You are on page 1of 151

ታሊ

መሠረታዊ
የቢዝነስ ክህሎት
ሥልጠና

የአሰልጣኞች መጽሐፍ
ትርጉም ፡ እምነትን መሰረት ያደረገ

ቋንቋ ፡ ዓማርኛ

ህትመት ፡ 2012 ዓ.ም


የአሳታሚው መብት በየትኛውም ሀገር መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ያለ ታሊ እና አልትርኔቲቭ የጽሑፍ ፈቃድ ይህን መጽሐፍ በማንኛውም መልኩ በከፊልም እንኳ ቢሆን ለመገልበጥና ለማስቀመጥ߹ ወይም
በኤሌክትሮኒክ߹ በሜካኒካል߹ በፎቶኮፒ߹ በድምጽ ወይም በሌላ መንገድ በመቅዳት (በመገልበጥ)߹ በመተርጎም ለመጠቀም መሞከር በህግ
ያስጠይቃል ፡፡

በሰሜን አሜሪካ ( U.S.A ) የታተመ

የቅጂ መብት © 2020 ታሊ

በመጀመሪያ ከአልትርኔቲቭ ግሎባል አንተርፐረነርስ ተወስዶና እንዲጣጣም ተደርጎ እንደገና የታተመ፡፡


የቅጂ መብት © 2018 በአልትርኔቲቭ

2914 ቤከን ጎዳና፣ ኮሎራዶ ሰፕሪንግስ፣ ሲኦ 80907

719-354-9986
info@alternativeproject.org // www. alternativeproject.org

1
ማውጫ
PREPARATION // Overview 3
PREPARATION // Planning Your Training 6

TEACHING SESSIONS (session lengths are approximate)


SESSION 1 // Course Introduction (.5 Hours) 15
SESSION 2 // Dream Big (1 Hour) 18
SESSION 3 // Overcoming Obstacles (1 Hour) 24
SESSION 4 // Business Basics 1 (1 Hour) 32
SESSION 5 // Business Basics 2 (1 Hour) 39
SESSION 6 // Marketing 1 (1.5 Hours) 44
SESSION 7 // Marketing 2 (1.5 Hours) 53
SESSION 8 // Customer Service (1 Hour) 61
SESSION 9 // Pricing (1.5 Hours) 68
SESSION 10 // Comparative Advantage (1 Hour) 79
SESSION 11 // Recordkeeping (1.5 Hours) 85
SESSION 12 // Building Business Budgets (1 Hour) 92
SESSION 13 // Building Household Budgets (1 Hour) 98
SESSION 14 // Savings for Businesses (2 Hours) 104
SESSION 15 // Savings for Households (1.5 Hours) 113
SESSION 16 // Ethics (1 Hour) 120
SESSION 17 // Leadership (1 Hour) 126
SESSIONS 18 // Review, Action Plan, and Graduation 133

RESOURCES // Forms, Certificates, and References 139

2
አጭር መግለጫ
ወደ ታሊ መሠረታዊ የቢዝነስ ስልጠና እንኳን በደህና መጡ! ይህ ስልጠና በዓለም ዙሪያ ባሉ የአገልግሎቱ
አጋሮችቻችን አማካኝነት ምንም ቋሚ የገቢ ምንጭ የሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች አነስተኛ የንግድ
ሥራዎችን መጀመር የሚያስችሉ ግብዓቶችን በማሟላት የተሻለ ውጤታማ ለማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡

ታሊ ማን ነው?
ተች ኦቭ ላቭ ኢንተርናሽናል ወይም ታሊ ወደ ተለያዩ የዓለማችን ማህበረሰብ ውስጥ በመግባት፤ እንደ እርስዎ
ካሉ አጋሮቻችን ጋር በመሆን አነስተኛ ብድሮችንና የቢዚነስ ስልጠናዎችን በመስጠት፤ እንዲሁም የክርስቶስ
ደቀመዛሙርትን በማፍራት፤ሰዎች ከገቡበት የድህነት አዙሪት ለማውጣትና የቀደመ ክብራቸውን ለመመለስ
የሚተጋ ክርስቲያናዊ አበዳሪ ድርጅት ነው፡፡ ፕሮግራማችንም ሆነ ይህ ስልጠና ከዚህ በታች በተገለጹ እሴቶች
ላይ የተመሰረ ነው፡-

> ክብር- ማንኛውም ሰው የተወለደው ከክብርና ከፈጠራ ክህሎት ጋር እንደሆነ እናምናለን፡፡ እናም ሴቶች ሆኑ
ወንዶች ለቤተሰቦቻቸው ብሎም ለማህበረሰባቸው ዓላማ መር አገልግሎት ሰጭዎች እንዲሆኑ
የሚያስችሏቸውን እነዚህን ክህሎቶች የማዳበርና የማብቃት ስራ እንሰራለን፡፡

> ዘላቂነት. አንድ ሰው የተሰጠውን አነስተኛ ብድር በተባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ ከፍሎ ሲያጠናቅቅ፡
በአካባቢው የተሻለ የህይወት ለውጥ እንዳመጣና እንደመጨረሻ አማራጭ ተቆጥሮ፤ታሊ የተመለሰውን ገንዘብ
ለሌሎች በአካባቢው ላሉ ሰዎች “እንደገና በማበደር ጥቅም ላይ ያውለዋል” ፡፡

> ወንጌል። የእያንዳንዱን ደንበኛ ቁሳዊ፣መንፈሳዊ፣ስሜታዊ እና ማህበራዊ ገሃዶችን ለመድረስ ክርስቶስን


ማዕከል አድርገን የምንዘረጋ ሁሉን አቀፍ መንፈሳዊ አገልግሎት ሰጭዎች (ሚንስትሪዎች) ነን፡፡ ከአጋር
ሚንስትሪዎቻችን ጋር በመተባበር፤ብቸኛና እውነተኛ የመትረፍረፍ /የመብዛት/ እና የነጻነት ምንጭ ኢየሱስ
ክርስቶስ ብቻ የመሆኑን ወንጌል እያወጅን ተግባራዊ ድጋፍ ለመስጠት እንሰራለን።

> ለውጥ፡- ምንም እንኳን የአሰራር ስልታችን በእያንዳንዱ ግለሰብ ሕልም ላይ ቀስ በቀስ መዋዕለ ንዋያ
ማፍሰስ/ኢንቨስት ማድረግ/ ቢሆንም ግባችን ግን ለሁሉም ማህበረሰብ ስር-ነቀል ለውጥ ማምጣት ነው።
ለአንድ ሰው እገዛ ማድረግ መቻል፤በቤተሰብ፣በጎረቤት፣በከተሞች እና በሃገራት ላይ ማመን የሚያዳግት ኃይለኛ
የእድገት፣ስር-ነቀል ለውጥ እና የተሃድሶ ማዕበል መፍጠር ይጀምራል፡፡

ይህ ስልጠና ለማን ነው?


የታሊ መሠረታዊ የቢዝነስ ስልጠና የተዘጋጀው፤የማህበረሰቦቻቸውን እሴቶች በጠበቀ መልኩ መሠረታዊና
ተግባራዊ የንግድ ክህሎት ስልጠና መውሰድ ለሚፈልጉ ግለሰቦች ሁሉ ነው፡፡

3
ታሊ አገልግሎቱን የሚሰጠው በአጋሮቻችን ሚንስትሪዎች በኩል ያለ ክፍያ በነጻ ነው፡፡ ስልጠናው ለብድሩ
መርሃግብር እንደ ቅድመ-ሁኔታ ወይም ከብድሩ ጎን ለጎን ያለዚያም ከብድር ጋር ባልተገናኘ መልኩ ሊቀርብ
ይችላል፡፡ በአጠቃላይ፤የታሊ ደንበኞች ብድሩን ከመውሰዳቸው በፊት ወይም ከተበደሩ በኋላ ባሉት በርካታ
ወራት ውስጥ ይህን ስልጠና ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የታሊ መሠረታዊ የቢዝነስ ስልጠና ለሁሉም የትምህርት ደረጃዎች በሚመጥን፣በአነስተኛ ቁጥር በተገደበ
ቡድን፣ሁሉን አሳታፊ በሆነ መልኩ የተነደፈ ነው፡፡ መጽሐፉ በገለጻ፣በውይይት፣በጥያቄና
መልስ፣በድራማ፣በተግባር ልምምድ እና በጭውውት መልክ ተዘጋጅቷል። ቀለል ያለ፣በቀላሉ ተግባራዊ የሚደረግ
እና ብዙ ወጭን የማይጠይቅ ነው፡፡ በአልተርኔቲቭ ግሎባል አንተርፕርነርስ (www.alternativproject.org)
ስርአተ-ትምህርት የተቀረጸ ሲሆን ፈቃድ በመጠየቅ ለታሊ አገለግሎት እንዲውል ሆኖ ተጣጥሞ ቀርቧል።

ይህ ስልጠና ለሁሉም የዕድሜ ክልል ወይም በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ላሉ ሁሉ ይጠቅማል።


በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኙና ብቻቸውን ልጅ አሳዳጊ የሆኑ ሴቶችን፣አነስተኛ ገቢ ያላቸው
ገበሬዎች፣መበለቶች፣የእስራት ጊዜያቸውን ጨርሰው የተፈቱ እስረኞች፣የአካል ጉዳተኞች፣የዘመኑ ሥራ
ፈጣሪዎች፣የቴክኒክና ሙያ ት/ቤት ተመራቂዎች፣የቢዝነስ ሰዎች፣አያቶች፣የዕደ-ጥበብ ሙያተኞች፣የጉልበት
ሠራተኞች፣የቁጠባ ቡድን አባላትን እና ሌሎችን ያካትታል፡፡

እ ያንዳንዱ ስልጠና፤የታሊ አነስተኛ የብድር አገልግሎት ፐሮገራም ላይ በመመስረት ግሩፕ መፍጠርን ዒላማ
ያደረገ (በዚህ ርዕሰ-ጉዳይ ላይ የበለጠ ለመረዳት የታሊን የሰልጣኞች ማንዋል ይመልከቱ) ቢሆን ተመራጭ
ነው፡፡ ግቦቻቸውን ወይም የህይወት ልምዶቻቸውን ማጋራት የሚችሉ ጓደኞችን በክፍል ውስጥ መፍጠር
መቻል እጅግ ጠቃሚ ሲሆን የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያጎለብት ጠንካራ ትስስር ይፈጥራል ፡፡

ሰልጣኞች ከዚህ ምን ይማራሉ?


በመጽሐፍ ቅዱስ ዋንኛ መርሆዎች ላይ በመመስረት፤መሠረታዊ የቢዚነስ ጽንሰ-ሀሳቦችን የሚዳሰስበት
መሠረታዊ ትምህርት ነው፡፡ የመግቢያ ክፍሉ፤ሥራ እንድንሰራ እግዚአብሔር ለምን ግድ
እንደሚለው፣ባለራዕይነትና ራስን ፈልጎ ማግኘትን ይዳስሳል፡፡ ከዚያም በመቀጠል፤

ስለቢዚነስ አጀማመር መሠረታዊ ጽንሰ-ሃሳብና ስለዕቅድ አወጣጥ (ስለተልዕኮ፣ግብ፣ግብይት፣ ስለዕቃ ወይም


ምርት ልዩነት) ያስተምራል፡፡ ከዚህም ባሻገር ጠለቅ ወዳለ የክህሎት ስልጠና (ስለዋጋ አተማመን፣ሂሳብ አያያዝ፣
በጀት አወጣጥ፣ ስለቁጠባ) ይሻገራል፡፡ በመጨረሻም ፤ክለሳና የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ ስለስነ-ምግባርና
ስለአመራር ተካትተዋል።

በተለያዩ አጋጣሚዎች የመከታተል ዕድሎችን ይፍጠሩ፡፡ ተሳታፊዎች ስልጠናቸውን አጠናቅቀው የታሊ


አነስተኛ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች በመሆን የቢዚነስ እንቅስቃሴያቸውን ሲመሩ እገዛ
በሚያደርጉላቸው ወቅት ይህን የማሰልጠኛ መጽሐፍ እንደገና መከለስዎን አይርሱ፡፡ እንዲያውም የክለሳ
ክፍለ-ጊዜ ወይም ሁሉንም ሰልጣኞች ያካተተ ልዩ ፕሮግራም ለማዘጋጀት ዕቅድ ያውጡ፡፡ በቀጣይ ስልጠናዎች
ላይም እነዚህ ተመራቂዎች እንዲካተቱ ያድርጉ፤ ወይም ስለቢዝነሳቸው የህይወት ተመክሮ ለአዳዲስ
ሰልጣኞች ለማጋራት ፈቃደኝነታቸውን ይጠይቁ።

ትንሽ ቁጥር ያላቸው ቡድኖች። ይህ ሥርዓተ-ትምህርት በዋነኛነት ትኩረት የሚደረገው ትንሽ ቁጥር
ያላቸው ቡድኖች በሚያደርጉት ውይይት ነው፡፡ በተለይ በውይይት ወቅትና በቡድን ስራ ክፍለ-ጊዜ፤ትልቁ ቡድን
ወደ ብዙ ትናንሽ ቡድኖች ይከፋፈላሉ፡፡ ‘ራስን ማወቅ’ እና ‘የአመራር ክህሎት’ የመሳሰሉ ስልጠናዎች ትንሽ
ቁጥር ባላቸው ቡድኖች ውስጥ ይበልጥ ውጤታማ እንደሚሆኑ እናምናለን፡፡ እነዚህ ቡድኖች፤ አባሎቻቸው

4
ሃሳቦችን በነጻነት የሚያጋሩበት፣ፅንሰ-ሀሳቦችን የሚያንሸራሽሩበት፣ችግሮቻቸውን በጋራ የሚፈቱበት እና
ማህበረሰብን የሚገነቡበት አመቺ ቦታዎች ናቸው፡፡

የታሊ መሠረታዊ የቢዝነስ ስልጠና በህብረተሰብዎ ዉሰጥ፤ተስፋን ለመፀነስ፣ቢዝነስ ለመጀመር፤የመንፈሳዊ


አገልግሎት ዕድሎችን ለመፍጠር እና ዕድገትን ለማምጣት የመጀመሪያው ጠንካራ እርምጃ ሊሆን ይችላል፡፡
እናም ራስዎን ያዘጋጁ፣በሚገባ ያንብቡ፣ግልጽ ይሁኑ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ማህበረሰብዎን ለመለወጥ
በእርስዎ በኩል ሲሠራ ይመልከቱ!

