You are on page 1of 16

A&B Law Office

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ


የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የሰ/መ/ቁ 228726

ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ/ም

ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር)

እንዳሻው አዳነ

ተሾመ ሽፈራው

መላኩ ካሳዬ

ነጻነት ተገኝ

አመልካች፡- ወ/ሮ ሰገድ ሞገስ

ተጠሪ፡- አቶ አወቀ ተገኝ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች ሰኔ 7/2014 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የአ/ብ/ክ/መ ጠቅላይ

ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 03-110565 በቀን 17/09/2014 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ

የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በጎንደር

ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ባቀረቡት አቤቱታ ነው፡፡

ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው በስር ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ በቀን 07/01/2011 ዓ.ም ባቀረቡት

አቤቱታ ከአሁን አመልካች ጋር ህጋዊ ጋብቻ ፈጽመን ለ 2 ዓመታት ያህል እንዲሁም ከመጋባታችን

በፊት በወዳጅነት አብረን የኖርን ሲሆን በዚሁ ግኑኝነት ሁለት ልጆች ማለትም እዮብ አወቀ ዕድሜው 6

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

ዓመት ከ 5 ወር የሆነው እና ሚካኤል አወቀ ዕድሜው 2 ዓመት ከ 5 ወር የሆነውን ወልደናል፡፡ ነገርግን

ያፈራነው የጋራ ንብረት የለም፡፡ በመሆኑም በመካከላችን ያለው ጋብቻ በፍ/ቤት ውሳኔ እንዲፈርስ

በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

አመልካች ባቀረቡት መልስ ጋብቻ የፈፀምነው መስከረም 8/2009 ዓ.ም ነው፤ ጋብቻው

እንዳይፈርስ እቃወማለሁ፤ ከወለድናቸው ልጆች ውስጥ ህፃን ሚካኤል አወቀ ሲወለድ ጀምሮ ማየት፣

መስማት፣ መናገር፣ መንቀሳቀስ የማይችል በመሆኑ ልጁን በብቸኝነት ማሳደግ አልችልም፡፡ ጋብቻ

ከመፈፀማችን በፊት ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በባልና በሚስትነት ለ 7 ዓመት አብረን ኖረናል፤ በዚህ ጊዜ

ውስጥ ሁለቱ ልጆች ተወልደዋል፡፡ በ08/01/2009 ዓ.ም የተደረገው ውል ፍላጎቴን መሰረት ያላደረገ

ነው፡፡ ከጋብቻ ውሉ በፊት እንደባልና ሚስት ባለ ግንኙነት 3 ዓመትና ከዚያ በላይ የቆዩ ከሆነ ያፈሯቸው

ንብረቶች የጋራ ይሆናሉ፡፡ በመሆኑም ከሳሽ በሆቴል ንግድ ሥራ ዘርፍ የተሰማራና እውቀት በር ሆቴል

የተባለ ድርጅት ያለው በመሆኑ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ሆቴሉ ያስገኘው ገቢ የጋራችን ነው፡፡ እንዲሁም

አዘዞ ቀበሌ አካባቢ በ2007 ዓ.ም ተጀምሮ በመጠናቀቅ ላይ ያለ ባለ 1 ፎቅ የመኖሪያ ቤት በባልና

ሚስትነት አብረን መኖር ከጀመርንበትና ልጅ ከወለድን በኃላ የተገነባ በመሆኑ የጋራ ሃብታችን ነው

በማለት መልስ ሰጥተዋል፡፡

በሌላም በኩል ተከሳሽ ባቀረቡት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የጋብቻ ውል ስምምነቱ ሲፈፀም ግራ

ቀኛችን በውሉ ውጤት ላይ ተወያይተን ሳይሆን የራሱን ሃሳብ እኔ በማላውቀው መንገድ ከሌላ ሰው

አስፅፎ እና አዘጋጅቶ በመምጣት እንድፈርምና ይህን ማድረግ ካልቻልኩ አራሲቱን (በአራስነቴ)

እንደሚያስወጣኝ ስለነገረኝና ማስገደድ ሲፈጽምብኝ ውሉን ሳልረዳው ነፃ ፈቃድ ሳልሰጥ ውሉ ላይ

እንድፈርም አድርጎኛል፡፡ በመሆኑም ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 07/01/2009 ዓ.ም ድረስ እንደ ባልና

ሚስት አብረን ቆይተናል፤ በዚህ መልኩ የመኖር ውጤት ደግሞ አብረን እያለን የተፈራ ሃብት የጋራ

ማድረግ በመሆኑ ከእውቀት በር ሆቴል ገቢ ላይ በድርሻየ ያላካፈለኝን ገቢ ብር 1,800,000.00 ( አንድ

ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ እንዲከፍል) እንዲያካፍለኝ ይወሰንልኝ ፤ አዘዞ ቀበሌ የሚገኘው በ2011

ዓ.ም የተጠናቀቀ ባለ 1 ፎቅ የመኖሪያ ቤት የጋራ ተብሎ እንዲወሰንልኝ፤ ቤቱ የግሉ ነው ከተባለም

ለቤቱ መስሪያ የወጣው ወጪ ከጋራ ገቢያችን በመሆኑ የድርሻየን ብር 500,000.00 (አምስት መቶ

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

ሺህ) እንዲከፍለኝ፤ እንዲሁም የጋራ ንብረት የሆነ ሚኒባስ መኪና ተሽጦ የተገኘው ገንዘብ ድርሻየን ብር

187,500.00 (መቶ ሰማንያ ሰባት ሺህ አምስት መቶ) እንዲከፍለኝ፤ የልጆች ቀለብም እንዲከፍል

ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ለተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ከሳሽ በሰጡት መልስ እንደባልና ሚስት አልኖርንም፤ በአጋጣሚ

ተገናኝተን ልጆች ወልደናል፤ ይህ አይካድም፤ ነገር ግን ይህ የአብሮ የመኖርን መስፈረርት አያሟላም፤

በማህበራዊ ግንኙነትም ህብረተሰቡ እንደባልና ሚስት አይቆጥረንም፤ ያ ቢሆን ኖሮ በጋብቻ ውላችን

ላይ ስለነበረው ግንኙነት ባስቀመጥን ነበር፡፡ ከዚህም ሌላ በፅሁፍ ያለን ውል በምስክር ማስተባበል

እንደማይቻል በህጉ የተደነገገ በመሆኑ በምስክር ላስረዳ ብላ ማቅረቧ የህግ ድጋፍ የለውም፡፡ ውሉን

ወዳና ፈቅዳ ያደረገችው እንጂ የደረሰባት ተፅዕኖ የለም፤ ያቀረበችው ምክንያት ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1973

አንጻር ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ደረሰባት የሚያሰኝ አይደለም በማለት በንብረቱም ረገድ የተጠቀሱት

ንብረቶች የግላቸው እንደሚሆኑ በውሉ ስለተመለከተ የቀረበው ጥያቄ ውድቅ እንዲደረግ

ክርክራቸውን አቅርበዋል፡፡

ጉዳዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ አመልካችና ተጠሪ ውሉን

ወደውና ፈቅደው ግልጽ ስምምነት በማድረግ ስለንብረታቸው ተስማምተው እያሉ የአሁን አመልካች

የጋራ ንብረት በማለት የገቢ መጋራት ጥያቄ ማቅረባቸው ተገቢ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን የጋብቻ ውል

