You are on page 1of 2

ዳግም የተፈጠርነዉ ለምንድ ነዉ?

 እግዚአብሔርን እንድናመልክ ነዉ

 መልካሙን የእርሱ ሥራ አንድንሰራ ነዉ ኤፈ 2፡10

 በጎነቱን እንድናወራና እንድናገር ነዉ 1 ጴጥ 2፡9-10

የእርሱን በጎነትና መልካምነት የሚናወራዉ ደግሞ በወንጌል በኩል ነዉ::

ወንጌል ማለት:-

 ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንዴሆነና በሥጋ እንደተወለደ፣ ስለ ሰዎቸ ሐጢአትም ከሞተ ቦኃላ


እንደተነሣ ያበስራል” ሮሜ 1፡3-4፡፡

 የእግዚአብሔር የክብር ኃይል የሆነዉ አዳኛችን ኢየሱስን ያሳያል 2 ቆ 4፡4፣

 የሰላም ምንጭ የሆነልን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ነዉ ኤፈ 2፡15፣ 20 ና 21፣ 6፡15፡፡

 ሲለዚህ ወንጌል ማለት አስደሳች፣ ድንቅ፣ የሚሥራች፣ ያልዳኑትን የሚጠራ፣ ላልሰሙት የሚናሰማና
ሕያዉ ምስክርነት ያለዉ የኢየሱስ መልዕክት ነዉ፡፡

ወንጌል ስሰበክ ምን ይሆናል?

 መልካም ምስክር ይሆናል ፡፡ ሉቃ 3፡18፣

 ለታሰሩት መፈታት ለተጠቁት ነጻነት ነዉ ፡፡ ሉቃ 4፡17-19

 ከተለያዩ እስራት ነጻ ያወጣል ፡፡ ሉቃ 7፡2

ወንጌል ለምን ይሰበካል?

 ለሰዉ ልጅ ደኄንነት የሚያስፈልግና አምላክ የሆነዉን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከላይ ከክብሩና
ከዙፋኑ ያመጠዉ ትልቁ ተልዕኮ ስለሆነ ይሰበካል ማቴ 28፤18-20 ማር 16፡15-17 ሉቃ 24፡44፣ ሐዋ 1፡
8፡፡

 አምላክነቱን እንድያጥና ዝቅ ዝቅ እንድል ያደረገበት ስለሆነ ይሰበካል (ፍል 2፡5-10)፡፡

 ክርስቶስ የጠፋዉን ሊፈልግና ሊያድን ስለመጣ የክርስቶስ ወንጌል ይሰበካል (ሉቃ 19፡10)፡፡

 በስብከት ሞኝነት በኩል ለሚድኑት የእግዚአብሔር በጎ ፍቃድ ስለሚሆንላቸዉ ነዉ (1 ቆሮ 1፡22)፡፡


 ካልተሰበከና ካለተነገር ሰዎች ስለማይድኑ በወንጌል ለምድኑ ኢየሱስ ክርስቶስ መሰበክ ስላለበት ነዉ
(ሮሜ 10፡9-17)፡፡

 የአዳኙ ብቸኛ ስምና የሚያድን ሰለሆነ ለሰዎች ሁሉ ማብሰር ስለሚያስፈልግ ነዉ ፍል 2፡9-11፡፡

 “መዳን በለላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ
የለም” (ሐዋ 4፡12)፡፡

 ክርስቶስ “ለሐጢአታችን ብቻ አይደለም ነገር ግን ለዓለም ሐጢአት ሁሉ እንጅ” ስለተስዋ(1 ዮሐ 2፡


2)፡፡

 ሰዎችን ሁሉ የሚያድን ታላቅ የደስታ ምሥራች ስለሆነ (ኢሳ 40፡9-10፣ ሉቃ 2፡8-11)

 ለሰዎች ሁሉ የድነታቸዉ ድምጽና ኃይል የሆነዉ ጌታችን ኢየሱስ እዉነት፣ መንገድና ሕይወት እኔ ነኝ
ከእኔ በቀር ወዴ አብ የሚያደርስ ሌላ መንገድ የለም ስላለ ስለዚህ እንሰብካለን (ዮሐ 14፡6)፡

ወንጌል ለማን ይሰበካል?

 ወንጌል ለሰዉ ዜር ሁሉ ይሰበካል(ዘፍ 3፡15)፡፡

 ለወንጌል ከሰዎች ለሰዎች ይሰበካል ለምሳሌ ወዴ ሰማርያ የገቡ ጉንድሾች እኛ ያጌኜነዉ ለለሎች
እናበስር ስሉ እናያለን 2 ነግ 6፣

 በጎ ማን ያሳየናል ለምሉ ለምጨነቁና ለተጨነቁ ይሰበካል(መዝ 4፡6)

 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሳዉ በኃላ ይህ የወንጌል ሥራ ለአንድ ወገን ብቻ ወይንም ለእስራኤል
ሰዎች ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ የወንጌል ሥራ እንድሰሩ በአራቱም ወንጌል በመጨረሻ ምዕራፎች
(ማቴ 28፡16-20፣ ማር 16፤15-19 ሉቃ 2:8-11, 4:16-20 24፡44-49 ዮሓ 20፡21)

 ለሐዋርያት የወንጌል ሀደራ እንዲወጡና በጊዜያቸዉ እንድሠሩ ሃላፍነት ሰጣቸዉ እና (ሐዋ 1፡8) ላይ
እናገኛለን፡፡ በእነዝህ ቦታዉች እንደሚንመለክተዉ “አህዛብን ሁሉ”፣ “ወደ ዓለም ሂዱ”፣ “ለአህዛብ
ምስክሮቸ ትሆናለችሁ”

 “ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ፀጋ እንደሆነ ተገልጦዋል (ቲቶ 2፡11)፣

 እግዚአብሔር አንዲያ ልጁ እስክሰጥ ድረስ ዓለሙን እንደሁ ወዶአልና (ዮሐ 3፡16)

መቼ መቼ መሰበክ አለበት?

ጳዉሎሰ ጢሞቴዎስ በመከረ ጊዜ ቃሉን ስበክ በጊዜም አለ ጊዜ በመሰብክም ጽና አለ 2 ጢሞ 4፡4፣

You might also like