You are on page 1of 9

የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የ 2014 በጀት ዓመት ዕቅድ (ረቂቅ) ላይ እንደገና ሊታዩና ሊስተካከሉ

የሚገባቸው ዋና ዋና ግቦች/ዒላማዎች
መግቢያ
ኤጀንሲው ሚያዚያ 4 ቀን 2013 ዓ/ም በቁጥር ጠጉፋ 206/265/01 በተፃፈ ደብዳቤ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች
የ 2014 በጀት ዓመት ዕቅዳቸውን በማዘጋጀት እስከ ግንቦት 15 ቀን 2013 ዓ/ም እንዲልኩ መጠየቁ ይታወሳል፡፡ ለዕቅድ
ዝግጅቱ እንዲረዳ የዕቅድ ማዕቀፍ (outline) የተላከ ሲሆን በዚሁ መሠረት የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የ 2014
በጀት ዓመት ዕቅድ በሥራ አመራር ቦርድ የታየ ሰኔ 02 ቀን 2013 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ የተላከው ደርሶናል፡፡

በዚሁ መሠረት የፋብሪካውን የ 2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዋና ዋና ግቦች/ዒላማዎች ላይ
ትኩረት በማድረግ ተገምግሟል፡፡

ይኸውም፡-

ሀ. ከኤጀንሲው በተላከው የዕቅድ ማዕቀፍን (outline) ተከትሎ ስለመዘጋጀቱ፣


ለ. የ 2013 በጀት ዓመት የዋና ዋና ግቦች ዕቅድ አፈፃፀም፣ የባለፉት 3 ዓመታት ክንውን አማካይ
በመውሰድ እንዲሁም የ 2014 በጀት ዓመት ጋር በማነፃፀር መታቀዱን፣
ሐ. የድርጅቱን አምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ከተቀመጠው ጋር በማነፃፀር መታቀዱን፣
መ. የ 2014 በጀት ዓመት ዕቅድ እድገት፣
በማየት ከዚህ እንደሚከተለው የድርጅቱን የ 2014 በጀት ዓመት ዕቅድ በመገምገም ግብረ-መልስ ተዘጋጅቷል፡፡
ሀ. ከኤጀንሲው በተላከው የዕቅድ ማዕቀፍን (outline) ተከትሎ ስለመዘጋጀቱ፡-

 ከኤጀንሲው በተላከው የዕቅድ ማዕቀፍ (outline) መሠረት ዕቅዱ ተዘጋጅቶ መላኩ፤


 በዕቅድ ማዕቀፋ ያልተካተቱ በመርሃ- ግብር ተደገፎ የስጋት አስተዳደር፣ የውስጥ ኦዲት፣ የሥራ አመራር
ቦርድ እና የሠራተኛ የአቅም ግንባታ፣ እንዲሁም ሌሎች በዕቅዱ ሊካተቱ የሚገባቸውን ግቦች
ተካትተው መታቀዱ፡፡