ካደረጉበት ቀን 08/01/2009 ዓ.ም ጀምሮ ያለ የሆቴሉ ገቢ የጋራ በመሆኑ ከግብር አስገቢው መ/ቤት

በተገለፀው የገቢ መጠን መሰረት ወጪው ተቀንሶ እኩል እንዲካፈሉ፤ በጋብቻ ውላቸው ላይ ግራቀኙ

በግላቸው የነበራቸው ንብረት የግላቸው ሆኖ እንዲቀጥል የተስማሙ ስለሆነ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ

እስከ 08/01/2009 ዓ.ም ላለው ጊዜ የአሁን አመልካች የጠየቀችውን ልታገኝ አይገባም፤ የልጆች ቀለብ

ብር 3000.00 ይክፈል በማለት ወስኗል፡፡

በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በበኩሉ በስር

ፍርድ ቤት የቀረበውን ማስረጃ ይዘት መርምሮ የምስክሮች ቃል ሲመዘን የአካባቢው ማህበረሰብ እና

የሚያውቃቸው ሰው በሙሉ ግራቀኙን እንደ ባልና ሚስት የሚያዩዋቸው እንደነበር አስረድተዋል፤

ይህንንም የአመልካች ምስክሮች እና የተጠሪ 1 ምስክር የሚያስረዱ ሲሆን ተጠሪ እራሱ የምስክርነት

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

ቃሉን ሲሰጥ የነበራቸውን ግንኙነት ወደ ጋብቻ ከፍ እንዲል የተስማሙት ቤተሰቦቿ በነበራቸው

ግንኙነት ደስተኛ ባለመሆናቸው መሆኑን ገልጿል፤ ይህ ደግሞ የግራ ቀኙ ግንኙነት ተራ ከመሆን ባለፈ

እንደባልና ሚስት መሆኑን ነገር ግን የማህበረሰቡ ልምድና ባህል ወደሚያከብረው ጋብቻ ከፍ እንዲል

ያደረጉት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ስለዚህ አመልካች ግንኙነታቸው እንደባልና ሚስት እንደነበር

አስረድታ እያለ በ2009 ዓ.ም የጋብቻ ውል በመፈፀማቸው ብቻ ቀድሞ የነበረውን በህግ ተቀባይነት

ያለው እንደባልና ሚስት ግንኙነት የልነበረ ሊያደርገው አይችልም በማለት የስር ፍርድ ቤት ያሳለፈውን

ውሳኔ ሽሯል፡፡ ይህን ተከትሎም ከ2003 እስከ 2009 ዓ.ም የነበራቸው ግንኙነት እንደ ባልና ሚስ ነው፤

በዚህ ጊዜ ውስጥም ሆነ ከጋብቻ በኃላ እስከ ፍቺ ድረስ ከሆቴሉ የተገኘው ገቢ የጋራ ነው፤ የመኖሪያ

ቤቱም በግንኙነታቸው ጊዜ የተጀመረና መሰረቱ የወጣ እንዲሁም ጋብቻ ከፈፀሙ በኃላ የማጠናቀቂያ

ስራዎች የተሰሩለት በመሆኑ ቤትና ቦታው የጋራ ነው፤ የልጅ ቀለቡም ተሻሽሎ በተለይ 2ኛው ልጅ

ያለበትን የጤንነት ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት ለሁለቱ ልጆች በየወሩ 6000.00 ሊከፍል ይገባል

በማለት ወስኗል፡፡

የአሁን ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኝት ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ

ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ ችሎቱም ጉዳዩን መርምሮ ግራቀኙ ወደውና ተዋደው የጋብቻ

ውል መፈራረማቸውን ውላቸው የሚያስረዳ ሆኖ እያለ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ከ2003-2009 ድረስ

ህብረተሰቡ በሚያውቀውና በሚረዳው መልኩ እንደባልና ሚስት አብረው ይኖሩ እንደነበር በምስክሮች

ስለተነገረ ከ2003-2009 እንደባልና ሚስት ኖረዋል በ8/01/2009 ዓ.ም የተፈፀመው የጋብቻ ውሉም

የግራቀኙን አስቀድመው እንደባልና ሚስት የነበራቸውን ግንኙነት የሚያመለክት እንጂ ቀሪ የሚያደርግ

አይደለም በማለት የጋብቻ ውሉን ወደጎን በመተው የሰው ምስክርን መሰረት በማድረግ ከጋብቻ

ውጪ እንደባልና ሚስት ለኖሩበት ጊዜም ሆነ ከጋብቻው በኃላ እስከፍቺ ድረስ ከሆቴሉ የተገነኘውን ገቢ

እንዲካፈሉ መወሰኑ፤ እንዲሁም መኖሪያ ቤቱም የጋራ ሀብት ነው በማለት መወሰኑ ከማስረጃ ምዘና

አንፃር የፅሑፍ ውል እያለ በምስክሮች ቃል ተመስርቶ የሰጠው ውሳኔ በመሆኑ በአግባቡ ሆኖ

አልተገኘም በማለት ውሳኔውን ሽሯል፡፡ የጋብቻ ውሉ ከጋብቻ በፊት የተፈራ ንብረት ከጋብቻ በፊት

ለነበረው ግለሰብ ይሆናል ስለሚል የአሁን አመልካች ከ2003 – 2009 ዓ.ም ድረስ ያለውን የሆቴሉን

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

ገቢ ልትካፈል አይገባም፤ መኖሪያ ቤቱም በጋብቻ ውሉ የተጠሪ ነው በማለት ስለተስማሙ ቤቱ

የተጠሪ ነው በማለት ወስኗል፡፡

የአሁን አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኝት የሰበር አቤቱታ ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር

ሰሚ ችሎት ያቀረቡ ሲሆን ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ ከቀረቡት ማስረጃዎች ይዘት አኳያ ሲታይ ከጋብቻ

በፊት እንደ ህጉ አነጋገር ጥበቃ የሚደረግለት እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት ነበራቸው

ለማለት የሚቻል ሆኖ አላገኘነውም፤ በዚህ ጊዜ ተገኙ የተባሉት ንብረቶች በግንኙነቱ ውስጥ የተፈሩ

ናቸው የሚያሰኝ ካለመሆኑም በላይ ግንኙነታቸው እንደባልና ሚስት ግንኙነት ነበር የሚባል ቢሆን

እንኳን ጋብቻቸውን ሲፈጽሙ ከጋብቻ በፊት የነበሩትን አከራካሪ ንብረቶች የተጠሪ የግል ንብረት

እንዲሆኑ እስከተስማሙ ድረስ የተጠሪ የግል ንብረት ከመሆን የሚድኑም አይሆንም በማለት ጠቅላይ

ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አፅንቷል፡፡

የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ነው፡፡ አመልካች ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት

ማመልከቻ ግራቀኝ የጋብቻ ውል የፈፀምነው መስከረም 8 / 2009 ዓ.ም ነው፤ ከዚህ ጊዜ በፊት

ከ2003 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2009 ዓ/ም ድረስ እንደ ባልና ሚስት አብረን ኖረናል፤ አንድ የጋብቻ ውል

ውጤት የሚኖረው ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑ እየታወቀ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት እና ሰበር ሰሚ

