You are on page 1of 1

የብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ መለያ ቁጥር 01/2015፣


የደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት መምሪያ በ UIIDP-ፕሮግራም በ 2015 በጀት ዓመት በዋና ዋና መንገዶች
የመብራት ዝርጋታ ስራዎችን/ Supply and Installation of LED Street Light/, የተፋሰስ ግንባታ (Drainage Construction)፤
የሰፈር ልማት ፕላን ስራ(Neigbourhood development plan)፤ የትራፊክ መብራት ዝርጋታ (Trafic light installation)፤ የአካባቢ
ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት (ለአስፓልት መንገድ፣ ለፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ፣ ለጥልቅ ውኃ ጉድጓድ ቀፋሮና ለቄራ ግንባታ)፤
ለአስፓልት መንገድ ግንባታ የዲዛይን ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፣
 በመንገድ መብራት ዝርጋታ ስራዎችን/ Supply and Installation of LED Street Light/ እና የትራፊክ መብራት
ዝርጋታ (Trafic light installation), በ Electro-Mechanical /Electricity Contractor ደረጃ 5 እና በላይ
የሆናችሁ፣
 በተፋሰስ ግንባታ (Drainage Construction) በመንገድ ግንባታ (RC) እና አጠቃላይ ግንባታ ተቋራጪ (GC), ደረጃ
6 እና በላይ የሆናችሁ፣
 ለሰፈር ልማት ፕላን ስራ (Neigbourhood development plan) በኢንጅነሪንግ፣ አርክቴክትና የከተማ ፕላን
አማካሪነት (Engineering Archictect and Urban planning ደረጃ 3 እና በላይ፣
 ለአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ስራ በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት ወይም በአካባቢ ኦዲት እና አጠባበቅ ደረጃ 1
የማማከር ፍቃድ ያላችሁ፤
ሆናችሁ የሚከተሉትን ዝቅተኛ መስፈርቶች የምታሟሉ ተቋራጮች እንድትወዳደሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን
1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ማቅረብ የሚችሉ፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN /ያላቸው እና ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የግዥ መጠን ብር 100,000.00 አንድ መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን
የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቶች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ
ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ
ብር/ በመክፈል ደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተልማት መምሪያ ቢሮ 2 ኛ ፎቅ የግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ
ማግኘት ይቻላሉ፡፡
6. ስለ ስራው ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት እና
የፋይናንስና ቴክኒክ መወዳደሪያው ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ደ/ማ/ከ/አስ/ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ህንጻ 2 ኛ ፎቅ ግዥ
ፋ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 ኛዉ ቀን 11፡
00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለመንገድ መብራት ዝርጋታ ስራ ተወዳዳሪዎች ብር 200,000.00 /ሁለት
መቶ ሺህ ብር/፣ ለትራፊክ መብራት ዝርጋታ ተወዳዳሪዎች ብር 90,000.00 /ዘጠና ሺህ ብር/፣ ለተፋሰስ ግንባታ ስራ እና
ለሰፈር ልማት ፕላን ስራ ተወዳዳሪዎች ብር 30,000.00 /ሠላሳ ሺህ ብር/ እንዲሁም ለአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ስራ
ተወዳዳሪዎች ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በ ባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ
የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ዋጋ ለ 90 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
9. ጨረታው ተጫራቾች እራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ 2 ኛ ፎቅ ጋዜጣው በአዲስ
ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ በ 30 ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ታሽጎ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
ደ/ማ/ከ/አስ/ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ህንጻ 2 ኛ ፎቅ ግዥ ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
10. በ JV (Joint Venture) የሚወዳደሩ Joint Venture የሚፈጥሩ ሁሉም ድርጅቶች ከላይ በስራዉ ለሚወዳደሩበት የስራ
ዓይነት የተጠቀሰዉን ፈቃድና ዝቅተኛ መስፈርቶችን ማሟላት የግድ ይሆናል፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተልማት መምሪያ፣

You might also like