You are on page 1of 42

ያልታሸጉ ምግቦች ፕሮግራም

የገበያ ድጋፍ አሰጣጥ ስልጠና


 ለጤና ኤክስቴሽን ባለሙያዎች

 ለቀበሌ የግብርና ባለሙያችዎች እና

 ለቀበሌ ስራስኪያጆች

January 2022

Bati
የውይይቱ ርዕሶች

o ያልታሸጉ ምግቦች ምንነት


o ያልታሸጉ ምግቦች ፕሮገራም ዓላማዎች
o ያልታሸጉ ምግቦች ፕሮገራም ተጠቃሚዎች

o ያልታሸጉ ምግቦች ፕሮግራሞች

o የተጠቃሚዎች መብትና ግዴታ

o ያቅራቢዎች መብትና ግዴታ


o የሰልጣኞች ተግባርና ሀላፊነት

o ቅፃቅፅ
ያልታሸጉ ምግቦች ምንነት/ትርጉም
o ፕሮሰስድ ያልሆኑ፤ ፋብሪካ ያልነካቸው የምግብ ዓነቶችን
ያጠቃልላል፡፡ ለዚህ ፕሮግራም ያልታሸጉ ምግቦች ከዕፅዋት ዘር
አትክልትና ፍራፍሬ፤ ከእንስሳት ዘር ስጋ፤ወተት ና እንቁላልን
ይይዛል፡፡
o ያልታሸጉ ምግቦች ጥሩ የቫይታሚንና የማዕድናት ምንጪ
ናቸው፡፡ ቫይታሚኖችና ማዕድናት ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል
አስፈላጊ ቢሆኑም በተለይ ለእናቶችና ለህፃናት እጅግ በጣም
አስፈላጊ ናቸው፡፡
ያልታሸጉ ምግቦች ፕሮገራም ዓላማዎች

o የእናቶችንና የህፃናትን አመጋገብ በማስተካከል መቀንጨርን


ለመከላከል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን መደገፍና ውጤታማ
እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ መቀንጨር መታከም የማይችል የምግብ
እጥረት ዓይነት ነው፡፡ መቀንጨር የቁመት ማጠርና የአእምሮ
አለመዳበርን ያስከትላል፡፡ መቀንጨር ምርታማነትን በ 10%
ይቀንሳል፡፡ በአማራ ክልል ከ 100 ህፃናት 46 ቱ የቀነጨሩ ናቸው፡፡
መቀንጨርን ለመከላከል ቢያንስ 1000 ቀናት ላይ አተኩሮ መስራት
ያስፈልጋል፡፡
ያልታሸጉ ምግቦች ፕሮገራም ዓላማዎች:-የቀጠለ…

o ያልታሸጉ ምግቦች ፕሮገራም መቀንጨርን ለመከላከል ከሚያደርጉት

አስተዋፅኦ በተጨማሪ የተስተካከለ የውልደት ክብደት እንዲኖር፤

መቀጨጭን እና under weight ለመከላከል አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

o የተወሰነ ገንዘብ/ብር/ በዕየወሩ ወደ ተመረጡ ገበያዎች

እንዲገባ በማድረግ አካባቢያዊ አምራቾችንና ዝቅተኛ

ነጋዴዎችን ማበረታታት ነው፡፡


ያልታሸጉ ምግቦች ፕሮገራም ዓላማዎች፡- የቀጠለ…

o እናቶች የተለያዩ የምግብ ዓይነቶችን እዲመገቡ


ማስቻል/ Improve dietary diversity of women/

o አንድ እናት በቀን ከ 10 ሩ የምግብ ዓነቶች ቢያስን


አምስቱን መመገብ አለባት/WHO Recommendation/
ያልታሸጉ ምግቦች ፕሮገራም ዓላማዎች፡- የቀጠለ…

o ከ10ሩ የምግብ ዓይነቶች በቀን ከአምሰት ዓይነቶች


ያነስ መመገብ ለምግብ እትረት ያጋልጣል
o የምግብ እጥረት በሽታ በእርግዝና ጊዜ ይጀምራል፡፡
ስለዚህ የምግብ እጥረት በሽታን ለመከላከል ቢያንስ
ከእርግዝና ጊዜ ጀምሮ ለእናቶች የመከላከል ስራ
መስራት አለበት፡፡
ለእናቶች አስፈላጊ የሆኑ 10ሩ የምግብ ዓይነቶች

