You are on page 1of 40

ኢኽላስ (ልበ-ጽዱነት)

የሰው ልጅ በተለያዩ አላማዎች እየተገፋ ለሥራ ይነሳሳል፡፡ ግብሩንም እንከን የለሽ ለማድረግ ይጥራል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ
የሚገጥሙትን እክሎች ተ k ቁሞ ዓላማውን ለማሳካት መስዋእትነት ይከፍላል፡፡ ለሥራ ከሚያነሳሱት እና ከሚያጓጉት ነገሮች ውስጥ
ከፊሉ በቅርብ ለሚያገኛቸው ጥቅሞች አልያም በልቦናው ያለማቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
የሰው ልጅ ለሥራ አነሳሽ የሆኑ የሚታወቁ ስሜቶች አሉት፡፡ አንድ ሰው በሚያደርገው እንቅስቃሴ ላይ ተመስርተን ራስ ወዳድ፣
ለሰላም የቆመ፣ ገንዘብ አፍቃሪ፣ ጉራ የሚወድ አልያም ዝና ፈላጊ መሆኑን መገመት እንችላለን፡፡ ብዙ ጊዜ በሰው ልጆች መካከል
በሚደመጡ ውይይቶች እንደሚታየው፣ አድናቆት ወይም ጥላቻ፣ ትህትና አልያም ኩራት፣ የጨዋታ ምንጭ ሁኖ እናገኘዋለን፡፡
ኢስላም የሰው ልጅ ስለሚሰራው ሥራ አመራር ይሰጣል፡፡ የሰው ልጅ ሥራ ካለው ኒይያ (ውስጣዊ እሳቤ ወይም ውሳኔ) ጋር
ይታያል፡፡ ውስጣዊ ቀስቃሽ ፍላጎቱ ምን እንደሆነ ለማየት ይሞክራል፡፡ በኢስላም የተግባር መለኪያው ከምንም ነገር በፊት የሥራውን
አነሳሽ ከምንጩ አበጥሮ ማወቅ ነው፡፡ ምናልባት አንድ ሰው ከፍተኛ ስጦታ ሊሰጥ ይችላል፡፡ ይህንን ስጦታ የሰጠው የሰዎችን ፍቅር
ለማግኘት አልያም ውለታ ለመመለስ ሊሆን ይችላል፡፡ ሁለቱም ድርጊቶች የሰውየውን ቸርነት የሚያመላክቱ ናቸው ሊሉ ይችላሉ
የሥነ-ልቦና ሰዎች፡፡ ሆኖም በኢስላም ይህ በጎ ድርጊት ምንዳ የሚያስገኘው፣ ከግል ጥቅም ውጭ ከሆነና፣ ለአላህ ብቻ ተብሎ ከተደረገ
ነው፡፡
٩ :‫ﭽ ﭩ ﭪ ﭫ ﭬ ﭭ ﭮ ﭯ ﭰ ﭱ ﭲ ﭼ اإلنسان‬
"የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው፤ ከናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም::" (አድ-ደህር፡ 9)
٢١ - ١٨ :‫ﭽ ﭝ ﭞ ﭟ ﭠ ﭡ ﭢ ﭣ ﭤ ﭥ ﭦ ﭧ ﭨ ﭩ ﭪ ﭫ ﭬ ﭭ ﭮ ﭯ ﭰ ﭱ ﭼ الليل‬
"ያ የሚጥራራ ኾኖ ገንዘቡን (ለድኾች) የሚሰጠው:: ለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ
የለችም፡፡ ግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህንን ሠራ)፡፡ ወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል፡፡ " (አል-
ለይል: 18-21)
ማንኛውም በጎ ተግባር ከንጹሕ ልብ የመነጨ ሊሆን ይገባል፡፡ ከትንሽና ርካሽ ፍላጎት መፅዳት አለበት፡፡ የአላህ መልዕክተኛ
(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ሥራ የሚለካው በኒያ (ውስጣዊ እሳቤ ወይም ውሳኔ)፡፡ በርግጥ ሁሉም ሰው በልቡ የ k ጠረውን ነገር
ያገኛል፡፡ ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) አልሞ በስደት (ከመካ ወደ መዲና) የሄደ ሰው፣ በእርግጥ ስደቱ ወደ አላህና
መልዕክተኛው ነው (ተቀባይነት አግኝቷል)፡፡ ስደቱ ምድራዊ ሕይወቱ ላይ (ምድራዊ) ስኬት ለማምጣት ወይም ሴትን ለማግባት ከሆነ፣
ስደቱ ለአለመበት ነገር ነው፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመካ ወደ መዲና ለተለያየ ዓላማ ይጓዛሉ፡፡ ሆኖም ይህ ጉዞ ለኢስላም ለመኖርና ኢስላምን አሸናፊ
ለማድረግ ከሚደረግ ጉዞ በጣም ይለያያል፡፡ ይህ ነው እንግዲህ በተራ ተጓዥና በአላህ መንገድ በተሰደደ (ሙሃጂር) መካከል የሚኖረው
መሠረታዊ ልዩነት፡፡ ምንም እንኳ ሁለቱም ጉዞዎች በዓይን የሚታይ ልዩነት ባይታይባቸውም፡፡
በሃይማኖት ምክንያት የሚደርስበትን ጭቆና ለማስወገድ ተጉዞ፣ በአዲሱ የኢስላም አገር ውስጥ የዲን ግንብ ለመትከል ከመካ
ወደ መዲና የተጓዘ ሰው በርግጥ ሙሃጂር (ስደተኛ) ነው፡፡ ለሌሎች ጉዳዮች ብሎ የተጓዘ ሰው፥ ከሂጅራው (ከስደቱ) ምንም አያገኝም፡፡
ትክክለኛ ውሳኔ እና ልብን ለአላህ ማፅዳት (ኢኽላስ)፥ ምድራዊ ጥቅም ብቻ የሚያስገኙ ሥራዎችን በአላህ ዘንድ ተቀባይነት
የሚያስገኙ ዒባዳዎች ያደርጋቸዋል፡፡ ኒያ ከተበላሸ ንጹህ ዒባዳ (አምልኮ) አይኖርም፡፡ ዒባዳውን ለመፈፀም የከፈለው የትኛውም ጥረት
ፋይዳ ቢስ ይሆናል፡፡ አንድ ሰው የሚያማልል መናፈሻ ያለው የተንጣለለ ቪላ ሠርቶ በተንጣለለ ቤቱና ልብ በሚሰልብ መናፈሻው ውስጥ
ባለው ሃብት ከምድር ነገስታት ተርታ ሊቆጠር ይችላል፡፡ ሆኖም ይህ ሰው ከዚህ የላቀ ሀብት በስተጀርባ በገነባው ቤትና በተንከባከበው
አትክልታማ መናፈሻ ሰዎችን መጥቀምና ማስደሰት ካሰበ፥ ከተመኘና ከጓጓ፥ በዚህ ሃሳቡ የማይቋረጥ ምንዳ ያገኝበታል፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ድንበር ሳያልፍ እና ሰዎችን ሳይበድል ቤት የሠራ፣ ድንበር ሳያልፍ እና ሰዎችን
ሳይበድል አትክልት የተከለ፣ ከአር-ረሕማን ፍጡራን ውስጥ አንዱ (በዚህ ንብረት) ከተጠቀመበት የማይቋረጥ ምንዳ (አጅር)
ያገኝበታል፡፡” (አህመድ ዘግበውታል)
በሌላ ዘገባ፡- ‹‹ማንኛውም ሙስሊም የተከለው ተክል ወይም የዘራው እህል ሰው ወይም በራሪ ወፎች ቢበሉለት፥ ባለቤቱ ሰደቃ
ይሆንለታል፡፡››
ከዚህም በተጨማሪ የሰው ስሜት የሚወዳቸው አርኪና ጥቅም ያላቸው ተግባራት፣ ምርጥ ዓላማ (በጎ ኒይያህ)
ከታከለባቸው ወደ አላህ ያቃርባሉ፡፡ አንድ ሰው የራሱንና የዲኑን ክብር ለመጠበቅ ብሎ ከሚስቱ ጋር ብቻ ግብረ ስጋ ግንኙነት
ቢፈፅም፣ በዚህ ተግባሩ ምንዳ ያገኝበታል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “በብልታችሁ ሰደቃ ታገኙበታላችሁ፡፡”
አንድ ሰው ራሱን& ሚስቱንና ልጆቹን በቅንነት በማስተዳደሩ ምንዳ ያገኝበታል፡፡ ሰዕድ ኢብኑ አቢ ወቃስ (ረ.ዐ) በዘገቡት
ሐዲስ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋቸዋል፡- “አንተ አንድ ነገርን ለአላህ ብለህ ስትለግስ አላህ ሽልማት ይሰጥሃል፡፡
ሚስትህን የምታጎርሰውም ቢሆን፡፡” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ለራስህ የተመገብከው ለአንተ ሰደቃ ነው፡፡ ልጅህን የመገብከው ለአንተ ሰደቃ ነው፡፡
ሚስትህን የመገብከው ለአንተ ሰደቃ ነው፡፡ አገልጋይህን የመገብከውም ለአንተ ሰደቃ ነው፡፡” (አህመድ ዘግበውታል)
በእርግጥ አንድ ሰው፥ ለአላህ ፍቃድ እስካደረ፥ ኒይያውን ለአላህ እስከ አደረገ፥ እንቅስቃሴውና እርጋታው፤ መኝታውና ንቃቱ ወደ
አላህ (ሱ.ወ) ውዴታ የሚደረግ እርምጃ ተደርጎ ይቆጠርለታል፡፡ ምናልባት አንድ ሰው በጤና መታወክ አልያም ገንዘብ በማጣት
ሊሠራው የሚፈልገውን በጎ ሥራ መሥራት ይሳነው ይሆናል፡፡ ሆኖም አላህ (ሱ.ወ) ምስጢር አዋቂ ጌታ ነው በበጎ ሥራ ለመሥራት
የሚጓጓን ሰው፤ ከበጎ ሠሪዎች ተርታ ይቆጥረዋል፡፡ ጂሃድ ለመሳተፍ የሚጓጓን ሰው ከሙጃሂዶች መደብ ይመድበዋል፡፡ ምክንያቱም አላህ
ሰዎች በጎ ውጥን (ኒይያህ) ኑሯቸው አላማቸውን ከግብ ለማድረስ መሰናክል ቢገጥማቸው ለበጎ ውጥናቸው የአድራጊን ሽልማት
ይሰጣቸዋል፡፡
በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘመን ፈታኝ ዘመቻ ነበር፡፡ ሰዎች ወደ አላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መጡ፡፡ ከሳቸው ጋር ሆነው ጦርነት
ለመሳተፍ ፈለጉ፡፡ ነፍሳቸውን በአላህ መንገድ ለመሰዋት ቆረጡ፡፡ ሆኖም እነርሱ የዘመቻ መሰናዶ ለማድረግ አልቻሉም፡፡ ነቢዩም
(ሰ.ዐ.ወ) እነሱን ለማሰናዳት የሚያስችል ገንዘብ አላገኙም፡፡ ከጂሃድ ስለቀሩ ልባቸው አዝኖ፣ ቅስማቸው ተሰብሮ፣ ዓይኖቻቸው
አነቡ፡፡ እነሱንም በማስመልከት ይህ የቁርኣን አንቀጽ (አያህ) ወረደ፡-
٩٢ :‫ﭽ ﮭ ﮮ ﮯ ﮰ ﮱ ﯓ ﯔ ﯕ ﯖ ﯗ ﯘ ﯙ ﯚ ﯛ ﯜ ﯝ ﯞ ﯟ ﯠ ﯡ ﯢ ﯣ ﯤ ﭼ التوبة‬
"በነዚያም ልትጪናቸው በመጡህ ጊዜ በርሱ ላይ የምጭናችሁ (አጋሰስ) አላገኝም፤ ያልካቸው ስትኾን
የሚያወጡት ገንዘብ ባለማግኘታቸው ለማዘናቸው ዓይኖቻቸው እንባን እያፈሰሱ በዞሩት ላይ (የወቀሳ
መንገድ) የለባቸውም፡፡" (አት-ተውባህ: 92)
ይህንን የጉጉት ፅናት፣ መስዋዕት የመሆን የጠለቀ ፍቅር፣ አላህ በከንቱ አላለፈውም፡፡ ስለዚህም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እነዚህን ሰዎች
በማስመልከት ያላቸውን ኢኽላስና ኢማን፣ እንዲሁም ደረጃ እንዲህ በማለት ካብራሩ በኋላ ዘመቻው ላይ ለመሳተፍ ለሄዱት ታጋዮች
እንዲህ አሉ፡-
“ሰዎች በችግር ምክንያት ከኛ ኋላ ቀርተዋል፡፡ ሸለቆ ስንወርድ፣ ተራራ ስንወጣ፣ እነርሱ ከእኛ ጋር ናቸው (በምንዳ
ይጋሩናል)፡፡” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
እውነተኛ ኒይያቸው ይህንን የሙጃሂዲኖችን ደረጃ እንዲያገኙ አደረጋቸው፡፡ ከጅሃድ የቀሩት ግድ ሆኖባቸው ነውና፡፡ እውነተኛ
ኒይያ ይህንን የመሰለ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ተቀባይነት ያስገኛል፡፡ በተበላሸ ኒይያ ላይ ተመስርቶ፣ በጎ የሆነን ተግባር መፈጸም፣ ተግባሩን
ከጥሩ ተግባርነት ወደ ኃጢአትነት ይቀይረዋል፡፡
٦ - ٤ :‫ﭽ ﭶ ﭷ ﭸ ﭹ ﭺ ﭻ ﭼ ﭽ ﭾ ﭿ ﮀ ﮁ ﮂ ﭼ الماعون‬
"ወዮላቸው ለሰጋጆች፤ ለነዚያ እነሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)፡፡ ለነዚያ እነሱ እዩልኝ
ባዮች ለኾኑት፤" (አል-ማዑን:4-6)
ለይዩሉኝ ተብሎ የሚሰገድ ሰላት ኃጢአት ነው፡፡ ኢኽላስን መሠረት ያላደረገ ተግባር መንፈሳዊ ፍሬ የለውም፡፡ ዘካ (ሶደቃ)
አላህ ዘንድ ከፍተኛ ደረጃ ለማግኘት ለአላህ ብሎ ከተለገሰ፥ ተቀባይነት ያገኛል፡፡ ያለበለዚያ ተቀባይነት የለውም፡፡
‫ ﯾ ﯿ ﰀ ﰁ ﰂ ﰃﰄ ﭼ‬O‫ﭽ ﯤ ﯥ ﯦ ﯧ ﯨ ﯩ ﯪ ﯫ ﯬ ﯭ ﯮ ﯯ ﯰ ﯱ ﯲﯳ ﯴ ﯵ ﯶ ﯷ ﯸ ﯹ ﯺ ﯻ ﯼﯽ‬
٢٦٤ :‫البقرة‬
"እላንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደዚያ ገንዘቡን ለሰዎች ማሳየት ሲል፥ እንደሚሰጠውና በአላህና በመጨረሻውም
ቀን እንደ ማያምነው ሰው፣ ምጽዋቶቻችሁን በመመፃደቅና በማስከፋት አታበላሹ፤ ምሳሌውም በላዩ
ዐፈር እንዳ ለንጣ ደንጊያ ኀይለኛም ዝናም አንዳገኘውና ምልጥ አድርጐ እንደተወው ብጤ ነው፤
ከሠሩት ነገር በምንም ላይ (ሊጠቀሙ) አይችሉም፤ አላህም ከሓዲያንን ሕዝቦች አይመራም፡፡" (አል-
በቀራህ፡ 264)
አለት ዘር አያፈራም፡፡ ኢኽላስ ያጣ ቀልብ ፍሬው ተቀባይት የለውም፡፡ የሚያምር ቅርፊት የውስጡን ቆሻሻ ይደብቃል እንጂ
ውስጡን አያፀዳውም፡፡ ኢኽላስ በጣም ውድ ነገር ነው፡፡ በረከቱ ወደር የለውም፡፡ ትንሽ ተግባር በኢኽላስ ከተሠራ ተራራ ያክላል፡፡
አያሌ ተግባር ኢኽላስ በማጣቱ ምክንያት አላህ ዘንድ ኢምንት ይሆናል፡፡ ለዚህም የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) “ሃይማኖትህን ለአላህ
ብቻ ፅዱ አድርግ፡፡ ለተግባሩ ትንሽ ይበቃሃል፡፡” (ሐኪም ዘግበውታል)
አላህ የሚሰጠው ደረጃና ምንዳ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ የሚበልጥበት ምስጢር ልቦና ውስጥ በተመሠረተ ኢኽላስ ላይ ነው፡፡
ልቦናን ተመልካች አላህ ብቻ ነው፡፡ ኢኽላስ እና ሌሎችን ለመጥቀም በቅን ልቦና የሚደረግ ድርጊት ሽልማቱ እጅግ የተነባበረ ነው፡፡
የሰው ልጅ ተክለ ሰውነት፣ ዱንያዊ ብልጭልጭ ሕይወቱ፣ አላህ ዘንድ ምንም ዓይነት ክብደት የላቸውም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የሚፈሩትን
እና እሱን ብቻ የሚገዙትን ባሮች ስራቸውን ይቀበላቸዋል፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “አላህ ተክለ ሰውነታችሁን እና ቅርጻችሁን አይመለከትም፡፡ ነገር ግን
ልቦናችሁንና ተግባራችሁን ይመለከታል፡፡” (ሙስሊም ዘግበውታል)
በሌላ ሐዲስ፡- “የቂያማ ቀን ዱንያ አላህ ፊት ትቀርባለች፡፡ ለአላህ ተብሎ የተሠራና ያልተሠራ ይለያል፡፡ ለአላህ ፈቃድ ተብሎ
ያልተሰራው ወደ ጀሀነም እሳት ይወረወራል፡፡” (በይሀቂ ዘግበውታል)
ሕይወቱን በኢኽላስ ላይ የገነባ በምድራዊ ህይወቱ እፎይታ ያገኛል። ለመጭው ዓለምም ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህ ዓለም ላጣው ነገር
አይበሳጭም፡፡ ለመጭው ዓለም ስላስተላለፈው አይቆጭም የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “አላህን ብቻ እየተገዛ በእሱ
ላይ ምንም ሳያጋራ በኢኽላስ ሰላትን የሰገደ፣ ዘካን ያወጣ፣ ከዚያም ከዚህ ዓለም በሞት የተሰናበተ፣ አላህ ወዶታል፡፡” (ኢብን ማጃህ
ዘግበውታል)
ይህንንም ለመረዳት የሚከተለውን የቁርአን አንቀጽ ማስተዋሉ ይጠቅማል፦
٥ :‫ﭽ ﮘ ﮙ ﮚ ﮛ ﮜ ﮝ ﮞ ﮟ ﮠ ﮡ ﮢ ﮣ ﮤﮥ ﮦ ﮧ ﮨ ﭼ البينة‬
"አላህን፣ ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ፣ ዘካንም
ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ (ሃይማኖት) ድንጋጌ ነው" (አል-በይናህ: 5)
የሰው ልጅ ስሜቱን ሲቆጣጠር፣ ከወንጀሉ ሲፀዳ፣ በአላህ መንገድ ላይ ለመኖር ሲቆርጥ፥ ኢኽላስ በልቦናው ውስጥ ብርሃኑን
ይለግሳል፡፡ ስለዚህም ሰውየው በችግርና በጭንቀት በተዋጠበት ጊዜ ኢኽላስ ይታደገዋል፡፡
የሰው ልጅ በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ በጭንቀት ይዋጣል፡፡ከእዚህም ፈተና ይታደገው ዘንድ አላህን ይማጸናል፡፡ ቁርአን
እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡-
‫ﭽﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﭼ‬
"ከየብስና ከባሕር ጨለማዎች በግልጽና በምስጢር የምትጠሩት ስትኾኑ ከነዚህ ቢያድነን በእርግጥ
ከአመስጋኞች እንኾናለን (ስትሉ) የሚያድናችሁ ማነው? በላቸው፤ አላህ ከሷና ከጭንቅም ሁሉ
ያድናችኋል፤ ከዚያም እናንተ ታጋራላችሁ፡፡ በላቸው::" (አል-አንዓም: 63-64)
የጭንቀትና የጥበት ጊዜ ብቅ የሚል ሌላ ጊዜ የሚጠፋ ኢኽላስ ጤናማ ዝንባሌን አያመላክትም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ሰዎች በትክክል
እንዲያውቁት፣ ትክክለኛ ማንነቱን እንዲገነዘቡት መልዕክት አስተላልፏል፡፡ በችግርም፣ በድሎትም፣ በጭንቀትም፣ በእፎይታም ጊዜ
አላህን አጥብቀው እንዲይዙ ከአላህም በየትኛውም ጊዜ እንዳይቆራረጡ በነቢያቱ አማካኝነት ያስተምራል፡፡
የሰው ልጅ የንዋይና የዝና ፍቅር፣ የስልጣን ጥማት፣ ኩራትና ማን አለብኝነት በልቦናው ሲገባ ኢኽላስ ይከስማል፡፡
٣ :‫ﭽ ﮆ ﮇ ﮈ ﮉﮊ ﭼ الزمر‬
"ንቁ፤ ፍጹም ጥሩ የኾነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው፡፡" (አዝ-ዙመር: 3)
ምርጥ ሥነ-ምግባር ልክ እንደበሰለ መልካም ፍሬ ነው፡፡ ይህ ፍሬ ጣፋጭና ንጹህ ሁኖ እንዲገኝ እንክብካቤና ክትትል ይሻል፡፡
የሚያበላሸውና የሚቀይረው ነገር አያስፈልግም፡፡
ኢስላም ለመታየትና ለዝና ተብሎ የሚሠራ ተግባርን ይጠላል፡፡ በአላህ ማጋራት እንደሆነ አድርጐም አውጇል፡፡ በእርግጥ
ይዩልኝና ይስሙልኝ አደገኛ የልብ በሽታ ነው፡፡ ይህ በሽታ ነፍስ ላይ ከተዘራ፣ ከአደገና ነፍስን ከተቆጣጠረ፣ ባእድ አምልኮ (ሺርክ)
ይሆናል፡፡ ይህም ሰውየውን የእሳት ማገዶ ያደርገዋል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ማንኛውም ሥራ ትንሽ እንኳ
ቢሆን የይዩልኝ ስሜት ከተቀላቀለበት ሽርክ ነው፡፡ ...አላህ (ሱ.ወ) ሰናይ ምግባር የተዋሃዳቸውን፣ ለዝና የማይ k ምጡ፣ አላህን
የሚፈሩ፣ ርቀው የማይጠፉ፣ ታድመው የማይታወቁ፣ በልቦናቸው ውስጥ የምሪት ቀንዲል የሚንቦገቦግ ሰዎችን ይወዳል፡፡ ›› (ሐኪም
ዘግብውታል)
ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት አንድ ሰው፡- “የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሆይ! የአላህን ውዴታ ለማግኘት የምችልበትን
አንድ ሥራ መሥራት እፈልጋለሁ፡፡ እንዲሁም ዝነኛ መሆን እፈልጋለሁ›› አለ፡፡ የአላህ መልዕክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) ቁርኣን እስኪወርድ
ዝም አሉት፡፡ ይህቺም የቁርኣን አንቀጽ ወረደች፡፡
١١٠ :‫ﭽ ﰐ ﰑ ﰒ ﰓ ﰔ ﰕ ﰖ ﰗ ﰘ ﰙ ﰚ ﰛ ﰜ ﭼ الكهف‬
"የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፣ መልካም ሥራን ይሥራ፤ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ
በላቸው፡፡" (አል-ከህፍ፡ 110)
የይዩልኝ ተግባር ኢስላም ከሚጠላቸው ዋናዋና ኃጢአቶች አንዱ ነው፡፡ ለዝና እና የይዩልኝ ስሜት የሚጨነቅ ሰው ስሜቱ
ለምሬት፣ የድርጊቱም ዓላማ ለችግር ይጋለጣል፡፡ ከፅዱ ልቦና ያልመነጨ ግብር ፍሬው መሪር ይሆናልና፡፡ በግልፅ እኩይ ነገር ማድረግ
ወንጀለኝነት ነው፡፡ ወንጀልንም እንዲንሰራፋ ያደርጋል፡፡ ክፉ ተግባርም ነው፡፡ ይህን መጥፎ ስራ የሰራ ሰው ጥፋቱን ተገንዝቦ በፍጥነት
ወይም ዘግይቶ ቢሆን ወደ አላህ ሊመለስ ይችላል፡፡
ጥሩ ስም የለበሰ መጥፎ ተግባር፣ አስከፊ አደጋ አለው፡፡ ግለሰቡ በራሱ ይመፃደቃል፡፡ ህብረተሰቡም በጎ ሰው ነው ብሎ
ያስባል፡፡ ችግሩን ለመረዳት ኃጢአቱንም ለመገንዘብ ይሳነዋል፡፡ ጥሩ ብሎ ከሚያስበው መጥፎ ተግባሩ ተፀፅቶ ለመመለስ የሚያስችል
ርዕይ ይጎለዋል፡፡
አንድ ማኅበረሰብ የሥነ-ምግባር ካባ ተጎናፅፈው ዕኩይ ከሚሸርቡ አስመሳዮች የሚደርስበት ችግር ወደር የለውም፡፡ ዘራፊ
ወንበዴ ከሚሰራው ግልጽ ግፍ የበረታና የከበደ በደል በሕብረተሰብ ላይ ይፈጽማሉ፡፡ ተሰጥኦና ችሎታ እንዲሁም ለድርጊት ብቃት
ያላቸው፣ በአንፃሩ ኢኽላስ ያጡ ግለሰቦች፣ ተሰጥኦዋቸውን አገር ለማቆርቆዝ ሰላምን ለማደፍረስ ሊያውሉት ይችላሉ፡፡
ብቃትንና ችሎታን እኩይ ዓላማ ማዋል ጥሩን ነገር ማበላሸት ነው፡፡ የሰው ልጅን እሴት (value) መቀማት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሌላ
ውድቅ ተግባር ነው፡፡ ይህ ኢኽላስ ማጣት የሚያመጣው ጣጣ ነው፡፡ በስራው የሰዎችን ከንቱ ውዳሴ የሚፈልግ፣ ከጌታው ቅርበት
የሚርቅ፣ የሚሰራውን ሥራ ከንቱነት ያልተገነዘበ ነው፡፡ በዚህ ርካሽ ተግባሩ ከቀጠለ፣ ከክብሩ፣ ከጠንካራና ብርቱ አምላኩ እርቆ ወደ
አመለካከት ድሆችና ደካሞች፣ ብልሃትና ብርታት ወደሌላቸው ሰዎች ይጠጋል፡፡
ስለዚህም የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “አላህ የመጀመሪያዎቹንም የመጨረሻዎቹንም የሚሰበስብበት መሆኑ
ጥርጥር በሌለበት በቂያማ ቀን ተጣሪ ይጣራል፡፡ ለአላህ ብሎ በሚሰራው ሥራ ላይ ቅንጣት ያጋራ ከአጋራበት (ሺርክ ከፈጸመበት) ምንዳ
ይጠብቅ፡፡ በርግጥ አላህ ከሚያጋሩ ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡” (ቲርሚዚ ዘግበውታል)
ማንኛውም ሰራተኛ በስራ ገበታ ላይ ሲሆን፣ የሚጽፈውን በአግባቡ መጻፍ፣ የሚያስበውንም በትክክል ማሰብ ይጠበቅበታል፡፡
አእምሮውን የሚጠቀመው፣ እጁን የሚያደክመው፣ አገሩን ለማበልጸግ እና የአላህን ፍቅር ለማግኘት በመጓጓት ሊሆን ይገባል፡፡
የመጓጓዣ እንስሳ ቀኑን ሙሉ በመልፋት የምትበላውን ምግብ ወጪ ትከፍላለች፡፡ በአንፃሩ ግን ብልህ ሰው አስተሳሰቡን፣ ንቃቱንና
ጥረቱን ከዚህ በላይ ላለ ከፍተኛ አላማ ያውላል፡፡ የሰው ልጅም ስራውንና ጥረቱን ለሚያገኘው ደመወዝ ክፍያ ብቻ ብሎ ከሰራ፣ ወደ
እንስሳነት ደረጃ ይወርዳል፡፡
ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሠራተኞች የሚያሳስባቸው ነገር ገንዘብ፣ ሹመት፣ ስልጣን ብቻ መሆኑ በጣም ያሳዝናል፡፡ ዲናቸውም፣ ሆነ
ምድራዊ ሕይወታቸው በዚህ መሰረት ላይ የተገነባ ነው፡፡ ደስታቸውም ሆነ ቅሬታቸው፣ ንቃታቸውም ሆነ ድክመታቸውም በዚሁ ሚዛን
ይለካል፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹የመጨረሻው ቀን ሲሆን ህዝቦቼ ለሶስት ይከፈላሉ፡፡ ከፊሎቹ አላህን በቀና ልቦና
የሚያመልኩ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ አላህን ለታይታ ወይም ደግሞ ለዓለማዊ ጥቅም ብለው ያመልኩታል፡፡ አላህ የቂያማ ዕለት በአላህ
ፊት ሁሉም ይታደማሉ፡፡ ምድራዊ ጥቅም ለማግኘት ያመለኩትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‹‹በክብሬና በልቅናዬ ይሁንብህ፤ ለምንድን ነበር
የምታመልከኝ?›› እሱም ‹‹በክብርህ በልቅናህ ም§ እመሰክራለሁ፡፡ ከሰዎች ምድራዊ ጥቅም ለማግኘት ስል አመለኩህ›› ይላል፡፡ አላህ
እንዲህ ይለዋል፡- ‹‹አንድም ሥራህ ከኔ ዘንድ ተቀባቀይነት አላገኘም፡፡ ወደ እሳት ውሰዱት፡፡›› ከዚያም ለይስሙላ ለሚያመልከው ሰው
አላህ፦ ‹‹በክብሬና በልቅናዬ ይሁንብህ፤ ለምንድን ነበር የምታመልከኝ?›› ይለዋል፡፡ ‹‹በልቅናህና በክብርህ›› ይሁንብኝ፤ የማመልክህ ሰዎች
እንዲያዩልኝ ብዬ ነበር -ይለዋል፡፡›› አላህ እንዲህ ይለዋል፡- ‹‹አንድም ስራህ ከኔ ዘንድ ተቀበቀይነት አላገኘም፡፡ ወደ እሳት ውሰዱት፡፡››
ከዚያም ለዚያ በንጹሕ ልቦና ለሚያመልከው ‹‹በልቅናዬና በክብሬ ይሁንብህ፤ ለምንድን ነበር የምታመልከኝ?›› ይለዋል፡፡ “በክብርህና
በልቅናህ ይሁንብኝ፤ አንተ ከኔ የበለጠ ለምን እንደማመልክህ ታውቃለህ፡፡ አንተን ማውሳት አንተን ማግኘት ፈልጌ ነው የማመልክህ፡፡››
አላህም እንዲህ ይላል፡- “ባሪያዬ እውነት ተናገረ፡፡ ወደ ጀነት ውሰዱት፡፡” (አቡዳውድ ዘግበውታል)
በእውቀትና በምርምር ዘርፍ ኢኽላስ (ቅንነትና ቀጥተኝነት) ሊሰፍን ይገባል፡፡ እውቀትና ምርምር አላህ የሰው ልጆችን ከሌሎች
ፍጡራን ያላቀበት ልዩ ስጦታው ነው፡፡ በጣም አሰቃቂው ነገር ይህ እውቀት ለመጥፎ ድርጊት ሲውል ነው፡፡ ከመልካም ሥነ-ምግባር
የተጣላ ስሜታዊነት የሚነዳው የእውቀት አግበስባሽነት፣ ለምንኖርበት አለም መከራ መንስኤ እንጂ መፍትሄ አይሆንም፡፡ ዓለማችን
ላጋጠማት የሁከትና የሰላም ማጣት አደጋ ዋናዎቹ ተዋናዮች ቅንነት የጎደላቸው ምሁራን ነበሩ።
በእርግጥ ኢስላም በአስተማሪም ሆነ በተማሪ ላይ በትጋት እውቀትን እንዲለዋወጡ፣ ከምንም በላይ ለትልቅ አላማና ለሕብረተሰብ
ጥቅም እንዲጥሩ ያስተምራል፡፡ ማስተማርና መማር ገንዘብ ለማፈስና ለግል ጥቅም ለማግኘት ብቻ ከሆነ፣ በብዛት (ዛሬ ሰዎች
እንደሚያደርጉት) በእውቀት እሴት ማላገጥ፣ የእውቀትን ክብር ማቆሸሽ ነው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “አላህን
ለማግኘት እውቀትን መፈለግ ሲገባው፣ እውቀትን የዱንያ ድርሻ (ብቻ) ለማግኘት የተማረ፣ የቂያማ እለት የጀነትን ሽታ አያገኝም፡፡”
(አቡዳውድ ዘግበውታል)
እንዲሁም ኢስላም የሰው ልጅ በሌሎች ላይ ለመንጠባረር በሚል እውቀትን እንዲማርና እንዲቀስም አይፈቅድም፡፡ “አዋቂዎች
(ኡለማ) ላይ ለመንጠባረር፣ አላዋቂዎች ላይ ለማሾፍ፣ ማኅበራዊ ደረጃችሁን ለማሳመር ብላችሁ አትማሩ፡፡ ይህን ያደረገ እሣት ውስጥ
ነው፡፡›› (አቡዳውድ ዘግብውታል)
እውቀት በዚህ ስፋቱና ጥልቀቱ ብልጽግና ላይ ሊደርስ የቻለው ለእውነት በማደር ላይ ስለተመሰረተ ነው፡፡ እውነተኛ
ምሁራን ለትናንሽ ጥቅማጥቅሞች ሕሊናቸውን አይሸጡም፡፡ ሆኖም ተማሪዎችም ሆኑ ምሁራን (ዑለማእ) የሕይወትን መከራ
ያለአግባብ ሊሸከሙ አይገባቸውም፡፡ በሕይወት ተገፍተውም ወደ ፈታኝ ቀውስ ውስጥ መገፋት የለባቸውም፡፡ ትክክለኛ ኒይያ ማለት
በችግር መዋጥ፤ አደጋ መሸከም ማለት አይደለም፡፡ ሰዎች ቅን ልቦና አላቸው ይባል ዘንድ መቸገር የለባቸውም፡፡
ኢኽላስ በማጣት የሚመጡ ችግሮች በርካታ ናቸው፡፡ ኢኽላስ ከጠፋ ኢማንን ያቀጭጫል፡፡ ከቀጨጨም ለሸይጣን መስኮት
ይከፍታል፡፡ ዓላማቸውን ታይታ የሰለበው፣ የገንዘብና የዝና ባሮች አላህን ያስቆጣሉ፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ሙስሊም አላማውን በሙሉ
ለአላህ ማድረግ ግንኙነቱንም ሆነ ፍላጎቱን በአላህ መስመር ማሳደር ግዴታው ነው፡፡
የፈርኦን መተተኞች ለትክክለኛ እምነትና ለከፍተኛ ኢኽላስ ተምሳሌት ናቸው፡፡ ማባበያ አላንበረከካቸውም፡፡ ማስፈራሪያ
አላንዘፈዘፋቸውም፡፡ የገንዘብንና የስልጣንን ፍላጎት ረግጠው ለዚያ ኃይለኛ ንጉስ እንዲህ አሉት፡-
‫ ﯥ ﯦ ﯧ ﯨ ﯩ ﯪ ﯫ ﯬ ﯭ ﯮ ﯯ ﯰ ﯱ ﯲﯳ ﯴ ﯵ ﯶ ﯷ ﭼ‬O‫ ﯣ ﯤ‬O‫ ﯢ‬O‫ ﯚ ﯛﯜ ﯝ ﯞ ﯟ ﯠﯡ‬O‫ ﯘ ﯙ‬O‫ ﯖ ﯗ‬O‫ ﮱ ﯓ ﯔ ﯕ‬O‫ﭽ‬
٧٣ - ٧٢ :‫طه‬
"ከመጡልን ታምራትና ከዚያም ከፈጠረን (አምላክ) ፈጽሞ አንመርጥህም፤ አንተም የምትፈርደውን
ፍረድ፤ የምትፈርደው በዚች በአነስተኛይቱ ሕይወት ብቻ ነው አሉ፡፡ ኃጢአቶቻችንንና ከድግምትም
በርሱ ላይ ያስገደድከንን ለኛ ይምረን ዘንድ እኛ በጌታችን አምነናል፤ አላህም በጣም በላጭ ነው፤
(ቅጣቱም) በጣም የሚዘወትር ነው አሉ፡፡" (ጣሃ: 72-73)
ከዚህ የምንረዳው የምድራዊ ጥቅማቸውን ሰውተው በአላህ መንገድ በሚታገሉና ዲንን ለስልጣን መረማመጃ በሚያደርጉ ሰዎች
መካከል ግዙፍ ልዩነት እንዳለ ነው፡፡

