Professional Documents
Culture Documents
ቁጣ
ቁጣ
በመንፈስ ቅዱስ ስም አምኜ መንፈስ ቅዱስን ሠራጺ ብየ ምንም ለአጠይቆተ አካላት በስም፣
በውስጣዊ ግብር፣ በአካል፣ በኲነት ሦስት ብል በባሕርይ፣ በውጫዊ ግብር፣ በሥልጣን፣
በህልውና፣ በመንግሥት፣ በዕሪና አንድ አምላክ ብየ አምኜ ረዴኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ
በማድረግ ስለ ቊጣ ምንነት መጻፍ፥ እዠምራለኹ።
በገብረ ኢየሱስ
የመጸሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ቊጣን በሚገባ ወይም በማይገባ በሰው ላይ መፍረድ፣ መናገር፣
ሰውን መቅጣት፣ መገሠጽ በማለት ይተረጉመዋል።
፩. የእግዚአብሔር ቊጣ (ፍርድ)
1
መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሀት እግዚአብሔር ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ
እንያዝ፤ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና” ዕብ ፲፪፥፳፰-፳፱፣ ራዕ ፲፮፥፭-፯፤
፲፱፥፩-፪።
፪. የሰው ቊጣ
“በከንቱ ወንድሙን የሚቈጣ የገሃነም ፍርድ ይገባዋል” (ማቴ ፭፥፳፪)፤ “በከንቱ ወይም
ያለምክንያት” የሚለው ቃል ምክንያታዊና ለመንፈሳዊ ሕይወት ጠቃሚ በኾነ ጉዳይ መቈጣት
የሚገባ መኾኑን ጠቃሚ ነው። ማለትም እግዚአብሔር አምላክ ከንቱ የኾነን ቊጣ እንጂ
ተገቢን ወይም ምክንያታዊ የኾነን ቊጣን አልከለከለም። ምክንያቱም፥
“ወንድሙን በከንቱ የሚቈጣ የገሃነም ፍርድ ይገባዋል” (ማቴ ፭፥፳፪)። “በከንቱ የሚቈጣ”
ይላል እንጂ “የሚቈጣ” ብቻ አይልም። ሰዎች ከስሕተታቸው ለመመለስ፣ ለማነጽና
ለመገሠጽ፣ ሕጻናት ያልተማሩትን እንዲማሩ የተማሩትን እንዳይገድፉ፣ መናፍቃን
እንዳይሰለጥኑ፣ ሃይማኖት እንዳይጠፋ፣ ክህደት እንዳይስፋፋ የሚደርግ ቊጣ የጽድቅ ቊጣ
ወይም ተገቢ ቊጣ ይባላል። ተገቢ ቊጣ አስተዋይ ሰውን ከስሕተት አረንቋው ታወጣዋለች።
፩መቃ ፲፪፥፳፱፣ ዘፍ ፴፩፥፴፮-፶፭
ይኽም ማለት ቊጣ አለጊዜው ሲኾን እንጅ መቈጣት በራሱ በደል ወይም ኀጢአት አይደለም።
“ተቈጡ ግን አትበድሉ (ኀጢአትን አታድርጉ)” የሚለን ለዚኽ ነው፤ (መዝ ፬፥፬፤ ኤፌ
4
፬፥፳፮)። ነገር ግን መጽሐፍ “ተቈጡ” ሲል ትእዛዝ እያስተላለፍ ሳይኾን ሰው በተፈጥሮው
የሚቈጣ መኾኑን ለመግለጽ ነው። “ኃጢአትን አታድርጉ” የሚለንም ብትቈጡ እንኳ
ቊጣችኹን ፀሓይ ሳይጠልቅ አብርዱ ማለቱ ነው። ለዚኽ የቅዱስ ጻውሎስ ትምህርት
(በቈጣችኹ ፀሓይ አይግባ ለሚለው ትምህርት) መነሻው መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ
“እንግዲኽ መባኽን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ በዚያም ወንድምኽ አንዳች ከአንተ ላይ
እንዳለው ብታስብ በዚያ በመሠዊያው ፊት መባኽን ትተኽ ኺድ አስቀድመኽም ከወንድምኽ
ጋራ ታረቅ በኋላም መጥተኽ መባኽን አቅርብ” ብሎ በወንጌል ያስተማረን ትምህርት ነው
(ማቴ ፭፥፳፫-፳፬)።
