You are on page 1of 19

የመደበኛ ትምህርት በሬዲዮ

የመምህሩ መምሪያ አጠቃቀም

በመደበኛ ትምህርት በሬዲዮ ኘሮግራም አጠቃቀም


ሥልጠና ላይ የቀረበ

ጥቅምት 2009 አ.አ

1.የትምህርት በሬዲዮ የመምህሩ መምሪያ ምንድነው;


1.1.እንደ መደበኛው የማስተማሪያ መጽሐፍ ሁሉ
የክፍል መምህሪን የሬዲዮ ትምህርቱን
አሰጣጥ ስኬታማ በሆነ መልኩ ለማከናወን
የሚረዳው አጋዝ መመሪያ(ማኑዋል) ነው፡፡
1.2. የክፍል መምህራንን እና የት/ት ሬዲዮ
አቅራቢውን የሚያግባባና የሚያገናኝ ድልድይ ነው፡፡
1.3.በክንዋኔ ጊሄያት የክፍል መምህራንና
ተማሪዎች አሳታፊ ተግባራትን እንዴት ማከናወን
እንዳለባቸው የሚጠቁም ነው፡፡
2.የትምህርት ሬዲዮ የመምህሩ መምሪያ ዓላማዎች፡-
2.1 የየዕለቱን የት/ት ሬዲዮ ሥርጭት የፕሮግራም
ቁጥር፡ ርዕስ፡ ዓላማና ይዘት የክፍል
መምህሩ በቅድሚያ እንዲያውቀው ያደርጋል፡፡
2.2 በሦስቱ የክንዋኔ ጊዜያት (ከሥርጭት በፊት፡
በሥርጭት ወቅትና ከሥርጭት በኃላ)
የክፍል መምህራንን የሳውቃል፡፡
2.3 የት/ት ሬዲዮ ፕሮግራሞች ተማሪ-አሳታፊ
ስለሆኑ መምህራን የክንዋኔውን ሁኔታ በቅድሚያ
ተረድተው ዝግጅት ያደርጉበታል፡፡
3.የትምህርት ሬዲዮ የመምህሩ መምሪያ ይዘት፡-
እያንዳንዱ የት/ት ሬዲዮ ፕሮግራም የራሱ መምሪያ
ወይም መግለጫ አለው፡፡ በዚህም መሠረት
ለእያንዳንዱ የሬዲዮ ትምህርት ፕሮግራም የተዘጋጀ
የሬዲዮ ት/ት መምሪያ በውስጡ ያካተታቸው፡-
3.1 የትምህርቱን ዓይነት፡የክፍል ደረጃውን፡
የፕሮግራም ቁጥር፡ የትምህርቱን ርዕስ ይይዛል፡፡
3.2 የትምህርቱን ርዕስና ይዘት በመማሪያና
ማስተማሪያ መጻህፍት ላይ በየትኞቹ ገጾች እንደሚገኙ
ይጠቁማል፡፡
3.3 የሬዲዮ ትምህርቱን ዝርዝር ዓላማዎች ይገልጻል፡፡
3.4 ዝርዝር የሬዲዮ ትምህርቱን ይዘቶች ይይዛል፡፡
3.5 የክንዋኔ ጊዜያትን (ከሥርጭት ወቅት፡ከሥርጭት
በኃላ) ይዘረዝራል፡፡
3.6 የሬዲዮ ትምህርቱ እንዴት እንደሚቀርብ
የማስማሪያ ዘዴዎችን ይጠቁማል፡፡
3.7 በፕሮግራሙ ውስጥ በድጋፍነት የሚቀርቡ
ትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ማለትም ስዕሎች፡
ቻርቶችን፡ ሠንጠሪዦችንና ሙዝሙሮችን ይይዛለረ፡፡
4. የትምህርት በሬዲዮ የመምህሩ መምሪያ
አወቃቀር፡-
4.1 የውጭ ሽፋን ገጽ(cover page}
