You are on page 1of 19

የኢትዮጵያ የሂሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ህጎች ላይ

ለኢትዮጵያ ምርት ገበያ አባላት (ECX Members) የተዘጋጀ ገለፃ

አቅራቢ፡ አሸናፊ ገበየሁ


ሰኔ 2009
ቦታ፡ አዲስ አበባ
1. ስለሂሣብ አያያዝ ሞያ ቀደም ሲል የነበሩ አሰራሮች
-ፈቃድ የሚሠጠው በዋናው ኦዲተር ቢሮና በዘርፍ ተቆጣጠሪ አካላት ነበር
-ወጥነትና ተመሣሣይነት ያልነበረው አሠራር ነበር
-አንዳችም ብሔራዊ ደረጃዎችና ሥርዓት የሌለው ነበር
-የሙያ ማህበራት እንዲመሰረቱ ለማድረግ የሚያስችል ስርዓት አልነበረም
2. ለቦርዱ በህግ የተሠጠው ሥልጣን
አዋጅ 847/2006
የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አዋጅ
ዓላማዎች
-የተሟላ፣ ግልፅና በቀላሉ ሊረዱት የሚችሉት የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ሥርዓት መዘርጋት
-ግልፅነትና ተጠያቂነትን የሚያጎለብት ወጥ የሆነ የሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ሥርዓት እንዲኖር ለማድረግ
-የኢኮኖሚውን ምሦሶዎች ለመደገፍ፣ የፋይናንስ ቀውስ፣ የድርጅቶችን ውድቀት ስጋትና ተያያዥነት ያላቸው አሉታዊ የኢኮኖሚ ውጤቶች ለመቀነስ
-ከድርጅቶች የሚገኘውን የፋይናንስ መረጃ አቅርቦት ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ደረጃዎችን የጠበቀ ለማድረግ
-የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብን በኃላፊነት የሚመራና የሚቆጣጠር አካል ለማቋቋም
የተፈፃሚነት ወሰን
-በኢትዮጵያ ህግ መሠረት በተቋቋሙ ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ በሚሠሩ ሪፖርት አቅራቢ አካላት ሁሉ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል
አ ዋ ጅ 847 /2006 የ ቀ ጠ ለ …

-ሙያ ውን ለመቆ ጣጣ ር ናለ ማሣ ደግቦ ርዱ እንደ ሚቋ ቋ ምይ ደነ ግጋ ል


-የቦ ርዱ ንሥል ጣን ና ኃላ ፊነ ቶችይ ዘረ ዝራል

-የህ ጉን የተፈ ፃሚ ነ ትወ ሰን ያስቀ ምጣ ል


- ተ ፈ ፃ ሚ የ ፋ ይ ና ን ስ ሪ ፖ ር ት አ ዘ ገ ጃ ጀ ት ና አ ቀ ራ ረ ብ ደ ረ ጃ ዎ ች ን ( I F RS, I FR Sf or S M Es , I PSAS ) እ ን ዲ ሆ ኑ ያ ዛ ል

