You are on page 1of 6

መግቢያ

በሃገራችን የተማረ የሰው ኃይል ከማፍራት ባሻገር በየዘርፉ ገበያው የሚፈልገውን ተወዳዳሪ ፣ ጥራት እና ብቃት ያለው የሰው ኃይል ማፍራት ግድ ይላል።
የጀመርነውም የእድገት አቅጣጫ ጠንክሮ ይሄድ ዘንድ የቲቬት እስትራቴጂን በየዘርፉ መተግበር እና ማስቀጠልም ወሣኝነት አለው።

ይህንን መሠረት አድርጎ በየዘርፉ እድገታችንን የሚያስቀጥሉ እና ጉልህ ድርሻ በሚጫወቱ ዘርፎች ላይ የትኩረት አቅጣጫ ተነድፎ እየተሰራ ይገኛል። ከነዚህም
ዘርፎች አንዱ የተለያዩ ብረት ነክ የሆኑ አካላትን በማያያዝ ጉልህ ድርሻ ያለው የብየዳ ቴክኖሎጂ አንዱ ሲሆን በዘርፉ በተደረገው ጥናትም በሃገራችን ያሉትን
የልማት እንቅስቃሴ መሰረት አድርጎ እስከ አስር ሺህ (10,000) የሚደርሱ ብቁ የሰው ሃይል ማፍራት እንደሚጠበቅ ተለይቷል።

ይህንን የሰው ኃይል ለማፍራትና ወደ ገበያ ለማሰማራት በተለይም በዘርፉ ለተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመደገፍ በፌደራል ቴ/ሙ/ት/ስ/
ኤጀንሲ ምህንድስና ብቃት ማዕከል ስር የብሔራዊ የብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከል በአዲስ አበባ እንዲሁም የመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ማሰልጠኛ ተቋም
በመቀሌ ተቋቁሟል። ይሁን እንጂ እነዚህ ሁለት ተቋማት በዘርፉ ሊፈሩ የታሰበውን ባለሙያዎች በእድገት ዘመኑ ብቻቸውን ሊያሳኩ እንደማይችሉ ስለታመነበት
በዘርፉ የተመረጡ ሌሎች አብዢ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በክልሎች አቋቁሞ በትብብር ለመስራትና የተቋማቱን አብዢ መምህራንን በቅድሚያ በአለም አቀፍ
እውቅና በተቋሙ እንዲሰለጥኑ ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል።

በዚህም በተለይ በ Cee የሚገኘው የብሔራዊ የብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከል ከአጫጭር የዘርፉ የብየዳ ሂደቶች በተጨማሪ የመካከለኛ ጊዜ ስልጠናዎች ከክልልና ከተማ
መስተዳድር ለሚመጡ አብዢ የቴ/ሙ/ ተቋማት አሰልጣኞች እና ለኢብኮ ባለሙያዎች እንዲሰጥ ታቅዶ የታቀደው እቅድም የተጀመረ ሲሆን በ 2007 ዓ.ም.
በሁለት ዙር ሁለተኛ ሩብ ዓመትና አራተኛው ሩብ ዓመት ብቃታቸው የተረጋገጠ 38 ሰልጣኞችን ከጀርመኑ /SLV Manhaim/ የብየዳ ማሰልጠኛ ተቋም ጋር
በመተባበር ማሰልጠንና ማስመረቅ የተቻለ ሲሆን በተጨማሪም 30 ሰልጣኞችን አሰልጥኖ ፈተና በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

በቀጣይ ቀድመው በሌቭል 4(አራት) የሰለጠኑትን ወደ ልቭል 6(ስድስት) የለማሳደግ ስልጠና ተቋሙ እንዲሰጥ የታቀደ ሲሆን እቅዱንም ለማስተግበር የሚያስፈልጉ
መስፈርቶችን እና የድርጊት መርሃ ግብሮችን የያዘ የ TOR ሠነድም እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።