1
ሠንጠረዥ 1፡- የ 2013 በጀት ዓመት የዋና ዋና ግቦች ዕቅድ አፈፃፀም፣ የባለፉት 3 ዓመታት ክንውን አማካይ፣ በስትራቴጂክ ግቡ
ለ 2014 የተቀመጠ ዕቅድ እንዲሁም የ 2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ማጠቃለያ
የ 3 ዓመታት ክንውን በስትራቴጂክ ዕቅዱ የሚያሳየው እድገት መግለጫ
ስትራቴጂካዊ ግቡ ከባለፉት 3 ዓመታት ከስትራቴጂክ ግቡ
ተ/ቁ መለኪያ የክንውኑ ለ 2014 የ 2014 ዕቅድ
ግቡ 2011 2012 2013 ክንውን ጋር የ 2014 ዕቅድ ከተቀመጠው ጋር የ 2014
አማካይ የተቀመጠ ሲነፃፀር ዕቅድ ሲነፃፀር
1 የምርት አቅም
አጠቃቀም (ሊደረስበት በ% 64 61 51.50 58.83 65.50 51.50 -12.46 -21.37
የሚችል)
2 ምርትና ምርታማነትን
19,925,632 18,910,719 16,010,319 18,282,223 20,082,000 15,968,987 -12.65 -20.48
ማሳደግ
-12.27
አልኮል መጠጥ በሊትር 13,500,496 12,999,193 10,951,469 13,502,000 10,951,469 -18.89
12,483,719
-12.66
ንፁህ አልኮል በሊትር 5,998,613 5,260,413 4,624,441 6,065,000 4,624,441 -23.75
5,294,489
-13.00
እሳት አልኮል በሊትር 426,523 522,268 406,592 515,000 393,077 -23.67
451,794
128,845
ሳኒታይዘር በሊትር 27,817
52,221
3 ሽያጭ በሊትር 0
አልኮል መጠጥ በሊትር 13,895,091 12,769,317 9,937,808 9,897,894
12,200,739
ንፁህ አልኮል በሊትር 28,816 161,874 48,976 72,000
79,889
እሳት አልኮል በሊትር 460,418 428,680 354,954 393,077
414,684
87,128
ሳኒታይዘር በሊትር 86,777
57,968
4
የማምረቻ ወጪ በሺህ ብር 371,535 534,094 341,431 415,687 373,822
5 817,513 945,474 837,160
አጠቃላይ ሽያጭ ገቢ በሺህ ብር 748,492 908,453 750,000 -10.41 -17.44
አልኮል መጠጥ በሺህ ብር 797,504 718,000
804,611 887,688 700,214
ንፁህ አልኮል በሺህ ብር 9,259 8,000
1,629 20,197 5,951
እሳት አልኮል በሺህ ብር 11,273 17,870 25,338 18,160 24,000

2
የ 3 ዓመታት ክንውን በስትራቴጂክ ዕቅዱ የሚያሳየው እድገት መግለጫ
ስትራቴጂካዊ ግቡ ከባለፉት 3 ዓመታት ከስትራቴጂክ ግቡ
ተ/ቁ መለኪያ የክንውኑ ለ 2014 የ 2014 ዕቅድ
ግቡ 2011 2012 2013 ክንውን ጋር የ 2014 ዕቅድ ከተቀመጠው ጋር የ 2014
አማካይ የተቀመጠ ሲነፃፀር ዕቅድ ሲነፃፀር
በሺህ ብር 19,719 16,989 12,236
ሳኒታይዘር 0
6 በሺህ ዶላር 465 508 534 502.45 440 440 -12.43
የኤክስፖርት ሽያጭ ገቢ
በሺህ ዶላር 491 516 490.67
አልኮል መጠጥ 465
በሺህ ዶላር 16.5 18 17.25
የእሳት አልኮል
በሺህ ዶላር 0.84 0 0.84
ሳኒታይዘር
7 242,045 290,635.33 263,592 210,000 -27.75 -20.33
ትርፍና ኪሳራ በሺህ ብር 304,855 325,006
8 አገልግሎት የማይሰጡ 200
በሺህ ብር
ንብረቶች በማስወገድ
9 የካፒታል በጀት በሚ/ን ብር 6.60 65.50 47.00 39.70 284.5 257.54 548.72 -9.48
አጠቃቀም
10 የመንግሥት ትርፍ
በሚ/ን ብር 102.00 75.00 65.00 80.67 60.00
ድርሻ ክፍያ
10 የአቅም ግንባታ ስልጠና 352 (ወንድ
255.00
ለሠረተኞች (አጭር በቁጥር 189 325 251 275 ሴት
ጊዜ) 77)
የረጅም ጊዜ ስልጠና ቁጡሩ
/ትምሀርትድጋፍ/
በቁጥር አልተገለፀም
11 የስራ ዕድል ፈጠራ በቁጥር 18 33
12 ማህበራዊ ኃላፊነት
በሚ/ን ብር 9.17
መወጣት
13 ወጪ ቅነሳ በሚ/ን ብር 1,000
14 የፕሮጀክቶች
አፈፃፀም
የፊዚካል ሥራዎች 23.41
በ% 23.41 96.4
ዕቅድ አፈፃፀም
የፋይናንሺያል ዕቅድ 5.07
በሚ/ን ብር 5.07 75.5
አፈፃፀም