ችሎት ከጋብቻ ውሉ በፊት የነበረን እንደ ባልና ሚስት የመኖር ጉዳይ የጋብቻ ውል እያለ የሰው ማስረጃ

በመስማት ይህንኑ መሰረት በማድረግ ውሳኔ መስጠት በህጉ አግባብ አይደለም በማለት የሰጡት

ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለተፈፀመበት ነው፡፡ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ከ2003 እስከ 2009

ዓ.ም ድረስ ያለውን ጊዜ ከ2009 ዓ.ም በኃላ ካለው ጊዜና ከውሉ ይዘት ጋር በማምታታት እንዲሁም

በህግ ከተሰጠው ስልጣን አልፎ የፍሬ ነገር ጉዳይ ላይ በስር ፍርድ ቤቶች ሳይረጋገጥ የራሱን ድምዳሜ

በመውሰድ የሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው፡፡ አመልካችና ተጠሪ በ2009 ዓ.ም

አደረግነው የተባለው የጋብቻ ውል ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ የነበረውን እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር

ውጤት የማይቀይር ሆኖ እያለ በውሉ ንብረቱ የግል ነው በሚል ተስማምተሻል በማለት አመልካች

የምከራከርበትንም ሆነ እየጠየኩት ያለሁትን ዳኝነት ባለመረዳት የውሉን መኖር ብቻ በመመልከት

ውሳኔ መሰጠቱ ስህተት ያለበት በመሆኑ ሊሻር ይገባል፡፡ በአጠቃላይ ውሳኔው ተሸሮ የማዕከላዊ ጎንደር

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሆቴሉን ገቢ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ ያለውን እንዲሁም

መኖሪያ ቤቱ የጋራ ነው ሲል የሰጠው ውሳኔ እንዲፀና፤ መኖሪያ ቤቱ የጋራ ሀብት የማይሆንበት

ምክንያት ቢኖር ከጋራ ሀብት የወጣውን ወጪ እንድንካፈል ይወሰንልኝ በማለት ቅሬታቸውን

አቅርበዋል፡፡

ቅሬታው ተመርምሮ አመልካች ከተጠሪ ጋር ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እንደ ባልና ሚስት ከጋብቻ

ውጭ በሆነ ግንኙነት ኖረናል በማለት የሚያቀርቡት መከራከሪያ የጋብቻ ውል በ2009 ዓ.ም

መፈጸማቸው ተጠቅሶ የአመልካች ክርክር ውድቅ የተደረገበትን አግባብነት ለማጣራት በሚል ጉዳዩ

ለዚህ ሰበር ችሎት እንዲቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዲሰጡበት ተደርጓል፡፡

ተጠሪ ባቀረቡት መልስ የስር ክርክራቸውን አጠናክረው አመልካችና ተጠሪ እንደ ባልና ሚስት

አብረን አልኖርንም፤ ልጆች የወለድነው ከጋብቻ ውጪ በነበረን ግንኙነት ነው፤ አመልካች የጋብቻ

ውሉን የፈረመችው ቤተሰቦቿ በተገኙበት ወዳ እና ፈቅዳ ነው፤ ግልጽ የሆነ ውል ባለ ጊዜ በሌላ ማስረጃ

ማስረዳት እንደማይቻል የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 125656 አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል፤ አመልካች እና

ተጠሪ በአንድ ጣሪያ ስር ሆነን ያፈራነው ንብረት የለም፤ አለ ቢባል እንኳን ንበረቱ ለጋራ ጥቅም

እንደዋለ እንደሚቆጠር የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 27697 አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል፤ በአመልካች እና

በተጠሪ መካከል የፈፀምነው ጋብቻ ውጤት የሚኖረው ከተቋቋመበት ቀን አንስቶ እንጂ ወደ ኋላ ሄዶ

ተፈጻሚ አይሆንም፤ ይህንን ጉዳይ በተመለከተም የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/መ/ቁ 41896 አስገዳጅ ውሳኔ

ሰጥቷል፡፡ የክልሉ ሰበር ችሎት በህግ ጥበቃ የሚደረግለት እንደባልና ሚስት አብሮ መኖርን በተመለከተ

ፍሬ ነገሩን መመርመሩ የህግ ጥሰት ነው ሊባል አይገባም፤ ቀድመን እንደባልና ሚስት ብንኖር ኑሮ

በ2009 ዓ.ም የጋብቻ ውል አንይዝም ነበር፤ እንደባልና ሚስት ለመኖራችንም በምስክር

አላረጋገጠችም፤ ስለሆነም የክልሉ ሰበር ችሎት ሙሉ መዝገቡን ከምስክሮች ቃል ጋር ጨምሮ

በመመልከት እንደባልና ሚስት ስለመኖራችን በምስክር ያላረጋገጠች መሆኑን አረጋግጦ ክፈተቱን

ደፍኖ መወሰኑ በአግባቡ ነው፡፡ መኖሪያ ቤቱን በተመለከተም የአመልካች ንብረቷ ያልተቀላቀለበት

መሆኑ ተረጋግጦ የተወሰነ በመሆኑ ቅሬታው ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል፡፡ አመልካችም

ክርክራቸውን አጠናክረው የመልስ መልስ አቅርበዋል፡፡

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

ከፍ ሲል በአጭሩ የገለጽነው የጉዳይ አመጣጥ ሲሆን የግራ ቀኙን ክርክር ቅሬታ ከቀረበበት

ውሳኔ እና ከተገቢው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ የተፈፀመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን

መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው አመልካች በተፅዕኖ የተፈፀመ ነው በማለት ክርክር ቢያቀርቡበትም

ግራቀኙ መስከረም 8/2009 ዓ.ም የጋብቻ ውል የተባለ ሰነድ መፈራረማቸውን አልተካካዱም፡፡ በሌላ

በኩል አመልካች ከዚህ ጊዜ በፊት ከ2003 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2009 ዓ/ም ድረስ እንደ ባልና ሚስት

አብረን ኖረናል፤ ይህ ግንኙነት በህጉ በንብረታችን ረገድ ውጤት አለው በማለት ይከራከራሉ፡፡ ተጠሪ

በበኩላቸው እንደ ባልና ሚስት አብረን አልኖርንም፤ ልጆች የወለድነው ከጋብቻ ውጪ በነበረን

ግንኙነት ነው፤ አመልካች እና ተጠሪ በአንድ ጣሪያ ስር ሆነን ያፈራነው ንብረት የለም ብለዋል፡፡ የስር

ፍርድ ቤቶች ከፍሲል እንደተገለፀው ውሉን እና ከውሉ በፊት ነበር የተባለውን ግንኙነትና ውጤቱን

አስመልክቶ የተለያየ ውሳኔ ሰጥተዋል፡፡

በበኩላችን እንደተመለከትነው ተከታዩችን ሁለት መሰረታዊ ጭብጦች ይዞ ለጎዳዩ እልባት

መስጠት ተገቢ ሆኖ አግኝተነውል፡፡ ይኸውም፡-

1ኛ - ግራቀኙ ጋብቻ ከመፈፀማቸው በፊት ያለው ግንኙነት እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት

ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ አግባብነትና በህጉ ተቀባይነት ባለው ማስረጃ በስር ፍርድ ቤቶች

እንዲረጋገጥ ተደርጓል ወይስ አልተደረገም? ከዚህ ጋር በተያያዘ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ

ችሎት በዚህ ረገድ የቀረበውን የፍሬ ነገር ክርክርና ማስረጃ ሳይመለከት ማለፉ በአግባቡ ነው? የክልሉ

ሰበር ሰሚ ችሎትስ ማስረጃውን መዝኛለሁ በማለት ከውሉ በፊት እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር

ግንኙነት አልነበረም በማለት የሰጠው ውሳኔ የሰበር ችሎቱን ስልጣን መሰረት ያደረገ ነው ወይስ

አይደለም?

