You are on page 1of 16

የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡ ጁኒየር የኮንቴነር ኦፕሬሽን ኦፊሰር

ቅርንጫፍ ጽ/
ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ

ዋና ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን ዋና ክፍል

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለኦፕሬሽን ዋና ክፍል

ዝርዝር ተግባራት

1. ከበር ቁጥጥር ሠራተኛ በሹፌር አማካኝነት የቀረቡለትን ሰነዶች በመቀበል የመኪና ሰሌዳ፣ የኮንቴነር ቁጥር፣
የሹፌር ስምና የመንገድ ወረቀት (way bill) በማመሳከር ኮንቴነሩ ቀድሞ በተዘጋጀለት ሥፍራ (Location)
እንዲራገፍ ለማሽን ኦፕሬተር የሥራ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ስለመራገፉ “way
“way bill” ላይ ማህተምና ፊርማውን
በማኖር ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡ በመጨረሻም በአገልግሎት መከታተያ ቅፅ ላይ ሥራው የተጠናቀቀበትን ሠዓት
በመሙላት ሹፌሩን ያሰናብታል፡፡

2. በተርሚናል የተቀመጠ ኮንቴነር የተራገፈበትን ትክክለኛ ቦታ የሚጠቁም መረጃ በ”EIR” ላይ ሞልቶ


ወዲያውኑ የተርሚናል ሎኬሽን መረጃ ቅርንጫፍ ጽ/
ጽ/ቤቱ አሁን ባለበት የመረጃ አያያዝ መዝግቦ ይይዛል፡፡

3. በየጊዜው የተርሚናል አጠቃቀም መረጃ ይይዛል፡፡ክፍት ቦታዎች እና ኮንቴይነር ያረፈባቸውን በቦታዎች


በመለየት መረጃ ይያዛል፡፡የተርሚናል አጠቃቀም በ Occupancy Rate መሰረት ያከናውናል፡፡

4. ባዶ ኮንቴነሮችን ከበር ቁጥጥር ሠራተኛ በሹፌር አማካኝነት የቀረቡትን ሠነዶች በማረጋገጥ ቀድሞ
በተዘጋጀላቸው ቦታ ተረክቦ ያስቀምጣል፣ የባዶ ኮንቴነር መረጃ ለሚመለከተው የሥራ ክፍል ያሰራጫል፡፡

5. አደገኛ የሆኑ (Hazardous) ኮንቴነሮች ምንነት ቀደም ብሎ በመለየት ለብቻ በተዘጋጀላቸው ቦታ እንዲራገፉ
ያደርጋል፡፡

6. የኮንቴነር ቦታ ለውጥ (Shifting)


Shifting) በሚኖርበት ወቅት ይህንኑ የኮንቴነር እንቅስቃሴ መረጃ በተቀመጠው
ሥታንዳርድ መሰረት መረጃ መያዝ፡፡ ከስምንት ቀን በላይ ወይንም አዲሱ ታሪፍ በሚያፀድቀው የነፃ የመጋዘን
አገልግሎት ታሪፍ በላይ በቆዩ ኮንቴይነሮች ላይ ሽፍቲንግ የሚሰራ ከሆነ ስራውን ለሁሳብ ክፍል ማሳወቅ፡፡

7. ኮንቴነር እንዲጫን በተላለፈለት የሥራ ትዕዛዝ መሰረት ተገቢውን የማሽንና የሰው ኃይል ዝግጅት በማድረግ
ጭነቱን የሚጭነው ተሽከርካሪ እንደደረሰ የሰሌዳ ቁጥር፣ የሚጫነው ኮንቴነር ቁጥርና መጠን በማመሳከር
አስጭኖ ተሽከርካሪው ወደበር እንዲሄድ ያደርጋል(
ያደርጋል(ይልካል)
ይልካል)፡፡

8. ለጉምሩክ ፍተሻና ለአስንስታፊንግ ጥያቄ የሚቀርብባቸው ኮንቴነሮች በተላለፈበት የሥራ ትዕዛዝ መሰረት
ወደ ተፈለገው ቦታ እንዲዛወሩ ያደርጋል፡፡(
ያደርጋል፡፡(የወደፊት የስራ አካል ነው)
ነው)

9. ባለማቀዝቀዣ ኮንቴነር ጭነቶች መረጃ ቀድሞ በመያዝ ቀድሞ በተለየለት ቦታ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡
(የወደፍት የስራ አካ ነው)
ነው)

10. ስለሥራ አፈፃፀሙ ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡


11. ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡ ጁኒየር የበር ቁጥጥር ኦፊሰር

ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ

ዋና ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን ዋና ክፍል

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለኦፕሬሽን ዋና ክፍል

ዝርዝር ተግባር

1. የወደብ በር ቁጥጥር ሠራተኛ የመድረሻ ወደብ ጉምሩክ ትራንዚት ኦፊሰር በመንገድ ወረቀቱ (Way bill)
bill) ላይ
የትራንዚት ማብቂያ መግለጫ ፊርማና ማህተም ማኖሩን አረጋግጦና ተቀብሎ በተጨማሪም ሌሎች ተዛማች
ሠነዶችን ከሹፌሩ በመቀበል ቀድሞ ከደረሰው የገቢ ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ ጋር በማገናዘብና በማመሣከር፣
የኮንቴይነር ውጫዊ አካል በመፈተሽ የመግቢያ ፍቃድ (Gate pass)
pass) እና የኮንቴይነር መረካከቢያ ቅፅ (EIR)
EIR)
በማዘጋጀትና ወደ ወደብ ተርሚናል እንዲገባ ያደርጋል፡፡