3
የ 3 ዓመታት ክንውን በስትራቴጂክ ዕቅዱ የሚያሳየው እድገት መግለጫ
ስትራቴጂካዊ ግቡ ከባለፉት 3 ዓመታት ከስትራቴጂክ ግቡ
ተ/ቁ መለኪያ የክንውኑ ለ 2014 የ 2014 ዕቅድ
ግቡ 2011 2012 2013 ክንውን ጋር የ 2014 ዕቅድ ከተቀመጠው ጋር የ 2014
አማካይ የተቀመጠ ሲነፃፀር ዕቅድ ሲነፃፀር
15 እስከ
ሂሳብ መዝጋትና
በቁጥር መስከረም
ማስመርመር
/2013

4
ከዚህ በታች የተገለጹት የድርጅቱ የ 2014 በጀት ዓመት ዕቅድ በኤጀንሲው፣ በሥራ አመራር ቦርድ እና ማኔጅመንት ጋር
በጋራ መድረክ ከመገምገሙ በፊት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንደገና ታይተውና ተስተካክሎ እንዲላክልን እናሳስባለን፡፡

1. በክፍተት የተገመገሙ እና ሊስተካከሉ የሚገባቸው ነጥቦች


1.1. በ 2014 በጀት ዓመት 15,968,987 ሊትር ምርት በማምረት ሊደርስ የሚችለው የማምረት አቅም አጠቃቀም
51.5% ታቅዷል፡፡ ከኤጀንሲው በተላከው የ 2014 በጀት ዓመት የዕቅድ ዝግጅት ማዕቀፍ መሠረት የ 2014
ዕቅድ ከ 2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም በተከታታይ በአቅም አጠቃቀም ቢያንስ በ 15 በመቶ እድገት
ማሳየት እንዳለበት ተገልፀዋል፡፡ ነገር ግን የድርጅቱ የ 2014 በጀት ዓመት የማምረት አቅም አጠቃቀም
1.1.1. ከ 2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም 51.5 በመቶ ላይ ቢያንስ በ 15 በመቶ እድገት በማሳየት 59.23
በመቶ መድረስ ሲገባ 51.50 በመቶ ታቅዷል፣
1.1.2. ከፋብሪካው የ 3 ዓመታት አማካይ የማምረት አቅም አጠቃቀም 58.83 በመቶ አንፃር ሲታይ
የ 2014 በጀት ዓመት የማምረት አቅም አጠቃቀም እድገቱ በ 12.46 በመቶ ያንሳል፣
1.1.3. እንዲሁም በስትራቴጂክ ግቡ ላይ ለ 2014 የተቀመጠው 65.5 በመቶ አንፃር ሲታይ የ 2014
በጀት ዓመት የማምረት አቅም አጠቃቀም በ 21.37 በመቶ ያንሳል፡፡
ስለዚህ የፋብሪካው የማምረት አቅም አጠቃቀም ከኤጀንሲው ከተላከው የዕቅድ ዝግጅት ማዕቀፍ፣
የ 3 ዓመታት አማካይ ክንውን እና ከስትራቴጂክ ዕቅድ መሠረት ተስካክሎ የማምረት አቅም አጠቃቀም
እንደገና እንዲታቀድ፣
1.2. ከማምረት አቅም አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የኦፕሬሽን ሥራዎች ማለትም የምርትና ምርታማነት ዕቅድ
መታየት ስላለበት የጠቅላላ የምርት መጠን
1.2.1. ከ 2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም ላይ 15 በመቶ እድገት በማሳየት መታቀድ ሲገባ ያንኑ መልሶ
ታቅዷል፤
1.2.2. ከፋብሪካው ያለፉት 3 ዓመታት አማካይ ክንውን ጋር ሲነፃፀር የ 2014 በጀት ዓመት ጠቅላላ የምርት
ዕቅድ በ 12.65 በመቶ አንሷል፣
1.2.3. በተጨማሪም የ 2014 የምርት ዕቅድ እድገት ከስትራቴጂክ ግቡ ላይ ከተቀመጠው 20,082,000
ሊትር ጋር ሲነፃፀር የ 2014 ጠቅላላ የምርት ዕቅድ 15,968,987 ሊትር (በ 20.48 በመቶ አንሷል)፡፡
ስለዚህ ከላይ በሠንጠረዡ የቀረበውን መረጃ መሠረት በማድረግ የፋብሪካው የ 2014 በጀት ዓመት የጠቅላላ
ምርት ዕቅድ እንደገና ታይቶ እንዲታቀድ፣
1.3. ፋብሪካው ከ 2012 ጀምሮ እስከ 2013 በጀት ዓመት ሲመረቱ ከነበሩት ምርቶች መካከል አንዱ ለኮቪዲ-19
ወረርሽን ንጽሕ መጠበቂያ የሚያገለግል የሳኒታይዘር ምርት ነው፡፡ በ 2014 በጀት ዓመት የምርት ዕቅድ ውስጥ
ያልተካተተበት ማብራሪያ ካለ፡፡ ከፋብሪካው ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመሆኑ ቢታቀድ፣
1.4. የማምረቻ ወጪን አስመልክቶ የ 2014 በጀት ዓመት ወጪ ከ 2013 በጀት ዓመት ክንውን ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ
የማምረቻ ወጪ የታቀደ በመሆኑ ትርፍ ከታክስ በፊት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አለው፡፡ ስለዚህ ፋብሪካው ወጪ
ቁጠባ ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት፣