2ኛ - ግራቀኙ ውል ሲያደርጉ ከጋብቻ በፊት የነበሩትን አከራካሪ ንብረቶች በተመለከተ እስከተስማሙ

ድረስ የግራቀኙ ግንኙነት እንደባልና ሚስት ነበር የሚባል ቢሆን እንኳን በንብረቱ ረገድ ውጤት

አይኖረውም የሚባልበት የህግ ምክንያት አለ? ወይስ የለም? የሚሉት ናቸው፡፡ በዚሁ ቅደም ተከተል

እንደሚከተለው መርምረናል፡፡

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

ቀዳሚው ጭብጥ ግራቀኙ ውል አደረጉ ከመባሉ በፊት የነበራቸው ግንኙነት እንደባልና ሚስት

አብሮ የመኖር ግንኙነት ስለመሆኑ አግባብነትና ተቀባይነት ባለው ማስረጃ መረጋገጥ/አለመረጋገጡን

የሚመለከት ነው፡፡ በፌዴራሉ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 106 ስር እንደተመለከተው

ጋብቻ ሳይፈፀም እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖሩን የግንኙነቱ ሁኔታ መኖሩን በማረጋገጥ ማስረዳት

እንደሚቻል፤ አንድ ወንድና አንድ ሴት ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት ይኖራሉ የሚባለው

የተጋቡ ሰዎችን ሁኔታ ሲያሳዩና ቤተዘመዶቻቸውና ማህበረሰቡ እንደተጋቡ ሰዎች የሚኖሩ ናቸው

ብለው ሲገምቷቸው መሆኑን፤ ይህን ሁኔታ አንደኛው ወገን ለማስረዳት የቻለ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ

እንደባልና ሚስት አብረው የሚኖሩ ናቸው ሲል የህግ ግምት እንደሚወስድ፤ እንዲሁም ይህ ግምት

ማናቸውንም አይነት አስተማማኝ ማስረጃ በማቅረብ ግንኙነቱ ያለመኖሩን በማስረዳት ማፍረስ

እንደሚቻል ይደነግጋል፡፡

ከጋብቻ ሥርዓት ወይም ጋብቻ ሳይፈፀም እንደባልና ሚስት አብሮ ከመኖር ውጪ በአንድ

ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚደረጉ ሌሎች ንኙነቶች በህግ ፊት ምንም ውጤት

እንደማይኖራቸው በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 107 ይደነግጋል፡፡ የአማራ ክልል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር

79/1995 አንቀጽ 117 እና 118 ከፍሲል የተመለከተውን በተመሳሳይ የሚደነግጉ ናቸው፡፡

ከዚህ አንጻር አመልካች ከ2003 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2009 ዓ/ም ድረስ እንደ ባልና ሚስት

አብረን ኖረናል፤ ይህ ግንኙነት በህጉ በንብረታችን ረገድ ውጤት አለው በማለት የሚከራከሩ በመሆኑ

የግንኙነቱ ሁኔታ መኖሩን በማረጋገጥ ማስረዳት እንደሚጠበቅባቸው፤ ለዚህም በተጠቀሰው ጊዜ

የተጋቡ ሰዎችን ሁኔታ ያሳዩ እንደነበርና የግራቀኙ ቤተዘመዶችና ማህበረሰቡ እንደተጋቡ ሰዎች የሚኖሩ

ናቸው ብለው የሚገምቷቸው መሆኑን ማስረዳት እንደሚኖርባቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡ በዚህ መልኩ

በቂ ማስረጃ አቅርበው ፍርድ ቤቱ እንደባልና ሚስት አብረው የሚኖሩ ናቸው ሲል ግምት የሚወስድ

ከሆነ ተጠሪ ማስረጃ አቅርበው እንደ ክርክራቸው አብረው ያልኖሩ መሆኑን፤ ልጆች የተወለዱትም

ከጋብቻ ውጪ በነበረን ግንኙነት መሆኑን፤ አመልካች እና ተጠሪ በአንድ ጣሪያ ስር ሆነው ያፈሩት

ንብረት አለመኖሩን ሁሉ ማናቸውንም አይነት አስተማማኝ የሚባል ማስረጃ በማቅረብ ግንኙነቱ

ያለመኖሩን ማስረዳት እንደሚችሉ ከፍሲል ከተጠቀሰው የህጉ ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

ይሁንና የስር ፍርድ ቤቶች በዚህ የህግ አግባብ ለጉዳዩ አግባብነትናተቀባይነት ያለው ማስረጃ

ሰምተው መወሰን ሲገባቸው በዋናነት የግራቀኙን ምስክርነት መሰረት አድርገው የወረዳው ፍርድ ቤት

እንደ ባልና ሚስት የመኖር ግንኙነቱ የለም ማለቱ፤ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ያንኑ ማስረጃ መዝኖ

አመልካች ግንኙነታቸው እንደባልና ሚስት እንደነበር አስረድታለች በማለት መወሰኑ፤ የክልሉ ጠቅላይ

ፍርድ ቤት በዚህ የፍሬ ነገር ክርክር ምንም ሳይል ማለፉ፤ እንዲሁም የክልሉ ሰበር ችሎት መሰረታዊ

የህግ ስህተት ከማረም ስልጣኑ ውጪ ማስረጃዎችን መዘንኩ በማለት ከቀረቡት ማስረጃዎች ይዘት

አኳያ ከጋብቻ በፊት እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት ነበራቸው ለማለት የሚቻል ሆኖ

አላገኘሁትም በማለት መወሰኑ የሚነቀፍ ነው ብለናል፡፡

ሁለተኛው ጭብጥ ከጋብቻ ውጪ እንደ ባልና ሚስት ኖረዋል የሚባሉ ሰዎች ንብረታቸውን

በተመለከተ በግንኙነቱ ጊዜ ውል ቢያደርጉ ከውሉ በፊት በግንኙነታቸው ጊዜ የተፈሩትን ንብረቶች

በተመለከተ እንደባልና ሚስት የነበሩበት ጊዜ በንብረቱ ረገድ ውጤት አይኖረውም የሚባልበት የህግ

ምክንያት መኖር አለመኖሩን የሚመለከት ነው፡፡ እደሚታወቀው ጋብቻም ሆነ ከጋብቻ ውጪ እንደ

ባልና ሚስት አብሮ መኖር ግንኙነት የቤተሰብ መሰረት ሲሆን ህብረተሰቡም ሆነ ፍርድ ቤትን ጨምሮ

የመንግስት አካላት ግንኙነቱን የማወቅ፣ የማክበር እና የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው፡፡ ወንድ እና ሴት

ጋብቻ ሲመሰርቱ፣ በጋብቻው ዘመን እና በፍቺ ወቅት እኩል መብት አላቸው፡፡ እንደባልና ሚስት

አብረው የኖሩም ግንኙነቱ ፀንቶ ባለበት እና በሚቋረጥበት ጊዜ ሁሉ በህጉ የሚታወቅ መብት

አላቸው፡፡ ይኸው ህጋዊ መብት ንብረት በማፍራት፣ በማስተዳደር፣ በመቆጣጠር፣ በመጠቀምና

በማስተላለፍ ረገድ ሴቶች ከወንዶች እኩል መሆናቸውን ከሚደነግገው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት

አንቀጽ 34(1) እና 35 እንዲሁም ተያያዥ ድንጋጌዎች የሚነሳ ነው፡፡ የህገ መንግስቱም ሆነ የቤተሰብ

ህጉ ድንጋጌዎች የተመሰረቱት በዚህ የእኩልነት መርህ ላይ ነው፡፡

ግንኙነቱ በፀናበት ጊዜ የሚደረግ ውልን በተመለከተ ባልና ሚስት ተጋብተው በሚኖሩበት ጊዜ

በመካከላቸው የሚያደርጓቸው ውሎች ፍርድ ቤት ካላፀደቃቸው በስተቀር ውጤት እንደማይኖራቸው

የፌዴራሉ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 73 ይደነግጋል፡፡ የአማራ ክልል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 84 በተመሳሳይ

ባልና ሚስት ተጋብተው በሚኖሩበት ጊዜ በመካከላቸው የሚያደርጓቸው ውሎች ውል ለማዋዋል

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

ሥልጣን የተሰጠው የፍትህ አካል ካላፀደቃቸው በስተቀር ውጤት እንደማይኖራቸው ይደነግጋል፡፡

በተጋቢዎቹ መካከል የሚደረግ የውል ግንኙነት በመኖሩ ምክንያት ከፍሲል የጠቀስነውን የእኩልነት

መርህ የጣሰ ህገወጥ ስምምነት እንዳይሆን በፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል

መረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ ህጉ ጥንቃቄ ማድረጉን ከዚህ ህጉ ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡ እነዚህ

ከፍሲል የጠቀስናቸው የቤተሰብ ህግ ድንጋጌዎች ጋብቻ ውስጥ ስላሉ ባልና ሚስት የሚደነግጉ ሲሆን

እንደባልና ሚስት ግንኙነት ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ ተፈፃሚነት ያላቸው ስለመሆኑ በህጉ በግልፅ

አልተመለከተም፡፡ በዚህ ረገድ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 185895 እና በሌሎችም መዝገቦች

አስገዳጅ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ከውሳኔዎቹ መገንዘብ እንደሚቻለው እንደ ባልናሚስት ያለው ግንኙነት ከ

3 ዓመት በላይ ከዘለቀ በንብረት ረገድ ያለው ውጤት ከጋብቻ የሚለይ ካለመሆኑም በላይ ግንኙነቱ

ሲቋረጥ እንደ ባልና ሚስት የኖሩ ሰዎች የጋራ ንብረትን ማጣራት የሚደረገው የጋብቻ ንብረትን

ለማጣራት በተደነገጉት የቤተሰብ ህጉ ድንጋጌዎች መሰረት በመሆኑ (የተሸሻለውን የቤተሰብ ህግ

አንቀጽ 133 እና ከአንቀጽ 112 – 120 ይመለከቷል) ፤ የንብረቱ ማጣራት የሚደረገው ደግሞ

በቅድሚያ ግራቀኝ በሚያደርጉት ውል መሰረት ውል ከሌለ/የማይፀና ከሆነ ደግሞ በህጉ ድንጋጌዎች

መሰረት በመሆኑ፤ ጋብቻ ሳይኖር እንደ ባልና ሚስት አብረው የሚኖሩ አንድ ወንድ እና አንዲ ሴት

ስለንብረታቸው አስተዳደር፣ የሶስተኛ ወገን ዕዳ አከፋፈልና የንብረት ማጣራት ሂደት በአጠቃላይ

በጋብቻ ስለሚፈጠር የጋራ ንብረትና የማጣራት ሂደት እንዲሁም የሚነሱ ክርክሮች ሁሉ

የሚወሰኑበትን ሁኔታ በተመለከተ ለጋብቻ የተመለከቱት የቤተሰብ ክጉ ድንጋጌዎች ጋብቻ ሳይኖር

እንደ ባልና ሚስት አብረው በሚኖሩ ሰዎች ላይም በተመሳሳይ ተፈፃሚ የሚሆኑ መሆኑ (የቤተሰብ ህጉ

አንቀጽ 103 አና 114 ይመለከቷል) በህጉ ተቀባይነት ያገኘ ነው፡፡ ስለሆነም ጋብቻ ሳይፈፅሙ እንደ ባልና

ሚስት አብረው የሚኖሩ በመካከላቸው የተደረገ በፍርድ ቤት ያልፀደቀ ስምምነት ተቀባይነት

እንዲኖረው ማድረግ ሁለቱ ግንኙነቶች (ጋብቻ እና ከጋብቻ ውጪ አብሮ መኖር) በንብረት ረገድ

ያላቸው ውጤት የተለያየ ስላለመሆኑ ይልቁንም በአንድ አይነት መልኩ እንዲታዩ በህጉ የተቀመጠውን

አስገዳጅ ድንጋጌ የሚፃረር እና በህግ አውጪው ያልታሰበውን ልዩነት መፍጠር ይሆናል፡፡ ስምምነቱ

አንዱ ወገን በሌላው ላይ የሚያሳድረው ጫና የእኩልነት መርህን የሚጥስ መሆን አለመሆኑን በፍርድ

ቤት እንዲረጋገጥ የተፈለገበትን አላማ የሚያሳካ አይደለም ተብሎ ትርጉም ተሰጥቶ ተወስኗል፡፡

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

ከዚህ አንጻር ከጋብቻ ውጪ እንደ ባልና ሚስት ኖረዋል የሚባሉ ሰዎች በግንኙነታቸው ውስጥ

ንብረታቸውን በተመለከተ የውል ስምምነት ቢያደርጉ ውሉ የእኩልነት መርህን የሚጥስ መሆን

አለመሆኑን፤ እንዲሁም የሚኖረው ህጋዊ ዋጋ ሁሉ በፍርድ ቤት ተመርምሮ ውሳኔ ሊሰጥበት ከሚገባ

በቀር በተቃራኒው አስቀድሞ እንደባልና ሚስት የነበሩበት ጊዜ በንብረቱ ረገድ ውጤት አይኖረውም

የሚባልበት የህግ ምክንያት እንደሌለ ከፍሲል ከተጠቀሱት የህጉ እና የሰበር ችሎቱ ውሳኔዎች መገንዘብ

ይቻላል፡፡

በመሆኑም በተያዘው ጉዳይ የግራ ቀኙ ግንኙነት እንደባልና ሚስት ነበር የሚባል ቢሆን እንኳን

ውል ስላደረጉ ውሉ የሚኖረው ህጋዊ ዋጋ ሳይመረመር ከጋብቻ በፊት በነበረ ግንኙነት የተፈሩ

ንብረቶች የተጠሪ የግል ንብረት እንዲሆኑ እስከተስማሙ ድረስ የተጠሪ የግል ንብረት ከመሆን የሚድኑ

አይሆንም በማለት የተሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል፡፡

በአጠቃላይ ግራ ቀኙ ውል አደረጉ ከመባሉ በፊት ከ2003 – 2009 ዓ.ም ድረስ ከጋብቻ

ውጪ አብረው መኖራቸው በተገቢው ማስረጃ ከተረጋገጠ በንብረት ክርክሩ ህጋዊ ውጤት የሚኖረው

በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ግንኙነቱ ስለመኖሩ ለማስረዳት በህጉ በተመለከተው አግባብ ተገቢ

