You are on page 1of 27

የፈተና ስጋትን መከላከል

ለጎንደር ዩንቨርሲቲ አዳሪ ላልሆነ ትምህርት ቤት


ተማሪዎች የተዘጋጀ ስልጠና

አሰልጣኝ ተሾመ አጀበው


ሀሳብ ማፍለቂያ ጥያቄዎች
• የራሳችሁ የሆነ የፈተና አወሳሰድ ስልቶች አላችሁ?

• የፈተና ስጋት አጋጥሞህ ያውቃል?

• የፈተና ስጋትን እንዴት ማስወገድ ይቻላል?

• ፈተና ባግባቡ ለመስራት ምን ማድረግ አለብን?

12/28/2023 በሳይኮሎጅ ት/ክፍል የተዘጋጀ


የፈተና ስጋት

ወይኔ
ፈተና ደረሰ
ምን
ይውጠኝ
ይሆን??
የፈተና ስጋት ምንድነው?
ከፈተና በፊት፣በፈተና ጊዜ ወይም ከፈተና በሁዋላ
የሚስማ የስጋት፣ የጭንቀት፣ ያለመረጋጋት፣
ያለመመቸት ስሜት ነው::
የፈተና ሰጋት አብዛኛውን ተማሪ ያጠቃል::
ደረጃው ከግለስብ ግለሰብ ይለያያል::
Performance anxiety/የውጤታማነት ስጋት ነው
(ይሄን ፈተና እወጣው ይሆን?)
12/28/2023
በሳይኮሎጅ ት/ክፍል የተዘጋጀ
የፈተና ስጋት ምልክቶች
አስተሳሰሰብ፡ ዝቅተኛ በራስ መተማመን ፣ አሉታዊ
አስተሳሰብ፣ የመስራት ችሎታን መጠራጠር፣ ትኩረት
ማድረግ አለመቻል
ስሜት፡ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ ውጥረት፣ ግራመጋባት፣
ደብርት፣ ንዴት
አካላዊ ምልክቶች፡ የሆድ ህመም፣ ማቅለሽለሽ፣ የልብ
ምት መጨመር፣ የጡንቻ መኮማተር፣ የእጅ ማላብ፣ ቶሎ
ቶሎ መሽናት ፣ የድካም ስሜት….
ባህሪ/ድርጊት፡ እንቅልፍ ማጣት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣
ጥናትን ለነገ ማለት፣ ፈተናው ዋጋ የሌለው ማሰመሰል

12/28/2023 በሳይኮሎጅ ት/ክፍል የተዘጋጀ


የፈተና ስጋት ምክንያቶች
የጥናት ክህሎት ማነስ
ጥናትን ለነገ ማለት
አሉታዊ የፈተና ልምድ
ፈተናውን ለማለፍ ከፍተኛ ፍላጎት/ጫና
ፈተናውን እወድቃለው ብሎ ማሰብ/መጠበቅ
በቂ ያልሆነ የፈተና ዝግጅት
ራስን መጠራጠር
መሳሳት የለብኝም ብሎ ማሰብ/perfectionist
ስለ ፈተና ስጋትህ መጨነቅ
12/28/2023 በሳይኮሎጅ ት/ክፍል የተዘጋጀ
የፈተና ስጋት ውጤቶች
ፈተናው ላይ ትኩረት ማድረግ አለመቻል
ያጠኑትን አለማሰታወስ
የማስተዋል ወይም ችግር የመፍታት ችሎታ
መቀነስ
የፈተና ውጤት መቀነስ
አጠቃላይ የመማር አቅምን/ችሎታን ይጎዳል
12/28/2023 በሳይኮሎጅ ት/ክፍል የተዘጋጀ
እኔ ምለው ይህን
የፈተና ስጋት
መቀነስ ይቻል
ይሆን?
አዎ ይቻላል!!!
የፈተና ስጋት ለመቀነስ እና በፈተና ውጤታማ
እንድትሆኑ የሚያግዙ አምስት ዘዴዎች

• አንደኛ፡- በራስ ማመን

• ሁለተኛ፡ መዘጋጀት
•ሦስተኛ፡- ጊዜን በአግባቡ መጠቀም

• አራተኛ፡- በብልሃት ማጥናት

• አምስተኛ:- የፈተና አወሳሰድ ስልቶች


አንደኛ፡ በራስ ማመን!

1. አዎንታዊ አስተሳሰብ መያዝ


በጣም አስፈላጊ ነው!
2. ጥንካሬና ድክመትህን/ሽ
መገንዘብ!
3. ሊታሳኮቸው የሚገቡ ግቦችን
መጣል!

“ ስኬታማ ለመሆን መጀመሪያ እንደምንችል ማመን ይገባናል”


Michael Korda
ሁለተኛ፡ መዘጋጀት
እንዴት???