5
1.5. ከኤጀንሲው በተላከው የዕቅድ ዝግጅት ማዕቀፍ መሠረት የ 2 ዐ 14 በጀት ዓመት ከምርት ሽያጭ የሚገኝ ገቢ
ከ 2 ዐ 13 በጀት ዓመት አፈፃፀም ቢያንስ በ 15 በመቶ እድገት እንዲኖረው ይጠበቃል፡፡ ነገር ግን የፋብሪካው
የ 2014 በጀት ዓመት ከጠቅላላ ምርት ሽያጭ የሚጠበቅ ገቢ
1.5.1. ከ 2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም ብር 748.50 ሚሊዮን ላይ 15 በመቶ እድገት በማሳየት ብር
860.77 ሚሊዮን መታቀድ ሲገባ ብር 750.00 ሚሊዮን (በ 12.87 በመቶ ወይንም የብር
110.77 ሚሊዮን በማሳነስ) ታቅዷል፣
1.5.2. ከፋብሪካው የባለፉት 3 ዓመታት አማካይ ክንውን ጋር ሲነፃፀር የድርጅቱ የ 2014 ከምርት ሽያጭ
የሚጠበቅ ጠቅላላ ገቢው በ 10.41 በመቶ አንሷል፣
1.5.3. እንዲሁም ከስትራቴጂክ ግቡ ላይ ከተቀመጠው ጋር ሲነፃፀር የ 2014 በጀት ዓመት የሚጠበቅ ጠቅላላ
የሽያጭ ገቢ በ 17.44 በመቶ ያነሰ ነው፡፡
ስለሆነም የድርጅቱ የ 2014 የምርት ሽያጭ የሚጠበቅ ጠቅላላ የገቢ ዕቅድ ከላይ የቀረበውን ማብራሪያ መነሻ
በማድረግ እንደገና እንዲታይ፣
1.6. ከድርጅቱ ከውጭ ምርት የሚጠበቅ የውጭ ሀገር ምንዛሪ (የኤክስፖርት ሽያጭ ገቢ) ከላይ በተራቁጥር 1.4

