You are on page 1of 45

የኢትዮጵያ ፌዴራል ድጎማ በጀት ክፍፍል

ተሞክሮ
ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የተዘጋጀ
ግንቦት 2010 ዓ.ም.
የፅሁፉ ይዘት
1. የድጎማው አስፈላጊነት
2. የወጪ ፍላጎቶች ልዩነት ምክኒያቶች
3. በክልሎች መካከል የገቢ ልዩነት ምክኒያቶች
4. ፋይናንስን በተመለከተ የአገራችን ሕገመንግስታዊ መርሆዎቹ
5. የፌዴራል፣ የክልልና የጋራ ገቢ ምንጮች
6. የፌዴራልና የክልል መንግስታት የወጪ ሃላፊነቶች
7. የአገራችን ጥቅል ዓላማ ያለው ድጐማና የመጀመሪያዎቹ
ተሞክሮዎች
8. የተለየ አሰራር ያስፈለጉበት ምክኒያቶች
9. የአዲሱ ቀመር አሰራር ዓላማ፣ ታሳቢዎችና ተሞክሮዎች
10. የአሮጌውና የአዲሱ አሰራር ንፅፅር
11. እስከ አሁን ድረስ ያልተቀረፉ ውስንነቶች
1. የድጎማው አስፈላጊነት
• ክልሎች በአማካይ ወደ 90 በመቶ የሚሆነውን ወጪያቸውን
የሚሸፍኑት ከፌዴራል መንግስት በሚያገኙት የበጀት ድጋፍ ነው
• በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀመር መሰረት በሚከፋፈሉት ድጎማ ደግሞ
ክልሎች በአማካይ 80 በመቶ የሚሆነውን ወጪያቸውን ይሸፍናሉ
• በሕገመንግስቱ አንቀፅ 94/2 መሰረት የፌዴራሉ መንግሥት
ለክልሎች የሚሰጠው ድጎማ ክፍፍል ፍትሃዊ ሊሆን ይገባል
– ክፍፍሉን ፍትሃዊ ማድረግ የሚችለው ደግሞ ማከፋፈያ ቀመሩ ነው
• የድጎማው ጉዳይ ለክልሎች ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ በመሆኑ መላ
ሕብረተሰቡ በክፍፍሉ ላይ ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል
• የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ደግሞ ከሁሉም ቀድመው ግንዛቤውን
ማግኘት ይኖርባቸዋል (ለራሳቸው ስራ አቅም ለመፍጠርና ለሌሎች
በጉዳዩ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት)
የክልሎች በጀትና ራሳቸው የሚሰበስቡት የገቢ መጠን
120
103.24
100

