You are on page 1of 3

ርኆቦት ወተት እና የወተት ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ እና ማምረቻ ኃ. የተ. የግ. ማ.

Rihobot Dairy farming and Milk processing plc


የኮንትራት ሠራተኛ ቅጥር ውል

ውል ሰጭ /አሰሪው/፡- ርኆቦት ወተት እና የወተት ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ እና ማምረቻ ኃላ.የተ. የግ. ማ.

አድራሻ አረርቲ ከተማ ቀበሌ 04 ስልክ………………………………….


የውል ተቀባይ/ሰራተኛው ስም፡-----------------------------------------------ጾታ--------ዕድሜ-------
አድራሻ---------------------የስልክ ቁጥር………………የት/ደረጃ-----------------የሰለጠነበት
ሙያ---------------------------------የስራ መደብ---------------------------------------------------------------
እኛ ስም እና አድራሻችን ከላይ ከፍ ብሎ የተገለፅነው ከዚህ በታች "አሰሪ" እና "ሠራተኛ" እየተባልን የምንጠራው ተዋዋይ ወገኖች በነፃ እና
በሙሉ ፈቃዳችን ፈቅደን እና ወደን በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 የተደነገጉ መብትና ግዴታዎቻችን እንደተጠበቁ ሆነው የሚከተለውን
የህብረት ስምምነት የሥራ ቅጥር ውል ተፈራርመናል፡፡

የውሉ አላማ

በአረርቲ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ርኆቦት ወተት እና የወተት ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ እና ማምረቻ ኃላ.የተ. የግ. ማ.
በ…………………………………የስራ መደብ ውል ተቀባይን የድርጅቱ ሰራተኛ አድርጎ መቅጠር ነው፡፡
የአሰሪው መብትና ግዴታ
መብት
1. ለሰራተኛው በተስማማው ስምምነት መሰረት ስምሪት መስጠት ይችላል
2. ሰራተኛው ለሰራበት የወር ክፍያ በስምምነቱ መሰራት መክፈል ይችላል
4. ስለ ሰራተኛው አስፈላጊው መረጃ የመያዝ ህጋዊ ጥያቄ ላለው 3 ኛ ወገን ህጋዊ መረጃ የመስጠት መብት አለው
5. ከሰራኛው ለሚቀርብ የመልቀቂያ ጥያቄ በስምምነቱ መሰረት የማስተናገድ መብት አለው
6. በትርፍ ሰዓት የሚሰራ ስራ ካለው የማሰራት መብት አለው
የአሰሪው ግዴታ
1. በቀጣሪው በስምምነቱ መሰረት ሰራተኛው ለሰራበት ጊዜ በውሉ ላይ የተገለጸውን ደመወዝ ፣ጥቅማ ጥቅም የመክፈል
ግዴቴ አለበት
2. በውሉ መሰረት ለሰራተኛው ስራውን ቆጥሮ የመስጠት ግዴታ አለበት
3. በስራ ላይ እያሉ ጉዳት ለሚያጋጥማቸው ሰራተኞች ለሚደርስባቸው ጉዳት የማሳከም ግዴታ አለበት
4. ቀጣሪው ለሰራተኛው ወር ከገባ ከ----------- እስከ --------- ባለው ቀን ውስጥ የደመወዝ ክፍያ ይፈጽማል ፡፡
5. ሰራተኛው ከድርጅቱ በራሱ ፍላጎት ስራ መልቀቅ ከፈለገ ህጋዊ በሆነ መንገድ ማለትም ስራ ከመልቀቁ በፊት ከአንድ ወር አስቀድሞ
የአንድ ወር ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ለድርጅቱ የሰው ሃይል አስተዳደር በማመልከቻ ካስገባ በኋላ በሚመለከተው አካል አስፈርሞ
በህጉ መሰረት ከድርጅቱ የሚገባውን ማንኛውም ነገር ለምሳሌ በቂ የሥራ ስንብት እና የሥራ ልምድ ማስረጃ በጊዜው ይሰጣል፡፡ ነገር ግን
ይህን ህግ ሳያሟላ ስንብት ለሚጠይቅ ማንኛውም ሰራተኛ ከድርጅቱ የሚፈልገውን ነገር ለማግኘት የአንድ ወር ደመዎዝ ቅጣት ከፍሎ
ማግኘት ይችላል፡፡ ምክንያቱም ድርጅቱ የአንድ ወር የጊዜ ገደብ ከተሰጠው የድርጅቱ ስራ እንዳይበደል ባለው 1 ወር የጊዜ ገደብ ውስጥ
በሚለቀው ሰራተኛ ምትክ ሌላ የሰው ሃይል መቅጠር ስላለበት ፡፡
የሰራተኛው መብትና ግዴታ

