You are on page 1of 7

ትክክለኛውን የገና በዓል አከባበር ለትውልዱ እናውርስ……!!!

በየዓመቱ የገና በአልን ስናከብር ከእምነቱና ከባህሉ ጋር ተያያዥነት የሌላቸው የምዕራባውያኑ ባህል የሆኑት
የገና አባት (ሳንታ) ፣ የክሪስማስ ዛፍና ብልጭልጭ ኮተቶቹ በከፍተኛ ፍጥነት ከከተማ እስከ ገጠር ተስፋፍተው ቱባውን ባህላችንን
ውጠውታል።
እየጠፋ ያለውን ባህላችን ታሳቢነት ስንል በዚህ ፔጅ ላይ የገና አባት (ሳንታን) ፣ የክሪስማስ ዛፍና ብልጭልጭ ኮተቶቹን የሚያንፀባርቁ
ማንኛውንም
የልጆችዎን ፎቶግራፍ ፖስት የማናረግ መሆናችንን እናሳውቃለን። ይህን መልክት ሁላችንም ላይክ ፣ ሼርና ፣ ኮሜንት በማድረግ ለብዙሀን
በማድረስ
የድርሻችንን እንወጣ
የገና በዓልና አከባበሩ
"ታኅሣሥ ገሠገሠ ከተፍ አለ ገና፣
እጠብቅሃለሁ አንተ ልጅ ቶሎ ና፡፡
የታኅሣሥ ትውው የገና ፍቅር፣
ይላል ቅር ቅር፡፡"

ዓመት ጠብቀው፤ ዐውደ ዓመትን ዙረው ከሚመጡት በዓላት አንዱ የገና (ልደት) በዓል ነው፡፡ በያመቱ ታኅሣሥ 29 ቀን ይከበራል፡፡
"ዮም ተወልደ ቤዛ

ኵሉ ዓለም" (ዛሬ የዓለም ቤዛ ተወለደ) እያሉ ኢትዮጵያውያኑ በደማቅ ሥነ ሥርዓት በዓሉን ያከብራሉ፡፡ ይህን በዓለ ልደት ለማክበር
በመንፈቀ ኅዳር

የጀመሩትን ጾም ለ 43 ቀኖች አሳልፈዋል፡፡

"ያለም ሁሉ መድኃኒት
ተወለደ በበረት፣
እያሞቁት እንስሳት
ብርሃን ሆነ በዚያች ሌት
ሲዋዥቡ መላእክት
ደስ አሰኙ ለኖሩት" የሚለው ኅብረ ዝማሬ የበዓሉ መገለጫ ነው፡፡
ልደት የእምነታችን መክፈቻ በር
ቤተ ክርስቲያን የክርስቲያኖችን መንፈሳዊ ሕይወት ከዕለት ዕለት በጋለ ሁኔታ ለማሻሻል እንዲረዳ በዓመቱ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት
የተለያዩ በዓላትን
ታከብራለች ከእነዚህም በዓላት በጣም በደመቀ ሁኔታና በታላቅ ደስታ የሚከበረው የልደት በዓል ነው፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት
የክርስቶስ ልደት
የእምነታችን መክፈቻ በር በመሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪም በየትኛውም የዓለም ክፍል አዲስ ህፃን ተወልዶ ወደ ህብረተሰቡ በሚቀላቀልበት
ጊዜ የሚኖረው
ደስታና ፈንጠዝያ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡ የህፃኑም ልደት በየዓመቱ በሚከበርበት ጊዜ በመጀመሪያ የቤተሰቡ ከዚያም የወዳጅ
ዘመድና የጓደኛ
ደስታ ፍፁም ልዩ ነው፡፡ ለዚህም ነው የክርስቶስ ልደት በክርስቲያን ቤተሰቦች ዘንድ በትልቅ ጉጉትና ደስታ የሚጠበቅ ልዩ ቀን የሆነው፡፡