- በገጽ ላይ ተገቢው መረጃ መልዕክት
የሚያስተላልፍ ሥዕልዊ መግለጫ ወይም
አርማ ይይዛል፡፡
- የመምህሩ መምሪያው ለየትኛው የክፍል
ደረጃና የትምህርት ዓይነት እንደሆነ
ይገልጻል፡፡
- የትምህርት ሬዲዮ ፕሮግራሙን አዘጋጅ
ስም (ክፍል) ይገልጻል፡፡
- አዘጋጁን መሥሪያ ቤትና ክፍል ይገልጻል፡
- መምሪያው የታተመበትን ጊዜና ቦታ
ይጠቁማል፡፡
- የሽፋኑ ገጽ ውበት ሳቢና ማራኪ
እንዲሆን ይደረጋል፡፡
4.2 ውስጣዊ ገጽ(Title page}
-ከሽፋኑ ቀጥሎ ያለው ገጽ ሲሆን በውጭ
ሽፋኑ ላይ ካሉት መረጃዎች በተጨማሪ የአርታኢው
ስም፡
አሳታሚ ድርጅት፡ኮፒራይት ባለቤትንት
መግለጫ ያስፈራሉ፡፡
4.3 ማውጫ (preface}
በመምሪያው ውስጥ የተከተቱትን የት/ት
ሬዲዮ ርዕሶች፡ ፕሮግራም ቁጥርና ገጾችን ይጠቁማል፡፡
4.4 መግቢያ (introduction} ጠቃሚ የሆኑ
መረጃዎች የሚጠቆሙበት ነው፡፡
- ስለ ሬዲዮና የሬዲዮ ትምህርት አጠቃላይ
መግለጫ ይሰጥበታል፡፡ ይህም ሲባል
- ት/ት በቴክኖሎጅ መሣሪያዎች መደገፍ
ያለውን ጠቀሜታ ይገልጻል፡፡
- የሥርዓተ ትምህርቱን የሬዲዮ ት/ቱን
ግንኙነት ያሳያል፡፡
- መምሪያው ለማንና ለምን ዓላማ
እንደተዘጋጀ ይገለጽበታል፡፡
- አቀራረቡንና አጠቃቀሙን ያሳያል፡፡
- የመምህሩ መምሪያ ምንነትና አስፈላጊነት
ይገለጽበታል፡፡
- የመምህሩ መምሪያ ለማንና፡ለምን እንደተዘጋጀ
ይገልጻል፡፡
- የመምህሩ መምሪያ እንዴት እንደተዘጋጀ ይገልጻል፡፡
- የት/ት ሬዲዮ ፕሮግራሞቹ ለተማሪዎች በአግባቡ
ደርሰው እንዲጠቀሙባቸው
ያስችላል፡
-የት/ት ሬዲዮ ፕሮግራሞች ከትምህርቱ ሲለበስ፡
መማሪያና ማስተማሪያ መጻህፍት ጋር ያላቸውን
ግንኙነት ይገልፃል፡፡
4.5 የትምህርት ሬዲዮ ርዕስ (Topic of the lesson}
- ለትምህርት ሬዲዮ ፕሮግራሞች ዝግጅት
የሚመረጡት ርዕሶች የሚመረጡት ከመማሪያና
ማስተማሪያ መጻህፍት ውስጥ ነው፡፡
-ርዕሶቹ የሚመረጡት በክፍል መምህራን፡ በሥረዓተ
ትምህርት ባለሙያዎችና በፕሮግራሙ
አዘጋጆች ጣምራ ግንኙነት ነው፡
-ለት/ት ሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅት የሚረጡ ርዕሶች
አመራረጣቸው የተለያዩ መስፈርቶች ነው፡፡
- በመማሪየና ማስተማሪያ መጻህፍት ውስጥ በስፋት
ተብራርተው ያልተቀመጡ ርዕሶች (የበለጠ መረጃ
