You are on page 1of 48

የኢትዮጵያ ፌዳራሊዊ ዳሞክራሲያዊ ሪፐብሉክ

የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ


ማስፈጸሚያ መምሪያ (Guideline)

ረቂቅ 1.0

አዱስ አበባ- ኢትዮጵያ


2013 ዓ.ም

i
ትርጉም፣

 ዓሊማ:-የትኩረት አቅጣጫው ሇምን እንዲስፈሇገ የሚገሌጽ ነው፡፡


 አዴማስ:-እያንዲንደ የትኩረት አቅጣጫ በምን ሁኔታዎች ሊይ ሉተገበር እና ሉከናወን
እንዯሚችሌ ያሇውን ትኩረት የሚያሳይ ነው፡፡
 መስፈርት:-እያንዲንደን የትኩረት እቅጣጫዎች በሥራ ሊይ ሇማዋሌ ምን ምን
ጉዲዮች መከናወን እንዲሇባቸው ይገሌጻሌ፤
 ቁጥጥር:-አንዴ የትኩረት አቅጣጫ መተግበሩን ወይም አሇመተግበሩን የሚያሳዩ
ምክንያቶችን የሚያትት ነው፡፡
 የትግበራ መምሪያ፡-የሚመሇከታቸው አካሊት እንዳት አዴርገው በዚህ መምሪያ
ውስጥ የተጠቀሱ የትኩረት አቅጣጫዎች በስራ ሊይ ማዋሌ
እንዯሚችለ የሚገሌጽ ነው፡፡

ii
ማውጫ
1. መግቢያ ...................................................................................................................... 4
2. የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ ማስፈጸሚያ መምሪያ አስፈሊጊነት ......................... 4
3. አዴማስ....................................................................................................................... 5
4. ዓሊማ.......................................................................................................................... 5
4.1. ዝርዝር ዓሊማዎች................................................................................................. 5
5. መምሪያውን እንዳት መጠቀም ይቻሊሌ ?..................................................................... 6
6. የብሄራዊ ሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ የትኩረት አቅጣጫዎች ............................ 6
6.1. የህግና የቁጥጥር ማዕቀፍ ...................................................................................... 6
6.2. የሳይበር ዯህንነት ንቃተ-ህሉና................................................................................ 9
6.3. የሳይበር ዯህንነት አቅም ግንባታ .......................................................................... 12
6.4. የሳይበር ዯህንነት ምርምርና ሌማት ..................................................................... 19
6.5. የዱጂታሌ ማንነትና ግሊዊ መረጃ ጥበቃ ............................................................... 20
6.6. ቁሌፍ የመረጃ መሰረተ-ሌማት ጥበቃ ................................................................... 22
6.7. ሃገር-አቀፍ እና ዓሇም-አቀፍ ትብብር .................................................................... 25
7. የባሇዴርሻ አካሊት ኃሊፊነትና ሚና ............................................................................... 31
7.1. ኢንፎርሜሽን መረብ ዯህንነት ኤጀንሲ ............................................................... 31
7.2. ብሔራዊ የሳይበር ዯህንነት ምክር ቤት.............................................................. 32
7.3. የኢትዮ ሰርት (CER2T) .................................................................................. 32
7.4. የህግ አካሊት .................................................................................................. 32
7.5. የግለ ዘርፍ ..................................................................................................... 32
7.6. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ............................................................................ 33
7.7. ቁሌፍ የመሰረተ-ሌማት ዘርፎች ........................................................................ 33
8. ብሔራዊ የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲ እና ስትራቴጂ የማስፈጸሚያ መርሃ ግብር .............. 34

iii
1. መግቢያ

ይህ የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ ማስፈጸሚያ መምሪያ የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና


ስትራቴጂ በብሄራዊ ዯረጃ ግሌጽና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገዴ ሇመተግበር ያስችሊሌ፡፡
መምሪያው በፖሉሲና ስትራተጂው የተጠቀሱ አንኳር ሰባት የትኩረት አቅጣጫዎች
የሚተገበሩበትን መንገድች በማሳየት የአገሪቱን የሳይበር ዯህንነት አቅም በሁለም ዘርፎች
ሇማሳዯግ ያሇመ ነው፡፡

በመሆኑም ፖሉሲና ስትራቴጂው በስኬት እንዱተገበር እና ሇትግበራው ተግዲሮት የሚሆኑ


ውጫዊ ሁኔታዎች በማስወገዴ በእያንዲንደ ዯረጃ ሊይ ተስማሚ የሆኑ የሀብት ምንጮች
በማቀናጀት፣ ተቀባይነት ያሇው የመንስኤና ውጤት ንዴፈ-ሀሳብ በማስቀመጥ፣ በመንስኤና
ውጤት መካከሌ ቀጥተኛ የሆነ ትስስር እንዱኖር በማዴረግ፣ አንዴ ዋና እና ብቸኛ ሇሆነ
ተግባሪ ተቋም ኃሊፊነት በመስጠት፣ በሚከናወኑ ግቦች ዙሪያ መግባባትና ስምምነቶች
በመፍጠር ሉፈጸሙ ስሇሚገባቸው ተግባራት ዝርዝር የሆነ ገሇጻ ማስቀመጥ፣ ግሌጽ የሆነ
ተግባቦትና ቅንጅት እንዯቁሌፍ ተሞክሮ አዴርጎ በመውሰዴ አስፈሊጊ ነጥቦችን በተፈሇገው
ጊዜና ቦታ ታሳቢ በማዴረግ የተቀረጸ ነው፡፡

በአጠቃሊይ ይህ የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ መተግበሪያ መምሪያ የተቀናጀውና


የተዘጋጀው ከሊይ የተጠቀሱትን የጽንሰ-ሀሳብ ማዕቀፎች ግምት ውስጥ አስገብቶ በመሆኑ
በኢትዮጵያ በሳይበር ዯህንነት ዘርፍ ሇማሳካት የሚፈሇገውን መሻሻሌ በማምጣት በኩሌ
ጉሌህ ሚና ይኖረዋሌ፡፡

2. የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ ማስፈጸሚያ መምሪያ አስፈሊጊነት

አሁን ያሇው አሇም አቀፍ የሳይበር ዯህንነት ነባራዊ ሁኔታ እና በሃገራችን የኮሙኒኬሽን
እና ኢንፎርሜሽን ስርዓት እያዯገ መምጣት መሌካም አጋጣሚዎች እንዲለት ሁለ
ተግዲሮቶችም ይስተዋሊለ፡፡ እንዱሁም ብሔራዊ ዯህንነት ሊይ የተጋረጠ የሳይበር ስጋትና
ተጋሊጭነት እንዳሇ ሁለ ዯህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ሇማስቻሌ የሕዝብ ሰሊምና
ዯህንነት፣ የዜጎች መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶችን መጠበቅ ተገቢ ነው፡፡ ይህም ሃገራት
የሚገጥሟቸውን እነዚህን ተግዲሮቶች ሇመቋቋም የራሳቸውን የሳይበር ዯህንነት ማረጋገጥ
ተገቢ ስሇሆነ የተሇያዩ ፖሉሲዎችና ማዕቀፎች ያወጣለ፡፡

4
የዚህ ማስፈጸሚያ መምሪያ መኖር አሁን ሊሇው የሃገሪቱ የሳይበር ዯህንነት ወቅታዊ እና
መፃኢ ዕድልች ትክክሇኛ አቅጣጫ እና ስትራቴጂ ሇማመሊከት፣ ፖሉሲ እና
ስትራቴጂውን በአግባቡ ሇመምራት፣ የመንግስት እና የግሌ አጋርነት ትብብር እንዱኖር
ሇማዴረግ፣ እንዱሁም የሚመሇከታቸው አካሊት ፖሉሲውን ሇማስፈጸም በሃገር ዓቀፍ
ብልም በአሇም ዓቀፍ ዯረጃ የተሰጣቸውን ኃሊፊነት እንዱወጡ አስፈሊጊ ነው።

ስሇሆነም ይህ የማስፈጸሚያ መምሪያ የሳይበር ዯህንነት ዓሊማዎች፣ግቦች፣መርህዎችና


አጠቃሊይ ይዘት መነሻ በማዴረግ የተዘጋጀ ሲሆን ሇተግባራዊነቱ የዜጎችን፣ የመንግስትን፣
የግሌ ተቋማትን እንዱሁም ላልች ባሇዴርሻ አካሊትን በማቀናጀት የሳይበር ዯህንነትን
በማረጋገጥ ብሔራዊ ጥቅሞችን ሇማስጠበቅ ያስችሊሌ፡፡

3. አዴማስ
ይህ መምሪያ የመንግስትና የግሌ ተቋማትን ጨምሮ በሃገሪቱ የሚመሇከታቸው ባሇዴርሻ
አካሊት በቀሊለ እንዳት ብሄራዊ የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂን ወዯ ተግባር
ሉያወርደት እንዯሚችለ የሚያሳይ ጠቋሚና ተግባራዊ ምክረ-ሀሳቦችን የያዘ ነው፡፡

4. ዓሊማ
የዚህ መምሪያ ዓሊማ የብሔራዊ የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ የትኩረት
አቅጣጫዎችን እና ግቦችን በአግባቡ በማመሊከት የፖሉሲና ስትራቴጂውን ተፈፃሚነት
ዕውን ሇማዴረግ፤እንዱሁም የፖሉሲና ስትራቴጂው አተገባበር ግሌጽና ሁለን አሳታፊ
እንዱሆን በማዴረግ የሚመሇከታቸው አካሊት ኃሊፊነታቸውን እንዱወጡ ሇማዴረግ ነው፡፡

4.1. ዝርዝር ዓሊማዎች

 የፖሉሲና ስትራቴጂ የትኩረት አቅጣጫዎችን በዝርዝር ሇማመሊከት፤


 ሇመንግስት እና ሇግሌ ተቋማት ፖሉሲና ስትራቴጂውን ሇመተግበር የሚረደ
ጠቃሚ ምክረ-ሀሳቦችን ሇማመሊከት፤
 ኢትዮጵያ ከላልች ሃገር-አቀፍ እና ዓሇም-አቀፍ ተቋማት፤ እንዱሁም ከተሇያዩ
ሃገራት ጋር አጋርነት እና ትብብር በመፍጠር እንዳት የሳይበር ዯህንነቷን
ማሳዯግ እንዯምትችሌ አቅጣጫ ሇማሳየት፤
 ግሌጽና ሁለን ዓቀፍ በሆነ ሁኔታ የባሇዴርሻ እና ተባባሪ አካሊት ሚና በአግባቡ
በዝርዝር በማስቀመጥ ሁለም አካሊት የየራሳቸውን ዴርሻ እና ሚና በመሇየት
ሇተግባራዊነቱ የበኩሊቸውን እንዱወጡ ሇማስቻሌ፤
5
5. መምሪያውን እንዳት መጠቀም ይቻሊሌ
 ብሄራዊ የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂን በሚገባ መረዲት፤
 ፖሉሲና ስትራቴጂው ከትግበራ መምሪያው ጋር በማነጻጸር መረዲት፤
 ከእያንዲንደ የትኩረት አቅጣጫ ትይዩ የተቀመጠውን የትግበራ መምሪያ መረዲት፤
 ዓሊማዎቹ በትግበራ መምሪያው ስር ከተቀመጡትን ነጥቦች ጋር ያሇውን ዝምዴና
መረዲት፤
 በትግበራ መምሪያው ስር ያለትን ነጥቦች ወዯ ተግባር ሇማውረዴ መትጋት፤

6. የብሄራዊ ሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ የትኩረት አቅጣጫዎች

6.1. የህግና የቁጥጥር ማዕቀፍ

6.1.1. መግቢያ

የሃገራችንን የሳይበር ዯህንነት የሚያስጠብቁ ሕግጋት እና የቁጥጥር ማዕቀፎች ማሌማቱ፣


ማጽዯቁ እና ተፈጻሚ ማዴረጉ የሳይበር ተጋሊጭነትና ስጋት ከመቀነስ ባሻገር
የሚመሇከታቸው አካሊት ኃሊፊነቶቻቸውንና ግዳታዎቻቸውን እንዱወጡ ያዯርጋሌ፡፡
ስሇሆነም የሃገሪቱን ብሄራዊ የሳይበር-ምህዲር እና ቁሌፍ መሰረተ-ሌማቶችን ዯህንነት
ሇማስጠበቅ፣ ከጥቃት ሇመከሊከሌ፣ ጥቃት ሲፈጸም ምሊሽ ሇመስጠት፣ ሇሕግ ሇማቅረብ
እና የሳይበር ዯህንነት ግንዛቤ በማህበረሰቡ ዘንዴ እንዱሰርጽ ሇማዴረግ ይቻሌ ዘንዴ
የሚከተለት ግቦች፣ መስፈርቶች፣ የቁጥጥርና የትግበራ መምሪያዎች ተግባራዊ ይዯረጋለ፡፡

6.1.2. ግቦች
1. የሳይበር ዯህንነት ስጋቶችንና ተጋሊጭነቶችን ሇመቀነስ፤ ጥቃቶችን ሇመከሊከሌ እና
ሇመቋቋም የሚያግዙ፤ እንዱሁም ሀገሪቱ ከተቀበሇቻቸውቀጠናዊ፣ አህጉራዊና ዓሇም
አቀፍ ህጎችእና ስታንዲርድች ጋር ተጣጣሚነት ያሊቸው የሳይበር ዯህንነት ሕግጋት እና
ቁጥጥር ማዕቀፎችን ማውጣት፤ በቀጣይነትም ማሻሻሌ፤

2. የሳይበር ወንጀሌ፣ ሳይበር ሽብርተኝነት፣ የሳይበር ስሇሊ እና መሰሌ ጥቃቶች ሇመከሊከሌ


የሚያስችሌ የህግ አካሊትን አቅም መገንባት፤
3. በሀገር ውስጥ የሚመረቱና ወዯ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የሳይበር ዯህንነት ምርቶችና
አገሌግልቶች፤ እንዱሁም ቁሌፍ የመሰረተ ሌማት ዝርጋታዎች ሀገራዊ የሳይበር

6
ዯህንነት ፍሊጎትን ያሟለ መሆናቸውን ሇማረጋገጥ የሚያስችሌ የቁጥጥር ስርዓት
መዘርጋት፤
4. ማህበረሰቡ በሀገሪቱ የሳይበር ዯህንነት አቅሞች ዙሪያ ያሇውን ዓመኔታ ሇማሳዯግ
በኢንፎርሜሽን አሰባሰብ፣ ትንተና፣ ስርጭት፣ አጠቃቀም፣ ክምችት እና አወጋገዴ ዙሪያ
ዯረጃቸውን የጠበቁ የህግና ቁጥጥር ማዕቀፎችን መዘርጋት፤

6.1.3. አዴማስ
ይህ የትኩረት አቅጣጫ በኢትዮጵያ የሳይበር ዯህንነት የህግና ቁጥጥር ማዕቀፎችን
በማሌማት፣ አቅም በመገንባት እና የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ዙሪያ የሚያተኩር ነው፡፡

6.1.4. መስፈርት

የሃገሪቱን የሳይበር ዯህንነትን በተፈሇገው መጠን ሇማሳዯግ የሚመሇከታቸው አካሊት


እንዯአስፈሊጊነቱ የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ ወዯ ተግባር ሇማውረዴ የሚያችለ
ህጎች፣ አዋጆች፣ ዯንቦች፣ ስታንዲርድች፣ መመሪያዎች እና ላልች የቁጥጥር ማዕቀፎችን
በመውጣት ስራ ሊይ ማዋሌ ይኖርባቸዋሌ፡፡

6.1.5. ቁጥጥር

ይህ የትኩረት አቅጣጫ በትክክሌ ተተግብሯሌ የሚባሇው የሃገሪቱ የሳይበር ዯህንነት የህግና


የቁጥጥር የትኩረት አቅጣጫ ክፍተት በጥናት እየተሇየ ሲሇማና ሲተገበር ነው፡፡

6.1.6. የትግበራ መምሪያ


 ተጋሊጭነቶችን በማግኘት መፍትሄ ሇመስጠት ይቻሌ ዘንዴ ህጋዊና የቁጥጥር
እርምጃዎችን አሁን ያሇውን የመንግስት/የህዝብ ዘርፍ፣ የግለ-ዘርፍ እና
የኮምፒውተር ኢንፎርሜሽን ስርዓት ተጠቃሚዎችን ህጋዊ ግዳታዎችና
ኃሊፊነቶችን ባካተተ መሌኩ ግምገማ ማዴረግ፤
 ኢትዮጲያ የፈረመቻቸው ከሳይበር ጋር የተያያዙ የዓሇም-አቀፍ ህግ ስምምነቶች እና
ግዳታዎች፣ እንዱሁም በተሇያዩ ዓሇም-አቀፍና አህጉር-አቀፍ ዴርጅቶች ውስጥ
አባሌ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ኃሊፊነቶችና ግዳታዎችን ሇመወጣት
እንዱቻሌ የፖሉሲና ህጋዊ ማእቀፎችን ማሻሻሌ፤
 ብሄራዊ የሳይበር ህግጋት ተያያዥነት ባሇው አጠቃሊይ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ
መንገዴ ሇሳይበር ስጋቶች መሌስ እንዲይሰጥ የሚያዯርጉትን ክፍተቶች መሇየት፣
እነዚህ ክፍተቶች ሇመመከት አስፈሊጊ የሆኑ ህጋዊ እርምጃዎችን ማጎሌበት

7
እንዱሁም እነዚህን የቀረቡ ሀሳቦች ከላልች ህጋዊ የሆኑ ግሇሰባዊና ማህበረሰባዊ
ባሇዴርሻ አካሊት ጥቅሞች ጋር በጥንቃቄ ሚዛናቸውን የጠበቁ እንዱሆኑ ማዴረግ፤