በእረኞቹ አጠገብ ቆመ፤ የእግዚአብሔርም ብርሃን በዙሪያቸው በራ፤ በጣምም ፈሩ፡፡ መልአኩም እንዲህ አላቸው ‹‹እነሆ ለእናንተና
ለሕዝቡ ሁሉ ደስታ
የሚሆን ታላቅ የምስራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ‹‹ እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት የሆነ ተወልዶላችኋል፡፡ ይኸውም ጌታ እና
እግዚአብሔር የሆነ
መድኃኒታችን ኢያሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እናንተም ባገኛችሁት ጊዜ ምልክቱ እንዲህ ነው፡፡ ሕፃን በጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ
ታገኙታላችሁ››
ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ እነዚህ እረኞች እርስ በርሳቸው
‹እስኪ ቤተልሔም
እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን ነገር እንወቅ አሉ፡፡ ፈጥነውም ሄዱ፡፡ ማርያምንና ዮሴፍን አገኙአቸው፡፡ ሕፃኑንም በበረት
ውስጥ አገኙት፡፡
በአዩትም ጊዜ የነገሩአቸውን ሰምተው በጣም ተደነቁ፡፡ እረኞቹም እንደነገሩአቸው ባዩትና በሰሙት ሁሉ እግዚአብሔርን
እያመሰገኑ‹‹በሰማይ
ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን በምድርም ለሰው ልጆች በጎፈቃድ ሆነ›› ብለው እያመሰገኑና እያከበሩ ወደመጡበት ተመለሱ፡፡
ምክንያተ ልደት
በገና በዓል ቀን እያንዳንዱ ክርስቲያን በሀሳብ ወደ ኋላ ተመልሶ በቤተልሔም በከብቶች ግርግም ውስጥ ክርስቶስ የተወለደበትን ምሽት
ያስታውሳል በጣም
ጣፋጭ ምሽት አብዛኛውም ክርስቲያን ወንድ ሴት ህፃን ሽማግሌ መስዋእተ ቅዳሴን ለመስማት በምሽት ወደ ቤተክርስቲያን ያዘግማል፡፡
ምክንያቱም
አምላክ ሰው የሆነበት የተባረከች እለት ናትና ለአምላኩ ምስጋና ያቀርባል ለክርስቲየኖች ትልቅ በዓል በመሆኑ አብያተ ክርስቲያናት በልዩ
ሁኔታ ያሸበርቃሉ
አበባዎች፣ ምንጣፋ፣ሻማው ጌጣጌጡ ሁሉም ልዩ ነው እንዲሁም በማንኛውም ቋንቋ የሚዘመሩት የልደት መዝሙሮች በጣም ውቦች
ናቸው፡፡ ነገር ግን
ይህንን በዓል በውጫዊ መልኩ በድምቀት እንደምናከብረው ሁሉ በውስጣችንም ህፃኑ ኢየሱስ መቀበል ይገባናል ምክንያቱም ክርስቶስ
የተወለደው ሰው
መሆን ምን እንደሚመስል አይደለም አምላክ ነውና ሁሉን ያውቃል ይልቁንም ከገባንበት የኃጢአት ማቅ ውስጥ ሊያወጣን በትምህርቱና
በህይወቱ አብነት
ሊሆነን በመጨረሻም በሞቱ የክብሩ ተካፋዮች ሊያደርገን በማሰብ ነው፡፡
ጌታችን በተወለደበት በዚያች ሌሊት መንጋቸውን ለሚጠብቁ እረኞች የእግዚአብሔር መላእክት “በሰማይ ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን
በምድርም
እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች ሰላም ይሁን” ሉቃ 2፡14 ብለው እንደዘመሩ ክርስቶስ የመጣው በሰዎች ሰላምን ለማምጣት ነው፡፡
ስለዚህም በጌታ
ልደት ቀን አሁንም ደግሞ በልባችን ሊወለድ የሚፈልገውን ክርስቶስ ሰላሙን ይሰጠን ዘንድ በንጹህ ልብ እንቀበለው፡፡
እንዲሁም በጌታችን ልደት በዓል ልናስተውለው የሚገባ የእመቤታችንን ታላቅነት ነው፡፡ አምላክ ከሁሉም በላይ ወዶና መርጦ ማደሪያው
እንድትሆን
የመረጣት እመቤታችንን ነው፡፡ እመቤታችን መልአኩ ገብርኤል “ያለ ወንድ ትወልጃለሽ” ብሎ የነገራት ትርጉሙ ባይገባትም
በእግዚአብሔር ላይ በነበራት
ታላቅ ፍቅርና ትህትና በእምነት ሁሉን ተቀብላለች እመቤታችን ማርያም በጊዜዋ እንዲሁ ያለ ባል መውደሉ በድንጋይ ተወግሮ ለመገደል
የሚያበቃ
ኃጢያት መሆኑን ብታውቅም በእግዚአብሔር በመታመን ከሰዎች የሚመጣባርን ይሉኝታ ወደ ጐን በመተው ይህንን ታላቅ ሚስጢር
ተቀብላ በአለም
ብርሃንን ሰጥታናለች፡፡ ይህም ወደ ትልቅ ክብር እንድትደርስ አድርጓታል፡፡ እኛም በክርስቶስ ፍቅር ብለን “አንተ እንዳልክ ይሁንልኝ”
ብለን
የእግዚአብሔርን ፍቃድ ለመፈጸም ያለ ይሉኝታ ለምናደርገው ጥረት በቃላት ሊገለጽ የማይችል ክብር ይጠብቀናል፡፡
የልደት በዓል በምናከብርበት ጊዜ በየቤተክርስቲያናችን አንድ ለየት ያለ ልማድ አለ ይኸውም በልደት በዓል ከሁለት ሺ ዓመት በፊት
በቤተልሔም ክርስቶስ
በበረት የተወለደበትን በማስታወስ በተለያየ ሁኔታ የበረት ቅርጽ ይደረጋል፡፡ ይህ በየአብያተ ክርስቲያኑ የሚገኘው በፊት በእያንዳንዱ
ክርስቲያን በልቡ

