Professional Documents
Culture Documents
2009
2009
1. የቻርተሩ አላማ
የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ
ለዜጎች ጥራት ያለዉ አገልግሎት ለመስጠት
ግልፀኝነትንና ተጠያቂነትን በግልጽ ለማመላከት
2. የተቋሙ ስም የመተማ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት
የጽ/ቤቱ ራዕይ
የትምህርት ጽ/ቤቱ ራዕይ በስልጣኔ ፣ በልማት እና በዲሞክራሲ ባህሉ የላቀ ደረጃ ላይ የደረሰ ህብረተሰብ በወረዳው ተፈጥሮ ማየት
የጽ/ቤቱ ተልዕኮ
በወረዳው ትም/ትና ስልጠናን በስፋት ፣በጥራት እና በፍታሃዊነት በማዳረስ ፣የህብረተሰቡን አመራር ተሳትፎ ባረጋገጠ
አደረጃጀት ተነሳሽነቱ የጎለበተ፣በመብቱ የሚጠቀም፣ግዴታውን የሚወጣ፣ምርታማነቱ የዳበረ፣ለአጠቃላይ ልማት መምጣት ምክንያት
የሚሆን ሰብአዊ ሃብት ማፍራት
የጽ/ቤቱ እሴቶች
የዳበረ የዲሞክራሲ ባህል ስር እንዲሰድ ማድረግ
የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ
ቁጠባ ባህሉ የሆነ ዜጋ መፍጠር
የስራ ፍቅር፣ ከበሬታና መልካም ስነ- ምግባርን ማጎልበት
በራሱ ባህላዊ እሴት የሚኮራ፣ ቀጣይነት ላለው ለውጥና ዕድገት የሚተጋ ዜጋ መገንባት
ለሴቶችና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ቅድሚያ መስጠት
ለፈጠራና ምርምር ልዩ ትኩረት መስጠት
አመራር ሰጭነት
በግብ ስኬት ላይ ማነጣጠር (outcome based)
ደንበኛ ተኮር (Customer focused) መሆን
የአንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጅ (ICT) አጠናክሮ መጠቀም
አሳታፊነት
ችግር ፈቺነት (Problem Solving)
የማትጋት ሥርዓትን (Reward)ማጠናከር
ለስነ ምግባር መርሆዎች ተገዢ መሆን
በጋራ መስራት
አቅምን በማሳደግ በራስ መተማመን
የህብረተሰቡን ባህል ማክበር
በሂስና ግለሂስ ማመን
የጽ/ቤቱ ተገልጋዮች
የወረዳው የመንግስት ተቋማት
የወረዳዉ ት/ቤቶች
ሌሎች ዜጎች
1. አጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማስጠበቅ በውስጥ የተካተቱን 6 ቱ መርሃ ግብሮች ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፍና
ክትትል ማድረግ
2. የትምህርት ሽፋን ማሳደግ
3. የትምህርት ፍትሃዊነትን ማረጋገጥ
4. የትምህርት ብቃትን በማሻሻል
5. የተቋምት፣ የቡድኖች እና የግለሰብ ስትራቴጂያዊና ዓመታዊ የአፈፃፀም ግቦች ተመጋጋቢና እንዲተሳሰሩ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል
ለማድረግ
6. ለት/ቤቶች እድገት ህብረተሰቡ ቀጥታ ተሳታፊ እንዲሆን መቀስቀስ መስተባበር
7. የጽ/ቤት ባለሙያና የመ.ር.ሱ.የረዥምና የአጭር ጊዜ ስልጠናዎችን ማስተባበር
8. ሙያዊ ድጋፍ ለሚጠይቁ ለጽ/ቤት ባለሙያና ለመ.ር.ሱ. ሙያዊ ድጋፍ መስጠት