“በቀረውስ፣ወንድሞች ሆይ፣እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፣ጽድቅ የሆነውን ነገር
ሁሉ፣ንጹህ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፣መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፣በጎነት ቢሆን
ምስጋናም ቢሆን፣እነዚህን አስቡ፤ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም
እነዚህን አድርጉ፤ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።”

- ፊልጵስዩስ 4:8-9

5
ለስልጠናዎ ዕቅድ ማውጣት

ከዚህ የሚከተሉት ክፍሎች ስልጠናውን ለማሳለጥ /ለማመቻቸት/ የሚረዱ ቁሳቁስና መሰል አቅርቦቶችን
የሚዳስሱ ናቸው፡፡

ለሰልጣኞች ከማቅረብዎ በፊት የስልጠናውን አጠቃላይ ስርዓተ-ትምህርት በሚገባ መከለስ እና ተግባራዊ


ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

የስልጠናው ጊዜ እና ዕቅድ፡- የታሊ መሠረታዊ የቢዝነስ ስልጠና፡የመግቢያ ገለጻን፤የእረፍት ጊዜ፤ እና


የምረቃ ሥነ-ስርዓት ጊዜያትን ጨምሮ 20 የገለጻ ሠዓታት የሚፈጁ እንዲሆኑ ተደርገው ተቀርጸዋል፡፡ አንዳንድ
ቡድኖች ከሌሎች ቡድኖች የበለጠ አዝጋሚ ሊሆኑ ይችላሉ። እናም ስልጠናው እንደየማህበረሰቡ ፍላጎት
ተለዋዋጭ መዋቅር እንዲኖረው ሆኖ የተነደፈ ነው፡፡

በመማር ማስተማሩ ወቅት የተለያዩ ሀሳቦች በስርአተ ትምህርቱ ውስጥ ተካትተዋል። የስልጠና ሠኣትን
በአግባቡ መጠበቅ በጣም ወሳኝ ነገር ነው፡፡ያለዚያ ትምህርቱ ከሚያስፈልገው ሠዓት በላይ የሚወስድ ከሆነ፤
ስልጠናውን በታቀደው የጊዜ ገደብ ማጠናቀቅ ያዳግታል።

> ጠቃሚ ምክር:- ጊዜዎን በአግባቡ ለመጠቀም፤ከሰልጣኞች መካከል አንድ ፈቃደኛ ሠዓት መቆጣጠሪያ
እንዲይዝና ምልክት እንዲያሳይዎ ያድርጉ። ከዚህም በተጨማሪ፤ በክፍል ውስጥ የሚፈጠርን አላስፈላጊ
ጫጫታ ለመቆጣጠር ወይም ቡድኑ ትኩረጡ እንደገና ወደ እርስዎ ለማድረግ ደወልን መጠቀም ይችላሉ።

የስልጠና ፕሮግራም አወጣጥ ናሙና- የሰልጣኞችን የመማር ፍላጎት በሚጨምር መልኩ እና ምቾት በሚፈጥር
መንገድ ፕሮግራም ማውጣት መብትዎ ነው፡፡ ሆኖም አንዱ ርዕሰ-ጉዳይ ሌላኛውን ርዕሰ-ጉዳይ እንዲገነባ
ተደርጎ የተቀረጸ እንደመሆኑ መጠን፤ በያንዳንዱ ስልጠና መካከል ጽንሰ-ሓሳቦች እንዳይረሱ ለማድረግ
ተከታታይና ተያያዥ ዕቅድ መንደፍ ወሳኝ መሆኑን ልብ ይበሉ። ስልጠናዎን እንዴት ማዋቀር እንደሚችሉ
የሚያሳዩ ጥቂት ምሳሌዎች እነሆ፡-

➔ ሦሥት-ቀናት ጠንካራ ስልጠና፡- 3 ተከታታይ የሙሉ ቀናት ትምህርቶች


➔ አንድ-ሳምንት ስልጠና፡- 5 ተከታታይ የግማሽ ቀናት ትምህርቶች (ጠዋት፣ከሠዓት፣ወይም ምሽት)
➔ ሁለት-ሳምንታት ስልጠና፡- 6 የግማሽ ቀናት ትምህርቶች፣ለሁለት ተከታታይ ሳምንታት
➔ አንድ-ወር ስልጠና፡- 4 የሙሉ ቀናት ትምህርቶች፣በሳምንት አንድ ጊዜ፡፡ የክለሳ ጊዜን ያካትታል።

እነዚህን እንደ ምሳሌ በመቁጠር ለእርስዎ በሚያመች መልኩ ማስተካከል ይችላሉ፡፡ እቅድዎን አንድ ጊዜ
ካስተካከሉ በኋላ ሊያጋጥምዎት በሚችል መጠነኛ አለመጣጣም ምክንያት ፕሮግራምዎን አይለዋውጡ፡፡
ተሳታፊዎች ለስልጠናው ያላቸውን ቁርጠኝነት ጠብቀው እና ቃላቸውን አክብረው እንዲቀጥሉ
ያበረታቷቸው፤ውጤታማ መሆን የሚችሉት ወደ ውስጣቸው ባስገቡት ልክ መሆኑንም ያስታውሷቸው፡፡

6
> ጠቃሚ ምክር:- ለስልጠናዎ መርሐ-ግብር /ዕቅድ/ ለማውጣት የሚረዱ የተለያዩ ስልቶችን ለመገንዘብ፤
በዚህ ምዕራፍ የመጨረሻ ክፍል ላይ የሚገኘውን የስልጠና አማራጭ ዕቅዶች የሚለውን ክፍል ይመልከቱ፡፡

አመቻቾች፡፡ ቢያንስ ሦስት አመቻቾች እንዲኖሩ እንመክራለን፡፡ አስር እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ትናንሽ ቡድኖች
ግን ተጨማሪ አመቻቾችን መጨመር ያስፈልግዎታል፡፡ ስልጠናውን ለማቅረብ የሚያስፈልጉ ሦስቱ ዋና
ተዋናዮች፤ መሪ አመቻቾች፣ ትንንሽ ቡድን አመቻቾች እና በጎ ፈቃደኞች ናቸው፡፡

> መሪ አመቻቾች- ብዙውን ጊዜ ለዚህ ሃላፊነት የሚሰጠው ለታሊ ማህበራዊ አገልግሎት ሰራተኛ
/ሶሻል ወርከር/ ወይም ኮርሱን በማስተማር ልምድ ላለው ለታሊ የኮሚቴ አባል ነው፡፡ መሪ አመቻቹ
ከክፍሉ ፊት ለፊት ቆሞ ያስተምራል፣ሠዓት ይቆጣጠራል፣በአነስተኛ ቡድን ተከፋፍሎ በሚደረግ
ውይይት ወቅት ከቡድኑ አመቻቾች ጋር ይወያያል፣በውይይቱ ወቅት የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ
ራሱን ያዘጋጃል እንዲሁም ስልጠናው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡
> የትንንሽ ቡድን አመቻቾች- እነዚህ አመቻቾች፤ የታሊ ፕሮግራም ኮሚቴ አባላት፣የአካባቢው በጎ
ፈቃደኞች፤ ወይም ከዚህ ቀደም የተሰጠውን ስልጠና የወሰዱ የመምራት አቅም ያላቸው ደንበኞችን
ያካተተ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ትንንሽ ቡድን ውስጥ ውይይቶችን በመምራት ያግዛሉ፣ በየተራ እንደ መሪ
አመቻች በመሆን ይረዳሉ፣ እያንዳነዱን አባል ያሳትፋሉ፣ እንዲሁም ስልጠናው በሚሰጥባቸው ጊዜያት
ሁሉ ከእያንዳንዱ አባላት ጋር የግል ግንኙነቶችን ያዳብራሉ፡፡
>በጎ ፈቃደኞች- በድራማዎች፣በመክሰስ /ስናክ/ አገልግሎቶች፣ ሠዓትን በመቆጣጠር ረገድ እና
በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ለማገዝ የሚረዱ በጎ ፈቃደኞች ናቸው፡፡

>ጠቃሚ ምክር፡- በማህበ ረሰቡ ውስጥ ያሉ የአሁን ሆነ የቀድሞዎቹን የታሊ ደንበኞች በመጋበዝ ስልጠናው
ይበልጥ እንዲሳለጥና እንዲጠናከር ያድርጉ! ከእነዚህ ደንበኞች የሚቀርብ የግል ተሞክሮ እና ተዛምዶ፤
ተሣታፊዎች የተሻለ መረዳትን እንዲያገኙ ያግዛቸዋል፡፡ በጎ ፈቃደኞችም ቢሆኑ ጠቃሚ የአመራር ልምድን
የቀስሙበታል።

ስለ ትንንሽ ቡድኖች- ይህ ስርዓተ-ትምህርት ትኩረት የሚያደርገው አነስተኛ ቡድን ላይ ነው-ለውይይት እና


ለቡድን ስራ በሚያመች መልኩ አንድን ትልቅ ቡድን ወደ ብዙ ትንንሽ ቡድኖች መከፋፈል፡፡ ትምህርትም ይሁን
ራስን የማወቅ እና የአመራር ስልጠና የተሻለ ውጤታማ የሚሆነው በትንንሽ ቡድኖች ሲከፋፈል እንደሆነ
እናምናለን፡፡ ተሳታፊዎች ሀሳቦቻቸውን በተሻለ ነጻነትና ምቾት የሚያጋሩት፣ፅንሰ-ሀሳቦችን
የሚዳስሱት፣ለችግሮች መፍትሔ የሚያመነጩት ብሎም ማህበረሰብን የሚገነቡት በእንዲህ ዓይነት ቡድኖች
ውስጥ ነው ፡፡ ትንንሽ ቡድኖችን ለመመስረት የሚረዱ አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮች፡-

> የቡድን ብዛት፡- ሰባት ቢሆኑ እጅግ ተመራጭ ነው፤ ትንንሽ ቡድኖች ብዙውን ጊዜ ከአምስት እስከ
አስር ናቸው፡፡
> ቋንቋ፡- በተቻለ መጠን ተመሳሳይ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ያላቸውን ተሳታፊዎች አንድ ላይ ያድርጉ፡፡
> ሁሉን አካታችነት፡- የአቻ ለአቻ ተግባቦትን ለማጎልበት የተለያየ የዕውቀት ደረጃ ያላቸውን
ተሳታፊዎች ለማካተት ይሞክሩ፡፡ ይሁን እንጅ፤ በዝቅተኛ የዕውቀት ደረጃ ላይ የሚገኙ አባላት ከእነሱ
በእጅጉ ከሚበልጧቸው ጋር ሲቧደኑ የበታችነት ስሜት ሊሰማቸው እንደሚችል በመገንዘብ፤ በሁሉም
የክህሎት ደረጃ ላይ የሚገኙ አባላትን ተሳትፎ እኩል ማበረታታትዎን ርግጠኛ ይሁኑ፡፡

7
ዝግጅት፡- መሪ አመቻቾችም ሆኑ የትንንሽ ቡድን አመቻቾች ስልጠናው ከመጀመሩ አስቀድሞ የአሠልጣኝ
መምሪያውን ሙሉ በሙሉ መከለስ ይኖርባቸዋል፡፡ አንዳንድ የስልጠና ዓይነቶች ሰፊ ቅድመ-ዝግጅትን
ይጠይቃሉ፡፡ ለምሳሌ፡- ለዕደ-ጥበብ ስራ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን እንዲሁም ለስልጠናው አጋዥ የሚሆኑ
ግለሰቦችንና አቅርቦቶችን ማዘጋጀት፣ የትወና /ድራማ/ ገጸ-ባህርያትን መምረጥና ድራማዎችን መለማመድ
ወይም ለጨዋታዎች/ጌሞች/ እቅድ ማውጣት የመሳሰሉ ይገኙበታል፡፡

እያንዳንዱ ክፍል የስልጠናውን ጽንሰ-ሃሳብ የሚያሳይ አጠቃላይ መግለጫ ገጽ አለው፡-

> ግቦች

> ቁልፍ ቃላት (በነጭ ሰሌዳ ላይ የሚጻፍ)

> መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ (በነጭ ሰሌዳ ላይ የሚጻፍ)

> አስፈላጊ አቅርቦቶች

> ትዕይንቶች (በፖስተር ወይም በሠልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ)

> የዝግጅት ጠቃሚ ምክሮች

አንዳንድ ድራማዎች የሰልጣኞችን ተሳትፎ የሚጠይቅ ስለሆነ የትምህርት ክፍለ-ጊዜው ከመድረሱ


በፊት፣በእረፍት ክፍለ-ጊዜ፣ወይም ከስልጠና በኋላ አብረው ፍጣን ክለሳ ማድረግ ሊያስፈልጋቸው እንደሚችል
ልብ ይበሉ፡፡ በእነዚህ መሰል ድራማና ጭውውቶች ውስጥ ሰልጣኞችንችን ከማካተት ወደኋላ አይበሉ።
ብዙውን ጊዜ በጣም ውጤታማ እና የማይረሱ የስልጠና ጊዜያትን ጥለው የሚያልፉ ናቸው!

ጸሎትና አምልኮ። በእርስዎ ተጨባጭ ሁኔታ ተገቢ ሆኖ ካገኙት፤እያንዳንዱን የስልጠና ቀናት በጸሎት መክፈት
እንዲሁም ጥቂት የአምልኮ ጊዜ እንዲኖር ማድረግ በእጅጉ ይበረታታል። እነዚህ መንፈሳዊ ነገሮች በዚህ
የስልጠና መምሪያ ውስጥ አልተካተቱም፡፡ ስለሆነም በሚፈልጉት ዓይነት፣እንደ ባህሉ፤ በመሪዎችና አመቻቾች
ላይ በመመርኮዝ መንፈሳዊውን ክፍል አጣጥመው ማዘጋጀት ይችላሉ፡፡ ይህ ስልጠና በመጽሐፍ ቅዱስ
እውነቶች ላይ የተመሠረተ እና ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ዓለም ዓቀፍ እምነት ተኮር ነው፡፡ ከማህበረሰብዎ
ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ከክፍል ሠልጣኞች ጋር በግልጽ መጸለይ ተገቢ የማይሆን ከሆነ፣ እንደ አመቻች
በፕሮግራሙ መጀመሪያና መጨረሻ ለእያንዳንዱ ቡድን ለመጸለይ ይወስኑ፡፡

>ጠቃሚ ምክር፡- በተለየ እንዲጸለይላቸው የሚፈልጉ ሠልጣኞችን ስም ዝርዝርና የጸሎት አርዕስት በመዝገብ
ላይ የሚያሰፍር ከሠልጣኞች መካከል አንድ ፈቃደኛ ይጠይቁ፡፡ ስልጠናውን ከመጀመርዎ በፊት ለአመቻች
ቡድንዎ ይጸልዩላቸው።

አቅርቦት:- ይህንን ስልጠና ለማካሄድ የሚያስፈልገው መሠረታዊ አቅርቦት ብቻ ነው፡፡ በአካባቢው በቀላሉ
የሚገኙ ከሆነ፣ለእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መሠረታዊ ቁሳቁሶች ቢሟሉ ይመረጣል፡-

> የመመዝገቢያ ቅፅ (“መረጃ” በሚለው ክፍል ይመልከቱ)፤ የቅጹን ቅጅ በሠልጣኞች ቁጥር ልክ ያዘጋጁ

8
> የስም መቆጣጠሪያ ቅጽ (“መረጃ” በሚለው ክፍል ይመልከቱ)፤ እንደ አስፈላጊነቱ ኮፒ ያድርጉ
> የስም መጻፊያ ታግ
> ለተሳትፎ ሽልማት የሚረዱ እንደ ከረሜላና መሰል ጣፋጭ ነገሮች
> እስክሪፕቶዎች
> የቀለም እርሳሶች (ክሬዮን)
> መቁረጫ መቀሶች
> የታሊ መሠረታዊ የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና የሠልጣኞች መጽሃፍ፤ ለእያንዳንዱ ሠልጣኝ
> ጉልህ ተዕይንቶች (ከተገኙ)
> ትዕይንቶችን ግድግዳ ላይ ለመለጠፍ የሚያገለግል ፕላስተር(ቴፕ)
> ነጭ ሠሌዳ (የቆመ ወይም ግድግዳ ላይ የተሰቀለ)፤ ወይም ትልቅ የፖስተር ሠሌዳ
> መጻፊያ ማርከሮች (ለነጭ ሰሌዳ ወይም ለፖስተር ወረቀት)
> ተንቀሳቃሽ ምስል፤በእያንዳንዱ የስልጠና ክፍል ቅድመ-ዕይታ ላይ እንደተገለጸው
> የሒሳብ ማሽኖች/ካልኩሌተሮች/ ፤ማግኜት ከተቻለ፡፡ አንድ ባለ አራት መደብ የሒሳብ ማሽን
ለአንድ ሠልጣኝ ቢሆን ተመራጭ ነው።
> የምረቃ ምስክር ወረቀቶች (መረጃ የሚ ለውን ክፍል ይመልከቱ); ለእያንዳንዱ ሰልጣኝ አንዳንድ
ቅጅ