1. ማስታወሻ ፁህፎች /Notes


• የትምህርት ማስታወሻ ፁህፎች ከሌላ ትምህርቶች ለያይቶ ማስቀመጥ
• ማስታወሻ ፁህፎች በጊዜ በይዘት ቅደም ተከተል ማስቀመጥ
• ሁሉም አስፈላጊ የጥናት ቁሳቁሶች መኖራቸውን ማረጋገጥ (ለምሳሌ፡-
መማሪያ መፀሐፍ፣ ኳልኩሌተር፣ የቀድሞ ፈተናዎች ወዘተ)
2. ቀና ሁኑ!
• ከዚህ በፊት እንደሰራችሁት አድርጋችሁ ባትሰሩትም አልረፈደም
• ራሳችሁን በቁጥጥር ስር በማድረግ ባላችሁ ጊዜ በቂ ዝግጅት አድርጉ
ጠንካራ ስራ !!

ስኬት ጠንካራ ስራ ይፈልጋል


ጥንቃቄ አድርጉ!
ምንም ሳይሰሩ ጨርሻለሁ እያሉ ሚያወሩትን መስማት ጫና
ሊያሳድርባችሁ ሲለሚችል ሰምታችሁ እንዳልሰማችሁ በመሆን በራሳችሁ
የአጠናንን ፍጥነትና ችሎታ የቀራችሁን ለመጨረስና ለመከለስ ጥረት
አድርጉ!
ማከናወን እንደምትችሉ ስለሚታስቡት ነገር ጥርጣሬ አይግባችሁ
በጥልቀት ከልሱ እንዲሁም ልዩነት ሊፈጥሩ ከሚችሉት ሰዎች እገዛና
ድጋፍ ወሰዱ
ስለሆነም በፍፁም ለራሳችሁ እንዳማትችሉት አትናገሩ!
ሦስተኛ፡- ጊዜን በአግባቡ መጠቀም

ሽመዳዳን ማስወገድ!!
• የጥናት መርሃ-ግብር ማዘጋጀት
- በቀን በየትኛው ሰዓት ብታጠኚ|ብታጠና በደንብ ታጠናለህ?
- ምን አይነት ተግባሮችን ታከናውናለህ/ሽ?
- ምን ያህል ይዘቶች በእያንዳንዱ ትምህርት ይቀርሃል?
-ከአሁን ጀምሮ እስከ ፈተና ምን ያህል ጊዜያት ይቀርሃል/ሻል?
እውነተኛ ሁን/ኚ!
አራተኛ፡- በብልሃት ማጥናት
• የተለያዩ የጥናት ዘዴዎችን በጥምረት መጠቀም ለምሳሌ፡ ድምፅን አውጥቶ
መወያየት፣ዋነኛ ሃሳቦችን የያዙ ካርዶች መጠቀም፣ ቻርት፣ ወዘተ
 ኖቶችን ብቻ አታንብብ!
 የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አስፈላጊ የጥናት ፁህፎችን
ሦስት ጊዜ ደጋግሞ መከለስ

አስታውሱ፡
አእምሯችሁ ውስጥ መረጃን
ለማደራጀት እየሞከራችሁ
ነው!!!
አራተኛ፡- በብልሃት ማጥናት
• “ተማሪዎች 10% ካነበቡት፣ 20% ከሰሙት፣ 30% ካዩት፣ 50%
ካዩትና ከሰሙት፣ 70% ከሌሎች ጋር ካደርጉት ውይይት፣ 80%
በግል ካገኙት ልምድ፣ እና 95% ሌሎችን ካስተማሩት ይማራሉ”
William Glasser
• ለፈተናዎች እንዴት እናጥና
1. በፈተና ወቅት ምን ሊገጥም እንደሚችል ማወቅ
2. በ40 ደቂቃ ውስጥ ሊነበቡ የሚችሉ ነገሮችን በይዘት በመከፋፈል
ማዘጋጀት እያንዳንዱን ይዘት ካጠናቀቅን በኋላ እረፍት መውሰድ
• በጥናት መጀመሪያ እና መጨረሻ ላይ በደንብ እንማራለን
3. በምንከልሰብት ጊዜ ራሳችን ማን፣ ምን፣ መቼ፣ የት፣ ለምንና እንዴት
የሚሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ
4. ያለፉ ፈተናዎችን በምንከልስበት ጊዜ ጥብቅ ትኩረት ማድረግ
5. የመማሪያ መፅሐፍ ከያዝን ጎልተው የተፃፉ ቃላቶችን መከለስ
6. የመለመማጅያ ቅፅ ካለን ማጠናቀቅ
7. ማንኛውንም ማስታወስ የሚገቡ ስሞች፣ ቀናት፣ ፎርሙላዎች
(formulas) ትርጓሜዎች (definitions) ወይም እውነታዎች
(facts) በማስታወሻ ካርዶች ላይ መፃፍ
አምስተኛ፡- የፈተና አወሳሰድ ስልቶች

አጠቃላይ መመሪያዎች
በራስህ/ሽ መተማመን፡ ፈተናወን መስራት ትችላለለህ/ሽ
የፈተና ውጤት ያንተ/ቺ ማንነት መለኪያ አይደለም
በፈተና ወቅት የተወሰነ ውጥረት ተገቢ/የሚጠበቅ ነው
ፈተናውን ምን ያህል እንዳጠናህ ለማሳየት እንደ ዕድል አዎ የፈተና
ስጋትን መቀነስ
ተጠቀምበት
ይቻላል!
ዝግጁ ሁን/ኚ፣

