You are on page 1of 5

የኢፌድሪ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አገልግሎት አሰጣጥ

ማሻሻያ ካውንስል የተሸከርካሪ ሰሌዳ አሰጣጥ አገልግሎትን


በተመለከተ ከተገልጋዮች በሰበሰበው መረጃ መሰረት የተሰጠ ትንተና

መያዝያ 2014 ዓ.ም


የተሸከርካሪ ሰሌዳ አሰጣጥ አገልግሎትን በተመለከተ
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ካውንስል በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የተሸከርካሪ ሰሌዳ
አገልግሎት አሰጣጥ ስርአት በተመለከተ መረጃ በመሰብሰብ በዚህ ጥናት ተካታች አድርጓል፡፡

1
በጥናቱ መጀመሪያ የተዳሰሰው ተገልጋዮች የሰሌዳ አሰጣጥ ስርአቱን እንዴት እንደሚመዝኑት ማረጋገጥ ሲሆን በዚህም 43%
ያህል ተገልጋዮች የሰሌዳ አሰጣጥ ስርአቱ በቀላሉ የሚያልቅ የአሰራር ሂደት እንዳለው ጥቆማ ሲያደርጉ በተመሳሳይ 43%
የሚሆኑ ተገልጋዮች ደግሞ የሰሌዳ አሰጣጥ ስርአቱ ቅልጥፍና እንደተሸከርካሪው አይነት የሚወሰን እንደሆነ የገለጹ ሲሆን
የተቀሩት 13.8% ተገልጋዮች ደግሞ የሰሌዳ አሰጣጥ የአሰራር ሂደት ጊዜ የሚወስድ መሆኑን በጥናቱ የሰበሰብነው መረጃ
ያመለክታል፡፡
ስለዚህም ከተወሰደው የጥናቱ ናሙና ላይ መገንዘብ እንደሚቻለው የተሸከርካሪ ሰሌዳ አሰጣጥ አገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍና
እንደ ተሸከርካሪው አይነት የሚወሰን ቢሆንም አብዛኛው ተገልጋይ ህብረተሰብ በአስፈላጊው ፍጥነት አገልግሎቱን ማግኘት
እንደሚችል ጥናቱ ያሳያል፡
ጥናቱ በቀጣይነት ተገልጋዮች ሰሌዳ ለማግኘት የሚወሰደባቸው ጊዜ በተመለከተ ዳሰሳ ያደረገ ሲሆን በዚህም 83.3% ያህል
ተገልጋዮች ሰሌዳ ለማውጣት ከአንደ ሳምንት ያነሰ ጊዜ እንደሚወስድባቸው በጥናቱ ላይ ሲያሳዩ የተቀሩት 10%፣ 3% እና
3.7% ደግሞ ሰሌዳ አግኝቶ ለመረከብ ከሁለት እስከ ሶስት ሳምንት፣ከአንድ እስከ ሁለት ሳምንት እና እና ከወራቶች በላይ ጊዜ
ቸእንደሚፈጅባቸው በተከታታይ ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡
ስለዚህም ተገልጋዮች በአብዛኛው ሰሌዳ ለማግኘት ከአንድ ሳምንት ያነሱ ቀናት እንደሚፈጅባው ጥናቱ ያረጋግጣል፡፡
በቀጣይነት ሰሌዳ ለማግኘት የሚወስደው ጊዜ አሁን ካለበት በተሻለ ቅልጥፍና ተደራሽ ማድረግ ያልተቻለበትን ምክንያት
የተዳሰሰ ሲሆን ለዚህም ተከታዮቹ ምክንያቶች በጥናቱ ላይ ተገልጸዋል፡፡
 22% ከአሰራር ግድፈት ጋር የተያያዘ እንደሆነ
 36% ከጉምሩክ ጋር ተያይዞ ባለ የተጓተተ የአሰራር ሂደት ምክንያት
 42% አገልግሎቱ ከሚሰጥበት አጠቃላይ ሲስተም ጋር በተያያዘ
ስለሆነም ጥናቱ እንደሚያሳየው ከሰሌዳ አሰጣጥ ስርአት ጋር በተያያዘ ላለው የአሰራር ቅልጥፍና ግድፈቶች ትልቁን ድርሻ
የሚይዘው አገልግሎቱ ወደ ተገልጋይ ህብረተሰቡ ተደራሽ የሚሆንበት የአሰራር ሂደት ሲስተም እና ከጉምሩክ ጋር በተያያዘ
ያለው አሰራር መሆኑን ጥናቱ ያረጋግጣል፡፡
የተሸከርካሪ ሰሌዳ አሰጣጥና ምትክ ማውጣት ወጥ የሆነ የአሰራር ስርአት እንዳለው ማረጋጋገጥ ሌላው የጥናቱ አላማ ሲሆን
በዚህም መሰረት በጥናቱ ከተሰበሰበው ናሙና 76.66% ያህሉ አገልግሎቱ ወጥ የሆነ የአሰራር ሂደትን እንደሚከተል
አረጋግጧል፡፡
ስለዚህም ምንም እንኳን 23.34% ያህል ተገልጋዮች የተሸከርካሪ ሰሌዳ አሰጣጥ እና ምትክ ማውጣት ወጥ የሆነ የአሰራር
ሂደትን የተከተለ አለመሆኑን በጥናቱ ላይ ቢገልጹም አብዛኞቹ ተገልጋዮች ከሰሌዳ ማውጣት ጋር ተያይዞ ወጥ የሆነ የአሰራ
ሂደት መኖሩን የጠቆሙ በመሆኑ አገልግሎቱ ወጥ የሆነ የአሰራር ሂደት ተከትሎ ለተገልጋዮች በአብዛኛው ተደራሽ ይሆናል
ለማለት ያስችላል፡፡
ምትክ ሰሌዳ በሚያስፈልግበት ጊዜ ተመሳስለው ከሚሰሩ ሃሰተኛ ማስረጃዎች የተጠበቀ እና ከወንጀል የጸዳ የአሰራር ሂደት
የሰፈነ መሆኑን ማረጋገጥ ሌላው በጥናቱ የተዳሰሰ ጉዳይ ሲሆን በዚህም 86.66% ያህል የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች አሰራሩ
ከብልሹ አሰራር እና ከሃሰተኛ ማስረጃዎች የተጠበቀ መሆኑን በጥናቱ አመላክተዋል፡፡
ሆኖም የተቀሩት 13.34% ተገልጋዮች አገልግሎት አሰጣጡ ከሃሰተኛ ማስረጃዎች የተጠበቀ እና ከወንጀል የጸዳ አለመሆኑን
በጥናቱ ላይ ያመላከቱ በመሆኑ ሙሉለሙሉ ለማረጋገጥ ያልተቻለ መሆኑን ካውንስሉ ለማሳወቅ ይወዳል፡፡
ሌላው በጥናቱ ውስጥ ተካታች የተደረገው የሰሌዳ ጥራትን በተመለከተ ሲሆን በዚህም 73.33% ያህል የአገልግሎቱ
ተጠቃሚዎች ሰሌዳው ጥራቱን የጠበቀ እንዳልሆነ የገልጹ ሲሆን ይህንንም ያሉበትን ምክንያት የሚከተሉት ናቸው፡፡
 አመት ሳይሞላው ቀለሙ እየለቀቀ ለተጨማሪ ወጪና እንግልት የሚዳርግ መሆኑ
 የሰሌዳ ቁጥሩ ቀለም በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚደበዝዝ ብሎም የሚጠፋ መሆኑ