80

60

40

20.05
20

0
የክልሎች በጀት የ2005-2007 አማካይ የክልሎች የራሳቸው ገቢ የ2005-2007 በጀት
(በቢሊየን ብር) ዓመት አማካይ (በቢሊየን ብር)
የክልሎች በጀትና የራስ ገቢ ንፅፅር (በአማካይ 2005-07)
በድጎማ በጀት አማካይነት
• የፌፈዴረል መንግስቱ የክልሎችን የበጀት ክፍተት በሚሰጣቸው ድጎማ
ያስተካክላል (ይህ ዓይነቱ የበጀት ድጋፍ ቀጥተኛ የፊስካል አለመመጣጠን
የሚባለውን ችግር ለመቅረፍ ያግዛል)
• በክልል መንግስታት መካካል የወጪ ፍላጎት እና የገቢ አቅም በተለያየ
ምክኒያት ተመሳሳይ ስለማይሆን የመንግስታቱን የፊስካል አቅም ተቀራራቢ
ማድረግ ይቻላል (አግድሞሽ የፊስካል አለመመጣጠን ለማስተካከል
ያግዛል)
• የወጪ መጋራት የሚያስከትለውን ተፅኖ ይቀነሳል
• እንደ አገር ቅድሚያ የሚሰጣቸው ስራዎችን እንዲሰሩ ይደረጋል (ለምሳሌ
በፊት የሚሊኒየሙን የልማት ግቦችን አሁን ደግሞ የዘላቂ ልማት ግቦችን
ለማሳካት)
• በእድገት ወደ ኋላ የቀሩ ክልሎችን ለመደገፍ (1 በመቶ ከአጠቃላይ
ድሮማው ውስጥ ለ 4 ክልሎች ብቻ የተሰጠበት ጊዜ ነበር)
• የበጀት አጠቃቀምን ውጤታማነት ማሻሻል ይቻላል
2. በክልሎች መካከል የወጪ ፍላጎቶች ልዩነት ምክኒያቶች
• የወጪ ፍላጎት ልዩነት
– የአገልግሎት ተጠቃሚዎች
የህዝብ ብዛት፣ ስብጥር እና አሰፋፈር
ስብጥረ ሲባል፤ ዕድሜ፣ ፆታ፣ ጊዚያዊ የሆኑ ኑዋሪዎች (ለምሳሌ
ስደተኞች)፣ የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች ብዛት
አሰፋፈር፤ ተከማችቶ ወይም ተራርቆ መስፍር
–የመልካ ምድር አቀማመጥ፤ ዳገታማ፣ ሜዳ
–የአየር ንብረት ሁኔታ፤ ሞቃታማ፣ ብርዳም
–የአገልግሎት መጋራት
3. በክልሎች መካከል የገቢ ልዩነት ምክኒያቶች
• የገቢ አቅም ልዩነት የሚከሰተው
– የባህል ልዩነት (ታክስ የመክፍል ግንዛቤ)
– የሰው ኃይል (ታክስ የማስተዳደር አቅም)
– የታክስ መሰረትና ጥረት
– ታክስን የማስተዳደር ወጪ
• በጀትን በአግባቡ መጠቀም አለመቻል የወጪ ፍላጎትን
እንዲጨምር የሚያደርግ ሲሆን በጀትን በአግባቡ መሰብሰብ
መቻል ደግሞ የገቢ ሁኔታን ያሻሽላል
4. የአገራችን የፋይናንስሕገመንግስታዊ መርሆዎቹ
• አንቀጽ 94 የፋይናንስ ወጪን በሚመለከት
– የፌዴራሉ መንግሥትና ክልሎች በሕግ የተሰጧቸውን ኃላፊነቶችና
ተግባሮች ለማከናወን የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በየበኩላቸው
ይሸፍናሉ፤ ሆኖም ማንኛውም ክልል በውክልና ለሚፈጽመው ተግባር
የሚያስፈልገው ወጪ ሌላ ስምምነት ከሌለ በቀር ውክልናውን በሰጠው
ወገን ይሸፈናል፡፡
– የፌዴራሉ መንግሥት ለክልሎች የተመጣጠነ እድገት እንቅፋት ካልሆነ
በስተቀር ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ፣ ለመልሶ መቋቋምና ለልማት
ማስፋፊያ ለክልሎች ብድርም ሆነ እርዳታ ሊሰጥ ይችላል፡፡ የፌዴራሉ
መንግሥት ክልሎች ለሚያስፈልጋቸው ወጪ የሚያደርገውን ድጐማ
በሚመለከት ኦዲትና ቁጥጥር የማድረግ ሥልጣን ይኖረዋል፡፡