 አስፈሊጊ የሆኑ ህግጋትን ከሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማስማማት መጠቀም


እንዱሁም ዓሇም-አቀፍ ስምምነቶችን መፈረም፤
 ሌዩ ስሌጠና የወሰደ አባሊትን የያዙ ብሄራዊ የሳይበር-ወንጀሌ መምሪያዎችን/units/
(ህግ አስፈጻሚና የህግ አውጪ ባሇስሌጣናትን የያዘ) ማቋቋም፤
 ሇፀጥታ አካሊት ቀጣይነት ያሇውና ሌዩ የሆነ ስሌጠና መሰጠቱን ማረጋገጥ
(ሇምሳላ፡- ዱጂታሌ ፎሬንሲክን በተመሇከተ)፤
 ፖሉሶች እና ዲኞች ተጣጣሚ በሆነ መሌኩ መረጃን ማስቀመጥ/record-keeping/
የሚያስችሎቸውን ዯንቦች እንዱሁም የኮምፒውተር ወንጀልችን ስነ-
ግምታዊ/statistical ትንተና ሇማዴረግ የሚያስችለ ተገቢ መሳሪያዎችን መፍጠር፤
 በተሇያዩ ባሇዴርሻ አካሊት መካከሌ ትብብርን ሇማጎሌበት መዴረኮችን ማዘጋጀት
(ሇምሳላ፡- የኮምፒውተር ዴንገተኛ አዯጋ መሌስ ሰጪ ቡዴኖች/CERTs እና የመረጃ
አካሊት)፤
 ኢንደስትሪዎች በኮምፒወተርና ኮምፒውተር ስርዓቶች ጋር የተያያዙ ወንጀልችን
ሇመከሊከሌ ቀጥተኛ እርምጃ እንዱወስደ ማበረታታት፤
 አዲዱስ ዱጂታሌ ፎረንሲክ ስሌቶችን በተመሇከተ መሪ ከሆኑ የትምህርት እንዱሁም
ከምርምርና ሌማት ተቋማት ጋር ትብብር ማዴረግ፤
 ከሳይበር ወንጀልች ጋር ዝምዴና ያሊቸውን ጉዲዮች በፍጥነት ሇመሇየትና መሌስ
ሇመስጠት የመንግስትና የግሌ አጋርነቶችን፤ መመሰረትና ማጠናከር፤
 የሳይበር ዯህንነት ችግሮች ከሞሊ-ጎዯሌ ሉሸፍኑ የሚችለ የሚከተለትን የህግ
ዓይነቶች አጽዴቆ ስራ ሊይ ማዋሌ፣
1. የግሊዊ ሕይወት እና የግሌ ዲታ ማስኬጃ ህግ/Privacy and Personal Data
Processing Law/፡- የሳይበር-ክስተት ኩነት በሚኖርበት ጊዜ ኦፐሬሽናሌ
የኢንፎሜሽን መጋራት መርሆችን ጨምሮ፤
2. የቴላኮሙኒኬሽኖች ህግ/Telecommunications Law/፡- የኮምፒውተር ስርዓት
መሰረተ-ሌማቶችና የአገሌግልት ቀጣይነትን ሇማጋገጥ የሚረደ የዲታ
ኮሙኒኬሽኖች አገሌግልት ሰጪዎችን፤ የኮሙኒኬሽን ኔትዎርኮች ሊይ የዯህንነት
ወይም የተአማኒነት ስጋት ሁኔታ በሚፈጠርበት ጊዜ አገሌግልት ሰጪዎች
ጣሌቃ የሚገቡባቸውን ዘዳዎች ጨምሮ፤

8
3. የሳይበር ወንጀሌ እና የሳይበር ወንጀሇኛ ስነ-ስርዓት ህግ፡-
4. ቁሌፍ የመረጃ መሰረተ-ሌማት ጥበቃ እና የቀውስ አስተዲዯር ህግ/Critical
Information Infrastructure Protection and Crisis Management Law/፡-

6.2. የሳይበር ዯህንነት ንቃተ-ህሉና

6.2.1. መግቢያ
የሳይበር ዯህንነት ስጋቶችና ተጋሊጭነቶች በማህበረሰቡ ሊይ የሚያሳርፉትን ተጽእኖ
በተመሇከተ የማህበረሰቡን ንቃተ-ህሉና ማሳዯጉ እጅግ ጠቃሚ እየሆነ መጥቷሌ፡፡ ስሇሆነም
በሀገሪቱ በሳይበር ዯህንነት አካሊት ዘንዴ የሳይበር ስጋቶችንና ተጋሊጭነቶችን ሇመቀነስ
የህብረተሰቡ ንቃተ-ህሉና ከፍ በማዴረግ፤ የመረጃ ዋጋና የሳይበር ዯህንነት ጥቃት
አስመሌክቶ በእውቀት ሊይ የተመሰረተ የመረጃ ሌውውጥ ባህሌ እንዱጎሇብት፤ እንዱሁም
የአመሇካከትና የባህሪ ሇውጥ እንዱመጣ እና እንዱዲብር ትኩረት ሰጥቶ ይሰራሌ፡፡

6.2.2. ግቦች
1. የመንግስት ተቋማት፣ የግሌ ተቋማትና ዜጎች በሳይበር ዯህንነት ዙሪያ ያሊቸውን
እውቀትና አመሇካከት ማዲበር፤
2. ከጥንቃቄ ጉዴሇትና ካሇማወቅ የሚዯርሱ የሳይበር ጥቃቶች፣ ስጋቶች እና
ተጋሊጭነቶችን መቀነስ፣
3. የሳይበር ዯህንነት ተጋሊጭነቶችና ስጋቶች ሇመቀነስ፤ እንዱሁም ጥቃቶች ሇመከሊከሌ
የሚያስችሌ የዜጎች ንቃተ-ህሉና ማሳዯግ እና ሀገራዊ የሳይበር ዯህንነት ባህሌ መፍጠር፤

6.2.3. አዴማስ
ይህ የትኩረት አቅጣጫ የሚያተኩረው የማህበረሰቡን የሳይበር ዯህንነት ንቃተ-ህሉና ከፍ
በማዴረግ ዙሪያ ነው፡፡

6.2.4. መስፈርት

የማህረሰቡን የሳይበር ዯህንነት ንቃተ-ህሉና ሇማዲበር ቀጣይነት ያሊቸው መዴረኮች፣


ሴሚናሮች፣ ኮንፈረንሶች፣ ስሌጠናዎች፣ መርሀ-ግብሮች፣የሚዱያ ፕሮግራሞችና ላልችም
በሃገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ በሚካሄደትም ሊይ ተሳትፎ መዯረግ ይኖርበታሌ፡፡

6.2.5. ቁጥጥር
ይህ የትኩረት አቅጣጫ በአግባቡ መተግበሩ የሚረጋገጠው የሳይበር ዯህንነት ንቃተ-ህሉናን
ሇማሳዯግ ዘርፈ-ብዙ እንቅስቃሴዎች በሁለም ባሇዴርሻ አካሊት ሲዯረግ ነው፡፡
9
6.2.6. የትግበራ መምሪያ
 በሁለም ዯረጃዎች ሊለ የማህበረሰብ ክፍልች ተገቢ የሆነ የመረጃ አጠቃቀም
አቅም የመጨመር አስፈሊጊነት ግምት ውስጥ በማስገባት ሇንቃተ-ህሉና
እርምጃዎች ተገቢ የሆኑ አዴማጮች እና/ወይም ተመሌካቾች መሇየት፤
 በሃገሪቱ ውስጥ የሳይበር ዯህንነት ባህሌን ማጠናከርን እና ሇህዝብ ይፋ
የሆኑትን እና/ወይም ኢሊማ የተዯረጉ የመረጃ ቁሶችን ጨምሮ ከሳይበር
ዯህንነት ጋር በቀጥታ የተገናኙ ወይም ሳይበር ዯህንነትን ሇማረጋገጥ የተሇያዩ
የሙያ መስኮች ሊይ የተሰማሩ ሙያተኞችን የሳይበር ዯህንነት ንቃተ-ህሉና
ማሻሻሌ፣
 በኦንሊይን የንቃተ-ህሉና እና መማሪያ ከባቢና መሳሪያዎችን፣ የሳይበር
ዕውቀት ሇማሳዯግ የሚረደ መሰረታዊ የትምህርት መርሀ-ግብሮችን፤
እንዱሁም ከዚህ ከፍ ባሇ ዯረጃ የንቃተ-ህሉና እርምጃዎች ተስማሚነትና
ውጤታማነት ሇመዲሰስ ጠቃሚ ሚና ያሇው በመረጃና ኔትዎርክ ዯህንነት፣
ቴክኒካዊና/ኦፕሬሽናሌ ገጽታዎችን፣ ስትራቴጂያዊና ፖሇቲካዊ ውሳኔ
የመስጠት ቅዯም-ተከተልችን ወይም ሁሇቱንም ያካተተ የሳይበር መከሊከሌ
ሌምምድች ሌዩ የሆነ የስሌጠና ካሪኩሇምና መርሀ-ግብሮችን የያዙ
እንቅስቃሴዎች ማዴረግ፤

 ሇንቃተ-ህሉና ማጎሌበት ዘመቻ ኢሊማ ተዯርገው የተመረጡትን አዴማጮች


እና/ወይም ተመሌካቾች በሚገባ መሇየት (ሇምሳላ፡- ዜጎች፣ የኮምፒወተር
ምርቶች ተጠቃሚዎች/end-users/፤
 ሇተሇያዩ የሳይበር ተጠቃሚ ማህበረሰብ ክፍልች ንቃተ ህሉና ማሳዯጊያ
ዘዳዎችን ማሌማት፤
 ኢሊማ የተዯረጉትን አዴማጮች እና/ወይም ተመሌካቾች ሊይ ተጽዕኖ
ሉያሳዴሩ የሚችለ የተሇመደ ባህሪያዊ ችግሮችን ወይም ኢሊማ የተዯረጉት
አዴማጮች እና/ወይም ተመሌካቾች ሉያውቋቸው የሚገቡ ጉዲዮችን
መሇየት፤
 የብሄራዊ መረጃ ዯህንነት ሌዩ መሇያ/unique/ መፍጠር፡- የስትራቴጂ
ዓሊማዎችን የሚዯግፉ ግሌጽ የሆነ የመረጃ ዯህንነት ርዕሶችን መምረጥ
ከዚያም በሃገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓሇም-አቀፍና በአካባቢያዊ ኩነቶች ሊይ

10
ተገቢ የሆኑ የኮሙኒኬሽን መስመሮችን/channels/ በመጠቀም ማዯረጀትና
ማስተዋወቅ፤
 የሳይበር ዯህንነት ንቃተ ሂሉና ባህሌ ግንባታውን ሇማጠናከር እንዱቻሌ
በየጊዜው የተሇያዩ ጉዲዮችን የያዘ በመንግስት፣ ወይም ከግለ ዘርፍ ጋር
በአጋርነት ብሄራዊ የሳይበር ዯህንነት ወር፣ ሳምንትና ቀን ማዘጋጀት፤
 ዯህንነቱ በተጠበቀ መንግስታዊ ዴረ-ገጽ ከመረጃ ዯህንነት ጋር ዝምዴና
ባሊቸው ቁሶች(ሇምሳላ፡- በዴረ-ገጽ ሊይ የሚዯረጉ ሴሚናሮች/webinars/፣
ትምህርታዊ ዱስኩሮች/lectures/ እና የሚቀርቡ ትምህርቶች ማዲበር፤
የተጠቀሱትን ቁሶች ወዯ ላልች ቋንቋዎች መተርጎም፤
 ተገቢ የሆኑ ዓሇም-አቀፍ ማነቃቂያ ዘመቻዎች ሊይ መሳተፍ ወዘተ፤

11
6.3. የሳይበር ዯህንነት አቅም ግንባታ
6.3.1. መግቢያ

በሀገራችን ከሳይበር ዯህንነት ጋር በተያያዘ በቂ የሆነ የሰሇጠነ የሰው ኃይሌ እና ጠንካራ


የሳይበር ዯህንነት የአሰራር ስርዓቶችና ተቋማዊ መዋቅሮች ባሇመኖራቸው ምክንያት
የሳይበር ዯህንነት አቅም በዝቅተኛ ዯረጃ ሊይ እንዱሆን አስተዋጽኦ አዴርጓሌ። በመሆኑም
ጠንካራ የሆነ የሳይበር ዯህንነት አቅም መገንባት መቻሌ ሇአንዴ ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣
ፖሇቲካዊ እና ማህበራዊ ዕዴገት እና ሇውጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያሇው ስሇሆነ መንግስት
በህብረተሰቡ ዘንዴ ጠንካራ የሳይበር ዯህንነት ባህሌ ሇመገንባት፤ የትምህርት እና ስሌጠና
ፕሮግራሞች ሇማስፋፋት፤ ተቋማዊ/ መዋቅራዊ አቅሞች እና የአሰራር ስርዓቶች ሇመገንባት
በሃገር ዯረጃ የማይበገር እና ተጣጣፊ የሆነ የሳይበር ዯህንነት አቅም መገንባት ተገቢ ነው፡፡

6.3.2. ግቦች
1. የሳይበር ዯህንነት ስጋት፣ ተጋሊጭነት እና ጥቃት ሇመሇየት፣ ሇመዲሰስ እና ምሊሽ
ሇመስጠት የሚያስችለ ተቋማዊ መዋቅሮችንና አቅሞችን መገንባት፤
2. የመንግስት፣ የግሌ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሳይበር ዯህንነት አቅማቸውን
ማጠናከር፤
3. በሀገር ዯረጃ ብቃት ያሊቸው የሳይበር ዯህንነት ባሇሙያዎችን መፍጠር፤

6.3.3. አዴማስ
ይህ የትኩረት አቅጣጫ አዴማስ የሚያተኩረው አስፈሊጊ እርምጃዎችን በመውሰዴ የሃገሪቱን
ሁሇንተናዊ የሳይበር ዯህንነት አቅም በመገንባት ሊይ ነው፡፡

6.3.4. መስፈርት

ይህ ትኩረት አቅጣጫ ግቦቹን እንዱያሳካ የሚከተለት መዯረግ አሇባቸው፡-


1) በሃገሪቱ ከሳይበር ዯህንነት ጋር የተያያዙ ስሌጠናዎችና የትምህርት ፕሮግራሞች
ማጠናከር፤
2) ሇክስተቶች ጠንካራ የሆነ መሌስ የሚሰጥ አቅም መዘርጋት፤
3) ስትራቴጂዎችን ሇማሌማት፣ ሇመፈጸምና ሇመገምገም ብሄራዊ የስጋት ዲሰሳ
አካሄዴን መከተሌ፤
4) ስትራቴጂዎቹ እንዱሳኩ ግሌጽ የሆነ የሳይበር አመራርና አስተዲዯር መዋቅር
መዘርጋት፤

12
5) ከጥቃት ቶል ማገገም/resilience/ የሚያስችሌ የሳይበር ዯህንነት ሌምምድችን
ማጎሌበትና ማዯራጀት፤
6) ተቋማት ሉከተሎቸው የሚገቡ ዝቅተኛ የዯህንነት መስፈርቶችን/baseline
security requirements/ ማሌማት፤

6.3.5. ቁጥጥር
ይህ የትኩረት አቅጣጫ ዓሊማዎቹን አሳክቷሌ የሚባሇው የሃገሪቱን የሳይበር ዯህንነት አቅም
ሇማሳዯግ የሚረደ የትምህርት፣ የስሌጠና፣ የሌምምዴ፣ የምርምርና ሌማት ተግባራን በማከናወን
በዘርፉ ጠንካራ አቅም ሲገነባ ነው፡፡

6.3.6. የትግበራ መምሪያ

6.3.6.1. ስሌጠናዎችን እና ትምህርታዊ ፕሮግራሞችን ማጠናከር


 ብሄራዊ የመረጃ ዯህንነት ስሌጠና እና ትምህርታዊ ፕሮግራሞችን መጀመር፤
 በሁለም የኢንደስትሪ ዘርፎች ሊለ ቁሌፍ የስራ ቦታዎች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች
ክህልት ያሊቸው እንዱሆኑ የዯህንነት እውቅና/accreditation/ እና የምስክር
ወረቀት/certification/ መስጠት፤
 የመረጃ ዯህንነት ኃሊፊነት ሇመውሰዴ የሚረደ ሚናዎች እና ተገቢ የሆኑ
የትምህርት ዲራዎችን ዝርዝር ማዘጋጀት፤
 በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ሊለ በኮምፒውተር ሳይንስም ሆነ በላልች
የትምህርት መስኮች ውስጥ የሳይበር ዯህንነት ትምህርት ካሪኩሇም መንዯፍና
መተግበር፤

6.3.6.2. ሇክስተቶች መሌስ መስጠት የሚያስችሌ አቅም መፍጠር


ብሔራዊ የሳይበር ዴንገተኛ ዝግጁነትና ምሊሽ ሰጪ ቡዴኖች /CERTs/ የክስተት አስተዲዯር
በብሄራዊ ዯረጃ ከተገቢ ባሇዴርሻ አካሊት ጋር በመቀናጀት ቁሌፍ ሚና ሉጫወቱ ይችሊለ፡፡
እንዱሁም በላልች ሃገራት ከሚገኙ መሰሌ ተቋማት ጋር የማቀናጀቱን ኃሊፊነት ይሸከማለ፡
፡ በተጨማሪ ተግባራቶቻቸው በተፈሇገው መሌክ እንዱሳካ የሳይበር ዴንገተኛ ዝግጁነትና
ምሊሽ ሰጪ ቡዴኖች/CERTs/ በሚከተለት ምዴቦች ሊይ በቂ የሆኑ አቅሞች እንዱኖራቸው
ስሌጣን መስጠቱ አስፈሊጊ ነው፡-
 ሇቡዴኖቹ(/CERTs/ )ዴርሻና ኃሊፊነትን መስጠት፡- በሚመሇከተው የመንግስት አካሌ
ሇቡዴኑ መሪዎችና ባሇሙያዎች ሚናዎችና ኃሊፊነቶች በግሌጽ ሇይቶ መስጠት፤