ወንድማማችነት
ሰዎች ተለያይተውና ተራርቀው በጥላቻ መንፈስ እንዲኖሩ የሚያደርግ አሳማኝ ምክንያት የለም፡፡ እንደውም የሰው ልጅ በንጹህ
አእምሮ፣ ተፈጥሯዊ ስሜት እና ትክክለኛ ሚዛን ነገሮችን ካብላላና ካስተዋለ፤ በአንድነት፣ በፍቅርና በሰላም መኖሩ ግድ ይለዋል፡፡ ይህ
በአንድነት በመተሳሰርና በመፋቀር ላይ የተመሰረት ሕብረተሰብ ለመፍጠር ይመቻል፡፡ በዚህም ሳቢያ በምድር ላይ ሰላም ይሰፍናል፡፡
አላህ (ሱ.ወ) የሰው ልጆችን የዘር ግንድ ምንጭ አንድ እናትና አባት ላይ ቋጥሮታል፡፡ ይህ የሰው ልጆች በሙሉ መገኛ ዘር ይህን ሰብአዊ
ፍጡር ያስተሳስራል፡፡ ጠንካራ ግንኙነት ይፈጥራል፤ ያፋቅራል፤ ያዋድዳል፡፡
١٣ :‫ﭽ ﭵ ﭶ ﭷ ﭸ ﭹ ﭺ ﭻ ﭼ ﭽ ﭾ ﭿﮀ ﮁ ﮂ ﮃ ﮄ ﮅﮆ ﮇ ﮈ ﮉ ﮊ ﭼ الحجرات‬
"እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፤ እንድትተዋወቁም ጐሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ
ዘንድ በላጫችሁ፣ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፤ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡" (አል-ሑጁራት፡ 13)
መቀራረብና መተዋወቅ የሰው ልጆች መሠረታዊ የግንኙነት ምንጭ ነው፡፡ አልፎ አልፎ ይህን መቅረት የሌለበትን ትውውቅና
መቀራረብ እንዳይዘወትር የሚያደርግ ብሎም የሚያበላሽ ጥፋት ሊከሰት ይችላል፡፡ የሰው ልጆች የሃብት ምንጭ የሆኑ ማዕድናት
ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ግፊያና እውነታን በመገንዘብና ጥሩን ነገር በመለየት ዙሪያ የሚኖሩ አለመግባባቶች ግጭት ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡
ሆኖም እነዚህ መጥፎ ክስተቶች የሰው ልጆችን አብሮ የመኖር፣ የመተጋገዝንና የመግባባት፣ ምድር የማልማትና የማሣመር ተልዕኳቸውን
ሊያስረሣቸው አይገባም፡፡
ይህንን ግንኙነት ሊያሳካ የሚችል የትኛውም ትስስር ሊበረታታ ግድ ይላል፡፡ በአንጻሩ ትስስር እንዳይጸና፣ ውዴታ እና ፍቅርን
እንዳይሰምር የሚያደርግ እንቅፋት ሊወገድ ይገባዋል፡፡ ኢስላም ጥቂት ወይም ብዙ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ብቻ ለማስተሳሰር አንድ ላይ
ለመሰብሰብ የሚጥር ሃይማኖት አይደለም፡፡ ኢስላም የሰው ልጆችን በሙሉ ከአምላካቸው ጋር ትክክለኛ ግንኙነት እንዲኖራቸው
ይጥራል፡፡ ብሎም የሰው ልጆችን በሙሉ በአንድነት ያሰልፋል፡፡
ከዚህም በላይ የኢስላምን ዓላማ ለማሳካት የሚጥሩ የለውጥ ሐዋሪያት ልቦናቸውን ክፍት በማድረግ አርአያነት ያለው ተግባር
እንዲፈጽም በኢስላም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ልቦናቸውንም በዚሁ ላይ ሰብስቦላቸዋል፡፡ የዲኑን እምነት ትልቅነትም በአግባቡ ሊገነዘቡ
ይገባል፡፡
በፍጡራን መካከል ያለ የጋራ የትስስር ምንጭን ማወቅ የሁሉም የሰው ልጆች አባት አደም መሆናቸው ላይ ይጠቀለላል፡፡
እንዲሁም የሁሉም ሃይማኖቶች አስተምህሮት አንኳር መልዕክት በኢስላም መልዕክት ተጠቃሏል፡፡ ከዚህ በመነሳትም እውነተኛ
ሃይማኖት ጠንካራ ትስስር ወዳለው ወንድማማችነት ይገባል፡፡ ስለሆነም በምድር ላይ በምስራቅም ሆነ በምዕራብ የሃይማኖቱ ተከታዮች
መካከል የጠለቀ ፍቅር ይመሰረታል፡፡ የቦታም ሆነ የዘመናት ርቀቶች ቢኖሩም፣ የጠለቀ መሰረት ላይ የቆመ ጠንካራ ግንብ ስለሆነ፣ አውሎ
ነፋስ አይበግረውም፡፡
ይህ ወንድማማችነት የህያው እምነት መገለጫ ነው፡፡ ሙስሊም ለወንድሞቹ በውስጡ ያመቀው፤ የፍቅርና የውዴታ መሰረት
ነው፡፡ እሱ በእነሱ ድጋፍ ይኖራል፡፡ ለእነርሱም ይኖርላቸዋል፡፡ እነሱ ልክ ከአንድ ዛፍ ላይ የበቀሉ ዘለላዎች ናቸው፡፡ ወይም በብዙ አካል
ላይ ያለ አንድ ነፍስ፡፡

ራስ ወዳድነት
ራስ ወዳድነት ለበጎ ነገር ትልቅ እንቅፋት ነው፡፡ ጥሩ ሥራን ያደፈርሳል፡፡ ሰውየው በዚህ በሽታ ከተለከፈ ጥሩ ሥራው ይበላሻል፡፡
መጥፎነቱ ያድጋል፡፡ በጠባብ ክልል ውስጥ ይታጠራል፡፡ የራሱን ስሜት ከማሳደድ ውጭ አያውቅም፡፡ ራሱ በሚያገኘው ጥሩ ወይም
አስከፊ ነገር እንጂ በሌላ ነገር አይደሰትም፤ አያዝንምም፡፡ ይህቺ ፊት ለፊቱ ያለች ምድራዊ ሕይወት እንጂ እልፍ አእላፍ የሰው ዘርን እርሱ
አያውቃቸውም፡፡ የሚያውቃቸው እሱ የሚስገበገብባትን ዓላማ በእነርሱ መንገድ ለማሳካት ድልድይ ይሆኑኛል ብሎ ሲያምን ብቻ ነው፡፡
ወይም ፍርሃት ሲያርደው ፍርሃቱን ለማስወገድ፡፡
በእርግጥ ኢስላም ይህን ራስ ወዳድነት በፍትሃዊ ወንድማማችነት ዘምቶበታል፡፡ የሰው ልጅ ሕይወት ለርሱ ብቻ እንዳልሆነች
አስተምሯል፡፡ ብቸኝነት ምንም እንደማይጠቅመውና እሱን የሚመስሉ ሰዎች መኖራቸውን ማስተዋል እንዳለበት አስተምሮታል፡፡
እነርሱ ላይ ያለውን መብት ጉዳይ እንደሚያውቅ ሁሉ እነርሱም እሱ ዘንድ ያላቸውን መብት ያውቃል፡፡ ይህ ግንዛቤ ከራስ ወዳድነት
ምርኮ ያወጣዋል፡፡ ስለራሱ ማሰቡና መብከንከኑ እንኳ መሠረታዊ ነገር ቢሆንም ስለሌሎች እንዲያስብና እንዲብከነከን ያደርገዋል፡፡
መስመር አይስትም፡፡ ከልክ አያልፍም፡፡

ወንድምህን ጠብቀው
ወንድምህ እንዳይጐዳ ማሰብ አለብህ፡፡ ይህ የአንተ ግዴታ ነው፡፡ ጉዳቱን ለማስወገድ ጣር፡፡ ስቃይ ከገጠመው ተጋራው፡፡
አብረኸው እዘን፡፡ ችግሩ አንተን ስላላገኘህ ከአንተ ስለራቀ አያገባኝም ብለህ ግድየለሽ አትሁን፡፡ ይህ የመናጢ ሥራ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት
ስሜት ከወንድማማችነት ውጭ ያደርጋል፡፡ ኢስላማዊ ወንድማማችነት የሙስሊሞችን መንፈስ ያዋህዳል፡፡ ሰው ለወንድሙ ስቃይ
እንዲሰቃይ ያደርጋል፡፡
የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግር ለዚህ ተምሣሌት ነው፦ “ሙስሊሞች ሲዋደዱ፣ ሲተዛዘኑ፣ ርህራሄ በመካከላቸው መስፈኑ ልክ እንደ
አንድ አካል ናቸው፡፡ አንድ (የሰውነት) ክፍል ከታመመ ሁሉም አካል እንቅልፍ ያጣል፡፡ ይሰቃያል፡፡” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
እውነተኛ የስቃይ አንድነት ከወንድሞችህ ላይ ችግርን እንድታስወግድ ይረዳሃል፡፡ ስቃዩ እስኪወገድ አታርፍም፡፡ ዳመናው
እስኪገፈፍ ትጥራለህ፡፡ በዚህ ስኬታማ ከሆንክ ፊትህ ያበራል፡፡ ልብህ እፎይታ ያገኛል፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “ሙስሊም ለሙስሊም ወንድሙ ነው፡፡ አይበድለው፤ አሳልፎ አይስጠው፡፡
የወንድሙን ጉዳይ ጉዳዬ ያለ፥ አላህ ለጉዳዩ ይቆምለታል፡፡ ከሙስሊም ላይ ጭንቀትን የገላገለ፥ አላህ የቂያማ ዕለት ጭንቀቱን
ይገላግለዋል፡፡ የሙስሊምን ነውር የደበቀ፥ አላህ የቂያማ ዕለት (ነውሩን ይደብቅለታል)፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

ወንድምህን አግዝ
ዋናው የወንድማማችነት መገለጫ ወንድምህን ለመጥቀም መጣር ነው፡፡ አንተ የሚያስደስት ነገር ስታገኝ እንደምትፍለቀለቅ ሁሉ
ለወንድምህም ለሚያስደስተው ነገር ጥረት አድርግ፡፡ ጠቃሚና ደጋፊ ለመሆን ጥረት ካደረግክ፤ አላህ ዘንድ በላጭ አጅር ባለው ጥሩ
የአላህ መቃረቢያ ወደ አላህ ተቃርበሃል፡፡
ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንዳወሩት፥ እርሳቸው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) መስጂድ ኢዕቲካፍ ተቀምጠው ነበር፡፡ አንድ ሰው መጥቶ ሰላም
ብሏቸው ተቀመጠ፡፡ ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንዲህ አሉት፡- ‹‹እገሌ ሆይ! ምን ሆነህ ነው የተጐሳቆልከው? ያዘንከው?›› ‹‹አዎ! የአላህ
መልዕክተኛ የአጐት ልጅ ሆይ! ከእገሌ ወላእ (የባርነት እዳ) አለብኝ፡፡ በዚህ ቀብር ባለቤት ጌታ ክብር ይሁንብኝ፡፡ ችሎታው የለኝም
(መክፈል አልችልም)፡፡›› ኢብኑ ዐባስ እንዲህ አሉ፦ ‹‹በአንተ ጉዳይ ላናግረው?›› ‹‹ከተመቸህ ጥሩ›› አላቸው፡፡ ኢብኑ ዐባስ
ጫማቸውን ተጫሙና ከመስጂድ ወጡ፡፡ ሰውየው እንዲህ አላቸው ‹‹የነበርኩበትን (ኢዕቲካፍ) ረሳሁትን? አይ! ይህንን ጉዳይ
አስመልክቶ የዚህ ቀብር ባለቤት ሲናገሩ ከሰማኋቸው ብዙም አልቆየም›› ብለው ዓይናቸው አለቀሰ፡፡ ነቢዩ እንዲህ ሲሉ
ሰምቻቸዋለሁ “ለወንድሙ ጉዳይ የሄደ፣ ጉዳዩን የፈፀመ ሰው ሃያ ዓመት ኢዕቲካፍ ከማድረግ ይበልጥለታል፡፡ አንድ ቀን የአላህን ውዴታ
ለማግኘት ብሎ ኢዕቲካፍ የገባ ሰው አላህ በሰውዬውና በእሣት መካከል ሦስት ሸለቆዎች ያህል ያርቀዋል፡፡ ይህም አንዱ ሸለቆ እንደ
ምስራቅና ምዕራብ ይራራቃል፡፡” (በይሀቂ ዘግበውታል) በሌላ ዘገባ “ሁሉም ሸለቆዎች እንደምስራቅና ምዕራብ ይራራቃሉ፡፡”
ይህ ሐዲስ ኢስላም ለጥሩ ወንድማማችነት ያለውን ክብር፣ ለማኅበራዊ ኑሮ ያለውን ደረጃ ያሣያል፡፡ ሕብረተሰቡ መሰረቱን
ለመትከል ግንኙነቱን ለመጠበቅ ይህ አይነት ምክር ያስፈልገዋል፡፡
በእርግጥ ኢብኑ ዐባስ ኢዕቲካፍ ለመተው ወሰኑ፡፡ ኢዕቲካፍ ንጹህ ዒባዳ ነው፡፡ አላህ ዘንድ ትልቅ ደረጃ ያስገኛል፡፡ ምክንያቱም
ኢዕቲካፍ መስጂድ ውስጥ አላህን በማውሳት መስጠም ማለት ነው፡፡ ደግሞም እሱ በአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መስጂድ ውስጥ
ነው፡፡ ያ መስጂድ ከሌሎች መስጂዶች አንድ ሺህ ደረጃ ይበልጣል፡፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ አጅር የወንድምን ጉዳይ ከማስፈፀም
አይበልጥምና፡፡ ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) ኢስላማዊ ግንዛቤው ይህንን ትቶ እንዲወጣ አደረገው፡፡ እገዛውን ለሚከጅል ሙስሊም እርዳታ
ለማድረግ፡፡ ከአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ይህንን ነው የተማረው፡፡

በሕይወት መተጋገዝ
የዱንያ ኃላፊነቶች ከባድ ናቸው፡፡ መከራዎች በሰዎች ላይ ይዘንባሉ፡፡ ዝናብ ዶፉን ሲያወርደው ደረቁንም ለምለሙንም ያዳርሳል፡፡
ሰው ብቻውን እነዚህን መከራዎች ለረጅም ጊዜ መቋቋም አይችልም፡፡ እችላለሁ ብሎ ቢያምን መሸከም እንኳ ቢችል የሚከፍለው
መስዋእትነት ከባድ ነው፡፡ ወንድሞች ቢኖሩት ሮጥ ብለው በቀላሉ ይገላግሉት ነበር፡፡ ዓላማውን ከግብ እንዲያደርስ ያግዙታል፡፡
በእርግጥ እንዲህ ተብሏል፦ “ሰው ብቻውን ትንሽ ከወንድሞቹ ጋር ግን ብዙ ነው፡፡”
ከወንድማማችነት ዘርፍ ውስጥ ሰው ለክፉም ለደጉም ደራሽ ወንድሞች እንዳሉት ሊሰማው ይገባል፡፡ የእርሱ ጉልበት ለብቻዋ
ምንም አትፈይድም፡፡ የሙእሚኖች ጉልበት ይጨመርለታል፡፡ ያግዙለታል፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፦ “ሙእሚን ለሙእሚን እንደ አንድ ግንብ ናቸው፡፡ ከፊሉ ከፊሉን ያግዛል፡፡” (ቡኻሪ
ዘግበውታል)
ከዚህም ባሻገር እውነተኛ ወንድማማችነት እጥፍ ድርብ ፀጋ ነው፡፡ የመንፈሣዊ አንድነት ፀጋ ብቻ አይደለም፡፡ ቁሣዊ የመተጋገዝና
የመተባበር ፀጋም ጭምር እንጂ፡፡
በእርግጥ አላህ (ሱ.ወ) ይህንን ፀጋ ቁርኣን ውስጥ በአንድ አንቀጽ ውስጥ ሁለቴ ደጋግሞታል፡፡
١٠٣ :‫ﭽ ﭱ ﭲ ﭳ ﭴ ﭵ ﭶﭷ ﭸ ﭹ ﭺ ﭻ ﭼ ﭽ ﭾ ﭿ ﮀ ﮁ ﮂ ﮃ ﮄ ﭼ آل عمران‬
"የአላህን ጸጋ አስታውሱ፤ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፤ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡" (አል ዒምራን፡
103)

መረዳዳት
ኢስላማዊ ወንድማማችነት በሙስሊሞች መካከል መተጋገዝን ግዴታ ያደርጋል፡፡ ይህ መተጋገዝ የቦዘኔዎችና ወሮበሎች መተጋገዝ
አይደለም፡፡ የሙእሚኖች የለውጥ ሐዋሪያት መተጋገዝና መረዳዳት ሥነ-ምግባራዊ መሠረት አለው፡፡ እውነትን ለመትከል፣ ውሸትን
ለመንቀል፣ በዳይን መግታትና ተበዳይን ለመርዳት፡፡ ሙስሊም የሕይወትን ጣጣ እንዲዋትት ብቻውን መተው ትክክል አይደለም፡፡
በየትኛውም ሁኔታው ላይ ከጐን መቆም ግዴታ ነው፡፡ ፈር ሲስት መስመር ማስያዝ፡፡ በጥመት ሲጎብጥ ማቅናት፡፡ ከተጠቃ ጥቃቱን
መከላከል፡፡ ጦርነት ከታወጀበት አብሮ መታገል፡፡ ይህ ነው ኢስላም ያዘዘው መተጋገዝ መረዳዳት፡፡

አክብሮት ይኑርህ
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አንዲህ ብለዋል፡- “ወንድምህን በዳይም ተበዳይም ሁኖ እርዳው፡፡ “ተበዳይ ሁኖ እረዳዋለሁ፡፡
በዳይ ሁኖ እንዴት እረዳዋለሁ?” አለ፡፡ “ከበዳይነቱ ታቅበዋለህ፡፡ ይህ እርሱን መርዳት ነው” አሉ፡፡
ሙስሊምን ማዋረድ ከባድ ወንጀል ነው፡፡ ሁሉንም ሙስሊሞች ለማዋረድ መንገድ ይከፍታል፡፡ ከዚያም በእነርሱ መካከል
የነበረውን መከባበርና መቻቻል ያበላሸዋል፡፡ ተበዳይ ሰው በርሱ ላይ የደረሰውን በደል ለመበቀል ይሞክራል… የከፋ ጥፋት
ይፈጽማል፡፡ እሱን በበደሉትና በራሱ መካከል የወንድማማችነት ገመድ ትበጠሳለች፡፡ በእርግጥ ሙስሊሞች በየግላቸው ተዋርደዋል፡፡
በመካከላቸው ያላቸው የወንድማማችነት ክር የተበጠሰ ጊዜ፥ እንደ ሕዝብም ተዋርደዋል፡፡ አንዱ ሌላውን በበዳይነትና በጥላቻ
መመልከት ሲጀምር፡፡ አንዱ ወንድሙ ሲዋረድ አይቶ ምንም እንደማያገባው ትከሻውን ነቅንቆ ወደ ጉዳዩ በሚሄድ ጊዜ ነገሩ ሁሉ ጠፋ፡፡
ይህ ውርደት ሙስሊሞችን ለቅሌትና ለንቀት አጋለጣቸው፡፡ በእርግጥ ይህን ተግባር ኢስላም በከፍተኛ ሁኔታ ተዋግቶታል፡፡
በእርግጥም አላህ ይህንን ወራዳና ርካሽ ተግባር የሚያከናውኑትን ሰዎች ረግሟል፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “አንዳችሁ አንድ ሰው ተበድሎ ሲመታ እያያችሁ ዝም አትበሉ፡፡ በወቅቱ የነበሩ
ለሰውዬው ያልተከላከሉ ሰዎች እርግማን ይወርድባቸዋል፡፡” (ጦበራኒ)
ወንድምህ ላይ ክፋት ሲሰራበት ወይም አደጋ ሲጣልበት አይተህ አንተ ልታግዘው እንደምትፈልግ ግለጽለት፡፡ በአንተ እገዛ
መብቱን እስኪያገኝ አብረኸው ሁን፡፡
ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንደተላለፈው፦ “ከተበደለ ሰው ጋር መብቱን እስኪያገኝ አብሮ የሆነ ሰው፥ እግሮች በሲራጥ1 ላይ
በሚንዣለጡበት ቀን አላህ እግሮቹን ያፀናለታል፡፡” (አስበሐኒ ዘግበውታል)

አቅምህን ተጠቀምበት
በሕብረተሰብህ ውስጥ ገናና ባለስልጣን፣ የምትፈራና የምትሰማ ከሆንክ፣ ያለብህ ግዴታ ይበዛል፡፡ ከፍተኛ ኃላፊነት አለብህ፡፡
ከገንዘብ ላይ ዘካ እንደሚወጣ ሁሉ ለታዋቂነትና ተደማጭነት ዘካ አለው፡፡ አላህ ለአንተ በምድር ላይ ስልጣን ከለገሰህ ወይም በሰዎች
መካከል ክብር ካለህ ይህ ከጨዋነት ወጥተህ እንድትኮፈስ አልያም ከትህትና ወደ መንጠባረር እንድትለወጥ አይደለም፡፡ አላህ ለአንተ
ይህንን ያገራልህ በአንተ ቀናነትና እገዛ ብቻ ሊፈፀሙ የሚችሉ ጉዳዮችን እንድታስፈጽም ነው፡፡ አንተ ይህን ጉዳይ ትኩረት ሰጥተህ
ኃላፊነትህን በአግባቡ ከተወጣህ ጥሩ፡፡ የተቀመጠልህን ምንዳ ትጐናፀፋለህ፡፡ አለበለዚያ ግን በእርግጥ የአላህን ፀጋ ክደሃል፡፡ ለአደጋም
ፀጋህን አጋልጠሀል፡፡
ከአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ የሚል ሐዲስ ተላልፏል፥ “በእርግጥ አላህ ሰዎች ዘንድ ፀጋ አኑሯል፡፡ (ፀጋው የሚፀናው)
የሙስሊሞች ጉዳይን እስካወጡ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ጉዳይ የማያስፈጽሙ ከሆነ ወደ ሌሎች ይወስደዋል፡፡” (ጦበራኒ ዘግበውታል)
አንድ ሰው በሰዎች መካከል ያለውን ማኅበራዊ ደረጃ ተጠቅሞ ሰዎች ላይ ክፉ እንዳይደርስና መጥፎ ነገር እንዳይገጥማቸው ሲጥር
ሙሉ ለሙሉ ለአላህ ብሎ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህን ተግባር ጉቦ ወይም ስጦታ ለመቀበል አስቦ ካደረገው፣ አላህ ዘንድ ምንዳ
የለውም፡፡ በራሱም ላይ ጉድጓድ ቆፈረ፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “ለአንድ ሰው ሽምግልና የሸመገለ፣ በዚህ ስራው ስጦታ የተሰጠው፣ (ስጦታውን)
የተቀበለው፣ በእርግጥ የትላልቅ ወንጀሎችን ከባዱን በር ከፍቷል፡፡” (አቡ ዳውድ ዘግበውታል)
ኢስላም የተዋጋቸው ብዙ ከንቱ ወንድማማችነትን የሚያናጉ ነገሮች አሉ፡፡ ኢስላማዊ ወንድማማችነት ሁሉንም ሰው በፍትሃዊነት
ያያል፡፡ አፈ-ጮሌትም ሆነ ዝምተኝነት፣ ፈጣንነትም ሆነ ዝግታ፣ ከወንድማማችነት መብት አያስተጓጉሉም፡፡ አንዱ ባህሪ ከሌላው የተሻለ
መብት አይሰጥም፡፡ ጠብ ቢጫር፣ ከፍተኛ አለመግባባት ቢከሰት፣ ሁሉም በእኩልነት በአንድ ደረጃ ላይ ተቀምጠው የወንድማማችነት ሕግ
ይተገበራል፡፡
‫ﭽﯜ ﯝ ﯞ ﯟ ﯠ ﯡﯢ ﯣ ﯤ ﯥ ﯦﭼ الحجرات‬
"ምእመናን ወንድማማቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፤ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን
ፍሩ፡፡" (አል-ሑጃራት: 10)
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በሐዲሳቸው ከመጥፎ ጥርጣሬ አስጠንቅቀዋል፡፡ ጥርጣሬ፥ አርቆ ማሰብ ለማይችል ሰው ተራ ነገር
ልትመስል ትችላለች፤ ሆኖም ላስተዋይ ሰው ልብን ታስደነግጣለች፡፡ የፍቅርን ስሜት ታደርቃለች፡፡
“አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ፡፡ በእርግጥ ጥርጣሬ ትልቅ ውሸት ነው፡፡ አትሰላለሉ፣2 አትፎካከሩ፣ አትመቀኛኙ፣ አትጣሉ፣
አትኳረፉ፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዳዘዛችሁ የአላህ ባሪያ ወንድማማቾች ሁኑ… ሙስሊም የሙስሊም ወንድሙ ነው፡፡ አይበድለው፡፡ እርዳታ
አያቋርጥበት፡፡ አይናቀው፡፡ አንድ ሰው መጥፎ ኃጢአት ውስጥ ለመዘፈቅ ሙስሊም ወንድሙን በንቀት ዓይን ማየት ብቻ ይበቃዋል፡፡
ሁሉም ሙስሊም በሙስሊም ላይ ገንዘቡ፣ ደሙ፣ ክብሩ (ሊነካበት) ክልክል ነው፡፡ በእርግጥ አላህ የናንተን ቅርፃችሁንና ተክለ
ሰውነታችሁን አይመለከትም፡፡ ግን (አላህ) የናንተን ልቦናችሁንና ሥራችሁን ይመለከታል፡፡… አላህን መፍራት እዚህ ጋር ነው፡፡ (ወደ
ልባቸው እየጠቆሙ) አላህን መፍራት እዚህ ጋር ነው፡፡ አላህን መፍራት እዚህ ጋር ነው፡፡ ንቁ! አንዳችሁ በሌላው ገበያ ላይ አይሽጥ፡፡

1
ሲራጥ፥ ከፀጉር የቀጠነ ከሰይፍ የሰላ በጀሀነም ላይ የተዘረጋ ድልድይ ነው፡፡ ሲራጥን ያለፈ ጀነት ይገባል፡፡
2
አንዳችሁ በሌላችሁ ላይ የስለላ ተግባር አይፈፅም
የአላህ ባሪያ ወንድማማቾች ሁኑ፡፡… አንድ ሙስሊም ወንድሙን ከሦስት ቀን በላይ ማኩረፍ አይፈቀድለትም፡፡” (ሙስሊም
ዘግበውታል)
በአላህ መንገድ የተፋቀሩ የኢስላምን አርማ በማንገብ የተዋሃዱ ሰዎች፣ ፍቅራቸው በመዋለድ እንደተገኘ ወንድማማችነት ይሆናል፡፡
ምናልባትም የኢማን ትስስር ከዘር ትስስር በላይ ጥንካሬ ሊኖረው ይችላል፡፡
በእውነቱ ኢስላም የበኩር ልጆቹን የሰበሰባቸው በአላህ መንገድ በተመሰረተ ኢስላማዊ ወንድማማችነት ነው፡፡ ለዚሁ
ወንድማማችነት ኢስላማዊ አገር ተመስርቷል፤ የኢስላምን ባንዲራ ከፍ አድርጓል፡፡ ይህንን ወንድማማችነት ተንተርሰው የአላህ
መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጠንካራ ታጋሽ ሕብረተሰብ መሰረቱ፡፡ ጠላቶቻቸውን የሆኑትን ጣኦት አምላኪዎችን አንበረከኩ፡፡ ከመራራ እልህ
አስጨራሽ ትግል በኋላ ጠንካራ መሰረቶችን አቆሙ፡፡ ብርቱ ማዕዘናትን ተከሉ፡፡ በአንጻሩም ጠላቶቻቸው ተገረሰሱ፤ ተሸነፉም፡፡ ነገሮች
በተቃራኒያቸው የበለጠ ይገለጻሉ፡፡ በክፍለ ዘመናችን አይሁዶች የእነሱን በውሸት ላይ የተመሠረተ ሀገር ለመመስረት ይጥራሉ፡፡ ወደ
ተቀደሰችው ከተማ ከምስራቅም ከምዕራብም ይሰባሰባሉ፡፡ የመጀመሪያ የሀብት፣ የትዝታ፣ የድሎት አገራቸውን ትተው ይነጉዳሉ፡፡ ይህ
በውሸት ላይ የተመሰረተ እምነት (ዐቂዳ) ተልእኮ ከዛሬ 14 ክፍለ ዘመናት በፊት የተከሰተውን ምርጥ የተልዕኮ እንቅስቃሴ
ያስታውሰናል፡፡ ሙስሊሞች ከየቦታው ወደ “የሥሪብ”3 ተመሙ፡፡ ከመጀመሪያው ሀገራቸው የመጀመሪያ የኢስላም ሀገር ለመመስረት
ወደ መረጡት ሀገር ተሰደዱ…

የአንሷሮች እና የሙሃጂሮች ተምሣሌታዊ ወንድማማችነት


መዲና ኢስላምን የታቀፈች ሀገር ናት፡፡ የኢስላምን ቃል ያላቀች፣ ባንዲራ ያውለበለበች ከተማ፡፡ በሀገሬው ሰዎችና ከሌላ ሀገር
በመጡ እንግዶች መካከል በአላህ ላይ የተመሰረተ ፍቅር ልብ ውስጥ ሰርፆ የታየበት፡፡ በሙሉ ፍላጐት የራስን አሳልፎ ለወንድም ማሰብ
የተስተዋለበት፣ ድንቅ ሕዝብ መሰረቱ፡፡ ዘርና ብሄር ላይ ሳይሆን በኢማን ላይ የተመሰረተ ወንድማማችነት ሰፈነ፤ ተመሰረተ፡፡
በወንድማማችነት፣ በፍቅር እና በመከባበር የተዋበ፣ እውነትን የሚያልቅ፣ እርስ በእርሳቸው ባላቸው ግንኙነት ለበጎ ነገር ከፍተኛ ተነሳሽነት
ያላቸው የታላቅ ስብእና ምትሀታዊ ተምሳሌት የሆኑ ሕዝቦች ሆኑ፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‫ﭽ ﯦ ﯧ ﯨ ﯩ ﯪ ﯫ ﯬ ﯭ ﯮ ﯯ ﯰ ﯱ ﯲ ﯳ ﯴ ﯵ ﯶ ﯷ ﯸ ﯹ ﯺ ﯻ ﯼ ﯽﯾ ﭼ الحشر‬
"እነዚያም ከበፊታቸው አገሪቱን መኖሪያ ያደረጉት፣ እምነትንም የለመዱት፣ ወደነርሱ የተሰደዱትን ሰዎች ይወዳሉ፤
(ስደተኞቹ) ከተሰጡትም ነገር በልቦቻቸው ውስጥ ቅሬታን አያገኙም፡፡ በነሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸውም
በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ይመርጣሉ፡፡ የነፍሱንም ንፍገት የሚጠበቅ ሰው እነዚያ እነሱ ምኞታቸውን
አግኚዎች ናቸው፡፡" (አል-ሐሸር፡ 9)
በእምነት ላይ ለአላህ ተብሎ የተመሰረተ ወንድማማችነት፣ እውነተኛ የወንድማማችነት መገለጫ ነው፡፡ ለምትጠፋ ምድራዊ ጥቅም
የምድራዊ ሕይወት አላማን አንግቦ የተመሰረተ ወንድምነት አይደለም፡፡ ኢስላማዊ አስተምህሮዎች ይህን ወንድማማችነት የሚያደፈርስ
የትኛውንም አደጋ ይመክታሉ፡፡ ሙስሊም ወንድሙ ላይ የሚረብሽ አልያም የሚያስደነግጥ ተግባር እንዲፈፅም አይፈቀድም፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አብለዋል፡- “ሙስሊም አንድ ሙስሊምን ማስደንገጥ አይፈቀድለትም፡፡” (አቡ ዳውድ
ዘግበውታል)
በሌላ ዘገባም እንዲህ ብለዋል፡- “አንድ ሙስሊምን ያለአግባብ በሚያስፈራራ እይታ ማየት ይህን ሰው አላህ የቂያማ ዕለት
ያስፈራራዋል፡፡” (ጦበራኒ ዘግበውታል)

አታስቸግር
ሙስሊምን ሊያስቸግር የሚችል ወይም እርሱ ላይ እንደ ጥቃት ሊቆጠር የሚችል ነገር መፈፀም ከባድ ወንጀል ነው፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “ወንድሙን በብረት ያስፈራራ ሰው ማስፈራራቱን እስኪያቆም ድረስ መላእክት
ይረግሙታል፡፡ ወንድምነቱ የአባት የእናቱ እንኳ ቢሆን፡፡”
በእነዚህ ምክሮች ወንድማማችነት ምሉዕ ዋስትና ያገኛል፡፡ በሕብረተሰቡ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት ያስፋፋል፡፡ ኢስላም ይህን
ወንድማማችነት ከሚያጠናክርበት መንገድ አንዱ ኩራትና ጉራን መከላከሉ ነው፡፡ ከአንድ አባት እንደተፈጠሩ፣ የስሜት አንድነት ያላቸው
እንዲሁም በአንድ የሃይማኖት ጥላ ስር ያሉ ሰዎችን የዱንያ ድርሻ ጠላት አታደርጋቸውም፡፡ ክብር በተቅዋ እንደሆነ የሚያውቁ ሰዎች
መካከል፣ ጉራ መቸርቸር ዋጋ የለውም፡፡ አላህን መፍራት ደግሞ በልብ ውስጥ ነው ያለው፡፡ ልበ-ምስጢሯን ከአላህ ሌላ ማንም
አያውቃትም፡፡
3
የሥሪብ፤ የመዲነተል ሙነወራ ቀደምት ስም ነው
ሰይጣን የሚያታልላቸውንና የሚጫወትባቸውን፣ በወንድሞቻቸው ላይ የሚንጠባረሩ፣ በምድር ላይ የበላይነትን የሚፈልጉ ሰዎችን
ኢስላም ማስጠንቀቂያ ሰጥቷቸዋል፡፡ እነዚህ የሚኮፈሱ ሰዎች የቂያማ እለት ይተናሉ፡፡ በተነፋፉበት ልክ ይኮማተራሉ፡፡ በጫማ የሚረገጥ
አቧራ ያክላሉ፡፡
በሐዲሱ እንደተዘገበው “የቂያማ ዕለት ኩራተኞች በሰው ቅርፅ ብናኝ ሁነው ይቀሰቀሉ፡፡ ከየቦታው ውርደት ይከናነባሉ፡፡”