ውስጥ ልዩ መንፈሳዊነትንና ደስታን ይፈጥራል፡፡ ይህ ልማድ የተጀመረው በ 13 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በትልቁ ቅዱስ
ፍራንቸስኮስ ሲሆን
በወቅቱም ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ጌታችን የተወለደበትን ሁኔታ ለማስታወስ ይህን በረት ሰርቶ በቅዳሴው መሀል በሕፃኑ እየሱስ መልክ
የተቀመጠውን
አሻንጉሊት ባነሳ ጊዜ ህፃኑ ህይወት ዘርቶ እንዳቀፈው በቅዱስ ፍራንቸስኮ ታሪክ ተጽፎ እናገኛለን ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ይህ የበረት
አምሳል
በየቤተክርስቲያኑ እየተሠራ በጌታችን ክርስቶስ ልደት ወቅት በቤተክርስቲያናችን ልዩ ድምቀትን ይሰጣል፡፡ ክርስቲያኖችም በዚህች ሌሊት
ወደ በረቱ

በመጠጋትና ተንበርክከው በመጸለይ ከ 2 ዐዐዐ ዓመት በፊት የተወለደውን ክርስቶስ ዛሬም በየቤተክርስቲያናችንና በየልባችን
እንደሚወለድ ያስታውሳሉ፡፡

December 25(ታህሳስ 16) ወይስ ታኅሣሥ 29

በ 16 ኛው ምእት ዓመት ከጁሊያንን ቀመር ተከልሶ የተዘጋጀውን የጎርጎሪያን ቀመር የተከተሉት ምዕራባውያን በነርሱ "ዲሴምበር 25"
ባሉት ታኅሣሥ 16

ቀን ያከብሩታል፡፡ በዓሉ አንድ ሆኖ የቀኑ ልዩነት የተፈጠረው መሬት ፀሐይን ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ በምሥራቆች 365 ቀን ከ 6 ሰዓት
ነው በማለታቸው

ምዕራቦች ደግሞ 365 ቀን ከ 5 ሰዓት 48 ደቂቃ 46 ሰኮንድ ነው በሚል ልዩነት በመፈጠሩ ነው፡፡በዋናነት ግን

ከጥንት ጀምሮ ሮማውያን ታህሳስ 16 (December 25 ) ቀንን እውነተኛ ፀሐይ የተወለደበት ቀን እያሉ ያከሩ ነበር ምክንያቱም
በሮማውያን ግዛት
የረጅሙ የክረምት ወቅት አብቅቶ በመጀመሪያ ጊዜ የፀሐዩን ብርሃን የሚያዩት በዚህች ቀን ነው፡፡ ሮማውያን በተለምዶ ከዚያ
ከሚያኮራምት የክረምት
ወቅት በማለፍ ብርሃንና ሙቀትን ስለሚያገኙ ለተክሎቻቸው ልማት ለከብቶቻቸውም የፍንደቃ ወቅት ስለሆነ ለዚህ ብርሃን በየዓመቱ
የምስጋና መስዋእትን
በመያዝ ሁሉም ወደ ተራራ ጫፍ ላይ በመውጣት መስዋዕትን ያቀርቡ ነበር፡፡
ክርስቲያኖች እስከ አራተኛ ክፍለ ዘመን ድረስ በስደት ላይ ባልተረጋጋ ህይወት ውስጥ ስለነበሩ እምነታቸውም በዓለም ላይ በሰፊው
ያልታወቀበት ዘመን