-በቁ ጥጥ ርሥር ዐቱ ው ስጥ የሚ ታቀፉ አካ ላትን በሥ ፋ ትይ ገል ፃል


- ሪ ፖ ር ት አ ቅ ራ ቢ ዎ ች ( PI E, SM E, M i croE nt erpr i ses)
- ባ ለ ሞ ያ ዎ ች ( CP As, C Au, Pu bl i cA udi t or s)
አዋጅ 847/2006 የቀጠለ….
-በኃላፊነትና ግዴታዎች ዝርዝሩ ያካተታቸው፡
የሪፖርት አቅራቢ አካላትና የዳይሬክተሮቻቸው
የሂሣብ ባለሞያዎችንና ኦዲተሮች
የሞያ ማኅበራት
-የሪፖርት አቅራቢ አካላት ዳይሬክተሮች ግዴታዎች
የፋይናንስ ሪፖርት ከኦዲት ሪፖርት ጋር ለቦርዱ ያቀርባሉ
የተናጠልና የተጠቃለሉ የፋይናንስ ሪፖርቶች ኦዲት መደረጋቸውን ያረጋግጣሉ
-ደረጃዎች ለማጽደቅ፣ ለመቀበልና ለማሻሻል የሚከናወኑ ሥርዓቶች
-ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር
-የህዝብ አስተያየት ማሰባሰብ
-የደረጃዎችን መረጃ ሥርጭት
በቦርዱ ድረ-ገጽ
ዕለታዊና ብሔራዊ ሥርጭት ባላቸው ከሁለት በላይ ጋዜጣዎች ቢያንስ ለሦስት ቀናት ማሣተም
በሌሎች የማሰራጫ መንገዶች ማስተዋወቅ
-የደረጃ ህትመቶቹ ይዘቶች ን ምን መሆን እንዳለበት ይዘረዝራል
አዋጅ 847/2006 የቀጠለ…
ከቦርዱ ፈቃድ ያላገኘ ሰው ለPIE/RE የኦዲት አገልግሎት ለመሥጠት መሰየም እንደሌለበት
ፈቃድ የማሣደሻና ስረዛ ሁኔታዎችን ይገልፃል
ቦርዱ ባላፀደቀው የድርጅት ስም በመጠቀም የኦዲት አገልግሎት መሥጠትን ይከለክላል
ፐብሊክ ኦዲተሮች ለቦርዱና ለደንበኞች መረጃ እንዲሠጡ ግዴታዎችን ይጥላል የሚሰጡት መረጃም
የአድራሻ ለውጥ፤ የድርጅት ስምና የሞያተኛ ስብጥሮችን ማሳወቅ አለባቸው፡፡
አዋጅ 847/2006 የቀጠለ….
ለቦርዱ የተሠጠው ሥልጣን
የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብን በመከታተል አዋጁ መከበሩን ማረጋገጥ
የኦዲተሮችን የሥራ ጥራት መመርመር
ከሪፖርት አቀራረብ ጋር በተያያዘ ለቦርዱ መረጃና ማሥረጃዎችን ማቅረብና ተደራሽ የማድረግ ግዴታ የተጣለባቸው
-ሪፖርት አቅራቤ አካላትና ዳይሬክተሮቻቸው
-ፐብሊክ ኦዲተር
- የተመሰከረለት ኦዲተር ወይም የኦዲት ድርጅት
-የሪፖርት አቅራቢውን የሂሳብ መግለጫና ሪፖርት ያዘጋጀ ሰራተኛ
አዋጅ 847/2006 የቀጠለ…
ለሞያ ማኀበራት ዕውቅናና አክሪዴሽን የመሥጠት ሥልጣን
የሞያ ማኀበራት አክሪዴሽን ለማግኘት ማሟላት ያለባቸውን መሥፈርቶች ይገልፃል
- የ CPD መሥፈርቶችን ማክበርና የሞያ ብቃት ደረጃን ማሣደግ
- የአባላትን በተከታታይ የሙያ ማሣደግ ተሣትፎ ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥርዐት መኖር
-የአባላትን ዲሲፕሊን መኖር ለመከታተል የሚያስችል ሥርዐት መኖር
-ቦርዱ በሚያዘው መልኩ የአባላት ምዝገባ ማድረግ
የሞያ ማኀበራት ዕውቅናና አክሪዴሽን ስረዛ ምክንያቶችን ይጠቅሣል
የሞያ ማኀበራት የህዝብ ጥቅም የማስጠበቅ ግዴታቸውን መወጣታቸውን እንዲያረጋግጥ ያዛል
አዋጅ 847/2006 የቀጠለ….
የኦዲተሮችን የአሠራር ደረጃ -

-ሁኔታዎች ከላስገደዱ በስተቀር የሂሣብ መግለጫና አባሪ የተመለከቱትን ጉዳዮች ትክለኛነት ያሣያል፣ አጥጋቢ ነው ወይም በትክክል
ያመላክታል ብሎ ማረጋገጫ መስጠት ወይም ሪፖርት ማድረግ ወይም አስተያየት መስጠት እንደሌለበት ግዴታ ያስቀምጣል

-የሚሰጡት ማረጋገጫ፣ የሚቀርቡት ሪፖርት ወይም አስተያየት ሥራው ከተጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አራት ወራት ውስጥ
መቅረብ አለበት

-በሥራው ሂደት ጉልህ ጥፋት መፈጸሙን ሲያረጋግጡ ወይም መፈጸሙን እንዲያምን የሚያደርግ ምክንያት ሲኖር ለሪፖርት
አቅራቢው አካል ኃላፊዎችና ለሁሉም የቦርድ አባላት በጽሁፍ የማሣወቅ ግዴታ