o የእህል ዘር

o የስራስር ዘር
o አትክልት

o ፍራፍሬ

o ስጋ፤ ዶሮ
ለእናቶች አስፈላጊ የሆኑ 10ሩ የምግብ ዓይነቶች፡- የቀጠለ…

o እንቁላል

o ጥራጥሬ
o ወተትና የወተት ውጤቶች

o ቅባት

o አሳ
o ነፍሰጡር እና አጥቢ እናቶችን ከመግብ እጥረት በሽታ
ለመከላከል፡-
 አንድ ነፍሰጡር እናት ከሌሎች ነፍሰጡር እና ከማያጠቡ እናቶች
በተለየ መልኩ ቢያንስ አንድ ተጨማሪ ምግብ በቀን መመግብ
አለባት:: አንድ አጥቢ እናት አጥቢ ካልሆነች እናት ቢያንስ ሁለት
ተጨማሪ ምግብ መመገብ አለባት
 ወደ ጤና ተቐማት ቢያንስ አራት ጊዜ በመሄድ የጤና ክትትል
ማድረግ አለባት
 አስፈላጊ የሆኑ ክትባቶችንና supplements መውሰድ አለባት
ያልታሸጉ ምግቦች ፕሮገራም ዓላማዎች፡- የቀጠለ…

o ከ 6 ወር እስከ ሁለት አመት የሆኑ ህፃናት የተለያዩ


የምግብ አይነቶችን እዲመገቡ ማድረግ፡፡ አንድ ህፃን
ቢያንስ ከ 8 ቱ የምግብ ዓይነቶች አራቱን መመገብ
አለበት፡፡ ከአራት ያነሰ የሚመገብ ከሆነ ለምግብ እጥረት
በሽታ የመጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው፡፡
ያልታሸጉ ምግቦች ፕሮገራም ዓላማዎች፡- የቀጠለ…
o የህፃኑ እድሜ ሲጨምር በቀን የመመገብ ድግግሞሹ
መጨመር አለበት:-
 ከ6-8 ወር ያሉ ህፃናት ቢያንስ በቀን 2 ጊዜ
 ከ 9-23 ያሉ ህፃናት ቢያነስ በቀን 3 ጊዜ
 ጡት የማይጠቡ ህፃናት ቢያንስ 4 ጊዜ በቀን መመገብ
አለባቸው
 ለታመሙ ህፃናት የሚደረገው እንክብካቤ ካልታመሙ
ህፃናት ከሚደረገው እንክብካቤ በበለጠመሆን አለበት
ለህፃናት አስፈላጊ ሆኑ 8ቱ የምግብ ዓይነቶች
o የእናት ጡት ወተት
o የእህል ዘር ና ስራስር
o ጥራጥሬና ለውዝ
o ወተትና ወተት ውጤቶች
o ስጋ
o እንቁላል
o የቫይታሚን ‘A’ ምንጭ የሆኑ አትክልትና ፍራፍሬዎች
o ሌሎች የአትክልትና የፍራፍሬ ዓይነቶች
የፕሮገራሙ ተጠቃሚዎች
 የፕሮግራሙ ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች፡-
o ነፍጡር እናቶች
o አጥቢ እናቶች
o ከሁለት አመት በታች የሆኑ ህፃናት
 የፕሮግራሙ ቀጥተኛ ያልሆ ተጠቃሚዎች፡-
o ቸርቻሪ ነጋዴዎች
o የተጠቃሚ ቤተሰቦች
o አቅራቢዎች
o አርሶ አደሮች
ያልታሸጉ ምግቦች ፕሮግራሞች

o የማህበረሰብ ባህሪ ለውጥ ስርፀት

 Market drama
 Radio show/program (FM Amhara)
 Cooking demonstration
o Direct restricted cash support in the form of
electronics voucher/
የደንበኞች መብት

