You are on page 1of 1

ኦሜጋ ትምህርት ቤት

OMEGA SCHOOL

የተማሪ ስም : __________________ የት/አይነት : አማርኛ


ክፍል: 9 ምደባ (ሴክሽን) :_____ መንፈቀ ዓመት : 1 ኛ መለማመጃ ጥያቄ-1
ቁጥር: ______ ቀን: ጥቅምት 2016 ዓ.ም

መመሪያ 1 ፡- የሚከተሉት ጥያቄዎች የያዙት ሀሳብ ትክክል ከሆነ “እውነት” ትክክል ካልሆነ ደግሞ
“ሀሰት” በማለት መልሱን መልስ መስጫው ላይ ጻፍ/ጻፊ፡፡
_________1. ቋንቋ ሰብዓዊ መግባቢያ ነው፡፡
_________2. መልዕክትን ማስተላለፍ የቋንቋ ማህበራዊ ተግባርን ያመለክታል፡፡
_________3. እንስሳት የሚግባቡት በተራ ጩኸት እንጂ በቋንቋ አይደለም፡፡
_________4. ዘዬ የቋንቋው ተናጋሪዎች እንዳይግባቡ ያግዳቸዋል፡፡
_________5. ቋንቋ የተናጋሪውን ማንነት የሚያመለክትበት አጋጣሚ አለ፡፡
_________6. ውይይት ችግር ፈቺ የሀሳብ መለዋወጫ ስልት ነው፡፡
መመሪያ 2፡- በ”ሀ” ምድብ ለሚገኙት የቋንቋ ባህርያት ማብራሪያዎች ከ”ለ” ምድብ የሚስማማቸውን
በመፈለግና በማዛመድ መልሱን በተዘጋጀው ቦታ ላይ ጻፍ/ጻፊ፡፡
ሀ ለ
_________7. ሁሉም ቋንቋዎች የተናጋሪያቸውን ባህል በተሟላ ሁኔታ ይገልፃሉ ሀ. ረቂቅነት
_________8. ተወካዩ በሌበት አውድ በቃላት መግለጽ (መረዳት) ለ. ሰብዓዊነት
_________9. የሰዎች ብቻ መግባቢያ መሆኑ ሐ. ዘፈቀዳዊነት
_________10. ድምጾችን ወይም አገላለጾችን ከሌላ ቋንቋ መውሰድ መ. ውሰት
_________11. በመጀመሪያ ለነገሮች የተሰጠው ስያሜ በአጋጣሚየሆነ ነው ሠ. ምሉዕነት
_________12. በተናጋሪዎቹ አኗኗር ለውጥ ምክንያት አዳዲስ ቃላት ሲፈጠሩ ረ. የቋንቋ ዕድገት
ሰ. የቋንቋ መወለድ
መመሪያ 3 ፡- ከዚህ ቀጥሎ ለቀረቡት ጥያቄዎች በተዘጋጀው ቦታ ላይ አጭር መልስ ጻፍ/ጻፊ፡፡
13. ከውይይት አቀራረብ መመሪያ አንዱ __________________________ ነው፡፡
14. የቋንቋ ማህበራዊ አገልግሎት _________________ን ያመለክታል፡፡
15. አንድ ቋንቋ በሌላ ቋንቋ ሲዋጥ ምን ይከሰታል? _________________

You might also like