ማስረጃዎች እንዲቀርቡ በማድረግ አጣርቶ ውሳኔ መስጠት ሲገባ ከውል በፊት የነበረው ግንኙነት

ውጤት እንደማይኖረው በመውሰድ እንዲሁም ተደረገ የተባለው ውል አስቀድሞ በህጉ አግባብ የጋራ

ባለሃብትነት በተቋቋመበት ንብረት ላይ የሚኖረው ውጤት በአግባቡ ሳይጤን በየደረጃው ባሉ ፍርድ

ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ከፍሲል የተጠቀሱትን የህግ ድንጋጌዎችና የሰበር ውሳኔዎች ያልተከተለ በመሆኑ

ውሳኔው በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ አንቀጽ 2(4)(ሸ) እና አንቀጽ 10(1)(ሐ) መሰረት በዚህ

ችሎት ሊታረም የሚገባ ነው ብለናል፡፡ ተከታዩንም ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1. የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 0134134 በቀነ 07/04/2012 ዓ.ም፤ የማዕከላዊ

ጎንደር ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ቁ 01-45495 በቀን 02/10/2012 ዓ.ም፤ የአ/ብ/ክ/መ ጠቅላይ

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 01-03038 በ03/03/2014 ዓ.ም እና የክልሉ ሰበር ሰሚ

ችሎት በመ/ቁ 110565 በቀን 17/09/2014 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.

348/1/ መሰረት ተሻሽሏል፡፡

2. ንብረትን በተመለከተ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሸሯል፡፡

3. የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ ግራቀኙ ከ2003 – 2009

ዓ.ም ድረስ ከጋብቻ ውጪ አብረው መኖር/ አለመኖራቸውን በተመለከተ ከፍሲል በፍርዱ

ክፍል በገለፅነው መሰረት በተገቢው ማስረጃ አጣርቶ እንዲወስን፤ ከጋብቻ ውጪ አብሮ

የመኖር ግንኙነት አለ የሚባል ከሆነ በዚህ ግንኙነት ጊዜ የተፈራ ንብረትን በተመለከተ ግራቀኙ

አደረጉት የተባለው ውል የሚኖረውን ህጋዊ ውጤት እንዲወስን፤ እንዲሁም ከጋብቻ ውጪ

አብሮ መኖር ግንኑነት አልነበረም ከተባለም ውሉ የሚኖረውን ውጤት መርምሮ ተገቢውን

እንዲወስን ጉዳዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 343/1/ መሰረት መልሰናል፡፡ ይጻፍ፡፡-

4. የልጆችን ቀለብ በተመለከተ የተሰጠው ውሳኔ አልተነካም፡፡

5. ዕግድ ተነስቷል፡፡ ይፃፍ፡፡

6. ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ ይቻቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መ/ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአራት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

የልዩነት ሃሳብ

እኔ በሦስተኛ ተራ ቁጥር ላይ የተሰየምኩት ዳኛ ከአብላጫዉ ድምጽ ዉሳኔ የሚለይበትን ምክንያት

እንደሚከተለዉ አስፍሬያለሁ፡፡

ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ እንደሚቻለዉ ግራ ቀኝ በመካከላቸዉ መስከረም 08 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረጉት የጋብቻ

ዉል በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ቀጠና 02 የሚገኘዉ መለያ ስሙ ዕዉቀት በር ሆቴል ተብሎ የሚጠራዉ ባለ አራት

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

ፎቅ ህንፃ እንዲሁም በጎንደር ከተማ ቀበሌ 20 አዘዞ አሜሪካን ሠፈር እየተባለ ከሚጠራዉ ሠፈር ባለአንድ ፎቅ

ቤት በመጠናቀቅ ላይ ያለ ቤት የተጠሪ ንብረት መሆኑን የተስማሙ ስለመሆኑ በየደረጃዉ ባሉ የክልሉ ፍርድ

ቤቶች የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ አመልካችም ክዳ አትከራከርም፡፡ ለሁሉም ግልጽ እንደሚሆነዉ ዉል ተዋዋይ

ወገኖች በእራሳቸዉ ጉዳይ እራሳቸዉ ለመወሰን ያላቸዉን ነፃነት ተጠቅመዉ በሚያደርጉት ስምምነት

የሚያቋቁሙት መብትና ግዴታ ሲሆን፤ ስምምነቱን ሲያደርጉም የዉሉ ዓይነት፣ ይዘት እና ዉጤቱ ምን ሊሆን

እንደሚችል አዉቀዉ እና በአግባቡ ተረድተዉ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ተዋዋዮች በዚህ መልኩ ወደዉ እና ፈቅደዉ

በሚያደርጉት ስምምነት በህግ ጥበቃ የተደረገላቸዉን መብት ሊተዉ እንደሚችሉም እሙን ነዉ፡፡ በመርህ

ደረጃ ተዋዋዮች በእራሳቸዉ ጉዳይ ራሳቸዉ ለመወሰን ያላቸዉን መብት ተጠቅመዉ በፈለጉት ጉዳይ ላይ

በፈለጉት ዓይነት ሁኔታ (ፎርም) መስማማት የሚችሉ ቢሆንም አንድ ዉል ህጋዊ ዉጤት ያስከትል ዘንድ

ማሟላት ያለበትን ቅድመ ሁኔታ (መስፈርት) ህግ አዉጪዉ በግልጽ ያስቀመጣቸዉን አስገዳጅ ድንጋጌዎችን

ተከትሎ ሊደረግ ይገባል፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ፍትሐብሔር ህግ አንቀጽ 1678 አንድ ዉል ህጋዊ ዉጤት

ያስከትል ዘንድ እንዲያሟላ የሚጠበቅበትን ቅድመ ሁኔታዎች እንደ አጠቃላይ የሚደነግግ ሲሆን፣ በልዩ ሁኔታም

የዉሉን ጉዳይ መሠረት ባደረገ መልኩ ከግምት ዉስጥ ሊገቡ ይገባል የሚላቸዉን ቅድመ ሁኔታዎች ህግ

አዉጪዉ በሌሎች ህጎች ይደነግጋል፡፡ ከዚህም ዉስጥ ፎርም አንዱ ነዉ፡፡ በዚህም መሠረት ተዋዋይ ወገኖች

ፎርምን ጨምሮ በህግ የተመለከቱትን ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን መሠረት በማድረግ ወደዉ እና ፈቅደዉ

ያደረጉት ዉል የህግ ኃይል ተሰጥቶት ግራ ቀኝን የማስገደድ ዉጤት ያለዉ ሲሆን (በፍትሐብሔር ህጋችን አንቀጽ

1731/1 አና 2 ድንጋጌዎች ይመለከቷል)፣ በሌላ በኩል ዉሉ በህግ የተመለከተዉን አስገዳጅ ሁኔታ ያላማሏ ከሆነ

ምንም እንኳ የግራ ቀኝን ስምምነት መሠረት ያደረገ ቢሆንም ዉሉ ህጋዊ ዉጤት አያስከትልም፡፡

ስለሆነም አንድ ዉል አስገዳጅ ዉጤት ያስከትል ዘንድ እንዲያሟላ የሚጠበቅበት በህግ የተደነገገ ልዩ ሁኔታ ካለ

ተዋዋይ ወገኖች ተገቢዉን የህግ ድንጋጌ ከግምት ዉስጥ ባስገባ መልኩ ዉላቸዉን ሊያደርጉ ይገባል፡፡ ከዉሉ

አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ክርክር የቀረበ እንደሆነም፣ ክርክሩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ዉል