የክፍል ዝግጅት፡፡ ይህንን ስልጠና በአግባቡ ለማከናወን፤ሰፋ ብሎ በቂ ብርሃን ያለው፣ጠረጴዛዎች


፣ወንበሮች፣ነጭ ሰሌዳ እንዲሁም በጨዋታና በእረፍት ሊሰፋ የሚችል ምቹ ክፍል/አዳራሽ/።

የዕርዳታ መስጫ ማዕከላት፣አብያተ-ክርስቲያናት፣ትምህርት ቤቶች፣ወይም የሠፈር አዳራሾች ሁሉ ምቹ


የማሠልጠኛ ቦታዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሁሌም አመቺ ቦታና ቁሳቁስ ማግኘት አስቸጋሪ ቢሆንም፤ከዚህ በታች
የተቀመጠውን የአደረጃጀት ናሙና በማየት ባለዎት ነገር ያመቻቹ፡፡

9
የመበረታታት እና የተሳትፎ ምህዳር ፍጠሩ፡፡ በዚህ ስልጠና ውጤታማ ለመሆን ፣ከፍተኛ መበረታታትን እና
ተግባቦትን ይጠይቃል፡፡ ተሳታፊዎች መልስ ሲመልሱ (የተሳሳቱ እንኳን ቢሆን!) በመሳተፋቸው ብቻ እነደ
ከረሚላ ያሉ ጣፋጭ ነገሮቸችን የመሸለምን አዎንታዊ የማበረታቻ ስልት ይጠቀሙ፡፡ እያንዳንዱን ሰልጣኝ
ያለመሰሰት በማወደስ በራስ የመተማመን መንፈሳቸውን እና የተሳትፎ ደረጃቸውን ከፍ ያድርጉ።

የእርስዎ ግብ መሆን ያለበት፤ሁሉም ተሳታፊዎች የለውጦቻቸው ባለቤቶች ራሳቸው እንዲሆኑ እና ለቡድኑ


ተመክሮ የየራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ የሚያስችል ምህዳር መፍጠር ነው። ይህ መጀመሪያ ላይ በአንድ ጊዜ
ላይመጣ ይችላል። ብዙዎቹ ሠልጣኞች መደበኛ ትምህርት ቤት ገብተው ጥልቅ ግንዛቤ እና የፈጠራ እሳቤዎች
ያዳበሩ አይደሉም። እናም እነዚህን መሰል መሰናክሎች ጥሶ ለማለፍ የተወሰኑ ክፍለ-ጊዜዎችን ሊወስድ
ስለሚችል ታጋሽ፣ትጉህ እና አወንታዊ ይሁኑ፡፡ ውጤቱን በመጨረሻ ያዩታል!

ስለ አሠልጣኙ መምሪያ አጠቃቀም፡፡ የዚህ መምሪያ ሥርዓተ-ትምህርት በርካታ ክፍሎችን ያካተተ ነው፡፡ 18
ክፍሎችን ይዟል፡፡ እያንዳንዱ ክፍል ደግሞ በውስጡ የሚከተሉትን ያካትታል፡-

> አጭር መግለጫ፡፡ ለእያንዳንዱ ስልጠና ለመዘጋጀት ይረዳዎ ዘንድ ይህንን ገጽ ይከልሱ፡፡
> ለመሪ አመቻቹ የተዘጋጁ ጽሑፎች እንዲሁም ተንጋድደው የተጻፉ (ኢታሊሳይዝድ) ወይም የቀለሙ
ልዩ ምልክቶች፡፡ ሥርዓተ-ትምህርቱ ለአጠቃቀም እንዲያመች እና ወጥነት እንዲኖረው፣ መሪ አመቻቹ
ቃል በቃል እንዲያነብበው ተደርጎ የተቀረጸ ነው፡፡ ሆኖም ልምድ ያላቸው አሠልጣኞች ከተሳታፊዎች

10
ጋር የተሻለ ቅርርብ ለመፍጠር እና ትምህርቱ የተሻለ ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ጽንሰ-ሀሳቡን
ለማስረዳት በራሳቸው አገላለጽ ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ ከይዘቱ እንዳይወጡ ግን በጣም ጥንቃቄ ያድርጉ።
በተቀመጠው ስክሪፕት/ጽሁፍ/ መሠረት ፕሮገራሙን ማስኬድ ከአርዕስት እንዳይወጡና ስልጠናውን
እጅግ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲያጠናቅቁ ይረዳዎታል። የተንጋደዱ (ኢታሊሳይዝድ) ወይም
የተቀለሙ ጽሑፎች፤ለክፍሉ ጮክ ተብለው የማይነበቡ መመሪያዎች ናቸው።
> ለትንንሽ ቡድን አመቻቾች የተዘጋጁ ጽሑፎች እንዲሁም ተንጋድደው የተጻፉ (ኢታሊሳይዝድ)
ወይም የቀለሙ ልዩ ምልክቶች፡፡ መምሪያው፤የትንንሽ ቡድን አመቻች ውይይቶችን፣እንቅስቃሴና
ጨዋታዎችን እንዴት መምራት አንዳለባቸው የሚያሳውቁ ምልክቶችን ያካተተ ነው፡፡ አመቻቾቹ
ከእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ በፊት እነዚህን መከለስ አለባቸው፡፡
> ድራማዎች በከለር ቀልመዋል፡ ልዩ ምልክቶችም ተደርገውባቸዋል፤ እንዲሁም በጎ ፍቃደኞች
ስልጠናው ከመጀመሩ አስቀድሞ ልምምድ ለማድረግ እንዲረዳቸው ከስር ተሰምሮባቸዋል፡፡
>ተግባራዊ ልምምዶች፤ ለመሪ አመቻቾችና ለትንንሽ ቡድን አመቻቾች በከለር ቀልመዋል፡ ልዩ
ምልክቶችም ተደርገውባቸዋል፡፡
> መልመጃዎች፤ በከለር ቀልመዋል፡ በምስል፣በጽሁፍ፣በሰልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ተግባራዊ
ጥያቄዎችን ያካተተ ነው፡፡
>የስኬት ታሪኮች፤ በከለር ቀልመዋል፡፡ ይህ የታሊ ደንበኞች እውነተኛ የሕይወት ታሪክ ስለሆነ
ተሳታፊዎች ከዚህ ተሞክሮ ሊቀስሙበት እንዲሁም ተነሳሽነትን ሊፈጥርላቸው ይችላል፡፡

የሠልጣኞች መጽሐፍ አጠቃቀም። እያንዳንዱ ሠልጣኝ የታሊን መሠረታዊ የቢዝነስ ክህሎት ማሠልጠኛ
የሠልጣኞች መጽሐፍ አንድ አንድ ቅጅ እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡ ተሳታፊዎች ስማቸውን በመጽሐፉ ሽፋን ላይ
እንዲጽፉ፣ማስታወሻ እንዲይዙና ለነዚህ ነገሮች የተለየ ዋጋ እንዲሰጡ ያበረታቷቸው፡፡ ተሳታፊዎች
በመጽሐፍቶቻቸው ላይ ብዙ በጻፉ ወይም በስዕል በገለጹ ቁጥር በቀላሉ በውስጣቸው ይሰርጻል​​፡፡

> ጠቃሚ ምክር:- ደህንነቱ እንዲጠበቅ እንዲሁም በቀጣይ የትምህርት ክፍለጊዜ ረስተው እንዳይመጡ
ለማድረግ ሠልጣኞች መጽሓፍቶቻቸውን ክፍል ውስጥ አስቀምጠው ወይም ለአመቻቾቻቸው ሰጥተው
እንዲሄዱ ቢደረግ መልካም ነው ጥሩ ሀሳብ ሊሆን ይችላል፡፡

11
10 የስኬታማ ስልጠና መርሆዎች

1. ይጸልዩ። ጥበብንና ጥሩ ተግባቦትን እንዲሰጥዎ እግዚአብሔርን ይጠይቁ፡፡ ይህ ሥልጠና የተሳታፊዎችን


ህይወት ሙሉ በሙሉ የሚለውጥ እንዲሆን በእርሱ ላይ ይደገፉ፡፡
2. በሚገባ ይዘጋጁ። ከሁሉ በፊት የመጽሐፉን ይዘት ይረዱ። ቡድንዎን አስቀድመው ሰብስበው
በማንበብ፣ ማንኛውንም እንቅስቃሴ፣ድራማ ወይም መልመጃዎችን በመስራት ይዘጋጁ፡፡
3. ከፍተኛ ጉጉት ይኑርዎት! ይህ ስሜትዎ ወደ ሌሎችም ይጋባል!

4. ሠዓት መቆጣጣሪያ ያዘጋጁ። በውይይት ወቅት፤ቡድኑ ውይይቱን እንደጨረሰ እና ወደ ቀጣይ ለማለፍ


እንደፈለገ ወይም ተጨማሪ ጊዜ እንደሚፈልግ ለማወቅ ቡድን አመቻቾችን በንቃት ይቃኙ፡፡ አንዳንድ
ጊዜ ሁሉም ማጠናቀቅ ሳይጠበቅብዎት ወደ ቀጣይ አርዕስት/ክፍል/ ሊሻገሩ ይችላሉ።

5. ሁሉን አሳታፊ የሆኑ የስልጠና ክፍሎችን አይዝለሏቸው፡፡ እንደ ድራማ፣ ማስመሰል፣ የትንንሽ ቡድን
ውይይቶች የመሳሰሉ ልምምዶችን በፍጹም አይለፏቸው፡፡ እነዚህን መሰል የትምህርት አላባዎች
በሰልጣኞች የሚወደዱና አይረሴ መሆናቸውን በስራ ፈጣሪዎች ብዙ ጊዜ ሲነገሩ ይደመጣል፡፡

6. አዘውትረው ይለማመዱ፡፡ ለድራማ የተዘጋጁ ተውኔታዊ የመነባንብ ረቂቆችን አስቀድመው


በመለማመድ በቂ ግንዛቤን ያዳብሩ፤የመልዕክቱን ጭብጥም ይረዱ፡፡ ከመጀመሪያው ጽንሰ-ሃሳብ
እስካልወጡ ድረስ ማሻሻያ ማድረግ ይችላሉ፡፡
7. ከቻሉ የስልጠና ፕሮገራሙ ከመጀመሩ አስቀድመው ቁልፍ ቃላትንና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻዎችን
በነጭ ሰሌዳው ላይ ይጻፉ፡፡

8. ትዕይንቶችን ይጠቀሙ፡፡ ትዕይንቶች በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍል ባለ አጭር መግለጫ ውስጥ


ተጠቅሰዋል፡፡ በቂ ቦታ ከተገኘ ትልልቅ መጠን ያላቸውን ትዕይንቶች በተሳታፊዎች ፊት ለፊት
መለጠፍ ይችላሉ፤ያለዚያም በሠልጣኞች መጽሐፍ ላይ ወዳለው ትዕይንት እንዲያተኩሩ ያድርጉ፡፡

9. ታጋሽ ይሁኑ፡፡ በስልጠናዎ መጀመሪያ ባሉ ጥቂት ቀናት ከተሳታፊዎች ዝምታ ቢገጥምዎ አይጨነቁ፡፡
ሰዎች በነጻ ስሜት ለመነጋገርና ለመወያየት ትንሽ ጊዜን ይወስዳሉ፡፡
10. ዘና ይበሉ፤ደስተኛ ይሁኑ! ወዳጅነትን ይመስርቱ፤ብዙ ይጫወቱ ይሳቁ፤ የስልጠናው ተሳታፊዎች
ምናልባትም በሌላ መንገድ ሊያገኟቸው የማይችሏቸውን መረጃዎች/እውቀቶች/ እርስዎ
እያካፈሏቸው እንደሆነ ይገንዘቡ!

ለመሪ አመቻቾች 5 ጠቃሚ ምክሮች


1. ለክፍሉ ሙሉ ኃላፊነት ይውሰዱ፡፡ እራስዎን ያስተዋውቁ፤ርዕሱን ያስተዋውቁ፤ድምጽዎን ከፍ
አድርገው በቀጥታ ይናገሩ፤ማረጋገጫ ለመስጠት አያመንቱ!

12
2. በጽሑፉ ላይ ብቻ ይደገፉ። ለአጠቃቀም ምቾት እና ወጥነት ሲባል ሥርዓተ-ትምህርቱ ቃል በቃል
አንዲነበብ ተደርጎ የተቀረጸ ነው፡፡ ያም ሆኖ ከተሳታፊዎች ጋር የበለጠ ለመቀራረብና ስልጠናውን
በሚገባ እንዲረዱት ለማስቻል፤ ልምድ ያካበቱ አሠልጣኞች የመጽሐፉን መሠረተ-ሃሳብ አንደጠበቁ
የራሳቸውን ቃላትና አገላለጽ ተጠቅመው ሊያስተምሩ ይችላሉ፡፡ ከትምህርቱ አፈንግጠው እንዳይወጡ
ግን ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡ በጽሑፉ ላይ ብቻ መደገፍ መቻል፤ ከርዕሱ ሳይወጡ በጣም ውጤታማ በሆነ
መንገድ ስልጠናውን ለማጠናቀቅ ይረዳዎታል። ተንጋድደው የተጻፉ (ኢታሊሳይዝድ) መልዕክቶች
ለተሳታፊዎች በቀጥታ የማይነበቡ፤ ነገር ግን ለአሰልጣኙ ምሪትን የሚሰጡ ናቸው።

3. አድናቆትና ሽልማትን ይለግሱ። መልሳቸው ትክክል እንኳ ባይሆን ለጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት
መሳተፍ በመቻላቸው ብቻ እንደከረሚላ ያሉ ጣፋጭ ነገሮችን ከአድናቆት ጋር ይሸልሙ፡፡ የተለዩ
ግለሰቦችን ብቃትም አጉልተው ያሳዩ። ብዙ ተሳታፊዎች በየተራ የሚናገሩበትና መስተጋብርን የጠበቀ
ትምህርት የመከታተል ዕድል በጭራሽ ያልገጠማቸው /ተመክሮ የሌላቸው/ ናቸው። ሁሌም
አድናቆት፣አድናቆት፣አድናቆ!

4. ስልክ ያጥፉ፡፡ ይህ ተሳታፊዎችንም ሆነ አመቻቾችን ያለማቋረጥ ማሳሰብን የሚጠይቅ ተግባር ነው!

