You are on page 1of 31

 

ቴክኖሎጂን መቶ
ፐርሰንት
የመቅዳትና
የማሸጋገር ሂደት

ኢትዮጵያን
ታህሳስ 2012ዓ/ም እንገንባ
ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና
ይዘት
ክፍል 1፡ አጠቃላይ የቴክኖሎጂ መቶ ፐርሰንተ
መቅዳት አስፈላጊነትና ምንንት
ክፍል 2፡ የቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደት
ክፍል 3፡ የቴክኖሎጂ ሽግግር አስፈጻሚ አካላት
ተግባርና ሃላፊነት
የማንዋሉ አስፈላጊነት

 በቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፋችን ቴክኖሎጂ የመቅዳት፣ የማላመድና የማሸጋገር ስራን


ወጥ ባልሆነ ሁኔታ መተግበር ከጀመርን አመታት ተቆጥሯል፡፡
 ሆኖም ግን ለትግበራው ውጤታማነት ክፍተት የነበረበት በመሆኑ የተለያዩ
ተግዳሮቶች ሲያጋጥሙ ይስተዋላል፡፡
 ለአብነትም ከልማት ፕሮግራሞቻችን ፍላጎት የሚነሳ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ
ለማቅረብ በአግባቡ የእሴት ሰንሰለቶችን በመስራት የሚፈለገውን
ቴክኖሎጂ መቶ ፐርሰንት ቀድቶ ለሚፈለገው ዘርፍ በማቅረብና
ተወዳዳሪነትን በጉልህ ማረጋገጥ አለመቻልና የቴክኖሎጂ ሽግግር አስፈጻሚ
አካለት የማስፈጸም ውስንነት ዋና ዋና ችግሮች ናቸው፡፡
 በመሆኑም ያሉብንን ተግዳሮቶች አስወግደን ወጥ በሆነ መልኩ የቴክኖሎጂ
ሽግግር ስራዎችን ከልማት ፕሮግራሞቻችን ተወዳዳሪነትና ተጠቃሚነት
አንጻር በመቃኘት መተግበር ያስችለን ዘንድ ይህን ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ
የመቅዳትና የማሸጋገር ትግበራ ሰነድ ማዘጋጀት ተችሏል
የስልጠናው ዋና ዓላማ
 በትኩረት ዘርፎች የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ

ኢንተርፕራይዞች ያለባቸውን የቴክኖሎጂ


ክፍተቶችን በመለየት መሙላት የሚችሉ ምርጥ
ቴክኖሎጂዎችን መቶ ፐርሰንት በመቅዳት
በዘላቂነት ተወዳዳሪነቸውን የሚያረጋግጥ
ውጤታማ የቴክኖሎጂ ክፍተት መለየት
መቅዳትና ሽግግር ስርዓት እንዲኖር ለማስቻል
ግንዛቤ መፍጠር ነው፡፡
ቴክኖሎጂ ምንድነው?
o የተለያዩ መዝገበ ቃላት ቴክኖሎጂን በተለያዩ
አስተሳሰቦች የተረጎሙት ቢሆንም
በቴ/ሙ/ት/ስ ስትራቴጂ መሠረት ቴክኖሎጂ
ማለት አንድ አዲስ እሴት በመፍጠሩ ወይም
በመጨመሩ ምክንያት ተጠቃሚዎች ወይም
ደንበኞች ከሌሎች አብልጠው በፍላጎት
ሊገዙት የሚችሉት ቁስ፣ ማምረቻ መሳሪያ፣
አሰራር ወይም አገልግሎት ተብሎ ሊገለጽ
ይችላል፡፡
THIO of Technology (cf. Sharif 1993, p. 4)
የቴክኖሎጂ አይነቶች
1. የምርት/አገልግሎት ቴክኖሎጂ
የምርት ቴክኖሎጂ የሚባለው ሰዎች በነፍስ ወከፍ
የሚጠቀሙበት (consume) የሚያደርጉት እንደ
ምግብ፤ሸቀጣ ሸቀጦች፤ኬሚካል ፕሮሰሰኒንግ የግንባታ እና
የኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች እንዲሁም ሌሎች ሲሆኑ
2. የማምረቻ/አሰራር ቴክኖሎጂ
የምርት ቴክኖሎጂዎችን ለማምረት የሚውሉ መሳሪያዎች
ወይም ማሽኖች ናቸው፡፡
ቴክኖሎጂዎች በየሙያ ዘርፎቹ ሲተረጎሙ የምርት ቴክኖሎጂ
የአገልግሎት ቴክኖሎጂ ሊሆን የሚችል ሲሆን የማምረቻ
ቴክኖሎጂ ደግሞ በአሰራር ቴክኖሎጂ ሊተካ ይችላል፡፡
የቀጠለ……..
ቴክኖሎጅን በይበልጥ ለመረዳት አንዱ መንገድ አምራች
ድርጅቶች የሚፈልጉትን ቴክኖሎጅዎች በአራት ዋና ዋና
ክፍሎች በማየት ነው
1. ቁሳዊ ቴክኖሎጅ Technoware
ቁስን ያካተቱ መሳሪያዎች፡- የተለያዩ መሳሪያዎች
2. ዕውቀታዊ ቴክኖሎጅ Humanware
ሰውን ያካተቱ ችሎታዎች፡- ሙያ፣ ዕውቀት፣ ችሎታ፣
የቀጠለ….
3. ሠነዳዊ ቴክኖሎጅ Inforware
መዝገብን ያካተተ ሰነዳዊ ማስረጃዎች፡- ደረጃዎች፣
የንድፍ ዝርዝሮች፣ ያሰራርና የጥገና ማንዋሎች፣
4. ድርጊታዊ ቴክኖሎጅ Orgaware
ተቋምን ያካተተ የአደረጃጀት ማዕቀፎች፡- ዘዴዎች፣
ቴክኒኮች፣ ግንኙነቶችና ልምዶች፣
የቴክኖሎጂ አቅም ምን ማለት ነው

 የቴክኖሎጂ አቅም ማለት ከቴክኖሎጂ ለውጥ ጋር ተስማምቶ መሄድ


የሚያስችል የተቀናጀ ችሎታ ሲሆን ይህ አቅም የሚገኘው
በቴክኖሎጂአዊ የመማር ሂደት ውስጥ በሚገኝ የመቀበል ችሎታ ነው፡፡
 የመቀበል አቅም የነባራዊ እውቀት እና የተጠናከረ ጥረት ተብሎ በሁለት
ዋና ዋና ጉዳዮች ይወሰናል፡፡
ነባራዊዉ እውቀት
አዲስ ቴክኖሎጂ (እውቀትን፣ አሰራርን፣አደረጃጀት) ለማዋሃድና
ለመጠቀም የተሻለ የመቀበል አቅመ የሚፈጥር ነው
የተጠናከረ ጥረት
 የተጠናከረ ጥረት ችግሮችን ለመፍታት በጋራ የሚደረግ የተጠናከረ ኃይል
ማለት ሲሆን የመቀበል አቅምን ለመፍጠር ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል፡፡
ቴክኖሎጅና ቴክኖሎጅን የመማር አቅም

የተጠናከረ
ዝቅተኛ
ከፍተኛ ጥረት

የቴክኖሎጅ አቅም የቴክኖሎጅ አቅም


ከፍተኛ ከፍተኛና በፍጥነት ከፍተኛ ግን
እያደገ የሚሄድ እየወረደ የሚሄድ
ነባራዊ (Q1) (Q2)
የዕውቀት
መሠረት
የቴክኖሎጅ አቅም የቴክኖሎጅ አቅም
ዝቅተኛ ዝቅተኛ ግን ዝቅተኛና በፍጥነት
እያደገ የሚሄድ እየወረደ የሚሄድ
(Q4) (Q3)