2. የበር ቁጥጥር ሰራተኛው ያዘጋጀውን ‘Gate pass’ እና ‘EIR’ ፓድ ላይ ከቀረው በሥተቀር ያሉትን ከአባሪ ሰነዶች
ጋር በማያያዝ ለኦፕሬሽን ዶክመንቴሽን ኦፊሰር እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

3. ገቢ ጭነቶችን ጭኖ የገባው አሽከርካሪ ጭነቱን አራግፎ ሲመለስ የመግቢያ ፍቃዱንና የአገልግሎት መከታተያ ቅፁን
በመቀበል ሠዓቱን በመሙላት በተቀመጠለት ጊዜ ለማስተናገዱ በማረጋገጥ እንዲወጣ ያደርጋል፡፡

4. ጭነት ለመጫን ወደ ወደብ የሚገቡትን ተሽከርካሪዎች የበር ቁጥጥር ሠራኛው ከተርሚናል ኦፕሬሽን ክፍል
በተላከለት ትዕዛዝ መሠረት ተሽከርካሪዎቹ ባዶና ለጭነት የተዘጋጁ መሆናቸውን በማረጋገጥ እንደቅድመ
ተከተላቸው ‘Gate pass’ በማዘጋጀትና የሚጭኑበትን ቦታ በሠነድ ላይ በመጥቀስ ወደ ወደብ ተርሚናል እንዲገቡ
ያደርጋል፡፡

5. ጭነት ከወደቡ ጭነው ለመውጣት የሚመጡ ተሽከርካሪዎች የበር ቁጥጥር ሠራተኛው የወደብ አገልግሎት ክፍያ
የተፈፀመባቸው ለመሆኑ የክፍያ ደረሰኝ ወይም ማረጋገጫ ሲደርሠው በማገናዘብ፣ በማመሣከርና የኮንቴይነሩን
ውጫዊ አካል በመፈተሽ ‘FULL EIR OUT’ በማዘጋጀት ከሹፌሩ ጋር በመተማመንና በመፈራረም፣ የጉምሩክ
ኢንስፔክተር መኖሩን በማረጋገጥ በጋራ ጭነቱ እንዲወጣ በማድረግ ያዘጋጀውን ‘FULL EIR OUT’
ለሚመለከተው ሰራተኛ ያስተላልፋል፡፡

6. ገቢ ባዶ ኮንቴይነር ወደ ወደብ ሲመጣ የበር ቁጥጥር ሰራተኛው አሽከርካሪው በመጣበት ቅድመ ተከተል መሰረት
ቀድሞ በወደቡ የተስተናገደ ከሆነ ሙሉ ኮንቴይነሩን ጭኖ ሲወጣ የተሰጠው ‘FULL EIR OUT’ ያለው መሆኑን
ያረጋግጣል፣ ቀድሞ በወደቡ ያልተስተናገደ ከሆነ ከመርከብ ወኪል ጥያቄ የቀረበና በወደቡ እንዲስተናገድ የተፈቀደ
መሆኑን በማረጋገጥ የባዶ ኮንቴይነሩን ውስጣዊና ውጫዊ አካል በመፈተሽ ‘GATE PASS’ እና ‘EMPTY IN
EIR’ በማዘጋጀትና ከአሽከርካሪው ጋር በመተማመንና በመፈራረም ኮንቴይነሩን የሚያራግፍበትን ቦታ በሰነድ ላይ
በመጥቀስ ወደ ወደብ ተርሚናል እንዲገባ ያደርጋል፡፡

7. በፓዱ ላይ ቀሪ ከሚሆነው በስተቀር ያሉ ‘GATE PASS’ እና ‘EIR’ ¢ú c’Ê‹ KT>SKŸ}¨< W^}— ¾}LŸuƒ”
W¯ƒ uSS<Lƒ Áe}LMóM::

8. ከወደቡ ለሚወጡ ወጪ ባዶ ኮንቴይነሮች ተገቢውን ሰነድ ማሟላታቸውን በማረጋገጥ እና የኮንቴይነሩን ውስጣዊና


ውጫዊ አካል በመፈተሽ ‘EMPTY OUT EIR’
EIR’ በማዘጋጀት እንዲወጡ ያደርጋል፡፡

9. የክፍያ ሰነድ ሥህተት ሲኖር ወደ ፋይናንስ ክፍል በመመለስ እንዲስተካከል ያደርጋል፡፡

10. ጭነቶች በተሣሣተ መንገድ ከወደቡ እንዳይወጡ ጥብቅ ቁጥጥርና ፍተሻ ያደርጋል፡፡

11. በተለያየ ምክንያት ጭነት ከጫኑ በኋላ ወደቡ ግቢ ውስጥ የሚያድሩ ጭነቶች ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍሉ ያደርጋል፣
ሣይከፍሉ እንዳይወጡ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
12. ጭነት ለመጫን ወደ ወደቡ ገብተው ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ሳይጭኑ የሚወጡትን ትራንስፖርተሮች
አስፈላጊውን የወደብ ክፍያ እንዲከፍሉ ያደርጋል፡፡