• አንቀጽ 95 የፋይናንስ ገቢን በሚመለከት
– የፌዴራሉ መንግሥትና ክልሎች የሚዋቀረውን የፌዴራል አደረጃጀት
የተከተለ የገቢ ክፍፍል ያደርጋሉ፡፡
5. የፌዴራል፣ የክልልና የጋራ ገቢ ምንጮች
የፌዴራል ገቢ ምንጭ የክልሎች የገቢ ምንጭ የጋራ የገቢ ምንጭ
 የጉምሩክ ቀረጥ፣ ታክስና  የክልል መስተዳድርና የድርጅት  ፌዴራልና ክልሎች
 የፌዴራል መንግስትና ተቀጣሪዎች ላይ የሚሰበሰብ የሥራ በጋራ በሚያቋቁሟቸው
ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ግብር የልማት ድርጅቶች ላይ
ተቀጣሪዎች የሥራ  የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያ የንግድ ትርፍ ግብር፣
ግብር  ከግልና ከሕብረት ሥራ ማህበራት የስራ ግብር፣ የሽያጭና
 በፌዴራል መንግስት ከተደራጁ ገበሬዎች ላይ የእርሻ ሥራ ኤክሳይዝ ታክስ
ባለቤትነት ስር ባሉ ገቢ ግብር  ከድርጅቶች የንግድ
የልማት ድርጅቶች ላይ  የግለሰብ ነጋዴዎች የንግድ ትርፍ ትርፍ እና ከባለ
የንግድ ትርፍ ግብር፣ ግብርና የሽያጭ ታክስ አክስዮኖች የትርፍ
የሥራ ግብር፣ የሽያጭና  በግል ባለቤትነት ሥር ካሉ ድርሻ ላይ ግብርና
አክስይዝ ታክስ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች ከሚገኝ የሽያጭ ታክስ
 የብሄራዊ ሎተሪና ገቢ ግብርና በክልሉ ባለቤትነት ሥር  በከፍተኛ የማዕድን
ሌሎች ዕድል ሙከራ ባሉ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች ላይ ስራዎችና በማናቸውም
ገቢዎች ላይ የሚሰበሰቡ ኪራይ የፔትሮሊየምና የጋዝ
ታክስ  በክልል መስተዳድር ባለቤትነት ስር ስራዎች ላይ የገቢ
 የፌዴራል መንግስት በሚገኙ የልማት ድርጅቶች ላይ ግብርና የሮያሊቲ
አካላት ከሚሰጧቸው የንግድ ትርፍ የሽያጭና ኤክሳይዝ ክፍያዎች
ፈቃዶችና አገልግሎቶች ታክስ
የሚመነጩ ክፍያዎች  በክልል መስተደድር አካላት ከሚሰጡ
 ከፌዴራል ቴምበር ፈቃዶችና አገልግሎቶች የሚመነጩ
ሽያጭ የሚሰበሰብ ቀረጥ ክፍያዎች፣ ከደን የሚገኝ ሮያሊት፣
የክልል ቴምበር ሽያጭ ቀረጥ
6. የፌዴራልና የክልል መንግስታት የወጪ ሃላፊነቶች
የፌዴራል መንግስት የክልል መንግስታት
 መከላከያ  ትምህርት፣ ጤና፣ ባህል፣ንፁህ
 የውጭ ጉደይ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት፣
 ከክልል አቅም በላይ በሆኑ የፀጥታ ሁኔታዎች ጣልቃ ክልላዊ መንገìC#
መግባት  ክልላዊ አስተዳደርና ፀጥታ፣
 ገንዘብ ማተም ክልላዊ የተፈጥሮ ሃብት
 ዋና ዋና መገናኛ አውታሮችን መዘርጋትና ማስተዳደር/ ጥበቃና ልማት
የአየር፣ የባቡር፣ የባህር፣ ፖስታ፣ ቴሌ# ሁለት ወይም  በሕገ መንግሥቱ ለØዴራል
ከሁለት ክልሎች በላይ የሚያገናኙ መንገዶች/ መንግሥት በተለይ ወይም
 ዋና ዋና የልማት ተቋሞችን መዘርጋትና ማስተዳደር ለØዴራል መንግሥትና
 የክልሎች የድጎማ በጀት መስጠት# የውጭ ዕዳ ክፍያ ለክልሎች በጋራ በግልፅ
 የኃይል ማመንጫዎች ግንባታÂ ስርጭት ያልተሰጠ ሥልጣን የክልል