o የተፈቀደላቸውን ብር/ገንዘብ/ በወቅቱ ማግኘት


o የፈለ¹ቸውን ያልታሸጉ የምግብ አይነቶችን እና
የፈለጉትን መጠን ባመኑበት/በዕለቱ የገበያ/ዋጋ መግዛት
o የሚፈል¹ቸውን ያልታሸጉ የምግብ ዓይነቶችን በሙሉ
ማግኘት
o ለመግዛት የሚፈልጓቸውን ያልታሸጉ የምግብ ዓይነቶችን
በሙሉ ማግኘት
የደንበኞች መብት፡- የቀጠለ…

o የሚገዟቸውን ያልታሸጉ የምግብ ዓይነቶች ጥራታቸውን የጠበቁ


መሆናቸውን ማረጋገጥ/በእጅ መርጦ መግዛት/

o በየወሩ የሚያገኙት የብር መጠን ከቀነሰ ምክንያቱን ማወቅ

o ከፕሮግራሙ የሚሰናበቱ ከሆነ ከመሰናበታቸው ከሁለት ወር

በፊት መረጃ ማግኘት


o ከሞባይላቸው ብሩ ወደ ነጋዴው ከመተላለፉ በፊት
የሚተላለፈውን መጠን ማወቅና መስማማት/ማንበብ ለማይችሉ/
የደንበኞች መብት፡- የቀጠለ…

o የቀራቸውን የብር መጠን ማወቅ

o ከፈለጉት አቅራቢ እና ከፈለጉት የገበያ ቦታመግዛት

o ጥያቄ ሲኖራቸው ለማን ማቅረብ እንዳለባቸው ማወቅ

o በክብር መስተናገድ

o ለሚያቀርቡት የአገልግሎት ጥያቄ ፈጣን ምላሽ

ማግኘት
የደንበኞች ግዴታ

o ነጋዴዎችን ማክበር

o ወረፋ በሚኖርበት ወቅት ለነፍሰጡሮችና፤ ጨቅላ ህፃን


ላዙ፤ ለአረጋዊያንና ለአካል ጉዳተኞች ቅድሚያ መስጠት
o በተላከላቸውን ብር/ገንዘብ/ ያልታሸጉ ምግቦችን ብቻ
መግዛት
o የተላከላቸውን ብር በአንድ ገበያ ብቻ አለመጨረስ

o የተላከላቸውን ብር በአንድ ወር ውስጥ ተጠቅሞ መጨረስ


የደንበኞች ግዴታ፡- የቀጠለ…
o እቤታቸው ከሌለ በስተቀር ከሁሉም ያልታሸጉ የምግብ
ዓይነቶች መግዛት
o ለገዙት የምግብ ዓይነት ክፍያ መፈፀም

