You are on page 1of 3

የንግግር እና የቋንቋ መዘግየት /speech and language delay

በመጀመሪያ የንግግር እና የቋንቋ መዘግየት ያላቸው ልዩነቶች ብናይ ጥሩ ነው


 የንግግር መዘግየት ስንል፡-
 ይህ ማለት የቋንቋ መገለጫ ሲሆን የአርቲኩሌሽን ችግርንም ያካትታል
 ይህ ችግር ያለባቸው ልጆች ቃላትን ሊሉ ይፈልጋሉ ነገር ግን ለሌሎች ሰዎች ብዙም
የማይገቡ ወይም ለመረዳት የሚያስቸግሩ ናቸው ወይም ቃላትን ይረዳሉ ነገር ግን ቃላቶችን
በትክክል ለማውጣት ሲቸገሩ ነው፡፡
 ይህ ችግር ከአካላዊ ጉዳት ጋር ወይም ከአፍ ፣ ከምላስ ወይም ከላንቃ ችግሮች ጋር የተያያዘ
ሊሆን ይችላል ለምሳሌ፡- የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ለዚህ ችግር ያጋልጣል ወይም
ለንግግር ከሚጠቅመው የአንጎል ክፍል ጉዳት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል፡፡
 የቋንቋ መዘግየት የምንለው ደግሞ
 የቋንቋ መዘግየት አንድ ልጅ የንግግር ቋንቋን በተገቢው መንገድ ሣይረዳ ሲቀር ወይም
መናገር ሳይችል ሲቀር ማለት ነው፡፡
 ልጆች ቃላቶች ለማውጣት ከሌሎች ቃላቶች ጋር በማየያያዝ ትርጉም ያለው አረፍተነገር
ለመስራት ሲቸገሩ ነው ይህ ችግር በተለያየ መልኩ ሊገለፅ ይችላል ለምሳሌ ፡-
 የመጀመሪያውን ቃል ለማውጣት መዘግየት/
 ሁለት ቃላትን አያይዞ ለመናገር መዘግየት
 የቃለት ትረጉሞችን የመርዳት ችግር
 የቋንቋ መዘግየት ከሌሎች ችገሮች ጋር ማለትም ከኦቲዚም ሰፔክትረም ዲሶረድረ ጋር ፣ከዳውን
ሲንደርም ጋር በተጎዳኝነት ሊከሰት ይችላል፡፡
 ልጆች በእድሚያቸው መናገር የሚጠበቅባቸውቃላት ከታች ተዘርዝርዋል
 12 ወር -2 to 6 (ከአባባ እና ከማማ ውጭ)
 15 ወር -10 ቃላት
 18 ወር- 50 ቃላት
 24 ወር -200-300 ቃላት
 36 ወር -1000 ቃላት

 የንግግር እና የቋንቋ መዘግየት መቼ ነው አሳሳቢ የሚሆነው


 ልጆቾዎን ከሌሎች ልጆች ጋር በማወዳደር ችግሩን ለመረዳት መሞከር የለብወተም ነገር
ግን የሚከተሉትን ምልክቶች ልጆቾዎ ላይ ካዩ በቶሎ ወደ ህፃናት ሀኪም ወይም ወደ
ንግግር ሀኪም መውሰድ ይመከራል፡፡
1. ልጆች በአንድ አመታቸው
 ከእርስዎ ጋር/ ከወላጆች ጋር ለመግባባት የማይሞክሩ ከሆነ ማለትም የሚፈልጉትን ነገር
በምልክትም ሆነ በድምፅ መግለፅ የማይችሉ ከሆነ ለምሳሌ፡-
 የተገደቡ የእጅ ወይም የምልክት ቋንቋዎችን መጠቀም ለምሳሌ በ 12 ወራቸው
ቻው ቻው በምልክት ስንላቸው መልሰው የማይሉ ከሆነ
 ምንም አይነት ድምፅ የማያወጡ ከሁነ
2. ልጆች በሁለት አመታቸው፡-
 በዚህ ዕድሜ ቢያንስ 50 ቃላትን ማለት አለባቸው ፣ይህን ያህል ቃላትን ማላት ካልቻሉ
 ሁለት ቃላቶችን አያይዘው መናገር ካልቻሉ ለምሳሌ፡- ውሃ ስጭኝ ካላሉ
 በራሳቸው ተነሳሽነት ቃሎችን የማይናገሩ ከሆነ ወይም የተባለላቸውን ቃላት ብቻ
የሚደግሙ ከሆነ
 የሚባሉትን ነገር ወይም ሲታዘዙ የመረዳት ችግር ካለባቸው
 ጥናቶች እንደሚያሳዩት በዚህ ዕድሜ ካሉ ልጆች ላይ ከ 5 ልጆች ውስጥ በአንዱ ላይ የቋንቋ
መዘግየት ይታያል፡፡

3. 3yr/ ሶስት አመት ላይ፡-


 በዚህ ዕድሜ ደግሞ ሁለት እና ከዚያ በላይ ቃላቶችን አያይዘው ማለት ካልቻሉ
 ትዕዛዝ ሲታዘዙ ወይም ጥያቄ ሲጠየቁ የማይገባቸው ከሆነ
 መፅሀፍ ወይም ስዕሎችን ለማየት ፍላጎት ከሌላቸው
 ጥያቄ ሲጠየቁ የማይመልሱ ከሆነ
 ስሞችን የመሰየም ወይም የመጥራት እክል ካለባቸው
 ከሌሎች ጋር ለመግባባት የሚቸገሩ ከሆነ
 የቋንቋ መዘግየት ያለባቸው ልጆች፡-
 አዳዲስ ቃሎችን ለመልመድ ይቸገራሉ
 አጫጭር አረፍተነገሮች መጠቀም ያዘወትራሉ
 ከታዘዙት ነገር ከፊሉን ብቻ ይተገብራሉ
 የቃሎችን ትርጉም ለመረዳት ይቸገራሉ
 ለተለያዩ የባህሪ ፣ የማህበራዊ እና የስነ ልቦና ችግሮች የተጋለጡ ይሆናሉ
 የትምህርት አቀባበል ችሎታቸው ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል
 ከሌሎች ልጆች ጋር ለመግባባት ይቸገራሉ
 እራሳቸውን ለመግለፅ ይቸገራሉ
ይህ ችግር በልጆችዎ ላይ ከተስተዋለ የሚከተሉትን ነገሮች ሊያደርጉ ይችላሉ
1/ወላጆች ልጆቻቸው ከተውለዱ ጀምሮ ይህ ችግር እንዳይከሰት በተቻለ መጠን ልጆቻቸውን
ማዋራት ፣ለልጆቻቸው መፅሀፍ ማንበብ፣በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ልጆቻቸው እንዲያወሩ
ማበርታታት አለባቸው፡፡

2/ልጆዎ የመስማት ችግር እንደሌለበት ማረጋገጥ ያስፈልጋል

3/በአቅራቢያ ካለው የህፃናት ሀኪም ወይም የንግግር ባለሙያ ማማከር ያስፈልጋል

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0936621689 ይደውሉ

ዶ/ር ሀድያ ይማም የህፃናት ህክምና ሰፔሻሊስት

You might also like