የተጠናከረ ጥረት ከነባራዊው ዕውቀት ይልቅ ለተቋም


ረጅም ጊዜ ልምድና ተወዳዳሪነት በጣም አስፈላጊ ነው
የቴክኖሎጂ መቶ ፐርሰንት መቅዳት ምንነት

ቴ/መ/ፐ መቅዳት ማለት በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነት


ያላቸውን የምርት/አገልግሎት ወይም የማምረቻ/አሰራር
ቴክኖሎጂዎችን በማፈላለግ አዋጭነታቸው የተረጋገጡትን
 ንድፉን/አሰራሩን በማግኘት ወይም ቴክኖሎጂውን

በማግኘት አንድ በአንድ አካሎቻቸውን በመፍታትና


በመለካት (RE) እና እንዲሁም በአገልግሎትና አሰራር
ዘርፍ ያሉትን በመፈተሽ አስመስሎ በመቅዳት ለአገር
ውስጥ ገበያ ማቅረብ ማለት ነው፡፡
የቀጠለ……
 ይሁንእንጂ አንዳንድ ሊቀዱ የማይችሉ
የቴክኖሎጂው አካላት ስለሚኖሩ እነኚህን
ስታንዳርድ የሆኑ እቃዎች በቀጥታ ከገበያ ላይ
ገዝቶ መጠቀም የሚቻል ሲሆን በዚህ መልኩ
የተቀዳ ቴክኖሎጂ ከኦርጂናል ቴክኖሎጂው
በጥራት፣ “በቀለም”፣ በአሰራርና
በውጤታማነቱ/functionality/ እስካልተለየ
ድረስ መቶ ፐርሰንት ተቀድቷል ማለት ይቻላል
ቴክኖሎጂን መቶ ፐርሰንት የመቅዳት ዝርዝር አላማ

 የልማት ፕሮግራሞችን ፍላጎት በማገናዘብ ሌሎች


ያፈለቁትን ቴክኖሎጂዎች ፈጥኖ በመኮረጅ ሀብት አፍርቶ
አቅም ለመገንባት፣
 በተገነባ አቅምና በፈራ ሀብት የተኮረጀውን ቴክኖሎጅ

በማላመድ በሂደት በማሻሻል ተጨማሪ ሀብት ለመፍጠር፣


 ደረጃ በደረጃ በዩኒቨርስቲ፣ በግል ኩባንያዎችና በመንግስት

የምርምር ተቋማት አቅምን በመፍጠር፣ በምርምር ሀብት


ለመፍጠር፣
የቀጠለ………
 አሰልጣኞችም ሆነ ሰልጣኞች በስፋት
በቴክኖሎጂ የመቅዳት ሂደት ውሰጥ በማካፈል
አቅምን በመፍጠር ፕሮጀክትን መሰረት ባደረገ
ስልጠናን እንዲያጎለብቱ ማድረግ፣
 በሂደት በርካታ ተመራማሪዎችና

ቴክኖሎጅስቶችን በማፍራት የግል ኩባኒያዎች


ለሚያቋቁሟቸው የምርምር ተቋማት የሚሆን
የሰው ሀይል በጥራትና በቁጥር ለማፍራት
ሀገራችን በቀጣዩ 40 ዓመታት የቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደት

ከፍ ተ ኛ
ገቢ 12,61 የሕ ዳ ሴ ጉ ዞ
12,615
6
ነ ፍ ስ ወ ከ ፍ ገ ቢ (‘0 0 0 U S $ )

10
ድ ህነ ት አ ዙ ሪ ት
ሌላው የሰራውን
ከፍ ተ ኛ ቴክኖሎጅ በአግባቡ
መ ካ ከለ ኛ ተጠቅሞ በዘላቂነት
ገቢ መወዳደር ካልተቻለ

መ ካከ ለ ኛ
5 ገቢ አዙሪ ት
4,086 ሌላው የሰራውን
4,085 ቴክኖሎጅ ከመኮረጅ
ዝቅ ተ ኛ
መ ካከ ለ ኛ አልፎ አዳዲስና በአለም
ገቢ የቴክኖሎጅ ድንበር ያሉ
1,036 ቴክኖሎጅዎችን ማፍለቅ
ዝቅ ተ ኛ 1 1,035 ካልተቻለ
ገ ቢ 0.1