ቊጣ የሥጋ ፍሬዎች ከሚባሉት አንዱ ሲኾን ውጤቱም ገነመ እሳት ነው። በከንቱ የሚቈጣ
ሰው ከዘለዓለም ሕይወት የተለየ ነው። “የሥጋ ሥራም የተገለተ ነው፤ እርሱም ዝሙት፣
ርኲሰት፣ መዳራት፣ ጣዖትትን ማምለክ፣ ሟርት፣ ጥል፣ ክርክር፣ ቅንዓት፣ ቊጣ፣ ዐድመኝነት፣
መለያየት፣ መናፍቅነት፣ ምቀኝነት፣ ይኽንም የሚመስል ነው። አስቀድሜ እንዳልኹ፥
እንደነዚኽ ያሉትን የሚያደርጉ ኹሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም”፤ “ወደድሙን
በከንቱ የሚቊጣ የገሃነም ፍርድ ይገባዋል”። ገላ ፭፥፲፱-፳፪፤ ማቴ ፭፥፳፪፣ “ተሳዳቢዎች
(በከንቱ የሚቊጡ) የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም” ፩ቆሮ ፮፥፱-፲፤ ኤፌ ፭፥፫-፭።
6
ሰው ለድንጋጤ፣ ለስሜት መጎዳት፣ ለብስጭት፣ ለፍርሐት፣ ለሞት የሚያጋልጥ ብሎም ለበቀል
የሚያነሣሣ ክስተት ነው።
7
ቊጣን ማስወገድ አለብን፤ እድናስወግድም ክርስትናችን ያስገድደናል። ስለኾነም ከቊጣን
ለመላቀቅ የሚከተሉትን መፍትሔዎች መተግበር ያስፈልጋል።
8
“ሐሰትን ተዉአት፤ ኹላችኹም ከወንድሞቻችኹ ጋራ እውነትን ተነጋገሩ፤ እኛ አንድ አካል
ነንና። ተቈጡ፤ አትበድሉም፤ ፀሓይ ሳይገባ ቁጣችኹንም አብርዱ፤ ለሰይጣንም መንገድ
አትስጡት። … ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ፣ የሚጠቅም
ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችኹ ከቶ አይውጣ። ለቤዛ ቀን የታተማችኹበትን
ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። መራራትና ንዴት፣ ቊጣንም፣ ጩኸትንም፣
መሳደብም ኹሉ ከክፋት ኹሉ ጋራ ከእናንተ ዘንድ ይወገድ” (ኤፌ ፬፥፳፮-፴፩)፤
“እናንተ ቊጣንና ንዴትን፣ ክፋትንም፣ ስድብን፣ የሚያሳፍርም ንግግር አስወግዱ” (ቈላ
፫፥፰)፤
“ሰው ኹሉ ለቊጣ የዘገየ ይኹን” (ያዕ ፩፥፲፱)፤
“ክቊጣ ራቅ” (መዝ ፴፯፥፰)፤
“ሕይወትን የሚፈቅድ (የዘለዓለም ሕይወት ሊያይ የሚፈልግ) ሰው ማን ነው? በጎንም
ዘመን ለማየት የሚወድ? አንደበትኽን ከክፉ ከልክል፤ ከንፈሮችኽም ሽንገላን እንዳይናገሩ።
ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ፤ ሰላምን ሻ፥ ተከተላትም። የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ
ጻድቃን ዦሮዎቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና።” (መዝ ፴፫፥፲፪-፲፭)፤
“ቊጡ ሰው አይጸድቅም፤ በቊጣ ጊዜ መከራ ይመጣል” (ሲራ ፩፥፳፩-፳፪)፤
“በአንደበትኽ አድጦኽ ከምትወድቅ በምድር ላይ አድጦኽ ብትወድቅ ይሻላል” (ሲራክ
፳፥፲፰)፤
“በውስጡ ብዙ ኃጢአት አለና ከአንደበትኽ የመዘባበት ነገር አይዉጣ፤ አባትኽንና እናትኽን
አትስደብ” (ሲራክ ፳፫፥፲፫)፤
“በአንድበት የማይስት ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ኹሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም
ሰው ነው። እነሆ፥ ይታዘዙን ዘንድ በፈረሶች በአፋቸው ልጓም እናገባለን፤ አካላቸውንም
ኹሉ ኣንመራለን። እነሆ መርከቦች ደግሞ አካላቸው ይኽን ያኽል ታላቅ ሲኾን በነፋስ
ኀይል ይነዳሉ፤ ይመላለሳሉም፤ ሰውም ይኽን ያኽል ታላሽ በኾነ መቅሰፊያ ይመልሳቸዋል፤
ወደ ወደደው ወደብም ያደርሳቸዋል። እንዲኹ ምላስም ትንሽ አካል ናት፤ ታላላቅ ነገርንም
ታመጣለች፤ እነሆ፥ እጅግ ትንሽ የኾነች እሳትም ይኽን የሚያኽል ጫካ ታቃጥላለች።
ምላስም እሳት ናት፤ እነሆ፥ ትንሽ ምላስ በሰውነታችን ውስጥ ዐመፅ የተመላበት ዓለም
ናት፤ ሥጋችንን ትበለዋለች፤ ውስጣዊ ሰውነታችንንም ትጠብሰዋለች፤ ከገሃምም ይልቅ
9
ታቃጥላለች። የአራዊትና የወፎች፥ የተቀሳቃሾች በባሕር ያለ የፍጥረት ወገን ኹሉ ለሰው
ይገዛል፤ ተአዝዞታልም። የሰው ምላስ ግን መግዛት የሚቻለው የለም፤ ክፉ ናት፤ ዐቅምም
የላትም፤ የሚገድል መርዝንም የተመላች ናት። በእርሷ እግዚአብሔር አብን
እናመሰግንበታለን፤ በእርሷም በአርአያ እግዚአብሔር የተፈጠረው ሰውን እንረግመዋለን።
ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ፤ ወንድሞቻችን ሆይ እንዲኽ አይኹን። ምንጭስ
ከአንድ አፍ የሚጣፍጥና የሚመርን ውኃ ያመነጫልን? ወንድሞቻችን ሆይ በለስ ዘይትን፥
ወይስ ወይን በለስን ሊያፈራ ይችላልን? እንዲኹም መራራ ውኃ ጣፋጭ ውኃ አይኾንም፤
ጣፋጭ ውኃም መራራ አይኾንም።” (ያዕ ፫፥፪-፲፪)
የሚሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይለ ቃሎችን በኅሊናችን ደጋግመን ማሰብ ቊጣን ለሚያነሣሱ
ሐሳቦችና ነገሮች በር እንዳንከፍት ይረዱናል።
10
አታስቡ፤ የሐሰትንም መሐላ አትውደዱ፤ ይኽን ነገር እጠላለኹና (ዘካ ፰፥፲፮-፲፯)፤ “በብርሃን
አለኹ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ፤ ወንድሙን የሚወድ በብርሃን
ይኖራል፤ ማሰናከያም የለበትም። ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ ይመላለሳል፤
የሚኼድበትንም አያውቅም፤ ጨለማው [ጥላቻው] ዐይኑን አሳውሮታልና” (፩ዮሐ ፪፥፱-
፲፩፣)፤ “ወንድሙን የማይወድ ኹሉ ከእግዚአብሔር አይደለም። … ወንድሞን የማይወድ
በሞት ይኖራል። ወንድሞን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው። … ማንም እግዚ አብሔርን እወደዋለኹ
እያለ ወንድሞን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚ አብሔርን
ሊወደው እንዴት ይችላል?። እግዚአብሔርን የሚወድ ወንድሙንም ደግሞ እንዲወድ ይችይ
ትእዛዝ ከርሱ [ከእግዚአብሔር] ናት” (፩ዮሐ ፫፥፲-፲፭፣ ፬፥፳-፳፩) በማለት መጽሐፍ ቅዱስ
ወንድምን መውደድ ማለት ምን ማለት እንደኾነ፣ ከእግዚአብሔር የሚያሰጠውን ጸጋ፤
በአንጻሩ ደግሞ ተግባሩን ሳይኾን አድራጊውን ወንድምን መጥላት ከእግዚአብሔር
እንደሚለየን፣ በዓይነ ሥጋችን የምናየውን ወንድማችንን ሳንወድ በዓይነ ልቦችን የምናየውን