አትሳለቅ
ወንድማማችነት ሌሎች ላይ በመኩራት ይበላሸል፡፡ ንቀት እና ፌዝ ግንኙነትን ይበጥሳሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት ምግባር ድቅድቅ
የመሃይምነት ጨለማና ከከንቱ ዝንጋታ የሚፈጠር ነው፡፡ ደካማ ሰው እገዛ ሊደረግለት ይገባል እንጂ በተንኮል ሊደረስበት አይገባም፡፡
የተምታታበት ሰው መንገድ ይጠቆማል እንጂ አይሳቅበትም፡፡ የማይረባ ሙስሊም ብቻ ነው እንደነዚህ ዓይነት ነገሮችን መሣለቂያ ማሾፊያ
አድርጐ የሚይዘው፡፡
١١ :‫ﭽ ﯨ ﯩ ﯪ ﯫ ﯬ ﯭ ﯮ ﯯ ﯰ ﯱ ﯲ ﯳ ﯴ ﯵ ﯶ ﯷ ﯸ ﯹ ﯺ ﯻ ﯼ ﯽﯾ ﭼ الحجرات‬
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ፤ ከነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ሴቶችም በሴቶች
(አይሳለቁ)፤ ከነሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታነውሩ፤ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፤ ከእምነት
በኋላ የማመጥ ስም ከፋ፤ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነሱ በዳዮቹ ናቸው፡፡"(አል-ሑጅራት፡ 11)
ሐሰን (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፦ “በእርግጥ በሰው ላይ የሚያሾፉ ሰዎች የአኼራ ዕለት ለአንዳቸው የጀነት በር ይከፈትለታል፡፡
ከዚያም ግባ ይባላል፡፡ ተጨንቆና ተጠቦ ይመጣል፡፡ ልክ ሲመጣ በላዩ ላይ ይዘጋበታል፡፡ ከዛም ሌላ በር ይከፈትለታል፡፡ ግባ ግባ
ይባላል፡፡ ተጨንቆና ተጠቦ ሲመጣ በላዩ ላይ በሩ ይዘጋበታል፡፡ …በዚህ ሁኔታ እንደቀጠለ ለአንዳቸው ከጀነት በር ይከፈትለትና ግባ፥
ይባላል፡፡ ተስፋ ከመቁረጡ የተነሣ አይመጣም፡፡” (በይሀቂ ዘግበውታል)
ይህ የአላጋጮች ምንዳ ነው፡፡ ይህቺ ቅጣት ልክ የተወነጀለው ወንጀል ዓይነት ናት፡፡ አሿፊዎችን ትኮረኩማለች፡፡ የሚሠሩትን ሥራ
ታስታውሳቸዋለች፡፡

የሰው ልጅ እኩልነት
ኢስላም አጠቃላይ ወንድማማችነትን ከሚጠብቅባቸው፥ ሰው ሠራሽ ጠቦችን ከሚያጠፋባቸው መንገዶች ውስጥ የዘር እኩልነትን
ማረጋገጡ ይጠቀሳል፡፡ የመብት አጠቃላይነትንና እኩልነትን ያውጃል፡፡ ሕብረተሰብን መናቅና በዘር መፎካከር ከንቱ ነገር መሆኑን
እንዲገነዘቡና እንዲሰማቸውም ያደርጋል። ምክንያቱም የአደም አባትነት የሁሉንም ማንነት በድንቅ ሁኔታ ሰብስባዋለች፡፡ አንዱ ሌላውን
ለራሱ በተጐናፀፈው የጥረት ውጤት እንጂ በላጭ አይሆንም፡፡
አቡ ሁረይራህ እንዳስተላለፉት፤ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “የቂያማ ዕለት ሲሆን አላህ ተጣሪ እንዲጣራ
አዘዘ፡፡ አዋጅ፤ እኔ ዘር (ፈጠርኩ) አደረኩ፡፡ እናንተም ዘር አደረጋችሁ፡፡ እኔ በላጫችሁን ከእናንተ አላህን የሚፈራ አደረግኩ፡፡ እናንተ
ግን እንዲህ ካልሆነ አሻፈረኝ አላችሁ፡፡ “እገሌ የእገሌ ልጅ (ትላላችሁ)፤ እኔ ዛሬ (ለተቅዋ) የእኔን የዘር ሚዛን ብልጫውን ሰጥቻለሁ፡፡
የእናንተን የዘር ሚዛን ውድቅ አድርጊያለሁ፡፡” (በይሀቂ ዘግበውታል)
ይህ የአላህ (ሱ.ወ) ንግግርን አረጋግጦ የመጣ ነው፡-
:‫ ﰀ ﰁ ﰂ ﭼ المؤمنون‬O‫ ﯾ ﯿ‬O‫ ﯨ ﯩ ﯪ ﯫ ﯬ ﯭ ﯮ ﯯ ﯰ ﯱ ﯲ ﯳ ﯴ ﯵ ﯶ ﯷ ﯸ ﯹ ﯺ ﯻ ﯼ ﯽ‬O‫ ﯦ ﯧ‬O‫ﭽ‬
١٠٣ - ١٠١
"በቀንዱም በተነፋ ጊዜ፣ በዚያ ቀን በመካከላቸው፣ ዝምድና የለም፤ አይጠያየቁምም፡፡ ሚዛኖቹም የከበዱለት ሰው፣
እነዚያ እነሱ ፍላጐታቸውን ያገኙ ናቸው፡፡ ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰው፣ እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን
ያከሰሩ ናቸው፤ በገሀነም ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡" (አል-ሙእሚኑን: 101-103)
የዐረቦች ባህል አስቀያሚነት በዘር መኩራራት፣ በአባት ተመክቶ ሌላውን ማናናቅ ላይ የተመሠረተ መሆኑ ነው፡፡ በሕብረተሰቡ
ውስጥ ኢስላማዊ ትምህርት ቢኖርም አልተለወጡም፡፡ ይህም የሆነው በአለፈው ታሪካችንና በአለንበት ዘመን የመጣ አደገኛ አለመግባባት
ውጤት ነው፡፡ ኢስላማዊ አስተምህሮት፣ በተከታዮቹ መካከል አገራቸው ቢራራቅም፣ ጐሣቸው ቢለያይም ወንድማማችነታቸው
መጠበቅ አለበት ይላል፡፡ ዘረኝነትን፣ ጐጠኝነትን እና ዜግነታዊ ጥላቻን መቅበር እንዳለባቸው ያስተምራል፡፡ አንድ ሰው ሀገሩንና ወገኑን
መውደዱ ተፈጥሯዊ ስሜት ነው፡፡ ሆኖም ይህ ውዴታ ሰውዬው ጌታውን፣ ፍጡራኑንና ወንድሞቹን ሊያስረሳው አይገባም፡፡ የአላህ
መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “ከናንተ ውስጥ በላጩ ወንጀል ውስጥ ሳይገባ ለወገን የሚታገል ነው፡፡” (አቡዳውድ ዘግበውታል)
እንዲህ ተብለው ተጠየቁ “ዘረኝነት ምንድን ነው?” ሲመልሱም “ወገንህን በጥፋት ላይ መርዳት ነው አሉ፡፡” (አቡዳውድ
ዘግበውታል)
በኢስላም ወንድማማችነት ማለት ለኢስላም ብቻ መኖር፣ በመንገዱም ላይ መጓዝ፣ በትዕዛዛቱም መሥራት ነው፡፡ በሕብረተሰብም
ሆነ በግለሰብ ደረጃ የኢስላምን ትዕዛዝ ማስቀደም፡፡ የሚገጥምህን ችግር እንዴት በኢስላማዊ ጎዳና እንደምትወጣው ማሰብ፡፡ ከዚህ ሌላ
ላሉ ጩኸቶችና ጥሪዎች ጀርባ መስጠት ነው፡፡
አንድነት
ኢስላም ግለሰብን ከማኅበራዊ ሕይወት አካል ገንጥሎ አያየውም፡፡ ግለሰብ የማሕበረሰብ አካል ነው፡፡ የአካል ክፍል ከሰው
ተገንጥሎ ህልውና እንደማያገኝ ሁሉ ግለሰብም ከሕብረተሰብ ተነጥሎ ጤናማ ህልውናው አይረጋገጥም፡፡
በእርግጥ መለኮታዊ ትእዛዛት ይህንን እውነታ ይመክራሉ፡፡ ‹‹አድርግ›› ‹‹አታድርግ›› የሚሉ ትዕዛዛት ለግለሰብ ብቻ አልወረዱም፡፡
አላህ (ሱ.ወ) መላውን ሕብረተሰብ በማረቅና አቅጣጫ በማስያዝ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡ ለሁሉም በሚተላለፈው ትምህርት ግለሰቡ
ያዳምጣል፤ ምክር ይወስዳል፡፡ በዚህ መልኩ በቁርኣንና በሐዲስ ያሉ ሸሪዓዊ ትእዛዛት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
‫ﭽ ﮕ ﮖ ﮗ ﮘ ﮙ ﮚ ﮛ ﮜ ﮝ ﮞ ﮟ ﮡ ﮢ ﮣ ﮤ ﮥ ﮦﮧ ﯴ ﭼ الحج‬
"እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! (በስግደታችሁ) አጎንብሱ፤ በግንባራችሁም ተደፉ፤ ጌታችሁንም ተገዙ፤ በጎንም ነገር
ሥሩ፤ ልትድኑ ይከጀልላችኋልና፤ በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ፡፡" (አል-ሐጅ፡ 77-78)
አንድ የአላህ ባሪያ አላህን ለማምለክ፣ ለእርሱ ለማጐብደድ እና እርሱን ለማናገር ሲቆም፣ ከምላሱ የሚወጣው መለኮታዊ ንግግር፣
ከወንድሞቹ የተገነጠለ ባሪያ ሆኖ አይደለም፡፡ ትስስርና ቀጣይነት እንዳለው ስብስብ እንዲህ ይላል፡-
٥ :‫ﭽ ﭢ ﭣ ﭤ ﭥ ﭼ الفاتحة‬
“አንተን ብቻ እንግገዛለን፡፡ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡” (አል-ፋቲሐ፡ 5)
‹‹አንተን ብቻ አመልካለሁ በአንተም ብቻ እታገዛለሁ›› አይልም፡፡
ከዚያም አላህ ቅኑን መንገድ እንዲመራው፤ ጥሩ እንዲለግሰው ሲጠይቅ ለራሱ ብቻ አይጠይቅም፡፡ የአላህ እዝነት ለራሱ ለሌችም
እንዲዳረስ ይጠይቃል፡፡ እንዲህ ይላል፡-
٧ - ٦ :‫ﭽ ﭧ ﭨ ﭩ ﭪ ﭫ ﭬ ﭭ ﭮ ﭴ ﭼ الفاتحة‬
"ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡ የነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና
ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ) ፡፡" (ፋቲሀ፡ 6-7)
አላህ (ሱ.ወ) ሰዎችን እንዲለያዩና እንዲበታተኑ አልፈጠራቸውም፡፡ በእርግጥ ለነሱ አንድ ሃይማኖት ደነገገላቸው፡፡ ሰዎችን በሙሉ
በአንድ ጐዳና ላይ እንዲያስጉዙ ብዙ ነቢያትን (ዐ.ሰ) ላከ፡፡ በሃይማኖት አልታዘዝም በማለት በሃይማኖት ስምም እንዳይለያዩና
እንዳይጻረሩ ቀድሞውኑ ከለከለ፡፡
ግና ከንቱ ስሜታዊነታቸው ይህን ምርጥ ምክር አስረሳቸው፡፡ ለዚህ መለኮታዊ ሀብት ጆሮ ዳባ ልበስ አሉ፡፡ ሰዎች ተለያዩ፡፡ ሰዎች
በሌሎች ላይ ተንኮልና ክፋት ማሴር ያዙ፡-
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-
‫ﭽ ﮡ ﮢ ﮣ ﮤ ﮥ ﮦ ﮧﮨ ﮩ ﮪ ﮫ ﮬ ﮭ ﮮ ﮯ ﮰ ﮱ ﯓ ﯔ ﯕ ﯖ ﯗ ﯘ ﯙ ﯚ ﯛﯜ ﯝ ﯞ ﯟ ﯠ ﯡ ﯢ ﯣ ﯤ ﯥ ﯦ ﯧ ﯨ ﭼ المؤمنون‬
"እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ ፤ በጎ ሥራንም ሥሩ፤ እኔ የምትሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ
ነኝ። ይህችም (በአንድ አምላክ የማመን ሕግጋት) አንድ መንገድ ስትኾን፣ ሃይማኖታችሁ ናት፤ እኔም
ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ፤ (ከዚያ ተከታዮቻቸው) የሃይማኖት ነገራቸውንም በመካከላቸው ክፍልፍሎች
አድርገው ቆራረጡ፤ ሕዝብ ሁሉ እነሱ ዘንድ ባለው ሃይማኖት ተደሳ Ë ች ናቸው፤ እስከ ጊዜያቸውም
ድረስ፣ በጥመታቸው ውስጥ ተዋቸው፡፡" (አል-ሙእሚኑን፡ 51-54)

ስሜታዊነት የክፍፍል ምንጭ ነው


አላህ (ሱ.ወ) ሰፊ ጥላቻ ላይ የተመሠረተ ክፍፍል፣ ስሜትን መከተልና ድንበርን መጣስ መሆኑን ገልጿል፡፡ እርግጥ ነው እውቀት
ከሰው ሲጠፋ፣ ለአላህ ፍቅር ብቻ መሆን ሲሳነው፣ ሰውየው ላይም ሆነ ሰዎች ላይ አደጋ ይፈጠራል፡፡ በእርግጥ ሰዎች ሃይማኖት
ከመምጣቱ በፊት መሃይምነትና ወንጀል ያጠማቸው ነበር፡፡ ኃይማኖት ሲመጣ የኃይማኖቱን እውቀት የተወሰኑ መናጢዎች
ተቆጣጠሩት፡፡ በእውቀቱ ለራሣቸው ለግል ጥቅማቸው ነገዱበት፤ አታለሉበት፡፡ ብዙሃኑ ሕብረተሰብ በከንቱ መንገድ ላይ ዋለለ፡፡
በእርግጥ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከማይጠቅም እውቀት አላህ እንዲጠብቃቸው ዱዓ ያደርጉ ነበር፡፡ እንዲህ አሉ፦ “እኔ
ለእናንተ እፈራለሁ፡፡ ከእኔ በኋላ የምፈራላችሁ ነገር ውስጡና ውጩ የተለያየ (የሙናፊቅ) ምላስ ነው፡፡” (አል-በዛር ዘግበውታል)
እርግጥ ነው፡፡ መጥፎ ልብ እውቀቱን በጥፋት ተልዕኮ ይሰማራበታል፡፡ ዓለም በፊትም አሁንም በዚህ አውዳሚ እውቀት መከራዋን
አይታለች፡፡ ምሁራን በክፉ ምላሳቸው የሰው ልጅን አንድነት እንደበታተኑት ቁርኣን ነግሮናል፡-
‫ﭽ ﭺ ﭻ ﭼ ﭽ ﭾ ﭿ ﮀ ﮁ ﮂ ﮃ ﮄ ﮅ ﮆ ﮇ ﮈ ﮉ ﮊﮋ ﮌ ﮍ ﮎ ﮏ ﮐ ﮑﮒ ﮓ ﮔ ﮕ ﮖ ﮗ ﮘﮙ ﮚ ﮛ ﮜ ﮝ ﮞ ﮟ ﮠ ﮡ ﮢ ﮣ‬
١٤ - ١٣ :‫ﮤ ﮥ ﮦ ﮧ ﮨ ﮩ ﮪ ﮫ ﮬ ﮭﯥ ﭼ الشورى‬
"ለናነተ ከሃይማኖት ያንን በርሱ ኑሕን ያዘዘበትን፥ ደነገገላችሁ፤ ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን፣ ያንንም በርሱ
ኢብራሂምን፣ ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን፣ ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ፣ በርሱም አትለያዩ፣ ማለትን
(ደነገግን)፤ በአጋሪዎቹ ላይ ያ ወደርሱ የምትጠራቸው ነገር ከበዳቸው፤ አላህ የሚሻውን ሰው ወደርሱ
(እምነት) ይመርጣል፤ የሚመለስንም ሰው ወደርሱ ይመራል፡፡ (የሃይማኖት ሰዎች) ዕውቀቱም
ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ለምቀኝነት እንጂ ለሌላ አልተለያዩም፡፡" (አሽ-ሹራ፡ 13-14)
አላህ በሌላ ምዕራፍ እንዲህ አለ፡-
‫ﭽﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﭼ‬
"በርሱም (በሃይማኖት) ግልጽ አስረጂዎች ከመጡላቸው በኋላ በመካከላቸው ለኾነው ምቀኝነት
እነዚያው የተሰጡት እንጅ አልተለያዩበትም፤" (አል-በቀራ፡ 213)

እውቀት ለበጎ ካልዋለ


እውቀት ለአላህ ፍቅር ብቻ ሁኖ ካልተገበየ፣ ለአላህ ፍጡራን ማዘን ካልተቻለ፣ በጣም አደገኛ እሣትን ይፈጥራል፡፡ አላህ
እንዲቀጠል ያዘዘውን ዝምድና ይቆርጣል፡፡ ልዩነትን እና ክፍፍልን ያነግሳል፡፡
የግንዛቤ ልዩነትና የርዕይ መራራቅ ለሕይወት አዲስ አይደለም፡፡ ሆኖም ይህ ለጥላቻና ለመቆራረጥ ሰበብ አይደለም፡፡ የጥላቻ
ምክንያት ሌሎች መነሻዎች አሉት፡፡ ውስጣዊ ስሜትን ለመተንፈስና ለማርካት የአመለካከትና የአስተሳሰብ ልዩነት እንደመሣሪያ
ይጠቅማል፡፡ ከዚህም ሌላ እውነትን ለመፈለግ ነው በሚል ፈሊጥ፣ እውነትን አሻፈረኝ ብሎ ሙግት ውስጥ መወሸቅ፣ እንዲሁም ምንም
ዓይነት የእውቀት ጭብጥ የሌለው መሰረት የለሽ ንትርክ ማካሄድ አግባብ አይደለም፡፡
በእርግጥ ከንቱ ነጥቦች ታላላቅ አለመግባባቶችን መፍጠራቸውን ተመልክተናል፡፡ በመሰረቱ ይህ አለመግባባት ከፖለቲካዊ ጥቅም
ጋር ስለተሣሰረ ነው፡፡ ስውር ጥቅምን አንግቦ ወደ ውይይትና ክርክር ካልተገባ ግን በከባባድ ጉዳዮች ላይ አለመግባባቶች ከመነሻው
ይቀበራሉ፡፡ ሰዎች ከአመለካከት ልዩነት ጋር ያለምንም ችግር ይኖራሉ፡፡ ምክንያቱም የዚህ ልዩነት ውጤት ንጹህ ኀልዬት (theory)
ነው፡፡
ከንቱ መነሻ ያላቸው አለመግባባትን የሚፈጥሩ ነጥቦች፥ የአላህን ሃይማኖት እና የሰዎችን ምድራዊ ሕይወት ቅርቃር ውስጥ
ይከቱታል፡፡ ስለዚህም ኢስላም ይህንን ክህደት ግፍ አድርጐ ቆጠረው፡፡
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-
١٥٩ :‫ﭽ ﭹ ﭺ ﭻ ﭼ ﭽ ﭾ ﭿ ﮀ ﮁ ﮂﮃ ﮄ ﮅ ﮆ ﮇ ﮈ ﮉ ﮊ ﮋ ﮌ ﭼ األنعام‬
"እነዚያ ሃይማኖታቸውን የለያዩ አሕዛብም የኾኑ በምንም ከነሱ አይደለህም፤ ነገራቸው ወደ አላህ ብቻ
ነው፡፡ ከዚያም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡ " (አል-አንዓም፡ 159)
አላህ ሙስሊሞች ከነርሱ በፊት እንደነበሩ ሕዝቦች እንዳይለያዩና እንዳይሰነጣጠሩ፣ ግንዛቤያቸው ስለተለያዩ ብቻ፣ በጥላቻና
በመናናቅ ላይ የተመሰረቱ የተለያዩ ቡድኖችን እንዳያቋቁሙ ከልክሏቸዋል፡፡
‫ ﯦ ﯧ ﯨ ﯩ ﯪ ﯫ ﯬ ﯭ ﯮ ﯯ ﯰ‬O‫ ﯤ ﯥ‬O‫ ﯟ ﯠ ﯡ ﯢ ﯣ‬O‫ ﯝ ﯞ‬O‫ ﯛﯜ‬O‫ ﮮ ﮯﮰ ﮱ ﯓ ﯔ ﯕ ﯖ ﯗ ﯘ ﯙ ﯚ‬O‫ ﮦ ﮧ ﮨ ﮩ ﮪ ﮫ ﮬ ﮭ‬O‫ﭽ‬
١٠٧ - ١٠٥ :‫ﯱ ﯲ ﯳ ﯴ ﭼ آل عمران‬
"እንደነዚያም ግልጽ ታምራት ከመጣላቸው በኋላ እንደ ተለያዩትና እንደ ተጨቃጨቁት አትኹኑ፤ እነዚያም
ለነርሱ ታላቅ ቅጣት አላቸው። ፊቶች የሚያበሩበትን፣ ፊቶችም በሚጠቁሩበትን ቀን (አስታውስ)፤ እነዚያ
ፊቶቻቸው የጠቆሩትማ፣ ከእምነታችሁ በኋላ ካዳችሁን? ትክዱት በነበራችሁት ነገር ቅጣቱን ቅመሱ፡፡
(ይባላሉ)፡፡ እነዚያም ፊቶቻቸው ያበሩትማ፣ በአላህ ችሮታ (ገነት) ውስጥ ናቸው፤ እነርሱ በውስጧ
ዘውታሪዎች ናቸው፡፡" (አል-ኢምራን፡ 105-107)
የቀልብና የስሜት ውህደት፣ እንዲሁም የአላማና የስልት አንድነት፣ የኢስላም ቁልጭ ያለ አስተምህሮት ውጤት ነው፡፡ ለአላህ ብቻ
የሚኖሩ ሙስሊሞችም መገለጫ ነው፡፡
በአንድ መሠረታዊ ዓላማ ስር መሰባሰብና የስልት ውህደት ሁለቱ የሕዝብ ብርታት ጠንካራ መሠረት ናቸው፡፡ የሀገርም ጥንካሬ
መለኪያ ናቸው፡፡ የተልዕኮ ውጤታማነትን ያሳያል፡፡ ተውሒድ (አሃዳዊ አምልኮ) የኢስላም በር መግቢያ ነው፡፡ በእርግጥ ተውሒድ
የኢስላም ቀጣይነት፣ በእሱም ፀንቶ የመኖር ምስጢር ነው፡፡ አላህ ጋር በሚያበራ ፊትና በጠራ ዒባዳ ለመገናኘት ዓይነተኛ ዋስትና ነው፡፡

በቡድን የሚሠራ ሥራ
የአንድ ሥራ ጭብጥ ይዘት፣ አንድ ሰው ለብቻው ሲሠራውና ከሌሎች ጋር ሲሠራው ከፍተኛ ልዩነት አለው፡፡ የሱብሒ ሁለት
ረከዓ ሰላት ወይም የዙህር ሰላት ምንም ሳይጨመርባት፥ በተናጥል ከሚፈጽማት፥ በስብስብ (ጀመዓ) መስገዱ ከሃያ አምስት በላይ ምንዳ
ወይም ከዚህ በላይ እጥፍ ይጨምርለታል፡፡ ይህ የሚሆነውም ሰውዬው ከሌሎች ጋር ሆኖ አላህ (ሱ.ወ) ፊት ስለቆመ ነው፡፡ ይህ
ከፍተኛ ማነሳሻ ነው፡፡ ብቸኝነትን አሽቀንጥሮ ስብስብ ውስጥ መጠቃለል፡፡ ኢስላም ሰውን ከነጠላነት አውጥቶ ወደ ሕብረተሰብ
መቀላቀል አንዱ ዓላማው ነው፡፡ ሙስሊም በራሱ ዓለም ተተብትቦ፣ በአስተሣሰቡም በስሜቱም አውሬ መሆንን እንዲሁም የራሱን
ጥቅም እያሣደደ የብዙሀኑን ጥቅምና ህልውና መፈታተን ኢስላም አጥብቆ ያወግዛል፡፡
በሐዲስ እንዲህ ተብሏል “…ሦስት (ነገሮች) የሙእሚን ሰው ቀልብ ውስጥ አይጠፉም፡፡ ሥራን ለአላህ ብቻ ብሎ መሥራት፡፡
ለሙስሊም መሪዎች ምክር መለገስ፡፡ ከእነርሱ (ከሙስሊሞች) ስብስብ ሙጥኝ ማለት…” (አልበዛር ዘግበውታል)

ጀመዓ ሰላት የአንድነት እርሾ ነው


አንድ ሙስሊም ከሚኖርበት ማኅበረሰብ ጋር በደንብ እንዲዋሃድ አላህ በየቀኑ የሚሰገድ ሰላት ደነገገ፡፡ ሰዎች ተሰብስበው
እንዲሰግዱ ብዙ ጊዜም መስጂድ እንዲጓዙ ጥሪ ቀረበ፡፡ በተጨማሪም የአንድ መንደር ወይም አካባቢ ሰዎች በየሣምንቱ ለጁሙዓ ሰላት
መገናኘትን ግዴታ አደረገ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ወደ ታላቅ የዒድ ሰላት ስብሰባ ተጠራ፡፡ ቦታውም ሰፊ አውላላ ሜዳ ላይ እንዲሆን
ተደረገ፡፡ ወንዶችም ሴቶችም (ሴቶች የማይሰግዱበት ምክንያት ቢኖራቸውም) እንዲገኙ መልዕክት ተላለፈ፡፡ ጥቅሙን ለማብዛት ኸይር
ሥራ ለመጨመር፡፡

ሐጅ የህብር መገለጫ
ከዚህም በላይ በጣም ታላቅ ወደሆነ ከምስራቅም ከምዕራብም የተበተነውን ሁሉ አንድ ወደሚያደርግ ስብስብ ተጠራ፡፡ ሐጅ
ግዴታ ተደረገ፡፡ ለዚህ ስራም የታወቀ ቦታ ተደረገለት፡፡ የታወቀ ጊዜም እንዲሁ፡፡ የተለያዩ ዘርና ቀለም ያላቸው ሙስሊሞች
መገናኘታቸው የማይቀር ግዴታ ሆነ፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የመገንጠልና የመነጠል አደገኛነትን በከፍተኛ ሁኔታ አስጠነቀቁ፡፡
ከሀገር ሀገር ሲወጡም ሆነ በሀገር ውስጥም ሆነው አንድነትንና መሰባሰብን ይመክሩ ነበር፡፡
ሰዕድ ኢብን ሙሰየብ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “ሸይጧን በአንድ ወይም
በሁለት(ሰዎች) ላይ ተንኮል ያስባል፤ ሦስት ከሆኑ (ተንኮል) አያስብባቸውም፡፡” (ማሊክ ዘግበውታል)
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በአንድ ጉዟቸው ላይ መንገደኞቹ ለእረፍት ወዲያና ወዲህ ተለያይተው ምንም የሚያስተሳስራቸው ነገር ያለ
በማይመስል ሁኔታ ተመለከቷቸው፡፡ ይህ ሁኔታ ስላላስደሰታቸው ገሰጿቸው፡፡
አቢ ሠዕለባ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፣ ሰዎች አንድ ቦታ ሲያርፉ በሸለቆና ተራራ ይበታተናሉ፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)
እንዲህ አሉ፡- “ይህ መበታተናችሁ የሰይጣን (ሴራ) ነው፡፡” ከዚህ በኋላ ሁሉም እርስ በእርስ፣ አንድ ልብስ ቢዘረጋላቸው ያዳርሳቸዋል
እስኪባል ድረስ ተቀራረቡ፡፡ (አቡዳውድ ዘግበውታል)
ፍቅርን መለዋወጥ፣ የመስመር አንድነት፣ የስሜት ውህደት፣ ውጤት ነው፡፡ በእርግጥ ሰዎችን እውነት ካልሰበሰባቸው፣ ውሸት
ይሰነጣጥራቸዋል፡፡ አር-ረሕማንን ማምለክ ካላዋሃዳቸው፣ ሸይጣንን መታዘዝ ይበታትናቸዋል፡፡ የመጭው ዓለም ፀጋ ካላጓጓቸው፣
ለዱንያ ጥቅማጥቅም ይጫረሳሉ፡፡ ስለዚህም መራራ ፍጭት የጨለማ መሃይምነት መለያ ነው፡፡ ኢማን የሌላቸው ሰዎች መገለጫ ነው፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “ከኔ በኋላ በከሀዲነት አፈንጋጭ እንዳትሆን፡፡ (ማለትም) አንዳችሁ የአንዳችሁን
አንገት እንዳይመታ፡፡” (ቲርሚዚ ዘግበውታል)
ይህ ደም አፍሳሽ ጦርነት እርስ በርሳቸው በቡድን የሚከፋፈሉ ከሐዲያን ባህሪ ነው፡፡

የአስተሳሰብ ልዩነት
በግንዛቤ ልዩነት ለሚመጣ የአስተሳሰብ አንድ አለመሆን ኢስላም ለዘብተኛ አቋም አለው፡፡ አመለካከቱ ስህተት ለሆነ አንድ ምንዳ
ይሰጠዋል፡፡ አመለካከቱ ትክክል ለሆነ ሁለት ምንዳ ይሰጠዋል፡፡ በኢስላም ሰፊ ሃይማኖት ውስጥ ሁሉንም ሰበሰባቸው፡፡ እውነትን
ለመፈለግ፣ ለማወቅና ለመተግበር ደፋ ቀና ብለዋልና፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “መሪ ተግቶ፣ ጥሮ ትክክል ከሆነ፣ ሁለት አጅር አለው፡፡ ተግቶ ጥሮ ከተሣሣተ፣
አንድ አጅር አለው፡፡” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
በሰዎች መካከል በምርምርና ጥናት (ኢጅቲሃድ) ላይ ተመስርቶ ሊፈጠር የሚችል የሃሳብ ልዩነት ተፈጥሯዊ የሆነ የአዕምሮ ፍሬ
ነው፡፡ ውስጣዊ ዓላማው በንጹህነት እና በቅንነት ላይ የተመሠረተ እውነትን ፍለጋ እስከሆነ ድረስ የአላህ እዝነት ታሳስበዋለች፡፡
ለምንድን ነው አላህ (ሱ.ወ) ሰፊ ያደረገውን ዲን የሰው ልጅ ጥብብ የሚያደርገው? ይህ በመካከላቸው ያለ መጨካከንና ግትርነት ለምን
ይሆን?
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከመዲና የሚወጡ ሙጃሂዲን የዐስር ሰላትን በኒ ቁረይሽ እንጂ እንዳይሰግዱ ባዘዙበት ጊዜ፣ ከፊሎቹ
ይህ የተባለው ጊዜው ሣያልፍ ከሆነ ብቻ ነው ብለው መንገድ ላይ ሰገዱ። ሌሎቹ ደግሞ እንደተባለው ማድረግ አለብን ብለው አስርን
በጨለማ ሰገዱ፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የሁለቱንም ግንዛቤ ተቀበሉ፡፡ ከዚያም አንድ ተርታ ተደርድረው በአንድ ጦር ተሰልፈው
ተዋጉ፡፡
እውቀት ላይ የተመሰረተን ልዩነት ለማስታረቅ ኢስላማዊው መንገድ ሰፊ ነው፡፡ በዚህም መንገድ አእምሮና ልቦና ቀጥ ሲል
መስተካከሉ አይቀርም፡፡ አለመግባባት፣ ምድራዊ ጥቅምን ለማሳደድ፣ እንደ ሽፋን ሲያገለግል፣ ድርቅና ክፋት ቦታውን ይይዛል፡፡ በዚህ
ጊዜ ምድራዊ ጥቅምም ይበላሻል፡፡ ከሁሉም በፊት ግን ዲን ይናዳል፡፡
አንድ ሸይኽ እንዲህ ተባሉ፡- “መስጂድ ለሚሰግዱ ሰዎች ድረስላቸው፡፡ ሊደባደቡ ነው፡፡” ‹‹በምን የተነሣ?›› አሉ፡፡ “ግማሾቹ
የተራዊሕ ሰላትን 8 ረከዓ መስገድ ይፈልጋሉ፡፡ ከፊሎቹ ደግሞ 20 ረከዓ መስገድ ይፈልጋሉ›› ተባሉ ‹‹ስለዚህ ምን ይሁን?›› አሉ፡፡
“የእርስዎን ብይን (ፈትዋ) እየጠበቁ ነው” ተባሉ፡፡ እንዲህ አሉ፦ “የኔ ብይን መስጂዱ ይዘጋ የሚል ነው፡፡ ተራዊሕ ከነጭራሹ
አይሰገድበት፤ ምክንያቱም የ(ተራዊህ) ሰላት ግዴታ አይደለም፡፡ የሙስሊሞች አንድነት ግን ግዴታ ነው፡፡ ግዴታ ያልሆነ ነገር ግዴታን
ሊያወድም አይገባም፡፡” በእርግጥ ለአላህ ብቻ ሲሉ መኖር፣ ለዲን ሲባል ለሕዝብ ምክር መለገስ፣ ከእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ከሚፈጠር
መበጣበጥና መራበሽ ማራቅ መቻል አለበት፡፡
ከኢስላም አስምህሮት ጋር ስንጓዝ ሕዝብን ከሚያበጣብጡ መንገዶች መራቅ አንዱ ትምህርት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ አንድ መጥፎ
ተግባርን መለወጥ ግዴታ የሚሆነው ያንን ለመለወጥ በሚደረግ ሙከራ ከባድ ጥፋት የሚከሰት ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ቀላሉን ጐጂ በግድ
እንመርጣለን፡፡ ሐኪምን ተመልከት፡፡ ይህ ሰው ቀዶ ህክምና የሚያደርገው አካሉ እንደሚችል ካረጋገጠ ብቻ አይደለምን?በሽታው
ባይለቅም እንኳ፡፡ በሕይወት ላይ አደጋ ያመጣል ካለ ይቆማል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የመዲና ሰዎችን ቃል ያስገቧቸው ነበር
“ለመስማት፣ ለመታዘዝ፣ ሲከብድም ሲቀልም፡፡ ንቃት ጊዜም፣ መጫጫን ላይም፡፡ ራሳችን ላይም (በመፍረድ) ቢሆን…” (ሙስሊም
ዘግበውታል)
ጥሩ ሰው ምድራዊ ድርሻውን ስላጣ ከመልካም ነገር እምቢኝ ሊል አይገባም፡፡ ስልጣን ለርሱ ባይሰጠው፣ ቢዘነጋ፣ ዱንያዊ
ድርሻው ሲወሰን ቢያንስበት፣ አድማሱን በጩኸት ኡኡታ ሕይወቱንም በቁጭት ሊሞላው አይገባም፡፡ ለምድራዊ ሕይወት
መብከንከን፣ በሥነ-ልቦና መናጋት፣ አላህ በቁርኣን ላይ የገለጻቸው የእነዚያ ሙናፊቆች ባህሪ ነው፡-
٥٨ :‫ﭽ ﭻ ﭼ ﭽ ﭾ ﭿ ﮀ ﮁ ﮂ ﮃ ﮄ ﮅ ﮆ ﮇ ﮈ ﮉ ﮊ ﭼ التوبة‬
"ከነሱም ውስጥ በምጽዋቶች የሚዘልፉህ ሰዎች አልሉ፡፡ ከርሷም (የሚሹትን) ቢስሰጡ ይደሰታሉ፤
ከርሷም ባይስሰጡ እነሱ ያን ጊዜ ይጠላሉ፡፡" (አት-ተውባህ፡ 58)

