጊነትን የሚመክሩ ም/አነጋገሮች ግለፁ፡፡

ያዘጋጀው፡- መምህር መሰረት ብ. ያረጋገጠው፡- አቶ ይመር ዳምጤ ገፅ 1


ማክሰኞ 29/2012 ዓ/ም

የምዕራፍ ማጠቃሊያ
 በምዕራፍ ሰባት ስር የቀረበው ትምህርት አከባቢን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ መስጠትን፣ ከንግግር ፅሁፍ
ማስታወሻ መያዝን፣ አስተዋፅኦ ነድፎ አስረጂ ድርሰት ማፃፍን ያጠቃልላል፡፡
 በክፍል አንድ በንባብ የቀረቡልንን ሀሳቦች ዋና እና መሪ የሚባሉትን ነጥቦች እንዴት መለየት እንዳለብን አይተናል፡፡
 በክፍል ሁለት ላይ ጠብቀው እና ላልተው ሲነበቡ የፍቺ ልዩነት የሚያመጡ ቃላትን ተመልክተናል፡፡
 በክፍል ሶስት የአስረጂ ድርሰት አፃፃፍ ስልቶችን አይተናል፡፡
 በክፍል አራት አስረጂ ድርሰትን ጨምሮ የቃል ክፍል ምድቦችን ተመልክተናል እንዲሁም በመጨረሸ የንሳሌአዊ
አነጋገሮችን ምንነት፣ ተግባር እና አገባብ አይተናል፡፡
ከእነዚህ ገለፃዎች በመነሳት የሚከተሉትን የምዕራፍ ማጠቃሊያ ጥያቄዎችን በደብተራችሁ ስሩ፡፡
ገፅ 13 የክለሳ ጥያቄዎች ከ1 - 5

You might also like