13
 የአገሌግልት ድሴ/Service portfolio/፡- ይህ የሚመሇከተው አንዴ ቡዴን ሇመንግስት
የሚሰጣቸውን አገሌግልቶች ወይም ሇራሱ ውስጣዊ ስራ የሚጠቀማቸውን
አገሌግልቶች የሚያካትት ነው፤
 ኦፕሬሽናሌ አቅሞች/Operational capabilities/፡- ይህ ቡዴኑ ሉያሟሊቸው የሚገቡ
ቴክኒካዊና ኦፕሬሽናሌ መስፈርቶችን የሚመሇከቱ ናቸው፤
 የትብብር አቅሞች/Cooperation capabilities/፡- ከሊይ ባለት ምዴቦች ያሌተነኩትን
መረጃ መጋራትን የሚመሇከቱ ጉዲዮችን የሚያቅፉ መስፈርቶች ናቸው፡፡ ሇምሳላ፡-
ፖሉሲ አውጪዎች፣ ወታዯራዊ አካሊት፣ ህግ አውጪዎች፣ የቁሌፍ ኢንፎርሜሽን
መሰረተ-ሌማት አንቀሳቃሽ/operators፣ ህግ አስፈጻሚ ባሇስሌጣናቶችን፤

6.3.6.2.1. የትግበራ መምሪያ

 የሳይበር ዴንገተኛ ዝግጁነትና ምሊሽ ሰጪ ቡዴኖች የውክሌና ስራቸውን


መስራታቸውንና የብሄራዊም ሆነ ዓሇም-አቀፍ የዲታ ጥበቃ ህግጋት መከተሊቸውን
ማረጋገጥ፤
 የሳይበር ዴንገተኛ ዝግጁነትና ምሊሽ ሰጪ ቡዴኖች ከብሄራዊና ዓሇም-አቀፋዊ
ህግጋት ጋር በተጣጣመ መሌኩ መረጃን መያዝ የሚችለባቸውን ስሌቶች እና ምርጥ
ተሞክሮዎችን በግሌጽ ማስቀመጥ፤
 የመረጃ ጥበቃ ህግጋትን ባሇመፈጸም ምክንያት የሚመጣ የመረጃ ጥሰት ወይም
አግባብነት የላሇው የግሌ መረጃ አጠቃቀም ቁጥጥር ማዴረግ የሚቻሌባቸውን
ስሌቶች መቀየስ፤
 የሳይበር ዴንገተኛ ዝግጁነትና ምሊሽ ሰጪ ቡዴኖች ምርጥ ተሞክሮዎችን እና የጋራ
የሆኑ መረጃ መቆጣጠሪያ ፕሮቶኮልችን በሚስተዋውቁበት ዓሇም-አቀፍዊና ክሌሊዊ
ስብሰባዎች ሊይ የሚሰሩ ቡዴኖችን ማዘጋጀት፤
 ባሇዴርሻ አካሊትን ሇማካተት ሲባሌ መረጃ ጥበቃ ሊይ የሚሰሩ ቡዴኖች/thematic
working groups/ (ሇምሳላ፡- የባንክ ኢንደስትሪ) መመስረት እና አጠቃሊይ
የሆነውን የመረጃ ሌውውጥን/information exchange/ ማሻሻሌ፤
 የግሌ መረጃ በመያዝ ዙሪያ ሉኖሩ የሚችለ ጥርጣሬዎችን ሇማስወገዴ በመረጃ
ቴክኖልጂ ሌዩ ስሌጠና የወሰዯ የህግ ባሇሙያ መቅጠር ወይም እንዱሳተፍ ማዴረግ፤

14
 ብሄራዊ የተጋሊጭነት መረጃ-ቋት ፈጥሮ ቁሌፍ ስራዎች ሊይ ሉኖር የሚችሇውን
ተጽእኖ ወይም ወሳኝ የሆኑ ኦፕሬሽኖች የመረበሽ አቅም ወጥነት ባሇው ሁኔታ
መዲሰስ፤
 ሇቁሌፍ መረጃ መሰረተ-ሌማቶች ቀዴሞ ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ ስርዓት የሚገነባ
ብሄራዊ ፕሮጀክት ማነሳሳት(መቅረጽ)፤
 ክፍተትን የመዴፈን/patch/ እና የተጋሊጭነት አስተዲዯር (ቅዴመ ማስጠንቀቂያ) ስራ
የመጀመር መስፈርቶች/deployment requirements ወዘተ) ሊይ የሚሰራ
ተጋሊጭነት ይፋ ማዴረጊያ ማዕቀፍ/disclosure framework/ማበሌጸግ፤
 ቁሌፍ የሆኑ ትግበራዎች የሚመሇከታቸው አካሊት ክፍተቶቻቸው ከተሸፈነ በኋሊ
የስርዓቶች ከፍተኛ መናወጥ ሇማስወገዴ የሚያስችለ የመሞከሪያ ከባቢዎች
ማዘጋጀት፤

6.3.6.3. ያለትን ፖሉሲዎች፣ ሬጉላሽኖችና አቅሞች ክምችት መመዝገብ

6.3.6.3.1. የትግበራ መምሪያ

 በሳይበር ዯህንነት ዙሪያ ሇዓመታት የሇሙትን የፖሉሲዎች ክምችት ማዯራጀት


(የኤላክትሮኒክ ኮሙኒኬሽኖች፣ የመረጃ ጥበቃና ዯህንነት… ወዘተ)፤
 በተሇያዩ ዘርፎች ሊይ የሳይበር ዯህንነትን ሇማሻሻሌ እሰከ አሁን ዴረስ የተተገበሩ
ሁለንም ሬጉሊቶሪ እርምጃዎችና ያመጡትን ተጽእኖ መሇየት፤
 ኦፕሬሽናሌ የሳይበር ዯህንነት ተግዲሮቶችን ሇመፍታት የሇሙ አቅሞች ክምችት መሇየት
(ሇምሳላ፡- ብሄራዊ ወይም መንግስታዊ CERTs)፤
 ያለትን ሬጉላቶሪ ዘዳዎች መሇየት (የመንግስትና የግሌ ትብብሮች) ከዚያም ግቦቻቸውን
በምን ያህሌ መጠን እንዲሳኩ መዲሰስ፤
 የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲዎች፣ ሬጉላሽኖችና ኦፕሬሽኖችን ሇማስተዲዯር ኃሊፊነት
የተሰጣቸው የመንግስት ተቋማት (ማሇትም ሃይሌን ሬጉላት የሚያዯርጉ፣
የኤላክትሮኒክ ኮሙኒኬሽኖችን ሬጉላት የሚያዯርጉ፣ የመረጃ ጥበቃ ባሇስሌጣናት፣
ብሄራዊ የሳይበር ወንጀሌ ማዕከሊት…ወዘተ) ሚናዎችና ኃሊፊነቶች መተንተን፤ ከዚያም
መዯራረቦችን እና ክፍተቶችን መሇየት፤
 አሁን ሊይ ያለ ፖሉሲዎች፣ ሬጉላቶሪና ኦፕሬሽናሌ ከባቢዎች የፖሉሲና ስትራቴጂውን
ዓሊማዎችና አዴማስ በምን ያህሌ መጠን እንዲሟለ መዲሰስ እና መሻሻሌ የሚገባቸውን
መሇየት፤

15
6.3.6.4. ግሌጽ የሆነ የአመራር ስርዓት/መዋቅር/ ማሌማት

ብሄራዊ የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ ሉሳካ የሚችሇው ግሌጽ የሆነ የአመራር
ማዕቀፍ ሲኖር ነው፡፡ የአመራር ማዕቀፍ ተገቢ የሆኑ ባሇዴርሻ አካሊትን ሚናዎች፣
ኃሊፊነቶችንና ተጠያቂነትን ሉያብራራ የሚችሌ ነው፡፡ እንዱሁም በፖሉሲና ስትራቴጂው
የሕይወት ኡዯት ውስጥ ሇሚካሄደ የተሇያዩ ተግባራት ሇውይይትና ቅንጅት የሚሆን
አቅጣጫ ይሰጣሌ፡፡

6.3.6.4.1. የትግበራ መምሪያ

 ፖሉሲና ስትራጂውን የማስተዲዯርና የመገምገም ኃሊፊነት የሚወስዯው ማን እንዯሆነ


መወሰን፤
 የፖሉሲና ስትራቴጂው የሳይበር ዯህንነት ጉዲዮችን የሚያማክረውን መስተዲዴራዊ
መዋቅር አማካሪ አካሌ ማቋቋም፤ በዚህ መዋቅር ውስጥ የሚሳተፉትን መንግስታዊና
የግሌ አካሊትን መወሰን፤ሰፊ የሆኑ ባሇዴርሻዎችን ሇመካተት መሞከር፤
 የሳይበር ዯህንነት ጉዲዮች አማካሪ አካሌ ተግባራት በግሌጽ ማስቀመጥ፤
 የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲ፣ ስትራቴጂና ሬጉላሽን እንዱሇሙ የሚያነሳሱ እና/ወይም
የሚያሇሙ አካሊት የተሰጣቸውን የውክሌና ተግባራት መግሇጽ ወይም ማረጋገጥ፤
እነዚህ አካሊት ከአማካሪ አካለ ጋር እንዳት እንዯሚገናኙ እና/ወይም ሇአማካሪ አካለ
እንዳት አስተዋጽኦ እንዯሚያዯርጉ ማብራራት፤
 ስጋቶችንና ተጋሊጭነቶችን መቀነስ፣ ሇሳይበር ጥቃት መሌስ የመስጠት፣ የአዯጋ
አስተዲዯርንና ላልችን የማጠናክር ኃሊፊነት የወሰደ አካሊት ተግባራት መግሇጽ፤እነዚህ
አካሊት ከአማካሪ አካለ ጋር እንዳት እንዯሚገናኙ እና/ወይም ሇአማካሪ አካለ እንዳት
አስተዋጽኦ እንዯሚያዯርጉ ማብራራት፤ቁሌፍ የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ሌማቶችን ጥበቃ
ማዴረግ፤
 ያለትን የብሄራዊ የሳይበር ዴንገተኛ ክስተቶች ምሊሽ ሰጪ ቡዴን/CERT/ በዯንብ
ማጥናት እና መግሇጽ፤ እንቅስቃሴዎቻቸውን መቆጣጠር፣ ታማኝነት ባሇው መሌኩ
መረጃ ማጋራት፣ በተከሰቱ ስጋቶች እና ላልች ቁሌፍ የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ሌማት
ጥበቃ እንቅስቃሴዎች ሊይ መረጃ መስጠት ተግባራትን ማከናወን፤
 የሳይበር ዴንገተኛ ክስተቶች ምሊሽ ሰጪ ቡዴን/CERT/ በብሄራዊና ዓሇም-አቀፋዊ ዯረጃ
ከላልች ተመሳሳይ ዴርጅቶች ጋር የማቀናጀትና ኢንፎርሜሽን በማጋራት ቁሌፍ ሚና
እንዱጫወት ማዴረግ፤

16
6.3.6.5. የሳይበር ዯህንነት ሌምምድችን ማዘጋጀት

በሳይበር ዯህንነት ሌምምድች ብቃት ያሊቸው ባሇስሌጣናት የአዯጋ ጊዜ እቅድች


እንዱኖሯቸው፣ ዴክመቶች ሊይ ኢሊማ እንዱያዯርጉ፣ በተሇያዩ ዘርፎች መካከሌ ትብብርን
መፍጠር እንዱችለ፣ ቀጣይነት ባሇው እቅዴ ሊይ መሻሻሌን ሇማምጣት እና ከዴንገተኛ
ክስተት ቶል ማገገምን ሇማሳዯግ ሲባሌ የትብብር ባህሌን ሇማመንጨት ያስችሊቸዋሌ፡፡
የሳይበር ዯህንነት ሌምምድች ማህበረሰቡ ሇተፈጥሮ አዯጋዎች፣ ሇቴክኖልጂ መሰረተ
ሌማቶች ውዴመት፣ ሇሳይበር ጥቃቶችና ሇአስቸኳይ ጊዜ ምን ያህሌ ዝግጁ እንዯሆነ
ሇማወቅ ጠቃሚ መሳሪያዎች ናቸው፡፡

6.3.6.5.1. የትግበራ መምሪያ

 ተከታታይ የሆኑ የሳይበር ሌምምድች ተጽእኖ መዲሰስ ከዚያም የሳይበር ዯህንነት


ፖሉሲና ስትራቴጂውን ፍሊጎት ይበሌጥ ሇማሳካት በሚያስችሌ ሁኔታ ራዕይን ማሻሻሌ፤
 ሉሳኩ የሚችለ ተጨባጭ ዓሊማዎች ያለት የሳይበር ዯህንነት ሌምምድች የመካከሇኛ
ወቅት ተሌዕኮ ማሌማት፤
 በሂዯቱ ውስጥ መካተት ያሇባቸውን ተገቢ የመንግስትና የግሌ ዘርፍ ባሇዴርሻ አካሊት
መሇየት፤
 ሇእያንዲንደ የሳይበር ዯህንነት ሌምምዴ የሚከተለት መዯረግ አሇባቸው፡-
o የሌምምደን አስተዲዲሪ(ዎች) ሇይቶ መግሇጽ፤
o ሌምምደን የሚያዘጋጅና ወሳኝ የሆኑ ጉዲዮች ሊይ የሚወስን እቅዴ አውጪ ቡዴን
ማዋቀር፤
o ሉዯረስባቸው የሚፈሇጉ ተጨባጭ ዓሊማዎችን መግሇጽ፤ሁሌጊዜ ከሚሞከሩት
የዴንገተኛ እቅድች ጋር ማዛመዴ፤
o በሌምምደ አጭር የዴርጊት ገሇጻ ሊይ መስማማት፤ አጭር የዴርጊት ገሇጻው
ሉተገበር የሚችሌ እና በእውነተኛ ክስተቶች ሊይ የተመሰረተ መሆኑን ማረጋገጥ፤
o መከተሌ የሚገባን የግምገማ እና የፍተሻ አካሄዴ ሊይ መስማማት፤
o ግሌጽ የሆነ የሚዱያና የህዝብ ግንኙነት ጉዲዮች ስትራቴጂን ሇይቶ መግሇጽ፤
o ከዓሇም-አቀፍ ትብብሮችና የታዛቢዎች ፕሮግራም ጋር መስማማት፤
o የሌምምደን ተዋንያኖች መሇየትና ማሳተፍ፤
o ተዋናዮቹን ከሌምምደ ገጽታዎች ጋር የሚያሊምዴ የስሌጠና ፕሮግራም መንዯፍ፤

17
o ሌምምደ በተገቢ ሁኔታ መዘጋጀቱን ሇማረጋገጥ የሙከራ ሂዯት ማዘጋጀትና
ማስፈጸም፤
o ሌምምደን ማስኬዴ፤ እዴገቱን መገምገምና መቆጣጠር፤
o ሌምምደ ካበቃ በኋሊ ማጠቃሇያ ፕሮግራም በማዘጋጀት ዋና ዋናዎቹን
መዯምዯሚያዎችና የተገኙ ትምህርቶችን መሰብሰብና አንዴ ሊይ ማጠናቀር፤
o ስሇስኬቶች፣ ቁሌፍ ግኝቶች እና ስሇተገኙ ትምህርቶች ሪፖርት በማዴረግ በአጭር
ወይም ማጠቃሇያ ሪፖርት ሉታተም የሚችሌ ዝርዝር የሆነ ሪፖርት ማዘጋጀት፤
(በሌምምደ ተዋናዮች መካከሌ ምስጢራዊ ሆኖ ሉቆይ ይገባሌ)፤
o የተገኙትን ትምህርቶች እና ቁሌፍ ምክረ-ሀሳቦች መከታተሌ ከዚያም ኢሊማ
የተዯረጉት ባሇዴርሻ አካሊት እንዯሚተገብሯቸውን ማረጋገጥ፤

6.3.6.6. መነሻ የሚሆን የዯህንነት መስፈርቶችን መፍጠር

ሁለም ወሳኝ መንግስታዊና ግሊዊ ዴርጅቶች የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ሌማቶቻቸው የአዯጋ


ዲሰሳ ተዯርጎ ካሇቀ በኋሊ የተገኙ ስጋቶች፣ተጋሊጭነቶች እና አዯጋዎች ሇመቀነስና
ሇመከሊከሌ አስፈሊጊ እርምጃዎችን መውሰዴ አሇባቸው፡፡ መነሻ የሚሆኑ የሳይበር ዯህንነት
መስፈርቶች ሁለም ተቋማት የሚተገብሯቸው ዝቀተኛ የዯህንነት ዯረጃዎች ናቸው፡፡