9. በሚመጡ አገልግሎቶች ላይ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት
10. የመ.ር.ሱ ፣የተማሪዎችና የጽ/ቤት ሰራተኞችን ስታስቲካዊ መረጃ ማጠናከር
11. የሰው ኃይል አስተዳደር ተግባሮች ይፈጸምልን ጥያቄዎች ተቀብለው መፈጸም
የዜጎች ቻርተር
በመተማ ወረዳ ትምህርት
ግልፀኝነት (Transparency)
ተደራሽነት ( Accessiblity )
አገልግሎታችን በስራ ሂደቶቻችን የስራ ሂደት ጥናት ባስቀመጥነው ተደራሽ ግብ መሰረት እስከ ታችኛው
የአስተዳደር እርከን እንዲደርስ ይደረጋል ፡፡
ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት የማስተካከያ የዳሰሳ ጥናቶች አስቀድመን በማካሄድ በመረጃ ላይ ተመስርተን
ችግሮችን እንከላከላለን፡፡
ዉጤታማነት (Effectiveness )
አገልግሎት አሰጣጣችን በመመሪያው ተልዕኮና ራዕይ በሚያሳኩ ተግባራት ላይ ያተኮረ ይሆናል ፡፡
የተገልጋዮች መብቶች
ለተገልጋዮቻችን የምንገባው ቃል
አስተያየትና ግብዓት
- ተገልጋዮች በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ በአካል ፣ በሚዲያ፣ በሃሳብ መስጫ መዝገብ ፣ በሀሳብ መስቻ ሳጥን እና
የተለያዩ የምክክር መድረኮችን በመጠቀም አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ይደረጋል
- ለተገልጋዮች የተገኘውን አስተያየት በመገምገምና እንደ ግብዓት በመጠቀም ግብረ- መልስ እንሰጣለን
የተሳትፎ ሂደት
ጽ/ቤቱ የምክክር መደረክ በየሩብ ዓመቱ በማዘጋጃት በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ ተገልጋዮችን በቀጥታ
እናሳትፋለን ፡፡
ተገልጋይ ባገኘው አገልግሎት ካልረካ ቅሬታውን አገልግሎቱን ለሰጠው ባለሙያ የቅርብ ኃላፊ ማቅረብ የሚችል
ሲሆን በዚህም ካልረካ የቅሬታው መንስኤ ለተከሰተበት ቀን ጀምሮ በ 10 የስራ ቀናት ዉስጥ ለፑሉ አገልግሎት
አሰጣጥና ቅሬታ ሰሚ ባለሙያ ያቀርባል ፡፡
የቅሬታ ባለሙያውም የአሰራር ሂደቱን ተከትሎ ለቀረበው ቅሬታ እጅግ ቢዘገይ በ 3 የስራ ቀናት ውስጥ
ያቀርባል ፡፡ በዚህም ካልረካ ለአስተዳደር ፍ/ቤት ማቅረብ ይችላል
ጽ/ቤቱ በቻርተሩ ላይ በተቀመጡት መሰረት ዜጋው አገልግሎት ስለማግኘቱ በክትትልና ድጋፍ ያረጋግጣል፡፡
በዚህም ኃላፊነት ያለባቸው የስራ ሂደት አስተባባሪዎችን ፈጻሚዎች በቻርተሩ መሰረት ስለመፈጸማቸው በልማት ሰራዊት
አግባብ በየሳምንቱ በመገምገም ሪፖርት ለተቋሙ ኃላፊ ያቀርባሉ ፡፡
በየወቅቱ በቀረቡት ክትትልና የግምገማ ሪፖርቶች ላይ በመመስረት የእርምትና የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል፡፡
በወቅታዊ መረጃዎች ፣በሚዲያ ፣ በበራሪ ጽሁፍ ፣ በመጽሄት ፣ በፋክስ፣ በፖስታ ቤት ፣ በመረጃ ማዕከል
አጋዥነት በአካል ፣ በስልክ ፣ በኢሜል ፣ መደበኛ የተገልጋይ መድረኮች በአካል በመገኘት ወዘተ የመሳሰሉት
ይሆናል፡፡