ልዩነቶቻችን ዓለማዊ ናቸው


ብዙ ክፍፍሎችና ስንጥርጥሮች መነሻቸውን በአትኩሮት ብትመለከት፥ የጠቡ ምንጭ የምድራዊ ሕይወት ፍቅር እንደሆነ እርግጠኛ
ትሆናለህ፡፡ አንድነት ኃይል ነው። ይህ ለሰዎች ብቻ አይደለም፡፡ የፍጥረተ ዓለሙ (Universe) ሕግ ነው፡፡ የማይረባ ክር ከተፈተለ ጠንካራ
ገመድ ይሆናል፡፡ ከባድ ነገሮችን ይጐትታል፡፡ ይህ ትልቅ ዓለም የብናኝ ስብስብ ውጤት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
አንድ ጥበበኛ ሰው ሊሞት ሲል ልጆቹን ይህን የአንድነት ትምህርት አስተማራቸው፡፡ ስንጥሮችን አንድ ላይ አስሮ ሰጣቸው፡፡
መስበር ተሳናቸው፡፡ ስንጥሩ ተፈታ፡፡ ለየብቻ ሆነ፡፡ አንድ ባንድ ተሰበሩ፡፡
ቀስቷን ተመልከቱ ብቻዋን አርጋችሁ፣
ተሰባሪነቷን ከአስተነተናችሁ፣
ስብስብ ሲፈጥሩ ቻሉ ጠነከሩ፣
ስብራትም የለ ቻሉና በገሩ፡፡
ጭቅጭቅ ጠንካራ ሕዝብን ያዳክማል፡፡ ደካማ ሕዝብን ይቀብራል፡፡ ስለዚም አላህ መጀመሪያ ለሙስሊሞች ይህን አጥፊ ነገር
እንዲያስወግዱ መከራቸው፡፡ የበድር ጦርነትን ካሸነፉ በኋላ አንድነታቸውን እንዲጠብቁ ጉዳያቸውን ለማሳካት በሚያደርጉት ጥረት
ሁሉ እርስ በርስ በመመካከር እንዲያደርጉም አሳሰባቸው፡፡
ልቦናዎች የምርኮ ገንዘብ ለማግኘት ሲጓጉ፣ ድርሻዎቻቸውን ለማግኘት ሲባዝኑ፣ ለመከፋፈል ሲሽቀዳደሙ የአላህ ንግግር ወረደ፦
١ :‫ﭽ ﭑ ﭒ ﭓﭔ ﭕ ﭖ ﭗ ﭘﭙ ﭚ ﭛ ﭜ ﭝ ﭞﭟ ﭠ ﭡ ﭢ ﭣ ﭤ ﭥ ﭼ األنفال‬
"ከጦር ምርኮ ገንዘቦች ይጠይቁሃል፤ ምርኮ ገንዘቦች የአላህና የመልክተኛው ናቸው፤ ስለዚህ አላህን ፍሩ፤
በመካከላችሁ ያለችውንም ኹኔታ አሳምሩ፤ አማኞችም እንደኾናችሁ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ
በላቸው፡፡" (አል-አንፋል፡ 1)
በአላህ መንገድ ላይ በአንድነት መታገል እና እንድ መሆን፥ ህዝብ በጠላቶቹ ዘንድ እንዲፈራ የሚያደርገው ኃይል ነው፡፡
٤٦ :‫ﭽ ﭑ ﭒ ﭓ ﭔ ﭕ ﭖ ﭗ ﭘﭙ ﭼ األنفال‬
"አላህንና መልዕክተኛውንም ታዘዙ፡፡ አትጨቃጨቁም፡፡ ትፈራላችሁና ኃይላችሁም ትኼዳለችና፤" (አል-አንፈል፡ 46)
ሙስሊሞች ምድራዊ ጥቅም ላይ እንዳይስገበገቡ፣ የዱንያ አረፋ ላይ እንዳይሻሙ፣ የአላህን ምንዳ የማይፈልጉ ስዎች ለንዋይ
እንደሚጓጉት ዓይነት እንዳይሯሯጡ ሲያስጠነቅቃቸው አላህ እንዲህ ብሏል፦
٤٧ :‫ﭽ ﭡ ﭢ ﭣ ﭤ ﭥ ﭦ ﭧ ﭨ ﭩ ﭪ ﭫ ﭬ ﭭﭮ ﭯ ﭰ ﭱ ﭲ ﭼ األنفال‬
"እንደነዚያ ለትዕቢትና ለሰዎች እዩልኝ ሲሉ ከአላህ መንገድ ለማገድ ከአገራቸው እንደ ወጡት አትኹኑ፤ አላህም
የሚሠሩትን ሁሉ (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡" (አል-አንፋል፡ 47)
ከዚህም በኋላ ሙስሊሞች በኡሑድ ጦርነት አሳማሚ ብትር ቀመሱ፡፡ ሰባ ጀግኖቻቸውን አጡ፡፡ ወደ መዲና ለመመለስ ተገደዱ፡፡
ሁለት ነገሮች ያብከነክኗቸዋል፡፡ የሽንፈት ውርደትና የከሀዲዎች ማላገጫ መሆናቸው፡፡ በአላህ ማመናቸው፣ ለእውነት መታገላቸው፣
ግልፅ ለሆነ አሸናፊነት የሚዳርግ ከመሆኑ ጋር ይህ ሽንፈት ለምን? ጉዳዩ እንዲህ ነው፡- በእርግጥ እነርሱ ስለተጨቃጨቁ፣ ስለተከፋፈሉ፣
የአላህንና የመልዕክተኛውን ትዕዛዝ ስለዘነጉ ነው፡፡
١٥٢ :‫ﭽ ﮄ ﮅ ﮆ ﮇ ﮈ ﮉ ﮊ ﮋ ﮌ ﮍ ﮎ ﮏ ﮐﮑ ﮒ ﮓ ﮔ ﮕ ﮖ ﮗ ﮘ ﮙﮚ ﮛ ﮜ ﮝ ﮞﮟ ﭼ آل عمران‬
"የምትወዱትንም ነገር ካሳያችሁ በኋላ በፈራችሁ፣ በትእዛዙም በተጨቃጨቃችሁና ባመፃችሁ ጊዜ፣
(እርዳታውን ከለከላችሁ)፤ ከናንተ ውስጥ ቅርቢቱን ዓለም የሚሻ አልለ፤ ከናንተም የመጨረሻይቱን
ዓለም የሚሻ አልለ፤ ከዚያም ሊሞክራችሁ ከነርሱ አዞራችሁ፤ በእርግጥም ከናንተ ይቅርታ
አደረገላችሁ፡፡ አላህም በምእምናን ላይ የችሮታ ባለቤት ነው፡፡"
(አል ዒምራን፡ 152)

የዓላማ አንድነት
ሙስሊሞች በዚህ ዘመን ያሉበትን አስቸጋሪ ታሪካዊ ሁኔታ ቢያስተውሉ፣ ይህን ውርደት ሊከናነቡ የቻሉት፣ የሚተሳሰሩበት
ገመድ በመበጠሱ፣ ከዚህም ባለፈ ፍላጐታቸውና ዓላማቸው ስለተበታተነ እንደሆነ ይገነዘቡ ነበር፡፡ የምዕራባውያን የመስቀል ዘመቻ እና
የቅኝ አገዛዝ፣ የሙስሊሞችን መዳከም ተከትሎ መጣ፡፡ የሙስሊም አገራትን መቆጣጠርና ሃብታቸውን መዝረፍ ሊሳካላቸው የቻለው
በሙስሊሙ ውስጣዊ ድክመት ነው፡፡ ቀድሞውኑ ሙስሊሞችን በመከፋፈል የተለያዩ አናሳ ቡድኖችን መሰረቱ፡፡ ትናንሽ የተጣሉ
አገሮችን ፈጠሩ፡፡ እርስ በእርስ ሕዝቦችን አጫረሱ፡፡ በመሀል ያለውን ቀዳዳ አሰፉ፡፡ ምዕራባውያን ምስራቆችን ለመውረር የተጠቀሙት
“ከፋፍለህ ግዛ” የሚል መርህ ነው፡፡
ኢስላም የሕዝቦችን አንድነት እና ክብራቸውን ለመጠበቅ ጥረት ያደርጋል፡፡ የጠብ ምንጭን ቶሎ ያደርቃል፡፡ እያንዳንዱን
ግለሰብ ሕዝቡን ከጠብ ማነቆ እንዲያወጣና እንዲያድን፣ ያ ካልሆነ ግን የሚገጥመው አስከፊ መከራ እንደሆነ ገልጿል፡፡
“የአላህ እጅ ከህብረት ጋር ነው፡፡ የተነጠለ እሣት ውስጥ ይነጠላል፡፡”
የኢስላም ጠላቶች እጃቸውን አንድ እውቅ ሰው ላይ ማሣረፍ ይወዳሉ፡፡ እርሱን የራሳቸው አድርገው ይይዙታል፡፡ በእርሱ
ተንተርሰው ሁሉንም ሕዝብ ይጐትቱበታል፡፡ እንዲህ ዓይነት የውስጥ ባንዳ ከሕብረተሰቡ ውስጥ ለማጥፋት ከስሩ ቢነቀል ጥፋት
የለውም፡፡ ስለዚህም የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፦ “ወደፊት ጥፋት፣ ፈተና (በታኝና አጣይ) ይኖራል፡፡ አንድ የሆነውን
ሕብረተሰብ ለመገነጣጠል የሚፈልግ ሰው፣ ምንም ማንም ቢሆን በሰይፍ በሉት፡፡” (ሙስሊም ዘግበውታል)
ከሕብረተሰብ ስምምነት ላፈነገጠና ማሕበራዊ ቀውስ ለመፍጠር የሚሯሯጥ ሰው፣ ይህ ምድራዊ ቅጣቱ ነው፡፡ ከዚህ
በኋላም እንዲህ የሚለው የአላህ (ሱ.ወ) ንግግር ውስጥ ይጠቃለላል፡-
١١٥ :‫ﭽ ﭮ ﭯ ﭰ ﭱ ﭲ ﭳ ﭴ ﭵ ﭶ ﭷ ﭸ ﭹ ﭺ ﭻ ﭼ ﭽ ﭾ ﭿﮀ ﮁ ﮂ ﭼ النساء‬
"ቅኑም መንገድ ለርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእመናኑ መንገድ ሌላ የኾነን
የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፤
መመለሻይቱም ከፋች!" (አን-ኒሳእ፡ 115)
በሰዎች ውስጥ መጥፎ ባህሪ ይኖራል፡፡ ለብቻዋ ስር ሳትሰድ ከተቀጨች ልትነቀል ትችላለች፡፡ አንድነትን የመከፋፈል ጥረት
በተወሰነ ደረጃ የመንቀሳቀስ እድል ካገኘ፥ እንዲህ ዓይነት አጋጣሚ ለሚፈልጉና ሕብረተሰቡን ለመፈታተን ሁሌም የሚተጉ ሰዎች በዚህ
የጥፋት ተልዕኮ ውስጥ ይሰበሰባሉ፡፡
ስለዚህም የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “ከታዛዥነት ያፈነገጠ፤ ከህብረት አምፆ የወጣና የሞተ፣ የጃሂሊያ ሞት
ሞተ፡፡” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
በሌላ ሐዲስ፣ “…ከሕዝቤ (ሕብረት) ያፈነገጠ፣ ጥሩውንም መጥፎውንም የሚማታ፣ ከሙእሚኖች (ጉዳት ከማድረስ)
የማይታቀብ፣ ቃል ለገባላቸውም ቃሉን የማይሞላ፤ ከኔ አይደለም፡፡ እኔም ከርሱ አይደለሁም፡፡” (ሙስሊም ዘግበውታል)

ሁሉም የድርሻውን
ብቃትና ችሎታ ያለው ሰው ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፡፡ በተሰጥኦ የታደለ ሰው ሕብረተሰብ ሊጠቀምበት ግድ ይላል፡፡ አንድ ሰው
የትኛውንም የሚያክል ብቃት፣ ችሎታና ተሰጥኦ ቢኖረው፣ ስልጣን የሚወድ በሽታ ካለበት እራሱም አይጠቀምበትም፡፡ ሕብረተሰቡም
ምንም ግልጋሎት አያገኝበትም፡፡ ሥልጣን አሳዳጅን አላህ አያመቻችለትም እንዲህ ዓይነት ሰው በችሎታው ወደር እንኳ ባይኖረው
መናጢ ነው፡፡
ከዚህም በላይ ኢስላም ሥልጣን አሳዳጆችን የሚጓጉለትን ቦታ እንዳያገኙ ከልክሏቸዋል፡፡ አቡ ሙሳ እንዳስተላለፉት፣ “ነቢዩ
(ሰ.ዐ.ወ) ጋር እኔና ሁለት የአጐቴ ልጆች ሁነን ገባን፡፡ አንዳቸው እንዲህ አለ፦ “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አላህ ኃላፊነት በሰጠዎት
ቦታዎች ላይ ሹመት ስጡን፡፡ ሌላኛውም እንደዚሁ አለ፡፡ ነቢዩም፦ “(በአላህ እምላለሁ!) አንድም ይህን ሥራ ለጠየቀ ሰው ወይም በጣም
ለጓጓበት ሰው አንሾምም” አሉ፡፡” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
የሚገርመው ነገር የኢስላምን መሠረት ያናጉ፣ ኡማውን የበታተኑና ሃይማኖቱን ከፍተኛ መቀመቅ ውስጥ የከተቱት የስልጣን ጥማት
ያሳበዳቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ናቸው፡፡ ገፈቱንም እስካሁን ሙስሊሙ እየተጋተው ይገኛል፡፡ ችሎታ እና ብቃቱ የስልጣን ጥማቱን ያክል
የላቀ እና የመጠቀ ቢሆን እንኳ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዳሉት ለስልጣን ለሚጓጓ ሰው ስልጣን አይሰጠውም፡፡ ታዲያ እንዴት ለእነዚያ
በእውቀትም በስብእናም ለደኸዩ ሰዎች ኃላፊነት ይሰጣል?
ጥንት ሙተነቢ እንዲህ ብሎ ገልጿቸዋል፡-
የሌሎቹ ሕዝቦች ሲመሩ በእውቀት፣
ሀገርን ሊያቀኑ ሲመክሩ ሊቃውንት፣
ለምን ይሆን የኛ የሙስሊም መሪዎች፣
ድንቁርና አድናቂ ዲዳ መሃይሞች
የፈጠሩት ሸንጎ ሀገር አኮሳሾች፡፡
ሁሉም ግዴታውን ይወጣ፡፡ በእንዲህ ዓይነት ጥሜት አደጋ ውስጥ እንዳንገባ እንጠንቀቅ፡፡

ጓደኞችን መምረጥ
ጓደኝነት ሥነ-ልቦና እና አስተሳሰብን በመቅረጽ በኩል ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ አንድ ሕብረት ለመረጋጋትና ለመፅናት፣ ወደፊት
ወይም ወደኋላ ለመጓዝ በሕብረተሰቡ አባላት ያለው ጉድኝት ወሳኝ ሚና አለው፡፡ ኢስላም ይህን ግንኙነት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶታል፡፡
ባልንጀሮችህ ተጽእኖ ያደርጉብሃል፡፡ አንተም ተፅእኖ ታደርግባቸዋለህ፡፡ ወደ ሕይወትህ ውስጥ ስር የሰደደ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ቀረቤታ
ይኖራቸዋል፡፡
በእርግጥ ይህ ግንኙነት ካደገ፣ ከበለፀገና ፍሬያማ ውጤት ካስመዘገበ፣ አላህ ተቀብሎታል፡፡ ባርኮታልም፡፡ ከንቱና የማይረባ ከሆነ፣
ለባለቤቶቹ ፍሬ አልባ ይሆናል፡፡
٦٨ - ٦٧ :‫ﭽ ﮜ ﮝ ﮞ ﮟ ﮠ ﮡ ﮢ ﮣ ﮤ ﮥ ﮦ ﮧ ﮨ ﮩ ﮪ ﮫ ﮬ ﭼ الزخرف‬
"ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፤ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፤ (ለነርሱስ)፡- ባሮቼ
ሆይ! ዛሬ ቀን በናንተ ላይ ፍርሃት የለባቸሁም፤ እናንተም የምታዝኑ አይደላችሁም (ይባላሉ)፡፡" (አዝ-
ዙኽሩፍ፡ 67-68)
ኢስላም የሕብረትና የፍቅር ሃይማኖት ነው፡፡ ከሰዎች ጋር የመተዋወቅና የመቀላቀል ጉጉት በኢስላም አስተምህሮት ውስጥ
መሠረታዊ ቦታ አለው፡፡ ኢስላማዊው አስተምህሮት ሌሎችን አውሬ በማድረግ ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ እንዲሁም ተከታዩችን
ብቸኛ ሆነው የሕይወትን ውጣ ውረዶች እንዲሸሹ አላዘዘም፡፡ የሙስሊም ምድራዊ ተልእኮ በገዳም ውስጥ መገለል፣ አልያም በልዩ ስፍራ
ዒባዳ ማድረግም በፍፁም አይደለም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ለእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ከፍተኛ ደረጃን አላዘጋጀም፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “ሙእሚን ያ ከሰዎች ጋር የሚቀላቀልና የእነርሱን አስቸጋሪነት በትእግስት
የሚያልፍ፣ ከዚያ ሰዎችን ከማይቀላቀል አስቸጋሪነታቸውንም ከማይታገስ ሰው በላጭ ነው፡፡”

ሕብረት የኢስላም አርማ


ሕብረት አስፈላጊነቱ ለማን ነው? ጁሙዓ ሰላት ማን ላይ ነው ግዴታ የተደረገው? የጂሀድን ኃላፊነት የሚሸከም ከባድ ፈተናዎችን
የሚያልፍ እርሱ ማን ነው? ይህ ሁሉ ነገር አጠቃላይ እና ልዩ ጥብቅ ትስስር ያላቸው ሰዎችን ይፈልጋል፡፡
ስለዚህም ኢብኑ ዐባስ ‹‹አንድ ሰው ቀን ይፆማል፡፡ ሌሊት ይሰግዳል፡፡ ግን ለጁሙዓ ሰላት አይገኝም፡፡ እንዴት ነው?›› ተብለው
በተደጋጋሚ ሲጠየቁ፣ እንዲህ አሉ፣ ‹‹እርሱ የእሳት መሆኑን ንገሩት፡፡› (ቲርሚዚ ዘግበውታል)
ኢስላም በከፍተኛ ደረጃ ትላልቅ መሰረታዊ መለያዎቹን ሙስሊሞች ለመወጣት እንዲተባበሩት ይፈልጋል፡፡ ከዚህም ንፁህ አየር
አንዲያገኙ፣ ልዩ ፍቅር እንዲለዋወጡ፣ ጥልቅ እምነት በመካከላችው እንዲሰርፅ ያደርጋል፡፡ ሙስሊም ከወንድሞቹ ጋር በሚሰለፍበት
ሥራ፣ ቁጥራቸው በበዛ ቁጥር የአላህ በረከት ይበዛል፡፡
በሐዲስ እንደተዘገበው፦ “አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር መስገዱ ብቻውን ከሚሰግደው ይበልጥለታል፡፡ ከአንድ በበዛ ቁጥር እርሱ
አላህ ዘንድ የተወደደ ነው፡፡” (አህመድ ዘግበውታል)
በሌላ ዘገባ፦ “ሁለት ሰዎች አንዱ አሰጋጅ ሆኖ መስገዳቸው፣ አላህ ዘንድ አራት ለየብቻቸው ከሚሰግዱት በላጭ ነው፡፡ የአራት
ሰዎች (በአንድነት) መስገድ፣ ከስምንት ለየብቻ ሰጋጆች በላጭ ነው፡፡ ስምንት ሰዎች አንዳቸው አሰጋጅ ሆኖ መስገድ መቶ ለየብቻ
ከሚሰግዱ አላህ ዘንድ በላጭ ነው፡፡” (ጦበራኒ ዘግበውታል)
እነዚህ የሐዲስ ዘገባዎች የኢስላምን በብዛት በከፍተኛ ቁጥር ሙስሊሞችን መመልከት እንደሚፈልግ ያሳያሉ፡፡ ለየብቻ ተበታትነው
ማየት አይፈልግም -ኢስላም፡፡

ብቸኝነት ማኅበራዊ ሽንፈት


ብቸኝነትና ከሰዎች ጋር አብሮ የመኖር ጉዳይ የተለያዩ የአስተሳሰብ መነሻዎች ውጤት ናቸው፡፡ ብቸኝነትም ሆነ ከስብስብ
መራቅ፣ በሕዝብ ውስጥ ገብቶ ለበጎ ነገር ለመትጋትና ሌሎችን ለማትጋት እንቅፋት ነው። ሕብረት ጠላት ሊያደርስ ከሚችለው አደጋ
በአግባቡ ለመመከት ይረዳል፡፡ በአንጻሩ መበታተን ከባድ ስህተት ነው፡፡ ይህንን ድርጊት የሚፈጽም ሠው ሊያቀርበው የሚችለው
ምክንያት ተቀባይነት የለውም፡፡
ከዚህም ሌላ ሰዎች የተለያዩ ባህሪያት አሏቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ስብሰባዎች ላይ ለመሳተፍ የሚሽቀዳደም፣ በፍጥነት ከዚህም
ከዚያም ጋር የሚግባባ፣ ከቅርቡም ከሩቁም ጋር መጫወት፣ እንዲሁም የሰዎችን ፊት መመልከት የሚያረካው ሰው አለ፡፡ በአንፃሩ ታላቅ
ስብሰባ ውስጥ ገብቶ፣ ለብቻው አጥር ከልሎ የሚቀመጥ፣ ሁሉንም በጥንቃቄ የሚመለከት፣ ሰዎች እንኳ ቢፈልጉት የሚደበቅ
አይጠፋም፡፡
ኢስላም ሁለቱንም ባህሪያት አስፈላጊ ትክክለኛ ጎዳና እንዲይዙ አድርጓቸዋል፡፡ አንደኛው እንዲህ ይባላል፡- "ከሰዎች ጋር
ተቀላቀል፡፡ ሆኖም ዲንህን በደንብ ጠብቅ፡፡" ለሌላኛው ደግሞ እንዲህ ይባላል “ሙእሚን ቀላል፣ ለስላሳ፣ ተግባቢና የሚግባቡት
ነው፡፡”
ኢስላም ፈተና ውስጥ ላለመግባት ሙከራ ማድረግን ግዴታ አድርጓል፡፡ አገር ሲረበሽ፣ ሰዎች ለምድራዊ ንዋይ ሲተናነቁ፣ ሥርዓት
አልበኝነት ሲነግስ፣ ይህን ፈተናና ረብሻ መሸሽ ተቃውሞን መግለጫ አንዱ መንገድ ነው፡፡ ይህም ለውጥ ለማምጣት ከምንጠቀምባቸው
ሸሪዓ ካስቀመጣቸው ደረጃዎች ሳንወጣ ነው፡፡ መጀመሪያ በእጅ ከዚያም በምላስ መቃወም፣ ይህ ካልተሳካ በልብ መጥላት ግድ ይላል፡፡
መጥፎ ነገርን እንኳን በእጁ ቀርቶ በምላሱ መቃወም የሚችል ሰው መሸሽ የለበትም፡፡ ደካማ ሕዝቦች በኃይል ሊያንበረክኳቸው
ከሚሞክሩ ኃያላን መንግስታት ላይ በሰላማዊ ትግል ማዕቀብ ለመጣል የሚያስችላቸውን ጥበብ አዳብረዋል፡፡ በሕብረተብ ውስጥ
ተሃድሶ ለመፍጠር የሚያስችሉ ስልቶችን ቸል ማለት ከትግል አውድማ መሸሽ አፀያፊ ተግባር ነው፡፡ ሰዎች መሸሽ የሚችሉት
ሁሉንም ዓይነት የትግል ስልቶች ሞክረው ሳይሳካላቸው ሲቀር ብቻ ነው፡፡ ይሄኔ ዲናቸውን ብቻ
በሚያስጠብቅላቸው መልኩ ከትግሉ ሊያፈገፍጉ ይችላሉ፡፡
በዚህ ማብራሪያ ላይ በመመርኮዝ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግር ግልፅ ይሆናል፤ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ "የአላህ መልክተኛ
(ሰ.ዐ.ወ) ሆይ! የትኛው ሰው በላጭ ነው?” ‹‹ሙእሚን ሆኖ በነፍሱና በገንዘቡ በአላህ መንገድ የሚታገል›› አሉ፡፡ ‹‹ከሱ በኋላስ?››
ተባሉ፡፡ ‹‹ገለልተኛ ሰው፡፡ በሸለቆ ውስጥ ሆኖ አላህን የሚገዛ›› አሉ፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ገለልተኝነትና ተቀላቅሎ መኖር የአንድ ሰው ቋሚ መገለጫ ሊሆን አይገባም፡፡ ሙስሊም ጊዜውን ጠቃሚ በሆነ መልኩ አንዳንዴም
በመገለል ይጠቀም፡፡ ሌላም ጊዜ በማኅበራዊ ሕይወቱ ጉልህ ሚና ይጫወት፡፡ በሁለቱም ሁኔታ ራሱን እያየ ትክክል ለመሆን ይጣር፡፡
ጓደኛን ለምድር
በሚከተሉት የ ¹ ደኝነት መስፈርቶች ላይ ቆመን ጓደኞችን እንምረጥ፡፡ የመጀመሪያው የጥሩ ጓደኝነት መለኪያ ጥቅም አሳዳጅ
አለመሆን ነው፡፡ ለአላህ ብቻ ብለን ጓደኝነት መመስረት፤ ጓደኝነት ሲያድግ ለአላህ ብቻ ሆኖ ይደግ፡፡ ለአላህ ብሎ ብቻ መዋደድ ታላቅ
ስጦታ ነው፡፡

ሰው በልቡ ውስጥ በአላህ ላይ ያለው እምነት ከጠለቀ፣ ቀልቡ በኢማን ከተሞላ፣ የኢማን ማጣጣም ከተዋሃደው፣ ፍጡራንን
በሙሉ የሚመለከተው በእምነት መለኪያ ብቻ ይሆናል፡፡ የፍቅር ስሜት መሰረቱ ኢስላማዊ ሚዛን ነው፡፡ ሲጠላም በኢስላማዊ
አስተምህሮት መሠረት ላይ እንጂ የፈለገው ስላልተሰጠው አይደለም፡፡
ከብቶች ኮለል ብሎ በሚፈስ ወይም በደፈረሰ ውሃ ሊሰበሰቡ ይችላሉ፡፡ ሰዎች በአጋጣሚ ወይም ለረጅም ጊዜ በተሳሰረ ምድራዊ
ንዋይ ሊገናኙ ይችላሉ፡፡ ምናልባትም ይህ ግንኙነት ጠንካራ መሠረት ተክሎ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ትውውቅና ፍቅር በአላህ መንገድ
ላይ ተገናኝቶ ከሚመሰረት ፍቅር፣ ንጹህ ግንኙነት፣ መተጋገዝና ወንድምን ማስቀደም ጋር ከቶ አይገናኝም፡፡
ኢስላም ለጓደኝነት ትልቅ ቦታ ሰጥቷል፡፡ ንጹህና ለአላህ ሲባል ብቻ መሆን እንዳለበት ለሙእሚኖች አስገንዝቧል፡፡ ትልቅ ምንዳ
ያለው ቅዱስ ተግባር ነውና፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ ‹‹አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ፦ "ለኔ ክብር ብለው ለተዋደዱ፣ የኔ እንጂ ሌላ ጥላ
በሌለበት ቀን፣ በአርሽ ጥላ ስር አደርጋቸዋለሁ፡፡›› (አህመድ ዘግበውታል)
ዑመር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ ‹‹(ለአላህ ብለው የሚዋደዱ ሰዎች) በእርግጥ ከአላህ
መንገድ የተሰው (ሸሂዶች) አይደሉም፡፡ አላህ ዘንድ ባላቸው ደረጃ የተነሳ ነቢያትም ሸሂዶችም ይቀኑባቸዋል፡፡ ‹‹የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!
እነርሱ እነማን ናቸው? ንገሩን›› አሉ ሰሓቦች፡፡ ‹‹እነርሱ ለአላህ ፍቅር ብለው የተዋደዱ፣ በመካከላቸው ምንም የዘር ትስስር ወይም
የሚቀባበሉት ገንዘብ የለም፡፡ ወላሂ ፊታቸው ብርሃን ነው፡፡ እነርሱም ብርሃን ናቸው፡፡ ሰዎች ሲፈሩ አይፈሩም፡፡ ሰዎች ሲያዝኑ አያዝኑም››
አሉ፡፡ ከዚያም ይህንን አንቀጽ አነበቡ፣ “አዋጅ በእርግጥ የአላህ ወዳጆች ፍርሃት አይገባባቸውም፡፡ እነርሱም ሀዘን አይነካቸውም፡፡”
ለአላህ ብሎ መዋደድ ሁሉም የራሱ ሀብት ሊያደርገው አይችልም፡፡ ‹‹ለአላህ ብዬ እወዳለሁ›› ያለ ሁሉ ትክክል ነው አይባልም፡፡
ለአላህ ብሎ መዋደድ ውስጣዊ መሠረት አለው፡፡ ሰው መጀመሪያ ጌታውን በትክክል ማወቅ አለበት፡፡ ይህ እውቀት በልቦናው ሲሰርጽ፣
ከአላህ ውጭ ያሉ ነገሮች ልቡ ውስጥ ሚናቸው ይጠፋል፡፡ ይህ እውቀት አድጎና አብቦ አላህን ራሱን ወደ ማፍቀር ይሸጋገራል፡፡ ያም
ለአላህ ብቻ ብሎ መስራትን፣ የአላህን ትዕዛዝ ከምንም በላይ ማስበለጥን በፅናት ይይዛል፡፡ በዚህ ጊዜ ለአላህ ብሎ መውደድ
በምላሱም ሆነ በተግባሩ የፀና ይሆናል፡፡ ይሄኔ ነው ሲወድም ሲጠላም ‹‹እርሱ ለአላህ ወደደ፤ ለአላህ ጠላ›› ማለት የሚቻለው፡፡
አንድ ሰው በሌላ ሰው ብቃት ቢማረክ፣ አልያም የአንድ ሰው የታሪክ ጀብዱ ቢያማልለው ከዚያም ይሄን ሰው ቢያፈቅር፣ ይህ
የመውደድ ዓይነት፣ እኛ ካለንበት ርዕስ የራቀ ሌላ ዓይነት የአድናቂነት ፍቅር ነው፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “ሦስት ነገሮች ያሉት ሰው የኢማንን ጥፍጥና (ጣዕም) አግኝቷል፡፡ አላህና
መልዕክተኛው እርሱ ዘንድ ከምንም በላይ የተወደዱ ሲሆኑ፥ ለአላህ ብሎ (ሰዎችን) ሲወድ፣ ለአላህ ብሎ ሲጣላ፣ በአላህ ከማጋራት
ይልቅ አንድ ትልቅ እሳት እየነደደ እሳት ውስጥ መግባት ሲያስበልጥ፡፡ (ሙስሊም ዘግበውታል)
ለአላህ ብሎ መዋደድ የኢማን ቁንጮ ነው፡፡ ለአላህ ብቻ ብለው የሚኖሩ ሰዎች የሚጎናፀፉት ልዩ ሽልማት፡፡ የዚህ ፍቅር ፍሰት
የምሉእነትና የንጽህና ውጤት ይሆናል፡፡ ስለዚህም ትልቅ ምንዳ ያገኛሉ፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “ለአላህ ብለው ከተዋደዱ ሁለት ባዕድ ሰዎች መካከል ከሁለቱም በጣም
ወንድሙን አፍቃሪው አላህ ዘንድ የበለጠ ተወዳጅ ነው፡፡”
ሁለት ለአላህ ብለው የሚዋደዱ ሰዎች በአላህ እገዛና ትብብር ስር ናቸው፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከአላህ (ሱ.ወ) ይዘው እንዳስተላለፉት፥ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፦ “በእርግጥ እነዚያ ለኔ
ብለው የሚዋደዱ ሰዎች የኔን ፍቅር አግኝተዋል፡፡ እነዚያ ለኔ ብለው የራሳቸውን ለሌላ የሚያስተላልፉ ሰዎች፣ የኔን ፍቅር አግኝተዋል፡፡
እነዚያ ለኔ ብለው ጓደኛ የሚሆኑ ሰዎች የኔን ፍቅር አግኝተዋል፡፡” (አህመድና ጦበራኒ ዘግበውታል)
ጓደኛ በጓደኛው ላይ የሚያሳርፈው አሻራ ጥልቅ ነው፡፡ ስለዚህም ሰውዬው ወንድሞቹን በደንብ መፈተሽ አለበት፡፡ በማንነታቸው
ላይ እርግጠኛ እስኪሆን ድረስ ትኩረት መስጠት አለበት፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “ሰውዬው በጓደኛው ሃይማኖት ላይ ነው፡፡ አንዳችሁ ማንን እንደምትጎዳኙ
ተመልከቱ፡፡” (አቡዳውድ ዘግበውታል)
ግዴታውን እንዲወጣ፣ መብቱን እንዲጠብቅ፣ ከመጥፎ እንዲርቅ እና ከሐራም እንዲታቀብ የሚያግዙ ጓደኞች ከሆኑ በእርግጥም
ጥሩ ቁርኝት መስርቷል፡፡ ይህን ወዳጅ አጥብቆ መያዝ አለበት፡፡ ፍቅራቸውን ይጠብቅ፡፡ ነገር ግን ወደ ማይረባ ነገር የሚጎትቱት፣ ሁሌም
ፌዝና ቀልድ እንጂ ቁምነገር የሌላቸው ከሆኑ ይጠንቀቅ፡፡

የሚጠቅመውን ምከረው
ቁም ነገረኛ ጓደኛ ጓደኛውን በምድራዊውም ሆነ በመጭው ዓለም ሕይወት ውጤታማ እንዲሆን ይረዳዋል፡፡ ምግባረ-ብልሹ ጓደኛ
ለጓደኛው አደገኛ ነው፡፡ ስንት ሰው በመጥፎ ጓደኛ ምክንያት ከንቱ ሆኖ ኖረ? ይህ ጓደኝነት ገደል አፋፍ አደረሰው፡፡ በመጨረሻም እሳት
ውስጥ ጣለው፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
٢٩ - ٢٧ :‫ﭽ ﮗ ﮘ ﮙ ﮚ ﮛ ﮜ ﮝ ﮞ ﮟ ﮠ ﮡ ﮢ ﮣ ﮤ ﮥ ﮦ ﮧ ﮨ ﮩ ﮪ ﮫ ﮬ ﮭ ﮮ ﮯ ﮰﮱ ﯓ ﯔ ﯕ ﯖ ﯗ ﭼ الفرقان‬
"በዳይም፡- ከመልዕክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በኾነ ዋ ምኞቴ! እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆቹን
የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ፤ (የእምነት ቃልን)
ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ፤ (ይላል)፤ ሰይጣንም ለሰው አጋላጭ ነው፡፡" (አል-ፉርቃን፡
27-29)
ባህሪ ከባህሪ ይወራረሳል፡፡ ሰው ብዙ ጊዜ የሚወደው ጓደኛውን ለመምሰል ፈጣን የሆነ እንቅስቃሴ ያደርጋል፡፡ ወረርሽኝ ከሰው
ወደሰው በፍጥነት እንደሚሰራጭ ሁሉ ባህሪም ይኸው ስርአት ይገዛዋል፡፡ አንድ ስብስብን የሚመራ መንፈስ ከጠንካራ ስብእና የመጣ
ሊሆን ይችላል፡፡ ዙሪያውን ያሉ ሰዎችን ከውስጡ በሚመጣው ጥሩ ነገር ያውዳቸዋል፡፡