13. የገቢና ወጪ ጭነቶች መረጃ መዝግቦ ይይዛል፡፡

14. ዕለታዊ፣ ሣምንታዊ፣ ወርሃዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመትና ዓመታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡

15. ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎችት ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡ ታሊ ክለርክ

ቅርንጫፍ ፡ ኮምቦልቻ

ዋና ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን ዋና ክፍል

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለኦፕሬሽን ዋና ክፍል

ዝርዘር የሥራ ተግባራት

1. ከኮንቴነር ለፍተሻ ወደ መጋዘን ሲገባ የጉምሩክ እንስፔክተር ሲሉን ሲቆርጥ ቆጥሮ መዝግቦ ይይዛል
የተቆጠረው እቃ ከቢል ኦፍ ሎዲንግ (Bill of lading) ጋር አመሳክሮ እኩል መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

2. በቆጠራ የተገኘ ዕቃ ከ ‘bill of lading’


lading’ ጋር ካለው ቁጥር ልዩነት ካለው CFS Aea ከሆነ ለእስታፊንግ/
ለእስታፊንግ/
አንስታፊንግ ኦፊሰር ያሳውቃል፡፡ ወደ መጋዘን ከሆነ ደግሞ ለመጋዘን ኃላፊ ያሳውቃል፡፡

3. ከኮንቴነር የሚወጣ ዕቃ በማሽን ወይም በሰው ኃይል ለማውጣት አስቸጋሪ ሆኖ ካገኘ ወዲያው
ለቅርብ ኃላፊው ያሳውቃል፡፡

4. ታሊ ሸት (Tally sheet) ያዘጋጃል፡፡


5. ዕቃው ወጥቶ የተጠናቀቀ ኮንቴነር በ‘stacking form’
form’ መሠረት ለባዶ ኮንቴነር ኦፕሬሽን ሠራተኛ
ያስተላልፋል፡፡

6. ባዶ ኮንቴነር ከ CFS ወይም ከመጋዘን ስፍራ ወደ ባዶ ኮንቴነር ተርሚናል እንዲጓጓዝ ያደርጋል፡፡

7. ስለ ሥራ አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል፡፡

8. ከኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎች ተጨማሪ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡ የፎርክሊፍት ኦፕሬተር (2.5-6 ቶን)

ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ

ዋና ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን ክፍል

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለኦፕሬሽን ክፍል

ዝርዝር የሥራ ተግባራት

1. የተሰጡትን የደህንነት መመሪያዎች ማክበርና መጠበቅ፣ የኦፕሬሽንና ጥገና ማኑዋል በጥንቃቄ


ማንበብና የሚያንቀሳቅሰውን ማሽን ብቃቱን ማረጋገጥ፡፡
2. የፎርክሊፍት ኦፕሬተር ክብደት የማንሳት አቅም የሚያሳየውን መሳሪያ በመጠቀም አደጋ
የሚያስከትልና ከአቅም በላይ አለመሆኑን በመረዳት ጥንቃቄ ማድረግ፡፡
3. የስራ ቦታው በቂ መንቀሳቀሻ ያለው መሆኑንና ከሰዎች ወይም ህይወት ካላቸው እንስሳት
የፀዳ እንዲሁም አደናቃፊ ነገሮች አለመኖራቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡
4. የፎርክሊፍት ኦፕሬተሩ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ለእይታ የሚጋርዱ ሁኔታዎች ወይም
የሠው እንቅስቃሴ በሚበዛበት አካባቢ በሚሠራበት ጊዜ ምልክት የሚሠጡትን ረዳቶች
መጠቀም እና በረዳቱ የሚሰጡትን ምልክቶች በሚገባ መገንዘብና መግባባቱን እርግጠኛ መሆን
አለበት፡፡
5. በድርጅቱ የሚወጡ የደህንነት ህጎችንና ሌሎች ደንቦችን ማክበር፡፡
6. በየዕለቱ የማሽኑን ሴፍቲና ደህንነት ማረጋገጥ አለበት፣ ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀውን ቼክሊስት
መሙላት አለበት፡፡
7. የፎርክሊፍት ኦፕሬተር ከሚመለከተው ክፍል በሚሰጠው የሥራ ትዕዛዝ ብቻ መሥራት
ይኖርበታል፡፡
8. ማሽኑን በየጊዜውና አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ማፅዳት፣ንፅህናውን መጠበቅ አለበት፡፡
9. የፎርክሊፍት ኦፕሬተሩ የሚጠቀምበትን ፎርክሊፍት ወይም ሌላ መሣሪያ ስራውን ሲያጠናቅቅ
ወይም በማንኛውም ጊዜ ሁሉ ሲያቆም ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እና በጥንቃቄ ማቆም
ይጠበቅበታል፡፡
10. ለሥራ አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
11. ከኃላፊ የሚሰጡት ተጨማሪ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ የሪች ስታከር ኦኘርተር