እንዲሰጥባችው)
- የተለያዩ የድምፅ ግብዓቶች የሚየስፈልቸው ርዕሶች
(የእንሰሳት፡ የተፈጥሮ አካባቢዎችና ሌሎችም)
- በተለያዩ የሬዲዮ ፕሮግራም አዘገጃጀት ፎርማቶች
ሊሰሩ የሚችሉ ርዕሶች (በድራማ፡ በቃለመጠይቅ)
- ለሳምንቱ ከተመደቡት የትምህርት ክፍለ ጊዜያት
መካከል በአንዱ ላይ የሚደርሰው ርዕስ ይመርጣል፡፡
- የት/ት ሬዲዮ ርዕሶች አስያየም ከዋናዎቹ ርዕሶቹ
ይዘት ሳወጣ በዓረፋተ ነገር፡ በጥያቄ ወይም በአንድ
ቃል
ሊሰየም ይችላል፡፡
4.6 የትምህርት ሬዲዮ ዓላማዎች (objectives of
the lesson}
በእያንዳንዱ የትምህርት ሬዲዮ ፕሮግራም
የሚቀረጹ ዓላማዎች የሚከተሉትን ነጥቦች ያየዙ
መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ምሳሌ - ከዚህ ክፍለ ጊዜ በኃላ የስምንተኛ ክፍል
ተማሪዎች
የዴሞክራሲያዊ ምርጫ አፈጻጸምና ሂደቶችን
በክፍል ውስጥ
በተግባር ያሳያሉ፡፡
-ከዚህ የሬዲዮ ት/ት በኃላ የአንደኛ ክፍል
ተማሪዎች በቃላት
ውስጥ የተገጣጠሙ ፊደላትን በመነጣጠል ወይም
በመለየት
ለየብቻ ያነባሉ፡፡
ዓላማዎች ሲቀረጹ ማስሪያ ቃላቱን የትምህርት
ክሂሎች (learning skills knowledge}
ዝንባሌንና (Attitude} ልምድ(practice}
የሚያሳዩ መሆን አለባቸው፡፡(ዕዝል KAP}
ዓላማዎች ከሬዲዮ ትምህርቱ ርዕሶችና
ከትምህርቱ ይዘቶች ጋር የተያያዙ መሆን አለባቸው፡፡
ዓላማዎች ለትምህርቱ አቀራራብ (format}
ዘዴ(methodology} እና ለግምገማ(evaluation}
በሚያመች መልኩ መቀረጽ ይኖርባቸዋል፡፡
4.7 የትምህርት ሬዲዮ ይዘቶች ( ፍሬሐሳቦች )
(concepts of the lesson}
- ይዘቶቹ የሚመነጩት ከመማሪያና ማሰተማሪያ
መጻህፋቱና ለማጠናከሪያ ወይም ማገናዘቢያ
ተጨማሪ መረጃዎች ውስጥ ይሆናል፡፡
- በተማሪዎች የማድመጥና የመቀበል ችሎታ
አንፃር በየክፍል ደረጃውና በየትምህርት ዓይነቶቹ
ይዘቶች ግልጽና ቀላል በሆኑ ዓረፍተ ነግሮች
ይቀመጣሉ፡፡
- በይዘቱ ውስጥ የትምህርቱ ዋና ዋና ፍሬ
ሐሳቦች በአጭሩ ነጥብ በነጥብ ይቀመጣሉ፡፡
- የይዘቶች አደራደር ከቀላል ወደ ከባድ መሆን
ይኖርበታል፡፡
4.8 የክንዋኔ ጊዜያት፡- እያንዳንዱ የትምህርት
ሬዲዮ ፕሮግራም በ 3 ተግባራዊ ክንዋኔዎች ተከፍሎ
ይቀርባል፡፡
4.8.1 ከሥርጭት በፊት፡- (before