ላይ በተገለፀው መሠረት የ 2 ዐ 14 በጀት ዓመት ምርቶችን ወደ ውጭ ኤክስፖርት በማድረግ የሚጠበቅ

የውጭ ሀገር ምንዛሪ ገቢ ከ 2 ዐ 13 በጀት ዓመት አፈፃፀም ቢያንስ በ 15% እድገት እንዲኖረው ይጠበቃል፡፡
በዚሁ መሠረት

1.6.1. ከ 2013 በጀት ዓመት የኤክስፖርት አፈፃፀም 534 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ላይ 15 በመቶ እድገት
በማሳየት 614.10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር መታቀድ ሲገባ 440 ሺህ የአሜሪካን ዶላር (በ 17.60
በመቶ ወይንም የ 94 ሺህ የአሜሪካን ዶላር) በማሳነስ ታቅዷል፣
1.6.2. ከፋብሪካው የባለፉት 3 ዓመታት አማካይ ክንውን ጋር ሲነፃፀር የድርጅቱ የ 2014 ከተለያዩ ምርቶች
ኤክስፖርት በማድረግ የሚጠበቅ የውጭ ሀገር ምንዛሪ ገቢ በ 12.43 በመቶ አንሷል፣
ስለሆነም የድርጅቱ በ 2014 የተለያዩ ምርቶች ወደ ውጭ ኤክስፖርት በማድረግ የሚጠበቅ የውጭ ሀገር
ምንዛሪ ገቢ ዕቅድ እንደገና ቢታይ፣
1.7. የፋብሪካው የ 2014 ትርፍ ከታክስ በፊት ዕቅድ ከ 2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም ላይ ቢያንስ በ 20 በመቶ
ዕድገት በማሳየት
1.7.1. የ 2014 በጀት ዓመት ትርፍ ከታክስ በፊት ብር 290.45 ሚሊዮን መታቀድ ሲገባ ብር 210 ሚሊዮን
(በ 27.70 በመቶ ወይንም የብር 80.45 ሚሊዮን) በማሳነስ ታቅዷል፣
1.7.2. ከፋብሪካው የባለፉት 3 ዓመታት አማካይ የትርፍ ከታክስ በፊት ክንውን ጋር ሲነፃፀር የድርጅቱ
የ 2014 የትርፍ ከታክስ በፊት ዕቅድ በ 27.75 በመቶ አንሷል፣
1.7.3. እንዲሁም ከስትራቴጂክ ግቡ ላይ ከተቀመጠው ጋር ሲነፃፀር በ 2014 በጀት ዓመት የሚጠበቅ ትርፍ
ከታክስ በፊት በ 20.33 በመቶ ያነሰ ነው፡፡