መጥፎ ባሕሪ ቶሎ ይዛመታል


በጎ ሥራን ከማሰራጨት ይልቅ የመጥፎ ሥራ ስርጭት ፍጥነት አለው፡፡ ብዙ ጊዜ ሲጋራ የማጨስ በሽታ ንጹሐንን ቶሎ ይበክላል፡፡
ብዙ ጊዜ ተቃራኒው ግን አይከሰትም፡፡
ጥሩ ስብእናን ለመታደግ፣ በጎ ባህልን ለመጠበቅ፣ የአላህ መልዕክተኛ አዋዋላችንን እንድንመርጥ እንዲህ ሲሉ አዘዋል፡፡
“የሚጎዳኝህ ሰው ጥሩ ከሆነ ልክ እንደ ሽቶ ነጋዴ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ ሽቶ ነጋዴ ባይቀባህ እንኳ ጥሩ መዓዛው ያውድሃል፡፡ የሚጎዳኝህ
ሰው መጥፎ ከሆነ እንደ ብረት ቀጥቃጭ ወናፍ ነው፡፡ ፍንጣሪው ባያገኝህ እንኳ ሽታው ያገኝሀል፡፡ (አቡዳውድ ዘግበውታል)
በአጋጣሚ መንገድ ላይ ለትንሽ ሰዓት የምታገኘው ጓደኛ እንዲህ ከሆነ፣ የእድሜ ልክ ጓደኛ ክፉውንም ደጉንም የሚካፈልህ፣
እንዴት ሊሆን ነው? አስተውል! አላህን ፈሪ ከሆነ ሰው ጋር ስትጎዳኝ ወደላይ ከፍ ትላለህ፡፡ መጥፎ ሰው በመጎዳኘት ወደ ክስረት
ቁልቁለት ትወርዳለህ፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
٢٠ - ١٩ :‫ﭽ ﮬ ﮭ ﮮ ﮯ ﮰ ﮱﯓ ﯔ ﯕ ﯖ ﯗ ﯘ ﯙ ﯚ ﯛ ﯜ ﯝ ﯞ ﯟ ﭼ الجاثية‬
"በደለኞችም ከፊላቸው የከፊሉ ረዳቶች ናቸው፤ አላህም የጥንቁቆቹ ረዳት ነው፡፡ ይህ (ቁርኣን)
ለሰዎች የልብ ብርሃኖች ነው፡፡ ለሚያረጋግጡም ሕዝቦች መሪና እዝነት ነው፡፡" (አል-ጃሲያ፡ 19-20)

ጓደኝነት ለታላቅ ዓላማ


ጓደኝነት በጠንካራ ኢማንና የላቁ ዓላማዎችን ላይ የተመረኮዘ መሆን አለበት፡፡ እንደ ሰለፎች አገላለጽ ጓደኛ ማለት ‹‹ሰዎች ጋር
ሲሠራ የማይበድላቸው፣ አውርቷቸው የማይዋሻቸው፣ ቃል ገብቶላቸው ያልከዳቸው፣ ይህ (ሰው) ሰውነቱ የተሟላለት፣ ትክክለኛነቱ
ግልፅ የሆነ ነው፡፡ ከዚህ ሰው ጋር ወንድማማችነትን መፍጠር ግዴታ ነው፡፡ ጓደኝነት ለአላህ ተብሎ ከተመሠረተ፣ ዘላቂ የሚሆነው
አላህን በመገዛት ብቻ ነው፡፡ ከውሸትና ከቅጥፈት በመራቅ፣ ወንጀልና ጥፋትም አንድነታቸውን እንዳይሸረሽረው በመመካከር ነው፡፡
በሐዲስ እንደተዘገበው፦ “ነፍሴ በእጁ በሆነችው (ጌታዬ) እምላለሁ፡፡ ሁለቱ ተዋደው በመካከላቸው ጠብ የሚመጣው፣
አንዳቸው በሚሠሩት ጥፋት ነው፡፡”
ለዚህም ነው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች በእውቀት ላይ አደራ ይባባሉ፡፡ በጥሩ ነገር ላይ ይተጋገዛሉ፡፡ በመካከላቸው
ያለውን የፍቅር ትስስር ጠበቁ፡፡ ወደ አላህ (ሱ.ወ) ምህረትና ውዴታ አቀረባቸው፡፡
አቢ ቂላባህ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለው አስተላልፈዋል፣ “ሁለት ሰዎች ንግድ ላይ ተገናኙ፡፡ አንደኛው ና አላህን ምህረት እንጠይቅ፣
ሰዎች ዘንግተዋል አለው፡፡ አደረጉት፡፡ አንዱ ሞተ፣ ሌላኛው በህልሙ እንዲህ ሲለው አየው፡፡ ማታ ንግድ ቦታ ላይ በተገናኘነው አላህ
እንደማረን አውቀሃል?”
አነስ ኢብን ማሊክ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ዐብዱላህ አብኑ ረዋሃ ከአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች አንዱን ካገኘ፣
“ጌታችንን ትንሽ እናስታውሰው” ይለዋል፡፡ አንድ ቀን ለአንድ ሰው “ና አላህን እናስታውስ” አለው፡- ሰውዬው ተቆጣ፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ዘንድ መጣ ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሆይ! የረዋሐን ልጅ አትመለከተውም? አንተ (የምታስተምረውን) ኢማን ትቶ፤ ወደ ሰዓት
(ቂያማ እለት) ኢማን ጥሪ ያደርጋል›› አላቸው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉት፡-
“የረዋሐን ልጅ አላህ ይዘንለት፡፡ እሱ መላኢኮች የሚቀኑበትን ስብስብ ይወዳል፡፡” (አህመድና ጦበራኒ ዘግበውታል)

ፍቅርህን ግለፅ
ጓደኛማቾች በደንብ ሊተዋወቁ ይገባል፡፡ ግንኙነታቸውም መሠረት ላይ መቆም ይኖርበታል። አንዳቸው ለሌላው ሰው በውስጡ
ያለውን ፍቅር መግለጽ ፍቅራቸውን ያፀናዋል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “አንዳችሁ ወንድሙን ከወደደው፥ እሱ
እንደሚወደው ይንገረው፡፡” (አህመድ ዘግበውታል)
አነስ እንዳስተላለፉት፡- አንድ ሰው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ ነበር፡፡ አንድ ሰው በአጠገባቸው አለፈ፡፡ “የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)
ሆይ! እኔ ይህን ሰው እወደዋለሁ” አለ፡፡ ‹‹ነግረኸዋልን?›› አሉት፡፡ ‹‹አይ አልነገርኩትም›› አለ፡፡ ‹‹ንገረው፤›› አሉት፤ ደረሰበት፡፡ ‹‹እኔ
ለአላህ ብዬ እወድሃለሁ›› አለው፡፡ ‹‹ያ ለእርሱ ብለህ የወደድከኝ (ጌታ) ይውደድህ›› አለው፡፡” (አቡዳውድ ዘግበውታል)
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “አንድ ሰው ሌላ ሰውን ወንድም ካደረገ፤ ስሙን፣ የአባቱን ስም፣ እንዲሁም
ከየት እንደመጣ ይጠይቀው፡፡ ይህ የፍቅር መስመር ነው፡፡” (ቲርሚዚ ዘግበውታል)
የፍላጎትና የአስተሳሰብ መመሳሰል ጓደኝነትን ለመመስረት እና ግንኙነትን ለማጠናከር ዓይነተኛ መግቢያ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡
ይህም የዚህ ሐዲስ ማረጋገጫ ነው፡፡ “ልቦች (ለመተዋወቅ) የተዘጋጁ ወታደሮች ናቸው፡፡ የተዋወቀው ይዋደዳል፡፡
ያልተግባባው ይጣላል”፡፡ (ቡኻሪ ዘግበውታል)
ስሜት፥ የእምነት የበላይነት ሥርዓት ሊገዛው ይገባል፡፡ እምነት ለሙእሚን በውስጡ የሰረጸ ስሜት መመሪያው ነው፡፡ ለአላህ
ብሎ እንዲወድ ያደርገዋል፡፡ ትውውቁ የረጅም ጊዜ ወይም የአጭር ሊሆን ይችላል፡፡ ሲወድም ሲጠላም ምክንያታዊ መሰረት አለው፡፡
ልቦና በዚህ መልክ ከተጓዘች ሰውዬው ከሚጠብቀው በላይ ከፍተኛ ደረጃን ይጎናፀፋል፡፡
አቡ ዘር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፦ “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰውዬው ሰዎችን ይወዳል፡፡ የእነርሱን ሥራ ግን መሥራት
አይችልም” አልኳቸው፡፡ ‹‹አንተ አቡ ዘር (ረ.ዐ) ሆይ! ከወደድከው ጋር ነህ›› አሉ፡፡ (ቲርሚዚ ዘግበውታል)

ጓደኛህን ጐብኘው
ከኢስላም የጓደኝነት አስተምህርዎች ውስጥ አንዱ ዚያራ (መጎብኘት) ነው፡፡ ከየትኛውም ምድራዊ ጥቅም የፀዳ ለአላህ ውዴታ
ብቻ መሆን አለበት፡፡ አቡ ሁረይራህ (ረ.ዐ) የአላህ መልዕክተኛን አብይ አድረገው እንዳስተላለፉት፦ “አንድ ሰው አንድ ወንድሙን
ለመጐብኘት (ለዚያራ) ወደ አንድ መንደር አቀና፡፡ አላህ (ሱ.ወ) መንገዱ ላይ መልአክ አወረደ፡፡ (መልአኩ) ወደ መንደሩ ሲመጣ
‹‹ምን ፈለግክ?›› አለው››። ‹‹በዚህ መንደር ወንድሜን (ለመጎብኘት) ፈልጌ ነው›› አለው፡፡ ‹‹እርሱ ላይ አንተ የምትፈልገው ጥቅም
አለን?›› አለው፡፡ ‹‹የለም ግን እኔ ለአላህ ብዬ ወደድኩት…›› አለ፡፡ ‹‹እኔ ወደ አንተ የመጣሁ የአላህ መልዕክተኛ ነኝ፡፡ በእርግጥ
ሰውዬውን ለእርሱ (ለአላህ) ብለህ እንደወደድከው አላህም ወዶሃል›› አለው፡፡ (ቡኻሪ ዘግበውታል)
እነዚህ እርምጃዎች ውድ ናቸው፡፡ ልክ በአላህ መንገድ እንደታገሉ ታጋዮች ታላላቅ ምንዳዎችን ያስገኛሉ፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- በሽተኛን የጠየቀ፣ ወይንም ለአላህ ብሎ ወንድሙን የጎበኘ፣ ጠሪ ይጠራዋል፡፡ “ጥሩ
ሁነሃል፡፡ መንገድህም አምሯል፡፡ ጀነት ውስጥም መቀመጫ አግኝተሃል፡፡” (አቡዳውድ ዘግበውታል)
እንዲህም ብለዋል፡- “ማንኛውም ባሪያ ወንድሙን ለመጎብኘት ለአላህ ብሎ ከመጣ፤ ከሰማይ ጠሪ መጥራቱ አይቀርም፡፡ ‹‹ጥሩ
ሁነሃል፡፡ ጀነትም ለአንተ ተሰናድታለች፡፡›› አልያም አላህ በአርሽ ንግስናው ሆኖ እንዲህ ይለዋል፦ "ባሪያዬ (ባርያዬን) ለኔ ብሎ ጎበኘ፡፡
እኔ ልመነዳው ይገባል፡፡ (አላህ) ለሰውዬው ከጀነት ያነሰ ምንዳ አይሰጠውም፡፡" (ሙስሊም ዘግበውታል)
ሙስሊም ሰዎችን ሁሉ መጥቀም ይወዳል፡፡ በተለይ ጓደኞቹን ለመጥቀም በጣም ይጥራል፡፡ ሁሌም ለእነሱ የሚያስደስት ነገር
መስራት ያረካዋል፡፡ ስለዚህም ተጨማሪ ነገር ካገኘ ጓደኞቹን ያስታውሳል፡፡
٢٣٧ :‫ﭽ ﯺ ﯻ ﯼ ﯽﯾ ﯿ ﰀ ﰁ ﰂ ﰃ ﭼ البقرة‬
"…በመካከላችሁም ችሮታን አትርሱ፤ አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና፡፡" (አል-በቀራ፡ 237)

ስጦታ
የአላህ መልዕክተኛ በጓደኞች መካከል የሚደረግ የስጦታ ልውውጥን ይወዳሉ፡፡ እንዲህም ብለዋል፡- “ስጦታ ተለዋወጡ፤ ስጦታ
የልብን ሽፋን ታነሳለች፡፡” (ቲርሚዚ ዘግበውታል)
ዓኢሻህ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለው አስተላልፈዋል፡- ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ስጦታን ይቀበሉ ነበር፡፡ ራሳቸውም ይሰጡ
ነበር፡፡›› (በዛር ዘግበውታል)
ይህ ትልቅ ሥርዓት ከሚወደድበት መስመር ከወጣ የተጠላ ይሆናል፡፡ ኢስላም አስመሳይነትን ተዋግቷል፡፡ ነገሮች በቀላሉ ተፈጻሚ
መሆናቸውን ይወዳል፡፡ ኢስላማዊ አስተምህሮ፣ ማስቸገርና ማስጨነቅ ይቃወማል፡፡ ኢስላም አላማው ጓደኝነትን ደሳስ በሚሉ ሁኔታዎች
መክበብ ነው፡፡ ጭብጡና ጥሩነቱ ከተረጋገጠ በኋላ የሽፋኑ ማማር ይወደዳል፡፡ ይህ ነገር (ስጦታ) ሕይወትን ለማቅለልና ችግርን ለመቅረፍ
ይጠቅማል፡፡ ‹‹አላህ ዘንድ ጥሩ ጓደኞች (የሚባሉት) ለጓደኞቻቸው ጥሩዎቹ ናቸው፡፡ አላህ ዘንድ ጥሩ ጎረቤቶች የሚባሉት፣
ለጎረቤታቸው ጥሩዎቹ ናቸው፡፡›› (ሐኪም ዘግበውታል)
ኢስላም አንድ ሰው ጓደኛው ቤት ማዕድ እንዲበላ ስለሚፈቅድ፣ “ከአባቱ፣ ከወንድሞቹ ወይም ከዘመዶቹ ቤት ምግብ
እንደሚበላው ጓደኛው ጋርም ይብላ” ብሎ ይመክራል፡-
:‫ ﭼ النور‬O‫ ﮥ ﮦ ﮧ ﮨ ﮩ ﮪ ﮫ ﮬ ﮭ ﮮ ﮯ ﮰ ﮱﯓ‬O‫ ﮞ ﮟ ﮠ ﮡ ﮢ ﮣ ﮤ‬O‫ ﮚ ﮛ ﮜ ﮝ‬O‫ ﮕ ﮖ ﮗ ﮘ ﮙ‬O‫ ﮐ ﮑ ﮒ ﮓ ﮔ‬... ‫ﭽ‬
٦١
"ከቤቶቻችሁ ወይም ከአባቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከናቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከወንድሞቻችሁ ቤቶች ወይም
ከእኅቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከአጐቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከአክስቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከየሹሞቻችሁ ቤቶች ወይም
ከየሹሜዎቻችሁ ቤቶች ወይም መክፈቻዎቹን ከያዛችሁት ቤት ወይም ከወዳጃችሁ ቤት (ብትበሉ) ኅጢአት
የለባችሁም፡፡" (አን-ኑር: 61)
ጓደኝነት መመስረት ትልቅ ደረጃ አለው፡፡ ከባድ አሻራም ያሳርፋል፡፡ ውጥረትና ጭንቀት በሚያጋጥም ጊዜም፣ የእርዳታና የእገዛ
ምንጭ ነው፡፡
አላህ (ሱ.ወ) አጋሪዎች እሳት ሲያሰቃያቸው ያላቸውን ሁኔታ ሲገልፅ እንዲህ ብሏል፡-
‫ﭽ ﮝ ﮞ ﮟ ﮠ ﮡ ﮢ ﮣ ﮤ ﮥ ﮦ ﮧ ﮨ ﮩ ﮪ ﮫ ﮬ ﮭ ﮮ ﮯ ﮰ ﮱ ﯓ ﯔ ﯕ ﯖ ﯗ ﭼ الشعراء‬
"በአላህ እንምላለን፤ እኛ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነበርን። (ጣዖቶቹን) በዓለማት ጌታ ባስተካከልናችሁ
ጊዜ፡፡ አመጠኞቹም እንጂ ሌላ አላሳሳተንም፡፡ ከአማላጆችም ለኛ ምንም የለንም፡፡ አዛኝ ወዳጅም
(የለንም)፡፡ " (አሽ-ሹዐራእ: 97-101)
ጓደኝነትን የመሳሰሉ ግንኙነቶች ከታላላቅ መብቶች ጋር ግንኙነት አላቸው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
"ሙእሚን እንጂ ጓደኛ አታድርግ፡፡ ምግብህን አላህን ፈሪ እንጂ አይመገብ፡፡” (አቡዳውድ ዘግበውታል)
ወንድሜ ነህ ብለው በየት በኩል አለኝ፣
እናቴ ባትወልድ ወንድምነት አለኝ ፣
የሚያስተሳስረኝ የሚያመ ሳስለን፣
እርሱ የዘነጋው የጋራ ምንጭ አለን፡፡
የአላህን ጸጋ ማመስገን
ለሰው ልጅ ከንጹህ ልቦና በላይ ትልቅ ሃብት የለውም፡፡ ጭንቅን የሚያጠፋ፣ መንፈስን የሚያረጋጋና አእምሮን የሚያረካ ሌላ
ነገር የለም፡፡ ንጹህ ልብ ማለት ከክፋት የራቀ፣ ከምቀኝነት የጸዳ ነው፡፡ አንድ ሰው ጥሩ ነገር ሲያገኝ የአላህን ትልቅነትና የፍጡራኑን
ድክመት የሚያስተውል ነው፡፡ ሁሌም ይህ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግር ይታወሰዋል፡፡ “አላህ ሆይ! ለእኔና ለፍጡራንህ ጸጋህ ምሉዕ ሁኖ
አደረ፡፡ ፍጹም ነህ፡፡ አጋር የለህም፡፡ ምስጋና ለአንተ ነው፡፡ ውዳሴም የሚገባው ለአንተ ብቻ ነው፡፡” )አቡዳዉድ ዘግበውታል(
በሌላ በኩል ሙስሊም አንድ የአላህ ፍጡር አደጋ ላይ ሲወድቅና ችግር ሲገጥመው፣ ያዝናል፤ ይራራል፡፡ አላህም ይህን ፍጡር
ከጭንቅ እንዲያላቅቀው ወንጀሉን እንዲምረው አላህን ይማጸናል፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አላህን እንደተማጸኑት፡፡
“አላህ ሆይ! የአንተ ፈቃድ ከሆነ ለሁሉም ባሮች ይቅር ባይ ነህ፡፡ ፍጡርህ ከወደቀበት አደጋ አንተ ጠብቀው፡፡”
በዚህ መልክ ሙስሊም የነጠረ ሰላማዊ ሕይወት ይኖራል፡፡ በሕይወቱም በአላህም ደስተኛ ይሆናል፡፡ ልቦናውም ከክፋትና
ከጭፍን ጥላቻ ይርቃል፡፡ ክፋትና ጭፍን ጥላቻ ልብ ውስጥ ድቅድቅ ጨለማ ይከታሉና፡፡ ኢማንም ከእንዲህ ዓይነት የተበላሸ ቀልብ
በፍጥነት ይተናል፡፡
ኢስላም ለቀልብ ያለው እይታ ጥብቅ ነው፡፡ ጸሊም ልብ በጎ ሥራን ይደመስሳል፡፡ የቀልብን ደስታ ያደፈርሳል፤ ያጠፋል፡፡ ጥሩ
ቀልብ ያለው ሰው አላህ ሥራውን ይባርክለታል፡፡ ጥሩ ሥራ ሁሉ ይገራለታል፡፡
ዐብደላህ ኢብን አምር እንደዘገቡት፡- “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ምርጥ ሰው ማን ነው?” ተብለው ተጠየቁ፡፡ ‹‹ምሉዕ ልቦና እና
እውነተኛ ምላስ ያለው ሰው›› አሉ፡፡ እውነተኛ ምላስ ማለት ይገባናል፡፡ ‹‹ምሉዕ ልቦና ማለት ምንድን ነው?›› ተብለው ተጠየቁ፡፡
‹‹አላህን ፈሪ፣ ንጹህ ቀልብ ያለው፣ ድንበር የማያልፍ፣ መጥፎ የማያስብ፣ ጥላቻና ምቀኝነት የሌለው›› በማለት መለሱ፡፡” )ኢብን ማጃህ
ዘግበውታል(
የሙስሊሞች ማኅበራዊ ሕይወት ምንጊዜም በመተሳሰብ፣ በፍቅር፣ በመከባበር፣ በመረዳዳትና ግንኙነትን በማጠንከር ላይ
የተመሰረተ ነው፡፡ ራስ ወዳድ ግለሰባዊነት በኢስላም ስፍራ የለውም፡፡ ሙስሊሞችን ቁርአን እንዲህ ሲል ይገልጻቸዋል፡-
‫ﭽﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭼ‬
"እነዚያም ከበኋላቸው የመጡት፡- "ጌታችን ሆይ! ለኛም ለነዚያም በእምነት ለቀደሙን ወንድሞቻችን ምሕረት
አድርግ፤ በልቦቻችንም ውስጥ ለነዚያ ለአመኑት (ሰዎች) ጥላቻን አታድርግ፡፡ ጌታችን ሆይ! አንተ ርኅሩኅ አዛኝ
ነህና" ይላሉ፡፡"(አል-ሐሽር: 10)
ንትርክና ጭቅጭቅ በልብ ውስጥ ከበቀለ፣ ክፋትና ድርቅና ከጠነከረ፣ እዝነትና ሰላም ይከስማሉ፡፡ ሕይወት ኢማን ያጣል፡፡በዚህ
መንፈስ ውስጥ ሁኖ የሚፈጸም ዒባዳ ፍሬ ቢስ ነው፡፡ ጭቅጭቅ ሰውን ውጤተ-ቢስ ያደርገዋል፡፡ ክብሩን ያዋርደዋል፡፡ የማይረባ ተግባር
ውስጥ ይከተዋል፡፡ ከአላህ እዝነት እንዲርቅም ምክንያት ይሆናል፡፡ ክፋት ላይ የተመሰረተ አመለካከት በጎ እይታን ያደበዝዛል፡፡ በጎ
ነገርን ለማየት ያዳግታል፡፡ ድክመትን ያጎላል፡፡ ብሎም ይህ ክፋትና የተንሸዋረረ ምልከታ ውሸት ወደ መፍጠር ይገፋፋል፡፡ ይህ ሁሉ
ኢስላም በፍጹም የማይቀበለው የሚጠላው አጸያፍ ተግባር ነው፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)፦ “ከጾም፣ ከሰላት፣ ከሰደቃ የበለጠ ተግባር ልነግራችሁ ትፈልጋላችሁን?” አሉ፡፡ “እንዴታ፡፡
ንገሩን” አሉ ሰሓቦች፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- “ጠበኞችን ማስታረቅ ነው፡፡ በሰዎች መካከል ጠብ መፍጠር ይላጫል፡፡ ‘ፀጉር
ይላጫል’ ማለቴ አይደለም፡፡ (ከልብ ላይ ኢማንን) ይላጫል፡፡” (ቲርሚዚ ዘግበውታል)
አስተዋይ ሰው ጣኦት እንዲያመልክ ማድረግ ለሰይጣን ይሳነው ይሆናል፡፡ ሆኖም ሰይጣን ሰውን ለማጥፋት የማይፈነቅለው
ድንጋይ የለም፡፡ ሰውን ከአላህ የሚያራርቅበት ሌላ መንገድ አያጣም፡፡ የአላህን ሃቅ ያስረሳዋል፡፡ አንድ ጣኦት አምላኪ እውነት
ከሚጨልምበት በላይ ያጨልምበታል፡፡ ይህም ሰውን የማጥፋት ስልት፣ የጥላቻ እሳት ልቦና ውስጥ ማቀጣጠል ነው፡፡ ከተጋጋመና
ከተቀጣጣለ ይህ ጥላቻ ሰዎችን መለብለብና ማንደድ ሲጀምር የሰዎች የዛሬውም ሆነ የወደፊቱ ሕይወታቸው ሲበላሽ፣ ግንኙነታቸው
ሲበጣጠስና አመድ ሲሆን ሰይጣን ይደሰታል፤ ይረካልም፡፡
ተንኮል ክፍት ልብ ውስጥ ከተቀበረ፣ ፍቅር ይጠፋል፡፡ የጥላቻ እሳት ይቀጣጠላል፡፡ ሰዎች ጭካኔና ችኮነት ይውጣቸዋል፡፡
አላህ ያዘዘውን ይተውና በምድር ላይ መጥፎ ነገርን ያስፋፋሉ፡፡
ኢስላም የጠብ መነሻዎችን ያስገነዝባል፡፡ ነገር ከመፋፋሙ በፊትና ወደ ጥላቻ ከመቀየሩ በፊት መድሃኒቱን ጠቁሟል፡፡ ለማንም
ያልተደበቀ ነገር አለ፡፡ የሰው ልጆች በዝንባሌያቸውም ሆነ በግንዛቤያቸው የተለያዩ ናቸው፡፡ በሕይወት መስክ ላይ በሚገኙ ጊዜ የሚያጋጭና
የሚያራርቅ ባይሆንም የተወላገደና የማያስማማ ነገር ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ ስለዚህም ኢስላም ክፍፍልና አለመግባባት ከሚፈጥሩ
ነገሮች ሙስሊሞችን ለመጠበቅ መሰረት አስቀመጠ፡፡ ልቦቻቸውን በፍቅርና በመግባባት እንዲጠበቅ አደረገ፡፡
በእርግጥ አንተ ልትበደል ትችላለህ፡፡ ታዝናለህ፣ ትጨናነቃለህ፣ ትረበሻለህ፡፡ በደል ከፈጸመብህ ሰው ጋር ለመቆራረጥም
ትወስናለህ፡፡ አላህ ግን የሙስሊሞች ግንኙነት በዚህ ሁኔታ እንዲቋጭ አይፈቅድም፡፡
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “አትቆራረጡ፤ አትኮራረፉ፤ አትጣሉ፤ አትመቀኛኙ፤ የአላህ ባሪያ ወንድማማቾች ሁኑ፡፡ ለአንድ
ሙስሊም ወንድሙን ከሶስት ቀን በላይ አያኩርፈው፡፡ (ቡኻሪ ዘግበውታል)
በሌላ ዘገባ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “አንድ ሙእሚን ከሶስት ቀን በላይ ሙእሚንን የማኩረፍ መብት የለውም፡፡ ሶስት
ቀን ከሞላው ያግኘውና ሰላም ይበለው፡፡ ሰላምታ ከመለሰለት አጅር (ምንዳ) ተጋርተዋል፡፡ መልስ ካልሰጠው በእርግጥ ወንጀል
ተሸክሟል፡፡ ሰላምታ ያቀረበው ሰው ከኩርፊያ (ኃጢያት) ወጥቷል፡፡” (አቡዳውድ ዘግበውታል)
ይህ የጊዜ ገደብ ቁጣው የሚበርድበት፣ ንዴት የሚሰክንበት ጊዜ ነው፡፡ ከእዚህ የእረፍትና የመርጋት ጊዜ በኋላ ሙስሊም
ወንድሞቹን በሰላምታ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ ግንኙነቱን እንደድሮው መመለስ ይጠበቅበታል፡፡
የሰው ልጅ በየትኛውም ግጭት በዳይ አልያም ተበዳይ ነኝ ብሎ ያስባል፡፡ በዳይ (አጥፊ) ሰው በደሉን መካስ አለበት፡፡ በደል
የተፈጸመበት ሰው ልቦና በቀላሉ አይሽርም፡፡ በዳይ ተበዳይን ይቅርታ መጠየቅና መካስ ግዴታው ነው፡፡ ይህንኑ ኢስላም ቁልጭ
አድርጎ አስቀምጧል፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “የወንድሙን ክብር በመንካት ወይም በሌላ መንገድ ወንድሙን የበደለ ዲናርም
ሆነ ዲርሃም (ገንዘብ) የማይከፍልበት ቀን (የቂያማ ዕለት) ከመድረሱ በፊት፡፡ እዚሁ ይቅርታ ያስብል፡፡ ጥሩ ሥራ ካለው በሠራው በደል
ልክ ይወሰድበታል፡፡ በጎ ሥራ ከሌለው የበደለውን ሰው ወንጀል እርሱ እንዲሸከም ይደረጋል፡፡” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
ይህ የኢስላም ምክር የሰው ሐቅ ላለበት ነው፡፡ የተበደለ ግፍ የተፈጸመበት ሰው የወንድሙን ጸጸት (ተውበት) በደስታ መቀበል
አለበት፡፡ ይቅርታ አለመቀበል ከባድ ስህተት ነው፡፡
በሐዲስ እንደተዘገበው፦ “ሙስሊም ወንድሙን ይቅርታ ጠይቆ፣ ይቅርታው ተቀባይነት ካጣ፣ (ይቅርታ ተጠያቂው) ዘረፋ የፈጸመ
ሰው የሚያክል ወንጀል አለበት፡፡” (ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል)
በሌላ ዘገባ፦ “ይቅርታ ተጠይቆ ያልተቀበለ ሰው ሐውድ4 አይጠጣም፡፡”
ለበዳይም ሆነ ተበዳይ ይህንን መመሪያ በመስጠት ኢስላም ቅሬታን ይዋጋል፡፡ የጥላቻን ተባይ አንቀልባው ላይ እያለ ይገድላል፡፡
ፍትሃዊ ግንኙነትን የሚያሰፍን፣ በመከባበር ላይ የተመሰረተ ምርጥ የሙስሊም ማኅበረሰብ እንዲኖር ኢስላም ያዛል፡፡
የክፋትና ጥላቻ ልቦና ውስጥ መስረጽ በመጥፎ ባህሪ የዘቀጠ ስብእና መገለጫ መሆኑን ኢስላም ይገልጻል፡፡ እንዲህ አይነት ባህሪ
ያላቸው ብዙ ሰዎች ልቦናቸው ውስጥ ያመቁት ቂም፣ ጥላቻ፣ ክፋት መተንፈሻ ባገኘ ጊዜ ቂም የያዙበት ሰው ካልተጎዳ፣ ካልተሰቃየ፣ ማጥ
ውስጥ ካልተቀረቀረ፣ ሰላም አያገኙም፤ አይረኩም፡፡ ኢብኑ አባስ በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
“ከናንተ ውስጥ መጥፎ ሰዎችን ልንገራችሁ?›› “አዎ ፍቃድዎ ከሆነ ይንገሩን፡፡” አሉ፡፡ “ከናንተ ውስጥ መጥፎ ሰው ማለት ያ ለብቻው
የሚኖር፣ ባሪያውን የሚገርፍና ትራፊውን የሚከለክል ነው፡፡ ከዚህ የከፋ ልንገራችሁ ወይ?” “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እርስዎ ፍቃድዎ
ከሆነ አዎ፡፡” “ሰዎችን የሚጠላ ሰዎችም የሚጠሉት” አሉ፡፡ “ከዚህ በላይ የከፋ ልንገራችሁ?›› “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እርስዎ
ፍቃድዎ ከሆነ አዎ፡፡” አሉ፡፡ “እነዚያ ጥፋትን የማያልፉ ይቅርታን የማይቀበሉ፡፡ ወንጀልን የማይምሩ ናቸው፡፡” “ከዚህ በላይ አስከፊ
ልንገራችሁ ወይ?” “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አዎን” አሉ፡፡ “ጥሩ ያደርጋል ተብሎ በፍፁም የማይጠበቅ፣ በተጨማሪም ተንኮሉ
የሚፈራ፡፡…” (ጦበራኒ ዘግበውታል)
46
ሐውድ፣ ጀነት ውስጥ የምትፈስ ወንዝ ናት፡፡ (ሐውድን የጠጣ የውሃ ጥም እስከ መጨረሻው አያገኘውም፡፡ ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተከታዮች ልዩ ስጦታ ናት፡፡
ይህ ሐዲስ የቆጠራቸው ሰዎች ክፋትና ጥላቻ በሰው ልቦና ውስጥ ሲሰርጽ ሰዎች እስከምን ድረስ ሊወርዱና ሊዘቅጡ እንደሚችሉ
ለማስረዳት ነው፡፡ ስለዚህም ከኢስላም በፊት ይኖሩ የነበሩ ሰዎች እንዲህ ብለዋል፡፡ ጥላቻና ክፋት የምድራዊ ሕይወት ያማለላቸውና
የተናቁ ሰዎች ባህሪ እንጂ የተከበሩ ሰዎች ስብእና አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡
አንተራ እንዳለው :-
ባተሌ ሲተጋ ውጤት ለማምጣት፣
በትግሉ አብቦ ጎምርቶ ለማፍራት፣
ምቀኝነት አድሮ በክፋት ልቦና፣
ውርጭ ሆኖ ነፍሶ የጥፋት ዳመና፣
ታግሎ ደክሞ ነበር ሊያስቀርበት መና፣
መልፋቱ ላልቀረ እንዲህ ለጥፋት፣
ምናለ ቢተጋ ለጋራ ስኬት፣
አልያም ቢደሰት ለሌሎች ውጤት ?