1995 2000 05 10 15 17 20 25 30 35 40 45 50 ጊዜ
ው ጤ ት ተ ኮር (ዓ .ም )
ው ጤ ት ተ ኮር ሥ ር ዓቱ ው ጤ ት ተ ኮር ሥ ር ዓቱ
ሥ ር ዓቱ በ ት ም ህር ት ና በኢ ን ዱ ስት ሪ
በ ት ም ህር ት ና
ሥ ል ጠ ና ዘር ፍ እና
ሥ ል ጠና
በ ኢ ን ዱ ስ ት ሪ የጋ ራ
(በ ቻ ም በ ሮ ች )
ዘር ፍ መ ሪነት
መ ሪነት ሙ ሉ መ ሪነት
2. ቴክኖሎጂን መቶ ፐርሰንት መቅዳትና ማሸጋገር የቅደም ተከተል የአሠራር ሂደት

የተመረጡ አዋጭ ቴክኖሎጂዎችን በተሳካ ሁኔታ


ለማሸጋገር ከታች በተቀመጠው የሽግግር ስርዓት
(high level map) መሰረት ከዘርፍ እሴት ሰንሰለት
ትንተና የተለዩትን ቴክኖሎጂዎች አዋጭነታቸውን
በማረጋገጥ፣ ሰነድ በማዘጋጀት፤ ናሙና አምርቶና
ፈትሾ እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ አሰራሮችን
ፈትሾ እስከ ሽግግር ድረስ ያለውን የቴክኖሎጂ
ሽግግር ሂደቶች የሚያሳይ ነው፡፡
የቀጠለ……..
 ይህንንሂደት በትክክል መተግበር ከተቻለ
የዘርፉን (ጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዞች) ተወዳዳሪነት
የሚያረጋግጡ ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳት
ማቅረብ/ማሸጋገር ይቻላል፡፡
ቴክኖሎጂ መቶ ፐርሰንት የመቅዳትና ማሸጋገር ሂደቶች

1. ከእሴት ሰንሰለት የተለየ መሆኑንና በቴክኖሎጂ


ዓይነቶች (humanware, technoware,
infoware and orgaware) ተለይቶ የተቀመተ
መሆኑን ማረጋገጥ፣
2. የተለየውን ቴክኖሎጂ በጥልቀት በመረዳትና
በመተንተን የአዋጭነት ትንተና ማከናወን፣
 ኢኮኖሚክ አዋጭነት
 ቴክኒካል አዋጪነት
 አካባቢ ደህንነት አዋጭነት
የቀጠለ…….
3. የቴክኖሎጂ ንድፍ(የሚያሰራ የአሠራር
ድሮዊንግ/ማኑዋል) እንደ ሙያ ዘርፉ
ማዘጋጀት፣
4. የቴክኖሎጂው የማምረቻ ወጪ ትመና
ማከናወን፣
5. በተዘጋጀው ንድፍ መሰረት የምርት
የአገልግሎት ቴክኖሎጂውን ናሙና ማዘጋጀት፣
የቀጠለ….

6. የተቀዳውን ቴክኖሎጂ በተቋም ውስጥና


በስራቦታ በተጠቃሚዎች ደረጃ የናሙና ፍተሻ
ማከናወን፣
7. በናሙና ፍተሻ የሚፈለግበትን አገልግሎት
መስጠቱ በተረጋገጠው ቴክኖሎጂ ላይ
አብዢዎችን በመምረጥ አብቅቶ ማሸጋገር፣
8 የፍይዳ ዳሰሳ ጥናት ማድረግና በውጤቱ
መሰረት አስፈላጊውን ማሻሻያ ማከናወን
ናቸው፡፡
በ ዓ ለ ም አ ቀ ፍ የጥራት ደረጃ/ መስፈርት ተ ፈ ላጊ ቴ ክ ኖ ሎ ጅ የ ማ ግ ኛ አ ማ ራ ጮ ች