6
ስለሆነም ፋብሪካው በ 2014 ትርፍ ከታክስ በፊት ዕቅድ ከኤጀንሲው ከተላከው የዕቅድ ማዕቀፍ መሠረት
ተስተካክሎ ቢታቀድ፣
1.8. የ 2014 ኘላን ሪቪው ላይ እንደተገለፀው ለ 2014 ካፒታል በጀት የሚያስፈልገው ብር 257.5 ሚሊዮን
እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
1.8.1. ፋብሪካው ለ 2013 በጀት ዓመት ይዞ ከነበረው ብር 159 ሚሊዮን ውስጥ ሥራ ላይ የዋለው ብር 47
ሚሊዮን (29 በመቶ) ብቻ ከመሆኑ አንፃር ለ 2014 በጀት ዓመት የተያዘው የካፒታል በጀት ጥያቄ
እንደገና ታይቶ ቢታቀድ፣
1.8.2. በሌላ በኩል የካፒታል በጀት አጠቃቀም ከባለፉት 3 ዓመታት አማካይ ክንውን ጋር ሲነፃፀር የእድገቱ
ልዩነት በጣም ትልቅ ነው፣ ከስትራቴጂክ ዕቅዱ ጋር ሲነፃፀር ደግሞ በ 9.48 በመቶ ያነሰ በመሆኑ
እንደገና ቢታይ፡፡
1.8.3. እንዲሁም በኘላን ሪቪው ላይ የካፒታል በጀቱ Fund availability ለ Retained earnings 49.76
million birr, ለ Legal reserve 50.66 million birr and ለ Dividend Outstanding 60 million
birr ተብሎ የተገለፀው እነዚህን ለካፒታል በጀት ምንጭ አድርጎ መጠቀም ስለማይቻል እንደገና
ታይቶ ቢታቀድ፣
1.9. በፋብሪካው የ 2014 ኘላን ሪቪው ገጽ 1 ላይ እንደተገለፀው የ 2014 በጀት ዓመት የሰው ኃይል ምርታማነት
ዕቅድ 8.08 በሬሾ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ይህም ከ 2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም 8.41 ጋር ሲነፃፀር በ 4 መቶ ያነሰ
ነው፡፡ በአንፃሩ ከሠራተኛ ምርታማነት ጋር ቀጥተኛ ግንኙት ያለው የሽያጭ ዕቅድ ከ 2013 በጀት ዓመት
አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር 100% ነው፡፡ የሠራተኛ ምርታማነት ዕቅድ ከ 2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር
ያነሰ በመሆኑ እንደገና ቢታይ፣
1.10. የመንግሥት ትርፍ ድርሻ ክፍያን አስመልክቶ ፋብሪካው ጠቅላላ ያለበት የትርፍ ድርሻ መጠን ብር 427.23
ሚሊዮን ውስጥ በ 2013 በጀት ዓመት ብር 211.103 ሚሊዮን ከጥቅምት እስከ ግንቦት ወር/2013 ዓ/ም ባሉት
ወራት ተከፋፍሎ እንዲከፍል መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ መርሃ-ግብር ተዘጋጅቶ መላኩ
ይታወሳል፡፡ በመርሃ-ግብሩ መሠረት እስከ ታህሣሥ ወር 2013 ዓ.ም ሲከፈል ቆይቶ ከጥር ወር /2013 ዓ/ም
በኃላ በመርሃ -ግብሩ መሠረት እየተከፈለ አይደለም፡፡ በ 2014 በጀት ዓመት ለመክፈል የታቀደው በጣም
ዝቅተኛ (ብር 60 ሚሊዮን ብቻ) በመሆኑ በመጀመሪያ ደረጃ እስካአሁን የተጠራቀመው የመንግሥት ትርፍ
ድርሻ ክፍያ እንዴት ከፍሎ ለማጠናቀቅ እንደታሰበ በቂ ማብራሪያ ቢሰጥ፡፡ እንዲሁም የ 2014 በጀት ዓመት
የመንግስት ትርፍ ድርሻ ክፍያ በኤጀንሲው የሚወሰን ቢሆንም የፋብሪካው ዕቅድ እንደገና ቢታይ፡፡
1.11. ገጽ 121 በፊደል ተራቁጥር “ለ” ላይ ድርጅቱ በተለያዩ ዘርፎች የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች
በዕውቀት የዳበሩ እንዲሆኑ በህብረት ስምምነት በተቀመጠው መስፈርት መሠረት የትምህርት
ወጪአቸውን በመሸፈን በትርፍ ጊዜያቸው መደበኛ ትምህርት ለማስተማር በዕቅድ ተይዟል ተብሎ
ተገልጿል፡፡ ነገር ግን ለስንት ሠራተኞች? ምን ዓይነት ትምህርት ደረጃ (ከዲፕሎማ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም
ከመጀመሪያ ዲግሪ ሁለተኛ ዲግሪ እና የመሳሰሉት) እና በፆታ አልተገለፀም፡፡ ስለዚህ የትምህርት ደረጃ እና
የፆታ ሁኔታ ተገልፆ በትክክል መታቀድ አለበት፡፡