5. በክፍሉ ውስጥ ይንቀሳቀሱ፡፡ ትንንሽ ቡድኖች ውይይት በሚያደርጉበት ወቅት ግብረመልሶችን


ለማዳመጥ እና ተሳታፊዎቹ ምን ያህል እንደተረዱ ለማወቅ እያንዳንዱን ይቃኙ።

ለቡድን አመቻቾች 5 ጠቃሚ ምክሮች


1. በሚገባ ይዘጋጁ። ውይይቶችን በጥሩ ሁኔታ ለመምራት እንዲችሉ ተንጋድደው የተጻፉ
(ኢታሊሳይዝድ) ወይም የቀለሙ ልዩ ምልክቶች ያሉበትን ክፍል በሚገባ ያንብቡ፡፡

2. በትንንሽ ቡድኖች ውስጥ እራስን ለማወቅ የሚረዱ ወሳኝ ጥያቄዎችን ይጠይቁ፡፡ ክህሎት፣ዕውቀት፣
እና ሙያን የሚያዳብር ጥያቄን በመጠየቅና በቀላሉ እንዲረዱ በማድረግ አስቸጋሪ ፅንሰ-ሀሳቦችን
ያቅልሉላቸው።

3. ተሳታፊዎችን በሚገባ ለይተው ይወቋቸው። ፅንሰ-ሀሳቦችን መገንዘብ አስቸጋሪ በሚመስሉበት ጊዜ፤


ምሳሌ ተጠቅሞ ለማስረዳት ያስችልዎ ዘንድ ግባቸውን ይወቁ። ተሳታፊዎችን በጋለ መንፈስ ያድንቁ
እንዲሁም ለተወሰኑ ግለሰቦች ጉልህ ውጤት እውቅና ይስጡ። ዝምታ የሚያዘወትሩ ሠልጣኞችን
በቀጥታ በመጠየቅ እንዲናገሩ ያበረታቷቸው፡፡

4. ስለ ሠዓት ቁጥጥር ከመሪ አመቻቾች ጋር ይነጋገሩ። ውይይቱን ለመጨረስ ምን ያህል ደቂቃዎች


እንደሚያስፈልግዎ ለመግለጽ የእጅ ምልክቶችን፤ ለምሳሌ፡- አውራ ጣትን ወደ ላይ ወይም ወደ ታች
በማድረግ፣ወይም ሌሎች ጣቶችን ይጠቀሙ፡፡

5. የእርስ በእርስ ጓደኝነትን ያበረታቱ ። የተሻለ ዕውቀት ያላቸው ሰልጣኞች ለሌሎች ላልገባቸው
ለማስረዳት የሚያደርጉትን ጥረት ያበረታቱ፡፡ እንዲያውም እንዲህ ዓይነት ሰዎችን ሆን ብሎ ማቧደን
ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ይህንን ለማመቻቸት ደግሞ ሳይሳቀቁ በየትኛውም ክፍለ-ጊዜ ወይም
የስልጠና ቀናት ተሳታፊዎችን ወንበር ይቀያይሯቸው፡፡

13
14
አማራጭ የስልጠና መርሃ-ግብር /ዕቅድ/
ይህ የስልጠና ዕቅድ ሊቀየር የሚችል ነው። ከዚህ በታች የቀረቡት መዘርዝሮች፤ ስልጠናዎችን ማቅረብ
የሚቻልባቸው አማራጭ መንገዶች ናቸው፡፡

15
16
// ክፍል 1 //

መግቢያ

የሚወስደው ጊዜ:- ግማሽ ሠዓት

ግቦች:-
﹥ ተሳታፊዎች፤ ስለ ስልጠናው አጠቃላይ ፕሮግራም ግልፅ ግንዛቤ ያገኛሉ፤
﹥ ተሳታፊዎች፤ ስራ ለእግዚአብሔር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ይረዳሉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ:-


﹥ ዘፍጥረት 1÷28

ከመጀመርዎ በፊት:-
> ምዝገባ፡- ማንኛውም ሠልጣኝ የምዝገባ ቅፅ በመሙላት ይመዘገባል፤(አባሪ “ሀ”ን ይመልከቱ)፡፡ በትምህርቱ
ማብቂያ ላይም ስለ ስልጠናው የዳሰሳ ጥናት ለማካሄድ ይሄው ቅፅ ጥቅም ላይ ይውላል።

> ስም መቆጣጠሪያ /አቴንዳንስ/፡- ማንኛውም ሠልጣኝ በእያንዳንዱ የስልጠና ክፍለ ጊዜ በስም መቆጣጠሪያ
ቅጹ ላይ ይፈርማል (አባሪ “ለ”ን ይመልከቱ)።

መጀመር:-
> ከመግቢያው ወይም ወደ ቀጣይ ክፍል ከመሸጋገርዎ በፊት ፕሮግራሙን በጸሎት ከተቻለም በአምልኮ
ይክፈቱ፡፡

> ስልጠናው ሚካሄደው በቤተክርስቲያን ውስጥ ከሆነ ፓስተሩን እና /ወይም የቤ/ክ ሽማግሌውን
ለማስተዋወቅና እግረመንገድም ስላደረጉት ትብብር ለማመስገን ጥሩ አጋጣሚ ነው።

> ከአመቻች ቡድኑ ውስጥ የታሊ ደንበኞች ወይም ተመራቂዎች ካሉ እንዲሁም የሚያግዙ አስተናጋጆች
ካሉም አስቀድመው ያስተዋውቋቸው፡፡ ከደንበኞች ወይም ተመራቂዎች መካከል አንድ ወይም ሁለት
ፈቃደኞች አጭር ምስክርነት እንዲያካፍሉ ወይም ተሳታፊዎችን የሚያነቃቃ አስተያየት እንዲሰጡ
ለማድረግ በዕቅድዎ ውስጥ ያካትቱ።

ይምሩ:- ሰላም ለእናንተ ይሁን! እንዴት ናችሁ? ይህን ስልጠና ለመከታተል ዝግጁ ሆናችሁ እዚህ
በመገኘታችሁ በጣም ደስ ብሎናል!

17
ይምሩ:- ስሜ ………………. ይባላል፡፡ እ… [ስለራስዎ ትንሽ ያጋሩ]።

ይምሩ:- እኔ እና ላይፍ ሴንተር እንዲሁም ዩናይትደ ስቴትስ ኦቭ አሜሪካ ከሚገኘውና ተች ኦቭ ላቭ


ኢንተርናሽናል በአፅዕሮተ-ቃል ታሊ በመባል ከሚጠራው ድርጅት በሚደረግ እርዳታ…መሆኑን ያሳውቁ፡፡

ይምሩ:- በሁሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙና ምንም ዓይነት ተግባራዊ የቢዝነስ ዕውቀት የመገብየት ዕድል
ላላገኙ መሠረታዊ የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና በጋራ እንሰጣለን፡፡

ይምሩ:- አነስተኛ የብድር ፕሮግራምም አለን፡፡ አንዳንዶቻችሁ በስተመጨረሻ ለዚህ ለታሊ የብድር
አገልግሎት ብቁ ልትሆኑ ትችላላችሁ የሚል እምነት አለኝ፡፡ ፕሮግራሙ በኑሮ ችግረኛ የሆኑ ደንበኞች ቢዝነስ
ለመጀመር ወይም ያላቸውን ለማስፋፋት እስከ ብር _____ የሚደርስ ዕቅድ ያወጣሉ፤ከ12 እስከ 18 ወራት
ባሉት ጊዜያት ውስጥ ብድሩን ከፍለው አስኪጨርሱ ድረስ ከታሊ ማህበራዊ ሞያተኛ ጋር አብረው ለመስራት
ቃል ይገባሉ፡፡ ደንበኛው ገንዘቡን ከፍሎ እንደጨረሰ፤ይሄው ገንዘብ በዚያው ማህበረሰብ ውስጥ ላለ ሌላ ሰው
ይሰጠዋል! በዚህ ፕሮግራም ላይ ፍላጎት ያላችሁ ዛሬውኑ ከዚህ ስልጠና በኋላ ልታነጋግሩኝ ትችላላችሁ፡፡

ይምሩ:- ከሁሉ አስቀድሞ፤ አንዳንድ ጠቃሚ የቢዚነስ ክህሎቶችን እንማራለን፡፡

ይምሩ:- በዚህ የስልጠና ክፍል፤ቢዝነስ እንዴት እንደሚጀመር፣እንዴት እንደሚካሄድ፣እንዲሁም እንዴት መሪ


መሆን እንደሚቻል እንማራለን፡፡ ስለ እግዚአብሔርም እንነጋገራለን፡፡

ይምሩ:- በቢዝነስ ሥልጠና ላይ ስለ እግዚአብሔር ለምን እንነጋገራለን? ለአፍታ ዝም ይበሉና ሀሳብ ያላቸው
ተሳታፊዎች ካሉ ለክፍሉ እንዲያጋሩ ይፍቀዱላቸው። ካልሆነ ይቀጥሉ።

ይምሩ:- ምክንያቱም እግዚአብሔር ስለ ምንሰራው ሥራ ግድ ይለዋል! እግዚአብሔር ራሱ ትጉህ ሠራተኛ


አምላክ ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ክፍል በሆነውና ስለ ዓለም አፈጣጠር በሚያስረዳው ኦሪት
ዘፍጥረት፣ እግዚአብሔር ሁሉን ነገር እንዴት እንደሠራው እናነባለን፡፡

ይምሩ:- ለእርሱ ተወዳጅ ፍጡራን የሆኑ ሰዎችንም ደግሞ ፈጥሯል። እናንተንና እኔን “በራሱ አምሳል”
ፈጠረን፡፡ ስለዚህም ልክ እንደ እርሱ ፈጣሪ እንድንሆን ተፈጠርን ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- እግዚአብሔር መጀመሪያ ለፈጠራቸው ሰዎች ሁለት ነገሮችን እንዲያከናውኑ ነግሯቸዋል፡- (1)
ፍጥረትን መግዛትና (2) ምድርን መሙላት። ዘፍጥረት 1÷28 እንዲህ ይላል፡-

” እግዚአብሔር ባረካቸው እንዲህም አላቸው ፤ ብዙ ተባዙ ፤ ምድርን ሙሏት ፤ ግዟት፤ የባህርን ዓሦችና
የሰማይ ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዟቸው።”

ይምሩ:- እግዚአብሄር የምንሰራውን ስራ ሰጠን! ቢዝነስ ማለት ቤተሰባችንን ፣ማህበረሰባችንን እና


ዓለማችንን ለመንከባከብ እግዚአብሔር በምድር ላይ የሰጠንን ስጦታ የምንጠቀምበት መንገድ ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- አንዳንድ ሰዎች፤ “ቢዝነስና እግዚአብሔር አይቀላቀሉም፤ምክንያቱም ቢዝነስ ማለት ገንዘብ


ማግኘት ሲሆን፡እግዚአብሔር ደግሞ ገንዘብን ይጠላል” ብለው ያስቡ ይሆናል፡፡ እውነታው ግን ሌላ ነው፤እርሱ
ገንዘብን አይጠላም፡፡ ለእኛ እንደሚያስፈልገን ያውቃል! ይልቁንም፣ ሰዎች ገንዘብን ከእግዚአብሔርና
ከወገናቸው በላይ አብልጠው ሲወድዱ ያዝናል ይናደዳልም፡፡

ይምሩ:- እግዚአብሔር ለዓለም አንድ ነገር እንድናበረክት እና የተሻለች እንድናደርጋት የሰጠን መርጃ
መሳሪያዎች ቢዝነስ እና ገንዘብ ናቸው። ቢዝነስ እና ገንዘብ ለእኩይ ወይም ለሰናይ ተግባራት ሊውሉ ይችላሉ
፡፡

18
ይምሩ:- በዚህ ስልጠና፤ ቢዝነስንና ገንዘብን ጨምሮ ሁሉም ነገሮች በእግዚአብሔር የተፈጠሩና የራሱ
የእግዚአብሔር መሆናቸውን በማስረዳት መጀመር እንፈልጋለን፡፡ ስለሆነም በቢዝነሶቻችን እና በገንዘባችን
እንዴት ለሌሎች መትረፍ እንደምንችል ለመማር እድሉ አለን።

ይምሩ:- እየተዝናናን ብዙ ብዙ እንደምንማር ተስፋ አደርጋለሁ! ብዙ መዝናኛዎች ይኖሩናል፤በትንንሽ


ቡድኖች በመከፋፈል ውይይቶች እናደርጋለን፤ፈቃደኛ ሠልጣኞች መድረክ ላይ በመውጣት የገባቸውን
እንዲያጋሩ/እንዲያካፍሉ/ እንጠይቃለን፡፡

ይምሩ:- ከትንሽ ነገር ተነስታችሁ ቀስ በቀስ ለማደግ እያንዳንዳችሁ ፈቃደኛ ከሆናችሁ፤በዚህ ምድር ላይ
ስትኖሩ በእግዚአብሔር የተፈጠራችሁለትን ዓላማ እንደምታሳኩ እናምናለን፡፡ እናንተም ወደዚህ በመምጣት
የመጀመሪያውን እርምጃ ወስዳችኋል!

ይምሩ:- ስለዚህ ይህን ስልጠና በሚገባ ለመከታተል ከፍተኛ ጥረት እንድታደርጉ እናበረታታችኋለን ፡፡ ተሳተፉ!
ፈቃደኛ ሁኑ! ሀሳባችሁን አጋሩ! የቤት ሥራችሁን ሥሩ!

ይምሩ:- መጀመሪያ ላይ ያልተለመደ ስሜት ሊሰማችሁ ይችላል፤ነገር ግን በዚህ ስልጠና ውጤታማ ለመሆን
ተመራጩ መንገድ ተሳትፎ ማድረግ እንደሆነ ቃል እንገባላችኋለን።

ይምሩ:- ለሠልጣኞች የተዘጋጀውን መጽሐፍ በሚገባ እንድትገለገሉበት ደግሞ እንጋብዛችኋለን፡፡


(የሠልጣኞችን መጽሐፍ ከፍ አድርገው ያሳዪ።)

ይምሩ:- እነዚህ ለእናንተ የተበረከቱ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ልክ ስትመረቁ ወደየቤታችሁ ትወስዳላችሁ!


በውስጡ ሥዕል መሳል፣ጠቃሚ ሀሳቦች ላይ ማክበብ፣ከስሩ ማስመርና ማስታዎሻዎችን መጻፍ ትችላላችሁ፡፡

ይምሩ:- ብዙ ስለምንማር ሁሉንም ለማስታወስ ከባድ ሊሆንብን ይችላል፤ አንኳርና ጠቃሚ ነጥቦችን
በመጽሐፍቶቻችን ላይ የምንጽፍ ወይም የምንስል ከሆነ ግን የተማርነውን ለማስታወስ በጣም ቀላል
ይሆንልናል፡፡

ይምሩ:- አሁን የምንጀምርበት ሠዓት ደርሷል። እስቲ ስማቸውንና ከዚህ ስልጠና ምን ለማግኘት ተስፋ
እንዳደረጉ ሊነግሩን የሚችሉ በጎ ፈቃደኛ ሰዎች ይኖራሉ?

ይምሩ:- ዋው!ሁላችሁም ጥሩ መረዳት ነው ያላችሁ፡፡ ሁላችሁንም እናመሰግናለን!