ቅርንጫፍ ጽ/
ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ

ዋና ክፍል ፡ ኦፕሬሽን ክፍል

ቀጥታ ተጠሪነት ፡ ለኦፕሬሽን ክፍል

ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት

1. የተሠጠውን ሪች ስታከር በአግባቡና በጥንቃቄ ከንብረት ውድመትና የህይወት አደጋ በመጠበቅ


በአግባቡ ይይዛል፡፡

2. የማሽኑን የጥገናና የቅድመ ጥንቃቄ ማንዋል በተገቢው ሁኔታ በማንበብ ማሽኑን መጠቀም
ይኖርበታል፡፡

3. ማንኛውንም ካርጎ ከመጫንና ከማውረድ በፊት የክብደት ማንዋል (Loading chart) በተገቢው
ሁኔት ማወቅና በሚያዘው መሠረት እንደ ስራው አይነት ይሠራል፡፡

4. ኦኘሬተሩ በስራ አካባቢ ማሽኑን በሚጠቀምበት ወቅት ሠዎች፣ ማሽኖችንና ሌሎች ለአደጋ
የሚዳርጉ ነገሮች አለመኖሩን ማረጋገጥና ጥንቃቄ በመውሰድ ይሠራል፡፡

5. ኦኘሬተሩ በወደቡ ውስጥ በስራ ላይ በቀላሉ ለእይታ የሚያሰቸግሩ ቦታዎች ላይ በሚሠራበት ወቅት
ሌላ ከሥራው ጋር ግንኙነት ያለው ሰው በሚያመላክተው መሠረት ማሽኑን እና ማንኛውንም
ንብረት ከአደጋ በመጠበቅ ይሠራል፡፡

6. ሁሉንም የትራክ ደህንነት ምልክቶችና ህጐችን ጠንቅቆ ማወቅና መተግበር አለበት፡፡


7. በሚጭንበት ወይም በሚያራግፍበት ጊዜ የዕቃውን (ኮንቴነር)
ኮንቴነር) እና ጭነት የሚጭን ተሽከርካሪ
ደህንነት መጠበቅ ይኖርበታል፡፡

8. ኮንቴነሮች በአግባቡ (standard) በጠበቀ መልኩ መደርደር እና በማሽኑ እንዳይጋጩ ጥንቀቄ ማድረግ
አለበት፡፡

9. ኦፕሬተሩ በተርሚናል ውስጥ በተገቢው ፍጥነት እና በጥንቃቄ ብቻ ማሽከርከር አለበት፡፡

10. ኦኘሬተሩ ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት የቅድመ ጥንቃቄ እይታ (Inspection) እና ስራውን ካጠናቀቀ
በኋላ በቼክ ሊስት ላይ ያለውን ሁኔታ በማስፈር ሪፖርት ያደርጋል፡፡

11. የተሠጠውን ሪች ስታከር በጽዳት መያዝ አለበት፡፡

12. ማሽኑን በማንኛውም ጊዜ ለአደጋ በማያጋልጠው ቦታ ላይ ማቆም አለበት፡፡

13. ኦፕሬተሩ ከሚመለከተው ክፍል በሚሰጠው የሥራ ትዕዛዝ ብቻ ይሰራል፡፡

14. የሥራ አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡

15. ከኃላፊው የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡


የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ የፎርክሊፍት ኦኘሬተር (7-10 ቶን)

ቅርንጫፍ ጽ/
ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ

ዋና ክፍል ፡ ኦፕሬሽን ክፍል

ቀጥታ ተጠሪነት ፡ ለኦፕሬሽን ክፍል

ዝርዝር ተግባራት

16. የተሰጡትን የደህንነት መመሪያዎች ማክበርና መጠበቅ፣ የኦፕሬሽንና ጥገና ማኑዋል በጥንቃቄ
ማንበብና የሚያንቀሳቅሰውን ማሽን ብቃቱን ማረጋገጥ፡፡
17. የፎርክሊፍት ኦፕሬተር ክብደት የማንሳት አቅም የሚያሳየውን መሳሪያ በመጠቀም አደጋ
የሚያስከትልና ከአቅም በላይ አለመሆኑን በመረዳት ጥንቃቄ ማድረግ፡፡
18. የስራ ቦታው በቂ መንቀሳቀሻ ያለው መሆኑንና ከሰዎች ወይም ህይወት ካላቸው እንስሳት
የፀዳ እንዲሁም አደናቃፊ ነገሮች አለመኖራቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡
19. የፎርክሊፍት ኦፕሬተሩ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ለእይታ የሚጋርዱ ሁኔታዎች ወይም
የሠው እንቅስቃሴ በሚበዛበት አካባቢ በሚሠራበት ጊዜ ምልክት የሚሠጡትን ረዳቶች
መጠቀም እና በረዳቱ የሚሰጡትን ምልክቶች በሚገባ መገንዘብና መግባባቱን እርግጠኛ መሆን
አለበት፡፡
20. በድርጅቱ የሚወጡ የደህንነት ህጎችንና ሌሎች ደንቦችን ማክበር፡፡
21. በየዕለቱ የማሽኑን ሴፍቲና ደህንነት ማረጋገጥ አለበት፣ ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀውን ቼክሊስት
መሙላት አለበት፡፡
22. የፎርክሊፍት ኦፕሬተር ከሚመለከተው ክፍል በሚሰጠው የሥራ ትዕዛዝ ብቻ መሥራት
ይኖርበታል፡፡
23. ማሽኑን በየጊዜውና አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ማፅዳት፣ ንፅህናውን መጠበቅ አለበት፡፡
24. የፎርክሊፍት ኦፕሬተሩ የሚጠቀምበትን ፎርክሊፍት ወይም ሌላ መሣሪያ ስራውን ሲያጠናቅቅ
ወይም በማንኛውም ጊዜ ሁሉ ሲያቆም ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እና በጥንቃቄ ማቆም
ይጠበቅበታል፡፡
25. ለሥራ አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
26. ከኃላፊ የሚሰጡት ተጨማሪ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ አሰስሜንትና ክሊራንስ ኦፊሰር

ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ
ዋና ክፍል ፡ ኬዝ ቲም

ቀጥታ ተጠሪነት ፡ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ

ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት

1. በደንበኞች የሚቀርቡ ሰነዶች ትክክለኛና የተሟሉ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡


2. የጉምሩክ ዲክላሬሲዮን በ Asycuda++ ሲስተም በመጠቀም መረጃዎችን ይሞላል፡፡
3. የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ከዋጋና ከታሪፍ አንጻር ሰነዶችን በመመርመር ማስላትና ደንበኛ ክፍያ
እንዲፈጽም ያደርጋል፡፡
4. የወደብ አገልግሎት ክፍያ መተመንና ደንበኞች ክፍያውን እንዲፈጽሙ ያሳውቃል፡፡
5. ደንበኛው የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ እንዲሁም የወደብ አገልግሎት ክፍያ እንደፈጸመ ሰነዶችን
ወደ ጉምሩክ ጣቢያ እንዲላክ ያደርጋል፡፡
6. ሰነዱን ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ ገቢ በማድረግ የትራንዚት ፈቃድ ያገኛል፡፡
7. የትራንዚት ፈቃዱን ኮፒ ለጅቡቲ ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት በፋክስ ወይም ኢሜል መላክና መድረሱን
ይከታተላል፡፡ለሚዘጋጀው ኦፕሬሽን ከዋናው መስሪያ ቤት የኦፕሬሽን ቁጥር ይቀበላል፣በሰነዱ
ይሞላል፡፡ለጅቡቲ የተላውን ሰነድ ከፐፒ ለዋናወ 3 መስሪያ ቤት ይልካል፡፡
8. የተቆጣጣሪ ባለስልጣናት ፍቃድ ከተገኘ በኃላ የወጪ ዲክላሬሲዮን በማዘጋጀት በመተመን
ሰነዱን ለጉምሩክ ኢንስፔክተር በመስጠት እንዲፈተሽ እና ዕቃው እንዲታሸግ ያደርጋል፡፡
9. ወጪ ዕቃ የጫነው መኪና ወደ ወደብ እንዲጓዝ የዕቃ መልቀቂያ ፍቃድ ከጉምሩክ በመቀበል
ለአጓጓዥ ይሰጣል፡፡
10. የዲስፓች ሪፖርት በማዘጋጀት ለጅቡቲ ጽ/
ጽ/ቤት ይልካል፡፡ኮፒ ለዋናው መስሪያ ቤት ይልካል፡፤
11. ከዋናው መ/
መ/ቤት የተላኩ ሰነዶች ጅቡቲ ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት መድረሳቸውን የጉምሩክና የወደብ ፎርማሊቲ
መጠናቀቁን መከታተል ችግር ካጋጠመ ከሚመለከታቸዉ ጋር በመነጋገር መፍትሄ እንዲያገኝ
ያደርጋል፡፡
12. የደንበኞች ጭነት ከወደብ መነሳቱን መከታተልና ለደንበኞች ያሳውቃል፡፡
13. የገቢም ሆነ የወጪ ዕቃዎች ሰነዶች ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያለውን የክሊራንስ ሂደት
በመፈፀም ኦፕሬሽኑ እንዲዘጋ ያደርጋል፡፡
14. ከጉምሩክ ተጓዳኝ መ/
መ/ቤቶች ለሚጠየቁ መጠይቆች ምላሽ ይሰጣል፡፡
15. ከወደብ የመጣው ገቢ ዕቃ መቅረጫ ጣቢያ እንደደረሰ ኦርጅናል ሰነድ ጉምሩክ ገቢ በማድረግ
እንዲፈተሽ አድርጐ የዕቃ መልቀቂያ ይቀበላል፡፡
16. የመጋዘን ክፍያ በማስላት ደንበኛው እንደከፈለ ዕቃው ከጉምሩክ ክልል እንዲወጣ ያደርጋል፡፡
17. ዕለታዊ፣ ሣምንታዊ፣ወርሃዊና ዓመታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
18. ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ ጁኒየር ከስተምስ ቦንድ ሪኮንስሌሽንና የኮንቴይነር ክትትል ኦፊሰር

ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ

ዋና ክፍል ፡ ኦፕሬሽን ክፍል

ቀጥታ ተጠሪነት ፡ ለኦፕሬሽን ክፍል ኃላፊ

ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት

1. በየእለቱ ሎዲንግ ሪፖርት በመከታተል ለወደቡ ከጅቡቲ የተጫኑ ኮንቴይነሮችን መረጃ ይቀበላል፡፡
ለመመለከታቸው አካላት ለስራ ዝግጁነት እንዲያገለግል መረጃ ያስተላልፋል
2. ከዋናው መ/
መ/ቤት ለደረቅ ወደብ የሚላኩትን ኢንተርቼንጅ /ባዶ ኮንቴነሮች ወደ ጅቡቲ ወደብ የተመለሱበት
ሰነድ/
ሰነድ/ እና ጋላፊ የሚገኘው የጉምሩክ ማስተባበሪያ ጽ/
ጽ/ቤት ኮንቴነሮች ከአገር የወጡ ለመሆናቸው
የሰጠውን ማረጋገጫ መሠረት በማድረግ የኮንቴነሮቹን ዝርዝር መረጃዎች መዝግቦ ይይዛል፡፡
3. በጅቡቲ ወደብ ላይ መዘግየት ያጋጠማቸውን ደንበኞች ወይንም ልዩ እገዛ የሚፈልጉ በማንፋክቸሪንግ ዘረፍ
የተሰማሩ ባለሀብቶችን እቃቸው እንዲጫንላቸው ልዩ ክትትል ያደርጋል፣ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካለ
ለሀላፊው ያቀርባል፡፡
4. አደጋ የደረሰባቸው ኮንቴይነሮችን በተመለከተ የካሳ ክፍያ እና መሰል ጉዳዮች እንዲጠናቀ ከዋናው መስሪያ
ቤት ጋር በመነጋገር ያስፈፅማል፡፡
5. ደንበኛው ወስዶ ያልመለሳቸውን ባዶ ኮንቴይነሮች በመከታተል እንዲመለሱ ያደርጋል፡፡ መልስ ከደንበኛው
የማያገኝ ከሆነ ለህግ ክፍል ደብዳቤ በመፃፍ ጉዳዩን ይከታተላል፡፡
6. ለኮምቦልቻ እና አካባቢው የሚገኙ ላኪዎች የባዶ ኮንቴይነር ጥያቄ ሲቀርቡ አስፈላጊው ሰነድ መሟላቱን
በማረጋገጥ ይሰጣል፡፡አስፈላጊውን መረጃ ይይዛል፡፡
7. የውጪ ፍተሻ ለተፈቀደላቸው ደንበኞች ጉምሩክ በግልባጭ በሚያሳውቁን መሠረት ከደንበኛው አስፈላጊ
ሠነዶች በመቀበል እቃው ወደ መጋዘኑ ቀጥታ እንዲሄድ ለዋናው መስሪያ ቤት ማሳወቅ፡፡
ማሳወቅ፡፡
8. ባዶ ኮንቴይነር ከወደቡ ከወጣ በኃላ ጅቡቲ መድረሱን ይከታተላል ያልደረሱ ካሉ ወዲያውኑ ለቅርብ
ኃላፊው ሪፖርት ያደርጋል፡፡
9. ከጉምሩክ በኩል ለሚቀርቡ ከተመላሽ ኮንቴይነሮች ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ተቀብሎ ያስተናግዳል'
ያስተናግዳል'
ከአቅም በላይ የሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ለቅርብ አለቃው ያሳውቃል፡፡
10. ስለሥራው አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
11. ከኃላፊ የሚሰጠውን ተጨማሪ ሥራዎች ያናውናል፡፡
የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ ዴሊቨሪ ኦርደር ኦፊሰር

ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ

ዋና ክፍል ፡ ኦፕሬሽን ክፍል

ቀጥታ ተጠሪነት ፡ ለኦፕሬሽን ክፍል ኃላፊ

ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት

1. የዕቃ መልቀቂያ የሚጠይቁ አስመጭዎች/


አስመጭዎች/ወኪሎች የሚያቀርባቸውን ሰነዶች የተሟሉና ሕጋዊ
መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
2. ሰነዶች መሟላታቸውን በማረጋገጥ የዕቃ መልቀቂያ (Delivery order) አዘጋጅቶና
የሚመለከተው ኃላፊ እንዲፈርም በማድረግ ለሚመለከታቸው አስመጪዎች/
አስመጪዎች/ወኪሎች ይሰጣል፡፡
3. Dangerous Cargo ሰነድ ላይ በሚቀርበው መሰረት ለሂሳብ ክፍል በስሌቱ መሰረት እንዲከናወን
መረጃ ይሰጣል፡፡
4. Dangerous Cargo ቢፈተሸበት ጊዜ ለቀን ሰራተኞች አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ ኮንቴይነሩ
ከመከፈቱ በፈት ለታሊ ማን በቅድሚያ መረጃ ይሰጣል፡፡
5. ዕቃቸውን ከደረቅ ወደቡ በኮንቴነር መውሰድ የሚፈልጉ ደንበኞች ሲጠይቁ የተሟሉ ሰነዶች
መቅረባቸውን በማጣራትና የሚፈለግባቸውን የኮንቴነር ዲፖዚት እንዲያስይዙ በማድረግ ወይም
ያለክፍያ እንዲወሰዱ ከሚመለከታቸዉ ኃላፊዎች ደብዳቤ ከተፃፈ ተቀብሎ የኮንቴነር መልቀቂያ
(Container release) ይሰጣል፡፡
6. ዕቃቸውን (Unstuff) በማድረግ ያለኮንቴነር ለመውሰድ ለሚፈልጉ ደንበኞች የዕቃ መልቀቂያ
D/O ከመስጠቱ በፊት ከክፍያ ነፃ የሆነው ጊዜ (grace period) ያበቃ (ያለፈ)
ያለፈ) መሆኑን አለማለቁን
አረጋግጦ ለደንበኞች በማሳወቅ ዲመሬጅ እንዲከፍሉ ያደርጋል፡፡
7. ለፋይል ቀሪ የሚደረጉ የዕቃ መልቀቂያ D/O ሰነዶች አመች በሆነ ቦታ በጥንቃቄ እንዲቀመጡ
ያደርጋል፡፡ በሚመለከታቸው ኃላፊዎች ሰነድ ሲጠየቅ ያቀርባል፡፡
8. ስለ ሥራ አፈፃፀሙ ወቅታዊ ሪፖርቶችን አዘጋጅቶ ለቅርብ አለቃውና ለሚመለከታቸው ሁሉ
ያቀርባል፡፡
9. ስለ ሥራ አፈጻጸሙ ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
10. ከቅርብ ኃላፊው የሚሠጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ የበር ቁጥጥር ኦፊሰር

ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ

ዋና ክፍል ፡ ለኦፕሬሽን ዋና ክፍል

ቀጥታ ተጠሪነት ፡ ለክፍሉ ኃላፊ

ዝርዝር የሥራ ተግባር

1. የወደብ በር ቁጥጥር ሠራተኛ የመድረሻ ወደብ ጉምሩክ ትራንዚት ኦፊሰር በመንገድ ወረቀቱ (Way bill)
bill) ላይ
የትራንዚት ማብቂያ መግለጫ ፊርማና ማህተም ማኖሩን አረጋግጦና ተቀብሎ በተጨማሪም ሌሎች ተዛማች
ሠነዶችን ከሹፌሩ በመቀበል ቀድሞ ከደረሰው የገቢ ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ ጋር በማገናዘብና በማመሣከር፣
የኮንቴይነር ውጫዊ አካል በመፈተሽ የመግቢያ ፍቃድ (Gate pass)
pass) እና የኮንቴይነር መረካከቢያ ቅፅ (EIR)
EIR)
በማዘጋጀትና ወደ ወደብ ተርሚናል እንዲገባ ያደርጋል፡፡

2. የበር ቁጥጥር ሰራተኛው ያዘጋጀውን ‘Gate pass’ እና ‘EIR’ ፓድ ላይ ከቀረው በሥተቀር ያሉትን ከአባሪ ሰነዶች
ጋር በማያያዝ ለኦፕሬሽን ዶክመንቴሽን ኦፊሰርና ለጭነትና ሰነድ ክትል ኦፊሰር እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

3. ገቢ ጭነቶችን ጭኖ የገባው አሽከርካሪ ጭነቱን አራግፎ ሲመለስ የመግቢያ ፍቃዱንና የአገልግሎት መከታተያ ቅፁን
በመቀበል ሠዓቱን በመሙላት በተቀመጠለት ጊዜ ለማስተናገዱ በማረጋገጥ እንዲወጣ ያደርጋል፡፡

4. ጭነት ለመጫን ወደ ወደብ የሚገቡትን ተሽከርካሪዎች የበር ቁጥጥር ሠራኛው ከተርሚናል ኦፕሽን ክፍል በተላከለት
ትዕዛዝ መሠረት ተሽከርካሪዎቹ ባዶና ለጭነት የተዘጋጁ መሆናቸውን በማረጋገጥ እንደቅድመ ተከተላቸው ‘Gate
pass’ በማዘጋጀትና የሚጭኑበትን ቦታ በሠነድ ላይ በመጥቀስ ወደ ወደብ ተርሚናል እንዲገቡ ያደርጋል፡፡

5. ጭነት ከወደቡ ጭነው ለመውጣት የሚመጡ ተሽከርካሪዎች የበር ቁጥጥር ሠራተኛው የወደብ አገልግሎት ክፍያ
የተፈፀመባቸው ለመሆኑ የክፍያ ደረሰኝ ወይም ማረጋገጫ ሲደርሠው በማገናዘብ፣ በማመሣከርና የኮንቴይነሩን
ውጫዊ አካል በመፈተሽ ‘FULL EIR OUT’ በማዘጋጀት ከሹፌሩ ጋር በመተማመንና በመፈራረም፣ የጉምሩክ
ኢንስፔክተር መኖሩን በማረጋገጥ በጋራ ጭነቱ እንዲወጣ በማድረግ ያዘጋጀውን ‘FULL EIR OUT’
ለሚመለከተው ሰራተኛ ያስተላልፋል፡፡