2
በተጨማሪም ተገልጋዩ ህብረተሰብ በአጠቃላይ የተሸከርካሪ ሰሌዳ አሰጣጥ አገልግሎት ላይ ያለውን አስተያየት በጥናቱ
ተካታች የተደረገ ሲሆን በዚህም ተከታዮቹ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡
 የመብራት ችግር በመኖሩ ተገልጋዩ የሚንገለሳታ በመሆኑ ይህንን መቅረፍ ቢቻል
 የፋይል አያያዝ ችግር ያለ መሆኑ
 የሰሌዳ አለመኖር የሚያጋጥም በመሆኑ መቅረፍ ቢቻል
 በሰው ወይም በዘመድ መስራት የተለመደ በመሆኑ ቢስተካከል
 እንግልት ያለው በመሆኑ ቢሻሻል
 በገንዘብ የመጨረስ ነገር የተስፋፋ በመሆኑ ትኩረት ቢሰጠው
 ቂርቆስ ክፍለከተማ መልካም አገልግሎት እና አሰራር ያለበት በመሆኑ ይቀጥልበት
 ሰሌዳ ለማውጣት የሚያስፈልጉ መረጃዎች ለህዝቡ በአግባቡ ቢደርስ ህብረተሰቡ ከመንገላታት የሚድን በመሆኑ
በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ይህ ታሳቢ ቢደረግ
 አገልግሎቱ የሚሰጥበት ሲስተም ከወረቀት የጸዳ ቢሆን የበለጠ መልካም ይሆናል
 ጥሩ የሆነ የአገልግሎት አሰጣጥ አለ በዚሁ ይቀጥል
 የመብራት መቆራረጥ ችግርን ተከትሎ የሚመጣ የአገልግሎት አሰጣጥ መስተጓጐልን መቅረፍ የሚቻልበትን
አማራጭ ማየት ቢቻል
 አጠቃላይ ሲስተሙ ቢሻሻል ወይም ቢቀየር
 ለአላስፈላጊ ምልልስ የሚዳርጉ አሰራሮችን ማሶገድ ቢቻል
 2 ቁጥር ሰሌዳ የለም እናም ይህ ቢስተካከል
 ያልተቀናጀ እና ያልተናበበ ብሎም ያልዘመነ አሰራር በመሆኑ ትኩረት ይሻል
 በአጠቃላይ በUN-UNCD የዲፕሎማት ሰሌዳዎች ላይ ያለው አሰራር ለሙስና ተጋላጭ በመሆኑ ለሃገርም ገጽታ
አደጋ በመሆኑ ተገቢው ጥናት ተደርጎ አሰራሩ ጥራትና ቅልጥፍና እንዲኖረው ማድረግ ቢቻል፡፡
 ከሞላጎደል ጥሩ ቢሆንም አጠቃላይ አገልግሎቱ ማሻሻያ ቢደረግበት
 በፊት ከነበረው አገልግሎት አሰጣጥ በእጅጉ የተሻለ ቢሆነም ይበልጥ ለማሳደግ ቢሰራበት
 በድርጅቱ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተሸለ አሰራር ቢኖር ብዙ ድርጅቶች ስራቸው እንዳይስተጓጐል አጋዥ ይሆናል፡፡