ይምሩ:- ቀጣዩን ክፍል ከመጀመራችን በፊት፤እራሳችንንም ሆነ ሌሎችን እንዳናደናቅፍ ሞባይል ስልኮቻችንን


እንድንዘጋ ለሁሉም ሰው ማሳሰብ እፈልጋለሁ፡፡ በእረፍት ጊዜያት ግን መደወል ወይም መሴጅ መላክ
ትችላላችሁ።

ይምሩ:- አሁን “ትልቅ ህልም ይኑርህ” ወደ ሚለው ትምህርት እናመራለን! የሚቻል ከሆነ እና እስካሁን
ካላደረጉት፤ አንድ የትንሽ ቡድን አመቻች ወይም በጎ ፈቃደኛ ይምረጡና በጸሎት እንዲከፍት ያድርጉ።

19
// ክፍል 2 //

በትልቁ አልም
የሚወስደው ጊዜ፡- 1 ሠዓት

ግቦች:-
﹥ ሠልጣኞች፤ ስለ ወደፊታቸው በፈጠራ የታጀበ ክህሎት እንደሚያዳብሩ ይገነዘባሉ፤
﹥ ሠልጣኞች ፤እንዴት እንደተፈጠሩ እና በማህበረሰባቸው ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሰው ምን ያህል ዋጋ
እንዳለው ይገነዘባሉ፤
﹥ ሠልጣኞች፤ ለራሳቸው፣ለቤተሰቦቻቸው እና ለማህበረሰባቸው ሊኖራቸው የሚገባውን ትልቅ ተስፋ
ለይተው ያውቃሉ፡፡

አቅርቦቶች፡-
﹥ እስክርቢቶዎች ﹥ መቀሶች
﹥ የሠልጣኞች መጽሐፍ ﹥ እንደ ከረሚላ ያሉ ጣፋጭ ነገሮች
﹥ የእርሳስ ቀለሞች! ﹥ ነጭ ሰሌዳ
﹥ ሁለት በእኩል መጠን የተቆረጡ የልብ ቅርጽ ﹥ የነጭ ሰሌዳ ማርከሮች
ያላቸው እና አንደኛው ምንም ያልተነካ
ካርቶን፣ወረቀት፣ሌላኛው ግን ብዙ ቦታ
የተቆራረጠ ስስ ወረቀት

ትዕይንቶች (በግድግዳ ላይ የተለጠፈ ወይም በሠልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰ)


﹥ የሰውነት ክፍሎችን የሚያሳይ

ዝግጅት:-
﹥ የልብ ቅርጽ አዘገጃጀት፡፡ ከሁሉ አስቀድመው ሁለት የካርቶን ዓይነት ጠንካራ ወረቀቶችን በእኩል
መጠን በልብ ቅርፅ ቀርጥጠው ያውጡ፡፡ ከዚያም አንደኛውን የልብ ቅርጽ የያዘ ወረቀት በሰልጣኞችና
በአመቻቾች ቁጥር ልክ በምላጭ ወይም በመቀስ ይቆራርጧቸው (ልክ እንደ puzzle ማለት ነው)፡፡
እያንዳንዱ ቁርጥራጭ! የመጀመሪያውን የልብ ቅርጽ እንደጠበቁ! በሌላኛው የልብ ቅርጽ ወረቀት ላይ
እያስደገፉ ይሳሏቸው፡፡ ለሰልጣኞች ከማደልዎ በፊት ከእያንዳንዱ ቁርጥራጭ ጀርባ እንዲሁም ከስር
ባለው ወረቀት ላይ ቁሮችን መጻፍ አይርሱ። ወደ ትምህርቱ ከመግባትዎ አስቀድሞ በእያንዳንዱ
ሠልጣኝ ፊት ለፊት ባለ ጠረጴዛ አንዳንድ ቁርጥራጭ ያስቀምጡ፡፡ ትምህርቱ እንደተጠናቀቀ አንድ
ፈቃደኛ ተነስቶ ሁሉንም ቁራጭ ወረቀቶች እንዲሰበስብ ያድርጉ፡፡
﹥ የተመደበው ሠዓት ሲደርስ ከመጽሐፍ ቀዱሳዊ ማጣቀሻው ውስጥ የተለያዩ ጥቅሶችን ጮክ ብለው
የሚያነብቡ ሌሎች ፈቃደኛ ሠልጣኞችን ያዘጋጁ፡፡ የሚነበቡ ጥቅሶችን በየመጽሐፍ ቅዱሶቻቸው
ላይ የተለየ ምልክት እንዲያደርጉ ለተሳታፊዎች በሙሉ ይነገሯቸው! እርስዎም ስለጥቅሶቹ
የሚያጋሩትን ፈቃደኞች ለመለየት እንዲያስችልዎ ስሞቻቸውን በመምሩ መምሪያ ላይ በየቁጥሮቹ
ትይዩ ስሞቻቸውን በእርሳስ ይጻፉ፡፡

20
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ:-
﹥ መዝሙር 37÷4
﹥ ሉቃ. 1÷37
﹥ 1ኛቆሮ. 12÷14-26

በጎ ፈቃደኛ:- የልብ ቅርጽ የያዙ ቁርጥራጭ ወረቀቶችን ያድል፡፡ በሰልጣኞችና በቡድን አመቻቾች ቁጥር ልክ
መሆኑን በጎ ፈቃደኛው ያረጋግጥ፡፡ ይህን አስቀድሞ ማዘጋጀት ይገባል፣ ዝርዝሩን በማስታወሻው ላይ
ይመልከቱ ፡፡

ይምሩ:- ሠላም ለእናንተ ይሁን፤እንደምን አላችሁ! ሁላችሁም እዚህ በመገኘታችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ከእናንተ ጋር ለመተዋወቅ እና በዚህ ስልጠና አብረን መሳተፍ በመቻላችን በጣም ደስ ይለናል፡፡

ይምሩ:- መሪ አመቻች እንደመሆንዎ ከሰልጣኞች ጋር ጥሩ ግንኙነት ለመመሥረት ትንሽ ስለ ራስዎ እና ስለ


ኋላ ታሪክዎ ያጋሯቸው፡፡

ይምሩ:- በዚህ ስልጠና ወቅት ሁላችንም ቢዝነስ ለመጀመር ወይም ያለንን ለማሻሻል የሚያስችሉንን አዳዲስ
ክህሎቶች እንማራለን፡፡

ይምሩ:- ከዚያ በፊት ግን፣ጥቂት ጊዜ ወስደን እንተዋወቅ፡፡ ትንንሽ ቁራጭ ወረቀቶች ከመጽሐፍቶቻችሁ ጎን
ለሁላችሁም አንድ አንድ ተቀምጠዋል።

ልምምድ

ይምሩ:- አሁን፤ እያንዳንዱ ሰው ከፊት ለፊቱ ባሉ ጠረጴዛዎች ላይ የተቀመጡትን የእርሳስ ቀለማት


በመጠቀም በተቆራረጠው ወረቀት ላይ የሚያምር እና ስለራሱ ማንነት /ምንነት/ የሆነ ነገር የሚናገር ስዕል
እንዲስል አንፈለጋለን። እርስዎን ከሌላው ልዩ የሚያደርግልዎ ምንድን ነው? በህይወትዎ ወሳኝ የሚሉት ነገር
ምንድነው? ምን ይወዳሉ? በስዕል ይግለጹት! ዘና ፈታ ይበሉ፤ ለየት ባለና በፈጠራ በታጀበ መልኩ ይሁን!
አራት ደቂቃ! ያህል ጊዜ አለዎት፡፡

ይምሩ:- እርስዎ ራስዎ ቀደም ብለው ሠርተው በምሳሌነት ሊያሳዩዋቸው ይችላሉ። አራት ደቂቃዎች
ይፍቀዱላቸው ፡፡ ከአንድ ደቂቃ በፊት ማስጠንቀቂያ ይስጡ ፡፡

ይምሩ:- አሁን እያንዳንዳችን የሠራነውን ስራ ለየቡድናችን የምናስተዋውቅበት ሠዓት ነው፡፡ በቁራጭ


ወረቀትዎ ላይ የሳሉትን ሥዕል በማሳየትና ምንን እንደሚወክል በማብራራት ይጀምሩ።

ቡድን አመቻቾች፡- ለ10 ደቂቃ ያህል፡፡ በቅድሚያ ራሳችሁን ምሳሌ አድርጋችሁ ስማችሁን አስተዋውቁ፤
ከየት እንደመጣችሁ፤ስለ ትዳር ሁኔታ፤ያገባችሁ ከሆነ ስለ ባለቤታችሁና ልጆቻችሁ፤ያላገባችሁም ከሆነ ስለ
ወላጆቻችሁና እህት ወንድሞቻችሁ አጋሩ። ከዚያም አሁን በምን ስራ ላይ እንደምትገኙ ወይም ስለ
ቢዝነሳችሁ ግለጹላቸው። በመጨረሻም በቁራጩ ወረቀት ላይ ምን እንደሳላችሁና ሥዕሉ ስለ እናንተ ምን

21
እንደሚናገር በዝርዝር አስረዱ። እነሱም ተራ በተራ እንዲሁ እንዲያደርጉ ጋብዙ። በደንብ ለመተዋወቅና
ለመግባባት እንዲያግዛችሁ እነሱ ሲናገሩ ልብ ብላችሁ አዳምጡ፡፡

ይምሩ:- ስለራሳችሁ ባጋራችሁን ነገር በጣም ደስ ብሎናል፡፡ እናመሰግናለን! በቀጣይ ሳምንተት የበለጠ
ለመማር በጉጉት እንጠብቃለን።

በጎ ፈቃደኛ:- ቁርጥራጮቹን ወረቀቶች ከሰልጣኞች ላይ ይሰብስቡ እና ጀርባቸው ላይ በተጻፈው ቁጥር


መሠረት ቦርድ ላይ በተለጠፈው በሌላኛው የልብ ቅርጽ ካርቶን ላይ በአግባቡ ይለጥፏቸው፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ
መሪው ማስተማሩን ይቀጥላል። የልብ ቅርጹን ጠብቆ ተለጥፎ እንዳለቀ በስርዓተ ትምህርቱ ውስጥ
እንደተገለጸው ትኩረትዎን ወደ ምስሉ ይመልሱ።

ይምሩ:- አሁን፤ ስለ ቢዝነስ ማውራት ከመጀመራችን በፊት ህልም ስለ ማለም አንዳንድ ሃሳቦችን
እንዳስሳለን፡፡ ህልሞች ማለቴ ተኝታችሁ የምታልሙትን ዓይነት ማለቴ ሳይሆን፤ለወደፊቱ ስለ ራሳችን ሆነ
ስለ ልጆቻችንና ስለ ማህበረሰባችን ተስፋ ወይም የወደፊት ዕጣ ፈንታ ማለቴ ነው ፡፡

ይምሩ:- በብዙ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ከመጠመዳችን የተነሳ፤ ስለ ወደፊት ተስፋችን በእውነት
ለማሰላሰያ ጥቂት ጊዜ እንኳ የለንም፡፡ እንዲያውም አንዳንዴ ጊዜ የሚኖረን ምግብ ለማዘጋጀት ፣ መደበኛ
ስራችንን ለመስራት ወይም ቤተሰባችንን ለመንከባከብ ብቻ ነው፡፡

ይምሩ:- ዛሬ ግን ጊዜ ወስደን ወደፊት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር በእውነት ማሰላሰል ያስፈልገናል፡፡ እናም
ይህንን በትክክል ለማከናወን፤ምንም እንኳን አሁኑኑ መተግበር እንችላለን ብለን ባናስብም፤ ህይወታችንን
የተሻለ ያደርግልናል ብለን ያመንነውን ማንኛውንም ነገር ለማሰብ እራሳችንን ነጻ ማድረግ አለብን።

ይምሩ:- በሕይወት ዘመን ሁሉ እንደሚቻል እያንዳንዳችን በዓይነ ሕሊናችን ልንስለው ያስፈልጋል፡፡ ከሁሉ
አብልጠን በነጻነት ልንፈልጋቸውን የሚገቡ ነገሮች አሉ።

ልምምድ

ይምሩ:- በየቡድኑ ውስጥ ያለን እያንዳንዳችን ወደፊት በተስፋና በጉጉት ከምንጠብቃቸው ህልሞች አንዱን
እንመርጣለን፤ እናም ያንን ህልም በስዕል እንድንገልጸው እፈለጋለሁ፡፡ ስዕሉን እየሳላችሁ ምን ደስ
እንደሚያሰኛችሁ አስቡ፡፡ ለራሳችሁ፣ለቤተሰባችሁ፣ለማህበረሰባችሁ እና ለወደፊቱ ቢዝነሳችሁ ምን
እንደሚያስፈልጋችሁ አስቡ ፡፡

ይምሩ:- እስከዛሬ ድረስ ምንም ዓይነት የቢዝነስ ሃሳብ ካልነበራችሁ፣ምንም ማለት አይደለም፡፡
ለማህበረሰባችሁ አስፈላጊ የሆኑ የተለያዩ የቢዝነስ አይነቶችን ለማሰብ ይህንን ጊዜ ተጠቀሙ።

ይምሩ:- በህይወት ዘመናችን ልናገኛቸው ወይም ልናከናውናቸው ስለምንፈልጋቸው ነገሮች ስናስብ ወደ


አዕምሯችሁ ቀድሞ የሚመጣው ምንድን ነው? በመጽሐፍቶቻችሁ በገጽ ____ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በስዕል
አስፍሩ፡፡

22
ቡድን አመቻቾች፡፡ ለ5 ደቂቃ ያህል፡፡ ሥራ ፈጣሪዎች/ሰልጣኞች/ በመጽሐፍቶቻቸው ላይ ለመሳል ጊዜ
ይስጧቸው፡፡ ማንኛውንም ዓይነት ሙከራዎቻቸውን ያለማቋረጥና ያለመሰልቸት በማድነቅ እያበረታቱ ጥሩ
ተግባቦት ለመፍጠር ይጣሩ!

ይምሩ:- አሁን ደግሞ አንድ አንድ ፈቃደኞች ከየቡድኑ ወደ መድረኩ ይመጡና በስዕል ስለገለጻችኋቸው
ህልሞች ይነግሩናል፡፡

ይምሩ: - ከየጠረጴዛው አንድ ፈቃደኛ ወደ እርስዎ እንዲመጣ ይጋብዙ፡፡ ለህልማቸው እውቅና እና ሞራል
ይስጧቸው፡፡ ለእያንዳንዱ ተሳታፊም እንደ ከረሚላ ያሉ ጣፋጭ ነገሮችን ይሸልሟቸው ፡፡

ይምሩ:- እስቲ አሁን ደግሞ “እነዚህ የገለጽናቸው ህልሞቻችንን እውን ማድረግ እንችላለን ብለን እናስባለን?”
በሚል ከአጠገባችን ካለ ጓደኛ ጋር ጥንድ ጥንድ ሆነን እንወያያለን፡፡

ቡድን አመቻቾች: - ለ4 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ይህንን ውይይት ይምሩ ፡፡ ሥራ ፈጣሪ ሠልጣኞች ህልማችንን
ማሳካት አንችልም የሚል እምነት ያደረባቸው ከሆነም ምንም ማለት አይደለም፡፡ ዋናው ጉዳይ ያሉበትን
ሁኔታ ምንም ሳይደብቁ መናገራቸውና ስሜቶቻቸውን ማጋራት መቻላቸው ነው ፡፡

ይምሩ:- አንዳንድ ጊዜ ሕልሞቻችን ልንደርስባቸው የማንችል በጣም ሩቅ ይመስሉናል፣ነገር ግን


እግዚአብሔር አምላክ በእርሱ እርዳታ ብዙ ነገሮችን ማከናወን እንድንችል አድርጎ እንዳዘጋጀን እናምናለን።

ይምሩ:- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለዚህ ጉዳይ የሚናገር አንድ ጥቅስ አለ፡፡ መዝሙር 37÷4 እንዲህ ይላል:-
“በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።”

ይምሩ:- ይህ ጥቅስ የሚነግረን ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ካለን እና የምንወደው ከሆነ፤ህልሞቻችንን


በውስጣችን ያስቀመጠው እርሱ እንደሆነ ማመን እንደምንችል ነው፡፡ በእሱ እርዳታ፣ከዚህም በላይ ለእኛ
ያለው ትልልቅ ህልሞች እንኳን ቢሆን እውን እንደሚሆኑ ልናምን እንችላለን፡፡

ይምሩ:- እግዚአብሔር፤ አመክንዮ ማቅረብ (ምክንያታዊነት)፣መማር እና ማደግ የሚችሉ አዕምሮዎችን


ሰጥቶናል፡፡

ይምሩ:-ይህ ደግሞ አዳዲስ ተሰጥኦ እና ክህሎቶችን መገብየት እንችላለን ማለት ነው። ሕፃናት በነበርንበት
ጊዜ መራመድን እንደተማርን፤ እንዲሁ አናጺነት፣ሂሳብ መዝገብ አያያዝ፣በምግብ ዝግጅት፣እና መሠል
ሞያዎች እስካሁን አልሰለጠንን ይሆናል፤ለመማር ግን ፍቅሩ ሊኖረን ይችላል፡፡ ይህም እግዚአብሔር ወደ ሰጠን
ሕልሞቻችን ጋር እንድንጠጋ ያደርገናል።

ይምሩ:- እርስዎም በአንድ ወቅት የነበረዎት ህልምና ተስፋ ከእግዚአብሔር የተሰጠዎት ጸጋ መሆኑን
በማመንዎ እንዴት ለውጤት እንደበቁ ለሰልጣኞች ምስክርነትዎን ያጋሯቸው።