ስለነበር ስለ ጌታችን ልደት ብዙም ትኩረት አይሰጡም ነበር፡፡ ስለዚህ እንደማንኛውም ሮማዊ በአባቶቻቸው የወረሱትን አምልኮ /የፀሐይ
አምልኮ/

መስዋዕትን ይሰው ነበር፡፡ ወደ 320 ዎቹ ገደማ ለመጀመሪያ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች በእርጋታ መኖር የጀመሩ ክርስቲያኖች የጌታችን ልደት
በታህሳስ 29

ማክበር ጀመሩ፡፡ በ 354 ዓ.ም ግን ሮማዊው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊብሮስ ክርስቲያኖች “ሳትሩን” እየተባለ በሚጠራው የፀሐይ አምላክ
ፈንታ መንፈሳዊ
ገናና የገና ጨዋታ
ልደት በኢትዮጵያ ዐውድ ከገና ጨዋታ ጋር ተያይዞ በባህላዊ ጨዋታዎች ይከበራል፡፡ የተለያዩ መንፈሳዊና ባህላዊ አከባበር
ከሚከበርባቸው ስፍራዎች
አንዱ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው ጃንሜዳ ተብሎ የሚታወቀው ገናን ነው፡፡
በዓሉ በሁለት ቡድኖች መካከል ሚና ለይተው በሚጫወቱበት ጊዜ ተጫዋቾቹም ሆኑ ታዳጊዎች በሆታና በዕልልታ ከሚያዜሟቸው
መካከል በዚህ ጽሑፍ
መግቢያው ላይ የተጻፈው አንጓ ይጠቀሳል፡፡
የገናን ባህላዊ ጨዋታን ስንመለከት አስቀድሞ የቡድን አባላት የሚሆኑ ሁለት ሰዎች ይመረጣሉ፡፡ ሁለት ሁለት ተጫዋቾች ወደ አባቶች
ይቀርቡና
በምርጫው ወደ ቡድን ውስጥ ይገባሉ፡፡ የሚያስፈልገው የተጫዋች ቁጥር ሲሞላ ወገን ወገናቸውን ይዘው በዱላ ቀልጣፋ የሆኑ
ተጫዋቾች ጥንጓን(

መጫወቻ ኳሱ) ወደፊት እንድትቀጥል ይመቷታል ወይም ይመልሷታል፡፡ ተጫዋቾች ብዙ ጊዜ በጨዋታው ስለሚሰጡ ጥንጓን ከእግር
መካከል በገባች
ጊዜ ከሰው እግር ጋር ደርበው ስለሚመቱ የእግር መሰበር በዚህም ሳቢያ ወገን ለይተው እስከመፈናከት ይደርሳሉ፡፡ በንጉሳውያን ዘመን
የመኳንንቱም
አሽከሮች፣ የንጉሡና የንግሥቲቷ አሽከሮች የጌቶቻቸውን ስም በጉብዝና የሚያስጠሩት በባህላዊው የገና ጨዋታ ነው፡፡
ጨዋታው በመንደር ልዩነት ከሆነ የታች አምባ ቡድን ሀምሳ ተጫዋቾች ቢሆኑ የላይ አምባ ቡድን ሰባ ሆነው ቢጫወቱ የሚከለክል ደንብ
አልነበረም፡፡
ጨዋታው በመጨረሻ ፀብ ስለሚያነሳ ብዙ ጊዜ ጉዳት ያጋጥማል፡፡ ጥንጓም ኃይለኛ ለጊ በመታት ጊዜ ዐይን እስከ ማጥፋት ትደርሳለች፡፡
ተጫዋቾች
"በሚና" ብለው በሚጫወቱበት በቆልማማ ዱላ ቢደባደቡም የሚገላግል ዳኛ አልነበረም፤ ጨዋታውን በሚመለከቱ አባቶችም
በድብድብ ከመሳቅ በስተቀር

