You are on page 1of 2

ውጤታማ ፆምና ጸሎት

ዓላማ፡- የጾምና ጸሎትን ትክክለኛ ትርጉም ለማስታወቅና የቤተ ክ/ን አገልጋዮችን


በጸሎት ህይወት ለማስታጠቅ ነዉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንድንጸልይ ያበረታታናል፡፡
ኤር33፡3. ማቴ 6፡5-18. ሮሜ 15፡30. ያዕ5፡13. ቆላ 4፡2. 2ዜና 7፡14. ፍልጵ
4፡6

1. ፆም ማለት ለመንፈሳዊ ምክንያት መሰረታዊ የስጋ ፍላጎቶቻችንን ለተወሰነ ጊዜ


ማቆም ማለት ነዉ፡፡ ምግብና ውሃ (ዘዳ9፡19) ማቆም፤ ስለታጣ መራብ
አይደለም. የግብረ ስጋ ግንኙነትንም (ለባለትዳር) ማቆም ነው1ቆሮ7፡14 ማቅ
ለብሰዉ አመድ ነስንሰው ጌጥ ማውለቅ እራስን ማዋረድ ነው
(አለባበስ)ማቴ11፡21፤ 2ነገ6፡26-31 ዉርደታቸዉን በጾምና ጸሎት ቀየሩት፤
ዮናስ 3፡1-10. የከተማ መገልበጥ መጥፋት የተቀየረው በዚህ ሁኔታ ነበር ፤
አስቴር ቤተሰቧንና ህዝቧን ያተረፈችዉ በጾምና ጸሎት ነበር፡፡ አስ 4፡16 ፤ዘጸ
33፡5-6. የጌታን ክብር ለማየት ጌጣቸዉን መቀየር አስፈለጋቸው፡፡ ነህ 1፡1-4
የሀገሩን ሁኔታ ጠየቀ ሰማ አዘነ ጾመ ጸለየ እግዚ/ርም ረዳው፡፡ ነህ 2፡8፣ 17-
18፣ ንጉሱም፤ ህዝቡም ተባበሩት የጠላትም ምክር ከንቱ ሆነ ነህ 4፡15
በ52በቀናት ውስጥ ቅጥሩ አለቀ 6፡15 ከዚህ በኃላ ነበር ዕዝራ መጥቶ
መንፈሳዊውን ጥገና የጀመረው፡፡ ም 8- ንጉስ ዳዊት በጣም ይጾምና ይጸልይ
ነበር መዝ35፡12-15 ፤69፡10፤ 102፡4፤ 109፡24፤ 2ሳሙ1፡11-12 ሳኦል
በሞተ ጊዜ ዳዊት ቀኑን ሙሉ ጾመ አለቀሰ፡፡ የጾም ሰዎች ሁሌ ይበረታሉ
በሄዱበት ቦታ ሁሉ ድል ያገኛሉ 2ሳሙ8፡6 ኤልያስ 2ነገ 19፡6-7 የጾም ሰው
ነበር፡፡ ታርክን የቀየረ ጌታን ያስከበረ ሰው ነበር፡፡ ዳንኤል ይፆምና ይጸልይ ነበር
ዳን 9፡3 ፤ 10፡2-3 ጾም ቀንበርን መስበርያ ነዉ፡፡ አስቴር 4፡16 ጠላትን
ማዋረጃ ነዉ፡፡ አከአብ 1ነገ20፡17-29 ትሞታለህ በተባለ ጊዜ እራሱን አዋረደ
ጾመ ቅስስ ብሎ ሄደ ሞቱን አስቀየረ፡፡ ኢዮሳፍጥና ይሁዳ 2ዜና20፡1- በተከበቡ
ጊዜ ጾሙ አለቀሱ እግዚ/ር ፊት ዝቅ አሉ ጌታም ከበባቸዉን ሰበረ
ጠላቶቻቸዉን እርስ በርስ አፋጀ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ሞታቸዉን ቀይረዋል፡፡
ለሌሎች ማካፈልን የምንለማመድበት ጊዜ ነው፡(ምሳህን ለድሃ ስጥና ጹም )
የእግዚ/ር ፍርድ ታሳልፋለህ ኢሳ 58፡ 6-12