o የገዙትን ምግብ በአግባቡ መጠቀም/ለጎረቢት አለማካፈል/

o ሞባይል ከመቀየራቸው በፊት አንድ ወር/ዙር/ ቀደም ብለው


አዲሱን ስልክ ቁጥር ለሚመለከተው አካል ማስመዝገብ
የነጋዴዎች መብት
o ለሸጡት የምግብ ዓይነት ክፍያ መቀበል

o ገንዘብ ማውጣት ሲፈልጉ ያለቅድመ ሁኔታ መስተናገድ

o የክፍያ ወኪሎችን ስም አድራሻና ስልክ ቁጥር ማወቅ

o ከደንበኞች ክብር ማግኘት


የነጋዴዎች መብት፡-የቀጠለ…

o የአቅም ግንባታ ስልጠና ማግኘት

o ገንዘብ መላኩን መረጃ ማግኘት

o የኮንትራት ውሉን ኮፒ ማግኘት

o ፖስተር ያለምንም ክፍያ ማግኘት


የነጋዴዎች ግዴታ

o በእለቱ የገበያ ዋጋ ጥራቱን የጠበቀ የምግብ ዓይነት

መሸጥ
o ውል የገቡበትን የምግብ ዓይነት ብቻ ለፕሮግራሙ

ተጠቃሚዎች ማቅርብና መሸጥ


o ጥራቱን የጠመቀ ምግብ ማቅርብ
የነጋዴዎች ግዴታ፡-የቀጠለ…

o በጥራትም፣ በመጠንም እና በአይነትም የተሻለ ምግብ

ማቅረብ
o የሚያቀረቡትን ምግብ ፀሀይና ከሌሎች ጎጂ ነገሮች

መከላከል
o ፖስተር በአግባቡና በሚታይ ቦታ መለጠፍ
የነጋዴዎች ግዴታ:- የቀጠለ…
o ለደንበኞች ክብር መስጠት

o ገበያውን ለመደገፍ ለሄዱ ሰዎች አስፈላጊውን መረጃ

መስጠት
o ለውይይት ሲፈለጉ መገኘት

o የሚሰጡትን አገልግሎት በተመለከተ አስተያየት ከተገልጋዮች

መሰብሰብ እና በአስተያየቱ መሰረት አገልግሎቱን ማስተካከል


o በገበያ ቀን መገኘት
የሰልጣኞች ተግባርና ኃላፊነት

o ለደንበኞች ገንዘብ መላኩን መረጃ ማስተላለፍ/መላኩን


ከሚመለከተው የወረዳ ሰው በማረጋገጥ/የደንበኞችን ሞባይል
በማየት/
o ደንበኞች በየሳምንቱ ገበያ በመሄድ የተላከላቸው ገንዘባቸው
እስከሚያልቅ ድረስ ግዥ እንዲፈጽሙ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
o ደንበኞች ከሁሉም ያልታሸጉ የምግብ ዓይነቶች ግዥ
እንዲፈጽሙ አስፈላጊውን ምክርና ክትትል ማድረግ
የሰልጣኞች ተግባርና ኃላፊነት፡- የቀጠለ..
o በገበያ ቀን ተገኝቶ ደንበኞችንና ነጋዴዎችን ማገዝ፡-

 የደንበኞችን ቀሪ ሂሳብ ማረጋገጥና መንገር/*803# በመጠቀም

*803*2*1* የደንበኞች የሚስጥር ቁጥር ማስገባት# መደወል

 ደንበኞች ግዥ ከፈፀሙ በኋላ ትክክለኛውን የብር መጠን ለነጋዴው


ማስተላለፍ

*803*1* የነጋዴ የሚስጥር ቁጥር* ማስተላለፍ የፈለጉት የብር


መጠን ማስገባት* የደንበኛው የሚስጥር ቁጥር# መደወል፡፡
የሰልጣኞች ተግባርና ኃላፊነት፡- የቀጠለ…

ወረፋ በሚበዛበት ወቅት ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ቅድሚያ


እንዲስተናገዱ ማድረግ

 የደንበኖችን ቅሬታና የአገልግሎት ጥያቄ ተቀብሎ


ማስተናገድ

 ቅሬታዎች በእነሱ አቅም መፈታት የሚችሉ ከሆነ


ወዲደውኑ መፍታት፡፡ ካልተቻለ ለሚመለከተው የወረዳ
ሰው/WFP/ ሪፖርት ማድረግ፡፡
የሰልጣኞች ተግባርና ኃላፊነት፡- የቀጠለ…

o ነጋዴዎች ያቀረቧቸው ያልታሸጉ ምግቦች ጥራት፤


ብዛትና ዓይነት መከታተል፡፡ ለምሳሌ አትክልት አቅራቢ፡-
 ሽንኩርት
 ድንች

 ጥቅል ጎመን
 ያበሻ ጎመን
የሰልጣኞች ተግባርና ኃላፊነት፡- የቀጠለ…
 ቀይ ስር

 ካሮት
 ሰላጣ
 ቆስጣ
 ስኳር ድንች ወ.ዘ.ተ መያዛቸውን መከታተል፡፡ ከዘጠኙ
ቢያንስ አራትና ከዚያ በላይ መያዝ አለባቸው፡፡
የሰልጣኞች ተግባርና ኃላፊነት፡- የቀጠለ…
o ፍራፍሬ አቅራቢዎቸ ወቅቱን መሰረት በማድረግ፡-