transmission}ነው፡፡
 ይህ ጊዜ የመምህሩ መምሪያ
በመምህራን እጅ ከገበባት ጊዜ አንስቶ
የዕለቱ ት/ት ሬዲዮ ፕሮግራም
ሥርጭት
አየር ላይ ለማዋል እስከሚጀምርበት
ያለው ነው፡
 -የመምህሩ መምሪያ በመምህራን እጅ
ከደረሰበት አንስቶ እስከ ዕለቱ ክፍለ ጊዜ
መግቢያ ያለው ረጅም ጊዜ (Long
before transmission} ረጅሙ ከሥርዓት
በፊት ጊዜ ነው፡፡
 -መምህሩ ክፍል ገብተው የዕለቱን
ትምህርት አስተዋውቀው ለዕለቱ ሬዲዮ
ትምህርት ተማሪዎችን የሚያዘጋጁበትና
 ሥርጭት እስከሚጀማርበት ያለው
አጭር ጊዜ(short before transmission}
እጭሩ ከሥርጭት በፊት ያለው ጊዜ
ይሆናል፡፡
 ከሥርጭት በፊት አያሌ ተግባራት
በመምህሩ ይከናወናሉ፡፡ከእነዚህም ዋና
ዋናዎቹ፡-
 በመምህሩ መምሪያ ላይ በታዘዘዉ
መሰረት ለሬዲዮ ትምህርቱ ድጋፍ
የሚዉል መርጃ መሰርያዎችን -ሥዕሎች
ቁሳቁሶች ይዘጋጃሉ
 የዕለቱ የሬድዮ ትምህረት በክፍል
ካስተማሩት የቀጠለ ከሆነ ከስርጭቱ
በፊት ትምህረቱን አጠር አድርገዉ
ይከልሳሉ ፡፡
 በክፍሉና በአካባቢው የሬዲዮ
ትምህርቱን ሊያደናቀፋ የሚችሉ አዋኪ
ሁኔታዎች መኖራቸውንና ካሉም
ለማስወገድ ጥረት ማድረግ
 ትምህርት መቀበያ መሣሪያውን
(ሬዲዮውን) ለተማሪዎች ፊት ለፊት
በሚታይ ቦታ በክፍሉ መካከል አካባቢ
ማስቀመጥ ፡፡
 የስርጭት ጣቢያ መስመር
ያስተካክላሉ፡፡
 በስርጭት ወቅት ተማሪዎች
ፕሮግራሙን በጸጥታ እንዲያዳምጡ፣መፃፍ
፣ ማናገርና የመሳሰሉትን አዋኪ ሁኔታዎች
እንዲፈጥሩ አስቀድሞ በመናገር በማሳሰብ
ትምህርት ሬዲዮ ፕሮግራም ስርጭት 1
ጊዜ ካለፈ ተመልሶ እንዳይደመጥ
በመንገር፡፡
 በትምህርት ሬድዮ ክፍለ ጊዜ
በማድመጫዉ ክፍል ዉጭ በር ላይ
‹‹ተማሪዎች የትምህር ሬድዮ መከታተል
ላይ መሆናቸዉን የሚገልጽ ማስታወቂያ
በመጻፍ እንዲታይ አድርገዉ ይስቀሉት -
አዋኪ ሁኔታዎችን ለማስወገድ
 የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን
እንዳስፈላጊነታቸዉ በክፍል ዉስጥ
ያስቀምጡ፣ መዝሙርም ካለ በጉልህ
ተጽፎ ይሰቀላል፡፡
 የዕለቱን ትምህርት ሬድዮ ፕሮግራም
ርዕስና ቁጥር በሰሌዳዉ ላይ ፅፈዉ
ያስተዋዉቋቸዉ፡፡
 የዕለቱ ትምህርት ሬድዮ ዙሪያ
የማስተዋወቂያና ለአዲሱ ትምህርት
መግቢያ እንዲሆን በመምህሩ መምሪያ