ክፋትና ምቀኝነት የወንጀል ምንጭ


ከታመቀ ክፋትና ምቀኝነት የሚመነጭ በሽታ ቀላል አይደለም፡፡ ስለዚህም ኢስላም በጣም አጥብቆ ይቃወመዋል፡፡ ንጹሃን ላይ
ወንጀልን መለጠፍ የክፋት ውጤት ነው፡፡ ባልሰሩት ሥራ መወንጀል የሰውዬውን ስብእና መቅበር ነው፡፡ ማንነቱን ማስካድ ነው፡፡
የተደበቀን ስህተት ማጉላት ኢስላም ከትላልቅ ወንጀሎች ይቆጥረዋል፡፡
ዓኢሻህ (ረ.ዐ) ባስተላለፉት አቡ የእለ በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ለሶሃቦቻቸው እንዲህ አሉ፡- “አላህ ዘንድ
ከወለድ በላይ ትልቅ ወንጀል ምን እነደሆነ ታውቃላችሁን?” “አላህና መልዕክተኛው ናቸው የሚያውቁት፡፡” አሉ፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
እንዲህ አሉ፡- “ከወለድ በላይ አላህ ዘንድ ትልቅ ወንጀል የሙስሊም ወንድምን ክብር መድፈር ነው፡፡” ከዚያም ይህንን የቁርአን አንቀጽ
አነበቡ፡-
٥٨ :‫ﭽ ﮐ ﮑ ﮒ ﮓ ﮔ ﮕ ﮖ ﮗ ﮘ ﮙ ﮚ ﮛ ﭼ األحزاب‬
"እነዚያም ምእምናንንና ምእምናትን ባልሠሩት ነገር (በመዝለፍ) የሚያሰቃዩ ፣ዕብለትንና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ
ተሸከሙ፡፡" (አል-አሕዛብ: 58(
ጥሩ ሰው የሰዎችን ጥፋት በማቅለል፣ ለጥፋታቸው ማለፊያ መንገድ ያበጃል፡፡ በተቃራኒው ሰዎች ያልሰሩትን ድርጊት ሰርተዋል
ብሎ ማውራትና መለፈፍ የሰውዬውን ርካሽነት ያመላክታል፡፡ ቅጥፈት ከፍ ያለ ወንጀል በመሆኑ ቀጣፊዎች በዱንያ ላይ ቅጣት
እንዲያርፍባቸው ኢስላም ያዛል፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “አንድን ሰው ለማዋረድ ብሎ የሌለበትን ነገር ያወራ፣ አላህ (ሱ.ወ) ሰውዬውን
እሳት ውስጥ ያስረዋል፡፡” )ጦበራኒ ዘግበውታል(
በሌላ ዘገባ “ማንኛውም ሰው በሙስሊም ላይ ያላደረገውን ነገር አድርጓል ብሎ ሰዎች ዘንድ ካወራ፣ አላህ ሰውዬውን የቂያማ እለት
እሳት ውስጥ ማቅለጡ የማይቀር ነው፡፡ ለተናገረው ነገር ማስረጃ እስኪያመጣ ድረስ ቅጣቱ ይቀጥላል፡፡”
ያሰራጨው ወሬ ቅጥፈት በመሆኑ ይህ ሰው ላወራው ወሬ መከላከያ መስጠት አይችልም፡፡ አላህ ፊት ምን ይውጠዋል? ከወንጀሉ
በምን ይፀዳል?
እንዲህ ዓይነት ወሬ የሚያሰራጭ ሰው አላህ ዘንድ ርካሽ ነው፡፡

ከሐሜት ሽሽ
ጥሩ ሰው፣ ልቦናው ለሰዎች ጥሩ ነገር እንዲያቀርብ ታደርገዋለች፡፡ ጥሩ ማቅረብ ቢያቅተው እንኳ ለሰው ልጆች ጥሩ ይመኛል፡፡
መጥፎ ስራ ሰው ላይ አለማግኘቱ አበሳጭቶት ፈብርኮና ፈጥሮ፣ ቀጥፎና ዋሽቶ በሰው ላይ የሐሰት ወሬ የሚያናፍስ፣ ቀጣፊና
ውሸታም ሰው ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-
١٩ :‫ﭽ ﯳ ﯴ ﯵ ﯶ ﯷ ﯸ ﯹ ﯺ ﯻ ﯼ ﯽ ﯾ ﯿ ﰀ ﰁﰂ ﰃ ﰄ ﰅ ﰆ ﰇ ﭼ النور‬
"እነዚያ በነዚያ ባመኑት ሰዎች ውስጥ መጥፎ ወሬ እንድትስፋፋ የሚወዱ ለነሱ በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም
ዓለም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፤ አላህም ያውቃል፤ እናንተ ግን አታውቁም፡፡" )አን-ኑር: 19(
አላህ ለባሮቹ ከዋለው ውለታ አንዱና ከፍተኛው የባሮቹን ነውርና ጥፋት መሸፈኑ ነው፡፡ አላህ የሸፈነውን ጥፋትና ነውር ለሌሎች
እያወሩ፣ በሰው ነውር ላይ መዝናናት፣ ጥሩ ባህሪ አይደለም፡፡ ጥሩ ልቦና ያለው ሰው፣ የሰዎች ጥፋት ያመዋል፡፡ ያዝንላቸዋል፡፡
መድሃኒትም ያፈላልጋል፡፡ የሰዎችን ቅሌት መፈለግ፣ ግርዶ ገልጦ ማዋረድ በሰው ቁስል ላይ መጨፈር የሙስሊም ባህሪ አይደለም፡፡
ስለዚህም ኢስላም ማማትን አጥብቆ ያወግዛል፡፡ ምክንያቱም ማማት የክፋትና የቅራኔ መተንፈሻ ነው፡፡ እንዲህ አይነት ደሃ ልብ
ያለው ሰው፤ የሰውን ነውር በማራገብ ልቡ የሚጸዳ የሚረካ ይመስለዋል፡፡
አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ማማት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?”
ሰሐቦችም “አላህና መልዕክተኛው ናቸው የሚያውቁት” በማለት መለሱ፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ወንድምህ የሚጠላውን ነገር (እሱ
በሌለበት) ማውራት ነው” አሉ፡፡ እንዲህ በማለት ተጠየቁ፡- “የምለው ነገር በወንድሜ ላይ ካለስ?” ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ በማለት
መለሱ፡- “የምትለው ነገር በወንድምህ ላይ ካለ በእርግጥ አምተኸዋል፡፡ በእርሱ ላይ ከሌለ ግን በእርግጥ ስም ማጥፋት ዘመቻ
አካሂደሃል፡፡” (ሙስሊም ዘግበውታል)
ኢስላም ማሕበራዊ ግንኙነቶችን ከጠበቀበትና ቅራኔን ከተዋጋበት መንገድ ዋናው ሀሜትን ማውገዝ ነው፡፡ ምክንያቱም ማማት
ፍቅርን ያደፈርሳል፣ ልብን ያቆሽሻል፡፡
ስለዚህም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሰሓቦቻቸው የማያስደስት ነገር ለመስማት አይፈልጉም ነበር፡፡ እንዲህም ብለዋል፡- “ማናችሁም
ስለሳሓቦቼ አንዳች (መጥፎ) ነገር አትንገሩኝ፡፡ እኔ ከእናንተ ውስጥ ስሄድ ንጹህ ልብ ኑሮኝ መሄድ እወዳለሁ፡፡” (አቡ ዳዉድ ዘግበውታል)
ትንሽ መጥፎ የሰማ ሰው የሰማውን ማራባትና ማባዛት የለበትም፡፡ ምን አልባት የተወራው መጥፎ ወሬ እዚያው በመሞቱ እዚያው
ይቀበራል፡፡ በሌላ በኩል ይህ ወሬ በመባዛቱ ጦርነት ይቀሰቅሳል፡፡ አገር ያወድማል፡፡ መአት ያወርዳል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)
እንዲህ ብለዋል፡- “ነገረኛ ሰው ጀነት አይገባም፡፡” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
በሌላ ሐዲስ እንደተዘገበው፡- “ሐሜትና ክፋት የእሳት ናቸው። በሙእሚን ልብ ውስጥ አይሰበሰቡም፡፡”
ከክፋት መነሻዎች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሰውን ጥፋት መከታተል፣ በሰው ላይ መጠቃቀስ፣ ሰዎች በሚጠሉት ስም መጥራት፣
በድክመታቸው ላይ እሳት መስደድ ናቸው፡፡ ይህን ሁሉ ኢስላም ይጠላል፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “የወንድሙን ጥፋት ተመልክቶ የደበቀ ሰው፥ አላህ የቂያማ እለት የእሱን (ነውር)
ይደብቅለታል፡፡” (ጦበራኒ ዘግበውታል)
በሌላ ዘገባ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “የሙእሚንን ነውር የደበቀ የተቀበረችን ሴት በሕይወት ከመቃብር እንደ አወጣ
ይቆጠርለታል፡፡” (ጦበራኒ ዘግበውታል)
በግልጽና በገሃድ ይፋ የወጣ ወንጀል ከሚሰሩ ሰዎች በላይ ልባቸው ከአላህ የራቀ፣ ወራዳ ሥራ ውስጥ የተዘፈቁ ሰዎች ማለት፣
የሰዎችን ነውር እያሳደዱ የሚረጩ ሰዎች ናቸው፡፡ የሰውን ወንጀል ፈልጎ ማጉላት ወንጀሉን ከመፈጸም በላይ ትልቅ ወንጀል ነው፡፡
የአላህ ሕግ ተጣሰ ብሎ መንገብገብ እና የአላህ ባሪያዎችን ወንጀል ፈልጎ በማጉላትና በማድመቅ መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ፡፡
የመጀመሪያው ስሜት፤ የላቀ ደረጃ ያደርሳል፡፡ የሰውየውን ትልቅነት ያሳያል፡፡ እርሱ በሰዎች ስህተት አይረካም፡፡ የሰዎችን ውድቀት
አይጠባበቅም፡፡ በቁስላቸው ላይ አይጨፍርም፡፡ ሌላኛው ደግሞ በሌሎች ስህተት ማላገጥ እኩይነት ነው፡፡

ብሩህ አስተሳሰብን አዳብር


ብሩህ አስተሳሰብና ንጹህ ልቦና በጎ ባህሪን ይወልዳል፡፡ ምርጥ ስብእና ይቀርጻል፡፡ ይህ ሰው በምድር ላይ ያገኘውን የዱንያ ድርሻ፣
ከሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት፣ የተለያዩ መሆናቸውን ጠንቅቆ ይረዳል፡፡ ምንአልባት ሰዎች አመርቂ ውጤት ባገኙበት ዘርፍ እሱ
አልተሳካለት ይሆናል፡፡ አሊያም እሱ ወደኋላ ቀርቶ ሌሎች ሊቀድሙት ይችላሉ፡፡
እሱ ስለወደቀ፣ ስለተሸነፈ፣ ሁሉም እንዲወድቅ እንዲሸነፍ መመኘት ርካሽ ባህሪ ነው፡፡ ስለከሰርኩ አብረን እንክሰር አይባልም፡፡
ከዚህም በላይ ሙስሊም ብሩህ አስተሳሰብ፣ ቅን ልቦናና ሆደ-ሰፊ ሊሆን ይገባል። ነገሮችን ከአጠቃላይ እውነታዎች ጋር አቆራኝቶ
ማየት እንጂ ከራሱ ምኞትና ስሜት አንጻር ብቻ ማየት በፍጹም አይገባም፡፡
በክፉና ርካሽ ሰዎች ልቦና ውስጥ ምቀኝነት ይነግሳል፡፡ ምክንያቱም ዱንያን ሲመለከቷት ለራሳቸው በተመ U ት መልኩ
አምልጣቸዋለች፡፡ በሌሎች ቁጥጥር ስር ውላለች፡፡ ይህም ሰላም ይነሳቸዋል፡፡ ሁሉም ቢያጣ ይመኛሉ፡፡
ድሮም ኢብሊስ የሚፈልገውን በጎ ድርሻና ደረጃ አደም (ዐ.ሰ) ስላገኙ፣ ማንም ሰው በዚህ ደረጃ እንዳይጠቀም ማለ፤ ተገዘተ፡፡ እሱ
ስላጣ ሁሉም ይጣ አለ፡፡
‫ﭽ ﭽ ﭾ ﭿ ﮀ ﮁ ﮂ ﮃ ﮄ ﮅ ﮆ ﮇ ﮈ ﮉ ﮊ ﮋ ﮌ ﮍ ﮎ ﮏﮐ ﮑ ﮒ ﮓ ﮔ ﮕ ﭼ األعراف‬
"ስለአጠመምከኝም ለነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ አለ፤ ከዚያም
ከበስተፊቶቻቸው፣ ከኋላቸውም፣ ከቀኞቻቸውም፣ ከግራዎቻቸውም፣ በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ፤
አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ኾነው አታገኛቸውም፡፡"
(አል-አዕራፍ: 16-17)
ይህ ሰይጣናዊ ስሜት፣ ንዴትና ብሽቀት በክፉና በምቀኛ ሰዎች ልቦና ውስጥ ይሰክናል፡፡ ልቦናቸውን ሰላም ይነሳዋል፡፡ ኢስላም
ሰዎች ከዚህ ስሜት እንዲወጡ መክሯል፡፡ ህይወታቸውንም በተረጋጋና በላቀ ጎዳና እንዲመሩ መንገዱን አሳይቷል፡፡
አነስ ኢብን ማሊክ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡- “ከአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ተቀምጠን ሳለን ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡-
‘አሁን የጀነት ሰው ወደናንተ ብቅ ይላል፡፡’ ከአንሷር (ከመዲና) የሆነ ሰው ብቅ አለ፡፡ የውዱእ ውሃ ከጺሙ ላይ ይንጠባጠባል፡፡
ጫማውንም በግራ እጁ ይዟል::በሚቀጥለውም ቀን ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በድጋሚ እንደ መጀመሪያው ቀን ተናገሩ:: ያው ሰውዬ በመጀመሪያ
ቀን በነበረበት ሁኔታ ላይ ሁኖ ብቅ አለ፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተነስተው ሲሄዱ ዐብደላህ ኢብን አምር ሰውዬውን ተከትሎት ሄደ:: እንዲህም
አለው፡- ‘እኔ ከአባቴ ጋር ተጋጭቼ ነበር፡፡ እሱ ቤትም ለሶስት ቀን እንደማልገባ ምያለሁ፡፡ ይህን ጊዜ ሦስት ቀን እስኪያልፍ አንተ ጋር
የምታስቀምጠኝ ከሆነ እቀመጣለሁ፡፡’ ‹‹እሺ›› አለው፡፡ አነስ እንዲህ አለ፡- “ዐብዱላህ (ሰውየው ቤት በእንግድነት የተቀመጠው ሰው
እነዚያን ሶስት ቀናት ሰውየው ጋር ማደሩን፣ እንዲሁም ሰውየው ለሊት ቁሞ ሲሰግድ እንዳላየው፣ ግን በመሃል ከእንቅልፍ ሲባንን
ሲገላበጥ አላህን እንደሚያወሳ፣ ለሱብሂ ሰላት ሲነሳ እንዳየውና ክፉ ሲናገር እንዳልሰማ ተናግሯል፡፡)” ሶስት ሌሊት ካደርኩ በኋላ ሌሊት
በሚሰራው ስራ ስላልተደነቅኩኝ እንዲህ አልኩት፡፡ ‹‹ዐብደላህ ሆይ! በእኔና በአባቴ መካከል ኩርፊያ የለም፡፡ ግን የአላህ መልዕክተኛ
(ሰ.ዐ.ወ) ‹‹ወደ እናንተ አሁን አንድ የጀነት ሰው ብቅ ይላል›› ብለው ሶስቴ ተናገሩ፡፡ በሶስቱም ጊዜ አንተ ብቅ አልክ፡፡ እኔም ወደ አንተ
መጠጋትና ስራህን ለመመልከት የአንተን አርአያ ለመከተል ወሰንኩ፡፡ ሆኖም ትልቅ የሚባል ስራ አልሰራህም፡፡ እንዴት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
እዚህ ደረጃ መድረስህን ተናገሩ?›› ሰውየውም እንዲህ በማለት መለሰ፡- ‹‹ነገሩ ልክ አንተ ያየኸው ብቻ ነው፡፡›› መንገድ ከጀመርኩ በኋላ
ጠራኝና ‹‹ነገሩ የተመለከትከው ብቻ ነው፡፡ ሆኖም እኔ ለየትኛውም ሙስሊም በልቦናዬ ውስጥ ተንኮልና ምቀኝነት የለኝም፡፡ አላህ
በሰጣቸው ደረጃ አልመቀኝም፡፡’ ዐብዱላህም እንዲህ አለው፡፡ ‹‹ይህቺ ናት፡፡ እዚህ ደረጃ ያደረሰችህ፡፡›› (አህመድ ዘግበውታል)
በሌላ ዘገባ ‹‹የወንድሜ ልጅ ሆይ! ስራዬ ያየኸው ነው፡፡ ሆኖም እኔ በሙስሊም ላይ ቂሚ ይዤ አላድርም፡፡››

አትመቀኝ
ኢስላም ምቀኝነትን ሐራም አድርጓል፡፡ አላህ ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ከምቀኞች ተንኮል በአላህ እንዲጠበቁ አዟል፡፡ ምክንያቱም
ምቀኝነት ፍም ነው፡፡ ልብ ውስጥ ይቀጣጠላል፡፡ ምቀኛውንም ሆነ ሌሎች ሰዎችንም ያቃጥላል፡፡ ያጠፋል፡፡
የሰዎች ጸጋ እንዲወገድ የሚመኝ ሰው፣ እንቅፋት ነው፡፡ አደጋ ነው፡፡ ሕብረተሰብን አደጋ ላይ እንዳይጥል ያሰጋል፡፡ ስለማይታመን
የሰራውን ስራ በእርጋታ ለመቀበል ያዳግታል፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “በአላህ ባሪያ ሆድ ውስጥ፣ በአላህ መንገድ ላይ የነካው አቧራና የጀሀነም ወላፈን
አንድ ላይ አይገኝም፡፡ እንዲሁም በባሪያው ሆድ ውስጥ ኢማንና ምቀኝነት አንድ ላይ አይሰባሰቡም፡፡ (በይሀቂ ዘግበውታል)
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “አደራችሁን ምቀኝነትን ተጠንቀቁ፡፡ እሳት እንጨትን እንደምትበላ ምቀኝነትም ጥሩ ሥራን
ትበላለች፡፡” (አቡዳውድ ዘግበውታል)
ያላቸውን ሰዎች የሚጠላ፤ ተቸግረው እንዲውሉ፣ አጥተው እንዲያድሩ፣ የሚፈልግ በእርግጥ የሕይወት ትርጉም አልገባውም፡፡
አእምሮው በጨለማ ተውጧል፡፡
ሰውየው በመጀመሪያ ነገሮችን ከዱንያ አርቆ ማሰብ አይችልም፡፡ ለዱንያ ይሞታል፡፡ ለሷም ያለቅሳል፡፡ ከዱንያ የተወሰነ ከፍተኛ
ደረጃ ያገኙ ሰዎችን ይጠላል፡፡ ይረግማል፡፡ ይህ አስተሳሰብ በዱንያም ሆነ በመጪው ዓለም ግንዛቤ የጠለሸ አመለካከት ነው፡፡ እንደውም
ለመጪው ዓለም (አኼራ) ያለው ግንዛቤ መሃይምነት የተሞላበት ነው፡፡ የሰው ልጅ ሊቆጭና ሊንገበገብ የሚገባው፣ አኼራን ሲያጣ፣
መንገዱ ሲከብደውና ሲቸግረው ሊሆን ይገባል፡፡
‫ﭽﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﭼ‬
"እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሣጼ፣ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድሀኒት
ለምእመናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ፡፡ በአላህ ችሮታና እዝነቱ (ይደሰቱ) በዚህም ምክንያት
ይደሰቱ፡፡ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው፤ በላቸው፡፡ ")ዩኑስ: 57-58(
ምቀኛ ሰው፤ ልፍስፍስ፣ አቋምየለሽ ደካማ እና ሰነፍ ነው፡፡ ጌታውን አያውቅም፡፡ የምድርን ሂደት አልተረዳም፡፡ ቂል ባይሆን ኖሮ
አንድ ጥሩ ነገር ሲያጣ ለውጤታማ ሰዎች ጉድጓድ አይቆፍርም፡፡ ተንኮል አያስብም፡፡
መድረስ ቢያቅት ከዳገቱ፣
ባይጐብዝ ለስኬቱ፣
አብሮ ማደግ ካልተቻለ፣
አብሮ መውደቅ ተሻለ።
አላህን ቢማጸን፣ ወደጌታው ቢያለቅስ፣ አላህ ከችሮታው እንዲለግሰው ቢጠይቅ የተሻለ ነበር፡፡ የአላህ መጋዘን ለተለየ ሰው ብቻ
የተቀመጠ አይደለም፡፡ ሕይወቱን እያደሰ፣ እየጣረ፣ እየተጋ፣ ቢጓዝ የተሻለ ነበር፡፡ ምንአልባትም መጀመሪያ ላይ ያጣውን በሁለተኛው
ሊደርስበት ይችላል፡፡ ይህ ተግባር ከክፋትና ከተንኮል ሙሉ በሙሉ የተሻለ የብልሆች ስራ ነው፡፡
በምቀኝነትና ጥሩን ነገር ለማግኘት በመጓጓት፣ በምቀኝነትና በጥሩ ነገር በመቅናት፣ መካከል ግዙፍ ልዩነት አለ፡፡ ጥሩን ነገር
ለማግኘት መጓጓት፣ መጣር፣ መልፋት ምርጥ የአላህ ባሪያዎች ባህሪ ነው፡፡
ነቢዩላህ ሱለይማን (ዐ.ሰ) እንዲህ ብለዋል፡-
٣٥ :‫ﭽﮫ ﮬ ﮭ ﮮ ﮯ ﮰ ﮱ ﯓ ﯔ ﯕ ﯖ ﯗﯘ ﯙ ﯚ ﯛ ﭼ ص‬
"ጌታዬ ሆይ! ለኔ ማር፤ ከኔ በኋላ ለአንድም የማይገባንም ንግሥና ስጠኝ፡፡ አንተ ለጋሱ አንተ ብቻ ነህና አለ፡፡ "
)ሷድ: 35)
የአር-ረሕማን ባሪያዎች እንዲህ ይላሉ፡-
٧٤ :‫ﭽ ﮣ ﮤ ﮥ ﮦ ﮧ ﮨ ﮩ ﮪ ﮫ ﮬ ﮭ ﮮ ﮯ ﭼ الفرقان‬
"እነዚያም ጌታችን ሆይ! ከሚስቶቻችንና ከዘሮቻችን የዓይኖች መርጊያን ለኛ ስጠን፤ አላህን ለሚፈሩትም መሪ
አድርገን፤ የሚሉት ናቸው፡፡" )አል- ፉርቃን: 74(
ጥሩን ነገር ለማግኘት ጉጉ መሆን፣ የሚፈልጉትን ለመጎናፀፍ ከፍተኛ ጥረት ማድረግና ጥሩ ነገር አላህ ያጎናፀፈውን ሰው ተመልክቶ
እሱን ለመሆን መጣር በኢስላም የሚጠላ አይደለም፡፡

የሌሎችን መመኘት
ኢስላም ሰዎች ሊጓጉባቸውና ሊቀኑባቸው የሚገቡ ነገሮችን አስቀምጧል፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ ሌሎች ያገኙትን ሁሉ ለኔም
ይጠቅመኛል በማለት በቀቢጸ ተስፋ መዋዠቅ የለበትም፡፡ በኢስላም ሌሎች የተጎናጸፉትን ነገር ለመጎናጸፍ መጣር አይከለከልም፡፡
በሌሎች መቅናት፣ እነሱ ላይ ለመድረስ መሽቀዳደም፣ የሚፈቀደው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በተናገሯቸው ነገሮች ላይ ብቻ ነው፡፡
ታላቁ ነቢይ ይህንን ብለዋል፡- “ቅናት በሁለት ነገሮች እንጂ አይቻልም፡፡ አላህ ሀብት የሰጠው ሰው ሀብቱንም በእውነት ነገር
ላይ ብቻ በሚያውል፡፡ እንዲሁም አላህ ጥበብን ሰጥቶት፣ ጥበቡን በሚያስተምር በሰዎች መካከልም በበጎ የሚፈርድ፡፡ (ቡኻሪ ዘግበውታል)
በዚህ ሐዲስ የተገለጸው ቅናት መልዕክቱ የሰውዬውን አይነት ጸጋ መፈለግ እንጂ የሱ ጸጋ እንዲጠፋ መመኘት ማለት አይደለም፡፡
የዚህ ሐዲስ መልዕክት የሰው ልጅ ዓላማ ትልቅ፣ ምርጥ ሊሆን እንደሚገባው ነው፡፡ የማይረባና ተራ ነገር እየተለሙ መኖር፣ ወኔ ቢስነትን
ያመላክታል፡፡ አንዳንድ ልዩ ተሰጥኦዎችን አገኛለሁ ብሎ መመኘት፣ አየር ለመዝገን መሞከር ነው፡፡ ልቦና ውስጥ ክፋትና ምቀኝነትን
መትከል ነው፡፡ ምክንያቱም አላህ (ሱ.ወ) ለአንዳንድ ሰዎች ብቻ የሰጠው የተፈጥሮ ስጦታዎች አሉ፡፡ በነዚያም የአላህ ተፈጥሯዊ
ስጦታዎች፣ ሰውዬው ሊታወቅበት፣ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ በዚህና በመሰል ጉዳዮች ላይ አላህ በቁርአን እንዲህ ይላል፡-
٣٢ :‫ﭽ ﮟ ﮠ ﮡ ﮢ ﮣ ﮤ ﮥ ﮦ ﮧﮨ ﮩ ﮪ ﮫ ﮬﮭ ﮮ ﮯ ﮰ ﮱﯓ ﯔ ﯕ ﯖ ﯗﯘ ﯙ ﯚ ﯛ ﯜ ﯝ ﯞ ﭼ النساء‬
"አላህም ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በርሱ ያበለጠበትን ጸጋ አትመኙ፡፡ ለወንዶች ከሠሩት ሥራ ዕድል አላቸው፤ ለሴቶችም
ከሠሩት ሥራ ዕድል አላቸው፡፡ አላህንም ከችሮታው ለምኑት፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡")አን-ኒሳእ: 32(
ስህተትን መፋለም፣ ድክመትን መሃየስ፣ ፍትሃዊነት ነው፡፡ ግዴታም ነው፡፡ ይህ ምቀኝነት አይባልም፡፡ ሰው ያልሠራውን ሲያፍስ፣
ያለ ደረጃው ወሳኝ ቦታዎችን ሲቆጣጠር፣ ያለልኩ ሲለብስ መናገርና መተቸት አግባብ ሊሆን ይችላል፡፡ የብዙሃንን መብት የማስከበር
ስሌት እስከሆነ ድረስ ግላዊ ክፋትና ምቀኝነትን አያሳይም፡፡
ኢስላም ነፍሳችንን በየጊዜው እንድንመረምር ያዛል፡፡ ከርካሽ ምቀኝነት እንድትጸዳ የሚያስችላት ሥርዓት አበጅ~ል፡፡
ሙስሊሞች ለሕይወት ለሰው ልጅ ንጹሕ አመለካከት እንዲኖራቸው፣ ንጹህ መንፈስ፣ ንጹህ ፍቅር በዓለም ላይ እንዲያሰፍኑ ኢስላም
ያዛል፡፡
ስለዚህም ኢስላም ሙስሊሞች ልባቸውን በፍቅር እንዲሞሉና በየቀኑ፣ በየሳምንቱ፣ በየዓመቱ፣ ንጹህ ፍቅር ልቦናቸው ውስጥ
መኖሩን እንዲመረምሩ ያደርጋል፡፡ ኢስላም ሁሌም ሰው ምን ላይ እንዳለ ራሱን እንዲመዝን ከሰላት ጋር ትስስር እንዲፈጥር
አድር¹ል፡፡ ኢስላም በግልጽ እንዳስቀመጠው አንድን ሰው የሰላትን አጅር (ሽልማት) የሚያጎናጸፈው፣ ልቡ ንጹህ፣ ለሰዎች ቀና የሆነ፣
ከማጭበርበርና ከጭቅጭቅ ከጸዳ ብቻ ነው፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “ሦስት ሰዎች ሰላታቸው ስንዝር እንኳ (ወደ ሰማይ) አትጓዝም፡፡ ሰዎች እየጠሉት
ኢማም (አሰጋጅ) የሆነ ሰው፡፡ ባሏ ተቆጥቶባት ያደረች ሴት፡፡ የተቆራረጡ ወንድማማቾች (ሙስሊሞች)፡፡ )ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል(
የሳምንት መገምገሚያም አለ፡፡ ሙስሊም የሚሠራውን የትኛውንም ሥራ የሚቆጠርበት ቀን አለ፡፡ የሰው ልጅ የፈጸመውንም ሆነ
በልቡ ያሰበውን ጉዳይ አላህ ይመለከተዋል፡፡ በዚህም ላይ ፍርዱን ይሰጣል፡፡ ንጹህ ልብ ካለው ፈተናውን በድል ይወጣል፡፡ ልቡ
በክፋትና በምቀኝነት የጠለሸ ከሆነ ፈተናውን ይወድቃል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “ሐሙስና ሰኞ ሥራዎች ወደ
አላህ ይቀርባሉ፡፡ የዚያም ቀን አላህ (ሱ.ወ) በአላህ ላይ ምንም የማያጋራ ሰውን ሁሉ ይምራል፡፡ ከወንድሙ ጋር የተጣላ ሰው ሲቀር፡፡
ይህን ሰው አላህ ‘እነዚህ ሰዎችን እስኪታረቁ ተውዋቸው’ ይላል፡፡” )ሙስሊም ዘግበውታል(
የአመታዊው የመገምገሚያ መንገድ ይህ ነው፤ ቀናት በሌሊት ተለውጠው፣ ሳምንታት በወራት ተቀይረው፣ ወራት ዓመትን ሲወልዱ
የሰው ልጅ በዚህ ሁሉ የዱንያ ዑደት ውስጥ የእሱ ልቦና በጥላቻ፣ በክፋት፣ በቁጣና በቁጭት ሰንሰለት ሊታሰር አይገባም፡፡
አላህ (ሱ.ወ) በሰዎች መኖሪያ፣ ምድር ላይ እዝነቱንና ምህረቱን ለሰው ልጆች ይለግሳል፡፡ ይህን እጣ ግን የሚያገኙት ንጹህ ልብ
ያላቸው፣ ሆደ-ሰፊና ይቅር ባይ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡
በሐዲስ እንደተዘገበው፦ “አላህ (ሱ.ወ) በሸዕባን ወር ግማሽ ላይ ባሪያዎቹን ይመለከታል፡፡ ምህረት አድራጊዎችን ምህረት
ይሰጣል፡፡ ለአብዛኞች እዝነቱን ይለግሳል፡፡ ልባቸው (ክፉ) ነገር የቋጠሩ ሰዎችን እንዳሉ ይተዋቸዋል፡፡” )በይሀቂ ዘግበውታል(
በዚህ ሁሉ ልብ የማጽጃ እንዲሁም ልብን ከበሽታ የሚያነጻ ተከታታይ ህክምና ሳይጠቀም ልቡ በክፋትና በቁጭት ተተብትባ የሞተ
ሰው፣ እሳት መግባት ይኖርበታል፡፡ ሸሪዐዊ ሃይማኖታዊ ምክሮች ልቡን ሊያጸዱት ከተሳናቸው፣ ጀሀነም እሱን ማስተካከል
አያስቸግራትም፡፡ ወንጀሉንም ክፋቱንም ታራግፍለታለች፡፡

ለዱንያ ብለህ አትጣላ


በዱንያ ስሜት፣ በጥቅማጥቅምና በስግብግብነት ምክንያት የሚከሰትን መኳረፍ፣ መጣላትና መቆራረጥ ኢስላም ያወግዛል፡፡ የአላህ
ድንበር ሲጣስ መቆጣት፣ የማያሻማ ሐቅ ሲደፈር እና የሰዎች ክብር ያለአግባብ ሲጎድፍ መናደድ ተፈጥሯዊ ጉዳይ ነው፡፡ በእነዚህ
ጉዳዮች የተነሳ ከሰዎች ጋር እስከ ሞት ቢኳረፍ ጥፋተኛ ላይባል ይችላል፡፡ የአላህን ትእዛዝ ከሚጥስ፣ ድንበር ከሚያልፍና ከሚያውክ
ሰው ጋር መጋጨት ላያስወቅስ ይችላል፡፡ እንዲያውም እነዚህ ነገሮች የትክከለኛ ኢማን መገለጫዎች ናቸው፡፡ ሰውዬው ለአላህ ያለውን
ኢኽላስ (ቅንነት) ያሳያል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የእሱን ጠላቶች ዘመዶቻችን እንኳን ቢሆኑ የልብ ወዳጅ አድርገን እንዳንይዛቸው አዞናል፡፡
‫ﭽ ﭦ ﭧ ﭨ ﭩ ﭪ ﭫ ﭬ ﭭ ﭮ ﭯ ﭰ ﭱ ﭲﭳ ﭴ ﭵ ﭶ ﭷ ﭸ ﭹ ﭼ التوبة‬
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አባቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ክሕደትን ከእምነት አብልጠው ቢወዱ ወዳጆች አድርጋችሁ
አትያዙዋቸው፤ ከናንተም ውስጥ ወዳጅ የሚያደርጋቸው እነዚያ እነሱ በዳዮች ናቸው፡፡ " (አት-ተውባህ: 23(
ሆን ብለው አደጋ የሚፈጥሩ፣ ቁምነገር ከቀልድ የማይለዩ እና እንቶ ፈንቶ ማውራት የማይደክማቸው ሰዎችን መራቅና መጠንቀቅ
ግዴታ ነው፡፡ የአላህን ሐቅ የማያውቅ ሰው ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ማኩረፍ ጥሩ ቅጣት ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሚስቶቻቸው
ውስጥ የተወሰኑትን ለአርባ ቀን አኩርፈዋቸው ነበር፡፡ ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር ልጃቸውን እስከሞት ድረስ አኩርፈዋቸዋል፡፡ ምክንያቱም
አባታቸው (ዑመር) የሚያወሩትን “ሴቶች ወደ መስጂድ መሄድ የሚፈቅደውን የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲስ አልቀበልም" ስላሉ፡፡ (እንዲህ
ዓይነት ሐዲሶች በስሜትና በስማ በለው ሃይማኖታዊ ትእዛዛት ተጣሱ ብለን ወደ ጠብና ወደ ኩርፊያ እንደንሄድ በር እንዳይከፍቱ
መጠንቀቅ ያሻል፡፡)