6.3.6.6.1. የትግበራ መምሪያ

 እሰከ ዛሬ ሲወሰደ የነበሩትን የሳይበር ዯህንነት መሇኪያዎች በሙለ መከሇስና


ማሻሻሌ፡-
o አሁን ሊይ ባለት የቁጥጥር ሰነድች ውስጥ የተገሇጹ የዯህንነት መሇኪያዎችን
መሇየት፤
o የመረጃ ዯህንነት ስጋቶችን በመሇየት ስጋቶች ካለት ከመሇኪያዎች ጋር
ማቆራኘት፤
o ካለት ቴክኒካሌ ስታንዲርድች (ሇምሳላ፡- ISO27001, ISO27002,
ISO27004, COBIT, ITIL,ወዘተ) በመጠቀም ክፍተቶችን መሇየትና
የክፍተቶቹን መቀነሻ እርምጃዎችን ማምጣት፤ ክፍተቶች ከተገኙ
የባሇሙያዎች አስተያየትና ተገቢ ስታንዲርድችን ግምት ውስጥ በማስገባት
የመሇኪያ ዝርዝሮቹን ማሻሻሌ፤
 የዯህንነቱን እዴገት የሚያሳዩ በራሳቸው ዲሰሳ ማዴረግ የሚችለ መሳሪያዎችን
መፍጠርና ባሇዴርሻ አካሊት እንዱጠቀሟቸው ማበረታታት፤
18
 ዝቅተኛ የመሇኪያዎች ዝርዝር መሰረት በማዴረግ የመረጃ ዯህንነት ምርመራዎችን
ሇላልች መስጠት፤.
 ትሌቅ ተጽእኖ ስሊሊቸው ክስተቶች የቀረበውን ሪፖርት በመንተራስ መነሻ
መስፈርቶችን ማሻሻሌ፤

6.4. የሳይበር ዯህንነት ምርምርና ሌማት

6.4.1. መግቢያ

የሳይበር መሰረተ ሌማቶችንና ቴክኖልጂዎችን በማበሌጸግ፣ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ


የሚያዯርጉ የቴክኖልጂ ሽግግሮች እና አዲዱስ ፈጠራዎች በማስፋፋት፤ እንዱሁም በተሇያዩ
ዯረጃዎች ሃገር በቀሌ እና አሇም አቀፍ ምርምር እና ሌማት ተግባራት ማከናወን ተገቢ
ነው፡፡ በመሆኑም በዘርፉ የራስ አቅም እንዱኖር፣ የሳይበር ቴክኖልጂ እና ፈጠራ ስራዎች
በተዯራጀ ጥናት እና ምርምር በመዯገፍ የሳይበር ዯህንነት ኢንደስትሪ ሇመገንባት ይሰራሌ፡፡
ይህንን የትኩረት አቅጣጫ ሇማሳካት የሚከተለት ግቦች እና የትግበራ መምሪያ በመሇየት
በሌዩ ትኩረት መንግስት ይንቀሳቀሳሌ።

6.4.2. ግቦች
1. ቁሌፍ የመረጃ መሰረተ ሌማቶችን ዯህንነት ሇማረጋገጥ የሚያስችለ ምርቶችና
አገሌግልቶች በምርምርና ሌማት ሊይ የተመሰረቱ ማዴረግ፤
2. የሳይበር ዯህንነት ተጋሊጭነቶች፣ ስጋቶች እና ጥቃቶች መንስዔዎቻቸውን በጥናትና
ምርምር መሇየት፤ መፍትሄዎች ማቅረብ፤
3. የሳይበር ዯህንነት ሇማረጋገጥ ሃገር በቀሌ ዕውቀት እና ፈጠራዎችን መሰረት ያዯረገ
የምርምር እና ሌማት አቅም መገንባት፤
4. በዓሇም አቀፍ ዯረጃ ተወዲዲሪ የሆነ እና የተቀናጀ ሃገራዊ የሳይበር ዯህንነት ምርምርና
ሌማት ባህሌ መገንባት፤

6.4.3. አዴማስ
የዚህ የትኩረት አቅጣጫ አዴማስ የሳይበር ዯህንነትን ሇማረጋገጥ ሃገሪቱ ማከናወን
የሚገቧት የምርምርና ሌማት ተግባራትን የሚያጠቃሌሌ ነው፡፡

6.4.4. መስፈርት
የሳይበር ዯህንነት አጀንዲ ማንሳት፣ በተነሳው አጀንዲ ሊይ ምርምር ማዴረግ ከዚያም
የተገኘውን ውጤት እያንዲንደ ባሇዴርሻ አካሌ ወዯ ተግባር እንዱሇውጥ መስራት ነው፡፡
19
6.4.5. ቁጥጥር
ይህ የትኩረት አቅጣጫ ተሳካ የሚባሇው የሚመሇከታቸው አካሊት በሙለ የሳይበር ዯህንነት
ምርምርና ሌማት ጉዲዮችን ማንሳት ሲችለ፤ምርምሮች በመንግስታዊና በግሌ ዘርፎች
ቅንጅት ሲሰሩ፤ በምርምር የተገኙ ውጤቶች ወዯ ተግባር ተሇውጠው በዘርፉ ጠንካራ የሆነ
የሳይበር ዯህንነት አቅም ሲገነባ ነው፡፡

6.4.6. የትግበራ መምሪያ

 የመካከሇኛ ጊዜ አዴማስ ያሊቸው የሳይበር ዯህንነት ዓሊማዎችን ያማከለ የምርምርና


ሌማት አጀንዲ መፍጠር፤
 በሳይበር ኢንደስትሪዎች ሇተሰማሩ አካሊት መዴረክ መፍጠር እና በምርምርና
ሌማት እንዱታዩ ስሇሚፈሌጓቸው ርዕሶች ጥያቄ ማቅረብ፤
 ከፍተኛ ዯረጃ ያሇው የምርምር ስራ ውስጥ የግለ ዘርፍ ተሳታፊ እንዱሆን
በማበረታታት የመንግስትና የግሌ ተቋማት የምርምርና ሌማት አጋርነት መፍጠር፤
 ከዓሇም-አቀፍ የሳይበር ዯህንነት ምርምርና ሌማት ተቋማት ጋር አጋርነት ወይም
ትብብር ማዴረግ፤
 የተሇያዩ ተቋማት በሚያከናውኗቸው የምርምር መርሀ-ግብሮች መካከሌ መዯራረቦችን
ሇማስቀረት የምርምር ቅንጅት እቅዴ ማዘጋጀት፤
 የሳይበር ዯህንነት ምርምር በሁለም ቦታ እንዱገኝ ውጤታማ የሆኑ ማበረታቻዎችን
በማዘጋጀት ግሇሰቦችና ዴርጅቶች የእነዚህ ማበረታቻዎች ተጠቃሚ እንዱሆኑ
ማዴረግ፤

6.5. የዱጂታሌ ማንነትና ግሊዊ መረጃ ጥበቃ

6.5.1. መግቢያ

ዱጂታሌ ማንነት እና ግሊዊ መረጃዎች ተገቢ የሆነ ትኩረት እና ጥበቃ ካሌተዯረገሊቸው


በዜጎች ሊይ የሚዯርስ የሳይበር ጥቃት እንዱስፋፋ፤ ማንነት ተኮር ጥቃቶች እንዱበራከቱ፤
እንዱሁም ከማህበረሰቡ ባህሌና እሴት ያፈነገጡ ክስተቶች የዜጎች የግሌ ሕይወትና ሰብዓዊ
መብቶች ስጋት ውስጥ እንዱገቡ ያዯርጋሌ። ስሇሆነም መንግስት በዜጎች ሊይ ያነጣጠሩ
የስነ-ሌቦና ጥቃቶች ሇመከሊከሌ፤ የማህበረሰቡን ግንዛቤ ሇማሳዯግ፤የዱጂታሌ ማንነትና
የግሊዊ መረጃ ስጋትናተጋሊጭነት ሇመቀነስ፤እንዱሁም ዜጎች ሇግሌ መረጃ ሌውውጥ

20
የሚጠቀሟቸውን የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ሌማቶች ዯህንነት ሇመጠበቅ ይህንን የትኩረት
አቅጣጫ ይተገብራሌ፡፡

6.5.2. ግቦች
1. በዜጎች ዘንዴ ታዓማኒነት ያሇው የዱጂታሌ አገሌግልት እና ግሊዊ መረጃ ጥበቃ
እንዱኖር ማዴረግ፤
2. በታዲጊዎች ሊይ የሚዯርሱ የሳይበር ስጋቶችን፣ ተጋሊጭነቶችንና ጥቃቶችን መከሊከሌ፤
በኢትዮጵያ ማህበረሰብ እሴቶችና በመሌካም ስብዕና ታንፀው እንዱያዴጉ ሳይበር
ሉጫወት የሚገባውን ገንቢ ሚና ማሳዯግ፤
3. በሳይበር ምህዲር ሊይ የሚዯርስ ጾታዊ ጥቃት፣ ወሲባዊ ትንኮሳ፣ የሥነ-ሌቦና ተፅዕኖ
መከሊከሌ እና መቀነስ፤
4. ማንነትን መሰረት ያዯረጉ በዱጂታሌ የሚፈጸሙ የሃይማኖት ጽንፈኝነት፣ የብሄር ተኮር
ጥቃቶችንና የመሳሰለትን መግታትና መከሊከሌ፤

6.5.3. አዴማስ

ይህ የትኩረት አቅጣጫ የሳይበር ዯህንነትን ሇማረጋገጥ በሃገሪቱ መከናወን ስሇሚገባቸው


የዱጂታሌ ማንነት እና ግሊዊ መረጃዎች ተግባራት ዙሪያ የሚያተኩር ነው፡፡

6.5.4. መስፈርት
የዜጎችን የስነ-ሌቦና ጥቃቶች መከሊከሌ፤ የማህበረሰቡን ግንዛቤ ማሳዯግ፤የዱጂታሌ ማንነትና
የግሊዊ መረጃ ስጋትና ተጋሊጭነት መቀነስ፤እንዱሁም ዜጎች ሇግሌ መረጃ ሌውውጥ
የሚጠቀሟቸውን የመረጃ መሰረተ-ሌማቶች ዯህንነት መጠበቅ ነው፡፡

6.5.5. ቁጥጥር
ይህ የትኩረት አቅጣጫ ዓሊማውን አሳካ የሚባሇው በዜጎች ሊይ የሚዯርሱ ማንነትን
መሰረት ያዯረጉ የሳይበር ጥቃቶች መከሊከሌና ግሊዊ መረጃ ጥበቃ ዙሪያ የሚያጋጥሙ
የሳይበር ዯህንነት ስጋትና ተጋሊጭነት መቀነስ ሲቻሌ ነው፡፡

6.5.6. የትግበራ መምሪያ


የግሊዊ መረጃ ዯህንነት ማረጋገጥ የሚያስችለ አቅሞች፣ ተቋማዊ ማዕቀፎች ማሌማት፣
የህግ እና የቁጥጥር አሰራር ስርዓቶች በቅንጅት ተግባራዊ ማዴረግ፤

21
6.6. ቁሌፍ የመረጃ መሰረተ-ሌማት ጥበቃ

6.6.1. መግቢያ
መረጃ ውዴ ሃብት እየሆነ በመምጣቱ ቁሌፍ የመረጃ መሰረተ-ሌማቶችን እና ተቋማትን
ከሳይበር ጥቃቶች መከሊከሌ፤ የሳይበር ስጋቶችንና ተጋሊጭነቶችን መቀነስ፤ የሳይበር ጉዲት
ሲዯርስ በፍጥነት መሌሶ ማቋቋም አንገብጋቢ ጉዲይ ነው። ስሇሆነም ኢኮኖሚያዊ፣
ማህበራዊ እና ፖሇቲካዊ ጉዲዮችን በአግባቡ ሇመምራትና ሇመተግበር፣ ከውዴመት
ሇመከሊከሌ፤ እንዱሁም የሳይበር ምህዲሩን ዯህንነት ሇማረጋገጥ እና ተዓማኒነቱን ሇማሳዯግ
ቁሌፍ የመረጃ መሰረተ-ሌማቶች ጥበቃ ማዴረግ አስፈሊጊ በመሆኑ ሇዘርፉ ትኩረት መስጠት
ተገቢ ነው፡፡ይህንን የትኩረት አቅጣጫ ሇማሳካት የሚከተለት ግቦች እና የትግበራ መምሪያ
በመሇየት መተግበር አስፈሊጊ ነው፡፡

6.6.2. ግቦች
1. ቁሌፍ መሰረተ-ሌማቶች እና ተቋማት ሊይ ሉዯርሱ የሚችለ ስጋቶች፣ ተጋሊጭነቶች፣
ጥቃቶችና ውዴመቶችን የመሇየት፣ የመከሊከሌ እና ምሊሽ የመስጠት አቅም ማጎሌበት፤
2. ከውጭ የሚገቡ እና በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ቁሌፍ የመረጃ መሰረተ-ሌማት ምርቶችና
አገሌግልቶች ዯህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ፤
3. ሇቁሌፍ የመረጃ መሰረተ-ሌማቶች ሌዩ ጥበቃ ሇማዴረግ የመንግስት እና የግሌ ዘርፍ
ትብብር እና ቅንጅት መፍጠር፤

6.6.3. አዴማስ

ይህ የትኩረት አቅጣጫ በሃገሪቱ ውስጥ ያለትን ቁሌፍ የመረጃ መሰረተ-ሌማቶችን


መሇየትና ሇሳይበር ስጋቶችና ጥቃቶች ተጋሊጭ እንዲይሆኑና አዯጋ እንዲይዯርስባቸው
ተገቢውን መከሊከሌና ጥበቃ ማዴረግ ሊይ የሚያተኩር ነው፡፡

6.6.4. መስፈርት

ቁሌፍ የመረጃ መሰረተ-ሌማቶችን በመሇየት ተገቢ የሆኑ የሳይበር ዯህንነት ዘዳዎችን


በመጠቀም ስጋቶቻቸውን መቀነስ እና አዯጋዎቻቸውን መከሊከሌ ነው፡፡

6.6.5. ቁጥጥር

ይህ የትኩረት አቅጣጫ ዓሊማውን አሳካ የሚባሇው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ቁሌፍ የመረጃ


መሰረተ-ሌማቶች ተሇይተው አስፈሊጊ የሆነ የሳይበር ዯህንነት ጥበቃ ሲዯረግሊቸው ነው፡፡

22
6.6.6. የትግበራ መምሪያ
1. ቁሌፍ የሆኑ መሰረተ ሌማት ተቋማትን መሇየት፣ የማይበገር የመከሊከሌ ዓቅም
መፍጠር፣ የቁሌፍ መሰረተ ሌማቶች ህጋዊ፣ ተቋማዊና ቴክኒካዊ ቀጣይነት ያሊቸው
እርምጃዎች ሇመውሰዴ የሚያስችለ ማዕቀፎች እና አገሌግልቶች መፍጠርና
ማበሌጸግ፤
2. ቁሌፍ የመሰረተ ሌማት ተቋማት ሚናና ሃሊፊነቶች የሚመሇከታቸው የመንግስት
እና የግሌ ተቋማት፣ እንዱሁም የግሇሰብ እና የጋራ ሃሊፊነቶች እና ግዳታዎች
ሁለን አቀፍ በሆነ ሁኔታ በህግ ወይም በስታንዯርዴ መሌክ መስፈርቶች በማዘጋጀት
እንዱተገበር ማዴረግ፤
3. ቁሌፍ የመሰረተ ሌማቶች ጥበቃ ሇማዴረግ የሚያስችለ የመረጃ ሌውውጥ ስርዓቶች
እና ማዕቀፎች ማዘጋጀት/ማበሌጸግ፤

6.6.6.1. ብሄራዊ የሳይበር ዯህንነት አማራጭ እቅድችን ማሌማት


ብሄራዊ የሳይበር ዯህንነት አማራጭ እቅድች የሚባለት ቁሌፍ የመረጃ መሰረተ-ሌማቶችን
የሚያካትቱ ዋና ክስተቶች ሲከሰቱ መሌስ ሇመስጠት፤ እንዱሁም ክስተቶቹን ተከታትል
አገሌግልቶች እንዱያገግሙ ማዴረጊያ ጊዜያዊ መዋቅሮችና እርምጃዎች ናቸው፡፡ ብሄራዊ
የሳይበር ዯህንነት አማራጭ እቅዴ የጠቅሊሊው ብሄራዊ አማራጭ እቅዴ አካሌ መሆን
አሇበት፡፡ በተጨማሪም የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ ወሳኝ አካሌም ነው፡፡

6.6.6.1.1. የትግበራ መምሪያ

 ስጋቶችንና ተጋሊጭነቶችን መሇየትንና ሉያስከትለ የሚችለትን ተጽእኖ እንዱሁም


ቀዯምትነቶችን የሚሸፍን መነሻ የስጋት ዲሰሳ ማዴረግ፤
 ተገቢ ባሇዴርሻ አካሊትን በሂዯቱ ውስጥ ማሳተፍ፤ ይህም ሚናዎቻቸውና
ኃሊፊነቶቻቸው ግሌጽና ያሌተዯራረቡ መሆናቸውን ማረጋገጥ፤
 የተሇያዩ አስጊ ሁኔታዎች በሚገጥሙበት ጊዜ ሁለም ተገቢ ባሇዴርሻ አካሊት
የሚጠቀሟቸውን የስታንዲርዴ ኦፕሬትንግ አካሄድች /standard operating
procedures/ ማሌማት፤
 አስፈሊጊ የትብብርና መሌስ የመስጫ ማዕቀፍ ማሌማት፤ (ሇምሳላ፡- አቅም
ግንባታዎች፣የስታንዲርዴ ኦፕሬትንግ አካሄድች/standard operating procedures/፣
መረጃን ያሇፈቃዴ ይፋ ያሇማዴረግ ስምምነት ወዘተ…)