ሥልጣን ይሆናል
7. የአገራችን ጥቅል ዓላማ ያለው ድጐማ
• ድጎማው በተግባር ጥቅል ዓለማ ሲኖረው የሕግ ማዕቀፍ ግን
የለውም
• ከፌዴራል መንግሰት ለክልሎች የሚሰጥ ድጎማ በህገመንግስቱ
መሰረት ለክልሎች የተመጣጠነ እድገት እንቅፋት መሆን የለበትም
ቢባልም፤
 ጥቅል ዓላማ ያለው ድጐማ ውጤትን ሳይሆን ክፍተትን ግምት ውስጥ
ስለሚያስገባ ዕድገትን ማመጣጠን አይችለም
 ጥቅል ዓላማ ያለው ድጐማ የሌሎች የፌዴራል መንግስትን ድጋፎች
ግምት ውስጥ ስለማያስገባ ክልሎችን ላያመጣጥን ይችላል
 በአዋጅ መሰረት ድጎማው ክልሎች ከፌዴራሉ ድጐማ እንዲላቀቁ
ማድረግ ቢጠበቅበትም ይህን እውን ለማድረግ የሚያስችል ስትራቴጅና
አሰራር የለም
 በብዙ መልኩ የተጠናከረ የህግ ማዕቀፍ የለውም
… ጥቅል ዓላማ
• የጥቅል ዓላማ ድጎማ ቋት አወሳሰን፤
 የቋቱ ምንጭ ከፌዴራል መንግሰት ገቢ ውስጥ የሚቆረስ የተወሰን ገቢ
ነው
 መጠኑ የሚወሰነው በየዓመቱ በሚደረግ ውሳኔ መሰረት ነው
 ቋቱን የሚሳተፉ ተቋማት
 የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር፣
 የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ እና
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ናቸው፡፡
 በቋቱ መጠን ውሳኔ ላይ ክልሎች ሃሳብ ከመሰጠት የዘለለ ተሳትፎ
የላቸውም
 በአማካይ 80 በመቶ የሚሆነውን ወጭያቸውን ክልሎች ከጥቅል
ዓላማ ድጎማ ድርሻ የሚሸፍኑ ቢኆንም የፌዴራሉ መንግሰት ድጎማ
የመሰጠት ህጋዊ ግዴታ የለበትም
… ጥቅል ዓላማ
• የጥቅል ድጐማው ክፍፍል፤
 ክፍፍሉ በቀመር መሰረት ነው
 ቀመሩ ምን መምሰል እንደሚገባው በህግ አልተመላከተም
 የቀመሩ ዝግጅት ሂደትን፣ የባለድርሻ ተሳትፎንና የቀመሩን መሰረታዊ
መርሆዎች ግልፅ በሆነ መልኩ የሚያሳይ የህግ ሰነድ የለም
 እስከ አሁን ድረስ ዘጠኝ የጥቅል ድጐማ ማከፋፊያ ቀመሮች ሲኖሩ
በሦስት የተለያዩ ታሳቢዎች ሊከፋፈሉ ይችላሉ፤
 ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1999 ዓ.ም ድረስ የነበሩት አምስት ቀመሮች
ሲዘጋጁ ጥቅል አመልካቾች ይመረጡና ለአመልካቾቹ ክብደት ይሰጥ ነበር
 ሁለተኛው ለየት ያለ ታሳቢ የነበረው በ1999ዓ.ም. የተዘጋጀ ቀመር ሲሆን
አሰራሩ የክልሎችን የፊስካል ክፍተት በሰው (Per Capital) በማየት ነበር
 በመቀጠል ያሉት ሦስት ቀመሮች የክልሎችን የወጭ ፍላጎት ሲገምቱ
ወጪውን ከአገልግሎት ተጠቃሚ/ ሥራ ጋር በማያያዝ ነው
… ጥቅል ዓላማ
• የድጐማው ክትትልና ቁጥጥር
 ሕገመንግስቱ የፌዴራሉ መንግስት ለክልሎች የሚሰጠውን ድጐማ
ኦዲትና ቁጥጥር እንደሚያደተርግ ደንግጓል
 በሁሉም የድጎማ ዓይነቶች ላይ ኦዲትና ቁጥጥር ማድረግ ይቻላል
ወይ? ከተቻለስ እንዴት የሚል ጥያቄም አልተቀመጠም፣ ስርዓትም
አልተዘረጋም
 በአዋጅ 251 መሰረት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ድጐማው በቀመሩ