ላይ በተገለጸዉ መሠረት ያዘጋጇቸዋል፡፡
4.8.2. በስርጭት ወቅት (during
transmission)
ይህ ጊዜ የእለቱ ት/ት ሬድዮ ፕሮግራም
መግቢያ (መለያ) ሙዚቃ መሰማት ከጀመረበት አንስቶ
የመዝጊያ
መለያ ሙዚቃ ተሰምቶ እስካለቀበት ድረስ
ያለዉ ነዉ፡፡ ይህም ትምህርቱ በሬድዮ የሚሰራጭበት
የ 15 ደቂቃ
ጊዜያት ማለት ነዉ፡፡ በዚህ ጊዜ ዉስጥ
የክፍሉ መምህሩ አቢይ ተግባራት
 ራሳቸዉን እንደ ሞዴል አድማጭ (model
listener) አድርገዉ በመዉሰድ የሬድዮ
ትምህርቱን በጥሞና ያዳምጣሉ፡፡
 የሬድዮ መምህሩ ተማሪዎችን አሳታፊ
ትያቄ በሚጠይቅበት ጊዜ በሚሰጠዉ
አጭር ጊዜ መልሶቹን ይቀበላሌ፡፡
 በስርጭት ወቅት የሬድዮ ፕሮግራሙን
የሚያደናቅፍ ሁኔታ ቢገጥም በከፍተኛ
ጥንቃቄ ሁኔታዉን ለማሻሻል ጥረት
ያደርጋሉ፡፡
 የትምህርቱን ድምጠት በማያዉክ ሁኔታ
የተማሪዎቹን ስነ- ስርዓትና ፀጥታ በጥንቃቄ
ይቆጣጠራሉ፡፡
4.8.3. ከስርጭት በኃላ (After transmission)
- ከስርጭት በኃላ የተባለው ጊዜ የሬዲዮ
ትምህርቱ ሥርጭት የመዝጊያ ሙዚቃ ካበቃብ ጀምሮ
የለውን ጊዜ ነው፡፡
ይህ ጊዜ ተማሪዎቹ ሬዲዮ ያዳመጡበት ክፍለ
ጊዜ ማለቂያ ድረስ ያለው ብቻ ተደርጎ መውሰድ
የለበትም፡፡ክፍለ
ጊዜው ላበቃም በኃላ የተማሪዎቹም ሆነ
የመምህራን ከሬዲዮ ትምህርቱ ጋር የተያያዙ
ሥራዎች (እንቅስቃሴዎች)
ሊከናውኑ ይችላል፡፡ ይህም በመሆኑ ከሥርጭተግ
በኃላ ያለው ጊዜ ርዝማኔ የሚለካው በመምህሩ
መምሪያ ላይ
መምህራንና ተማሪዎቻቸው ከሥርጭትበጋላ
እንዲየለናውኑ የተጠቀሱት ተግባራት ተጠናቀው
እስካበቁበት ጊዜ ድረስ
ያለው ይሆናል ማለት ነው፡፡ይህም እንደ
ከሥርጭት በፊት ባለው ጊዜ አመዳብ ከሥርጭት
በኃላም በሁለት ንዑሳን
ጊዜያት ይከፈላል፡፡
ሥርጭት ካበቃበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ክፍለ
ጊዜው ማጠናቀቂያ ያለው አጭር ጊዜ የክለሳ
ሥራዎች የሚሰሩበት ጊዜ
(lmmediately after broadcast)
ስርጭቱ ካበቃበት ጊዜ ጀምሮ በመምህሩ
መምሪያው ላይ የተጠቀሱት ከክፍለ ጊዜው ውጭ
የሚከናወኑ ተግባራት
ተከናውነው እስከተጠናቀቁበት ጊዜ ድረስ ያለው
ረጅም ጊዜ ሁለተኛው ነው፡፡(Long after broadcast)
በዚህ ከስርጭት በኃላ ባላ ጊዜ የክፍል መምህሩ ዋና
ዋና ተግባራት የሚከተሉት ይሆናሉ