6. ገቢ ባዶ ኮንቴይነር ወደ ወደብ ሲመጣ የበር ቁጥጥር ሰራተኛው አሽከርካሪው በመጣበት ቅድመ ተከተል መሰረት ቀድሞ
በወደቡ የተስተናገደ ከሆነ ሙሉ ኮንቴይነሩን ጭኖ ሲወጣ የተሰጠው ‘FULL EIR OUT’ ያለው መሆኑን
ያረጋግጣል፣ ቀድሞ በወደቡ ያልተስተናገደ ከሆነ ከመርከብ ወኪል ጥያቄ የቀረበና በወደቡ እንዲስተናገድ የተፈቀደ
መሆኑን በማረጋገጥ የባዶ ኮንቴይነሩን ውስጣዊና ውጫዊ አካል በመፈተሽ ‘GATE PASS’ እና ‘EMPTY IN
EIR’ በማዘጋጀትና ከአሽከርካሪው ጋር በመተማመንና በመፈራረም ኮንቴይነሩን የሚያራግፍበትን ቦታ በሰነድ
ላይ በመጥቀስ ወደ ወደብ ተርሚናል እንዲገባ ያደርጋል፡፡

7. በፓዱ ላይ ቀሪ ከሚሆነው በስተቀር ያሉ ‘GATE PASS’ እና ‘EIR’ ¢ú c’Ê‹ KT>SKŸ}¨< W^}— ¾}LŸuƒ”
W¯ƒ uSS<Lƒ Áe}LMóM::

8. ከወደቡ ለሚወጡ ወጪ ባዶ ኮንቴይነሮች ተገቢውን ሰነድ ማሟላታቸውን በማረጋገጥ እና የኮንቴይነሩን ውስጣዊና


ውጫዊ አካል በመፈተሽ ‘EMPTY OUT EIR’
EIR’ በማዘጋጀት እንዲወጡ ያደርጋል፡፡

9. የክፍያ ሰነድ ሥህተት ሲኖር ወደ ፋይናንስ ክፍል በመመለስ እንዲስተካከል ያደርጋል፡፡

10. ጭነቶች በተሣሣተ መንገድ ከወደቡ እንዳይወጡ ጥብቅ ቁጥጥርና ፍተሻ ያደርጋል፡፡

11. በተለያየ ምክንያት ጭነት ከጫኑ በኋላ ወደቡ ግቢ ውስጥ የሚያድሩ ጭነቶች ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍሉ ያደርጋል፣
ሣይከፍሉ እንዳይወጡ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡

12. የገቢና ወጪ ጭነቶች መረጃ መዝግቦ ይይዛል፡፡

13. ዕለታዊ፣ ሣምንታዊ፣ ወርሃዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመትና ዓመታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡

14. ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎችት ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ ጁኒየር ተርሚናል ቁጥጥር ኦፊሰር


ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ

ዋና ክፍል ፡ ለኦፕሬሽን ዋና ክፍል

ቀጥታ ተጠሪነት ፡ ለክፍሉ ሀላፊ

ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት

1. CFS area ላይ ፍተሻቸው የተጠናቀቁ ኮንቴነሮችን ወደ ማቆያ ቦታ መላክ፡፡

2. ለድጋሚ ፍተሻ ማቆያ ቦታ ካሉ ኮንቴነሮች መካከል በደንበኛው ተጠይቆ ሲፈቀድ ግራውንድ


ማድረግ፡፡

3. ከ CFS እና ከማቆያ ቦታ ኮንቴይነሮች ተገቢውን ሂደት አጠናቀው እንዲጫኑ ሲፈቀድ “Good


release order” ከኦፕሬሽን ክፍል ሲላክ ማስጫን፡፡

4. ኮንቴይነሮች ለ unstuff ወደ unstuffing area ሲላሉ በ work order ላይ የተጠቀሱትን ኮንቴይነሮች


ጉምሩክ ሲሉን ሲቆርጥላቸው ጉልበት ሠራተኞችን ወይም ፎርክ ሊፍት ኦፕሬተሮችን በማዘዝ
unstuff ማስድረግ፡፡
5. ፍተሻቸው ተጠናቆ ማቆያ ቦታ ወይም CFS area ያሉ ኮንቴይነሮች ደንበኛው unstaff አድርጎ
መወሰድ ሲፈለግ በ work order መሠረት ወደ unstuffing area መላክና Unstaff ማድረግ
6. Unstuff ተደርገው ባዶ የሆኑ ኮንቴይነሮችን የባዶ ኮንቴይነር መረካከቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት
ለ D/O ሠራተኛ ማስረከብ በተጨማሪ DPOIS ሲስተም ላይ ኮንቴይነሩን መመዝገብ፡፡
7. Unstuff ተደርገው ባዶ የሆኑ ኮንቴይነሮችን ወደ Empty ተርሚናል መላክ፡፡
8. የማሽን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ከተሰረው ስራ እና ከተሞላው ነዳጅ ጋር በማነፃፀር ሪፖረት
ያዘጋጃል፡፡በኪራይ ያለው ማሽንየስራ ሰአት ከእለታዊ ሪፖርት የተቀዳ ወርሃዊ ሪፖርት ያዘጋጃል፡፡
9. ስለስራው አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
10. ከኃላፊ የሚሰጡ ተጨማሪ ሌሎች ሥራዎች

You might also like