የሥልጠናው አጠቃላይ አላማ

በኢንዱስትሪና በማሽነሪዎች ግንባታዎች ላይ የጥራት ቁልፍ ማነቆ የሆኑትን የብየዳ ቲክኖሎጂ ችግሮችን እና የዘርፉን ሥር የሠደደ የባለሙያዎችን የክህሎት
ክፍተቶች እንዲቀረፉ አለማቀፍ መስፈርትና ተወዳዳሪነትን የጠበቀ የክህሎትና የንድፈ ሃሣብ ሥልጠና በ MMA (Manual Metal Arc welding) እና MAG
(Metal Active Gas) በተባሉ የብየዳ ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ 30 ሠልጣኞችን ለአራት ሣምንታት በአለም ዓቀፍ ደረጃ ማሰልጠን፡፡

የሥልጠናው ዝርዘር አላማዎች

1
 በብየዳ ቴክኖሎጂ በእውቀትና በተግባር አንፀው ገበያው የሚፈልገውን የሠው ኃይል የሚያፈሩ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ መሪ
አሠልጣኞችን የቴክኒክ፣ የክህሎትና የንድፈሃሣብ ክፍተቶችን በመለየት አለምአቀፍ መለኪያን መሠረት ባደረገ ሥልጠና ማሰልጠን፡፡
 አገረችን በጀመረችውና በማከናውን ላይ ላይ በምትገኘው ግዙፍ ፕሮጀክት ላይ እየሰራ ያለውን የብረታብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) የዘርፉ
ባለሙያዎችን የክህሎት ሥልጠና ለመስጠት ጥራታቸውን የጠበቁ ሥራዎችና ምርቶችን ለማምረት እንዲችሉ ማብቃት፡፡
 ሠልጣኝ መምህራኖች በቴክኒካል ክህሎት የአለም አቀፉን ተጨባጭ ተሞክሮ እንዲያውቁ በማስቻል፤ በሚሄዱባቸው ተቋማት ይህንን ተሞክሮ እንዲያበዙና
እንዲያሸጋግሩ ማገዝ፡፡
 ሠልጣኞች በሚሠለጥኑባቸው የሥልጠና ዘርፎች ላይ ከክህሎትና ሥልጠና በተጨማሪ የማሽነሪ እንክብካቤና ጥገና ሥርዓት፤ የቅድመ ጥንቃቄ ልምዶችና
ተሞክሮዎችን ማሳወቅ፡፡
 ሠልጣኝ የቴ/ሙያ መምህራን በሚሠለጥኑበት የብየዳ ዘርፍ ከአለም አቀፉ የሞጁል አሠራር በመነሳት ገበያና ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን እንዴት በአጭርና
በረጅም ጊዜ ከፋፍሎ ማሰልጠን እንደሚችሉ ልምድ መስጠት፡፡

ከሥልጠናው የሚጠበቁ ውጤቶች

 የበያጆችና ቴክኒሻኖችን የሚያፈሩ ከክልልና ከተማ መስተዳድር ቴ/ሙ/ተቋማት ተመልምለው የመጡ 20 (ሃያ) አብዢ መምህራንን የላቀ የንድፈ ሃሣብና
የክህሎት ሥልጠና በመስጠት ማፍራት፤
 በብሔራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ ያሉትን 2 (ሁለት) አሰልጣኞች በደረጃ ስድስት ማብቃት፤
 በብሔራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ 1 (አንድ) አሰልጣኝ በማስመዘን ሪሰርተፊኬሽን ማሰጠት፤
 በዌልዲንግ ቴክኖሎጂ በቴክኒክ ክህሎቶች ብቃታቸው የተረጋገጠ በአለም አቀፍ ደረጃ የሠለጠኑ ተወዳዳሪ ሊሆኑ የሚችሉና ኢንዱስትሪውን በቀጥታ
የሚደግፉ 7 (ሰባት) የኢብኮ ባለሙያዎችን ማፍራት፡፡

የሥልጠናው ቦታ

 ሥልጠናው ፌዴራል ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኤጀንሲ ምህንድስና ብቃት ማዕከል(cee) በሚገኘው የብሔራዊ የብየዳ ማሠልጠኛ ማዕከል የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሥልጠናው ተጠቃሚዎች

