You are on page 1of 1

ለ አለምሰገድ መስኤ ወልደሚካኤል

አዲስ አበባ

ጉዳዩ- በኢትዮጵያ የመጀመሪያ በሆነው Corporate Social Responsibility /CSR/ Directory ላይ ድርጅትዎን
እንዲያስተዋውቁ ስለመጋበዝ፤
ድርጅትዎ ምን ያህል አገርዎንና ህዝብዎን በታማኝነት እያገለገለ ነው? ካምፓኒዎ በየትኛው አገራዊና ህዝባዊ ጥሪ ተሳተፈ? በኮቪድ 19?
በገበታ ለአገር? በህደሴ ግድብ? በተማሪዎች ምገባና ዩኒፎርም? የህብረተሰቡን ንፁህ የመጠጥ ውሃ የትምህርት እና የጤና ተደራሽነት
በሚያሳድጉ ተግባራት? በአካባቢ ጥበቃ? በሞዴል ግብር ከፋይነት? በመንገድ ልማትና ተቋማት ግንባታ? በምን መስክ የሚመሩት ተቋም
አገራዊ ግዴታዎቹንና ማህበራዊ ሃላፊነቱን ተወጣ?
ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን በታማኝነት ከሚያገለግሉ ውጤታማ ድርጅቶች መካከል ስለሆኑ አንኳን ደስ አለዎት::
ለመሆኑ ድርጅትዎ ብዙ ገንዘብ፣ግዜና ጉልበት በነፃ ያፈሰሰባቸው እነዚህ መልካም ተግባራት በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ በሚገባ ተዋውቀዋል
ብለው ያስባሉ? በግልና በህዝብ ሚዲያዎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም በሌሎች የሚመለከታቸው አካላትሰ
የድርጅትዎ መልካም ስም ተገቢ ትኩረትና እውቅና ተችሮታል ብለው ያምናሉ ?
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ በሆነው የቢዝነስ ተቋማት የማህበራዊ ሃላፊነት ማስተዋወቂያ ዳይሬክተሪ (First Ethiopian Corporate Social
Responsibility/CSR/ Directory) ላይ ምርትና አገልግሎትዎን ብቻ ሳይሆን ለማህበረሰቡ ያበረከቱትን መልካም ተግባራት በማስተዋወቅ
በአገራችን አርአያ ከሆኑት ቀዳሚ የቢዝነስ ተቋማት ዝርዝር መካከል ስምዎን በክብር ያኑሩ::

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 341/95 የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት የንግዱን ማህበረሰብ በተሻለ ደረጃ
ለማገልገል በርካታ እንቀስቃሴዎች እያደረገ ነው፡፡ የማህበራዊ ሃላፊነት ተግባራትን የሚያስተዋውቀው ይህ ዳይሬክተሪ የንግዱ ማህበረሰብ
ከትርፍ ባሻገር ህዝቡን በሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ተግባራት ተሰማርተው አገራቸውን እያገለገሉ እንደሆነ ለህዝቡ ለማስተዋወቅ ከፍተኛ እድል
ይሰጣል ብሎ ያምናል፡፡

በአገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ሚዲያዎች፣ የህዝብ ወኪሎችና አደረጃጀቶች እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች በነፃ
በሚታደለው እና የንግድ ድርጅቶች ለማህበረሰባቸው ያበረከቱትን አስተዋፅኦ በሚያስተዋውቀው በዚህ የማህበራዊ ሃላፊነት ዳይሬክተሪ
ድርጅትዎ ቢሳተፍ የምርትና አገልግትዎ መለያ ብራንድ ተወዳዳሪነቱ ይጨምራል፣ በህዝብ በመንግስትና በሌሎች ባለድርሻ አካላት ድርጅትዎ
የሚኖረው ተቀባይነት ይጠነክራል ብሎም በህብረተሰቡ ዘንድ መልካም ስም ለመገንባት ያስችለዋል በዚህም ከስጋት ነፃ የሆነ ቀጣይነት ያለው
ሰላማዊና ትርፋማ ስራዎችን ለማከናወን የበለጠ እድል ያገኛል፡፡

ስለሆነም ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ድርጅትዎን ከኢትዮጵያ መልካም ልብ ያላቸው፣ የህዝብ አገልጋይ፣ አርአያና ቀዳሚ የቢዝነስ
ተቋማት ዝርዝር ውስጥ እንዲያሰልፉ ተጋብዘዋል፡፡ ለዚህ እንዲረዳዎ ከዚህ ደብዳቤ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የማስታወቂያና የስፖንሰርሺፕ
አማራጮች የሚያሳይ ቅፅ በመመልከትና እርስዎ ሊሳተፉ የወደዱትን በመምረጥ ሊታተም በታቀደው የንግድ ማውጫ ላይ እንዲሳተፉ
እንጋብዛለን፡፡
ከሠላምታ ጋር

አባሪ፤
 2 ገፅ

You might also like