ይምሩ:- አሁን በውስጣችን ያሉት መሻቶችና ተስፋዎች ከእግዚአብሔር ቃል የመነጩ ከሆነ፤ በእውነቱ
ትልልቅ ነገሮች ላይም በነፃነት ተስፋ ማድረግ እንችላለን፡፡

23
ይምሩ:- በእኛ በራሳችን ብቻ ማከናወን አንችልም ብለን ብናስብ እንኳ፤በሉቃስ 1÷37 ላይ “ለእግዚአብሔር
የሚሳነው ነገር የለም” በሚለው የእግዚአብሔር ቃልመተማመን እንችላለን፡፡

ይምሩ:- ሑላችንም አንድ ዓይነት ብንሆን ኖሮ፤ዓለም ምሉዕ (የተሟላች) ባልሆነች ነበር፡፡ ዓለማችንን
በሚገባ ውጤታማ እንድትሆን፤እኛ ሁላችን የተለያዩ ክህሎቶቻችንን ተጠቅመን ፡የተለያዩ ግቦቻችንን
አንግበን ለማህበረሰቦቻችን ፋይዳ ያላቸው ነገሮችን ለማበርከት መጣር አለብን።

ይምሩ:- በተመሳሳይ ሁኔታ፤እኛም እያንዳንዳችን ዛሬ እዚህ የተገኘነው ለተለየ ዓላማ ነው፡፡

ይምሩ:- እኛ እያንዳንዳችን በማህበረሰባችን ውስጥ ልንጫወት ስለሚገባው ከፍተኛ ሚና ለማሳየት መጽሐፍ


ቅዱስ ከብልቶች ጋር በማነጻጸር ይናገራል። 1ኛቆሮንቶስ 12÷14-26 እንዲህ ይላል፡፡

አካል ብዙ ብልቶች እንጂ አንድ ብልት አይደለምና፡፡ እግዚአብሄር እኔ እጅ አይደለሁምና የአካል ክፍል
አይደለሁም ብትል ይህን በማለትዋ የአካል ክፍል መሆንዋ ይቀራልን? ጆሮም፡-እኔ አይን አይደለሁምና የአካል
ክፍል አይደለሁም ቢል ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆንዋ ይቀራልን? አካል ሁሉ አይን ቢሆን መስማት
ወዴት በተገኘ? ሁሉም መስማት ቢሆን ማሽተት ወዴት በተገኘ? አሁን ግን እግዚአብሄር እንደ ወደደ
ብልቶችን እያንዳንዳቸው በአካል አድርጎአል፡፡ ሁሉም አንድ ብልት ቢሆንስ አካል ወዴት በሆነ? አይን፡- እጅን
አታስፈልገኝም ልትለው አትችልም ወይም ራስ ደግሞ እግሮችን፡-አታስፈልጉኝም ሊላቸው አይችልም፡፡ ነገር
ግን ደካሞች የሚመስሉ የአካል ብልቶች ይልቁኑ የሚያስፈልጉ ናቸው፡፡ ከአካልም ብልቶች ያልከበሩ ሆነው
የሚመስሉን በሚነዛ ክብር እናለብሳቸዋለን፡፡ በምናፍርባቸውም ብልቶቻችን ክብር ይጨመርላቸዋል፤ ክብር
ያላቸው ብልቶቻችን ግን ይህ አያስፈልጋቸውም፡፡ ነገር ግን ብልቶች እርስ በርሳቸው በትክክል ይተሳሰቡ ዘንድ
እንጂ በአካል መለያየት እንዳይሆን ለጎደለው ብልት የሚበልጥ ክብር እየሰጠ እግዚአብሄር አገጣጠመው፡፡
አንድም ብልት ቢሰቃይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሰቃያሉ ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ
ጋር ደስ ይላቸዋል፡፡

ይምሩ:- እያንዳንዱ የአካል ብልት (ክፍል) የተለየ ይመስላል፤እውነትም ለልዩ ዓላማምና ተግባር የተሰሩ ልዩ
ፍጥረት ናቸው፡፡

ይምሩ:- እንዴት ማለም እንዳለብን ከተማርን፡ ዓላማችንን እንድንረዳ ያደርገናል፡፡

ይምሩ:- በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያሉ ሕልሞች ልዩ ናቸው፡፡ እነዚህን ህልሞቻችንን እውን ለማድረግ


ካልተንቀሳቀስን፤ ለማህበረሰባችን፣ቤተሰባችን ብሎም ለዓለም አንድ ነገር እናጎድላለን ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- በሰሌዳው ላይ ወይም በሠልጣኞች መጽሐፍ ላይ ወዳለው የ“አካል ክፍሎች”ን ወደሚያሳየው


ትዕይንት ያመልክቷቸው። አካላችን በብዙ የተለያዩ ብልቶች የተገነባ ነው፡፡ እያንዳንዱ ብልት እጅግ አስፈላጊ
እና ልዩ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።

ይምሩ:- እያንዳንዱ ብልት ለአካሉ ውጤታማ ክንዋኔ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል። አንድ ብልት ቢጎዳ
ወይም ቢወገድ፣መላው አካል ይጎዳል።

ይምሩ:- እያንዳንዱ ብልት፤ምንም እንኳን የተለያየ ቢሆንም፤አገልግሎቱ እኩል ነው፡፡ ዐይን እጅን
አታስፈልገኝም ሊለው አይችልም። እግር ከአፍ የተሻለ አስፈላጊ አይደለም፡፡ አካል ምሉዕ (የተሟላ) ለመሆን
ሁሉም ብልቶች ያስፈልጉታል።

24
ይምሩ:- አንድ ብልት፤ ማለትም እግር ፣ ዐይን ፣ ጆሮ ወይም እጅ፤ ቢጎድል አካል ሙሉ ሁኖ መሥራት
እንደማይችል ሁሉ÷ማህበረሰባችንም በልዩ ተሰጥኦ ወደዚህ ዓለም የሚመጡትን ሰዎች በሙሉ አካትቶ
የማይጠቀም ከሆነ ስኬታማ ሊሆን አይችልም፡፡

ይምሩ:- ጥሩ ማገናዘብ፣ሌሎችን መረዳት ፣ጠንክሮ መሥራት፣መጓዝ፣ማፍቀር የሚችሉ እንዲሁም መማርና


መርዳት የሚወድዱ ሰዎችን ማህበረሰባችን ይፈልጋል፡፡

በጎ ፈቃደኛ:- ተለጥፎ የተጠናቀቀውን የልብ ቅርጽ እይታው ላይ እንደተጣበቀ ይያዙና ሁሉም ሠልጣኞች
በቅርበት ሊያዩት ወደሚችሉበት ርቀት ይጠጉና ያሳይዋቸው።

ይምሩ:- እነዚያ ቁርጥራጭ ወረቀቶች ተገጣጥመው ይህ የልብ ቅርጽ የተሰራበትን መንገድ እንዴት
አያችሁት? ወደዳችሁት? እጅግ በጣም ቆንጆ ይመስለኛል፡፡

ይምሩ:- ከሁሉም በላይ ምኑን እንደወደድኩት ታውቃላችሁ?

ይምሩ:- የሁሉም ሰልጣኝ ቁራጭ ወረቀቶች በዚህ ውስጥ መካተታቸውን ሳስብ ደስታ ይሰማኛል።

ይምሩ:- ይሄን የልብ ቅርጽ ራሴ ብቻዬን ብሠራው ኖሮ ይሄን ያህል ቆንጆ ይሆን ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ?፡፡
(በፍጹም!)

ይምሩ:- ለምን? (ምክንያቱም ውብ እና የተሟላ ለማድረግ የእያንዳንዱ ሰው የፈጠራ ስራ ያስፈልጋል)።

ይምሩ:- ምላሽ እንዲሰጡ ያበረታቷቸው። እንደከረሚላ ያሉ ጣፋጭ ነገሮችን መሸለምም አይርሱ፡፡

ይምሩ:- ልቡ እንዲህ ይበልጥ ውብ የሆነው የእያንዳንዱ ሰው ድርሻ ስለተካተተበት ነው፡፡

ይምሩ:- አንድ ሰው ብቻውን ከሚሠራው ስራ ይልቅ እያንዳንዳችን አንድ አንድ ቁራጭ ድርሻ ስናበረክት
ሙሉ ገጽታው እጅግ የሚያምር መሆኑን በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ አይተናል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ፡ ሁላችን
ራሳችንን የምንገልጥበት መንገድ የተለያየ ሊሆን ይችላል፤ይሁን እንጅ ውብና የተሟላ ለመሆን የእያንዳንዱ
አስተዋፅኦ አስፈላጊ ነው ፡፡

ይምሩ:- ከዚህ ትምህርት ስለቀሰማችሁት አንድ ነገር ሊነግሩኝ የሚችሉ ከመካከላችሁ ሁለት ሰዎች
ይኖራሉ?

ይምሩ:- ሁለት ሰዎችን ወደ መድረክ ይጥሩና አንድ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ ፡፡ መልሳቸውን እንደገና
በመድገም አስረግጠው ይናገሩ፡፡

ይምሩ:- አሁን የእረፍት ጊዜ ነው፡፡ ተመልሰን ስንመጣ፤ መሰናክሎችን ስለማለፍ እንነጋገራለን፡፡

25
// ክፍል 3 //

መሠናክሎችን ማለፍ

የሚወስደው ጊዜ፡- 1 ሠዓት

ግቦች:-
﹥ ተሳታፊዎች ፤/ሠልጣኞች/ መሠናክሎችን ስለማለፍ ዕውቀት ይገበያሉ፤
﹥ ተሳታፊዎች፤ ለችግሮች እንዴት መፍትሄ እንደሚሰጡና በሕይወታቸው የሚገጥሟቸውን
መሠናክሎች እንዴት ማለፍ እንደሚችሉ ለይተው ማወቅ ይጀምራሉ፤
﹥ ተሳታፊዎች፤ ለግል ሕይወታቸውም ሆነ ለቢዝነስ ሥራዎቻቸው ግብ ማስቀመጥ ይጀምራሉ፡፡

አቅርቦቶች፡-
﹥ እስክርቢቶዎች ﹥ የዐይን መሸፈኛ /ስካርፍ/
﹥ የሠልጣኞች መጽሐፍ ﹥ የጊዜ መቆጣጠሪያ ሠዓት
﹥ የእርሳስ ቀለሞች ﹥ እንደ ከረሚላ ያሉ ጣፋጭ ነገሮች
﹥ መጽሐፍ ቅዱስ ﹥ ነጭ ሰሌዳ
﹥ የመሠናክል ቁሳቁስ ﹥ የነጭ ሰሌዳ ማርከሮች

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


﹥ መሠናክሎች
﹥ ግቦች

ትዕይንቶች (በግድግዳ ወይም በቦርድ ላይ የተለጠፉ ወይም በሠልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ


የተጠቀሱ)
﹥ መሠናክሎች

ዝግጅት፡-
﹥ ስልጠናው ከመጀመሩ አስቀድሞ፤ ከቤት ውጭ ወይም ግልፅ ቦታ ላይ ለጨዋታ በሚያመች መልኩ
የመሠናክል ቁሳቁሶችን ይደርድሩ፤ስለ ጨዋታው ማን ማብራሪያ እንደሚሰጥም ይወስኑ፡፡ አስቀድሞ
መደርደር የማይቻል ከሆነ ደግሞ፤ የመሠናክል ቁሳቁሶችን ብቻ ዝግጁ ያድርጉና ልክ ስልጠናው
እንዳጠናቀቁ በፍጥነት ወደቦታው ሄደው ሊደረድሩልዎት የሚችሉ ፈቃደኞችን ይምረጡ፡፡
﹥ የመሠናክል መስሪያ ቁሳቁሶች፤አግዳሚ ወንበሮችን በተለያየ መንገድ በማጋደም፣ወንበሮችን እርስ
በእርስ ፊት ለፊት አገጣጥሞ በማጋደም፣የውሃ ቧንቧዎች፣የዛፍ ቅርንጫፎች፣ወዘተ. ሊሆኑ የችላሉ፡፡
መነሻና መድረሻው በግልጽ ተለይቶ የሚታወቅና ወደ 10 ሜትር የሚሆን ርቀት ያለው መሆን
አለበት፡፡
﹥ በመሠናክል ስልጠናው ጊዜ ሠዓት የሚቆጣጠርና እንደ ከረሚላ ያሉ ጣፋጮችን ይዞ ከመስመሩ
መጨረሻ ላይ የሚቆም ሌላ ፈቃደኛ አመቻች ይመድቡ፡፡

26
﹥ ይህ ስልጠና፤ “የካፒታል ወይም የገንዘብ እጥረት ተጨባጭ ወይስ ምናባዊ መሠናክል?” የሚለውን
ውይይት ያካትታል፡፡ ውይይቱ፤ ሰልጣኞቹ ግባቸውን ለማሳካት እንዲንቀሳቀሱና ቢዝነስ እንዲጀምሩ
በማድረግ ረገድ ወሳኝ ሚናን ይጫወታል፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ:-


> ሮሜ 12÷2
> መዝሙር 139÷14

ይምሩ:- ሁላችሁም በድጋሚ እንኳን ደህና መጣችሁ! አሁን ህልም ማለምን አብረን እየተማርን
ስለሆነ፣እያንዳንዳችሁ ቢዝነስ ያላችሁም ሆነ አንድ ቀን እንከፍተዋለን ብላችሁ ተስፋ ስለምታደርጉት ነገር
እንድታስቡ እፈልጋለሁ፡፡

ይምሩ:- ምንም እንኳን ስኬታማ ቢዝነስ እንዲኖረን ብንፈልግም፤አንዳንድ ጊዜ ይህን ግብ ማሳካት በብዙ
ምክንያቶች አስቸጋሪ ሊሆንብን ይችላል፡፡

ይምሩ:- አንደኛው ምክንያት፤ በምን ዓይነት ቢዝነስ ስኬታማ እንደምንሆን ርግጠኞች አለመሆናችን ሊሆን
ይችላል፡፡ ሌላው ምክንያት ደግሞ፤ ቢዝነሳችንን ለመቀጠል ወይም አዲስ ለመጀመር የቤተሰባችን ድጋፍ
አለመኖር ወይም ስኬታማ ሊያደርገን የሚችል የገንዘብ አቅም ወይም ችሎታ የለንም ብለን ማሰባችን
ይሆናል፡፡

ይምሩ:- አንዳንድ ጊዜ፤​​ቤተሰባችንን በመንከባከብ ወይም ምግብ ለመሸመት፣የት/ቤት ክፍያና የመሳሰሉ


ወጪዎችን ለመሸፈን በዕለት ተዕለት ስራ ከመወጠራችን የተነሳ አዲስ ነገር ለመሞከር ጊዜ አይኖረንም፡፡

ይምሩ:- ህልማችን እውን እንዳይሆን የሚያግዱን ወይም የቢዝነሳችንን ስኬት የሚያደናቅፉ ሁኔታዎች
መሠናክሎች ይባላሉ፡፡
ይምሩ:- እስቲ መሠናክል ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቅ?

ይምሩ:- ለሚሰጡ መልሶች እንደከረሚላ ያሉ ጣፋጭ ነገሮችን ምላሾች ይሸልሙ፡፡ (ግቦቻችን ላይ


እንዳንደርስ የሚከለክል ማንኛውም ነገር)፡፡

ይምሩ:- ትዕይንቱ ላይ ወዳለው መሰናክል ያመልክቷቸው። በምሥሉ ላይ እንደምታዩት፤አንድ ወንድና አንዲት


ሴት በጉዞ ላይ እያሉ መንገዳቸው ላይ የተጋደመ መሠናክል ገጠማቸው። በዚህ ምስል ላይ ያለው መሰናክል
ምን እንደሆነ ሊነግረኝ የሚችል ማን ነው? (የወደቀ ዛፍ):: እንደከረሚላ ያሉ ጣፋጭ ነገሮችን ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- አሁን የመሠናክሎችን ጨዋታ ልንጀምር ነው፤ እናም ሶስት በጣም ጎበዝ እና ፈጣን የሆኑ የሚያግዙን
ፈቃደኞችን እንፈልጋለን፡፡እስቲ ማነው ፈቃደኛ?