3
ታርጋ አሰጣጥን በተመለከተ
1.የሠሌዳ አሠጣጥ ስርዓቱ

በቀላሉ የሚገኝ ጊዜ የሚወስድ እንደ ተሽከርካሪው አይነት የሚወሰን

2. ሠሌዳ ለማግኘት ምን ያህል ጊዜ ወሰደቦት


አንድ ሣምንት ከ2‒ 3 ሣምንት ሌላ

ከ1‒ 2 ሣምንት ከ3‒ 4 ሣምንት

3. በእርስዎ አመለካከት የሠሌዳ አሠጣጡ ጊዜ የሚወስድ ከሆነ ምክንያቱ ምንድን ነው ብለው ያስባሉ

የአሠራር ግድፈት
ከገቢዎችና ጉምሩክ ጋር ባለ የተጓተተ የአሰራራ ሂደት
አገልግሎቱ የሚሰጥበት አጠቃላይ ሲስተም
ሌላ ___________________________________________________
4.የተሸከርካሪ ሰሌዳ አሰጣጥና ምትክ ማውጣት ወጥ የሆነ የአሰራር ስርአት አለው?

አዎ የለም
5. ሰሌዳው ጥራቱን የጠበቀ ነው ብለው ያምናሉ?

አዎ የለም

6.ምትክ ሰሌዳ በሚስፈልግበት ጊዜ ተመሳስለው ከሚሰሩ ሀሰተኛ ማስረጃዉች የተጠበቀና ከወንጀል የፀዳ አሰራር ሂደት አለ

አዎ የለም

7.የቀደመው ጥያቄ ላይ ምላሽዎ የለም ከሆነ እባክዎን ምክንያትዎን ያስረዱ

4
______________________________________________________________________________
______________________________________________________________________________
______________________________________________________________________________
________________________________________________________________________
8. በአገልግሎቱ አሰጣጡ ላይ ያልዎትን አጠቃላይ አስተያየት ያስፍሩ

_____________________________________________________________________________________
_____________________________________________________________________________________
____________________________________________________

You might also like