እግዚአብሔርን እንወደዋለን ማለት እንደማይገባን ይነግረናል። ስለኾነም በከንቱ መቈጣት
ወንድምን የመጥላት ምልክት ስለኾነ መሠረቱን (የቊጣ መሠረት - ጥላቻን) በፍቅር
ልንተካው ያስፈልጋል።
11
ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር የጸና ሲኾን የእግዚአብሔር ህልውና ኹሌም በፊታችን እናዳለን፤
የምንሠራውንም ማናቸውንም ነገር መልካምም ይኹን መጥፉ እንደሚያየን፤ በምንኼድበት
ኹሉ በመንገዳችን አብሮ እንዳለን፣ ዓይኖቹ ዘወትር እኛን እንደሚመለከቱን ይሰማናል። በፊቱ
እንድቆምን፣ ኹሌም እንደምንመለከተው ይረዳናል። ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር የጸና
ሲኾንሥራችንን ከእግዚአብሔር አንለይም፤ በምንሠራው ሥራ ኹሉ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር
መኾኑን እርግጠኛ እንኾናለን፤ ሥራንንም በእግዚአብሔር ስም እንከውናለን። ፩ነገ ፲፯፥፩፣
መዝ ፲፭፥፰።
ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ልባዊ፣ እውነተኛና ከልብ የመነጨ ከኾነ ትዕዛዙን የምንጠብቀው
ባንጠብቀው የሚመጣብንን ቅጣት አይኾንም። መልካምነት ከመውደድ የተነሣ ይኾናል እንጂ።
ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ጽኑ ኾነ ማለት ዲያብሎስ እኛን ከመዋጋት ይከለከለዋል ማለት
አይደለም። ስለዚኽ በጽናት ይጠበቅብናል ማለት ነው።
12
ስለዚኽ ቊጣን መውደድ የሚያመጣውን ክፉ ነገር - ሲዖልን ካወቅንና ከፈራን ቊጣን
እንድንርቅ፣ እና እዳንለማመድ ያደርገናል። ማለትም ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር ከመጨመር
በተጨማሪ ቊጣን ለመራቅ ሲዖልን መፍራት ሌላው መድኅኒት ነው። ሲዖልን መፍራት ክፉ
ምኞታችንን ማራቅ ሳይኾን በጎ ምግባራትም እጀግ ፈጥነው ወደ እኛ እንዲመጡ ያደርጋል።
ፍርሐት ባለበት ቅንአት፣ ፍቅረ ነዋይ፣ ስግግብነት፣ ቊጣ የለም፤ በምትኩ ምጽዋት፣ ጸሎት፣
ትኩስ ዕንባ፣ ራስን መውቀስ አለ እንጂ።
6. ጸሎት
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “መጋደላችን ከሥጋና ከደም ጋር አይደለምና፤ ከአለቆችና
ከሥልጣናት ጋራ፣ ከዚኽም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር፣ በሰማያዊም ሥፍራ ካለ ከክፋት
መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር እንጂ። ስለዚኽ በክፉ ቀን ለመቃወም ኹሉንም ፈጽማችኹ
ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ጋሻ ጦር ኹሉ አንሡ” (ኤፌ ፮፥፲፪-፲፫) በማለት
መንፈሳዊውን ውጊያ በመንፈሳዊ መሣሪያ እንጂ በሌላ ማሸነፍ እንደማይቻል ያስረዳናል።
የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ/ጋሻ የተባሉት ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት እና የመሳሰሉት የትሩፋት ሥራ