12/28/2023 በሳይኮሎጅ ት/ክፍል የተዘጋጀ


ከፈተና በፊት!!
• በቂ ምግብ መመገብ እና በቂ እረፍት ማግኘት
• ከፈተና በፊት ቀደም ብሎ ወደ መኝታ ስትሄድ ቴሌቪዝን
ወይም የኮምፒውተር ጌሞችን አለመጫዎት

የመጨረሻ ደቂቃ ጥናት እና ሽምደዳ


ብዙውን ጊዜ ለፈተና ስለማያግዝ ቀደም
ብሎ ጥናትን ማጠናቀቅና በቂ እንቅልፍ
ማግኘታችሁን ማረጋገጥ
ከፈተና በፊት
• ከፈተና በፊት መከለስ
• የፈተናውን ቀን እና ሰዓት በትክክል ማወቅ
• ፈተና ከመድረሱ አንድ ቀን በፊት ጥናት መጨረስ
• ፈተናዎችን ለክለሳ መጠቀም
• ከፈተና በፊት ባለዉ ሌሊት ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት
• ጥሩ ቁርስ መመገብ ፡በባዶ ሆድ ወይም በጣም ጠግቦ ወደፈተና አለመሄድ
• ከፈተና ሰዓት ቀድሞ መገኘት
• የሠዓትን አቆጣጠር ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ
• የተሰጠውን የጊዜ መጠን ማወቅ
• መቀመጫው ችግር እንደሌለበት ማረጋገጥ
• ጭንቀት ካለ በጥልቀት መተንፈስ
• የፈተና ወረቀት ብዛትና የጥያቄው ቁጥር ትክክል መሆኑን ልብ ማለት
• የፈተናውን ትዕዛዝ ማንብብ ፣ በትክክል መረዳትን ማረጋገጥ
• የልገባችሁ ቅር የሚል ነገር ካለ መጠየቅ
12/28/2023 በሳይኮሎጅ ት/ክፍል የተዘጋጀ
በፈተና ጊዜ
• ፈተናዉን ለመዉሰድ ምቹ ቦታ መምረጥ
• መመሪያዎችን በጥንቃቄ ማንበብ
• ለፈተና የሚበቃ ጊዜ መገመት
• ሁሉኑም ጥያቄዎች አንዴ ገረፍ ገረፍ አድገርጎ ማንበብ
• ቁልፍ ቃላቶች ላይ ማስመር
• በጣም ቀላሎቹን በቅድሚያ መሥራት ከዚያም ወደ ከባዶቹ
ማምራት
• ጥሩ ማርክ የሚያስገኘው ላይ ጥሩ ጊዜ መስጠት ፣ ቀላል ማርክ
ላለው ደግሞ አጠር ያለ ጊዜ መድብ
• ከባድ ጥያቄዎችን ምልክት አድርጎ ማለፍ
• ከተሰጠው ጊዜ ጋር አብሮ ለመሄድ ፍትነትን ማሰተካከል
• በ አንድ ጥያቄ ላይ ብዙ ጊዜ አለማጥፋት
• ሁሉንም ጥያቄዎች መሞክር
• በመጨረሻው ትርፍ ጊዜ እንደገና መከለስ
• ሌሎች ተማሪዎችን አለማየት
12/28/2023 በሳይኮሎጅ ት/ክፍል የተዘጋጀ
የምርጫ ጥያቄዎች
ጥያቄውን ሙሉ በሙሉ ማንበብ
አማራጮችን ሳያዩ ጥያቄውን
ለመመለስ መሞከር
ሁሉንም አማራጮች ማንበብ
ስህተት እንደሆኑ እርገጠኛ የሆንንበትን
አማራጮች መሰረዝ
የጥያቄው አካሄድ/pattern ላይ
አለማትኮር
አርፍተ ነገሩን ሐሰት ሊያድረጉ
የሚችሉ ቃላትን አስተውሉ
ምሰሌ፡ all, none, always, never,
none, no body, every one,
best, worst, absolutely,
certainly…
12/28/2023
በሳይኮሎጅ ት/ክፍል የተዘጋጀ
የቀጠለ….
አርፍተ ነገሩን እውነት ሊያድረጉ
የሚችሉ ቃላትን አስተውለውሉ
ምሳሌ፡ usually, sometimes,
probably, some, unlikely,
frequently, seldom,
much,most,may

12/28/2023
በሳይኮሎጅ ት/ክፍል የተዘጋጀ
ከፈተና በኃላ
ራሳችንን ማዝናናት
ከፈተናው ትምህርት
መውሰድ
በሚቀጥለው ፈተና ላይ
የበለጠ ለመሰራት ማቀድ

12/28/2023 በሳይኮሎጅ ት/ክፍል የተዘጋጀ


ሩቅ አላሚ ብዙ ይጓ ዛል!

26
አመሰግናለሁ

You might also like