ይምሩ:- ኑ ወደ መሠናክል ጨዋታው እንሂድ፡፡

ልምምድ

27
ይምሩ:- ሁሉንም ሰልጣኞች ወደ መሠናክል ጨዋታው ይውሰዱና በዙሪያው ክብ ሰርተው እንዲቆሙ
ያድርጉ፡፡ ሠዓት ተቆጣጣሪ አመቻቹ ከመሠናክሎች መጨረሻ ጫፍ ላይ እንደከረሚላ ያሉ ጣፋጮችን ይዞ
እንዲቆም ያድርጉ፡፡

ይምሩ:- ይህ ጨዋታ ህይወታችንን ይወክላል፡፡ ልክ በጨዋታው መጨረሻ እንደምንሸለመው ጣፋጭ፤


ሁላችንም በህይወታችን እውን ሆኖ ማየት የምንመኘው ህልም አለን፡፡

ይምሩ:- ቀጣዩን መመሪያ እያስተላለፉ፡ መሰናክሎችን እንዴት በመራመድ ማለፍ እነደሚቻል ያሳዩ ፡፡

ይምሩ:- እዚያ ጫፍ ላይ ጣፋጮችን ይዞ የቆመው ሰው ጋ ለመድረስ ማንኛውም ፈቃደኛ ሠልጣኝ እነዚህን


መሠናክሎች ማለፍ ያልፋል፡፡ አስታውሱ፤መሠናክሎችን ተሸግሮ መሄድ እንጅ ዙሮ ማለፍ አይቻልም፡፡

ይምሩ:- እያንዳንዱ ሰው በተናጠል በምን ያህል ፍጥነት እንዳጠናቀቀ ለማወቅ ሠዓት እንይዛለን! ፈጣን
ሠዓት ያስመዘገበ ጣፋጭ ይሸለማል፡፡

ይምሩ:- አንድ ፈቃደኛ ልክ መሠናክሎቹን ለማለፍ ሲጀምር በጭብጨባ ሞራል መስጠት ይኖርባችኋል።

ይምሩ:- የመጀመሪያው ፈቃደኛ መነሻ ቦታው ላይ እንዲቆም ያድርጉ።

ይምሩ:- ተዘጋጅ፤ጀምር!

ይምሩ:- የመጀመሪያው/ዋን ፈቃደኛ በመ ሠናክሎች ላይ እንዲ/ድት/ሄድ ሲልኩ፤ ማጠናቀቂያው ላይ


በጭብጨባ የሞራል ድጋፍ ማድረግን አይርሱ።

ይምሩ:- ዋው፡ ግሩም ነው! የወሰደብህ/ሽ ጊዜ ___________ ነው።

ይምሩ:- ቀጣይ ፈቃደኛ ይላኩ። አሁንም ማጠናቀቂያው ላይ በጭብጨባ የሞራል ድጋፍ መኖሩን ያረጋግጡ።

ይምሩ:- ዋው፡ ግሩም ነው! የወሰደብህ/ሽ ጊዜ ___________ ነው።

ይምሩ:- አሁን የሦስተኛው ፈቃደኛ ተራ ነው ፣ ግን ሌላ ተጨማሪ መሠናክል ሊኖር ነው! የዐይን መሸፈኛ
ስካርፉን ያውጡና ለሁሉም ያሳዩ።

ይምሩ:- ሦስተኛው ፈቃደኛ ከመጀመሩ በፊት ዐይኖቹ/ቿን ይሸፍኑ። ይህንንም ፊቱ/ቷን በማዞር ወይም ወደ
ሌላ ቦታ ፈቀቅ በማድረግ መሸፈን ይችላሉ፡፡ በዚህ ጊዜ፤ሌሎች አመቻቾች በቀስታና እና በድብቅ ሁሉንም
መሰናክሎች እንዲያነሱ ያድርጉ፡፡ የመሠናክሎቹን መነሳት በጎ ፈቃደኛው በምንም ዓይነት መንገድ ማወቅ
የለበትም፡፡ አንዳች ጥርጣሬ እንዳያድርበት፤ ዐይኑን ሲሸፍኑ ትኩረቱን ለመስረቅ ይሞክሩ። መሰናክሉ ሙሉ
በሙሉ እንደተነሳ ፊቱን ያዙሩ/ሯት ወይም ከወሰዱበት ይመልሱ/ሷትና መነሻው ቦታ ላይ አቁመው
“ቀጥል/ይ”/ ይበሉ! እና ሠዓት መቁጠር ይጀምሩ። ዐይኖቹን የተሸፈነው ይህ ፈቃደኛ መሠናክሉ አሁንም
እንዳለ ስለሚያምን እግሮቹን ቀስ እያለ ለማለፍ በቀስ ይሞክራል ፡፡ ሲጨርስ በደማቅ ጭብጨባ ሞራል
ከሰጡ/ጧት በኋላ ዐይኑ/ኗን ይግለጡ። ለሁሉም ተሳታፊዎች ጣፋጭ ይሸልሟቸው፡፡

ይምሩ:- ሁላችሁም ጥሩ ስራ ሰርታችኋል፤ስለዚህም ስለተሳትፏችሁ ጣፋጭ ሽልማት ይገባችኋል! እስቲ


አሁን ደግሞ ወደ ክፍላችን እንመለስ እና ስላየነው ነገር እንነጋገር፡፡

ይምሩ:- ትምህርቱ ከመጀመሩ በፊት ሁሉም ወደየጠረጴዛቸው ይመለሱ።

28
ይምሩ:- እስካሁን ያየነው ጨዋታ ህይወታችንን የሚያሳይ ሲሆን፤ ተስፋ ያደረግነውን ነገር እንዳናገኝ በቀላሉ
የሚያግዱን መሠናክሎች መኖራቸውን ነው፡፡

ይምሩ:- መሠናክሎቹን ስለተሻገሩት የመጀመሪያ ሁለት ፈቃደኞችስ ምን አስተዋልን? (መሠናክሎችን


በግልጽ ማየት ይችሉ ነበር፣በፍጥነት ተራምደዋል፣አልፈሩም፣ወዘተ፡፡)

ይምሩ:- ስለ ሦስተኛው ፈቃደኛስ ምን አስተዋላችሁ? (ሦስተኛው/ዋ ፈቃደኛ ፈርቶ/ታ ነበር፣ ተጠንቅቆ/ቃ


በዝግታ ነበር የተራመደ/ችው፣ማየት አይ/ትችልም፣በገሀድ በስፍራው ላይ የሌለ ነገር እንዳለ አድርጎ በመቁጠር
ተጨንቆ ነበር።)

ይምሩ:- የተለያዩ የመሠናክል ዓይነቶች አሉ፡፡ አንደኛው፤ቅድም እንዳየናቸው _____


(ወንበሮች፣አግዳሚዎች፣ወዘተ.) ያሉ ገሀድ የሆኑ መሠናክሎች ሲሆኑ ለእንደ እነዚህ ዓይነት መሠናክሎች
መፍትሄ መፈለግ እንደምንችል እናውቃለን፡፡

ይምሩ:- ሌላኛው ዓይነት መሠናክል ደግሞ፤ቀደም ሲል በሶስተኛው በጎ ፈቃደኛ ላይ እንዳስተዋልነው፤እንዳሉ


ተደርጎ በምናብ የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ መሠናክሎች በገሃድ የሌሉ ቢሆንም፣ወደ ግቦቻችን
በፍጥነት እንዳንጓዝ የማገድ ኃይል አላቸው፡፡

ይምሩ:- ሁለቱም አይነት መሠናክሎች፤ማለትም በገሃድ ያለውም ሆነ በምናብ የሳልናቸው፤ልናሸነፍ


የምንችልበትን መንገድ ካላገኘን ወደኋላ ሊጎትቱን ይችላሉ፡፡

ይምሩ:- ለማሸነፍ በጣም አስቸጋሪ የሆነው የመሠናክል ዓይነት የትኛው ነው?

ይምሩ:- የቡድኑን ምላሽ ይጠብቁ (“በምናብ እንዳሉ አድርገን የምናስባቸው መሠናክሎች”)፡፡

ይምሩ:- በገሃድ ከሚገጥሙን መሠናክሎች ይልቅ ምናባዊ መሠናክሎችን ለማሸነፍ አስቸጋሪ የሚሆኑት
ለምን እንደሆነ እስቲ በየቡድናችን እንወያይበት፡፡

የተግባራዊ ርምጃ ቡድን አመቻቾች፡- ለ5 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ??

ይምሩ:- ለምሳሌ፣ተማሪዎች ታናናሽ ወንድም እህቶቻቸውን በመንከባከብ ሲጠመዱና ህልሞቻቸውን እውን


ማድረግ የሚያስችላቸውን ስራ ለመስራት ጊዜ አጥተው ሲቸገሩ፤ ያ ገሃዳዊ መሠናክል ይባላል፡፡

ይምሩ:- በአዕምሯችን የምንፈጥራቸው /የምናምናቸው/ ወይም በምናባችን የምንስላቸው መሠናክሎች


ምሳሌ ደግሞ፤ሕልሞቻችንን ለማሳካት በቂ ዕውቀት ወይም ችሎታ የለንም ብለን ስናስብ ነው፡፡

ይምሩ:- ይህ ዓይነቱ መሠናክል እኛው ራሳችን በውስጣችን የፈጠርነው እንደመሆኑ መጠን፤ሊወገድ


የሚችለውም ስለ እኛነታችን እና ማከናወን ስለምንችለው ነገር የነበረንን አስተሳሰብ በመለወጥ ብቻ ነው፡፡

ይምሩ:- ስለ አስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት(መታደስ) እና ይህም በምንሰራው ነገር ላይ ስለሚኖረው ተጽዕኖ


እግዚአብሔር ምን እንደሚል ከመጽሐፍ ቅዱስ እንሰማለን፡፡ ሮሜ 12÷2 እንዲህ ይለናል፡-

“የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደሆነ


ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ (በአእምሮአችሁ) መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም
አትመስሉ።”

29
ይምሩ:- እግዚአብሔር ሀሳቦቻችንን በእርሱ ሀሳቦች እንዲለውጥ ስንፈቅድ፤ያኔ እውነተኛውን ለውጥ
እንለወጣለን። እግዚአብሔር ለሕይወታችን ያለውን ዓላማም ማወቅ እንችላለን። እግዚአብሔር አዲስ
አዕምሮ(ልብን) ሲሰጠን ስለራሳችንም ሆነ ስለ ለሌሎች ሰዎች ያለውን ሃሳብ ይሰጠናል ፡፡

ይምሩ:- እስቲ ከእያንዳንዱ ቡድን አንድ አንድ ሰው፤ አሁን ባለው ህይወቱ እያጋጠመው ስላለው መሠናክል
ሊያካፍል የሚችል ይኖራል?

ይምሩ:- ከተሳታፊዎች አንድ አንድ በየተራ ይጥሩ፡፡ ለምሳሌ አንደኛው፤የገጠመው መሠናክል “የመስሪያ
ካፒታል(ገንዘብ)” እጥረት ሊሆን ይችላል፤የቀጣዩ ተረኛም ችግር ገሃዳዊ ይሁን ምናባዊ ፤ሃሳባቸውን ስላጋሩ
ያመስግኑ። በዚህ ርዕሰ-ጉዳይ አሁንም ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ ጊዜ ይኖረናል ፡፡ ሃሳባቸውን ላጋሩት
ተሳታፊዎች/ሰልጣኞች/ እነደ ከረሚላ ያሉ ጣፋጮችን መሸለምዎን አይርሱ፡፡

ይምሩ:- ይህ መሠናክል ምናባዊ ነው ወይስ ገሃዳዊ?

ይምሩ:- ወደ እያንዳንዱ ቡድን በመሄድ አባላቱ ስለተለያዩ መሠናክሎች እያነሱ እንዲወያዩ ይጠይቋቸው፡፡

ይምሩ:- አንዱ የተለመደው የመሠናክል ዓይነት ______________ (ካፒታል ወይም ገንዘብ) ማጣት ነው፡፡
ይህ መሠናክል በምናባችን የሳልነው ወይስ እውን ሆኖ ያለ በሚል በየቡድናችን ውስጥ እንወያይበት፡፡ 5 ደቂቃ
ያህል ጊዜ አላችሁ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ከ5-7 ደቂቃዎች፡፡ ይህ በደንብ ሊወያዩበት የሚገባ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው። ምንም
እንኳን መሠናክሉ ለስራ ፈጣሪዎች በገሀድ የሚታይ ቢሆንም እንዲያሸንፋቸው ከፈቀዱለት ግን መቼም
ቢሆን ወደፊት አያራምዳቸውም፡፡ ሥራ ፈጣሪዎች የካፒታል እጥረታቸው ላይ ሳይሆን ካፒታል እንዳያገኙ
ያደረጓቸው ምክንያቶች ላይ እንዲያተኩሩ ማገዝ አስፈላጊ ነው ፡፡ ይህን ጉዳይ ለይቶ ማወቅ እና እዚያ
መጀመር አለብን ፡፡ እያንዳንዱ ሰው አቅሙ የፈቀደውን ፣ ባለበት ሁኔታ ፣ በእጁ ላይ ባለው ነገር ስራ
ለመጀመር የሚያስችለው የተወሰነ ሀብት አለው፡፡ ከትንሽ የሚጀምሩና ቀስ በቀስ የሚያድጉ ሁሉ በጊዜ ሂደት
ስኬታማ መሆናቸው አይቀሬ ነው፡፡

ይምሩ:- የካፒታል እጥረት ተጨባጭ መሠናክል ነው፤ነገር ግን ህልማችንን እውን ከማድረግ እንዲያግደን
ከፈቀድንለት በጭራሽ መጀመር አንችልም፡፡ ከዚህ ስልጠና በኋላ ምናልባትም አንዳንዶቻችሁ የታሊ አነስተኛ
የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ስለምትሆኑ፤ ይህን መሠናክል የማሸነፊያ አንዱ መንገድ ነው፡፡ ሌሎቻችሁም
እንዲሁ ከሌላ ስፍራ ብድር ታገኙ ይሆናል፡፡ ብድር ምርጫቸው ያልሆኑም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ
የትኛውም ምርጫ መልካም ነው፡፡

ይምሩ:- ሰዎች አቅማቸው በሚፈቅደው፣ባሉበት ስፍራ፣እጃቸው ላይ ባለ ነገር፣ የራሳቸውን ስራ መጀመር


የሚያስችል መጠነኛ ሀብት አላቸው፡፡ በትንሽ ጀምረው ቀስ በቀስ የሚያድጉ ሁሉ በጊዜ ሂደት ስኬታማ
መሆኑ አየቀሬ ነው፡፡

ይምሩ:- ሕልማችንን እንዳናሳካ የሚያግዱን መሠናክሎች ሁላችንም አሉብን፡፡

ይምሩ:- አብረን መሥራት እና እርስ በእርሳችን መበረታታት ከፊት ለፊታችን የተደቀኑ መሠናክሎችን
ለማሸነፍ እንድንነሳሳ ያነሳሳናል፡፡

ይምሩ:- ከየትኛውም ዓይነት መሠናክል የሚበልጥ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ? (እግዚአብሔር ነው!)