ናቸው። እነዚኽን ትሩፋት ለመሥራት የመጀመሪያው ተግባር ደግሞ በፍጹም እምነትና
በመልካም ምግባር ጸንቶ በእግዚአብሔር መደገፍ ነው።
መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ “ወደ ፈተና እንድትገቡ ትጉና ጸልዩ” (ሉቃ፳፪፥፵፮)፣
ሐዋርያው ያዕቆብም “ከእናንተ መከራ የሚቀበል ማንም ቢኖር ይጸልይ” (ያዕ ፭፥፲፫) በማለት
እንዳስተማሩን ከማንኛውም ፈተና ለመዳን ጸሎት አስፈላጊ መሣሪያ ነው።
13
መንፈስ በውስጤ ዐድስ” በማለት በጸሎት መጠየቅ ያስፈልጋል (መዝ ፻፵፥፩-፬፤ ፶፥፲፣ ኤፌ
፬፥፴፩፣ ቈላ ፫፥፲፪-፲፫)። ይኽም ማለት ቊጣን አስወግደን ትዕግሥተኛ ለመኾን [ትግሥትን
ገንዘብ ለማድረግ] የእኛን ፈቃድ፣ ጥረት፣ ቅንነት ይጠይቃል ማለት ነው። ቊጣን ከእኛ
ለማራቅ የእኛን ጥረት ካልጨመርንበት ፥ የእርሱን ክፉነት ማወቅ ብቻውን ምንም ጥቅም
የለውም። ለዚኽ ሐሳብ ማጠናከሪያ ይኾነን ዘንድ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ሐሳብ
እንዋሳለን። “[ቊጣ ክፉ ግብር መኾኑን] ፣ ትዕግሥት ደግሞ በጎ ነገር መኾኑን ኹላችንም ያለ
ምንም ችግር እናውቃለን፤ ዐዋቂነት ተፈጥሯዊ ነውና። ትግሥተኛ ለመኾን ግን ያለምንም
ችግር፣ ይኽን የማድረግ ፍላጎታችን ሳይገደብና ብዙ ጥረትን ሳናደርግ ማከናወን አይቻለንም፤
ይኽ ፈቃደኛ ልብንና ቅንነትን የሚፈልግ እንጂ ልክ እንደ ዐዋቂነት ተፈጥሯዊ ኾኖ የተሰጠን
አይደለም” ትምህርት በእንተ ምክንያተ ሐውልታት ፲፫፥፱።
ዋቤ መጽሐፍት
1. መጽሐፍ ቅዱስ 2000 ዓ.ም ዕትምና (እና በስስ ቅጅ (Geez Amharic Bible Pro Version
6.1.1, በብራና አፕስ )
2. ትርጋሜ ኤፌሶን በቅዱስ ዮሐንስ አፈወቅር (ተርጓሜ ኃይለ ኢየሱስ መርሻ፣ 2013
ዓ.ም)
3. ትርጓሜ ማቴዎስ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወቅር (ተርጓሜ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ፣ 2011
ዓ.ም)
14
4. ትምህርት ምክንያተ በእንተ ሐውልታት በቅዱስ ዮሐንስ አፈወቅር (ተርጓሜ ገብረ
እግዚአብሔር ኪደ፣ 2008 ዓ.ም)
5. የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት (የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፣ 2008 ዓ.ም)
6. የቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት ትርጓሜ /ማብራሪያ ክፍል ኹለት (ከኤፌሶን እስከ
ዕብራውያን) መ/ር ስቡሕ አዳምጤ፣ 2013 ዓ.ም
7. ሕግጋተ ወንጌል፣ ብዙነኽ ሺበሺ እና ደምሴ ተፈራ ፣ 2010 ዓ.ም
8. https://eotcmk.org/a ‹‹ተቈጡ፤ አትበድሉም›› (ኤፌ. ፬፥፳፮) ፣ መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም
9. ነፍሴ የወደደችውን አያችኹትን? በአቡነ ሲኖዳ ሣልሳዊ (ትርጉም ዘኤልያስ ወልደ
ሚካኤል፣ 2014 ዓ.ም)
ከቶ አትማሉ ማቴ ፭፥፴፬
15
16