Professional Documents
Culture Documents
Essential English Amharic Episode 12
Essential English Amharic Episode 12
Julie
How many cousins do you have?
Chris
I have eleven cousins. How about you?
Julie
I have four cousins.
የወንድ አያት
grandfather
የሴት አያት
grandmother
አክስት
aunt
አጎት
uncle
‘ምን ያህል የአክስትና የአጎት ልጆች አሉህ?’ የሚለውን ጥያቄ ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
ከዚያም ጁሊ ‘አራት የአክስትና የአጎት ልጆች አሉኝ’ ‘I have four cousins.’ ስትል ለክሪስ መለሰችለት። ሐረጉን
ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
በጣም ጥሩ፤ አሁን የተለያዩ ሰዎች ስለዘመድ አዝማዶቻቸው ሲጠያየቁ በመስማት እርስዎ ካሉት ጋር ያመሳክሩ።
እሺ፥ ያንን ደግመን እንሞክረው። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮቹን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን እንዳንድ
ጊዜ ይሰማሉ።
በጣም ጥሩ! እስኪ እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንደሚያስታውሱት እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና
የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
በጣም ግሩም! እሽ፥ አሁን ሰዎችን ምን ያህል የአክስትና የአጎት ልጆች አንዳሏቸው እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል
አውቀዋል። ለጁሊ ምላሽ በመስጠት ልምምድ ያድርጉ። ‘ምን ያህል የአክስት እና የአጎት ልጆች አሉሽ?’ የሚለውን ጥያቄ
ማስከተልን አይርሱ።፥
Julie
How many cousins do you have?
Chris
I have eleven cousins. How about you?
Julie
I have four cousins.
በጣም ጥሩ! አሁን በእንግሊዝኛ ሰዎች ምን ያህል የእክስትና የአጎት ልጆች፥ አክስቶች እና አጎቶች እንዳሏቸው መጠየቅ
ይችላሉ። የተማሩትን ነገር መለማመድን አይዘንጉ። ጓደኛ ይፈልጉና ‘ምን ያህል. . . አለህ/አለሽ?’ በማለት ይጠይቋቸው።
ለተጨማሪ የEssential English Conversation ዝግጅቶች በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። ደህና ይሁኑ!