 በእለቱ የትምህርት ሬድዮ ክፍለጊዜ የተነሱ
ሃሳቦችን ይከልሳሉ ፡፡
 ከፍሬ ሃሳቦቹ የተዉጣጡ አጫጭር ማስታወሻ
ለተማርዎች ያጽፋሉ ፡፡
 በስርጭት ወቅት ተነስተዉ ዉጭ ሌሎች
የክለሳ ጥያቄዎችን ለተማሪዎቻቸዉ ያቀርባሉ፡፡
 ከስርጭት በኃላ ለተማሪዎቻቸዉ እንዲያሳዩ፣
እንዲያስጎበኙ ፣ እንዲያሰሩ ወይም እንዲያስጠኑ
በመምህሩ መምሪያ ዉስጥ የተገለፁ ካሉ በዚህ
መሰረት ያከናዉናሉ
 የዕለቱን የትምህረት ሬዲዮ ፕሮገራም
በመገምገም ዉጤቱን በተዘጋጀዉ ቅጽ በማስፈሩ
በዝግጅት ክፍሉ እንዲደርሱ ያደርጋል
5 የትምህርቱ አቀራረብ (peresentation format)
በዚህ ስር የትምህረት ሪዲዮ ዝግጅት የተጠቀመ
ባቸዉ የትምህረት አቀራረብና ዘዴዎች ለክፍል
መምህሩ የሚገለጽበት ነዉ፡፡እያንድአንዱ የት/ት
ሪዲዮ ፐሮግራም ተመሳሳይ በሆነ የአቀራረብ
ዘደዎች ላይ የተመሰረተ ላይሆን ይችላል ፡፡እንደ
ትምህረቱ ርዕስ እና ለሬዮ ፐሮግራም ዝግጅት
አመቺነት የተለያዩ ያቀራረብ ስልቶችና ዘዴዎች
ተግባራዊ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡በዚህም መሠረት
በት/ት የረዮ ፐሮግራም አዘገጃጀት መረህ
መሰረት የተለያዩ ፎርማቶች ጥቅም ላይ
ይዉላሉ፡፡ በድራማ ፣በጭዉውት ፣በትረካ ፣በቃለ-
መጠይቅ ፣ በጥያቄና መልስ ፣በዉይይትና
በመሳሰሉት ፕሮግራሞቸ ሊዘጋጅ ይችላል፡፡
6 የትምህረት መርጃ መሳርያ ፡- በዚህ ስር የት/ት
ሬዲዮ ፐሮግራሙ ለትምህረቱ ስኬት በመርጃነት
ለሚያገለግሉና መምህሩ በቀድሞ
እንዲያዘጋጃቸው፣እንዲያሰባስባቸዉ የሚያስፈልጉ
ማቴሪያሎች የሚጠቀሙበት ነዉ፡፡
7 ማጠቃለያ
ይህ በተማሪዎችና በመምህራን በጣም
ተወዳጅ እየሆነ የመጣዉ አሳታፊ የትምህረት
ሬዲዮ ፐሮግራም (inter radio instruction)
ዉጤታማ እንዲሆን የክፍል መምህሩ
መምሪያዉን ከመጠቀምንና ከመተግበር አኳያ
ብረቱ ጥናት ይጠበቅበታል፡፡ ለመምህሩ መምሪይ
የታገዘትምህረት የሬዲዮ ፕሮግራም ሰርጭት
ስኬታማ መሆን አይችልም ፡፡ ይልቁኑ የሰዉ
ኀይል ፣የገንዘብና የምቴርያል ብክነት ማስከተል
ስለሚሆን በብረቱ ሊታሰብበት እንደሚገባ ነዉ፡፡
የጋራ ስራና የጋራ ጥምረት ወሳኝነት
ስላለዉምለመልካም ስኬት ለመብቃት ከዝግጅት
ክፍሉ ጋር የቀረበ ግንኙነት መፍጠር ጠቃሚነት
አለዉ፡፡


፤፤

You might also like