ሽምግልናቸው ለገና ጨዋታ አልተለመደም፡፡ "እግር ይብሳል፣ ያንከላውሳል፡፡" እያለ ማስፈራራት፣ ራስን መቀወር ወይም እንቆራቆስ
ብሎ እጅና እግርን
በዱላው መምታት በገና ጨዋታ የተለመደ ነበር፡፡
የገና ጨዋታ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አገሮች የታወቀውና በኦሊምፒክ የስፖርት በዓል ከሚደረጉ ውድድሮች አንዱ ሆኖ
ቆይቷል፡፡ ይህም
ጨዋታ ሆኪ በሚል ስም ይጠራል፡፡ ፈረንጆች የፊት አደጋን መከላከያ ዘዴ ይጠቀማሉ፡፡ በኢትዮጵያ ያገር ባህል ገና ጨዋታ በሚደርስ
አደጋ ማንም
ተጫዋች አይጠይቅም፡፡
በገና ጨዋታ አሸናፊ ለሆኑት ቡድኖች ፊሪዳና ጠጅ ተሰጥቷቸው እየበሉና እየጠጡ፣ እየዘፈኑ ሲሸልሉና ሲያቅራሩ ሜዳውን የጦርነት ድል
ያገኙበት
ያስመስሉት ነበር፡፡ ከሚዘፍኑትና ግጥሞች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
"ማታ ነው ድሌ፣
ይሄ ነው አመሌ፡፡
አሲና በል አሲና ገናዬ፡፡
ኦ! ጉ! አሲና በል አሲና ገናዬ፡፡
ግፋው ግፋው አለኝ እኔ እንደምን ልግፋው፣
የአንድ በሬ ጨጓራ እንደ ቅል የነፋው፡፡
የብብቱ ሽታ፣ የመንፈቅ በሽታ፡፡
የጀርባው መርሬ፣ ያውላል ጥድ በሬ፡፡
ካስር ጋን አተላ፣
አይተርፈው በአንኮላ፡፡
እግርህ የሸረሪት ሆድህ የእንቁራሪት፣
ቀን እንደጠላሁ ና እንዳትመጣ ሌሊት፡፡"
ስድብ ለተራው ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በመኳንንቱና በነገሥታቱም ላይ ሊሰነዘር ይችላል፡፡ በሚደርስባቸው ስድብ ግን ምንም ዓይነት ቁጣና
ቅጣት
አያደርጉም፡፡
"በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ

በገና ጨዋታ የለም ሎሌ ጌታ፡፡" የሚለው የዘፈን ግጥም ይህን ባህል ይገልፃል፡፡
አከባበር በላሊበላ
በዚህ በዓል በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ምዕመናን መንፈሳዊ በዓሉን ለማክበርና በረከት ለመሳተፍ የሚጓዙ ሲሆን ሌሎቹም
አብያተ
ክርስቲያናቱንና መንፈሳዊ የበዓል ሥርዐቱን ለመጎብኘት ነው። ይህም በዓል ሃይማኖታዊ፣ መንፈሳዊ፣ ትውፊታዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና
ሀገራዊ ፋይዳ
አለው።ይህንንም ለማስረገጥ በየዓመቱ ያለማቋረጥ ምዕመናን ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች መምጣታቸው ነው።
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በመላው ዓለም የሚከበር ሲሆን በሁሉም የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት፣
ሌሊቱ ማሕሌት

ተቁሞ ቅዳሴ እንዳበቃ፣ የበዓል ፍጻሜ ይሆናል፡፡ በላሊበላ ግን በተጨማሪ በዕለቱ ጧት ላይ "ቤዛ ኵሉ" የተሰኘው ክብረ በዓል ከአለት
ከተፈለፈሉት
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በአንዱ በቤተ ማርያም ካህናቱ ጋራና መሬት ላይ ሆነው ያከብሩታል፡፡ በተጨማሪ ዕለቱ እራሱ
ቅዱስ
ላልይበላ(ላሊበላ) ም የተወለደበት
በ ታህሣሥ 29 ቀን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልና የገናናው ንጉሥ የቅዱስ ላልይበላ የልደት በዓል
በመሆኑም ጭምር
በአንድነት በድምቀትና በደስታ ማራኪ በሆነ መንገድ ይከበራል፡፡
የላሊበላው "ቤዛ ኵሉ" አከባበር ትእምርታዊ ነው፡፡ ማሜ ጋራ /ቤዛ ኩሉ ዓለም ሥነ ሥርዓት የሚካሄድበት ቦታ/ ላይ ያሉት የመላእክት
ምሳሌ፣ መሬት
ላይ ያሉት ደግሞ የእረኞች ምሳሌ ሆነው ዝማሬውን በሆታና በዕልልታ ያጅቡታል፡፡ የክርስቶስ ኢየሱስን መወለድ መጀመሪያ ያወቁ
እረኞች በመሆናቸው
በአገር ቤት ትውፊቱ እየተነገራቸው የሚያድጉት እረኞች በተለየ ሁኔታ ያከብሩታል፡፡
በዓሉ በቦታው አገልጋይ በሆኑ 670 ካህናትና በአካባቢው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በሚያገለግሉ ከ 500 በላይ በሚሆኑ ካህናት
ታጅቦ ማህሌቱ