-የጥቅም ግጭት ሊኖር ከሚያስችል ወይም የሙያ ነፃነቴን ከሚያሣጣ ሁኔታ እንዲርቁ ይጠይቃል

-ኦዲተሮች ለሚፈፅሙት የሞያ ሥነምግባር ጥፋት ተጠያቂ መሆናቸውን ያስቀምጣል፡፡


ጉልህ ጥፋት
ማንኛውንም ሪፖርት አቅራቢ አካል በማስተዳደር ወይም
በመቆጣጠር ሂደት ሕግን በመተላለፍ በማድረግ ወይም
ባለማድረግ
በማንኛውም ሰው የተፈጸመ የማጭበርበር ወይም የስርቆት
ተግባር፣ ወይም
የገንዘብ ጥቅም ባለው ሌላ ማንኛውም ሰው የተጣለን እምነት
የማጉደል ተግባር፣ ወይም
እንደ እምነት ማጉደል የሚቆጠር ጉልህ የገንዘብ ኪሳራ ያስከተለ
ወይም ሊያስከትል የሚችል ተግባር
አዋጅ 847/2006 የቀጠለ….
በሚከተሉት ላይ ተፈፃሚ የህግ ማስከበሪያ ዘይቤዎችን ይደነግጋል፡-
በኦዲተሮችና የኦዲት ድርጅቶች
በሪፖርት አቅራቢ አካላትና የበላይ ኃላፊዎቻቸው/ዳይሬክተሮቻቸው
ቅጣቶቹም፡
አስተዳደራዊ እርምጃዎች
ማስጠንቀቂያ መስጠት
ሪፖርቱ ወይም የሂሣብ መግለጫው የሚጠበቅበትን መሥፈርት እንዲያሟላ ማዘዝ
አቅም እንዲገነባ የሚያስፈልገውን ስልጠና እንዲወስድ ማዘዝ
ፈቃድ ማገድ፣ መሠረዝ
ከኃላፊነት ማንሣት
ከብር 1,000 እአከ 50,000 ቅጣት
በወንጀል መጠየቅ፡
እንደጥፋቱ አስከፊነት ከ 1 እስከ 5 ዓመት እሥራት
በአስተዳደር እርምጃና ወንጀል ተጠያቂነት
3. የቦርዱ ቁልፍ ሥልጣንና ኃላፊነት
1. ደረጃዎችና መመሪያዎች ማውጣት
-የፋይናንስ አቀራረብ
-የኦዲትና ጥራት ማረጋገጥ
-የድርጅት መልካም አመራር
-በባለሞያነት ለመራት መሥፈርቶችን
2. ምዝገባና ፈቃድ መስጠት
-ለባለሞያዎች
-ለሪፖርት አቅራቢ አካላት
-ለሞያ ማኅበራት(ዕውቅና(ለውጪ) ወይም አክሬዴሽን(ሀገር በቀል)
3. ትምህርትና ሥልጠና
-የሥልጠናና የምሥክር ወረቀት ፕሮግራሞች
-የግንዛቤ ግንባታና ማጎልበቻ
4. ቁጥጥርና ግምገማ
-የኦዲት አሠራር ግምገማ
-የሂሳብ መግለጫና ሪፖርት መቆጣጠር
5. ህግ ማስከበር
-ምርመራ
-የአስተዳደር ችሎትና
-በየደረጃው ይግባኝ ሥርዓት
አዋጅ 847/2006 የቀጠለ…
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የጥቅም ግጭት ካለ እንዲገልጹ ግዴታ ይጥላል


ኃላፊነት ሲቀበሉ ምሥጢር ለመጠበቅ ቃለ መሃላ መፈጸም አለባቸው እነዚህም፤-
-የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት
-የቦርዱ የአማካሪዎች ኮሚቴ አባል
-የቦርዱ ሠራተኞች
-ቦርዱን የሚያገለግል አማካሪ
መረጃን ይፋ ማድረግ
-አስፈላጊ ነው ተብሎ የታመነበትን መረጃ የሚይዝ መጽሔት
-የይግባኝ ሰሚ ፓኔል ውሣኔዎችን ጨምሮ መረጃን ይፋ ማውጣት
በዕለታዊ ጋዜጦች(ኤሌክተሮኒክ ወይም በሌላ)
በድረ-ገፅ
ደንብና (የሚኒስቴሮች ምክር ቤት) መመሪያ(ቦርዱ) የማውጣት ሥልጣን
የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች
የተሻሩና ተፈፃሚነት የሌላቸው ህጎች
የቦርዱ ማቋቋሚያ ደንብ 332/2007