 በክልልና ከተማ መስተዳድር የሚገኙ የቴ/ሙ/ተቋማት የበቁ አሰልጣኞችን ለማፍራት እንዲችሉ አብዢ መምህራን በማሠልጠናቸው ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
 የብረታብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ለሚያካሂደው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፤ የማዳበሪያ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታና ተከላ እንዲሁም ለዘርፉ
በሚያስፈልጉ ሌሎች ፕሮጀክቶች ተሳትፎ የሚደርግ የበቃ ባለሙያ በማግኘት ተጠቃሚ ይሆናል፡፡
 ስልጠናው ሞጁል 5 እና 6 ስለሆነ ስልጠናውን ለመሳተፍ ማንኛውም ሰልጣኝ ከዚህ በፊት ከሞጁል 1 እስከ 4 ያለውን ስልጠና የወሰደ መሆን ይኖርበታል፡፡

የሥልጠናው አይነት

2
 ሥልጠናው በሁለት የብየዳ ሂደቶች /Process/ የሚሠጥ ሲሆን እርሱም የ MMA /Manual Metal Arc/ እና MAG /Metal Active Gas/ የተሰኙ የብየዳ
አይነቶች ሲሆኑ፤ ስልጠናውም በሞጁል 5 እና 6 የአለም አቀፉን የንድፈሃሳብና ተግባር ተኮር ስልጠና መሠረት ያደረገ ይሆናል፡፡

የሥልጠናው ጊዜ

 አጠቃላይ ስልጠናው የሚወሰወደው ጊዜ ከጥቅምት 1 እስከ 30/2008 ዓ.ም ለ 22 የሥራ ቀናት የሚሠለጥኑበት ይሆናል፡፡ የሥልጠናው ክፍፍልን ከሠንጠረዥ 3
ይመልከቱ፡፡
ለሠልጣኞች የሚደረጉ ጥቅማ ጥቅሞች
 ከቴ/ሙ/ተቋማት ለመጡት ሰልጣኞች የጉዞና የቀን አበል ኤጀንሲው ይሸፍናል፡፡
 ለሥልጠናው የሚመጡ ሁሉም ሠልጣኞች የመኝታ አገልግሎት በ cee ማዕከል ባሉት ማረፊያዎች ይሰጣል፡፡
 በሥልጠናው ቀናት ለሚደረጉ የምሣ፣ የሻይ፣ ቡናና የውሃ ወጪዎችን ለቲቬት መምህራንና ለአሠልጣኞች ኤጀንሲው ይሸፍናል፡፡
 ለንድፈሃሣብ ሥልጠና የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች እና ሃንድአውቶች ለሁሉም ሠልጣኞች ተባዝቶ ይሰጣል፡፡

ከሠልጣኞች ምን ይጠበቃል?

 ሁሉም ሠልጣኞች መስከረም 30/2008 ዓ.ም እሁድ በማዕከሉ ግቢ ተገኝተው ሪፖርት ማድረግና አዳራቸውንም በማዕከሉ የሠልጣኞች ማደሪያ ክፍል
ይሆናል፡፡
 ሁሉም ሠልጣኞች የሥራ ቱታና የሥራ ጫማ ለሥልጠናው ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡
 ሁሉም ሠልጣኞች በሥልጠናው ወቅት የሥራ ትጥቅ እና የቅድመ ጥንቃቄ ትጥቆችን መልበስና መሥራት አለባቸው፡፡

ከብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምን ይጠበቃል?

 ለሁሉም የኢብኮ ሰልጣኞች የሚበቃ ማቴሪያል ስልጠናው ከመጀመሩ በፊት በቅድሚያ ለብሔራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከል ገቢ ያደርጋል ይኸውም ከዚህ
በፊት ተፈጥሮ የነበረውን የስልጠና ማቴሪያል ዕጥረትና የጊዜ ብክነትለመከላከል ይረዳል፡፡

ሥልጠናውን ለማካሄድ የሚያስፈልገው የበጀት ግምት

አጠቃላይ ሥልጠናውን ለማካሄድ በብር 1,069,536.60 ሣንቲም የሆነ አጠቃላይ የበጀት ግምት የሚያስፈልግ ሲሆን፤ የዝርዝር በጀቶችን ክፍፍል ከሠንጠረዥ 1
ይመልከቱ