ተገቢዉን የህግ ድንጋጌ ተከትሎ የተደረገ መሆን አለመሆኑን በጥንቃቄ በመመርመር ዳኝነት የመስጠት ኃላፊነት

እንዳለበት የሚታወቅ ነዉ፡፡ ይህን በማድረግ ሂደት በአንድ በኩል ዉሉ የተወሰነ ፎርም ተከትሎ እንዲደረግ በህግ

የታዘዘ ሲሆን ይህንኑ ከግምት ዉስጥ በማስገባት፣ በሌላ በኩል ዉሉ የተወሰነ ፎርም ተከትሎ እንዲደረግ በህግ

በግልጽ የተመለከተ ድንጋጌ ከሌለ ግራ ቀኝ ወደዉ እና ፈቅደዉ ላደረጉት ስምምነት ዉጤት በመስጠት የተዋዋይ

ወገኖችን የመዋዋል ነፃነት ያከበረ ዉሳኔ ሊሰጥ ይገባል፡፡ ፍርድ ቤቶች ተዋዋዮች በዉላቸዉ ያመለከቱት

ስምምነት ግልጽ ከሆነ ግልጽ የሆነዉን ስምምነት መሠረት በማድረግ፣ ግልጽ ካልሆነ ተቀባይነት ያገኙትን የዉል

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

አተረጓጎም መርሆዎች መሠረት ያደረገ ትርጉም በመስጠት ለተዋዋይ ወገኖች ስምምነት ዋጋ በመስጠት ዉሉ

ተፈፃሚ እንዲሆን ከማድረግ ዉጪ በህግ ወይም በዉል ያልተመለከተ አዲስ መብትና ግዴታ ከመጨመር

መቆጠብ አለባቸዉ የሚለዉ መርህ በዉል ህግ ተቀባይነት ካገኙት አጠቃላይ መርሆዎች ዉስጥ አንዱ ሲሆን፤

ፍርድ ቤቶች ዉል መተርጎምን ሰበብ በማድረግ ለተዋዋይ ወገኖች ዉል መፍጠር እንደማይችሉ፣ ዉለታዎች

ግልጽ በሆኑ ጊዜ የተዋዋይ ወገኖች ሃሳብ ምን እንደነበረ መተርጎም እንደማይችሉ እንዲሁም በህግ በግልጽ

የተመለከተ ካልሆነ በቀር ርትዕን ምክንያት በማድረግ ዉልን ማሻሻልም ሆነ መለወጥ እንደማይችሉ

በፍትሐብሔር ሕጋችን አንቀጽ 1714(2)፣ 1733 እና 1763 ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎችም ለዚህ ማሳያዎች

ናቸዉ፡፡

ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ጉዳይ ስንመለከት አብላጫዉ ድምጽ ዉሉ ህጋዊ ዉጤት አያስከትልም ከሚል ድምዳሜ

ላይ የደረሰዉ በፍርድ ቤት ቀርቦ አለመመዝገቡን በመጥቀስ ነዉ፡፡ በሌላ በኩል ዉሉ የተደረገዉ ግራ ቀኝ እንደ

ባልና ሚስት አብሮ ሲኖሩ በነበረበት ወቅት ስለመሆኑ ማስረጃን መዝኖ ፍሬ ነገርን የማረጋገጥ ስልጣን

በተሰጣቸዉ የክልሉ ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2009 ዓ.ም ድረስ

ባለዉ ጊዜ ከተጠሪ ጋር የነበራቸዉ ግንኙነት እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት መሆኑን አመልካች

ባቀረበችዉ የሰበር አቤቱታ ክዳ አትከራከርም፡፡ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት እንደ ባልና ሚስት አብሮ በሚኖሩበት

ጊዜ የሚያደርጓቸዉ ዉሎች በፍርድ ቤት ወይም በህግ ስልጣን በተሰጠዉ አካል ሊመዘገቡ ይገባል የሚል ድንጋጌ

የለም፡፡ አብላጫዉ ድምጽ በዋቢነት የጠቀሰዉ ድንጋጌ የአማራ ክልል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 84 ላይ

የተመለከተዉን ድንጋጌ ሲሆን፣ ይህ ድንጋጌ ባልና ሚስት ተጋብተዉ በሚኖሩበት ጊዜ በመካከላቸዉ

የሚያደርጓቸዉ ዉሎች ዉል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠዉ የፍትሕ አካላት ካላጸደቃቸዉ በስተቀር ዉጤት

እንደሌለዉ የሚያሳይ ነዉ፡፡ ድንጋጌዉ የተለያዩ ዓላማዎች እንዳሉት የሚታመን ሲሆን አንዱ ዓላማዉ ባልና

ሚስት በጋብቻ በሚኖሩበት ጊዜ አንደኛዉ ተጋቢ በሌላኛዉ ተጋቢ በሚደርስበት ተጽዕኖ ምክንያት ባላመነበት

ጉዳይ ስምምነት ሊያደርግ የሚችልበት አጋጣሚ በመኖሩ ስምምነቱ ስልጣን ባለዉ አካል ዘንድ ቀርቦ ሳይረጋገጥ

ዉጤት እንዳይኖረዉ በማድረግ የተጋቢዎች ግላዊ ግንኙነት እንዳይሻክር ጥበቃ ማድረግ ስለመሆኑ መገንዘብ

ይቻላል፡፡ በእርግጥም ጋብቻ የቤተሰብ መሠረት በመሆኑም በተጋቢዎች መካከል የሚደረግ ስምምነት

የሚገዛበት ልዩ ድንጋጌ የሚያስፈልገዉ በመሆኑ ከላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ አቀራረጽም ይህን ሁሉ ታሳቢ

ያደረገ እንደሆነ ይታመናል፡፡

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

ይሁንና፣ ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ፣ በተያዘዉ ጉዳይ አመልካች እና ተጠሪ ከላይ የተመለከተዉን ዉል ሲያደርጉ

እንደባልና ሚስት አብሮ ሲኖሩ በነበረበት ወቅት እንጂ ጋብቻ ከፈጸሙ በኋላ ባለመሆኑ ከላይ የተመለከተዉ

የክልሉ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 84 ድንጋጌ ተፈፃሚነት የለዉም፡፡ በመሠረቱ በአብላጫዉ ድምጽ ዉሳኔ

በተገለጸዉ መልኩ እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖር የቤተሰብ መሠረት ነዉ ለማለት የሚቻል ባለመሆኑ

የቤተሰብ ብሎም የማህበረሰብ ተቋም ከሆነዉ ጋብቻ ጋር እኩል የህግ ጥበቃ አይደረግለትም፡፡ ለዚህም

ይመስላል አንድ ወንድ እና አንድ ሴት አንደባልና ሚስት አብሮ ለመኖር ወስነዉ ስለሚገናኙበት፣ አብረዉ

በሚኖርበት ወቅት በመካከላቸዉ ሊኖር ስለሚገባዉ ግላዊ ግንኙነት ብሎም እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር

ግንኙነቱ የሚቋረጥበት ሥርዓት የሚመራበትን ሁኔታ አስመልክቶ የፌዴራልም ሆነ የአማራ ክልል የቤተሰብ

ህጉ ጥበቃ አያደርግም (በተለይም የክልሉ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 118/1/ይመለከቷል)፡፡ በሌላ በኩል እንደባልና