23
 በአስቸኳይ ሁኔታዎች ጊዜ ሚዱያን ሇመቆጣጠር የምንጠቀማቸውን የስታንዲርዴ
ኦፕሬትንግ አካሄድች መግሇጽ፤
 የስታንዲርዴ ኦፕሬትንግ አካሄድች፣ አቅሞችንና ዘዳዎችን መሞከር፣ መገምገም እና
ማስተካከሌ፤
 አቅሞችን ሇመስጠት ኃሊፊነቱን የሚወስዴ ሰራተኛ ማሰሌጠን፤
 አሁን ያለትን ስታንዲርዴ የመስሪያ ቅዯም-ተከተልችን፣ ሚናዎችን፣ ኃሊፊነቶችን
እና የኮሙኒኬሽን ዘዳዎች የሚገመግሙ ሌምምድችን መዘጋጀትና መፈጸም፤.
 ከሳይበር ዯህንነት ሌምምድች የተወሰደ ትምህርቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት
አማራጭ እቅደን መከሇስ፤

6.6.6.2. ብሄራዊ የስጋት ዲሰሳ አካሄዴን መከተሌ

 ከተቻሇ መጠቀም በሚገባን የስጋት ዲሰሳ ዘዳ ሊይ መስማማት ካሌተቻሇ ዯግሞ


ያለትን ሇብሄራዊ ስጋቶች በሚስማማ መሌኩ ማዘጋጀት፤
 ስጋትን ሇመሇየትና ሇመዲሰስ “ሁለም አዯጋ ነው/all-hazard/” የሚሇውን አካሄዴ
መከተሌ፤
 ቁሌፍ ዘርፎችን መሇየትና ሇዘርፎቹ የሚስማማ የመከሊከያ እቅዴ ማዘጋጀት፡፡ ይህም
የሚከተለትን ተግባራት ሉይዝ ይችሊሌ፡-
o ህብረተሰቡና ኢኮኖሚው በሚገባ መስራት የሚያስችለትን ቁሌፍ
ሀብቶችን/assets/ እና አገሌግልቶችን መሇየት፤
o ቁሌፍ ሀብቶች ሊይ ተጽዕኖ የሚፈጥሩትን ሁለንም ስጋቶችን መዲሰስ፤
በሚፈጥሩት ተጽእኖ መሰረት በቅዯም-ተከተሌ ማስቀመጥ እና እውን
የመሆን እዴሊቸውን ማስሊት፤
o ትክክሇኛ የሆኑትን የግለ ዘርፍ ባሇዴርሻ አካሊት በማሳተፍ የተዯረጉ የስጋት
ዲሰሳዎች ማጋራት እና ከግኝቶች ጋር ዝምዴና መፍጠር፤
o የትኞቹን ስጋቶች እንዲለ መውሰዴ እንዯሚቻሌ፣ የትኞቹን ስጋቶች እንዳት
መቀነስ እንዯሚገባ፣ እንዱሁም ምንም ሉዯረጉ የማይችለ ስጋቶችን
በተመሇከተ ውሳኔ መወሰንና ሇምን እነዚህ ውሳኔዎች እንዯተወሰደ ግሌጽ
ማዴረግ፤
o የተሇዩትን ስጋቶች የሚይዝ ብሄራዊ የስጋት መዝገብ ማዘጋጀት፤
o ቀጣይነት ባሇው መሌኩ ስጋቶችንና ተጋሊጭነቶቸን ሇመቆጣጠር እና ብሄራዊ
የስጋቱን ስፋት ሇማሻሻሌ ተዯጋጋሚ የሆነን ሂዯት መግሇጽ፤
24
6.7. ሃገር-አቀፍ እና ዓሇም-አቀፍ ትብብር

6.7.1. መግቢያ

የሳይበር ዯህንነት ጥቃት እጅግ ውስብስብ፣ ኢ-ተገማች፣ ተሇዋዋጭና ዴንበር የሇሽ ከመሆኑ
የተነሳ በመንግስትና በተወሰኑ ተቋማት ብቻ መፍትሄ የሚያገኝ ጉዲይ አይዯሇም፡፡ ስሇዚህ
የሳይበር ዯህንነትን ሇማስጠበቅ ሃገራዊ ቅንጅት እና አጋርነት መመስረት፤ በሳይበር ዯህንነት
ሊይ የተጋረጡ ስጋቶችን መከሊከሌ የሁለም የመንግስትና የግሌ ዘርፍ (ባሇዴርሻ አካሊት)
የጋራ ኃሊፊነት ነው፡፡ እንዱሁም የሳይበር ዯህንነት ዓሇም አቀፍ ይዘት ያሇው በመሆኑ፤
ከምህዲሩ ተሇዋዋጭነትና ዴንበር የሇሽነት ባህሪ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ስጋቶች፣
ተጋሊጭነቶችና ጥቃቶች ሇመከሊከሌ ዓሇም አቀፍ ፖሉሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣
ስታንዯርድች፣ ሌምድች እና አመሇካከቶች የተሇያዩ በመሆናቸው የሳይበር ዯህንነትን
ከማረጋገጥ አንጻር ከፍተኛ ተጽዕኖ እያዯረገ ይገኛሌ፡፡ በመሆኑም ይህንን የትኩረት አቅጣጫ
ሇማሳካት የሚከተለት ግቦች እና የትግበራ መምሪያ በመሇየት መተግበር አስፈሊጊ ነው።

6.7.2. ግቦች

1. ሃገራዊ ሳይበር ዯህንነትን ሇማረጋገጥ በመንግስት፣ በግለ ዘርፍ እና በሚመሇከታቸው


ባሇዴርሻ አካሊት መካከሌ ቅንጅትና አጋርነት መመስረትና ማጠናከር፤
2. የሳይበር ዯህንነት ምርት በማምረትና አገሌግልት በማቅረብ ሊይ የተሰማሩ ሃገር በቀሌ
የግሌ ተቋማት እንዱበራከቱና እንዱጠናከሩ በማዴረግ የሃገሪቱን የሳይበር ዯህንነት
ምርትና አገሌግልት ፍሊጎት ከማርካት አሌፈው በዓሇም አቀፍ ገበያዎች ሊይ ተወዲዲሪ
እንዱሆኑ ማስቻሌ፤
3. የሳይበር ወንጀሌ፣ ሽብርተኝነት፣ ስሇሊ እና መሰሌ ዓሇም-አቀፍ ይዘት ያሊቸው የሳይበር
ዯህንነት ስጋቶች ሇመከሊከሌ ትብብር መፍጠር፤
4. በሳይበር ዯህንነት ዙሪያ የሚዯረግ ዓሇም አቀፍ ትብብር የሃገሪቱ የውጪ ጉዲይ
ዱፕልማሲ አካሌ እንዱሆን ማዴረግ፤
5. ሁሇትዮሽና ከዚያ በሊይ የሆኑ የሳይበር ዯህንነት ስምምነቶችን ማበረታት እና
ማጎሌበት፤

6.7.3. አዴማስ

ይህ ትኩረት አቅጣጫ የሳይበር ዯህንነት አጀንዲዎችን በተመሇከተ በሃገር-አቀፍ እና በዓሇም-


አቀፍ ዯረጃ ትብብርና ቅንጅት በመፍጠር ዙሪያ የሚያተኩር ነው፡፡

25
6.7.4. መስፈርት

በሳይበር ዯህንነት ዙሪያ ሰፊ ሌምዴ እና ጥሩ ተሞክሮ ያሊቸውን አካሊት፣ ዴርጅቶችና


ሃገሮች በመሇየት ጠንካራ የሆነ ትስስር በመፍጠር የሳይበር ስጋቶችንና ጥቃቶችን
የመቀነስና የመከሊከሌ አቅም ማጎሌበት ነው፡፡

6.7.5. ቁጥጥር

ይህንን የትኩረት አቅጣጫ ሇማሳካት በሳይበር ዯህንነት ዙሪያ ሰፊ ሌምዴና ጥሩ ተሞክሮ


ያሊቸው ሃገራዊ እና ዓሇም-አቀፍ አካሊት በመሇየት ጠንካራ ትስስር ተመስርቶ ከትስስሩ
ተጠቃሚ መሆን ሲቻሌ ነው፡፡

6.7.6. የትግበራ መምሪያ


 ብሔራዊ የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ መኖሩ ኢትዮጵያ ዓሇም-አቀፍ
ትብብርን በተመሇከተ ያሊትን አቋም የሚጠቁም በመሆኑ ዓሇም-አቀፍ ትብብርን
ሇማጎሌበት የሚያስችለ ስሌቶችን መቀየስና መተግበር፤
 የሳይበር ዯህንነት ትብብር ሇማዴረግ የሚፈሌጉ ሃገራትን በመሇየት፣ ሇምን ትብብር
መፍጠር እንዲስፈሇገ አቅጣጫ ማስቀመጥ፤(ሇምሳላ፡- የሳይበር ወንጀሌ፣ ኦፕሬሽናሌ
እና ላልችም)፤
 ዓሇም-አቀፍ ትብብር የሚያዯርጉ የሚመሇከታቸውን ዴርጅቶች(መ/ቤቶች) በብሔራዊ
ዯረጃ መሇየት፣ተግባራትን በዝርዝር መስጠት፣ ተግባራዊ እንዱሆን ክትትሌ
ማዴረግ፤
 መረጃ መጋራት(ሇምሳላ፡- ቤንችማርክ በማዴረግ፣ ቴክኖልጂያዊ እውቀት እና
በመሰረታዊ የስጋት ዲሰሳዎች)፣ ብዙ አገራትን ባሳተፈ ከፍተኛ ዯረጃ ያሇው
የመንግስት፣ የግሌ አጋርነት እና መረጃ የማጋራትና የመተንተን አቅም ባሊቸው
ማዕከሊት አማካኝነት ዓሇም-አቀፍ ትብብር መፍጠር፤
 ከመረጃ ዯህንነት ጋር የተያያዘ ሆኖ ከብሄራዊ ዯህንነት ጥቅሞች ተቃራኒ እስካሌሆነ
ዴረስ ሁሇትዮሽ፣ ብዙዮሽ ወይም ዓሇም-አቀፍ ስምምነቶችን እና ኮንቬንሽኖችን
መቀሊቀሌ፤
 ተጨባጭና ዋና አገር አቋራጭ የሆኑ ስጋቶችን በተመሇከተ መረጃ ሇመጋራትና
መሌስ ሇመስጠት የሚያግዙ የስታንዲርዴ ኦፕሬቲንግ አካሄድች (standard
operating procedures(SOPs) ሇመቅረጽ በሚዯረጉ ዓሇም-አቀፍ ጥረቶች ሊይ
አስተዋጽኦ ማዴረግ፤

26
 ከሳይበር ዯህንነት ስትራቴጂያዊ አጋሮች ጋር የሚዯረግን ትብብር መነሻ እንዱሆን
አካባቢያዊ፣ አህጉራዊና ዓሇም-አቀፋዊ ተሳትፎን ማበረታታት፤

6.7.6.1. በመንግስትና በግለ ዘርፍ አጋርነት መፍጠር


የመንግስት እና የግለ ዘርፍ የተጋሯቸውን ግቦች ሇማሳካት የጋራ የሆነ ዓሊማዎችን
በመንዯፍ፤የዯህንነትና ከስጋት ቶል ሇማገገም የሚያስችለ የተሇያዩ ገጽታዎች ሊይ ትኩረት
የሚያዯርጉ ተግባራት እንዯሚከተለት ናቸው-
 ወንጀሌ እንዲይሰራ ማዴረግ(ጥቃት ፈጻሚዎችን ጥቃት ከመፈጸም ማገዴ)፤

 መከሊከሌ (አዱስ ስጋት ሲኖር ጥናትና ምርምር ማዴረግ)፤

 መሇየት (ሇአዲዱስ ስጋቶች መፍትሄ ሇማግኘት ኢንፎርሜሽን መጋራትን ማከናወን)፤

 መሌስ መስጠት (አንዴ ክስተት መጀመሪያ ሊይ ያመጣውን ተጽእኖ ሇመቋቋም


የሚያስችሌ አቅም መፍጠር)፤

 ማገገም (አንዴ ክስተት መጨረሻ ሊይ የፈጠረውን ተጽእኖ ሇመጠገን የሚያስችሌ


አቅም መፍጠር)፤

6.7.6.1.1. የትግበራ መምሪያ


 መረጃ ሇመጋራትና የሙያ ሌቀትን ሇማግኘት እና ዴግግሞሽን ሇማስቀረት
በመንግስትና በግለ ዘርፍ መካከሌ ያሇውን አጋርነት ከላልች ዴርጅቶች ጋር እንዳት
ትስስር መፍጠር እንዯሚቻሌ እቅዴ ማውጣት፤
 ትብብር ሇማዴረግ የሚያስችለ ፖሉሲዎችን እና ማዕቀፎች ማዘጋጀት/ማጽዯቅ፤.
 የሚመሇከታቸው አካሊትን ሇመረዲትና ንቃተ-ህሉና ሇማጎሌበት ሲባሌ በከፍተኛ
ባሇስሌጣኖች ዯረጃ ስትራቴጂያዊ ትብብር የመፍጠርን ጥቅም ማሰስ፤
 በዴርጅታቸው ኃሊፊነት ተስጥቷቸው በተሇያዩ የሳይበር ዯህንነት ዙሪያ እርምጃ
መውሰዴና መቀየር የሚችለና ታማኝ የሆኑ ሌዩ ባሇሙያዎችን መመሌመሌ፤
 የመንግስት-የግሌ ትብብር ሇማዴረግ የሚያስችለ የህግ እና ቴክኒካሌ ማዕቀፎች
በማዘጋጀት/በማበሌጸግ/በህግ የመወሰን ስሌጣን እንዱኖር ምቹ ሁኔታዎችን
በመፍጠር የህግ ምክር መስጠት፤
 ከህግ አማካሪ ጋር በመሆን የአባሌነት ዯንቦችና መስፈርቶች የሚያብራራ መረጃን
ይፋ ያሇማውጣት ስምምነት/non-disclosure agreement/ ናሙና ማዘጋጀት፤
ይህንን ስምምነት በመጠቀም የሚመሇከታቸው አካሊትም እንዱፈርሙት መጠየቅ፤

27
 ሁለም የትብብሩ አባሊት ንቁ ተሳታፊ በመሆን ሇአባሌነቱ ተገቢ እሴት ያሊቸውን
ኢንፎርሜሽንና፣ አገሌግልቶች መስጠታቸውን እና ዴጋፍ ማዴረጋቸውን ማረጋገጥ፤
 ዴንበር ተሻጋሪ የሆነ መረጃ የመጋራትና ቅንጅት በመፍጠር ከላልች የመንግስት-
የግሌ ትብብሮች ጋር ዓሇም-አቀፍ ግንኙነቶችን ሇመፍጠር እዴልችን መፈሇግ፤

6.7.6.2. ባሇዴርሻ አካሊትን መሇየትና ማሳተፍ


ስኬታማ በሁነ ሁኔታ ብሄራዊ ሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ ሇመተግበር
በመንግስትና በግሌ ባሇዴርሻ አካሊት መካከሌ ተገቢ የሆነ ትብብርን ይሻሌ፡፡ ሇፖሉሲና
ስትራቴጂው ስኬት ባሇዴርሻ አካሊትን መሇየትና ማሳተፍ ወሳኝ የሆነ እርምጃ ነው፡፡
የመንግስት ባሇዴርሻ አካሊት በአብዛኛው የፖሉሲ፣ የሬጉላቶሪና የኦፕሬሽናሌ የውክሌና
ስሌጣን አሊቸው፡፡ የሃገሪቱን መሰረተ-ሌማቶች እና አገሌግልቶች ጤንነት እና ዯህንነት
ያረጋግጣለ፡፡ የግለም ዘርፍ የሌማት አካሌ መሆን ስሊሇባቸው አብዛኞቹ ቁሌፍ የመረጃ
መሰረተ-ሌማቶችና አገሌግልቶች እነርሱን ባካተተ ሁኔታ የወዯፊት ዕቅዴ አካሌ አዴርጎ
መሇየት ተገቢ ነው፡፡

6.7.6.2.1. የትግበራ መምሪያ

 ሁለንም የቁሌፍ መሰረተ-ሌማቶችና አገሌግልት ሰጪ አካሊትን በአግባቡ መሇየት፤


 የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲ፣ ስትራቴጂና ስርዓቶችን ሇማነሳሳት እና ሇማሌማት
ኃሊፊነት ያሇባቸውን የመንግስት ባሇዴርሻ አካሊት መሇየት፤ ሇምሳላ፡- ብሄራዊ
ቴላኮሙኒኬሽኖችን ሬጉላት የሚያዯርግ፣ ብሄራዊ መሰረተ-ሌማቶችን መጠበቂያ
ማዕክሌ፣ ወዘተ)፤
 በግሌጽ ሚናዎቻቸውንና ኃሊፊነቶቻቸውን በማስቀመጥ የመንግስትና የግሌ ባሇዴርሻ
አካሊትን ማሳተፍ (ሇምሳላ፡- የግሌ ባሇዴርሻ አካሊት መሰረተ-ሌማቶቻቸውን ጥበቃ
ያዯርጋለ፤ ሆኖም ብሄራዊ ዯህንነት ጥበቃ ዙሪያ የጋራ የሆነ ኃሊፊነት
ይኖራቸዋሌ)፤
 የመንግስትና የግሌ ባሇዴርሻ አካሊትን በሂዯቱ ውስጥ ተሳታፊ ሇመሆን የሚያስችሌ
ተገቢ የሆነ ማበረታቻ ማስቀመጥ (ሇምሳላ፡- የግለን ዘርፍ ተሳታፊ የሚያዯርጉ
የሚያስወጡ ሬጉላሽኖች ማውጣት)፤ እንዱሁም የመንግስትና የግለ ዘርፍ
ሉኖሯቸው የሚችለትን ሌዩነትና የፍሊጎት መጋጨት ግምት ውስጥ ማስገባት፤
 ፖሉሲና ስትራቴጂው ትግበራ ትክክሇኛ ባሇዴርሻ አካሊትን በትክክሇኛ ጊዜ በሂዯቱ
ውስጥ ማሳተፍ፤