የቴ ክ ኖ ሎ ጂ
መ ረ ጃዎ ች ዩኒቨርሲቲዎችና ምርምር
(P ate nts ) ተቋማት

 ከአምሮዊ ንብረት ጠባቂ


 From Open Sources,
ተፈላጊ ቴክኖሎጂ  Open Sources, e.g.
USPTO: Internet (e.g.
Biomass Briquette
e.g. Internet,
Press, etc.),
Donations (e.g.
 Imitation &
 Immediate Imitation
Assimilation (Trainers,
(Trainers, Trainees,
Trainees, Industry)
Industry)
 No restriction ከኢ ን ዱ ስ ት ሪ  Adequate capability
leads to further
በ re ve rs e Improvement & even
Engine e ring possibility to apply for
Imitation from at hand available Technology National Registration.
with Improvement options too.
e.g. Precious Stones Cutting Machine, Tricycle
using Motorcycle, etc.
የቴክኖሎጂ ንድፍ/የአሰራር ማኑዋል (Blue Print) ማዘጋጀት

የድሮዊንግ ንድፍ ሥራ ሲባል አንድን ቴክኖሎጂ በወጥነት ደረጃውን


ጠብቆ እንዲባዛ ለማገዝ
•የቴክኖሎጂ ልኬትና ምስል (Detail Drawing, sub-assembly, full

Assembly Drawing exploded view in isometric view)፤


•የአመራረትና አገጣጠም ሂደት (manufacturing Method
Description)፤
•የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎችን ዝርዝር ከነመገለጫቸው

(specification) የያዘ ሠነድ ሆኖ የሚዘጋጅ ሲሆን


የቀጠለ…….
 የአሠራር ንድፍ ማንዋል ደግሞ
የአሠራር/አገልግሎት ቴክኖሎጂ ለማሸጋገር
የሚያስችል ከመነሻው እስከ ምርት
ሥራው/አገልገሎት አሠጣጥ ድረስ
የሚያስፈልገውን
• የሥራ/ውህድ ቅደም ተከተል፤
• አስፈላጊ የጥሬ እቃ ዝርዝር ከነመገለጫቸው
(specification)፤ ቁሳቁስና መሳሪያዎችን
ያከተተ ሠነድ ሆኖ ይዘጋጃል፡፡
የወጪ ትመና ማዘጋጀት
 የተመረጠውን ቴክኖሎጂ ለማምረት የሚያስፈልጉ ወጭዎችን
በዝርዝር በመተነተን ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡
 ይህም ቴክኖሎጂው የሚሸጋግርለት ኢንተርፕታይዝ በትክክል
ቴክኖሎጂውን ለማምረት የሚፈጅበትን ወጪ ስለሚያሳየው
ምን ያህል ትርፍ ቢጨመርበት ደንበኞች ወይም ተጠቃሚዎች
ሊገዟቸው እንደሚችሉ ለመረዳት ያግዛል፡፡
 አጠቃላይ የወጭ ትመናው የሚያካትታቸው
ሀ. የጥሬ እቃ ወጪ (Material Cost)
ለ. የጉልበት ወጪ (Labour Cost)
ሐ. የተለያዩ ወጪዎች (Expenses cost)
በተዘጋጀው ንድፍ መሰረት የቴክኖሎጂውን ናሙና ማምረት

 ለአንድ ቴክኖሎጂ ንድፍ ከተሰራ በኋላ ያንን ንድፍ በተከተለ


መልኩ ናሙና ሊዘጋጅ ይገባል።
 በንድፍ ላይ የተመሰረተ የናሙና ዝግጅት በአሰራር ላይ ሊከሰቱ

በሚችሉ የልኬት፣ የቅርፅና የውህደት አለመጣጣም እነድዲሁም


ሊከሰት የሚችለው የገንዘብ፣ የጉልበትና የጊዜ ብክነት ሊያድን
ይችላል።
 በተጨማሪም ማንኛውም ናሙና በተዘጋጀው ዲዛይንና

ማቴሪያል መሰረት በሚፈለገው የጥራት ደረጃ (የብየዳ፣


የአገጣጠም፣ የአሰፋፍ፣ የውህድ፣ የቀለም አቀባብና ወዘተ)
መመረት ይኖርበታል።
 ሌላው በናሙና ዝግጅት ወቅት ሊስተዋል የሚገባው ነገር ናሙና