ሚስት አብሮ የመኖሩ ሁኔታ ሁለት ዐብይ ዉጤቶችን ያስከትላል፡፡ የመጀመሪያዉ የሦስተኛ ወገን መብትና

ጥቅምን የሚመለከት ሲሆን፣ ይሄዉም በግንኙነቱ ወቅት ከአብራካቸዉ ልጆች ሊወለዱ ይችላሉ፤ እንዲሁም

በግንኙነቱ ምክንያት ከሦስተኛ ወገን የሚመጣ የገንዘብ ወይም የንብረት ዕዳ ሊኖር ይችላል፡፡ ሁለተኛዉ

በግንኙነቱ ወቅት በየግላቸዉ ወይም በጋራ በሚያደርጉት ጥረት ንብረት ሊያፈሩ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም እነዚህን

ጉዳዮች በተመለከተ ብቻ የህግ ጥበቃ የሚያስፈልግ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት አንድ ወንድና አንዲት ሴት

እንደባልና ሚስት አብሮ በሚኖሩበት ጊዜ ለጋራ ኑሮአቸዉ ወይም ከግንኙነት የተወለዱ ልጆቻቸዉን መሠረታዊ

ፍላጎቶች ለማሟላት ሲባል የተገቡ እዳዎች ሲኖሩ ሁለቱም በአንድነትና በነጠላ ለዕዳዉ ኃላፊዎች እንደሚሆኑ፣

ከሦስት ዓመት ላላነሰ ጊዜ አብረዉ ከኖሩ በግንኙነቱ ዉስጥ እያሉ ያፈሯቸዉ ንብረቶች የጋራ ሀብቶቻቸዉ

እንደሚሆኑ የፌዴራል እና የክልሉ የቤተሰብ ህግ ይደነግጋል (የክልሉ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 113 እና 115

ይመለከቷል)፡፡ ባልና ሚስትን አስመልክቶ በክልሉ የቤተሰብ ህግ የተመለከቱ ድንጋጌዎች እንደባልና ሚስት

አብሮ ለሚኖሩ ሰዎች ተፈፃሚነት እንዳላቸዉ ተለይተዉ የተገለጹትም የባልና ሚስት የጋራ ዕዳን፣ የባልና ሚስት

የጋራ ንብረት ዉጤት አስመልክቶ እንዲሁም ተወላጅነት የሚረጋገጥበትን ሥርዓት አስመልክቶ በቤተሰብ ህጉ

የተመለከቱት ድንጋጌዎች ብቻ ስለመሆኑ በክልሉ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 114 እና 115 ላይ ከተመለከቱት

ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚህ ዉጪ ባልና ሚስት አብረዉ በሚኖሩበት ጊዜ የሚያደርጓቸዉ ዉሎች

በህግ ስልጣን በተሰጠዉ አካል ፊት ሊረጋገጥ እንደሚገባ በክልሉ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 84 ላይ የተመለከተዉ

ድንጋጌ እንደ ባልና ሚስት አብሮ የሚኖሩ ሰዎች በሚያደርጓቸዉ ዉሎች ላይ ተፈፃሚነት እንዳለዉ ህጉ

አይደነግግም፡፡ ከዚህ ሁሉ መገንዘብ የሚቻለዉ እንደ ባልና ሚስት አብሮ የሚኖሩ ሰዎች ግንኙነቱ ባለበት

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
A&B Law Office

ወቅት የሚያደርጓቸዉ ዉሎች ህጋዊ ዉጤት ይኖራቸዉ ዘንድ ዉሉ ስልጣን ባለዉ አካል እንዲመዘገብ በህግ

የተጣለ ግዴታ አለመኖሩን ነዉ፡፡

አብላጫዉ ድምጽ ለዉሳኔዉ መሠረት ያደረገዉ በኢፌዲሪ ህገ መንግስት ዕዉቅና የተሰጠዉን የወንዶችና

የሴቶችን የእኩልነት መብት ነዉ፡፡ ይሁንና ማንም ሰዉ በመብቱ የመጠቀም እና ያለመጠቀም ነፃነት ያለዉ

በመሆኑ ይህን ነፃነቱን ተጠቅሞ በሚያደርገዉ ስምምነት መብቱን የተወ ወይም ለሌላ ወገን አሳልፎ የሰጠ

እንደሆነ ይህ ነፃነቱ ሊከበርለት እንደሚገባ መገንዘቡ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም የዉሉን ህጋዊ ዉጤት የሚወስን

በህግ የተመለከተ ልዩ ድንጋጌ በሌለበት የእኩልነት መብትን መሠረት በማድረግ ብቻ ግራ ቀኝ ወደዉ እና

ፈቅደዉ ባደረጉት ዉል ንብረቶቻቸዉን አስመልክቶ ያደረጉት ስምምነት ህጋዊ ዉጤት አያስከትልም ማለት በቂ

እና አሳማኝ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ እንደባልና ሚስት አብረዉ የሚኖሩ ሰዎች

ግንኙነቱ ባለበት ወቅት የሚያደርጓቸዉ ዉሎች የእኩልነት መብትን የሚጋፋ ነዉ ብሎ ካመነ የዉል ግንኙነቱ

የሚገዛበትን ልዩ ድንጋጌ በማካተት ለግንኙነቱ ጥበቃ ማድረግ ያለበት ህግ አዉጪዉ ሲሆን፣ የክልሉ ህግ

አዉጪ አካል ይህን አስመልክቶ በህጉ የደነገገዉ ልዩ ሁኔታ የለም፡፡

በአጠቃላይ አመልካች እና ተጠሪ እንደባልና ሚስት አብሮ በሚኖሩበት ወቅት ወደዉ እና ፈቅደዉ ስለ

ንብረቶቻቸዉ ያደረጉት ግልጽ ዉል መኖሩ ባልተካደበት፣ እንደባልና ሚስት አብሮ የሚኖሩ ሰዎች

የሚያደርጓቸዉ ዉሎች ስልጣን ባለዉ አካል ሊረጋገጡ እንደሚገባ በፌዴራልም ሆነ በአማራ ክልል የቤተሰብ

ህግ ግልጽ ድንጋጌ በሌለበት ሁኔታ ዉሉ ህጋዊ ዉጤት አያስከትልም ሊባል የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የለም፡፡

በዚህ ምክንያት ዉሉን ዋጋ ማሳጣት ፍርድ ቤቶች ለሰዎች የመዋዋል ነፃነት ዋጋ በመስጠት ዉሎችን ማስፈጸም

አለባቸዉ የሚለዉንም አጠቃላይ መርህ የሚጋፋ ነዉ የሚል ሃሳብ አለኝ፡፡ በመሆኑም በዚህ ችሎት

በሰ/መ/ቁጥር 185895 ላይ የተሰጠዉ እና አብላጫዉ ድምጽ የጠቀሰዉ ዉሳኔም በፌዴራል ፍርድ ቤቶች

አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26(2) መሠረት ቢያንስ ሰባት ዳኞች ለተሰየሙበት ሰበር ችሎት ቀርቦ

ሊለወጥ ይገባል የሚል ሃሳብ ስላለኝ በሃሳብ ተለይቻለሁ፡፡

የማይነበብ የአንድ ዳኛ ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም

You might also like