7
1.12. የፋብሪካው የ 2014 በጀት ዓመት የሪፎርም ዕቅድ በተለዩ በአራት የሪፎርም አጀንዳዎች መሠረት ችግር ፈቺ
በሆነ መልኩ ስለመታቀዱ ማረጋገጥ፣
1.13. በገጽ 71 የ 2014 ካፒታል በጀት ዝርዝር ዕቅድ ላይ ለሰበታ ቅርንጫፍ ፋብሪካ ለ waste treatment plant 200
tonne per day ብር 70 ሚሊዮን ታቅዷል፡፡ የ waste treatment plant ግንባታን አስመልክቶ በ 2013 በጀት ዓመት ሞላሰስ
ስለማናገኝ በማለት ቀርቶ የነበረውን እንዴት በ 2014 በጀት ዓመት ሊታቀድ ቻለ እንደገና ዕቅዱ ቢታይ፡፡ እንዲሁም በተመሳሳይ ገጽ
በሠንጠረዡ ፊደል ተራቁጥር 4 ላይ የግንባታ ሥራዎች (የ G+2 ህንፃ ግንባታ) ወጪው ብር 50 ሚሊዮን ለምን ታቃደ?
በአጠቃላይ የ 2014 በጀት የካፒታል በጀት ዕቅድ ከላይ በተገለፀው መሠረት እንደገና ቢታይ፣
1.14. በ 2014 በጀት ዓመት የፋብሪካው የፕሮጀክት ዕቅድ ላይ የተሰጡ አስተያየት
የኦፕሬሽን ሥራዎች ዕቅድ እና የፕሮጀክቶች እቅድ (መርሃ-ግብር) መሠረታዊ የሆኑ ልዩነቶች አሏቸው፡፡
 የኦፕሬሽን እቅዶች መነሻ ስትራቴጂክ ዕቅድ ሲሆን የፕሮጀክት መርሃ- ግብር (ዕቅድ) መነሻ ደግሞ የፕሮጀክቶቹ
አዋጭነት ጥናት ሰነዶች ናቸው፡፡ የአዋጭነት ጥናት ያልተከናወነለት ፕሮጀክት በፕሮጀክትነት ሊመዘገብ
እንደማይገባው የፌዴራል መንግስት ፕሮጀክቶች አስተዳደርና አመራር አዋጅ ቁጥር 1210/2012 በግልፅ
ይደነግጋል፡፡ የአዋጭነት ጥናት ሰነዶችም በሚዘጋጁበት ጊዜ የአዋጭነት ጥናት ሥራዎቹን ለተቆጣጣሪው አካል
በማቅረብ ክትትልና ግምገማ እየተደረገበትና ውሳኔ እየተሰጠበት ሊታለፍ እንደሚገባውም ጭምር ይኸው
አዋጅ በግልፅ ያስቀምጣል፡፡ የአዋጭነት ጥናት የተከናወነላቸው ፕሮጀክቶች እንኳን ቢኖሩ ጥናቶቹ ለኤጀንሲው
ቀርበው ተገምግመው እንዲፀድቁና ወደ ትግበራ እንዲሸጋገሩ ፈቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡
 የኦፕሬሽን ዕቅድ በመሰረቱ የሚዘጋጀው ለአንድ ዓመት ሲሆን የፕሮጀክቶች መርሃ ግብር (ዕቅድ) ግን
የሚዘጋጀው ከፕሮጀክቱ መነሻ እስከ ማጠናቀቂያ ድረስ ያለውን ጊዜና የሥራ ሂደት በሚያሳይ መልኩ መሆን
ይኖርበታል፡፡ ይህም የሚሆንበት ዋነኛ ምክንያት ብዙ ፕሮጀክቶች የሚተገበሩት በሦስት አካላት (የፕሮጀክቱ
ባለቤት፣ ሥራ ተቋራጩና የፕሮጀክቱ አማካሪ) ተግባቦትና ስምምነት በመሆኑና እነዚህ አካላት ፕሮጀክቶቹን
ለመተግበር የሚገቧቸው ስምምነቶች በዓመታት የተከፋፈሉ ሳይሆን በቁርጥ፣ የጊዜ ገደብ እና ዋጋ የሚቀመጡ
በመሆናቸው ነው፡፡
 ለፕሮጀክቶች የሚያዘው በጀትም ቢሆን ለሙሉ ፕሮጀክቱ የሚሆን እንጂ እንደ ኦፕሬሽን ሥራ ማስኬጃ
በዓመታትና በወራት የተከፋፈለ መሆን የለበትም፡፡ በመንግስት በጀት አያያዝ ውስጥም የካፒታል በጀት እና
መደበኛ በጀት በመባል ተከፋፍሎ የሚቀመጥበት ዋነኛ ምክንያት ይኸው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
በመንግስት ልማት ድርጅቶች ሁኔታ የካፒታል በጀትን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የካፒታል ዕቃዎች
መተኪያ (አንድ ማሽን መግዣ ወይንም የማሽኖች አካል/መለዋወጫ መግዣ) እና ወጥ የሆኑ ፕሮጀክቶች
(አዲስ ፋብሪካና ፕሮሰስ) መተግበሪያ በጀቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
 የኦፕሬሽን ሥራ አፈፃፀም መለኪያዎች ሁልጊዜም ድርጅቶችና ተቆጣጣሪዎቻቸው ስምምነት ላይ
በሚደርሱባቸው ቁልፍ የአፈፃፀም መለኪያዎች (Key Performance Indicators [KPI]) የሚለኩ ሲሆን
የፕሮጀክቶች አፈፃፀም መለኪያዎች ግን ሁሌም አራት ማለትም ጥራት፣ ጊዜ፣ ወጪ እና የፕሮጀክቱ ስፋት
(Quality, Time, Cost and Scope) ናቸው፡፡