ጾም በአዲስ ኪዳን፡ ማቴ6፡16-18 ስትጦሙም እንደ ግብዝ አትሁኑ ይላል፡፡ሉቃ


5፡33-35 ሙሽራው በአካል ከነሱ ሲወሰድ ይጦማሉ፡፡ ኢየሱስ እኛን ወክሎ
ሞቶልናል እኛ መሞት አይገባንም ሌሎች ነገሮችን ግን ጾምን ጨምሮ እርሱ
ያደረገውን እኛም እንድናደርግ ይጠበቅብናል፡፡ ዮሐ 14፡12. ሉቃ 4፡2፤14
ሐዋርያት የጦሙና ይፀልዩ ነበር፡፡ የሐዋ 13፡ 1- 2 ፤10፡30- ቆርኔሌዎስም
ይጦም ይጸልይና ምጽዋት ያደርግ ነበር ቁ44 ጾም የጌታን ጉብኝት ያመጣል፡፡
የሐዋ14፡23፤ ጾመዉ ጸልየዉ ለጌታ አደራ ሰጡአቸዉ ይላል፡፡ 2ቆሮ 6፡6 ጳዉሎስ
በመጦም አሳለፍኩ ይላል፡፡ 1ቆሮ7፡5 በእንግሊዝኛዉ ለጾምና ለጸሎት ካልሆነ
በስተቀር ይላል፡፡ ኢሳ 58፡8- የዝያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፡፡

2. ጸሎት ማለት ምን ማለት አይደለም? - ማቴ 6፡5-8 እንደተለያዩ የሐይማኖት


ሰዎች ዝም ብሎ መጸለይ አይደለም ፤ ግብዝነትም አይደለም ማቴ 6፡5 ግብዝ
በግዕዝ nipocrat ማለት አስመሳይ ትያትረኛ ማለት ነዉ
- ተንበርክኮ መተከዝ ወይም ዝም ብሎ ማልቀስ ማለት አይደለም
- በሆነ ቦታ ብቻ ተገድቦ የሚደረግ ስርዓትም አይደለም ቁ5
- በከንቱ መደጋገምና የመናገር ብዛትም አይደልም ቁ7
- እግዚአብሔር የማያዉቀውን የማስረዳትና የማሳመን ጉዳይም አይደልም ቁ8
3. ጸሎት ማለት ምን ማለት ነው? ፀሎት ማለት - ከምወደንና ከምያፈቅረን
ከአባታችን ከእግዚአብሔር ጋር በክርስቶስ በኩል የፍቅር ህብረት ማድረግ ማለት
ነው፡፡ 1ቆሮ 1፡9፤ 2ቆሮ13፡14፤ 1ዮሐ1፡3 አብሮ በመሆን በመስማትና
ማዉራት ፍቅርን፤ ጸጋን የምንካፈልበት ህብረት ነው፡፡ ጸሎት እግዚአብሔራዊ
ፍቅር ነው፡፡
- ያዕ 5፡16 ትፈወሱ ዘንድ እያንዳንዱ ስለሌላው ይጸልይ፤ የመፈወሻ መሳርያና
ሐይል ነው፡፡ ጸሎት አገልግሎት ነው፡፡
- ጸሎት እድልና የመንፈሳዊ ህይወታችን የመተንፈሻ ስርዓት ነዉ፡፡
- የዲያብሎስን መንግስት ቀውስ ውስጥ የሚከት አደገኛ መሳርያ ነው፡፡
- ጸሎት ወደ እግዚ/ር ልብ ውስጥ መግቢያ መንገድ ነው፡፡
-

You might also like