የቦርዱ ዓላማ፡

-በሪፖርት አቅራቢ አካላት የሚቀርቡ የፋይናንስና ተያያዠ ሪፖርቶች አዘገጃጀትና አቀራረብ ጥራት ማስጠበቅ
-የኦዲተሮችና የሂሣብ ባለሞያዎችን የሙያ ደረጃ ማስጠበቅ
-የሂሣብ አያያዝና የኦዲት አገልግሎት ጥራት ማስጠበቅ
-የሂሳብ ሞያ የህዝብ ጥቅምን ማስጠበቁን ማረጋገጥ
-የሂሣብና ኦዲት ባለሞያዎችን የሙያ ነፃነት ማስከበር
ደንብ 332/2007 የቀጠለ…
4. የዳይሬክተሮች ቦርድ አሰያየም፣ የሥራ ዘመንና የውሣኔ አሠጣጥ ሥርዐት
የዳይሬክተሮች ቦርድ
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሰየማሉ
ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ተጠሪ ይሆናሉ
12 አባላት ይኖሩታል
በሂሣብ ሙያና ለሙያው ቀረቤታ ካላቸው ትምህርት መስኮች
ለሦስት ዓመት (ከአንድ ጊዜ በላይ ሊራዘም የሚችል)
በሁለት ሦስተኛ ምልዐተ ጉባዔና በድምፅ ብልጫ ይወስናሉ
በወር አንድ ጊዜ በመደበኛነት መሰብሰብ
ደንብ 332/2007
የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት
ተጠሪነቱ ለቦርዱ ይሆናል
ተጠሪነታቸው ለጽ/ቤቱ የሆነ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች
ሌሎች ሞያተኖችና ድጋፍ ሠጪ ሠራተኞች
ሥልጣንና ተግባር
-የቦርዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
-ቦርዱን ይመራል ያስተዳድራል
-ሠራተኞች ይቀጥራል
-የሥራ ፕሮግራምና በጀት ማዘጋጀት፣ ማስፈጸም ፤ የአፈጻጸም ሪፖርት ማቅረብ
-ክፍያዎችን መፈጸም
-ቦርዱን መወከል
-አስፈላጊ ነው ካለ ስልጣንኑን በውክልና መስጠት
ደንብ 332/2007 የቀጠለ…
ቦርዱ
የባለሞያዎች ምዝገባ ያካሂዳል
-የተመሠከረላቸው የሂሣብ ባለሞያዎች
-የተመሰከረላቸው ኦዲተሮች
-የሂሳብ ሙያ አገልግሎት ወይም የኦዲት አገልግሎት ለመስጠት የ ሚፈልጉ
ድርጅቶች
ያለምሥክር ወረቀት መሥራትን ይከለክላል
ሲኤዩ እና ሲፒኤ ምዝገባ ስለማገድና ስለመሰረዝ
የምዝገባና የሞያ ሥራ ፈቃድ አሠጣጥ
የቆይታ ጊዜና ዕድሣት መሥፈርቶችን ይደነግጋል
5. የአሠራር መንገዶች
የዳይሬክተሮች ቦርድ የቦርዱን እንቅስታሴዎች ይከታተላል
ፖሊሲና አቅጣጫ ያስቀምጣል
በጀትና የሥራ ፕሮግራሞች ይገመግማል
የአገልግሎት ክፍያዎችና ተመን ይገመግማል

ዋና ዳይሬክተሩና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮቹ ለቦርዱ ዕለታዊ እንቅስቃሴዎች ኃላፊዎች ናቸው


ከቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በጋራ መሥራት
የተጠያቂነት ሥርዓቶች
የአምስት ዓመት ዕቅድ
ዓመታዊ የድርጊት ዕቅድ
የሩብ ዓመትና ወርሃዊ የድርጊት ዕቅዶች
የሪፖርት ማቅረቢያና ምላሾች መቀበያ ሥርዓት
ገለፃው አበቃ
አመሰግናለሁ!

You might also like