የንግግር ሥነ-ሥርዓት
ሃሳብን በንግግር መግለጽ መቻል አላህ (ሱ.ወ) ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ታላላቅ ፀጋዎች አንዱ ነው፡፡ የሰው ልጅም ብቸኛ ስጦታ
ነው፡፡
‫ﭽﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﭼ‬
"አር-ረሕማን፤ ቁርኣንን አስተማረ፡፡ ሰውን ፈጠረ፡፡ መናገርን አስተማረው" (አር-ረሕማን፡ 1-4)
የአንድ ፀጋ ክብደት የሚገለፀው በፀጋው ትልቅነት ልክ ነው፡፡ እንደ ፀጋው ግዝፈት ምስጋናውም ከፍ እያለ መሄድ አለበት፡፡
ውለታን መካድ ታላቅ ወንጀል ነው፡፡
ኢስላም የሰው ልጅ የንግግርን ፀጋ እንዴት መጠቀም እንዳለበት አብራርቷል፡፡ የሰው ልጆች በሚናገሩበት ጊዜ ሁሉ ወደ አላህ
እንዴት መቅረብ እንደሚችሉ አስተምሯል። የንግግር ሥርዓት አስቀምጧል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ንግግር ከጀመሩ አያቆሙም፡፡ ምላሳቸው
ለአፍታም ዝም አይልም፡፡ የተናገሩትን ነገር ብታስተውል፣ ከንግግራቸው ለዛቢስ ቀልዶች ወይም አሉባልታዎች ይበዙበታል፡፡ አላህ
ምላስን አፍ ውስጥ የተከለው ለከንቱ ነገር እንድንጠቀምበት አይደለም፡፡
‫ﭽ ﭒ ﭓ ﭔ ﭕ ﭖ ﭗ ﭘ ﭙ ﭚ ﭛ ﭜ ﭝ ﭞ ﭟ ﭠ ﭡﭢ ﭣ ﭤ ﭥ ﭦ ﭧ ﭨ ﭩ ﭪ ﭫ ﭬ ﭭ ﭼ‬
"ከውይይታቸው በምጽዋት ወይም በበጎ ሥራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች
ውይይት በስተቀር በብዙው ውስጥ ደግ ነገር የለበትም፡፡ ይኸንንም (የተባለውን) የአላህን ውዴታ
ለመፈለግ የሚሠራ ሰው ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን፡፡" (አን-ኒሳእ፡ 114)
ኢስላም ለንግግር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቷል፡፡ ንግግር እንዴት መሆን እንዳለበት አብራርቷል፡፡ ንግግር ከአንድ ሰው አንደበት
ይወጣል፡፡ ንግግሩም የሰውየውን አስተሳሰብ፣ ባህሪ፣ ፀባይ፣ ቁልጭ አድርጐ ያሳያል፡፡ በአንድ ስብሰባ ውስጥ የሚደረጉ የንግግር
ልውውጦች የተሰብሳቢዎችን ማንነት ለመገምገም ይረዳል፡፡ በዚያ ስብሰባ ውስጥም በጎ ስብእና ያላቸው ተናጋሪዎች በመልካም አንደበት
ሃሳባቸውን ይገልፃሉ፡፡
አንድ ሰው ለሌሎች መናገር ከመጀመሩ በፊት ቆም ብሎ ይበል፡፡ ማሰብ ይገባዋል ይኸውም ለመናገር የሚያነሳሳ ነገር አለ ወይ?
መናገሩ አስፈላጊ ከሆነ ይናገር፡፡ አልያም ዝም ይበል፡፡ አስፈላጊ ባልሆነ ነገር ላይ ንግግርን መተው በአላህ ዘንድ ትልቅ ሽልማት ያለው
ኢባዳ (አምልኮ) ነው፡፡
ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡- “ከእሱ በቀር ሌላ አምላክ በሌለው እምላለሁ፡፡ በዚህች ምድር ውስጥ
ከምላስ በላይ ለረጅም ጊዜ በቁጥጥር ስር ሊውል የሚገባው ነገር የለም፡፡፡” (ጦበራኒ)
ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡- “አምስት ነገሮች ምርጥ ፈረስ ለሰደቃ ከመለገስ ይበልጣሉ፡- (የማያገባህን
መናገር) ትርፍ ነገር ነውና ራስህን ከአሉባልታ አርቅ፡፡ ከወንጀልም ይጠብቅሀል፡፡ የሚመለከትህም ነገር ቢሆን መናገር ያለብህ ቦታ
እስክታገኝ አትናገር፡፡ መነገር ባለበትም ሁኔታ ያለቦታው መናገር ደግሞ ነውር ነው…!” ከሞኝ እና ከሆደ ሰፊ ሰው ጋር አትሟገት፡፡
ሆደ ሰፊው ሰው ይንቅሀል፡፡ ሞኙ ሰላም ይነሳሀል፡፡ ወንድምህ በሌለበት እሱ አንተን እዲያነሳህ በምትፈልግበት አንተም እሱን
አውሳው፡፡ እሱ ስለአንተ እንዲያወራ የማትፈልገውን ነገር አንተም ስለእሱ አታውራ፡፡ አንድ ጥሩ ጉዳይ ስትጀምር ጥሩ ከሰራህ ምንዳ
እንደምታገኝ መጥፎ ከሰራህ እንደምትጠየቅ ሁነህ ስራ፡፡” (ኢብን አቢ ዱንያ ዘግበውታል)
ሙእሚን ይህን በተግባር ለማዋል ምላሱን መቆጣጠር፣ ዝም ማለት ያለበት ቦታ ዝም ማለት መቻል ግድ ይለዋል፡፡ ምላሱን
እንደፈለገው የሚለቃት ሰው በእርግጥ ወደ ጀሀነም ተገፍቷል፡፡
ወግ ማንዛዛት አእምሮን ያበላሻል፡፡ አስተዋይነትን ይቀንሣል፡፡ ብዙ ጊዜ በየስብሰባው ንግግር የሚያንዛዙ ሰዎች የሚሰጡት
ሀሳብም ብስል አለመሆኑን አድማጮች ይገነዘባሉ፡፡ የአመለካከት ብስለትና ወሬ ማንዛዛት አንድ ላይ የሚሄዱ አይደሉም፡፡
አንድ ሰው ሀሳቡን ለመሰብሰብ ወይም ስራውን ለመገምገም ሲፈልግ ዝምታን ይመርጣል፡፡ ከጩኸትና ከግርግር ርቆ ወደ
ብቸኝነት ይሸሻል፡፡ ዝምታ ወደ ሰፈነበት መንደር ይዘልቃል፡፡ ኢሰላም ካላስፈላጊ ንግግር ዝምታን ይመክራል፡፡ ዝምታ ጥሩ ስብእና
ከመገንቢያ መንገዶች አንዱ ነው፡፡
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አቡዘርን (ረ.ዐ) ከመከሩት ምክሮች ውስጥ “ለረጅም ጊዜ ዝም በል፡፡ ዝምታ ሰይጣንን ያባርራል፡፡ እንዲሁም
ለዲንህ እገዛ ነው፡፡” (አህመድ ዘግበውታል)
ምላስ በሰይጣን እጅ በቀላሉ እየተንቀሳቀሰ ሰውየውን አደጋ ውስጥ ሊከተው ይችላል፡፡ ሰውየው ምላሱን ካልተቆጣጠረ ምላስ
ቀልብን ያቆሽሻል፡፡ የስንፍናና የድክመት አቧራ በልቡ ላይ ይጋገራል፡፡የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “የአንድ ሰው ልቡ
ካልተስተካከለ ኢማኑ አይስተካከልም፡፡ አንደበቱ ካልተስተካከለ ደግሞ ቀልቡ አይስተካከልም፡፡” (አህመድ ዘግበውታል)
የሐዲሱ አስተምህሮት መጀመሪያ ሰውየው በማያገባው ነገር መግባት የለበትም፡፡
“የአንድ ሰው በማያገባው ነገር አለመግባቱ ኢማኑ ያማረ መሆኑን ያመለክታል፡፡” (ቲርሚዚ ዘግብውታል)
ከማይረባ ቀልድና ፌዝ መራቅ ለስኬት መሰረት ነው፡፡ የምሉዕ ስብእናም መገለጫ ነው፡፡ ቁርኣን የምእመናንን ባህሪ ሶላትና
ዘካ ሲገልፅ በአንፃሩ ከአሉባልታ የራቁ መሆናቸውን ያሰምርበታል፡፡
٤ - ١ :‫ﭽ ﭑ ﭒ ﭓ ﭔ ﭕ ﭖ ﭗ ﭘ ﭙ ﭚ ﭛ ﭜ ﭝ ﭞ ﭟ ﭠ ﭡ ﭢ ﭣ ﭤ ﭥ ﭼ المؤمنون‬
"ምእመናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡ እነዚያ እነሱ በስግደታቸው ውስጥ (አላህን)
ፈሪዎች፤ እነዚያም እነሱ ከውድቅ ንግግር ራቂዎች፤ እነዚያም እነሱ ዘካን ሰጭዎች፤.." (ሙእሚኑን፡ 1-4)
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰው ልጅ ብዙ ጊዜውን የሚያጠፋበትን ነገር ቢፈትሽ፣ በፌዝ፣ በጨዋታ፣ በቀልድና በሌሎችም አልባሌ
ነገሮች ረጅም ጊዜ ማጥፋቱን ያረጋግጣል፡፡ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ እውቅና ያላቸው ጋዜጦች፣ መጽሔቶች፤ ብዙ ሺህ ዲስኩሮችና
ዜናዎች ዓይንን ያማልላሉ፡፡ ጆሮን ያጓጓሉ፡፡ ግን ፋይዳቸው ግን እምብዛም ነው፡፡ በእርግጥ ኢስላም አሉባልታን ይጠላል፡፡ ዕርባና ቢስ
ነገሮችን አጥብቆ ይነቅፋል፡፡ እድሜን በከንቱ ማባከን ነውና፡፡ የሰው ልጅ የተፈጠረበትን ቁም ነገርም ያመክናልና፡፡
አንድ ሙስሊም አሉባልታን በራቀ ቁጥር ልክ ከአላህ ጋር ያለው ደረጃ ይጨምራል፡፡ ከአነስ ኢብኑ ማሊክ (ረ.ዐ) የተላለፈው
ሐዲስ እንዲህ ይላል፡- አንድ ሰው ሞተ፡፡ ሌላ ሰው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እየሰሙት ለሞተው ሰው “አይዞህ ጀነት ለአንተ ነው” አለ፡፡ የአላህ
መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- “ምን የምታውቀው ነገር አለ? ምናልባት አሉባልተኛ አልያም የባለፀጋ ንፉግ ሊሆን ይችላል፡፡”
(ቲርሚዚ ዘግበውታል)
አሉባልተኛ ሰው ስለንግግሩ ውጤት አያስብም፡፡ ምናልባትም በተናገረው ንግግር ምክንያት ሕይወቱን ያበላሻል፡፡ ተስፋውንም
ያጨልማል፡፡ አንድ የብልህ አባባል አለ፡- “ወሬ ያበዛ ስህተቱ ይበዛል!!” “የምላስ ወለምታ በቅቤ አይታሽም፡፡”
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብልዋል፦ “አንድ ሰው አንድ ነገር ከአንደበቱ ይወጣል፡፡ ዓላማው ሰዎችን ለማሳቅ ብቻ
ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ (መጥፎ) ንግግር ምክንያት ከሰማይ ወደ ምድር ይወረወራል፡፡ ሰው እግሩ አሰናክሎት ከሚመጣበት አደጋ ይልቅ
ምላሱ ያሰናክለዋል፡፡” (በይሀቂ)
አንድ ሰው ከተናገረ ጥሩ ይናገር፡፡ ምላሱንም ጥሩ መናገር ያለማምዳት፡፡ በውስጥ የሚብላላን ሃሳብ በጥሩ አንደበት መግለጽ
ምርጥ ችሎታ ነው፡፡ አላህ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮችን ሁሉ ጥሩ እንዲናገሩ አዟል፡፡ ሙሳ (ዐ.ሰ) የእስራኤል ልጆችን በጥሩ ንግግር
እንዲያዛቸው መታዘዙን ቁርኣን አብራርቷል፡፡
٨٣ :‫ﭽ ﯗ ﯘ ﯙ ﯚ ﯛ ﯜ ﯝ ﯞ ﯟ ﯠ ﯡ ﯢ ﯣ ﯤ ﯥ ﯦ ﯧ ﯨ ﯩ ﯪ ﯫ ﯬ ﭼ البقرة‬
"የእስራኤል ልጆችንም ጥብቅ ኪዳን፦ አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ በወላጆችም በግጐን ሥራ
(አድርጉ)፤ በዝምድና ባለ ቤቶችም፣ በየቲሞችም፣ (አባት የሌላቸው ልጆች) በምስኪኖችም፣ (በግጐ
ዋሉ)፤ ለሰዎችም መልካምን ተናገሩ፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ፣ በማለት
በያዝንባቸው ጊዜ (አስታውሱ) ፤ከዚያም ከናንተ ጥቂቶች ሲቀሩ ሸሻችሁ፤ እናንተም (ኪዳንን)
የምትተው ናችሁ፡፡" (አል-በቀራህ፡ 83)
ሥርዓት ያለው ጥሩ ንግግር ከወዳጅም ሆነ ከጠላት ጋር ያምራል፡፡ ጥሩ ፍሬም ይሰጣል፡፡ ጥሩ ንግግር ከወዳጅ ጋር ፍቅርን
ይጠብቃል፡፡ ጓደኝነትን ያዘወትራል፡፡ የሸይጣንን ተንኮል ያከስማል፡፡ ከጠብና ከመራራቅ ይታደጋል፡፡
٥٣ :‫ﭽ ﮀ ﮁ ﮂ ﮃ ﮄ ﮅﮆ ﮇ ﮈ ﮉ ﮊﮋ ﮌ ﮍ ﮎ ﮏ ﮐ ﮑ ﭼ اإلسراء‬
"ለባሮቼም በላቸው፡- ያችን እርሷ መልካም የኾነችውን (ቃል) ይናገሩ፤ ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና፤
ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና፡፡" (አል-ኢስራእ፡ 53)
ሰይጣን የሰው ልጆችን ለማጋጨትና ለማራራቅ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡ በሰዎች መካከል የሚከሰት አለመግባባት
ያስደስተዋል፡፡ ነገር አቀጣጥሎ ለማጣላት ይጥራል፡፡ ይህንን ተንኮል ጥሩ ንግግር ያከስመዋል፤ ያመክነዋልም፡፡ ከጠላት ጋር የሚደረግ
መልካም ንግግር የጠላትነት ስሜትን ያዳክማል፡፡ ሥለቱን ያጠፋዋል፡፡ የተንኮልን ሥርጭትና እድገት ይገታዋል፡፡
٣٤ :‫ﭽ ﮊ ﮋ ﮌ ﮍ ﮎﮏ ﮐ ﮑ ﮒ ﮓ ﮔ ﮕ ﮖ ﮗ ﮘ ﮙ ﮚ ﮛ ﭼ فصلت‬
"መልካሚቱና ክፉይቱም (ጠባይ) አይተካከሉም፤ በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ጠባይ
(መጥፎይቱን) ገፍትር፤ ያን ጊዜ ያ ባንተና በርሱ መካከል ጠብ ያለው ሰው እርሱ ልክ እንደ አዛኝ ዘመድ
ይኾናል፡፡" (ፉሲለት፡ 34)
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሰው ልጆች ጥሩ ንግግር እንዲናገሩ ሲመክሩና ሲያበረታቱ እንዲህ ይላሉ፡- “እናንተ ሰዎችን በገንዘብ ልታስደስቱ
አይቻላችሁም፡፡ ፊታችሁን በፈገግታ አድምቃችሁ በመልካም ምግባር አስደስቷቸው፡፡” (በዛር ዘግበውታል)
ኢስላም ሰጥቶ ከማሳቀቅ፣ መልካም ንግግር እና ቅን ልቦናን ይመርጣል፡፡
‫ﭽ ﯔ ﯕ ﯖ ﯗ ﯘ ﯙ ﯚ ﯛﯜ ﯝ ﯞ ﯟ ﭼ البقرة‬
"መልካም ንግግርና ምሕረት ማድረግ፣ ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው፤ አላህም ተብቃቂ
ታጋሽ ነው፡፡"(አል-በቅራህ፡ 263)
ጥሩ ንግግር ከጥሩ ሥራዎች ይመደባል፡፡ በላጭነትን ያመላክታል፡፡ ለአላህ ውዴታ ያሳጫል፡፡ ዘላለማዊ ፀጋም ያጐናጽፋል፡፡ አነስ
(ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፡- አንድ ሰው ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- “ጀነት የሚያስገባኝን ስራ አሰተምሩኝ” አላቸው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ
አሉት “ምግብ አብላ፣ ሰላምታ አብዛ፣ ሰዎች በሚተኙበት ሰዓት (ለይል) ሶላት ስገድ፡፡ ጀነት በሰላም ትገባለህ፡፡” (አል-በዛር ዘግበውታል)
አላህ (ሱ.ወ) ከሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ጋር የምናደርገው ውይይት በሰላምና በተረጋጋ መንፈስ ማስረጃ የማቅረብ ውይይት
መሆን እንዳለበት ያስተምራል፡፡ ከጭቅጭቅና ከስድብም ሊርቅ ይገባል፡፡ ለውይይት የማይመች ግትር፣ ብስጩና ተሳዳቢ ከሆነ ይህን
ባህሪውን ማክሰም ይገባል፡፡
‫ﭽﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭼالعنكبوت‬
"የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፤ ከነሱ እነዚያን
የበደሉትን ሲቀር፤" (አል-ዐንከቡት: 46)
ታላላቅ ሰዎች በየትኛውም ሁኔታቸው እኩይ ነገር ከአንደበታቸው አይወጣም፡፡ ማን አለብኝ አይሉም፡፡ ሁሉንም ሰው ያከብራሉ፡፡
ማሊክ የሚከተለውን ዘግበዋል፦ “ከየሕያ ኢብን ሰዕድ እንዲህ የሚል ነገር ሰምቻለሁ፡- ዒሳ (ዐ.ሰ) ከርከሮ ባለበት መንገድ ላይ አለፉ፡፡
(ለከርከሮው) ‹‹በሰላም እለፍ›› አሉት፡፡ ‹‹ይህ ከርከሮ ነው፤ እንዴት እንዲህ ትላለህ?›› ተባሉ፡፡ እሳቸውም እኔ ምላሴን መጥፎ
ንግግር ማስለመድ ፈራሁ›› አሉ፡፡”
ጭፍጋጋ ፊትና መጥፎ ባህሪ የተጠናወተው ሰው በጥሩ ባህሪ አልታነፀም፡፡ መጮህ፣ መሳደብና መዝለፍ አይታክተውም፡፡ ጥሩ
ሰው ከእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ጋር ሙግት አያበዛም፡፡ በአልታረመ አንደበታቸው መርዛማ ቃላትን የሚረጩበትን አጋጣሚ
አይከፍትም፡፡
አንድ ያልሰለጠነ መጥፎ ሰው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቤት መጣ፡፡ መግባት ፈለገ፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቀስ አድርገው አግባብተው መለሱት፡፡
እንዲህ ከማድረግ ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም፡፡ ያልተገራ አንደበት በዝምታ ሥርዓት እንዲይዝ ማድረግ ይቻላል፡፡ ዓኢሻህ (ረ.ዐ)
እንዳስተላለፉት፡- “አንድ ሰው ወደ ቤት ለመግባት ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ጠይቆ፤ ተፈቅዶለት ገባ፡፡ ከዚያም እንዲህ አለ ‘መጥፎ ዘመድ
ማለት እሱ (እርሳቸውን) ነው፡፡’ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ግን ፈገግ ብለው ተቀበሉት፡፡ ደግ ንግግር ተናገሩት፡፡ ሰውየውም ሄደ፡፡ እኔም እንዲህ
አልኩ፡- ‘የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰውየው ያለውን እኮ ስሰማ በጎን አላሰብኩም ነበር፡፡ አንተ ግን ፈገግ አልክ፡፡ ደስተኛ ሆነህ
ተቀበልከው፡፡’ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- “ዓኢሻህ ሆይ! ከአንደበቴ መጥፎ ወጥቶ ያውቃልን? የቂያማ ዕለት በአላህ ዘንድ መጥፎ
ደረጃ ያለው ሰው ሰዎች ክፋቱን ፈርተው የሸሹት ሰው ነው’፡፡” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
ይህን ዓይነት ስብእና ለመጎናፀፍ በበጎ ምግባር ላይ መትጋት ያሻል፡፡ ምርጥ ሰው በመጥፎ ሰዎች ተጽዕኖ ደግነቱ አይበከልም፡፡
ሁሉም ሰው በንግግሩ የታረመ ላይሆን ይችላል፡፡ ስለዚህም ቁርኣን ከመጀመሪያዎቹ የአር-ረሕማን ባሪያዎች ባህሪ አንዱ፣ ያልተገራ
አንደበት ያላቸውን ሰዎቸ ንግግር ቸል ብሎ ማለፍ እንደሆነ ቁርኣን ያስተምራል፡፡
٦٣ :‫ﭽ ﮱ ﯓ ﯔ ﯕ ﯖ ﯗ ﯘ ﯙ ﯚ ﯛ ﯜ ﯝ ﭼ الفرقان‬
"የአር-ረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት፣ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው
ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው፡፡" (አል-ፉርቃን: 63)
٥٥ :‫ﭽ ﭿ ﮀ ﮁ ﮂ ﮃ ﮄ ﮅ ﮆ ﮇ ﮈ ﮉ ﮊ ﮋ ﮌ ﮍ ﭼ القصص‬
"ውድቅንም ቃል በሰሙ ጊዜ ከርሱ ይርቃሉ፡፡ ለኛ ሥራዎቻችን አሉን፤ ለናንተም ሥራዎቻችሁ አሏችሁ፤ ሰላም
በናንተ ላይ (ይኹን)፤ ባለጌዎችን አንፈልግም ይላሉ፤" (አል-ቀሰስ: 55)
አንድ ሰው ቁጣውን አንዴ ወይም ሁለቴ ዋጥ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከዚያም እሱ ይቆጣል፡፡ ከምርጥ ሙስሊም የሚጠበቀው
ቁጣውን እስከመጨረሻ ዋጥ አድርጎ ራሱን መቆጣጠር ነው፡፡
ሰዒድ ኢብኑ ሙሰየብ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡- “የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከሰሐቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለዋል፡፡ አንድ ሰው
አቡበክር (ረ.ዐ) ላይ ይጮህባቸዋል፤ ያስቸግራቸዋል፡፡ አቡበክር ዝም አሉ፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ አወካቸው፡፡ ዝም አሉት፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ
ሰላም ነሳቸው፡፡ በዚህ ጊዜ አቡበክር (ረ.ዐ) መልስ ሰጡት፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቆሙ፡፡ አቡበክር (ረ.ዐ) ‘የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!
አጠፋሁ እንዴ?’ አሉ፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ‘አላጠፋህም፡፡ ግን መላኢካ ከሰማይ ወርዶ እሱን መልስ ሊሰጠው ነበር፤ ልክ አንተ ስትናገር
መላኢካው ሄደ፡፡ ሸይጣን ተቀመጠ፡፡ እኔ ደግሞ ሸይጣን የተቀመጠበት አልቀመጥም’ አሉ፡፡” (አቡዳውድ ዘግበውታል)
ቂላቂሎችን ማለፍና መተው መሸነፍ ማለት አይደለም፡፡ በማለፍና በመሸነፍ መካከል ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ ማለፍ ማለት
የሚተናኮልንና የሚለክፍን ሰው ቸል ማለት ነው፡፡ ክፉ ከመናገር፣ ከቁጣ፣ ከበቀል፣ ራስን ማቀብ ነው፡፡ መሸነፍ ማለት ግን ለክፋት እጅ
መስጠትና መንበርከክ ነው፡፡ አስተዋይ ሰው የማይመለከተውን አያደምጥም፡፡ ለእኩይ ነገር አይንበረከክም፡፡ ሥነ-ምግባር የጎደላቸው
ሰዎች ምላሽ ለመስጠት በማሰብ ወደነርሱ ደረጃ ራሱን አያወርድም፡፡
ቁርኣን ትንኮሳን መቃወም ፍትህ ነው ብሎ ቢመክርም ይቅር ባይነት ግን የበለጠ መሆኑን ያስተምራል፡-
‫ﭽ ﭒ ﭓ ﭔ ﭕ ﭖ ﭗ ﭘ ﭙ ﭚ ﭛﭜ ﭝ ﭞ ﭟ ﭠ ﭡ ﭢ ﭣ ﭤ ﭥ ﭦ ﭧ ﭨ ﭩ ﭪ ﭫ ﭬ ﭭ ﭮ ﭯ ﭰ ﭼ النساء‬
"አላህ ከንግግር በክፉው መጮህን፣ ከተበደለ ሰው (ጩኸት) በቀር አይወድም፤ አላህ ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡
ደግ ነገርን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት ወይም ከመጥፎ ነገር (ከበደል) ይቅርታ ብታደርጉ፣ አላህ ይቅር
ባይ ኃያል ነው።" (አን-ኒሳእ፡ 148-149)
የማይረባ ንግግርን ከመቆጣጠሪያ መንገዶች አንዱ አላስፈላጊ ሙግትን መተው ነው፡፡ ኢስላምም ይህንኑ ባህሪ አጥብቆ
ያወግዛል፡፡ ለእውነትም ሆነ ለስህተት ቢሆን የጭቅጭቅን በር ዘግቷል፡፡
ክርክር ነፍስን ይወጥራል፡፡ አሸናፊ ለመሆን ያጓጓል፡፡ ሰውየው ቃላት ይሰነጥቃል፡፡ ለማሸነፍ የሚረዳውን ሁሉ ያደርጋል፤
ያጋንናል፤ ያካብዳል፡፡ እውነትን ከመፈለግ ይልቅ ማሸነፍ ትልቅ ቦታ ይኖረዋል፡፡ ችክ ምንችክ፣ ድርቅ ይላል፡፡ ለማብራራትም ሆነ
ለመረጋጋት ጊዜ አይኖረውም፡፡ ኢስላም ይህንን በከፍተኛ ሁኔታ ይጠላል፡፡ ለዲንም ሆነ ለኢኽላቅ (መልካም ባህሪ) አደገኛ መሆኑን
ይገልፃል፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ተከራክሮ ማሸነፍ እየቻለ ክርክርን የተወ፤ የጀነት የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ቤት
ይገነባለታል፡፡ ባለመብት ሆኖ (ክርክርን) የተወ፣ መሀል ላይ ቤት ይገነባለታል፡፡ በቀና ሥነ-ምግባር ያማረ ሰው (የጀነት) ቁንጮ ላይ
ቤት ይገነባለታል፡፡” (አቡዳውድ ዘግበውታል)
የወሬ ሱሰኞች ከአዋቂም ሆነ ከአላዋቂ ጋር መሟገት ይወዳሉ፡፡አይሰለቻቸውም፡፡ እነዚህ ሰዎች በንግግራቸው የሰዎችን ጉዳይ
ያበላሻሉ፡፡ ስለሃይማኖት ከተናገሩ ለዛ ቢስ ያደርጉታል፡፡ የእምነቱን ክብር ያዋርዳሉ፡፡
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “አላህ ዘንድ በጣም የተጠላ ሰው አጉል ሙግት የሚወድ ነው፡፡” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
በሌላ ዘገባ “ትክክለኛውን መንገድ ከያዙ በኋላ ሰዎች የሚጠሙት ስሜታዊ ክርክር ሲጀምሩ ብቻ ነው፡፡” (ጦበራኒ ዘግበውታል)
እንዲህ ዓይነት ሰው ምላሱን አይቆጣጠርም፡፡ ልክና ለከት የለውም፡፡ “ሁሉን ስሙኝ እኔ ብቻ ልናገር፣ ላውራ” ይላል፡፡ የቃላቱ
መከሸን እንጂ መልዕክት መተላለፉ አያሳስበውም፡፡ ጥሩ ነገር መናገሩን እና አለመናገሩን የሚያስበው መጨረሻ ላይ ነው፡፡ ምናልባትም
ላያሳስበው ይችላል፡፡
እንደዚህ ዓይነት የክርክር አባዜ ካለባቸው ሰዎች ውስጥ አንድ ገበሬ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ መጣ፡፡ “…የተመፃዳቂነት ምልክት
ይታይበታል፡፡” ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ምንም ነገር ሲናገሩ እርሳቸውን ከማድመጥ ይልቅ የራሱን ስሜት ማስተጋባትን ይመርጣል፡፡
አያርፍም፡፡ ይንቀዠቀዣል፡፡ ይህ ሰው ሲሄድ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- “በእርግጥ አላህ (ሱ.ወ) ይህንንና አምሳያዎቹን
አይወድም፡፡” (ጦበራኒ ዘግበውታል)
በዲን፣ በፖለቲካ፣ በሳይንስ፣ በጥበብ፣ የመከራከርና የመሟገት ሱስ ያለባቸው ሰዎች ዲኑንም ሆነ ፖለቲካውን ለዛ ያሳጡታል፡፡
ሳይንሱን ያረክሱታል፡፡ የጥበቡን ውበት ያጠፉታል፡፡ ምናአልባትም ብዙ ግንባታዎች የሚናዱት፣ በኢ-ፍትሃዊ አመለካከቶች ሰዎች
የሚቧደኑት፣ በጎጥ የሚከፋፈሉት ከዚህም ሌላ ሙስሊም ህብረተሰብ ላይ ጉዳት የሚያደርሱት፣ በዚህ ቅጠ-ቢስ ክርክርና ጭቅጭቅ
ነው፡፡
ክርክር፣ ሳይንሳዊ ጨዋነት ከተላበሰ በምርምርና በማስረጃ ከተደገፈ ማብራሪያ በጣም የተለየ ነው፡፡ ብዙ ሰሐቦች (ረ.ዐ)
እንዳስተላለፉት፡- “አንድ ቀን በአንድ ሃይማኖታዊ ጉዳይ እየተከራከርን ባለንበት ጊዜ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መጡ፡፡ በጣም
ተቆጡ፡፡ እንደዚያ ቀንም ተቆጥተው አያውቁም፡፡ ክርክሩንም ከለከሉን፡፡ እንዲህ አሉን፡- ‹‹ተረጋጉ፡፡ እናንተ የሙሐመድ ሕዝቦች!
ከእናንተ በፊት የነበሩት ሕዝቦች ለጥፋት የተዳረጉት በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ክርክርን ተዉ፡፡ ጥቅሙ ትንሽ ነው፡፡ የሙእሚን ሥነ-
ምግባር አይደለም፡፡ ተከራካሪ ሕይወቱ ይከስራል፡፡ ተከራካሪ ወንጀለኛ ነው፡፡ ለተከራካሪ ሰው የቂያማ ቀን አላማልደውም፡፡ እኔ ጀነት
ውስጥ የሦስት ቤቶች ባለቤት ነኝ፡፡ እውነተኛ ክርክርን ባለመብት ሆኖ ለተወ ሰው፣ የመጀመሪያውንና የመካከለኛውን የላይኛውን ጀነት
ቃል እገባለታለሁ፡፡ ክርክርን ተዉ፡፡ ጌታዬ ጣኦትን ከማምለክ በኋላ መጀመሪያ የከለከለኝ ክርክርን ነው፡፡” (ጦበራኒ ዘግበውታል)
ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች እየተሰባሰቡ ወግ ሊሰነጥቁ ይችላሉ፡፡ የሚዝናኑበት ገንዘብ ብቻ ስላላቸው ቁጭ ብለው የሰውን ነውር
ማመን¶ክ አይሰለቻቸውም፡፡ ዝባዝንኬ የሚቀባጥሩና በማያገባቸው ጉዳይ ገብተው ነገር የሚያማስሉ ሰዎችን ኢስላም ያወግዛል፡፡
٤ - ١ :‫ﭽ ﭢ ﭣ ﭤ ﭥ ﭦ ﭧ ﭨ ﭩ ﭪ ﭫ ﭬ ﭭ ﭮ ﭯ ﭰ ﭱﭲ ﭳ ﭴ ﭵ ﭶ ﭼ الهمزة‬
"ለአሚተኛ፣ ለዘላፊ ሁሉ ወዮለት፡፡ ለዚያ ገንዘብን የሰበሰበና የቆጣጠረው (ያደለበውም) ለኾነ፤
(ወዮለት)፡፡ ገንዘቡ የሚያዘወትረው መኾኑን ያስባል፡፡ ይከልከል፤ በሰባሪይቱ (እሳት)፣ ውስጥ በእርግጥ
ይጣላል፡፡" (አል-ሁመዛህ: 1-4)
በሐዲስ እንደተዘገበው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) “መንገድ ላይ ከመቀመጥ ተቆጠቡ›› ሲሉ፡፡ ሶሐቦቹም “እዛ መቀመጣችን አይቀርም፡፡
እንጨዋወታለን” አሉ፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- “መቀመጣችን አይቀርም ካላችሁ የመንገዱን ሃቅ ጠብቁ፡፡” ሶሓቦችም “የአላህ
መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሆይ! ምንድን ነው የመንገዱ ሐቅ?” ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- “ዕይታን ከመጥፎ ነገሮች መቆጠብ፤
አለማስቸገር፤ ሰላም ለሚላችሁ ሰላምታ መመለስ፣ ጥሩን ማመላከት፣ መጥፎን መከላከል ነው፡፡” (ሙስሊም ዘግበውታል)