መሠረት መፈፀሙን እንደሚከታተል ቢደነግግም፣ የተዘረጋ የአሰራር
ስርዓት የለም
 አዋጁ ድጐማው ያስገኘውን ፋይዳ በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ምክር
ቤቱ እንደሚያደርግ ቢደነግግም፣ ስርዓት አልተዘረጋም
 የድጎማ ዓላማ ነጥሮ ሳይወጣና የህግ ማዕቀፍ ሳይኖረው የፋይዳ
ዳሰሳ ጥናት ማካሄድም አዳጋች ሊሆን ይችላል
… ጥቅል ዓላማ
• የድጐማው መረጃ አቅርቦት
 በአዋጅ 251 የፌዴሬሽራ ምክር ቤት ቀመር ለማዘጋጀት አግባብነት
ካላቸው የአስፈፃሚ አካላት መረጃ ማግኘት እንደሚችል ተደንግጓል
 ተቋማት ያላቸውን መረጃዎች በወቅቱና በጊዜው ባይሰጡ
ስለሚመጣው ተጠያቂነት የተገለፀ ነገር የለም
 ለቀመሩ ብቻ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ማመንጨት ሲያስፈልግም
ተቋማትን የሚያስገደድ አሰራር የለም
• ጥቅል ድጐማው ከሌሎች ድጐማዎች ጋር ያለው ቁርኝት
 አንዳንድ ውስን ዓላማ ያላቸው ድጎማዎች የፌዴሬሽንን ቀመር
ይጠቀማሉ - ምንም እንኳን ታሳቢዎቹ የተለያዩ በመሆናቸው
ተመሳሳይ ባህሪ ሊኖራቸው ባይችልም
 ሌሎቹ የየራሳቸውን ቀመር ይጠቀማሉ
በመሆኑም ቅንጅት አለ ለማለት አይቻልም
… ጥቅል ዓላማ
• የፌዴሬሽንን ቀመር የሚያዘጋጀው ተቋም አደረጃጀት
 የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽ/ቤት የምክር ቤቱ የድጎማ በጀትና
የገቢዎች ድልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት
የድጎማ ማከፋፋያ ቀመሩን እንደሚያዘጋጅ በአዋጅ ተመላክቷል
 የቋሚ ኮሚቴው
ምን ዓይነት አቅጣጫ ነው መስጠት ያለበት
 አቅጣጫውስ መቼ ነው መስጠት ያለበት
 ጽ/ቤቱ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በስንት ጊዜ ውስጥ ነው ቀመሩን
አዘጋጅቶ ማቅረብ ያለበት
 አቅጣጫውስ በተደራጀ መልኩ በሰነድ ደረጃ ነው ወይ መቅረብ ያለበት
 ወዘተ የሚሉተን ጥያቄዎች የያዘ የህግ ሰነድ በአገራችን የለም
ከ 1987 እስከ 1999 ያገለገሉ ቀመሮች
የቀመሩ አመልካቾች ክብደት በመቶኛ ስራ ላይ የዋሉት
 የህዝብ ብዛት 30
 የልማት ደረጃ ልዩነት 25 1987 በጀት ዓመት
 የራስ ገቢ የመሰብሰብ ጥረት 20
 የ19985 በጀት ዓመት ካፒታል 15
 የክልሉ ቆዳ ስፋት 10
 የህዝብ ብዛት 33.3 1988፣1989
 የልማት ደረጃ ልዩነት 33.3
 የራስ ገቢና የበጀት ጥመርታ
33.3
 የህዝብ ብዛት 60 1990፣1991፣
 የልማት ደረጃ ልዩነት 1992
25
 የራስ ገቢና የበጀት ጥመርታ
15
o የህዝብ ብዛት 55
o የገቢ የማሰባሰብ ጥረት 15 1993፣1994፣
o የልማት ደረጃ ልዩነት 20 1995
o የድህነት ደረጃ 10
 የገቢ የማሰባሰብ ጥረትና አፈፃፀም 10 1996 - 1999
 የህዝብ ብዛት 65
 የልማት ደረጃ ልዩነት 25
ለአመልካቾቸ የተሰጠው ክብደት መለዋወጥና የለውጡ መጠን በመቶኛ
አመልካቾች ቀመሮች በበጀት ዓመታት
1987 1988-89 1990-92 1993-95 1996-99