ከሞዴል የሚለይ መሆኑ ነው።


የተቀዳውን ቴክኖሎጂ ናሙና ፍተሻ ማከናወን

 የናሙና ፍተሻው የተመረተውን ቴክኖሎጂ ትክክለኛነትንና የታለመለትን


ግብ መምታት መቻሉን ማረጋገጫ መሳሪያ ነው።
 በናሙና ፍተሻ ወቅት ቴክኖሎጂው የታለመለትን ተግባር ከመወጣት ባሻገር
መቶ ፐርሰንት መቀዳቱን የሚረጋገጥበት ተግባር ነው፡፡
 ይህም ቴክኖሎጂው በውጤታማነቱ፣ በአካል እይታ (የብየዳ፣ የአገጣጠም፣
የአሰፋፍ፣ የውህድ፣ የቀለምና ወዘተ ጥራት) ከኦርጂናል ቴክኖሎጂው ጋር
መቶ ፐርሰንት መመሳሰሉ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡-
 በቴክኖሎጂው ናሙና ፍተሻ የሚሳተፉ አካላት በቴክኖሎጂው ዙሪያ
ባለሙያ መሆን ይገባቸዋል፡፡
 የፍተሻው ውጤት አሉታዊ ከሆነ ወደኋላ መለስ በማለት ከእሴት ሠንሠለት
ትንተና ወይም ከንድፍ ድሮዊንግ/ማኑዋል ወይም ናሙና ምርት ጀምሮ
እርምት ወስዶ አጠናቆ ማውጣት ያስፈልጋል።
በፍተሻ የተረጋገጠውን ቴክኖሎጂ ማሸጋገር
 ቴክኖሎጂውን ለማባዛት መጀመሪያ አብዢን መለየት
ያስፈልጋል፡፡
 የአብዢዎችን አቅም በሰው ሀይል ብዛት፣ በእውቀትና ክህሎት፣

የማምረቻ ቴክኖሎጂ፣ የገንዘብ አቅምን ከግምት ውስጥ


በማስገባት መለየት ያስፈልጋል፡፡
 የቴክኖሎጂ አብዢዎች ከተለዩ በኋላ ያለባቸውን የክህሎት

ክፍተት በመለየትና ክፍተቱን የሚሞላ ስልጠና አዘጋጅቶ


በመስጠት ማብቃት አስፈላጊ ነው
 በዚህ መልኩ ቴክኖለሎጂው ከተሸጋገረ በኋላ በአራቱ የኢ/ኤ/አ

የድጋፍ ማዕቀፎች መሰረት ድጋፉን በመስጠት ቀጣይነት ባለው


መልኩ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን በመስራት
ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
ፋይዳ ዳሰሳ (Impact Assessment)
 የፋይዳ ዳሰሳ በቴክኖሎጂው ሽግግር የመጣን ለውጥና
ህብረተሰቡ ተጠቃሚ መሆኑን የምናረጋግጥበት ስልት ነው
 የተሸጋገረን ቴክኖሎጂ በማህበረሰቡ ኑሮና ዕድገት ላይም ሆነ

በተሸጋገረበት ኢንዱስትሪ ምርት ጥራት፣ ምርታማነትና ገበያ


ላይ ለውጥ ማምጣቱን የዳሰሳ ጥናት በማከናወን ማረጋገጥ
ያሰፈልጋል፡፡
 የፋይዳ ዳሰሳው በአሰልጣኝ፣ በተቋም፣ በክልልና በፌዴራል ደረጃ

የሚከናወን ሲሆን
 በአጠቃላይ በዚህ ዳሰሳ ጥናት የሚገኘው ውጤት በቀጣይ

ቴክኖሎጂው ላይ ለሚደረገው ለውጥና ለእሴት ሰንሰለት ክለሳ


እንደ ግብዓት ያገለግላል፡፡
የቀጠለ….
አመስግናለሁ

You might also like