8
በመሆኑም ከላይ በተብራሩት የኤጀንሲው የፕሮጀክቶች አተገባበር መስፈርቶች መሠረት የብሔራዊ አልኮልና
አረቄ ፋብሪካ ለ 2014 በጀት ዓመት ያቀረቡት የጥናትም ሆነ የትግበራ ፕሮጀክት እስካአሁን የለም ማለት
ይቻላል
 ስለሆነም የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ያለበትን ከፍተኛ የሆነ የግብዓት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ አንድ
ራሱን የቻለ የቴክኒካል አልኮል ፋብሪካ ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር በመሆን ስኳር ኮርፖሬሽን እስካሁን ባልተከለበት
አንድ የስኳር ልማት ፕሮጀክት የቴክኒካል አልኮል ፋብሪካ እንዲተክልና የራሱንም ችግር እንዲቀርፍ የኢታኖል
ምርትንም ለሚመለከተው አካል በማቅረብ የተሻለ ተወዳዳሪ እንዲሆን ከኤጀንሲው የተሰጠው አካሄድ ላይ
የፕሮጀክት አዋጭነት ጥናትም ያልተጀመረ ሲሆን በፕሮጀክቱ ላይም እንዴት እንደሚከድ መርሃ-ግብር
አዘጋጅቶ አላቀረበም፡፡ በ 2014 ከብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የሚጠበቀው በፕሮጀክትነት ሊያዝ እና
መርሃ-ግብር ተዘጋጅቶ ሊቀርብ የሚገባው ፕሮጀክት ይህ ቢሆን በማለት አስተያየታችን እናቀርባለን፡፡

You might also like