የህዝብ ብዛት 30 33.3 60 55 65


ለውጡ በመቶኛ - 3.3 26.7 -5 10
ገቢ የመሰብሰብ ጥረት 20 33.3 15 15 10
ለውጡ በመቶኛ - 13.3 -18.3 - -5
ያለፈው ዓመት የካፒታል 15 - -
በጀት መጠን
የቆዳ ስፋት 10 - 10 - -
የዕድገት ልዩነት 25 33.3 15 20 25
ለውጡ በመቶኛ - 8.3 -18.3 5 5
የድህነት ሁኔታ/ ደረጃ - - - 10 -
ድምር 100 99.9 100 100 100
የአመልካቾቸ ክብደት መለዋወጥ
የአመልካቾችና ክብደታቸው መለዋወጥ
አመልካቾች ክብደት በመቶኛ ልዩነት አንፃራዊ ልዩነት
ከፍተኛ ዝቅተኛ በመቶኛ በመቶኛ

የህዝብ ብዛት 65 30 35 53.85


ገቢ የመሰብሰብ ጥረት 33.3 10 23.3 69.97
ያለፈው ዓመት የካፒታል በጀት 15 0 15 100.00
መጠን (1 ጊዜ ብቻ)
የቆዳ ስፋት (2 ጊዜ ብቻ) 10 0 10 100.00
የዕድገት ልዩነት 33.3 15 18.3 54.95
የድህነት ደረጃ (1 ጊዜ ብቻ) 10 0 10 100.00
የአመልካቾችና ክብደታቸው መለዋወጥ
በተለያዩ ቀመሮች የክልሎች ድርሻ በመቶኛ
ክልል የየክልሉ መቶኛ ድርሻ
1988-89 1990-92 1993-95 1996-99 ህዝብ ብዛት
ትግራይ 8.33 7.67 8.29 7.18 6.04
አፋር 3.61 5.04 5.47 3.75 1.97
አማራ 20.73 19.20 21.40 23.65 26.65
ኦሮሚያ 27.48 25.29 27.97 33.28 36.70
ሶማሌ 4.22 7.57 8.12 7.27 6.04
ቤ/ጉምዝ 2.63 3.63 4.12 2.00 0.88
ደቡብ 16.58 15.90 17.97 18.61 20.58
ጋምቤላ 2.20 2.80 3.16 1.45 0.34
ሐረሪ 1.01 1.78 1.54 1.12 0.27
አ/አበባ 12.28 7.34 - - -
ድሬዳዋ 0.93 3.78 1.96 1.69 0.53
ድምር 100 100 100 100 100
የክልሎች የነፍሰወከፍ ድርሻ በብር
የክልሎች የህዝብ ብዛትና ቀመሮች ንፅፅር
የክልሎች የህዝብ ብዛትና ቀመሮች ንፅፅር
የክልሎች ድርሻ በመቶኛ
የ 4 ቀመሮች ንፅፅር
የክልሎች ድርሻ መለዋወጥ (1987-1999)
ክልል የየክልሉ መቶኛ ድርሻ አንፃራዊ ልዩነት በመቶኛ
ከፍተኛው ዝቅተኛው ልዩነት ከከፍተኛው ከዝቅተኛው
ትግራይ 8.33 7.18 1.15 13.81 16.02
አፋር 5.47 3.61 1.86 34.00 51.52
አማራ 23.65 19.2 4.45 18.82 23.18
ኦሮሚያ 33.28 25.29 7.99 24.01 31.59
ሶማሌ 8.12 4.22 3.9 48.03 92.42
ቤ/ጉምዝ 4.12 2 2.12 51.46 106.00
ደቡብ 18.61 15.9 2.71 14.56 17.04
ጋምቤላ 3.16 1.45 1.71 54.11 117.93
ሐረሪ 1.78 1.01 0.77 43.26 76.24
አዲስ አበባ 12.28 0 12.28 100.00 -
ድሬዳዋ 3.78 0.93 2.85 75.40 306.45
የክልሎች ድርሻ መለዋወጥ
የቀመር ዓላማዎች መለያየት
• በ1990-92 ቀመር አመልካቾች አመራረጥ ላይ እንደ ዓላማ
የተያዙት፤
– ሀብት ለሁሉም ዜጎች በዕኩልነት ማዳርስ፣
– በክልሎች መካከል ያለውን የልማት ደረጃ ልዩነት ማጥበብ፣
– የገጠሩን ልማት ማፋጠንና፣ እና
– ክልሎች የተሻለ ገቢ እንዲሰበስቡ ማበረታታት የሚሉ ነበሩ፡፡