ይካሄዳል፤ በዚህ በዓል መላው ነዋሪ ‘ካህን’ የመስሎ ሚታይበት አከባበር ነው፤ የማህሌት ሥነ ሥርዐቱ 2፡30 (ማታ) የሰሜን ወሎ ሀገረ
ስብከት ሊቀ
ጳጳስ መሪነትና ሌሎች ብጹአን አባቶች በሚገኙበት በየዓመቱ ይከበራል።
በዓሉ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ መከበር የጀመረው ከ 900 ዓመት በፊት ነው። ከታህሳስ 23(በዓለ ጊዮርጊስ) ጀምሮ እስከ ዛሬ (ታህሳስ
28) ድረስ ሁሌም

2፡00 ሰዓት ሲሆን የሥርዐተ ማህሌት ደወል ይደወልና በአገልግሎት ይታደራል።

ይህ በዋዜማው የሚካሄደው የማህሌት ሥርዐት 1፡30 አካባቢ የሚጀመር ሲሆን ልዩ የሚያደርገው የራሱ ቀለምና ዜማ ያለውና ሙሉ
ሌሊቱን በወረብ
ዝማሬ እየቀረበ የሚታደር መሆኑ ነው።
ማህሌት ሥነ ሥርዓቱ ሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አባታዊ መሪነትና በአስተዳዳሪው አስተባባሪነት እንዲሁም በመሪጌታው በሚመሩ ከ 7
ባልበለጡ
አስተናጋጆች በሥርዓት ይካሄዳል።የማህሌቱን አካሄድ ስንመለከትም አንድ ጊዜ ከ 12 ያልበለጡ ጥንግ ድርብ የለበሱ' አንድ ጊዜ ደግሞ ከ
12 ያልበለጡ

ጥቁር ካባ የለበሱ በድምሩ 24 ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ከቀኝና ከግራ ሆነው በተራ እያሸበሸቡ ያስኬዱታል፡፡

ማህሌቱም ማዕጠንት በያዙ 4 ካህናትና ከ 8 ያላነሱ ዲያቆናት ወርቅ ካባ ለብሰው፣ የወርቅ አክሊል ደፍተው፣ የወርቅ መስቀል ይዘው
መለከት እየነፉ
ዙሪያውን በመዞር ማህሌቱን ያጅቡታል። የዚህም ምሳሌነቱ ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ መላእክት መለከት እንደሚነፉ ለመግለጥ ሲሆን
ለማህሌቱ ትልቅ
ድባብ ይፈጥራል። የማዕጠንት ሥርዐቱ ካህናቱ በሊቀ ካህናቱ፤ ዲያቆናቱ በሊቀ ዲያቆኑ ይመራሉ።
ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ በአስራ አንዱም ቤተመቅደስ የቅዳሴ ሥርዐት ይፈጸማል። በተለይም ያሉትን ቆራብያን በተቀላጠፈ መልኩ
ለማስተናገድ በቤተ
ማርያምና በቤተ መድኃኒዓለም በሁለት ልዑክ ቅዳሴው ይከናወናል።
ከ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ጥንግ ድርብ፣ ካባ እንዲሁም ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናት ከአስራ አንዱ ቤተመቅደስ ከእያንዳንዳቸው ከአስራ
ሁለት ያላነሱ

ካህናት ይህንን ያሬዳዊ ዜማ ለማጀብ ወደ ማሜ ጋራ /ቤዛ ኩሉ ዓለም ሥነ ሥርዓት የሚካሄድበት ቦታ/ ይወጣሉ።
ልክ አንድ ሰዓት ሲሆን ከላይና ከታች የሚሰለፉ ካህናት ቦታቸውን ይይዙና እስከ 4 ሰዓት በሚፈጅ ክንውን እየተቀባበሉ ለሀገር፣ ለወገን፣
ለምድር ሰላም

በረከት የሚጸለይበት ‘ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ’ (ዛሬ የዓለም ቤዛ ተወለደ) የተባለው የቀለም ክንውን ይካሄዳል። እንግዲህ የበዓሉን
አከባበር በቅዱስ
ላልይበላ ልዩ የሚያደርገው አንዱ ይህ “ቤዛ ኩሉ ዓለም” የሚባለው የቀለም ዓይነት ነው።

You might also like