28
 ባሇዴርሻ አካሊት ሇፖሉሲና ስትራቴጂው ዓሊማዎች ሇምንና እንዳት አስተዋጽኦ
እንዯሚያዯርጉ፣ የግሇሰቦችን ተግባራትና የዴርጊት መርሀ-ግብርችን መግሇጽ
(ስጋቶችንና አዯጋዎችን ሇመዲሰስ ከቁሌፍ መሰረተ-ሌማት ባሇቤቶችና ቁሌፍ
አገሌግልት አቅራቢዎች ጋር የቅንጅት አካሄዴ መከተሌ)፤
 በብሄራዊ ዯረጃ በሚዯረጉ እንቅስቃሴዎች የሳይበር ዯህንነት ጉዲዮችን ማሳሇጥ
የሚያስችሌ ሚና መስጠት፤ (ሇምሳላ መረጃ መጋራት፣ ዓሇም-አቀፍ ትብብር፣
ስጋትን ማስተዲዴር)፤
 የባሇቤትነት ስሜት ሇመፍጠርና ሇእያንዲንደ ተወካይ አማራጭ ሇመመዯብ ከፍተኛ
ዯረጃ ያሊቸውን ተወካዮች ማሳተፍ፤
 በብሄራዊ ዯረጃ ንቃተ-ህሉናን ከፍ በማዴረግ ዜጎች የሳይበር ዯህንነት ስጋቶች በዯንብ
እንዱረደ፤ እንዱሁም ስጋቶቹ ከመከሰታቸው በፊት እርምጃዎች እንዱወሰደ
ማዴረግ፤
 እንዯ ሃገር መከሊከያ፣ የውጪ ጉዲዮች፣ፍትህ፣ ቴላኮሙኒኬሽን ተቆጣጣሪ፣ የመረጃ
ጥበቃ ባሇስሌጣን፣ እና የሳይበር ወንጀሌ መምሪያ ያለትን ተቋማት የሳይበር
ዯህንነት ቀውሶችን ማስተዲዯር፣ ከጉዲት ነጻ መሆን ያሇባቸውን ሚኒስትር መስሪያ
ቤቶች በፖሉሲና ስትራቴጂ ትግበራ ሊይ ተሳታፊ ማዴረግ፤
 በብሄራዊ ዯረጃ የመረጃ መጋራት አቅሞች ቁሌፍ አካሌ ሉሆኑ ስሇሚችለ አሁን ሊይ
ያለትን ብሄራዊ የሳይበር ዝግጁነትና ምሊሽ ሰጪ ቡዴኖች (CERTs) ማሳተፍ፤
 የተሇያዩ የባሇዴርሻ አካሊት ቡዴኖችን ፍሊጎት ሇማካተት ብሄራዊ ፍሊጎት ያሊቸውን
ቡዴኖች ማሳተፍ፤

6.7.6.3. የሚታመኑ የመረጃ መጋሪያ ስርዓቶች መዘርጋት

ያሇማቋረጥ ተሇዋዋጭ የሆነ ከባቢን ይበሌጥ ሇመረዲት በግሌና በመንግስት ባሇዴርሻ አካሊት
መካከሌ የመረጃ መጋራት ጠቃሚ ዘዳ ነው፡፡ መረጃ መጋራት ቁሌፍ በሆኑ የመንግስትና
የግሌ ባሇዴርሻ አካሊት መካከሌ ስትራቴጂያዊ ትብብር መፍጠሪያ መንገዴ ነው፡፡ የቁሌፍ
መሰረተ-ሌማት ባሇቤቶች በመከሰት ሊይ ያለ ጥቃቶች፣ ስጋቶች እና ተጋሊጭነቶች እንዳት
መቀነስ እንዯሚያስችለ ግብአቶችን ከመንግስት ባሇስሌጣናት ጋር የመጋራት እዴሌ
ሲኖራቸው፣ የመንግስት ባሇዴርሻ አካሊት ዯግሞ የብሄራዊ ዯህንነት ሁኔታ ገጽታዎች ሊይ
በስሇሊም ሆነ በሳይበር ወንጀሌ መምሪያ የተገኘ መረጃን ጨምሮ ማወቅ የሚያስፈሌጋቸው
በመሆኑ መረጃ ይሰጣለ፡፡

29
6.7.6.3.1. የትግበራ መምሪያ

 የመረጃ መጋራት ዘዳንና ዘዳውን የሚያስተዲዴሩ መሰረታዊ መርሆችና ዯንቦች


በሚገባ መግሇጽ(ሇምሳላ፡- መረጃን ይፋ ያሇማዴረግ ስምምነቶች፣ የመተማመኛ
ዯንቦች…ወዘተ)፤
 መረጃ ሇመጋራት ዘርፉን መሰረት ያዯረገ አካሄዴ መከተሌ (ሇምሳላ፡- አንዴ የመረጃ
መጋሪያ ሇኢንተርኔት አገሌግልት አቅራቢዎች፣ አንዴ ሇሃይሌ ማመንጫ፣…ወዘተ)፤
በሁለም የመረጃ መጋሪያ ስርዓቶች መካከሌ በቂ የሆነ የመረጃ ፍሰት መኖሩን
ማረጋገጥ)፤
 ስትራቴጂያዊ ጉዲዮችና ቁሌፍ ስጋቶች እና ተጋሊጭነቶች ሊይ ትኩረት ማዴረግ
(ሇምሳላ፡- ዋና/ቁሌፍ መቋረጦች፣…)፤
 ባሇዴርሻ አካሊት (በተሇይ የግሌ ዘርፉ) ተሳትፎ እንዱያዯርጉና ምስጢራዊ መረጃ
እንዱያጋሩ ተገቢ የሆኑ ማበረታቻዎችን (የትንተናውን ውጤቶች መጋራት)
ማቅረብ፤
 ትክክሇኛ ገጽታ ያሊቸው እና ትክክሇኛ የሆኑ ሌዩ ባሇሙያዎች በስርዓቱ ሊይ
መሳተፋቸውን ማረጋገጥ፤ በተሇምድ ተሳታፊዎቹ ከፍተኛ ዯረጃ ያሊቸው ሌዩ
ባሇሙያዎች (ሇምሳላ፡- ዋና የኢንፎርሜሽን ዯህንነት ኦፊሰሮች) ኢንፎርሜሽንን
በኮርፖሬሽን ዯረጃ መጋራት እንዱችለ ማዴረግ፤
 ሌዩ ባሇሙያዎች ከህግ አስፈጻሚ፣ ከስሇሊ፣ ከብሄራዊ/መንግስታዊ/CERTs እና
ተፈሊጊ የሆኑ ሬጉላቶሪ አካሊት መገኘት እንዲሇባቸው መወሰን፤
 በሌዩ ባሇሙያዎች መካከሌ መተማመን እንዱያብብ የመረጃ መጋሪያ ስርዓትን
መጠን ትንሽ ማዴረግ፤
 ምስጢራዊ መረጃን ሇመጋራት መዯበኛ የሆኑ ስብሰባዎችን ማዘጋጀት፤ መንግስት
ሂዯቱን ማሳሇጥና የልጂስቲክ ዴጋፍ ማዴረግ፤ የሁለንም ባሇዴርሻ አካሊት የጋራ
ኃሊፊነት መሆኑን ሇማሳየት ኢኒሸቲቩን መምራት፤
 የሳይበር ዯህንነትን በከፍተኛ ዯረጃ ሇማስፋት ተገቢ የሆኑ የሃገራዊና ዓሇም-አቀፍ
የሚታመኑ የመረጃ መጋራት ኮሚዩኒቲዎችን መሇየት እና የተሳትፎ ሁኔታን
መወሰን፤
 የብሄራዊ አዯጋ መዝገብን ወቅታዊ ማዴረግ እና በቀዴሞ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶች
ተገቢ ሇሆኑና ኢሊማ ሇተዯረጉ ተጠቃሚዎች ማንነትን ሳያሳውቁ የተሰበሰበውን
መረጃ ማሰራጨት፤

30
7. የባሇዴርሻ አካሊት ኃሊፊነትና ሚና

ሁለም የመንግስት እና ቁሌፍ የመረጃ መሰረተ ሌማት ተቋማት ይህንን የፖሉሲና


ስትራቴጂ ማስፈጸሚያ መመሪያ የመተግበርና ተሌዕኳቸውን መሰረት ያዯረጉ ላልች
ተግባራትን የማከናወን ግዴታ አሇባቸው። በተጨማሪ ከዚህ መመሪያ ዓሇምአቀፍ
ስታንዳርዶች ጋር የሚጣጣም የሳይበር ዯህንነት ሇማረጋገጥ የሚያስችለ ፕሮግራሞች
የመንዯፍና የመተግበር ኃሊፊነት አሇባቸው።

7.1. ኢንፎርሜሽን መረብ ዯህንነት ኤጀንሲ

1. የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ ትግበራ በባሇቤትነት ይመራሌ፤


ያስተባብራሌ፤
2. የኢንፎርሜሽንና ቁሌፍ የመሰረተ ሌማቶች ዯህንነት ሇማረጋገጥ የሚያስችለ
ብሔራዊ የፖሉሲና ስትራቴጂዎችን ተፈፃሚነት ይከታተሊሌ፤
3. መንግስታዊና የግሌ ተቋማት ሃገራዊ የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ
ማዕቀፎችን ተከትሇው የየራሳቸው ፖሉሲና ስትራቴጂ ቀርጸው ስራ ሊይ
እንዲያውለ ድጋፍ ይሰጣሌ፤ አፈጻጸማቸውንም ይቆጣጠራሌ፤
4. የሳይበር ዯህንነት ተሌዕኮውን ሇማስፈፀም አስፈሊጊ ሆኖ ሲገኝ ዓሇምአቀፋዊ
ቅንጅትን ይፈጥራሌ፤
5. ቁሌፍ የኢንፎርሜሽን መሰረተ ሌማቶች ዯህንነት ዙሪያ የትምህርትና ስሌጠና
ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ከላልች ጋር እየተባበረ አቅምን ይገነባሌ፤
6. ከመንግስትና ከግሌ ተቋማት፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከላልች
ባሇድርሻ አካሊት የተወከለ ብሔራዊ የሳይበር ዯህንነት ምክርቤት ያቋቁማሌ፤
ይመራሌ፤
7. ብሔራዊ የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ የትግበራ መሪ እቅድ (መርሃ
ግብር) በማዘጋጀት ተግባራዊ ያዯርጋሌ፤
8. በመንግስት እና በግለ ዘርፍ መካከሌ የሳይበር ዯህንነት ሇማረጋገጥ የሚያስችለ
የአጋርነት የአሰራር ስርዓቶች ይዘረጋሌ፤

31
7.2. የኢትዮ ሰርት (CER2T)

1. በሀገር ዯረጃ የኢንፎርሜሽን ዯህንነት ሁኔታዎችን ይተነትናሌ፤ ክትትሌ


ያዯርጋሌ፤
2. የሳይበር ዯህንነት ክስተቶችንና ጥቃቶችን ይቆጣጠራሌ፤
3. የሳይበር ዯህንነት ክስተቶችን ሇመከሊከሌ የሚያስችሌ አቅም ይፈጥራሌ፤
4. ከብሔራዊ የሳይበር ዯህንነት ምክር ቤት የሚተሊሇፉ ውሳኔዎችን ይፈጽማሌ፤

7.3. ብሔራዊ የሳይበር ዯህንነት ምክር ቤት(ብሔራዊ የሳይበር ዯህንነት አመራር


ስርዓት)

1. የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲና ስትራቴጂ በበሊይነት ይመራሌ፤ ያስተባብራሌ፤


ይቆጣጠራሌ፤
2. የፖሉሲና ስትራቴጂው አፈፃፀም ክትትሌና ግምገማ በማድረግ አቅጣጫ
ያስቀምጣሌ፤
3. የፖሉሲና ስትራቴጂው ውጤታማነት በመገምገም ውሳኔ ያስተሊሌፋሌ፤
ጉድሇቶች እንዲስተካከለ አቅጣጫ ያስቀምጣሌ፤
4. የፖሉሲውንና ስትራቴጂውን አፈፃፀም መነሻ በማድረግ ሇማሻሻሌ አቅጣጫ
ያስቀምጣሌ፤
5. በሳይበር ዯህንነት ጉዳዮች ዙሪያ የመንግስት አማካሪ አካሌ ሆኖ ይሰራሌ፤
6. በሳይበር ዯህንነት ዙሪያ የባሇድርሻ አካሊት ሚናና ኃሊፊነቶች ይሇያሌ፤
ይመራሌ፤ያስተባብራሌ፤

7.4. የህግ አካሊት

1. የሳይበር ወንጀሌ፣ ሽብርተኝነትና ስሇሊ ወንጀሇኛን ይሇያለ፤ ይከሊከሊለ፤


ይመረምራለ፤
2. የሳይበር ወንጀሌ ሲፈፀም ተጠርጣሪውን ወዯ ህግ ያቀርባለ፤
3. የሳይበር ወንጀሌ የህግ ተጠያቂነት ያረጋግጣለ፤ ውሳኔ ይሰጣለ፤

7.5. የግለ ዘርፍ

1. ሇቁሌፍ መሰረተ ሌማት ተቋማት የሚውሌ የሳይበር ዯህንነት ምርትና


አገሌግልት በማቅረብ የበኩሊቸውን ድርሻ ይወጣለ፤

32
2. የሳይበር ዯህንነት ሇማረጋገጥ የመረጃ ሌውውጥ ማድረግ እና የቴክኒካሌ ድጋፍ
ይሰጣለ፤
3. የሳይበር ጥቃቶችንና ስጋቶችን ሇመቀነስና ሇመከሊከሌ የሚያስችለ ምርቶችና
አገሌግልቶች ያቀርባለ፤
4. የሳይበር ዯህንነት ምክርቤት አባሌ በመሆን በምክር ቤቱ የሚሰጣቸውን
ኃሊፊነትና ግዴታዎች ተግባራዊ ያዯርጋለ፤

7.6. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት

1. በሳይበር ዯህንነት ዙሪያ የሰሇጠነ የሰው ኃይሌ ሇማፍራትና ሇማሳዯግ


የሚያስችሌ የትምህርትና ስሌጠና መረሃ ግብሮችን ያዘጋጃለ፤ ይሰጣለ፤
2. አስተማማኝና ወጪ ቆጣቢ የሳይበር ዯህንነት መፍትሄዎችን ሇማመንጨትና
ሇማበሇፀግ የሚያስችሌ ጥናትና ምርምር ያካሄዳለ፤
3. የሳይበር ዯህንነትን ሇማረጋገጥ በሚዯረጉ የምርምርና ሌማት ተግባራት
በግንባር ቀዯምትነት ከሚሰሩ የቴክኖልጂ ተቋማት ጋር በቅንጅት ይሰራለ፤
4. የሳይበር ዯህንነት ምክር ቤት አባሌ በመሆን የሚሰጣቸውን ኃሊፊነትና
ግዴታዎች ይወጣለ፤

7.7. ቁሌፍ የመሰረተ-ሌማት ዘርፎች

1. የቁሌፍ መሰረተ ሌማቶች ዯህንነት ስጋቶችና ክስተቶች ይሇያለ፤ በቅዯም


ተከተሌ ያሰቀምጣለ፤ ጥበቃ ያዯርጋለ፤
2. የሳይበር ዯህንነት ሇማረጋገጥ የሚያስችለ የዳሰሳ ጥናት ያዯርጋለ፤
3. የሳይበር ዯህንነት ስጋቶች፣ ጥቃቶች እና ክስተቶች የመረጃ ሌውውጥና
ሪፖርት ያዯርጋለ፤

33
8. ብሔራዊ የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲ እና ስትራቴጂ የማስፈጸሚያ መርሃ ግብር