• በ1993-95 ቀመር ላይ እንደ ዓላማ የተቀመጡት ነጥቦች፤
– ዋናው ዓላማ የክልሎችን የወጭ ክፍተት ለማጥበብ ሲሆን
– እንደ ተጨማሪ ዓላማዎች የተቀመጡት ደግሞ
በክከልሎች መካከል ያለውን የፊስካል አለመመጣጠን ማጥበብ እና
የክልሎች ገቢ አሰባሰብ ማበረታትት የሚሉት ነበሩ፡፡
8. የተለየ አሰራር ያስፈለጉበት ምክኒያቶች
• አሰራሩን/ አተያዩን ለመቀየር ያስፈለገበት ምክኒያቶች
– ለአመልካቾችና ክብደታቸው መለዋወጥ ተጨባጭ፣ አሳማኘና በቂ
ምክኒያቶች አለመኖር
– በተለያዩ ቀመሮች መሰረት የክልሎች ድርሻ ለውጡ ከፍተኛ መሆኑ እና
በየጊዜው መዋዠቁ
– የመደበኛንና የካፒታል ወጭን ፍላጎቶች ድርሻ በተጨባጭ፣ አሳማኘና በቂ
በሆኑ ምክኒያቶች መወሰን አለመቻል
– የድጐማው ዓላማ በግልጽ አስቀምጦ ያለመነሳት
– በቀመር ዝግጅቱ የክልሎች ተሳትፎ አነስተኛ መሆን
– የክልሎችን የወጭ ፍላጎቶችና ገቢ የመሰብሰብ አቅም በትክክል በመገመት
የበጀት ክፍተታቸውን ማወቅ አለመቻል
– የክልሎችን የወጭ ግዴታ የማያመላክቱ መረጃዎችን መጠቀም (ለምሳሌ
አስከ 1993 በጀት ዓመት የነበሩ ቀመሮች የቴሌኮሚኒኬሽንና የኤሌክትሪክ
ክልላዊ ስርጭትን ከክልሎች ዕድገት አንፃር ተመልክተዋል)
9. የአዲሱ ቀመር አሰራር ዓላማና ታሳቢዎች
• ዓለማው፡- የክልሎችን የፊስካል አቅም ማመጣጠን ነው
• ታሳቢዎች፡- ክልሎች የተመጣጠነ የፊስካል አቅም ካላቸው
የተመጣጠነ አገልግሎት ለክልላቸው ኑዋሪዎች ማቅረብ
ይችላሉ የሚል ነው
• የፊስካል አቅማቸውን ለማመጣጠን፤
– የክልሎች የወጭ ፍላጎትና የገቢ አቅም ዳሳሳዎች ተካሂደው
ክፍተታቸው ይታወቃል
– ለጥናቱ አስተማማኝና ገለልተኛ መረጃዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ
– የወጭ ፍላጎትና የገቢ አቅምን ለመለካት የሚያስችሉ መረጃዎች
በግምት ሳይሆን በተጨባጭ የክልሎችን ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች
መሰረት በማድረግ ይመረጣሉ
– ክልለች በሂደቱ በየደረጃው እንዲሳተፉ ይደረጋል
የክልሎች የወጭ ዳሰሳ አመልካቾች
በአዲሱ የቀመር አሰራር በተለያየ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉ የክልሎች ወጪ አመልካቾች
2000-2001 2002-2004 2005-2009
1. አስተዳደርና 1. አስተዳደርና ጠቅላላ 1. አስተዳደርና ጠቅላላ
ጠቅላላ አገልግሎት አገልግሎት አገልግሎት
2. ትምህርት 2. ትምህርት 2. ትምህርት
3. የገጠር መንገድ 3. የገጠር መንገድ 3. የገጠር መንገድ
4. የመጠጥ ውሃ 4. የመጠጥ ውሃ 4. የመጠጥ ውሃ
5. ጤና 5. ጤና 5. ጤና
6. ግብርና 6. ግብርና እና የተፈጥሮ ሃብት 6. ግብርና እና የተፈጥሮ ሃብት
7. ጥቃቅንና አነስተኛ 7. ጥቃቅንና አነስተኛ
8. የስራና ከተማ ልማት 8. የስራና ከተማ ልማት
9. የክልሎች የዋጋ ልዩነት ተፅኖ 9. የአካባቢ ጥበቃ
10. የክልሎች የዋጋ ልዩነት
የክልሎች የገቢ አቅም ዳስሳ አመልካቾች
በአዲሱ የቀመር አሰራር በተለያየ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉ የክልሎች የገቢ አመልካቾች

