You are on page 1of 13

ሰላም ለኪ እያለ!

ሰላም ለኪ እያለ ሰላም ለኪ እያለ፣


ሐርና ወርቁን ስታስማማ
የገብርኤል ድምፅ ተሰማ
ተሰማ የመላኩ ድምጽ ተሰማ
ተሰማ የገብርኤል ድምጽ ተሰማ 1
ውሀ ስትቀጅ ክንፉን እያማታ
ሊያበስርሽ የመጣው በታላቅ ደስታ
ከሞገስሽ ብዛት(2) ሲታጠቅ ሲፈታ
አቅርቦልሽ ነበር የክብር ሰላምታ
2
ሰላም ለኪ እያለ ሰላም ለኪ እያለ፣
ሐርና ወርቁን ስታስማማ
የገብርኤል ድምፅ ተሰማ
ተሰማ የመላኩ ድምጽ ተሰማ
ተሰማ የገብርኤል ድምጽ ተሰማ 3
የምስራቹን ቃል ምስጢር ተሸክሞ
ገብርኤል ተላከ ሊያረጋጋት ደግሞ
በእርጋታ ተሞልታ(2) ነገሩን መርምራ
የመላኩን ብስራት ሰማችው በተራ፡፡
4
ሰላም ለኪ እያለ ሰላም ለኪ እያለ፣
ሐርና ወርቁን ስታስማማ
የገብርኤል ድምፅ ተሰማ
ተሰማ የመላኩ ድምጽ ተሰማ
ተሰማ የገብርኤል ድምጽ ተሰማ 5
ይደሰታል እንጅ መንፈሴ በአምላኬ
በምስጋና ሳድር ዘወትር ተንበርክኬ
ሀሳቤ ለቅስፈት(2) ሌላ መች ያስባል
ለኔ ልጅን መውለድ እንዴት ይቻለኛል
6
ሰላም ለኪ እያለ ሰላም ለኪ እያለ፣
ሐርና ወርቁን ስታስማማ
የገብርኤል ድምፅ ተሰማ
ተሰማ የመላኩ ድምጽ ተሰማ
ተሰማ የገብርኤል ድምጽ ተሰማ 7
ካንች የሚወለደው ንዑድ ነው ክቡር
የተመሰገነ በሰማይ በምድር
ምስጢሩ ኃያል ነው(2) ይረቃል ይሰፋል
ካንች በቀር ይህን ማን ይሸከመዋል
8
ሰላም ለኪ እያለ ሰላም ለኪ እያለ፣
ሐርና ወርቁን ስታስማማ
የገብርኤል ድምፅ ተሰማ
ተሰማ የመላኩ ድምጽ ተሰማ
ተሰማ የገብርኤል ድምጽ ተሰማ 9
እጹብ ነው ድንቅ ነው አንችን የፈጠረ
አንችን በመውደዱ ሰውን አከበረ
ዓለም ይባረካል(2) በማህፀንሽ ፍሬ
ክብርሽን አልዘልቀው ዘርዝሬ ዘርዝሬ
10
ሰላም ለኪ እያለ ሰላም ለኪ እያለ፣
ሐርና ወርቁን ስታስማማ
የገብርኤል ድምፅ ተሰማ
ተሰማ የመላኩ ድምጽ ተሰማ
ተሰማ የገብርኤል ድምጽ ተሰማ 11
አብሠራ ገብርኤል ለማርያም ወይበላ
ወይበላ ትወልዲ ወልደ
ሚካኤል መልአክ በክንፉ ፆራ
መንጦላዕት ደመና ሠወራ
ንፅህት በድንግልና አልባቲ ሙስና
ተወልደ ወልድ እምኔህ 12
ገብርኤል ማርያምን አበሠራት /2/
ወንድ ልጅን ትወልጃለሽ አላት
ሚካኤል መላክ በክንፉ ጋረዳት
የሠማይ መጋረጃዎች ሸፈኗት
ንፅህት ናትና በድንግልና /2/ ጥፋት
የለባትምና ወንድ ልጅን ወልዳልናለችና
13

You might also like