You are on page 1of 2

የመምህሩ መምሪያ አደራደር

1. የትምህርት አይነት የአማርኛ ቋንቋ


2. ክፍል፡- 7 ኛ
3. የዝግጅት ቁጥር ፡-12
4. የትምህርት ርዕስ፡- ተራኪ ጽሑፍ
5. ትምህርቱ የሚገኝበት
5.1. በመማሪያ መፅሐፍ፡- ገፅ- 65
5.2. በመምህሩ መምሪየ ፡- ገፅ - 65
6. የትምህርቱ ዓላማ፡- ከዚህ የትምሀርት በሬዲዮ በኋላ ተማሪዎች!
6.1. የተራኪ ጽሑፍ ምንነትን ይገልጻሉ
6.2. የተራኪ ጽሑፍ አቀራረብ መንገዶችን ይለያሉ
7. የትምህርቱ ፍሬ ሐሳቦች ወይም ይዘት
7.1. የተራኪ ጽሑፍ ምንነት
7.2. የተራኪ ጽሑፍ ማቅረቢያ መንገዶች
8. ክንዋኔ
8.1. ከስርጭት በፊት
8.1.1. ለተማሪዎች ስለ እለቱ የትምህርት ርዕስ ማስተዋወቅ
8.1.2. የቅድመ እውቀታቸውን በመጠቀም የሚያውቁትን እንዲወስዱ ማድረግ
8.2. በስርጭት ወቅት
8.2.1. የትምህርት በሬዲዮ ክፍለ ጊዜን በንቃት እንዲከታተሉ ማድረግ
8.2.2. ተማሪዎች በትምህርት በሬዲዮ ክፍለ ጊዜ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ
እንዲሰጡ ማድረግ
8.2.3. ማስታወሻ እንዳይነት መከታተል
8.3. ከስርጭት በኋላ
8.3.1. የክለሳ ጥያቄዎችን መጠቀም
8.3.2. ያልገባቸውን ነጥቦች ማብራራት

9. በትምህርት ዝግጅት ውስጥ የተካተቱ የክለሳ ጥያቄዎች


1. ትዝታ በሶስት አንቀጽ የዶሮ ወጥ አሰራር ቅደም ተከተልን ብታቀርብ ከየትኛው የተራኪ ጽሑፍ
ዓነት ይመደባል?

መልስ፡- በጣም ጥሩ ተማሪዎች! ኢ-ልቦለዳዊ ተራኪ ጽሑፍ ይመደባል በማለት ከመለሳችሁ


ትክክል ናችሁ፡፡

2. ተራኪ ጽሑፍ በምንና በምን በሆነ መንገድ ሊቀርብ ይችላል?


መልስ፡- ልብ-ወለዳዊ እና ኢ-ልብ-ወለዳዊ በማለት ከመለሳችሁ
3. የ 7 ኛ ክፍል ተማሪ ባሮክ በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎችን የአኗኗር ሁኔታ ከራሱ የህይወት ልምድና
የምናብ ዕውቀቱን ተጠቅሞ ፈጠራ በመጠቀም በሁለት አንቀጽ ጽፎ ቢያቀርቡላችሁ የባሮክን
ጽሑፍ ከየትኛው የተራኪ ጽሑፍ አቀራረብ ትመደባላችሁ? ለምን?
መልስ፡- ባሮክ ያካባቢው ሰዎች አኗኗር የምናብ አቅሙን ተጠቅሞ ፈጠራ አክሎበት የቀረበው
በመሆኑ በልብ-ወለድ ተራኪ ጽሑፍ አቀራረብ እንመድበዋለን ካላችሁ ትክክል ናችሁ፡፡
10. የትምህርቱ አቀራረብ
- ገለፃ
- አሳታፊ ጥያቄና መልስ
- ውይይት

You might also like