3
ሠንጠረዥ 1. ለሥልጠናው የሚውል ዝርዝር የበጀት ክፍፍል

ተ.ቁ ዝርዝር መለኪያ የመለኪያ ዝርዝር የአንዱ አጠቃላይ ዋጋ/በብር/ አስተያየ


ብዛት ብዛት ዋጋ/በብር ት
የሰልጣኞች የውሎ አበል እና ሌሎች ወጪዎች
1. ከክልል ለሚመጡ ሰልጣኞች የትራንስፖርት በቁጥር 2 20 225 2*20*225=9,000.00
አበል
2. ለሁሉም የቲቬት መምህራን የቀን የውሎ አበል በቀን 30 20 225 30*20*225=135,000.00
3. ለሰልጣኞች እና አሰልጣኞች የካፍቴሪያ በቀን 22 30 100 22*30*100=66,000.00
አገልግሎት/የምሳ የሻይ ቡና እና የውሃ
/ወጪዎች
4. የአሰልጣኞች የወተት ወጪ በቀን 22 9 26 56*9*26=5,148.00
የስልጠና ቁሳቁስ እና የመሳሪያዎች ወጭ
5. ፓይፕ ∅ 168 x 200 x 8 ሚ.ሜ. በቤርጋ 1 16 7500 16*7500=120,000.00
6. ፓይፕ ∅ 120 x 80 x 5 ሚ.ሜ. በቤርጋ 1 20 10000 20*10000=200,000.00
7. የማግ የብየዳ ሽቦ ∅ 0.8 ሚ.ሜ. በቁጥር 1 13 500 13*500=6,500.00
8. የማግ የብየዳ ሽቦ ∅ 1.0 ሚ.ሜ. በቁጥር 4 13 1000 4*13*1000=52,000.00
9. OK Electrode በፓኬት
10. 1 የ CO2 ጋዝ ሙሌት በሲሊንደር 1 30 150 30*150=4,500.00
11. የማግ ዲፊውዘር በቁጥር 5 13 300 5*13*300=19,500.00
12. የኦክስጂን ጋዝ ሙሌት በሲሊንደር 1 30 150 30*150=4,500.00
13. የአሲቲሊን ጋዝ ሙሌት በሲሊንደር 1 15 120 15*120=1,800.00
14. ከተር ዲስክ ∅ 180 x 22 x 3.2 ሚ.ሜ. በቁጥር 1 120 30 120*30=3,600.00
15. ከተር ዲስክ ∅ 115 x 22 x 3.2 ሚ.ሜ. በቁጥር 1 40 25 120*25=3,000.00
16. ዋየር ብሩሽ በቁጥር 3 25 15 3*20*15=900.00
17. ካፕ ብሩሽ በቁጥር 1 15 75 15*75=3,750.00
18. የማግ ኮንታክት ቲፕ ∅ 1 ሚ.ሜ. በቁጥር 2 13 150 2*13*150=5,850.00
19. መጋዝ ባለ 24 ቁጥር 12’x300 ሚ.ሜ. በቁጥር 1 20 25 20*25=500.00
20. የባንድ ሶው ምላጭ በቁጥር 1 4 5000 4*5000=20,000.00
21. የማሽን ኩላንት በሊትር 50 1 37 50*37=1,850.00
የሴፍቲ መሳሪያዎች እና እቃዎች ወጭ (48350.00)
22. የእጅ ንት በቁጥር 4 30 50 4*30*50=6,000.00
23. የአይን መነጽር በቁጥር 1 30 40 30*40=1,200.00
24. ሄድ ማስክ በቁጥር 1 30 200 30*200=6,000.00
25. የክንድ መከላከያ ቆዳ (arm sleeve) በቁጥር 2 30 150 2*30*150=9,000.00
26. ክሊር ግላስ በቁጥር 6 30 10 6*20*10=1,200.00
27. ጥቁር መስታወት (የሽልድ) በቁጥር 3 30 25 3*30*25=2,250.00
4
28. የሴፍቲ ጫማ በቁጥር 1 10 2000 10*2000=20,000.00
29. የጆሮ መከላከያ ፕላግ በቁጥር 1 30 20 30*20=600.00
30. ደስት ማስክ በቁጥር 1 30 30 30*30=900.00
31. አቡጅዲ ጨርቅ በሜትር 30 1 40 30*40=1,200.00
ጠቅላላ ዋጋ 972,306.00
የመጠባበቂያ ዋጋ 10% 97,230.60
አጠቃላይ ድምር 1,069,536.60