 ሙዝ

 ብርቱካን/ አቅርቦቱ በሚኖርበት ስዓት/

 ማንጎ/አቅርቦቱ በሚኖርበት ስዓት

 ፓፓያ
የሰልጣኞች ተግባርና ኃላፊነት፡- የቀጠለ…

 አቮካዶ/አቅርቦቱ በሚኖርበት ስዓት/


 አፕል/አቅርቦቱ በሚኖርበት ስዓት
 ትርንጎ

 ዘይቱን

 መንደሪን
 ከአስሩ ቢያንስ ሁለትና ከዚያ በላይ መያዝ አለባቸው፡፡
የሰልጣኞች ተግባርና ኃላፊነት፡- የቀጠለ…

o የገበያ ዋጋ መከታተል፡- ነጋዴዎች ለደንበኖች በዕለቱ


የገበያ ዋጋ እየሸጡ መሆኑን መከታተል፡፡ ልዩነት ካለ
ተነጋግሮ ለማስተካከል መሞከር፡፡ የማያስተካክሉ ከሆነ
ለሚመለከታቸው የወረዳ ሰዎች/WFP/ ሪፖርት ማድረግ፡፡
o የዋና ዋና ያልታሸጉ ምግቦች ዋጋ በእየሳምንቱ መሰብሰብ

o ደንበኞች የገዟቸውን ያልታሸጉ ምግቦች በአግባቡ


እንዲጠቀሙ አስፈላጊውን ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ
የሰልጣኞች ተግባርና ኃላፊነት፡- የቀጠለ…
o የአካባቢው ማህበረሰብ የሚተላለፈውን የሬድዮ ፕሮገራም
እንዲከታተሉ መደገፍ
o መረጃ ለመቀየር የሚፈልጉ ደንበኞች ካሉ መረጃ ለመቀር መሞላት
ያለበትን ቅፅ ሞልቶ ለሚመለከተው የወረዳ ፎካል ፐርሰን/ተጠረ/
መላክ
o ከፕሮገራሙ የሚሠናበቱ ደንበኞች ካሉ ቀደም ብሎ መረጃ ማስተላለፍ
o ሪፖርት ለወረዳው ተወካይ በእየወሩ መላክ
o ሌሎች ተጨማሪ ስራዎችን ማከናወን፡፡
መረጃ ለመቀየር መሞላት ያለበት ቅፅ

o የደንበኛው መለያ ቁጥር___________


o ቀበሌ__________________
o መንደር______________
o ስልክ ቁጥር_____________
Type of data to Change from Change to
change (thick)
First Name
Last Name
Date of Birth/Age
HH size/ No. of benef
Kebele
Individual document
No.
Location
Phone number
Type of data to Change from Change to
change (thick

Principal

Alternate

Marital Status
o Reasons for
change__________________________________
________________________________________
________________________________________
____________________________________
o Requested by__________
Signature______________; Date_________
o Verified by_____________; Date_______
የመረጃ ለውጡን የሚያስሞላው ማን ነው?

o የጤና ኤክስቴሽን ባለሙያዎች


o የቀበሌ ስራስኪያጆች
o ሁለቱም በማይኖሩበት ወቅት የቀበሌ
አስተዳዳሪው
o ስልክ ለመቀየር ደንበኞች ስፈልጉ የት መምጣት
እንዳለባቸው ቀድመው መወቅ አለባቸው
ደንበኞች መረጃ ለመቀየር ሲመጡ ይዘው መምጣት ያለባቸው
ማስረጃዎች
o ደንበኛዋ/ደንበኛው ራሷ/ራሱ ከመጣች/ከመጣ፡-

 የቀበሌ መታወቂያ
 የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ለመሆናቸው የሚያስረዳ መታወቂያ
 ስልክ ቁጥር
o መረጃው እንዲቀየር የፈለጉት ተወካይ ከሆኑ ከላይ የተዘረዘሩት
እንዳሉ ሁነው፡-
 የቀበሌ ህጋዊ ውክልና
 መታወቂያ
Vegetables & Fruits
አመስግናለሁ!!!

You might also like