የትኩረት አቅጣጫ 1፦የህግ እና ቁጥጥር ማዕቀፍ

ግቦች የማስፈጸሚያ ስሌቶች የሚመራው ተባባሪ አካሌ የሚከናወንበት


አካሌ ጊዜ
የሳይበር ዯህንነት ስጋቶችንና ተጋሊጭነቶችን በመንግስት እና በቁሌፍ የግሌ ተቋማት ተግባራዊ የሚዯረጉ  ኢመዯኤ  ፍትህ አካሊት ከ2013 ጀምሮ
መቀነስ፤ ጥቃቶችን ሇመከሊከሌ እና ሇመቋቋም የሳይበር ዯህንነት ፖሉሲዎች፣ ዯንቦች፣ መመሪያዎች፣  ብሔራዊ
የሚያግዙ፤ እንዱሁም ሀገሪቱ ከተቀበሇቻቸው ስታንዯርድች እና የአሰራር ስርዓቶች መቅረጽ፣ መተግበር፤ የሳይበር
ቀጠናዊ፣ አህጉራዊና ዓሇም አቀፍ ህጎች እና የሳይበር ዯህንነት ሕግጋትና የቁጥጥር ማዕቀፎች ተቀባይነት እና ዯህንነት
ስታንዲርድች ጋር ተጣጣሚነት ያሊቸው የሳይበር ተፈፃሚነት ሇማሳዲግ በሂዯቱ ሁለንም ባሇዴርሻ አካሊት ም/ቤት
ዯህንነት ሕግጋት እና ቁጥጥር ማዕቀፎችን በማሳተፍ እንዱሰራ ይዯረጋሌ፤
ማውጣት፤ በቀጣይነትም ማሻሻሌ፤
የሳይበር ወንጀሌ፣ ሽብርተኝነት፣ የሳይበር ስሇሊ እና የሳይበር ዯህንነት ህጎችን ሇማስፈጸም የመርማሪዎች፣ አቃቤ
መሰሌ ጥቃቶች ሇመከሊከሌ የሚያስችሌ የህግ ህጎች፣ ዲኞች እና ላልች የፍትህ አካሊት በትምህርት፣
አካሊትን አቅም መገንባት፤ በስሌጠና፣ በምክክር መዴረኮች፣ በኮንፈረንሶችና በመሳሰለት
ዘዳዎች አቅማቸው በቀጣይነት ይገነባሌ፤
በሀገር ውስጥ የሚመረቱና ወዯ ሀገር ውስጥ የሚገቡ በሀገር ውስጥ የሚመረቱም ሆነ ከውጭ የሚገቡ የሳይበር ኢመዯኤ  ሁለም ከ2013 ጀምሮ
የሳይበር ዯህንነት ምርቶችና አገሌግልቶች፤ እንዱሁም ዯህንነት ምርቶች ጥራትና ብቃታቸው ይፈተሻሌ፤ የፈጻሚ የመንግስት
ቁሌፍ የመሰረተ ሌማት ዝርጋታዎች ሀገራዊ የሳይበር አካለን በቀጣይነት የማብቃት ስራዎች ይሰራለ፤ ተቋማት
ዯህንነት ፍሊጎትን ያሟለ መሆናቸውን ሇማረጋገጥ
የሚያስችሌ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት፤

ማህበረሰቡ በሀገሪቱ የሳይበር ዯህንነት አቅሞች ዙሪያ ከሳይበር ዯህንነት ህግጋትና ቁጥጥሮች ዙሪያ ማህበረሰቡ ግንዛቤ ኢመዯኤ  ፍትህ አካሊት ከ2013 ጀምሮ
ያሇውን ዓመኔታ ሇማሳዯግ በኢንፎርሜሽን አሰባሰብ፣ እንዱኖረው የንቃተ-ህሉና ስራዎች ይሰራለ፤  ሰሊም ሚ/ር
ትንተና፣ ስርጭት፣ አጠቃቀም፣ ክምችት እና
አወጋገዴ ዙሪያ ዯረጃቸውን የጠበቁ የህግና ቁጥጥር

34
ማዕቀፎችን መዘርጋት፤

35
የትኩረት አቅጣጫ 2፦ የሳይበር ዯህንነት ንቃተ ህሉና

ግቦች የማስፈጸሚያ ስሌቶች የሚመራው ተባባሪ አካሌ የሚከናወንበት


አካሌ ጊዜ
በሳይበር ዯህንነት ዙሪያ የተሰማሩ ተቋማት ተዯራሽነታቸውን ኢመዯኤ  ሁለም የመንግስት
በማስፋትና በማጠናከር ሇህብረተሰቡ የሳይበር ዯህንነት ግንዛቤ እና ቁሌፍ የግሌ ከ2013 ጀምሮ
የመንግስት ተቋማት፣ የግሌ ተቋማትና መስጠት፤ ተቋማት
ዜጎች በሳይበር ዯህንነት ዙሪያ ያሊቸውን  ከፍተኛ ት/ት
በሳይበር ዯህንነት ክስተቶች ዙሪያ ፈጣን ምሊሽ መስጠት
ተቋማት
እውቀትና አመሇካከት ማዲበር፤ የሚያስችለ የጥሪ ማዕከሌና ላልች ዘዳዎችን በመጠቀም  ትምህርት ሚ/ር
ሇህብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች ይሰራለ፤  ኢትዮ ቴላኮም
በትምህርት ተቋማት የሳይበር ዯህንነት ንቃተ-ህሉና ክበቦች
ይቋቋማለ፤
ከጥንቃቄ ጉዴሇትና ካሇማወቅ የሚዯርሱ በሳይበር ዯህንነት ዙሪያ የተሰማሩ ተቋማትን በማስፋትና  ሁለም የመንግስት
የሳይበር ጥቃቶች፣ ስጋቶች እና ተጋሊጭነቶችን በማጠናከር ሇህብረተሰቡ ወቅታዊ የሳይበር ዯህንነት ግንዛቤ እና ቁሌፍ የግሌ ከ2013 ጀምሮ
መቀነስ፣ እንዱሰጡ ይዯረጋሌ፤ ተቋማት
 ቁሌፍ መሰረተ
በሀገሪቱ ቁሌፍ የኢንፎርሜሽን መሰረተ ሌማት ተቋማት በሳይበር ሌማት ያሊቸው
ዯህንነት ዙሪያ ወቅታዊና ቀጣይነት ያሇው የምክክር መዴረኮች፣ ተቋማት
ፓነልች፣ ውይይቶች እና የመሳሰለ የግንዛቤ ማስጨበጫ  ከፍተኛ ትምህርት
መዴረኮች ይዘጋጃለ፤ ተቋማት
 ትምህርት ሚ/ር
የሳይበር ዯህንነት ተጋሊጭነቶችና ስጋቶች ብሄራዊ የሳይበር ዯህንነት ሳምንት በማክበር ሃገር አቀፍ የንቃተ-
ሇመቀነስ፤ እንዱሁም ጥቃቶች ሇመከሊከሌ ህሉና ማጎሌበቻ ዘመቻዎች ይከናወናለ፤
የሚያስችሌ የዜጎች ንቃተ-ህሉና ማሳዯግ እና የመገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም የህብረተሰቡ ንቃተ-ህሉና እና  የሚዲያ አካሊት
ሀገራዊ የሳይበር ዯህንነት ባህሌ መፍጠር፤ ግንዛቤ ሇማሳዯግ የተሇያዩ ወቅታዊነታቸውን የጠበቁ የሳይበር ከ2013 ጀምሮ
ዯህንነት ፕሮግራሞች ይዘጋጃለ፤ ይቀርባለ፤
በሳይበር ዯህንነት ዙሪያ ሇሚሰሩ ሇመገናኛ ብዙሃን፣ ሇግሌ  የሚዲያ አካሊት
ተቋማት፣ ሇሲቭክ ማሕበራት እና ላልች አካሊት እውቅና እና  ሲቪክ ማህበራት
ማበረታቻ ይሰጣሌ፤  ቁሌፍ የግሌ
36
ተቋማት
የትኩረት አቅጣጫ 3፦ የሳይበር ዯህንነት አቅም ግንባታ

ግቦች የማስፈጸሚያ ስሌቶች የሚመራው ተባባሪ አካሌ የሚከናወንበት


አካሌ ጊዜ
የሳይበር ዯህንነት ስጋት፣ ተጋሊጭነት እና የሳይበር ዯህንነት ትምህርት በሀገሪቱ የትምህርት ፖሉሲ ውስጥ  ኢመዯኤ  ትምህርት ሚ/ር
ጥቃት ሇመሇየት፣ ሇመዲሰስ እና ምሊሽ ይካተታሌ፣  ብሔራዊ  ከፍተኛ ት/ት ከ2013 ጀምሮ
ሇመስጠት የሚያስችለ ተቋማዊ መዋቅሮችንና የሳይበር ዯህንነት አቅም ሇማሳዯግ የሚረደ ወቅታዊ የሆኑ የሳይበር ተቋማት
የትምህርትና ስሌጠና ሰርትፊኬሽኖች ሇባሇሙያዎች ይሰጣሌ፤ ዯህንነት  ሳይንስና ከፍተኛ
አቅሞችን መገንባት፤
ም/ቤት ት/ት ሚ/ር
የሳይበር ዯህንነት ባሇሙያዎችን ሉያሰራ የሚችሌ የብቃት
መመዘኛ ስታንዲርዴ ማስቀመጥ፤

የመንግስት፣ የግሌ እና የከፍተኛ ትምህርት የመንግስትና የግሌ ተቋማት እንዲስፈሊጊነቱ የሳይበር ዯህንነት  ሁለም
የአሰራር ስርዓቶች ይተገብራለ፤ የመንግስት እና ከ2013 ጀምሮ
ተቋማት የሳይበር ዯህንነት አቅማቸውን
ቁሌፍ የግሌ
ማጠናከር፤ ተቋማት
በመንግስት፣ በግሌና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከሌ  ትምህርት ሚ/ር
በሳይበር ዯህንነት ዙሪያ የምርጥ ተሞክሮ፣ የሌምዴ ሌውውጥና፣  ከፍተኛ
የእውቀት ሽግግር ሇማዴረግ የሚያስችለ መዴረኮች ይዘጋጃለ፤ የትምህርት
ተቋማት(የመንግስ
ት እና የግሌ)
 የምርምር
ተቋማት
በሀገር ዯረጃ ብቃት ያሊቸው የሳይበር ዯህንነት በቁሌፍ የኢንፎርሜሽን መሰረተ ሌማት ተቋማት ውስጥ በሚሰሩ  ከፍተኛ
ባሇሙያዎችን መፍጠር፤ ባሇሙያዎች ስብዕና ሊይ ሌዩ ትኩረት በመስጠት የምሌመሊ እና የትምህርት ከ2013 ጀምሮ
የማብቃት ስራ ይሰራሌ፤ ተቋማት(የመንግስ
ት እና የግሌ)
 የሚዲያ አካሊት
በዓሇም ዓቀፍ ዯረጃ በዘርፉ ከተሰማሩ ተቋማት ጋር ትስስር  የሚዲያ አካሊት
በመፍጠር የሌምዴ ሌውውጥ እና የእውቀት ሽግግር ይዯረጋሌ፤  ቁሌፍ የግሌ
ተቋማት
37
የትኩረት አቅጣጫ 4፦ የሳይበር ዯህንነት ምርምርና ሌማት

ግቦች የማስፈጸሚያ ስሌቶች የሚመራው ተባባሪ አካሌ የሚከናወንበት


አካሌ ጊዜ
ቁሌፍ የኢንፎርሜሽን መሰረተ ሌማቶችን ቁሌፍ የመሰረተ ሌማቶች ከጥቃት መከሊከሌ የሚያስችለ በጥናት  ኢመዯኤ  የከፍተኛ ት/ት
ዯህንነት ሇማረጋገጥ የሚያስችለ ምርቶችና እና ምርምር የተሇዩ ሀገራዊ አሻራ ያሊቸው አስፈሊጊ  ብሔራዊ ተቋማት ከ2013 ጀምሮ
ቴክኖልጂዎች ሇተጠቃሚዎች እንዱዯርሱ ይዯረጋሌ፤ የሳይበር  ሳይንስ እና
አገሌግልቶች በምርምርና ሌማት ሊይ ዯህንነት
አዲዱስ ምርት እና አገሌግልቶች በዘርፉ እንዱበራከቱ የሳይበር ኢኖቬሽን
የተመሰረቱ ማዴረግ፤ ም/ቤት ሚኒስቴር
ዯህንነት ምርምርና ሌማት ሇማጠናከር የተሇያዩ ማበረታቻዎች
ይሰጣለ፤
የሳይበር ዯህንነት ተጋሊጭነቶች፣ ስጋቶች የምርምርና ሌማት ስራዎችን ሇማከናወን የሚያስችሌ እውቀት፣  ከከፍተኛ
ክሀልት፣ ሌምዴ እና የቴክኖልጂ አቅም ይገነባሌ፤ ትምህርት ከ2013 ጀምሮ
እና ጥቃቶች መንስዔዎቻቸውን በጥናትና ተቋማት(የመንግስ
በተሇያዩ የምርምር ተቋማት፣ የዯህንነት ተቋማት እና
ምርምር መሇየት፤ መፍትሄዎች ማቅረብ፤ ዩኒቨርሲቲዎች የሳይበር ዯህንነት እንዲስፈሊጊነቱ የሌህቀት ት እና የግሌ)
ማዕከሊት ይቋቋማሌ፤  የምርምር
በሳይበር ምህዲር ውስጥ ባለ ተዋናዮች መካከሌ ያሇው ትብብር ተቋማት
በማጠናከር የተቀናጀ የሳይበር ዯህንነት ምርምር እና ሌማት  የዯህንነት ተቋማት
አቅም ሇመገንባት የሚያስችለ ወቅታዊነታቸውን የጠበቁ  ሳይንስ እና
የእውቀትና የሌምዴ ሌውውጥ መዴረኮች፣ ኮንፈረንሶችና ኢኖቬሽን
ፕሮግራሞች ይካሄዲለ፤ ሚኒስቴር
የሳይበር ዯህንነት ሇማረጋገጥ ሃገር በቀሌ የሳይበር ዯህንነት የምርምር እና ሌማት ተግባራትን  ከከፍተኛ
ከሚመሇከታቸው የመንግስትና የግሌ ተቋማት እና ከፍተኛ ትምህርት
ዕውቀት እና ፈጠራዎችን መሰረት ያዯረገ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባብር ይፈጸማሌ፤ ተቋማት(የመንግስ
የምርምር እና ሌማት አቅም መገንባት፤ ብሄራዊ የምርምርና ሌማት ፍኖተ-ካርታ ሇሳይበር ዯህንነት ት እና የግሌ)
በማዘጋጀት ይሰራሌ፤  የምርምር
ተቋማት
ምርምር እና ፈጠራ የሚያበረታቱ የሳይበር ዯህንነት ጋር  ሳይንስ እና
የተያያዙ ፕሮግራሞችን ይቀረፃለ፤ ኢኖቬሽን
ሚኒስቴር
38
በዓሇም አቀፍ ዯረጃ ተወዲዲሪ የሆነ እና የግሌ ሴክተሩ በአገሪቱ የሳይበር ዯህንነት ምርምር እና ሌማት  ኢመዯኤ  ከፍተኛ
ፕሮግራሞች እንዱሳተፉ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራሌ፤ የትምህርት ከ2012 ጀምሮ
የተቀናጀ ሃገራዊ የሳይበር ዯህንነት ተቋማት(የመንግስ
ቁሌፍ የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ሌማቶችን ተጋሊጭነትና ጥቃት
ምርምርና ሌማት ባህሌ መገንባት፤ ት እና የግሌ)
ሇመከሊከሌ በሚያስችሌ ሁኔታ በቀጣይነት በምርምርና ሌማት
 ቁሌፍ መሰረተ
ይዯገፋሌ፤
ሌማት ያሊቸው
ተቋማት
 የምርምር
በብሄራዊ ዯህንነት ሊይ ጉዲት ሉያዯርሱ የሚችለ በሳይበር ተቋማት
 ሳይንስ እና
ዯህንነት ጉዲዮች ዙሪያ ሌዩ ትኩረት በመስጠት የምርምር እና
ከፍተኛ ት/ት
የሌማት ተግባራት ይከናወናለ፤ ሚ/ር
በሃገሪቱ ሇስጋት ሀይልች ጥቃት የማይበገር የሳይበር ክሌሌ
እንዱኖር ጠንካራ የሆነ የሳይበር ዯህንነት እንደስትሪ ሇመገንባት
በጥናትና ምርምር ይዯገፋሌ፤

39
የትኩረት አቅጣጫ 5፦ ዲጂታሌ ማንነት እና ግሊዊ መረጃ ጥበቃ
ግቦች የማስፈጸሚያ ስሌቶች የሚመራው ተባባሪ አካሌ የሚከናወንበት
አካሌ ጊዜ
በዜጎች ዘንዴ ታዓማኒነት ያሇው የዱጂታሌ የግሊዊ መረጃ ዯህንነት ማረጋገጥ የሚያስቸለ አቅሞች፣ ተቋማዊ  ኢመዯኤ  ፌዯራሌ ፍርድ
ማዕቀፎች፣ የህግ እና የቁጥጥር አሰራር ስርዓቶች በቅንጅት  ብሔራዊ ቤት ከ2013 ጀምሮ
አገሌግልት እና ግሊዊ መረጃ ጥበቃ የሳይበር  ሰብአዊ መብት
ተግባራዊ ይዯረጋሌ፤
እንዱኖር ማዴረግ፤ ዯህንነት ኮሚሽን
አስተማማኝ የሳይበር ዯህንነት ቴክኖልጂ እና ገሇሌተኛ የዲታ ም/ቤት  ፍትህ አካሊት
ፕራይቪሲ ህግ ማስተዋወቅ፣ ህጋዊ የመረጃ አሰባሰብ አሰራር እና
መቆጣጠርያ መመሪያ ይዘጋጃሌ፤
በግሊዊ መረጃ ጥበቃ እና በሳይበር ዯህንነት ማረጋገጥ መከካሌ
ያለ ተቃርኖዎችን ሇማስታረቅ የሚያስችለ አሰራሮች
ይተገበራለ፤
የግሇሰቦች መረጃ የሚሰበስቡ፣ ፕሮሰስ የሚያዯርጉ እና  ሁለም
የሚያከማቹ ተቋማትምንዓይነትኢንፎርሜሽን፣ከማን፣ የመንግስት እና ከ2012 ጀምሮ
እንዳትመሰብሰብ፣ፕሮሰስማዴረግ፣መጠቀም፣ማከማቸት፣ ቁሌፍ የግሌ
ተቋማት
እናማስወገዴእንዲሇባቸው በየጊዜው የማንቃት ስራ ይሰራሌ፣
 የፍትህ አካሊት
መንግስታዊያሌሆኑተቋማትበሌዩሁኔታየግሇሰቦችንግሊዊነት መብት
መጠበቅየሚያስችሌአሰራርበሚያወጧቸውየሳይበርዯህንነትህጎች፣
መመሪያዎች፣ዯንቦችእናላልችየአሰራርስርዓቶችእንዱካተቱ
የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት፡
የሚመሇከታቸው ተቋማት የዜጎችን ግሊዊመረጃ በተመሇከተ
በቀጣይነት ክትትሌ እናየትንተናስራተግባራዊ ይዯረጋሌ፤
ኤላክትሮኒክ የመንግስት አገሌግልቶች ዯህንነት ሇመጠበቅ
የሚያስችሌ ስርዓት ይዘረጋሌ፤ ተግባራዊ ይዯረጋሌ፤