የስልክ ቁጥር +251 943000002/+251 911285757 አረርቲ Page 1


ርኆቦት ወተት እና የወተት ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ እና ማምረቻ ኃ. የተ. የግ. ማ.
Rihobot Dairy farming and Milk processing plc
የሰራተኛው መብት
1. ለሰራበት ጊዜ ደመወዝ የመከፈል
2. ሰራተኛው ስራውን መልቀቅ ሲፈለግ ለድርጅቱ በውሉ መሰረት ከመልቀቁ በፊት አንድ ወር ቅድመ ማስጠንቀቂያ
በመስጠት ስራውን መልቀቅ ይችላል
3. በውል ስምምነቱ መሰረት የዓመት እረፍት የመጠየቅና የመውጣት በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሰራተኞች አዋጅ
መሰረት የወሊድ ፣ የሀኪም ፣ የጋብቻ፣ የሞት ፍቃድ ማግኘት ይችላል
የሰራተኛው ግዴታ
1. አሰሪውና ሰራተኛው የተስማሙበትን የመግቢያ እና የመውጫ የሥራ ሰዓት የማክበር ግዴታ አለበት፡፡
2. ሠራተኛው የአሰሪውን ንብረት በትጋትና በጥንቃቄ ይይዛል፡፡በሰራተኛው ጥፋት ወይም በቸልተኝነት በአሰሪው ንብረት ላይ ጉዳት
ቢያደርስ በጉዳቱ መጠን ልክ ተጠያቂ ይሆናል፡፡
3. በስራ አጋጣሚ ያወቃቸውን የድርጅቱን መረጃዎች በሚስጢር የመያዝ፣ ለስራ የተረከባቸውን የድርጀቱ
ንብረት/ሀብት/ገንዘብ በጥንቃቄ የመያዝ
4. ለድርጅቱ በተቀመጠው ቀን መጠን በማመልከቻ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ስራውን ጥሎ ያለመልቀቅ
5. ማንኛውም ሰራተኛ ድርጅቱ በቀን ከ 8 ሰዓት በላይ በትርፍ ሰዓት የሚሰራ ስራ ካለው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር
1156/2011 አንቀጽ 67 ላይ በተደነገገው መሰረት የመስራት ግዴታ አለበት
6. ከዋና ሥራ አስኪያጁ የሚሰጡ ተጨማሪ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
7. ተቀጣሪው/ሰራተኛው የመጀመሪያዎቹን 3 ወራት እንደስራ ግብር ጡረታ መዋጮ በስምምነታቸው መሰራት
ለሚመለከተው ተቋም የማስተላለፍ ግዴታ ያለበት ሲሆን ከሦስት ወር በኋላ ውሉ ሲታደስ አሰሪው ተቋም የሚከፍል
ይሆናል፣

ክፍያን በተመለከተ
ሰራተኛው በተመደቡበት የስራ መስክ በሚሰጣቸው የስራ ዝርዝር መሰረት ለሚሰጡት አገልግሎት በወር ያልተጣራ ደሞዝ፣
…………………..…(…………………………………………………) የትራንስፖርት አበል…………
(………………………………………)፣
የስልክ ክፍያ……......ብር (………………………………………)፣
የቤት ኪራይ ወጭ……………(…………………………………………….)
የወንበር………..(……………………………………….)
ሌላ………………(……………………………………………………………………..)
የሚከፈላቸው ይሆናል፡፡
አንቀፅ 5
ውሉ የሚቆይበት ጊዜ

የስልክ ቁጥር +251 943000002/+251 911285757 አረርቲ Page 2


ርኆቦት ወተት እና የወተት ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ እና ማምረቻ ኃ. የተ. የግ. ማ.
Rihobot Dairy farming and Milk processing plc
ይህ ውል ከተደረገበት ከቀን ……/……/ 20… ዓ.ም እስከ ቀን……/……/ 20… ዓ.ም ለ 90 የስራ ቀናት የሚያገለግል
ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ እና የሰራተኛው ጥንካሬ እና ለድርጅቱ ያለው ትርፋማነት እየታየ በየ 3 ወሩ የሚታደስ ይሆናል፡፡
አሰሪው እና ሰራተኛው ከላይ በተገለፁት ድንጋጌዎች መሰረት ወደን እና ፈቅደን ይህንን የስራ ውል በዛሬው እለት
በቀን……/……/ 20.. ዓ.ም በድርጅቱ ቅጽር ግቢ ውስጥ ተፈራርመናል፡፡

የቀጣሪው ስም እና ፊርማ የተቀጣሪው ስም እና ፊርማ ስም………………………


ፊርማ…………. ስም………………………ፊርማ…………
ቀን………………… ቀን…………………
የምስክሮች ስም ፊርማ
1. ………………………….. ……………………….
2. ………………………….. ……………………….
ቀን…………………

የስልክ ቁጥር +251 943000002/+251 911285757 አረርቲ Page 3

You might also like