2000-2001 2002-2004 2005-2009

1. የደመወዝ ገቢ ግብር 1. የደመወዝ ገቢ ግብር 1. ከቅጥር የሚገኝ ገቢ ግብር


2. የእርሻ ስራ ገቢ ግብር 2. የእርሻ ስራ ገቢ ግብር 2. የግብርና ገቢ ግብር
3. የግብርና መሬት 3. የግብርና መሬት 3. የመሬት መጠቀሚያ ክፍያ
መጠቀሚያ ክፍያ መጠቀሚያ ክፍያ
4. የንግድ ትርፍ ግብር 4. የንግድ ትርፍ ግብር 4. ከእንስሳት ከሚገኝ ገቢ ግብር
5. የጫት ቀረጥ 5. የሽያጭ ታክስ 5. የንግድ ስራ ገቢ (የትርፍ)
ግብር
6. ተጨማሪ እሴት ታክስ 6. ተጨማሪ እሴት ታክስ 6. ተርን ኦቨር ታክስ
7. የመድሃኒት ሽያጭና 7. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ
የህክምና አገልግሎት ክፍያ
በአዲሱ አሰራር በተለያዩ ቀመሮች የክልሎች ድርሻ
ክልል የየክልሉ መቶኛ ድርሻ
2002-04 2005-09 2010-12
ትግራይ 7.04 7.18 6.03

አፋር 3.34 3.15 3.02

አማራ 23.33 23.17 21.6

ኦሮሚያ 32.53 32.50 34.46

ሶማሌ 8.43 8.14 9.98

ቤ/ጉምዝ 1.96 2.10 1.83

ደቡብ 19.90 20.10 20.11

ጋምቤላ 1.57 1.50 1.33

ሐረሪ 0.89 1.00 0.76

ድሬዳዋ 1.01 1.16 0.88

ድምር 100 100 100


የክልሎች የነፍሰወከፍ ድርሻ በብር
በአዲሱ አሰራር ቀመሮች የክልሎች ድርሻ በመቶኛ
የሦስቱ ቀመሮች ንፅፅር
የክልሎች ቀመር ድርሻ መለዋወጥ (2002-2012)
ክልል የየክልሉ መቶኛ ድርሻ አንፃራዊ ልዩነት በመቶኛ
ከፍተኛው ዝቅተኛው ልዩነት ከከፍተኛው ከዝቅተኛው
ትግራይ 7.18 6.03 1.15 16.02 19.07
አፋር 3.34 3.02 0.32 9.58 10.60
አማራ 23.33 21.6 1.73 7.42 8.01
ኦሮሚያ 34.46 32.5 1.96 5.69 6.03
ሶማሌ 9.98 8.14 1.84 18.44 22.60
ቤ/ጉምዝ 2.10 1.83 0.27 12.86 14.75
ደቡብ 20.11 19.9 0.21 1.04 1.06
ጋምቤላ 1.57 1.33 0.24 15.29 18.05
ሐረሪ 1.00 0.76 0.24 24.00 31.58
ድሬዳዋ 1.16 0.88 0.28 24.14 31.82
የአዲሱ ቀመሮች መለዋወጥ በመቶኛ
10. የአሮጌውና የአዲሱ አሰራር ንፅፅር
ከ1987-1999 በጀት ዓመት ከ2002-2012 በጀት ዓመት
ክልል ልዩነት አንፃራዊ ልዩነት በመቶኛ ልዩነት አንፃራዊ ልዩነት በመቶኛ
ከከፍተኛው ከዝቅተኛው ከከፍተኛው ከዝቅተኛው
ትግራይ 1.15 13.81 16.02 1.15 16.02 19.07
አፋር 1.86 34 51.52 0.32 9.58 10.6
አማራ 4.45 18.82 23.18 1.73 7.42 8.01
ኦሮሚያ 7.99 24.01 31.59 1.96 5.69 6.03
ሶማሌ 3.9 48.03 92.42 1.84 18.44 22.6
ቤ/ጉምዝ 2.12 51.46 106 0.27 12.86 14.75
ደቡብ 2.71 14.56 17.04 0.21 1.04 1.06
ጋምቤላ 1.71 54.11 117.93 0.24 15.29 18.05
ሐረሪ 0.77 43.26 76.24 0.24 24 31.58
ድሬዳዋ 2.85 75.4 306.45 0.28 24.14 31.82
የክልሎች ቀመር ድርሻ መለዋወጥ ደረጃ
11. እስከ አሁን ድረስ ያልተቀረፉ ውስንነቶች
• በቂ የህግ ማዕቀፍ አለመኖር
• በቂ የአደራጃጀት አለመኖር
• በቂ የተዘረጋ አሰራር አለመኖር
• ለድጎማ ክፍፍል የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ መሆን
አሰግናለሁ

You might also like