40
ሃገሪቱ በዱጂታሌ ግሊዊ መረጃ አጠባበቅ ዙሪያ ያሊትን ክፍተት  ኢመዯኤ  ሁለም
ሇመሙሊት ከዓሇም አቀፍየግሇሰብ መረጃ ስምምነቶች፣  የውጭ የመንግስት እና
ከህግማዕቀፎችና ፖሉሲዎች ጋር የተጣጣመ የአሰራር ስርዓት ጉዳይ ቁሌፍ የግሌ
ሚ/ር ተቋማት
መዘርጋትና ተግባራዊ ማዴረግ፤
 የውጭ ጉዳይ
ሚኒስትር
ማንነትን መሰረት ያዯረጉ በዱጂታሌ የዱጂታሌ የጥሊቻ ንግግር፣ ፅሁፍ እና ላልች ተያያዥ ጉዲዮችን  ኢመዯኤ  የፍትህ አካሊት
የሚፈጸሙ የሃይማኖት ጽንፈኝነት፣ የብሄር የሚከሇክሌ፣ አግባብነት ያሇው የሳይበር አጠቃቀም የሚያበረታታ  ሰሊም  የሚዲያ አካሊት 2013 ጀምሮ
ሚ/ር  ሰሊም ሚ/ር
ተኮር ጥቃቶችንና የመሳሰለትን መግታትና ዯንቦችና አሰራር ስርዓት ይተገበራሌ፤  ከፍተኛ
መከሊከሌ፤ ትምህርት
ተቋማት(የመንግስ
በታዲጊዎች ሊይ የሚዯርሱ የሳይበር የታዲጊዎች የዱጂታሌ መብት ጥሰት መከሊከሌ የሚያስችሌ ት እና የግሌ)
የክትትሌ አቅም እንዱኖር ይሰራሌ፣  ትምህርት ሚ/ር
ስጋቶችን፣ ተጋሊጭነቶችንና ጥቃቶችን
 ሰብዓዊ መብት
መከሊከሌ፤ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ እሴቶችና ተቋማት በአወቃቀራቸው የታዲጊዎች ዱጂታሌ መብት እውቅና
ኮሚሽን
በመሌካም ስብዕና ታንፀው እንዱያዴጉ የሰጠ አወቃቀር እንዱኖራቸው ይሰራሌ፣
ሳይበር ሉጫወተው የሚገባ ገንቢ ሚና
ማሳዯግ፤
በሳይበር ምህዲር ሊይ የሚዯርስ ጾታዊ በታዲጊዎችና ሴቶች የዱጂታሌ ማንነትና ግሊዊ መረጃ ጥበቃ  ኢመዯኤ  ሁለም
ጥቃት፣ ወሲባዊ ትንኮሳ፣ የሥነ-ሌቦና ሇማጠናከር ማህበረሰቡን ያሳተፈ ህዝባዊ ንቅናቄዎች በተሇያዩ  ሴቶች፣ የመንግስት
መገናኛ ብዙሃን፣ መዴረኮች፣ ኮንፍረንሶች እና ወርክሾፖች ወጣቶች ተቋማት
ተፅዕኖ መከሊከሌ እና መቀነስ፤ እና  ሁለም
ይዘጋጃለ፤
ህጻናት መንግስታዊ
የሳይበርግሊዊነትዯህንነትአስፈሊጊነትሊይእውቅናየሚሰጡሰፋፊየምክ ሚ/ር ያሌሆኑ ተቋማት
ክርመዴረኮችይመቻቻለ፡  የፍትህ አካሊት

41
የትኩረት አቅጣጫ 6፦ቁሌፍ የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ሌማቶች ጥበቃ

ግቦች የማስፈጸሚያ ስሌቶች የሚመራው ተባባሪ አካሌ የሚከናወንበት


አካሌ የጊዜ ሰላዳ
ቁሌፍ መሰረተ-ሌማቶች እና ተቋማት ሊይ ቁሌፍ የመንግስትና የግሌ ተቋማትን ሳይበር ዯህንነት ሉያስጠብቅ  ኢመዯኤ  ሁለም
ሉዯርሱ የሚችለ ስጋቶች፣ ተጋሊጭነቶች፣ የሚችሌ የተቀናጀ ሀገራዊ የሳይበር ዯህንነት ሥርዓት ተግባራዊ  የሳይበር የመንግስት እና 2013 ጀምሮ
ጥቃቶችና ውዴመቶችን የመሇየት፣ ማዴረግ። ዯህንነት ቁሌፍ የግሌ
የመከሊከሌ እና ምሊሽ የመስጠት አቅም ቁሌፍ የኢንፎርሜሽን መሰረተ ሌማቶችንና ሉዯርሱባቸው ም/ቤት ተቋማት
የሚችለትን ጥቃቶችን የሚሇይና አፋጣኝ መሌስ የሚሰጥ አካሌ  የፍትህ አካሊት
ማጎሌበት፤
ይቋቋማሌ፤ ተቋሙን የሚያጠናክሩ የአሰራር ስርዓቶች እና
አቅጣጫዎች ይዘረጋለ፤
ብሔራዊ የቁሌፍ መሰረተ-ሌማቶች ዯህንነት አመራር ስርዓት
ይዘጋጃሌ፤ ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር በሚጣጣም መሌኩ
በቀጣይነት ይሻሻሊሌ፤
ቁሌፍ መሰረተ-ሌማቶችን ሇመጠበቅ የመንግስት እና የግሌ
ተቋማት ዓሇም አቀፍ ዯረጃቸውን የጠበቁና ሀገራዊ አውዴ
ያገናዘቡ የሳይበር ዯህንነት ሕግጋት፣ ፖሉሲዎች፣
ስታንዲርድችና፣ ማዕቀፎች ስራ ሊይ ይውሊለ፤
ቁሌፍየኢንፎርሜሽን መሰረተ-ሌማት ተቋማት ዓሇም-አቀፍ ይዘት
ካሊቸው የኢንፎርሜሽን ዯህንነት ስታንዲርድችና የአሰራር
ሥርዓቶች ጋር የተጣጣመ መርሃ-ግብሮች እንዱቀርፁና የስራ
ሂዯቶቻቸው አካሌ እንዱያዯርጉ ይዯረጋሌ፤
ሇሚመሇከታቸው አካሊት በቁሌፍ መሰረተ-ሌማቶች ሊይ ሉዯርሱ
የሚችለ ስጋቶች፣ ተጋሊጭነቶች፣ ጥቃቶችና ውዴመቶችን
ሇመሇየት፣ ሇመቀነስ፣ ሇመከሊከሌ እና ፈጣን ምሊሽ ሇመስጠት
ወቅታዊነታቸውን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስሌጠናዎች፣ የምክክር
መዯረኮች እና የመሳሰለት ይዘጋጃሌ፤ ይሰጣሌ፤

42
ሇቁሌፍ መሰረተ-ሌማቶች የሚውለ ሀገር በቀሌ የኢኮቴ
ምርቶችን የማምረት አቅም ይገነባሌ፤
ከውጭ የሚገቡ እና በሀገር ውስጥ ቁሌፍ የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ሌማቶች፣ የኢኮቴ ምርቶች እና ኢመዯኤ  ሳይንስና
የሚመረቱ ቁሌፍ የኢንፎርሜሽን መሰረተ- አገሌግልቶች ዯህንነት ሇመጠበቅ የሚያስችሌ የቴክኖልጂ ኢኖቬሽን ሚ/ር
ዯህንነት ቴክኒካዊ ስታንዲርድች ስራ ሊይ ይውሊሌ፤  ሁለም
ሌማት ምርቶችና አገሌግልቶች የመንግስት እና
ዯህንነታቸው የተጠበቀ እንዱሆን ማዴረግ፤ በማንኛውም ጊዜ የተጋሊጭነት ፍተሻና የኢንፎርሜሽንና ቁሌፍ የግሌ
የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ሌማት የዯህንነት ኦዱት እንዱካሄዴና ተቋማት
ፈጣን የማስተካከያ እርምጃ እንዱወስዴ ይዯረጋሌ፤

ሇቁሌፍ መሰረተ ሌማቶችና ስርዓቶች 24/7 አካሊዊና  ሁለም


ሇቁሌፍ የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ሌማቶች ምናባዊ ጥበቃ ይዯረጋሌ፤ የመንግስት እና 2013 ጀምሮ
ሌዩ ጥበቃ ሇማዴረግ የመንግስት እና የግሌ ቁሌፍ የግሌ
ተቋማት
ዘርፍ ትብብር እና ቅንጅት መፍጠር፤ ሇቁሌፍ መሰረተ-ሌማቶች ሌዩ ጥበቃ ሇማዴረግ የሁለም  ሚዲያ አካሊት
ባሇዴርሻ አካሊት ተግባራትና ኃሊፊነቶች በመሇየት ይሰጣሌ፤  ጸጥታ አካሊት

43
የትኩረት አቅጣጫ 7.1 ፦ሃገራዊ ቅንጅት እና አጋርነት

ግቦች የማስፈጸሚያ ስሌቶች የሚመራው ተባባሪ አካሌ የሚከናወንበት


አካሌ ጊዜ
የሳይበር ዯህንነት ቅንጅት እና አጋርነት የሚመራ ሥርዓት  ኢመዯኤ  ሁለም
ሀገራዊ ሳይበር ዯህንነትን ሇማረጋገጥ ይዘረጋሌ፤ ተግባራዊ ይዯረጋሌ፤  ብሔራዊ የመንግስት እና ከ2013 ጀምሮ
በመንግስት፣ በግለ ዘርፍ እና ሀገራዊ የሳይበር ዯህንነት ፎረም ይቋቋማሌ፤ የሳይበር ቁሌፍ የግሌ
በሚመሇከታቸው ባሇዴርሻ አካሊት መካከሌ በሀገር ዯረጃ የሳይበር ዯህንነት ኮንፈረንሶች፣ ሴሚናሮችና መሰሌ ዯህንነት ተቋማት
ቅንጅትና አጋርነት መመስረትና ማጠናከር፤ ቅንጅትን የሚያጠናክሩ መርሃ ግብሮች በየጊዜው ይዘጋጃለ። ም/ቤት
በባሇዴርሻ አካሊት ዘንዴ የዴርሻና ኃሊፊነት ግሌጽነት ይፈጠራሌ፤  ሁለም
የሳይበር ዯህንነት ባሇዴርሻ አካሊት መካከሌ የሌምዴ ሌውውጥና የመንግስት እና ከ2013 ጀምሮ
ቁሌፍ የግሌ
የዕውቀት ሽግግር ስርዓት ይዘረጋሌ፤
ተቋማት
 የፍትህ አካሊት
 ዜጎች
 ሲቪክ ማህበራት
የመንግስትም ሆነ የግሌ ተቋማት ዴንገተኛ የኮምፒውተር ኢመዯኤ  ሳይንስና
አዯጋዎች መከሊከሌ ክፍሌ እንዱኖራቸውና በክስተቶች ዙሪያ (ኢትዮ ኢኖቬሽን ሚ/ር
የሌምዴ ሌውውጥ እንዱኖር ይዯረጋሌ፤ ሰርት)  ሁለም
የመንግስትም ሆነ የግሌ ተቋማት ዴንገተኛ የኮምፒውተር የመንግስት እና
አዯጋዎች መከታተያ ሥርዓታቸው ከብሄራዊ የኮምፒውተር ቁሌፍ የግሌ
አዯጋዎች መከታተያ ሥርዓት ጋር የተቀናጀ እና የሚመጋገብ ተቋማት
ይዯረጋሌ።
የሳይበር ዯህንነት ምርት በማምረትና አዲዱስ ተቋማት እንዱፈጠሩና ያለት ተቋማት እንዱጠናከሩ ኢመዯኤ  ሁለም
አገሌግልት በማቅረብ ሊይ የተሰማሩ ሀገር በቀሌ የሚያግዝ መርሃ ግብሮች ይቀረጻለ፤ ተግባራዊ ይዯረጋለ፤ የመንግስት እና ከ2013 ጀምሮ
የግሌ ተቋማት እንዱጨምሩና እንዱጠናከሩ ቁሌፍ የግሌ
በማዴረግ የሀገሪቱን የሳይበር ዯህንነት ምርትና ሇህብረተሰቡ አገሌግልት የሚውለ የሳይበር ዯህንነት ውጤቶችን ተቋማት
አገሌግልት ፍሊጎት ከማርካት አሌፈው በዓሇም ሇሚያመርቱ ተቋማት ዴጋፍ ይዯረጋሌ፤  ሚዲያ አካሊት
አቀፍ ገበያዎች ሊይ ተወዲዲሪ እንዱሆኑ ዯረጃቸውን የጠበቁ የሳይበር ዯህንነት ምርትና አገሌግልቶች  ጸጥታ አካሊት
በሀገሪቱ ገበያ ቅዴሚያ ማግኘት የሚችለበት ዴጋፍ ይመቻቻሌ፤

44
ማስቻሌ፤ በዓሇም አቀፍ ገበያዎች ሊይ ተወዲዲሪ እንዱሆኑ የሚያግዝ ዴጋፍ
ይዯረጋሌ፤

ግቦች የማስፈጸሚያ ስሌቶች የሚመራው ተባባሪ አካሌ የሚከናወንበት

የትኩረት አቅጣጫ 7.2፦ዓሇም አቀፍ ትብብር

45
አካሌ የጊዜ ሰላዳ
የሳይበር ወንጀሌ፣ ሽብርተኝነት፣ ስሇሊ እና በሳይበር ዯህንነት ዙሪያ የሚኖሩ ዓሇም-አቀፋዊ የትብብርና  ኢመዯኤ  የውጭ ጉዳይ
መሰሌ ዓሇም-አቀፍ ይዘት ያሊቸው የሳይበር የአጋርነት ስምምነቶች እንዯ አስፈሊጊነታቸው ይፈረማሌ፤  ብሔራዊ ሚ/ር ከ2013 ጀምሮ
የሳይበር  የፍትህ አካሊት
ዯህንነት ስጋቶች ሇመከሊከሌ ትብብር ዯህንነት  ሰሊም ሚ/ር
የሳይበር ጥቃቶችን ሇመመከት ከተሇያዩ ሀገራትና ዓሇም አቀፍ
መፍጠር፤ ም/ቤት  የተሇያዩ በሳይበር
ዴርጅቶች ጋር የሌምዴ ሌውውጥ የሚዯረግባቸው መንገድች
ዯህንነት ዙሪያ
ይመቻቻሌ፤ የተሰማሩ ዓሇም
ዴንበር ተሻጋሪ የሳይበር ወንጀልች፣ ሽብርተኝነቶች፣ ስሇሊና አቀፍ
መሰሌ ጥቃቶችን ሇመከሊከሌ የሚያስችለ በሃገራት መካከሌ  ኢንተር ፖሌ
የመረጃ ሌውውጥ እና የቴክኒካሌ ዴጋፎች ይዯረጋለ፤
የሳይበር ዯህንነትን የውጪ ጉዲይ ፖሉሲ አካሌ ሆኖ  ኢመዯኤ  የውጭ ጉዳይ ከ2013 ጀምሮ
በሳይበር ዯህንነት ዙሪያ የሚዯረግ ዓሇም እንዱሰራበት ይዯረጋሌ፤ ሚ/ር
ዓሇም-አቀፍ በሆኑ የሳይበር ዯህንነት ትብብር መዴረኮች ሊይ  የፍትህ አካሊት
አቀፍ ትብብር የሃገሪቱ የውጪ ጉዲይ  አሇም አቀፍ
ዱፕልማሲ አካሌ እንዱሆን ማዴረግ፤ ንቁ ተሳትፎ ይዯረጋሌ፤
የሳይበር ዯህንነት
ዙሪያ የተሰማሩ
ተቋማት
ሁሇትዮሽና ከዚያ በሊይ የሆኑ የሳይበር በሳይበር ዯህንነት ጉዲዮች ሊይ ብቃት ያሊቸውን የሰው ኃይሌ  ኢመዯኤ  የውጭ ጉዳይ
ሇመፍጠር ዓሇም አቀፍ ስሌጠናዎች ይመቻቻሌ፤  ብሔራዊ ሚ/ር
ዯህንነት ስምምነቶችን ማበረታት እና የሳይበር  ሳይንስና
ማጎሌበት፤ የግሌና የመንግስት ተቋማት ከላልች ሀገራት መንግስታትና ዯህንነት ኢኖቬሽን ሚ/ር
የግሌ ተቋማት ጋር ያሊቸውን የሳይበር ዯህንነት ቁርኝት ተገቢ ም/ቤት  ሁለም
የመንግስት እና
በሆነ መሌኩ እንዱያጠናክሩ ሁኔታዎች ይመቻቻሌ፤
ቁሌፍ የግሌ
የሳይበር ዯህንነት ትብብር ሇመፍጠር የሚያስችሌ ሃገራዊ አቅም ተቋማት
ይገነባሌ፤  አሇም አቀፍ
የሳይበር ዯህንነት
ዙሪያ የተሰማሩ
ተቋማት

46
47
48

You might also like