ጊዜና አስተምህሮቱ
ያመለጠህን ነገር መልሰህ ልታገኘው ትችላለህ ጊዜ ሲቀር፡፡ ጊዜ ካመለጠ ይመለሳል ተብሎ አይታሰብም፡፡ የሰው ልጅ አንጡራ
ሀብት ጊዜ ነው፡፡ አስተዋይ ብልህ ሰው ጊዜውን የሚያየው እንደሚያሳሳ ብርቅ ሀብት ነው፡፡ ብዙውን ጊዜውን አይደለም፤ ትንሹንም ጊዜ
በዋዛ ፈዛዛ አያሳልፍም፡፡ ሁሉንም ነገር በጊዜውና በወቅቱ ይፈፅማል፡፡
እያንዳንዳችን መኖራችንን፣ ድርጊታችንን ስናስተውል ብሎም ሀሳባችን ወደኋላ መልሰን ያለፉትን ቀናት፣ ዓመታት በዚህ ምድር
ሕይወታችን መኖር የጀመርንበትን ወቅት ፍለጋ ብንባዝን፤ ብዙ መጓዝ የማይጨበጥ ምናብ ነው፡፡ ቀናትና ሌሊቶች ተጣምረው፣
ሣምንታትና ወራትን ወልደው፣ በውጤቱም ዓመታት ተፈጥረው፣ እኝህ ሁሉ ቀናት በእርዝመትም በስፋትም በይዘትም አንድ ቀን
ይመስላሉ፡፡
ይህ የሰው ልጅ አሁን የሚሰማው ስሜት ነው፡፡ እንዲሁም የቂያማ እለት ለሂሣብ በሚቆምበት ጊዜ ይኸው ዓይነት ስሜት
ይሰማዋል፡፡
٤٥ :‫ﭽ ﭩ ﭪ ﭫ ﭬ ﭭ ﭮ ﭯ ﭰ ﭱ ﭲ ﭳﭴ ﭼ يونس‬
"(ከሓዲዎችን) ከቀን አንዲትን ሰዓት እንጂ እንዳልቆዩ መስለው በመካከላቸው የሚተዋወቁ ሲኾኑ
በምንሰበስባቸው ቀን (አስታውስ)፡፡" (ዩኑስ፡ 45)
١٠٤ - ١٠٣ :‫ﭽ ﭼ ﭽ ﭾ ﭿ ﮀ ﮁ ﮂ ﮃ ﮄ ﮅ ﮆ ﮇ ﮈ ﮉ ﮊ ﮋ ﮌ ﮍ ﮎ ﮏ ﭼ طه‬
"ዐሥርን (ቀን) እንጂ አልቆያችሁም በመባባል በመካከላቸው ይንሾካሾካሉ፡፡ በሐሳብ ቀጥተኛቸው፣
አንድን ቀን እንጅ አልቆያችሁም በሚል ጊዜ የሚሉትን ነገር እኛ ዐዋቂዎች ነን፡፡" (ጧሃ፡ 103-104)
٤٦ :‫ﭽ ﰎ ﰏ ﰐ ﰑ ﰒ ﰓ ﰔ ﰕ ﰖ ﭼ النازعات‬
"እነርሱ በሚያዩዋት ቀን ያንዲት ቀን ምሽትን ወይም ረፋዷን እንጂ ያልቆዩ ይመስላሉ፡፡" (አን-ናዚዓቲ: 46)
በምድር ላይ ለዘመናት እንኖራለን ብለው ለሚቃዡ፣ የሕይወት ጉዟቸውን ከአፈር (ከአለም) ጋር ብቻ ላዛመዱ- ሰዎች-
(በመጪው አለም) ይህ ቁጭት ትክክል ነው፡፡ ምክንያቱም የምድራዊ የሕይወት ዋጋ በመጪው ዓለም ዕይታ ሲመዘን ያበሣጫል፣
ያፀፅታል፣ ያስቆጫል፡፡ ሕይወቱን በፌዝና በውድቅ ነገሮች ለሚገፋ፣ የሞት ድቅድቅ ጨለማ የገባ እለት በድንገት በአስደንጋጭ ሁኔታ
ይነቃል፡፡ ግን ዋጋ ቢስ ነው፡፡ ትርፉ ቁጭት ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ሰው በእርግጥ ሁኔታዎች መለወጥ በማይችሉበት ሰዓት ነው
የነቃው፡፡
ምድር ላይ የሰው ልጆች ሁኔታ በጣም ይደንቃል፡፡ ሞት አድፍጦ እየጠበቃቸው ያፌዛሉ፡፡ እያንዳንዷ ሥራቸው እየተመዘገበች
እነርሱ ይዘነጋሉ፡፡
٦ :‫ﭽ ﯭ ﯮ ﯯ ﯰ ﯱ ﯲ ﯳﯴ ﯵ ﯶ ﯷﯸ ﯹ ﯺ ﯻ ﯼ ﯽ ﭼ المجادلة‬
"አላህ ሁላቸውንም በሚቀሰቅሳቸው ቀን (ይቀጣቸዋል)፤ የሠሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል፤ የረሱት ሲኾኑ፥
አላህ ዐውቆታል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነው፡፡" (አል-ሙጃደላህ፡ 6)
እውነተኛ ሙስሊም በእርግጥ በጊዜው አይቀልድም፡፡ ለወቅቱ ከፍተኛ ክብር አለው፡፡ ምክንያቱም ለእርሱ ጊዜው ሕይወቱ ነው፡፡
ጊዜው እንዲመክን አይፈቅድም፡፡ ጊዜን በአልባሌ ነገር ማጥፋት ሕይወትን ገዳይ ተግባር እንደሆነ ይረዳል፡፡
በእርግጥ የሰው ልጅ በፍጥነት ወደ አላህ (ሱ.ወ) ይነጉዳል፡፡ ምህዋሩ በተዘዋወረ፣ ጨለማ በንጋት ያለማ k ረጥ በተጓዘ ቁጥር
የሰው ልጅም የሕይወት ጉዞውን በፍጥነት እየጨረሰ ነው፡፡ አእምሮ ያለው ሰው ይህን እውነታ መገንዘብና ማስተዋል አይጠበቅበትምን?
እንዲሁም አትኩሮት ችሮ፣ ያለፈውን መረዳትና ለሚመጣውም ሁኔታ መዘጋጀት ይጠበቅበታል፡፡ ትልቅ ውድቀት ማለት ዘመኑ እየበረረ፣
ሰውየው ግን ጊዜው ብቻውን እየበረረ እንደሆነ እና እድሜው ግን ምንም ያልተነካ ያህል ሲሰማው ነው፡፡ ትልቅ ክስረት ማለት አንድ
ሰው በባቡር እየተጓዘ ነገሮች እያለፉት የሚሄዱ፣ እሱ ግን የቆመ የሚመስል ምናባዊ እይታ ሲኖረው ነው፡፡ እውነታው ግን ዘመን በተጓዘ
ቁጥር ሰውን ራሱን ወደመጨረሻው የእድሜው ገደብ እየሾፈረው መንጐዱ ነው፡፡
ኢስላም የጊዜን ጥቅም በትክክል ይረዳል፡፡ የዘመንን አንጡራ ሃብትነት ከግምት ውስጥ ያስገባል፡፡ “ጊዜ ሰይፍ ነው፤ ካልቆረጥከው
ይቆርጥሃል” የሚለውን ውድ ጠቢባዊ አባባል ያረጋግጣል፡፡ አላህን የመፍራት ምልክት፣ የኢማን ጥልቀት መገለጫ ነው። ይህም የሆነው
አንድ ሙስሊም ጊዜን ጠንቅቆ ተረድቶ በሥርዓት መጓዝ ሲችል ነው፡፡
٦ :‫ﭽ ﯱ ﯲ ﯳ ﯴ ﯵ ﯶ ﯷ ﯸ ﯹ ﯺ ﯻ ﯼ ﯽ ﯾ ﭼ يونس‬
"ሌሊትና ቀን በመተካካታቸው አላህም በሰማያትና በምድር ውስጥ በፈጠረው ሁሉ ለሚጠነቀቁ ሕዝቦች
ምልክቶች አልሉ፡፡" (ዩኑስ፡ 6)
በምድራዊ ሕይወት ብልጭልጭነት ተተብትበው፣ በዚች ዓለም ፍቅር ሟሙተው ሰለነገው ሕይወት የተንሣፈፈ ምልከታ
ያላቸውን ሰዎች፣ ቁርኣን እንዲህ በማለት ይገልጻቸዋል፡-
‫ﭽﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭼ‬
"እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩ፣ ቅርቢቱንም ሕይወት የወደዱ፣ በሷም የረኩ፣ እነዚያም እነሱ
ከአንቀጾቻችን ዘንጊዎች የኾኑ፣ እነዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት መኖሪያቸው በእሳት ውስጥ ነው፡፡"
(ዩኑስ፡ 7-8)
ኢስላም ታላላቅ መለኮታዊ ተግባራትን በቀን ውስጥ በተለያዩ ሰዓታት እንዲሁም በዓመት ውስጥ በተወሰኑ ወራት እንዲፈፀሙ
አድር ¹ ል፡፡ አምስቱ የሰላት ጊዜያት በአንድ ቀን ውስጥ በተለያየ ሰአት ይፈፀማሉ፡፡ የሚሰገዱበት ሰዓትም የሚመች ነው፡፡ በሸሪዓ
እንደሚታወቀው ጂብሪል ከአላህ ተልኮ በቀን ውስጥ የሰላትን መጀመሪያና ማብቂያ ሰዓት ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምሯል፡፡
ይህ የጊዜ ሰሌዳ ኢስላማዊ ሕይወትን በትክክልና በተሳካ ሁኔታ ለመኖር ይመቻል፡፡ ሰላት በሕይወት ውስጥ ጊዜን ጐህ
ከሚቀድበት ጊዜ እስከ ጨለማው መዝለቂያ ድረስ ያሉትን ሰዓታት በደቂቃዎች ይከፋፍላል፡፡
١٨ - ١٧ :‫ﭽ ﭝ ﭞ ﭟ ﭠ ﭡ ﭢ ﭣ ﭤ ﭥ ﭦ ﭧ ﭨ ﭩ ﭪ ﭫ ﭬ ﭼ الروم‬
"አላህንም፣ በምታመሹ ጊዜ፣ በምታነጉም ጊዜ አጥሩት፤ (ስገዱለት)፡፡ ምስጋናም በሰማያትና በምድር
ውስጥ ለርሱ ብቻ (የተገባው) ነው፡፡ በሠርክም፤ በቀትር ውስጥ በምትገቡም ጊዜ፤ (አጥሩት)፡፡"(አር-ሩም፡
17-18)
ለሕይወት አጭር እይታ ያለው ሰው፣ የዘመንን ፋይዳ በትክክል አይመለከትም፡፡ የሚያየው መንጋትና መጨለሙን ብቻ ነው።
እንዲህ በማለትም ይገልፀዋል፡-
ሽማግሌ ሢሞት ይተካል ወጣቱ፣
ቀኑ ያለፈ እንደሁ ይመጣል ሌሊቱ፡፡
እንዲህም ተብሏል፡-
ጎህ ስለቀደደ ሌሊቱ ለቀቀን፣
እረሳን መንጎዱን እድሜያችንን ሰርቆን፡፡
ዘመን፣ ብልሆች ሊነቁበት የሚችሉበትን አጋጣሚ ይፈጥራል፡፡ ጥሩ ነገር እንዲሰሩ፣ የሚጠቅም ነገር እንዲያካብቱ፣ ለበጐ ነገር
እንዲተጉ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ በሌላ ጐኑ ጊዜ የአዛውንቶችን ቆዳ ይሰበስባል፡፡ እድሜን ይጠቀልላል፡፡ ሥልጣኔን ያወድማል፡፡
ሰዎች ይህን ሁሉ ነገር በአግራሞት ይመለከታሉ፡፡ የጊዜን ምስጢር ለመረዳት ይሳናቸዋል፡፡
=‫ﭽ ﮗ ﮘ ﮙ ﮚ ﮛ ﮜ ﮝ ﮞ ﮟ ﮠ ﮡ ﮢ ﮣ ﮤ ﮥ ﮦ ﮧ ﮨ ﮩ ﮪ ﮫ ﮬ ﮭ ﮮ ﮯ ﮰ ﭼ الفرقان‬
"ያ በሰማይ ቡሩጆችን ያደረገና በርሷም አንጸባራቂን (ፀሐይ) አብሪ ጨረቃንም ያደረገ ጌታ ክብሩ
በጣም ላቀ፡፡ እርሱም ያ (ያመለጠውን ሥራ) ማስታወስን ለሚፈልግ ወይም ማመስገንን ለሚፈልግ
ሰው ሌሊትንና ቀንን ተተካኪ ያደረገ ነው፡፡" (አል-ፉርቃን: 61-62(
ሌሊት ቀንን ይተካል፡፡ ቀን ደግሞ በእንቅስቃሴ የተሞላች፣ በሩጫና በወከባ የታጀበች ናት፡፡ ሆኖም የዓለማት ጌታ ይህን ሁሉ ነገር
ለጨዋታና ለፌዝ አልፈጠረም፡፡ በዚህ ዩኒቨርስ ውስጥ በቅጠ-ቢስነት መኖር ሕይወት ነው፤ ብለው ያሰቡ ሰዎች በእርግጥ ትልቅ ክስረት
ከስረዋል፡፡ ይህቺ ሕይወት ለረጅም ውድድር የተዘጋጀች ሜዳ ናት፡፡ ይህን ውድድር የሚያሸንፈው ጌታውን የሚያውቅ፣ የጌታውን ሃቅ
የሚያስተውልና ምስጋና የሚያደርስ ብቻ ነው፡፡
በቀጣዩ ዓለም ዘላለማዊ እረፍት ማግኘት የፈለገ ሰው በዚህ ዓለም ላይ ይተጋል፡፡ ከዓመታት ቆይታ የሕይወትን ልምድ
በማዳበር ለታላቅ ስኬት ይበቃል፡፡ የዚህ ዓይነት ሕይወት ትርጉም የማይገባቸው ሰዎች ለምድራዊ ጥቅም ብቻ የሚዋትቱ ግትልትሎች
ናቸው፡፡ ጥበብን አይረዱም፡፡ ከሕይወትም ትምህርት አይወስዱም፡፡
١٢٦ :‫ﭽ ﮄ ﮅ ﮆ ﮇ ﮈ ﮉ ﮊ ﮋ ﮌ ﮍ ﮎ ﮏ ﮐ ﮑ ﮒ ﮓ ﭼ التوبة‬
"በየዓመቱ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ እነርሱ የሚሞከሩ መኾናቸውን አያዩምን? ከዚያም አይጸጸቱምን?
እነሱም አይገሠጹምን?" (አት-ተውባህ: 126)

እድሜ ወረት ነው
እድሜህ ትልቅ ሃብትህ ነው፡፡ በመፃዒው አለም ዕድሜህን ምን ላይ እንዳዋልከውና እንዴት እንደመነዘርከው ትጠየቅበታለህ፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፦ “የቂያማ እለት የአንድ ባሪያ እግር ስለ አራት ነገሮች ሳትጠየቅ ንቅንቅ አትልም፤ እድሜውን
በምን እንዳጠፋው፣ ወጣትነቱን በምን እንዳሳለፈው፣ ገንዘቡን ከየት እንደሰበሰበውና በምን ላይ እንዳዋለው እንዲሁም እውቀቱን
ምን እንደሰራበት፡፡” (ቲርሚዚ ዘግበውታል)
ኢስላም የጊዜን ዋጋ በብዙ ትእዛዛቱና በከለከላቸው ነገሮች ውስጥ አካቷል፡፡ ኢስላም ከከንቱ ነገር መራቅን የኢማን ምልክት
አድርጎታል፡፡ ሥራፈትና ሥራ አስፈች የሆኑ ስብስቦችን ይዋጋል፡፡ ‹‹ጊዜአችንን እንግደል›› የሚል ጥሪ የሚያሥተላልፉ ሰዎችን
ይቃወማል፡፡ እነዚህ የጊዜን ጥቅም ያላወቁ ሰዎች፣ ጊዜን መግደል ማለት ሕይወትን ዋጋ ማሳጣት እንደሆነ አልተረዱም፡፡ ጊዜ መግደል፣
ግለሰብን ማውደም፣ ማኅበረሰብንም ማንኮታኮት ነው፡፡

ኃላፊነቶች ብዙ ናቸው
ብዙሃን የሚዘነጉት እውነታ “መሠራት ያለባቸው ነገሮች ሰዎች ካላቸው ጊዜያት በላይ ናቸው፡፡”
“ጊዜ ከሰው ሕይወት የተለየ አይደለም፡፡ ጊዜ በጣም ተወዳጅ ጓደኛ አልያም መጥፎ ጠላት ሊሆን ይችላል፡፡”
ከሀሰነል በስሪ ንግግሮች፡- “በየዕለቱ ጐህ በቀደደ ቁጥር ተጣሪ ይጣራል፡፡ አንተ የአደም ልጅ ሆይ! እኔ አዲስ ፍጡር ነኝ፡፡ በስራህ
ላይ መስካሪ ነኝ፡፡ ጥሩ ሥራ በመሥራት ስንቅ ሰንቅብኝ፡፡ እኔ እስከ ቂያማ እለት ድረስ አልመለስም፡፡”
ይህ ጥበባዊ ንግግር ከኢስላማዊ መንፈስ የመነጨ ነው፡፡የኢስላምን አስተምህሮዎች በአግባቡ የተገነዘበ ግለሰብ፣ ለቅርቡም ሆነ
ለመጪው ሕይወት ጠቃሚ እውቀቶችን ያገኛል፡፡ በእርግጥ አላህ ያደለውና የወደደው ሰው ምልክት አለው፡፡ እርሱም እያንዳንዷን
የእድሜውን ሰዓታት በቁም ነገር ላይ ማዋሉ፣ እንዲሁም ለተሻለና ለበለጠ ቁም ነገር መትጋቱ ነው፡፡
٧٣ :‫ﭽ ﭽ ﭾ ﭿ ﮀ ﮁ ﮂ ﮃ ﮄ ﮅ ﮆ ﮇ ﮈ ﮉ ﭼ القصص‬
"ከችሮታውም ለናንተ ሌሊትንና ቀንን በውስጡ ልታርፉበት፣ ከትሩፋቱም ልትፈልጉበት፣
አመስጋኞችም ልትኾኑ አደረገላችሁ፡፡" (አል-ቀሶስ፡ 73(
በጣም የሚያስተክዘው ነገር ብዙ ሰዎች ጊዜያቸውን በከንቱ ማጥፋታቸው አያሳዝናቸውም፡፡ ይባስ ብለው በዚህ መጥፎ
ዝንባሌያቸው ላይ ደግሞ የሌሎችንም ጊዜ ለማባከን ወደ ኋላ አይሉም፡፡ እነዚህ ሰዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ ለቁም ነገር የሚጠቀሙ
ሰዎችን በአልባሌ ጉዳይ እንዲጠመዱ ያደር ¹ ቸዋል፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ጤንነትና ነፃ ጊዜ ብዙ ሰዎች የሚዘነ ¹ ቸው ሁለት (የአላህ) ኒዕማዎች
(ፀጋዎች) ናቸው፡፡” )ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል(

ቀጣይነት ያለው ሥራ
ኢስላም ጊዜን አንጠፍጥፎ ለመጠቀም ከተጠቀመባቸው ስልቶች መካከል ሰዎች ሥራን ትንሽም እንኳ ቢሆን በቀጣይነትና
በዘውታሪነት እንዲሰሩ መገፋፋቱ ነው፡፡ ጊዜያዊና ወረተኛ ሥራን ብዙ እንኳ ቢሆን አይወድም፡፡ ምክንያቱም በትንሽ ሥራ ላይ
በቀጣይነትና በዘውታሪነት መቀጠል፣ ትንሽና ቀላል የሆነውን ሥራ ሰውዬውን ሳያስጨንቀው በጊዜ ብዛት የተራራ ያክል ሥር የሰደደ ጽኑ
ተግባር ያደርግለታል፡፡
በሌላ በኩል አንድ ሰው በአንድ ወቅት ሥራ የመሥራት ፍላጐት ቢያድርበትና ብዙ የተትረፈረፈ ተግባር ቢፈጽም፣ ነገር ግን ትንሽ
ቆይቶ ታክቶ ከተወው ይህ ኢስላም የሚጠላው የወረተኛ ባህሪ ይሆናል፡፡
በሐዲስ እንደተዘገበው፦ “እናንተ ሰዎች ሆይ! አቅማችሁ የሚፈቅደውን ሥራ ሥሩ፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እናንተ እስክትሰለቹ ድረስ
ምንዳ ከመስጠት ወደኋላ አይልም፡፡ አላህ ዘንድ የተወደደ ሥራ ማለት ትንሽ እንኳ ቢሆን ቀጣይነት ያለው ነው፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም
ዘግበውታል)
በሌላ ዘገባ ደግሞ “አልማችሁ አስተካክላችሁ ምቱ፡፡ (አልያም) ወደ ግቡ ለመቅረብ ሞክሩ፡፡ በጧት ተሰማሩ፡፡ በማታም ትጉ፡፡
ከሌሊት መጨረሻም (ተነስታችሁ የምትችሉትን ያህል ስገዱ)፡፡ ቀስ በቀስ አላማችሁን ከግብ ታደርሳላችሁ፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም
ዘግበውታል)
ዓኢሻህ (ረ.ዐ) በዘገቡት ሐዲስ “የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እኔ ቤት ገቡ፡፡ ከበኒ አሰድ (ጎሳ) የሆነች ሴት እኔ ቤት ነበረች፡፡
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፦ “ይህቺ ማን ናት?” እኔም እርሷ እገሌ ናት፡፡ ሌሊት አትተኛም (ዒባዳ ስታደርግ) አልኳቸው፡፡ ነቢዩ
(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- “ተዉ፡፡ በአቅማችሁ ልክ ስሩ፡፡” አላህ (ሱ.ወ) ዘንድ የተወደደ ዲን ሰውየው በቀጣይነት የሠራው ነው፡፡”
)ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል(
ማልደህ ተነሣ
ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ኢስላም ከመረጠው መንገድ አንዱ በጧት መነሳት ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ሙስሊም የቀኑን ሥራ
በማለዳ፣ በንቃት፣ በጥሩ መንፈስ፣ በጠንካራ ውሣኔ፣ በቆራጥነት፣ በንፁህ አየር መጀመር፣ የቀኑን መጀመሪያ በአግባቡ መጠቀም፣
ሌላውን የጊዜውን ክፍል በጉጉትና በጥንቃቄ ያለምንም ማባከን እንዲጠቀም ይረዳዋል፡፡
ኢስላማዊው የሕይወት ፕሮግራም ሥርዓት ቀንን በፈጅር ሶላት እንዲጀምር ያዛል፡፡ ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ሙሉ ንቃትን ግዴታ
ያደርጋል፡፡ ማምሸትን ኢስላም ይጠላል፡፡ ማምሸት የሱብሒ ሶላትን ከትክክለኛው የመስገጃ ሰዓት ያሳልፋል፡፡ በሐዲስ እንደተዘገበው
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ “አላህ ሆይ! ለእኔ ሕዝቦች ማለዳቸው (ጧታቸውን) በረካ አድርግላቸው፡፡”
(አቡዳውድ)
ዝንጉ ሰዎች ጧት ጧት እስከረፋድ ይተኛሉ፡፡ እነርሱ ተጋድመው ፀሐይ ትወጣለች፡፡ በአንፃሩ ትጉሃን የሕይወት ጉዳያቸውን
ለመፈፀም ይሯሯጣሉ፡፡ የአኼራ ጉዟቸውን ለማሳመር ይለፋሉ፡፡
ከነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ልጅ እንደተዘገበው ፋጢማ (ረ.ዐ) እንዲህ ብላለች፡- “እኔ ጧት ላይ ተኝቼ የአላህ መልዕክተኛ
(ሰ.ዐ.ወ) በአጠገቤ አለፉ፡፡ በእግራቸው ገፋ አደረጉኝና እንዲህ አሉኝ፦ ‘ልጄ ሆይ! ተነሽ፡፡ የአላህን ሲሳይ (ሪዝቅ) ፈልጊ፡፡ ከዝንጉዎች
አትሁኝ”፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ለሰዎች ሲሳያቸውን የሚያከፋፍለው ከፈጅር ጀምሮ እስከ ፀሐይ መውጫ ድረስ ነው፡፡’ )በይሀቂ(
ጠንካራና ብርቱ ሰዎች ከሰነፍና ደካማ ሰዎች የሚለዩበት ሰዓት ይህ ነው፡፡ ሁሉም ሰው እንደዝግጅቱ የዚህን ዓለምም ሆነ
የመጪውን ዓለም ስኬት ይ k ደሳል፡፡

ጊዜን አታማርር
የሰው ልጆች ግዴታዎች በጊዜ ውስጥ የሚፈፀሙ ናቸው፡፡ ጊዜ አላህ (ሱ.ወ) ለሰዎች የደነገገው ጥሩም ሆነ መጥፎ (ከሰዎቹ
አንፃር) የሚስተናገድበት ወቅት ነው፡፡
٤٤ :‫ﭽ ﭑ ﭒ ﭓ ﭔﭕ ﭖ ﭗ ﭘ ﭙ ﭚ ﭛ ﭼ النور‬
"አላህ ሌሊትንና ቀንን ያገላብጣል፤ በዚህም፣ ለባለ ውስጥ ዓይኖች፣ በእርግጥ ማስረጃ አለበት፡፡" )አን-
ኑር: 44(
እነዚህ የአላህ (ሱ.ወ) ምልክቶች እውነተኛ ምክርን ይሰጣሉ፡፡ምርጥ ትምህርቶችን ለሚያገናዝቡ ሰዎች ያመላክታሉ፡፡ ሰዎች
ክስተቶችን ይመለከታሉ፡፡ ከዱንያ ጥሩንና መጥፎ ይጐነጫሉ፡፡ ሆኖም የዚህን ክስተት ተቆጣጣሪ ይዘነጋሉ፡፡ የዱንያን ጥሩ ነገር
የሚያቀምሳቸውን አያውቁትም፡፡ በአንድ ጉዳይ ላይ ከተጨናነቁና ከተጠበቡ ቀኑን፣ ዘመኑንና ክስተቶቹን ይሰድባሉ፤ ይረግማሉ፡፡ ይህ
አላህን ያለማወቅ አንዱ ምልክት ነው፡፡ እንዲሁም አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን የርሱን ቀደር (ውሳኔ) መዘንጋት ያመጣው ክስተት ነው፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-“አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፦ “የአደም ልጅ ይሰድበኛል፡፡ ዘመንን ይሰድባል፡፡
እኔ የጊዜ ፈጣሪ ነኝ፡፡ ነገሮች በሙሉ በኔ ቁጥጥር ሥር ናቸው፡፡ ቀንና ሌሊትን እኔ እቀያይራለሁ’፡፡” )አቡዳውድ ዘግበውታል(
ማለትም ለሰው ልጅ ጥሩም ሆነ መጥፎ፣ ሰዎችን የሚያስደስትም ሆነ የሚያስከፋ ነገር ዘመኑ እራሱ አያመጣም፡፡ አይወስድምም፡፡
የፈለገውን ነገር የሚያደርገው የዘመንም የቦታም ጌታ የሆነው አላህ (ሱ.ወ) ነው፡፡
‫ﭽ ﯺ ﯻ ﯼ ﯽﯾ ﯿ ﰀ ﰁ ﰂﰃ ﰄ ﰅ ﭼ‬
"ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፤ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፤ ወደኛም
ትመለሳላችሁ፡፡" )አል-አንቢያእ: 35(
٢ :‫ﭽ ﭹ ﭺ ﭻ ﭼ ﭽ ﭾ ﭿ ﮀ ﭼ الرعد‬
"ነገሩን ሁሉ ያስተናብራል፤ በጌታችሁ መገናኘት ታረጋግጡ ዘንድ ታምራትን ይዘረዝራል፡፡ " )አር-ረዕድ: 2(

ከጊዜ ትምህርት ቅሰም


አስተዋይነት የጎደላቸው ሰዎች ጥሩና መጥፎ ሲያጋጥማቸው ከሕይወታቸው ተሞክሮ ምንም አይማሩም፡፡ በሐዲስ እንደተዘገበው
“… በእርግጥ ሙናፊቅ በሽታ ይዞት ከተሻለው ልክ እንደ ግመል ነው፡፡ ባለቤቱ አሰረው፡፡ ከዛ ፈታው፡፡ ለምን እንደታሰረም
አያውቅም፡፡ ለምን እንደተፈታም አይገባውም፡፡” (አቡዳውድ ዘግበውታል)
የሕይወት ልምድ፣ የአካባቢ ክስተቶችና ጊዜ ያላስተማረው ሰው በፍፁም አይሰለጥንም፡፡ ችግር ወይም በሽታ በሰዎች ላይ
የሚከሰተው፣ አላዋቂው እንዲያውቅ፣ ያልነቃው እንዲነቃ፣ ከአላህ ያፈነገጠ ሰው ወደ አላህ (ሱ.ወ) እንዲመለስ አይደለምን?
٤٣ - ٤٢ :‫ﭽ ﯝ ﯞ ﯟ ﯠ ﯡ ﯢ ﯣ ﯤ ﯥ ﯦ ﯧ ﯨ ﯩ ﯪ ﯫ ﯬ ﯭ ﯷ ﭼ األنعام‬
"ከበፊትህም ወደ ነበሩት ሕዝቦች (መልክተኞችን) በእርግጥ ላክን፤ እንዲተናነሱም በድህነትና በበሽታ
ያዝናቸው፡፡ ታዲያ ቅጣታችን በመጣባቸው ጊዜ አይዋደቁም ኖሯልን?" )አል-አንዓም: 42-43(
ሰዎች በባህሪያቸው ጌታቸውን በችግር ጊዜ ያውቁታል፤ይቀርቡታል፡፡ ብሶታቸውና ጭንቃቸው በበረታ ሰዓት ወደርሱ ይሸሻሉ፡፡
ልቦና ያለው፣ አዋቂና ብልህ ሰው ችግርና ጭንቀትና ሲገጥመው ወደ አላህ በተቃረበ ጊዜ፣ ይህንን ከአላህ ጋር ያለውን ቅርርብ፣ ችግሩ
ከተወገደ ወይም ጤናው ከተመለሰ በኋላ ይቀጥልበታል፡፡ በጣም ርካሽ ተግባር ማለት የአላህን እገዛ (ከአላህ የተብቃቃ መስሎት)
መካድ ነው፡፡
ለመልካም እሴቶችና ቁም ነገሮች ዋጋ የማይሰጡና በችግር ጊዜ ፅናትና ብርታት የሌላቸው ሰዎች አላህን የሚያውቁት በመከራ
ጊዜያት ብቻ ነው፡፡ በሰላምና በአማን ጊዜ ከአላህ ይሸሻሉ፡፡
‫ﭽ ﮞ ﮟ ﮠ ﮡ ﮢ ﮣ ﮤ ﮥ ﮦ ﮧ ﮨ ﮩ ﮪ ﮫ ﮬ ﮭ ﮮ ﮯ ﮰ ﮱ ﯓﯔ ﯕ ﯖ ﯗ ﯘ ﯙ ﯚ ﭼ‬
"ሰውንም ጉዳት ባገኘው ጊዜ በጐኑ ላይ ተጋድሞ ወይም ተቀምጦ ወይም ቆሞ ይለምነናል፤ ጉዳቱንም
ከሱ ላይ በገለጥንለት ጊዜ ወደ አገኘው ጉዳት እንዳልጠራን ኾኖ ያልፋል፤ እንደዚሁ ለድንበር አላፊዎች
ይሠሩት የነበሩት ሥራ ተሸለመላቸው፡፡" )ዩኑስ: 12(
ይህ ተግባር የከንቱ ሰዎች ባህሪ ነው፡፡ ቁም ነገረኛ ሰው የአላህን ፀጋ አይክድም፡፡

ታሪክን እናጥና
ከዘመን ለመማር በአጠቃላይ ታሪክን ማወቅ፣ በአላህ ተአምራት መደመም፣ በሰማይና በምድር ያሉ የአላህ ፍጥረታትን ማስተዋልና
የሕዝቦችን ሁኔታ ማገናዘብን ይጠይቃል፡፡ እንዴት አንድ ሕዝብ እንደተገነባና እንደፈረሰ? ከእድገት ወደ ውድቀት እንዴት እንደገባ?
አላህ (ሱ.ወ) የሰው ልጆች እነዚህን በተለያየ ዘመን የተከሰቱ ሁኔታዎች እንዲመለከቱና እንዲማሩበት ያዛል፡፡ እንዲሁም በውጤቱም
እንዲጠቀሙበት ይመክራል፡፡
٤٦ :‫ﭽ ﯤ ﯥ ﯦ ﯧ ﯨ ﯩ ﯪ ﯫ ﯬ ﯭ ﯮ ﯯ ﯰﯱ ﯲ ﯳ ﯴ ﯵ ﯶ ﯷ ﯸ ﯹ ﯺ ﯻ ﭼ الحج‬
"ለነርሱም በነርሱ የሚያውቁባቸው ልቦች ወይም በነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች ይኖሩዋቸው ዘንድ
በምድር ላይ አይኼዱምን? እነሆ ዓይኖች አይታወሩም፣ ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች
ይታወራሉ፡፡" )አል-ሐጅ: 46(
አንድ ሰው ከሁለት አንድ አማራጭ አለው፡፡ አስተሳሰቡን የሚያስተካክልበት፣ ኢማኑን የሚያጠነክርበት የራሱ ልምድ አለው
ወይም ብዙም እውቀት የለውም፡፡ ይህ ሰው ከሌሎች ይማር፡፡ ከሌሎች የእውቀት ልምድ ይገብይ፡፡ በሕይወት ማእበል የሚናጥ
ምድራዊ ሕይወት እየተመለከተ የማያስብ፣ ከባባድ ክስተቶችን እያየ የማይረዳ ሰው በእርግጥ የመሃይምነት ጨለማ ውጦታል፡፡ ይህ
ደግሞ ከሙእሚን የሚጠበቅ ስብእና አይደለም፡፡
እድሜ አጭር ነው፡፡ የሰው ልጅ የዚህ ዓለም የኑሮ ሁኔታ ጠባብ ነው፡፡ አእምሮም ምንነቱን ከሚያውቀው ነገር ኋላ ያለውን
ዓለም በቅጡ አይረዳም፡፡ ሰው የሚኖርበትን አካባቢ አልፎ ሰፋፊ ዓለማትን ለመመልከት ይሞክር፡፡ እሱ ያለበትን ዘመን ተሻግሮ
በረጅሙ ከእርሱ ኋላ ያለፉ ዘመናትን መለስ ብሎ መቃኘት አለበት፡፡

ጉብኝት የአመለካከት አድማስን ያሰፋል


የተለያዩ አካባቢዎችን መጎብኘት የአስተሳሰብ አድማስን ያሰፋል፡፡ስለታሪክም ያለንን ግንዛቤ ያጎለብታል፡፡ ጎብኚው
ለተለያዩ አስተሳሰቦችና ክስተቶች ስለሚጋለጥ ስለሚኖርበት ዓለም ያለው የሕይወት ልምድ ይካብታል፡፡ ስለዓለማት ጌታ ያለው
እውቀት ይጨምራል፡፡ ጉብኝት፣ የአንድ ግለሰብ ኢማን እንዲሰርጽ ያደርጋል፡፡ ተ ¹ ዥም በሄደባቸው ስፍራዎች ሁሉ
የሚያጋጥሙትን ነገሮች በአንክሮ እንዲመረምር ይመክራል፡፡
ኢስላም ሰዎች ረጃጅም ጉዞ እንዲያደርጉ ይመክራል፡፡ ሰፋፊ የጉብኝት እቅዶች እንዲኖራቸው ያበረታታል፡፡ እንዲሁም ምስራቅና
ምዕራብ ሳይሉ ጉብኝታቸውን ያካሂዱ ዘንድ በአፅንኦት ይመክራል፡፡ ጉብኝት ለፌዝና ለእንዝህላልነት ሣይሆን ለእውቀትና ለትምህርት
ሊሆን ይገባል፡፡ ለማሾፍና ጊዜን ለመግደል ሳይሆን ጥናትና ምርምርን ለማበረታታት መዋል አለበት፡፡ እውቀት ህያው ከሆኑ ህዝቦች
ተሞክሮ ብቻ ሳይሆን ካለፉ ህዝቦች የታሪክ ድልብም የሚዘገን ነው፡፡
‫ﭽ ﮖ ﮗ ﮘ ﮙ ﮚ ﮛ ﮜ ﮝ ﮞ ﮟ ﮠ ﮡ ﮢ ﮣ ﮤ ﮥ ﮦ ﮧ ﮨ ﮩ ﮪ ﭼ آل عمران‬
"ከናንተ በፊት ድርጊቶች በእርግጥ አልፈዋል፡፡ በምድርም ላይ ኺዱ የአስተባባዮችም ፍጻሜ እንዴት
እንደነበረ ተመልከቱ፡፡ ይህ ለሰዎች ገላጭ፤ ለጥንቁቆች መሪና ገሣጭ ነው፡፡" (አል ዒምራን: 137-138)
٢١ :‫ﭽ ﮌ ﮍ ﮎ ﮏ ﮐ ﮑ ﮒ ﮓ ﮔ ﮕ ﮖ ﮗﮘ ﮙ ﮚ ﮛ ﮜ ﮝ ﮞ ﮟ ﮠ ﮡ ﮢ ﮣ ﮤ ﮥ ﮦ ﮧ ﮨ ﮩ ﮪ ﭼ غافر‬
"የነዚያን ከነሱ በፊት የነበሩትን ሕዝቦች ፍጻሜ እንዴት እንደ ነበረ ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ
አይኼዱምን? በኀይልና በምድር ላይ በተውዋቸው ምልክቶች፤ ከነዚህ ይበልጥ የበረቱ ነበሩ፤ አላህም
በኀጢአቶቻቸው ያዛቸው፤ ለነሱም ከአላህ (ቅጣት) ምንም ጠባቂ አልነበራቸውም፡፡" (ጋፊር፡ 21)
ቁርኣን ያለፉ ሥልጣኔዎችን እንድናጠና የወደቁበትን ምክንያት እንድናውቅ ያደርገናል፡፡ ታሪክን ማወቅ ውድቀት የደረሰባቸው
ስልጣኔዎች በምን ምክንያት እንደተንኮታኮቱ ለተተኪው ትውልድ ትምህርት ይሰጣል፡፡ ለውድቀት የዳረ ¹ ቸውን
ምክንያቶች በማጥናት ከተመሳሳይ ውድቀት ራሳቸውን እንዲያድኑ ይረዳቸዋል፡፡
“በሌሊቶች ማጠን ተጎዝጉዞ ዘመን
ሁሉን ያስደንቃል መውለዱ ትንግርትን፡፡”

ጊዜ ምስጢር ነው
ጊዜ የአላህ ተአምር ነው፡፡ አእምሮ ምንነቱን ለመግለፅ ይሳነዋል፡፡ ጊዜን የምናውቀው በሚተወው ዱካና ቅርስ በመንተራስ ነው፡፡
የዘላለማዊነትና የመጥፋት ምስጢር በጊዜ ውስጥ ሳይኖር አይቀርም፡፡ የጊዜን ውጫዊና ምስጢራዊ ጉዳይ በምሉዕነት የሚያውቀው
አላህ ብቻ ነው፡፡
٨٠ - ٧٩ :‫ﭽ ﮀ ﮁ ﮂ ﮃ ﮄ ﮅ ﮆ ﮇ ﮈ ﮉ ﮊ ﮋ ﮌ ﮍ ﮎ ﮏﮐ ﮑ ﮒ ﮓ ﭼ المؤمنون‬
"እርሱም ያ በምድር ውስጥ የበተናችሁ ነው፤ ወደርሱም ትሰበሰባላችሁ፡፡ እርሱም ያ ሕያው የሚያደርግ
የሚገድልም ነው፤ የሌሊትና የቀን መተካካትም የርሱ ነው፤ አታውቁምን?፡፡" )አል-ሙእሚኑን: 79-80(
ይህች የምንኖራት ሕይወታችን ዓላማ ቢስ አለመሆንዋን ማወቅ ይገባል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ሕይወትን ያለ አላማ ከመፍጠር የጠራ ነው፡፡
የሚያልፍን ጊዜ በመልካም ሥራ ካስዋብነው ለራሳችን ዘልዓለማዊነትን እናረጋግጣለን፡፡ የእርጅናና የሞትን መሰናክል
እናልፋለን፡፡ ዘልዓለማዊ ሥራ ሰርተናል… ጀነት ውስጥ ቦታ ይዘናል፡፡

You might also like