ሠንጠረዥ 2. የሥልጠናው እቅድ እና የድርጊት መርሃ ግብሮች

ተ.ቁ ተግባራት የመፈጸሚያ ቀኖች ኃላፊነት የተሰጠው አካል አስተያየት


የብሔራዊ የብየዳ ማሰልጠኛ
1 የሥልጠና/TOR/ ማዘጋጀት ነሀሴ 28/2008 ዓ.ም
ማዕከል
2 የሥልጠና/TOR/ ማስፀደቅ ነሀሴ 30/2008 ዓ.ም የ CEE ዳይሬክተር
ከመስከረም 1-26 / የብሔራዊ የብየዳ ማሰልጠኛ
2 በወርክሾፑ ለስልጠናው የሚያስፈልጉ እቃዎችን ማዘጋጀት
2008 ዓ.ም ማዕከል
ለግዢ ታዘው ያልቀረቡ እቃዎችን በአስቸኳይ ግዢ እስከ መስከረም 15/2008 የብሔራዊ የብየዳ ማሰልጠኛ
3
እንዲቀርቡ ማድረግ ዓ.ም ማዕከል
4 ለሠልጣኞች ማረፊያ የሚሆኑ የመኝታ ክፍሎችን ማዘጋጀት መስከረም 26/2008 ዓ.ም የምህንድስና ብቃት ማዕከል
ለሥልጠናው ብቁ የሆኑ የተሻለ አፈጻጸም የነበራቸውን ከመስከረም 10-16 / 2008 የብ/ብ/ማ/ማዕከል እና
5
ሠልጣኝ መምህራንን ከተማት እንዲልኩ ማሳወቅ ዓ.ም የመምህራንን ልማት ቡድን
ከኢብኮ ለሚመጡ ሠልጣኞች ለስልጠናው የሚያስፈልጉ
7 እቃዎችን እንዲያቀርቡ ዝርዝሮችን መላክ እና እንዲያሟሉ መስከረም 2/2008 ዓ.ም. ብኢኮ በኢሜል
ማድረግ
ከኢብኮ ለሚመጡ ሠልጣኞች ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ብሔራዊ የብየዳ ማሰልጠኛ
መስከረም 25/2008 ዓ.ም.
እቃዎችን በተጠየቀው መሠረት መረከብ ማዕከል
ብሔራዊ የብየዳ ማሰልጠኛ
8 አጠቃላይ ሥልጠና መስጠት ከጥቅምት 1-28 / 2008 ዓ.ም
ማዕከል
በየሞጁሉ ማጠናቀቂያ የሠልጣኞችን ተግባር ተኮር ምዘና ጥቅምት 12 እና 26/2008 ብሔራዊ የብየዳ ማሰልጠኛ
9
ማካሄድ ዓ.ም. ማዕከል
ስለስልጠናው ሁኔታ አስተያየት እና ግምገማ ከሠልጣኞች ጥቅምት 5፣ 12፣ 19 እና የብሔራዊ የብየዳ ማሰልጠኛ
10
መቀበል 26/2008 ዓ.ም. ማዕከል
5
ስለ አጠቃላይ ሥልጠናው ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ብሔራዊ የብየዳ ማሰልጠኛ
12 ህዳር 6/2008 ዓ.ም
ማቅረብ ማዕከል

ሠንጠረዥ 3. የሥልጠናው የጊዜ ክፍፍል

የ/MMA/እና/MAG/
የመፈጸሚያ ጊዜያት ሳምንት 1 ሳምንት 2 ሳምንት 3 ሳምንት 4 ሳምንት 5
ሥልጠና

የሞጁል 5 ስልጠና ከጥቅምት 1-12/2008 ዓ.ም.

የሞጁል 6 ስልጠና ከጥቅምት 15-30/2008 ዓ.ም.

አጠቃላይ ፈተናና ምርቃት እስከ ህዳር 4/2008 ዓ.ም.

You might also like