ይምሩ:- ትንንሽ እርምጃዎችን ደረጃ በደረጃ መውሰድ፤ ግቦቻችን ላይ እንዳንደርስ ያገዱንን ነገሮች ለመሻገር
ሊረዳን ይችላል፡፡

30
ይምሩ:- ለምሳሌ፤ ልንሻገረው ከምንችለው መሠናክል አንዱ አለመማር ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ያለመማር
ችግር ለመቅረፍ በትንሹ ምን ዓይነት እርምጃ መውሰድ መጀመር ይኖርብናል? (ይህን ስልጠና በሚገባ
መከታተል፣የጎልማሶች ትምህርት መጀመር፣ልጆቻችን ወይም ጓደኞቻችን እንዲያስተምሩን
መጠየቅ፣ዩኒቨርሲቲ ገብቶ መማር፣መካሪና አርዓያ የሆነ ሰው ከጎናችን እንዲኖር ማድረግ፣ወዘተ…

ይምሩ:- ስለራሳችን ያለን አሉታዊ አስተሳሰብ፤ሌላው ልናሸንፈው ወይም ልንሻገርው የሚገባን የመሠናክል
ዓይነት ነው፡፡

ይምሩ:- አንድን ነገር ማድረግ እንደማንችል ካመንን፤ልናደርገው አንችልም፡፡

ይምሩ:- ሰዎች ስለ እኛ የሚሉንን፤ወይም እኛ ስለራሳችን ያሉንን አሉታዊ አስተሳሰቦች አምኖ ከመቀበል


ይልቅ፣ እግዚአብሔር እንደሚያየን እራሳችንን ማየት መቻል የእኛ ምርጫ ነው፡፡

ይምሩ:- መዝሙር 139÷14 እንዲህ ይላል:- “ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ስራህ ድንቅ
ነው፡ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።”

ይምሩ:- እግዚአብሔር እንዴት እንደፈጠረን ይህ መዝሙር ምን ይነግረናል? ከተሳታፊዎች ምላሾችን


ይቀበሉ፡፡

ይምሩ:- ስለራሳችን ያሉንን አሉታዊ አስተሳሰቦችን ሆነ በምናብ የሳልናቸው መሠናክሎችን ለማሸነፍ ይህን
እውነት እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል እስቲ በየቡድናችን እንወያይበት፡፡

ቡድን ማመቻቸት፡- 2 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ውይይቱን ይምሩ፡፡ በእግዚአብሔር የተፈጠርን እና የተወደድን ስለ


መሆናችን እንዲሁም ልጅ እያለን ስለነበረን ባህሪና አስተዳደግ ለመነጋገር ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡

ይምሩ:- ሌሎች ለእኛ ወይም ስለ እኛ ከሚሉት ይልቅ እግዚአብሔር የሚናገረውን ለማመን መምረጥ
እንችላለን፡፡

ይምሩ:- ስለራሳችን አሉታዊ ነገሮችን የምናምን ከሆነ፤የእኛ አደገኛ ጠላት ራሳችን እንሆናለን፡፡ ህልማችንን
እውን ለማድረግ እርምጃዎችን ከመውሰድም እንታቀባለን።

የስኬት ታሪክ

ይምሩ:- ሉሲ ስለምትባል አንዲት ኬንያዊት የታሊ ደንበኛ ሴት ታሪክ ልንገራችሁ፡፡ ፎቶና ታሪኳን
በሠልጣኞች መጽሐፍ በገጽ------ ላይ ማየት ትችላላችሁ፡፡ ሉሲ ስኬት ላይ ለመድረስ ብዙ መሠናክሎችን
አልፋለች፡፡ ዕድሜውን ሙሉ በሉካንዳ ስራ ይተዳደር የነበረው ባለቤቷ ከረዥም ዓመታት በፊት በካንሰር
በሽታ ይሞትባታል፡፡ ከእርሱ ሞት በኋላም ቢዝነሱን ማስቀጠል ፈለገች፡፡ ይሁን እንጅ በአካባቢዋ ባህል፤ ሴት
ልጅ በእንዲህ መሠል ሞያ መሰማራት ያልተለመደ በመሆኑ ተቀባይነት አላገኝም የሚል ስጋት አደረባት፡፡.

ይምሩ:- ሉሲ የታሊን መሠረታዊ የቢዝነስ ስልጠና ለመውሰድ ወሰነች፡፡ ከዚያም ከታሊ አነስተኛ የብድር
አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆንና የባለቤቷን ስራ በማስቀጠል የአካባቢው የመጀመሪያ የሉካንዳ ሞያተኛ ሴት
ለመሆን በቃች፡፡

ይምሩ:- ከእነዚህ መሠናክሎች ውስጥ የትኞቹ እውን/ገሃድ፤የትኞቹስ ምናባዊ ናቸው? ለሚሰጡ መልሶች
ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

31
ይምሩ:- ከሉሲ ምን ተማራችሁ? አንድ ሁለት መልሶችን ይቀበሉና ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- እስኪ አሁን ደግሞ በህይወታችሁ የሚገጥሟችሁን መሠናክሎች እንዴት እንደምታልፏቸው


እናስብ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በየቡድና ችሁ ተወያዩበት፤በመጽሐፍቶቻችሁ በገጽ______ላይ ባለው ባዶ ቦታም
መሠናክሎችን ስታልፉ የሚያሳይ ሥዕል በ5 ደቂቃ ውስጥ ሳሉ፡፡

ይምሩ:- ቡድን አመቻች፡- ለ5 ደቂቃ ያህል፡፡ ሰዎች መሠናክሎችን እንዲያልፉ እና አልፈውም ህልማቸው
እውን ሆኖ ማየት እንዲችሉ ማገዝ በጣም ወሳኝ ነገር ነው፡፡ እነዚህ ስራ ፈጣሪ ሠልጣኞች
መሠናክሎቻቸውን የሚሻገሩበትን አንድ የድርጊት መርሃ-ግብር በማመላከት ይምሯቸው፡፡ ይህን መሠናክል
ራሳቸው ሲሻገሩ የሚያሳይ ሥዕል እንዲሥሉም ይጠየቋቸው፡፡

ይምሩ:- ሁለት ተሳታፊዎች በፈቃደኝነት ወደዚህ በመምጣት መሠናክሎቻችሁን ለማለፍ ምን ማድረግ


እንደምትችሉ ልታጋሩን ትችላላችሁ፡፡

ይምሩ:- ለተሰጡ ምላሾች ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- የሚገጥሟችሁን መሠናክሎች የምታልፉበትን ዘዴ ስላጋራችሁን እናመሰግናለን፡፡

ይምሩ:- በእውነት ከፊት ለፊታችን የሚጋረጡ መሠናክሎችን ተሻግረን የምናልመው ህይወት ላይ ለመድረስ
ከፈለግን፤ የመጀመሪያው ርምጃ ህልሞቻችንን በጽሑፍ ማስፈር ወይም በሥዕል መግለጽ ነው፡፡ የተጻፉ
ወይም የተሳሉ ህልሞች እውን የመሆን ዕድላቸው ሠፊ ነው፡፡

ይምሩ:- ሕልምን በወረቀት ማስፈር ግብን ለይቶ ለማወቅ ይረዳል፡፡ ግብ ማለት፤ በህይወታችን
እንደርስበታለን ብለን ዒላማ/ታርጌት ያደረግነው ወይም እንደማናጣው ተስፋ የጣልንበት ማለት ነው፡፡ ልክ
አንድ እግር ኳስ ተጫዋች አነጣጥሮ ኳሷን የሚመታበት ግብ/ጎል ዓይነት ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- ግብን ማስቀመጥ ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው? ከየአቅጣጫው ምላሽ
ይቀበሉ፤ጣፋጭም ይሸልሟቸው፡፡

ይምሩ:- ግብን ማስቀመጥ በእውነት ተስፋ የጣልንበትን ነገር ጠንቅቀን እንድናውቅ፣ተግባራዊ ርምጃ
እንድንወስድ፣መሠናክሎችን እንድናልፍ፣ለውጣችንን መለስ ብለን ለመፈተሽ ያግዘናል፡፡

ይምሩ:- በመጽሐፍቶቻችሁ ገጽ------ ላይ፤በቢዝነሶቻችሁ ወይም በግል ህይወታችሁ ዙሪያ በሚቀጥሉት


ሁለት ዓመታት ልታሳኩ ምትፈልጓቸውን ሶስት ግቦች አስቀምጡ፡፡

ይምሩ:- ቡድን አመቻቾች፡- ለ5 ደቂቃ ያህል፡፡ መጻፍ የማይችሉ ካሉ፤በሥዕል መልክ ግባቸውን
እንዲያስቀምጡ ያድርጉ፡፡

ይምሩ:- እስቲ አሁን ደግሞ፤ወደዚህ መጥቶ ከግቦቹ አንዱን ሊያጋራን የሚችል ሰው አለ?

ይምሩ:- አድናቆትና ጣፋጭ ሽልማቶችን ያበርክቱላቸው፡፡ ሠዓቱ እስከፈቀደ ድረስ ብዙዎች ግባቸውን
እንዲያጋሩ ይፍቀዱላቸው፡፡ ይህ በእጅጉ ሊበረታታ የሚገባው ተግባር ነውና!

32
ይምሩ:- እነዚህ ግቦች ለስኬት እንዲበቁ ከፈለግን፤ ዘወትር በዕይታችን ውስጥ ሊሆኑ ይገባል፡፡ በዓለማችን ላይ
ብዙ ምርጥ ምርጥ ሃሳቦች አሉ፤ተግባራዊ የሚያደርጓቸው ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡ ህልሞቻችንን ወደ ተግባር
ለመለወጥ ርምጃዎችን እንድንወስድ እፈልጋለሁ!

ይምሩ:- በዚህ ስልጠና አብረን በምንቆይባቸው ጊዜያት ሁሉ፤ስለ ቢዝነስ ይሁን ስለ ቤተሰቦቻችን ውስጣችን
ያሉትን ህልሞች እውን ለማድረግ ግቦችን እንዴት እንደምናስቀምጥና መ ሠናክሎችን እንደምናልፍ
እንማራለን፡፡

ይምሩ:- ከዚህ የስልጠና ክፍል የቀሰማችሁትን ዕውቀት ጠቅለል አድርጎ ሊነግረን የሚችል ሁለት ሰው
ይኖራል?

ይምሩ:- ሁለት ተሳታፊዎችን ይጋብዙና የሆነ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ የእነሱን መረዳት በመደገፍ ያሉትን
እንደገና ያብራሩ፡፡

ይምሩ:- በቀጣይ ሥልጠና ስንገናኝ፤ስለ ቢዝነስ መሠረታዊ ዕውቀቶች እንወያያለን!

33
// ክፍል 4 //

መሠረታዊ የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና 1

የሚወስደው ጊዜ፡- 1 ሠዓት

ግቦች:-
> ተሳታፊዎች፤ የተልዕኮ መግለጫ ዝርዝርን አስፈላጊነት ይገነዘባሉ፤የራሳቸውን ተልዕኮም እንዴት
መፍጠር እንደሚችሉ ያውቃሉ፤
> ተሳታፊዎች፤(S) በግልጽ ተለይቶ የሚታወቅ፣(M) የሚለካ፣(A) ሊተገበር የሚችል፣(R) ተጨባጭ
እና(T) በጊዜ ሠሌዳ የተገደበ የድርጊት መርሃ-ግብር (SMART) ማዘጋጀት ይችላሉ፤
> ተሳታፊዎች ፤የመጀመሪያውን መሠረታዊ የቢዝነስ ዕቅድ ማብራራትና ማዘጋጀት ይችላሉ፤ይህንንም
በመጽሐፍቶቻቸው ገጽ ላይ በጽሑፍ ወይም በሥዕል ያሰፍራሉ፡፡

አቅርቦቶች፡-
> እስክርቢቶዎች > የነጭ ሰሌዳ ማርከሮች
> የሠልጣኞች መጽሐፍ > ጣፋጮች
> ነጭ ሰሌዳ

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


> ሥራ ፈጣሪ
> የቢዝነስ ዕቅድ > በግልጽ ተለይቶ የሚታወቅ
> ዕቃዎች/ሸቀጣሸቀጥ/ > የሚለካ
> አገልግሎቶች > ሊተገበር የሚችል
> ተልዕኮ > ተጨባጭ
> የድርጊትመርሃ-ግብሮች……….(SMAR > በጊዜ ሠሌዳ የተገደበ
T)
?? ትዕይንቶች(በግድግዳ ወይም በቦርድ ላይ የተለጠፉ ወይም በሠልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱ)፡-
ዝግጅት፡-
> ቡድኑ የተልዕኮ መግለጫ ዝርዝሮችን የሚያሰፍርበትን ስፍራ በነጭ ሰሌዳው ላይ ይከፋፍሉላቸው፡፡
> የሰዎች በተለያዩ ባህሎች ውስጥ ማደግ፤በህይዎታቸው እውን ሆኖ ማየት የሚፈልጓቸው ነገሮች እና
የሚያሰፍሯቸው የተልዕኮ መግለጫ ዝርዝሮች መብዛትና ማነስ፤መርዘምና ማጠር እንዲለያይ
ሊያደርገው ይችላል፡፡ የዚህ የተልዕኮ መግለጫ ዝርዝር ልምምድ ዋና ትኩረት ቢዝነሶቻቸው ምን
መሆን እንዳለበት መጻፍ ነው፡፡

34
> የተልዕኮ መግለጫ ዝርዝሮቻቸውን የሚደግፉ የድርጊት መርሃ-ግብሮችን /እርምጃዎችን/ ለመገንባት
ጊዜ ይወስዳል፡፡ የድርጊት መርሃግብር የተልዕኮ መግለጫን በዝርዝር የሚያብራራና ተልዕኮ እንዴት
ፍጻሜ እንደሚያገኝ የሚገልጽ፤የቢዝነስ ዕቅድ አንድ አካል ነው።

> ስለሆነም ስራ ፈጣሪዎች ግባቸውን ለማሳካት፤ በቢዝነስ ዕቅዶቻቸው ላይ ማለትም ቢዝነስ ከጀመሩ
በኋላ በሚያከናውኗቸው መሠረታዊ መርሃ-ግብሮች ላይ ይበልጥ ትኩረት ማድረግ ይችላሉ፡፡
> የቡድን አመቻቾች፡- ከዚህ ሥልጠና፤ጥሩ የተልዕኮ መግለጫ ዝርዝር ያዘጋጁ ተሳታፊዎችን
ከየቡድኖቻችሁ ለይታችሁ በማወቅ በቀጣዩ መሠረታዊ የቢዝነስ ክህሎት ሥልጠና 2 ወቅት የቢዝነስ
ሐሳብ የሚያጋሩ ፈቃደኞች ሲጠየቁ ይጠቁሟቸው፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ:-


> ምሳሌ 21÷5

ይምሩ:- ሁላችሁም በድጋሚ እንኳን ደህና መጣችሁ!

ይምሩ:- አንድ ቀን እንዲኖረኝ አፈልጋለሁ የምትሉትን የቢዝነስ ዓይነት እንድታልሙ ቀደም ሲል መጠየቃችን
ይታወሳል፡፡

ይምሩ:- ኃላፊነት ወስደው አዲስ የቢዝነስ ሥራን የሚጀምሩ ሰዎች ስራ ፈጣሪዎች (አንተርፕርነርስ)
ይባላሉ፡፡ ስራ ፈጣሪ ሰዎች ህልማቸውን ተከትለው የቢዝነስ ግባቸው ላይ ለመድረስ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ
የሚገጥሟቸው መሠናክሎች አያስፈሯቸውም፡፡

ይምሩ:- በዚህ ክፍል ውስጥ ያለን እያንዳንዳችን - ቢዝነስ የጀመርን ይሁን ወይም ለመጀመር በዕቅድ ላይ
ያለን - የአሁን ወይም የወደፊት ሥራ ፈጣሪዎች ነን፡፡

ይምሩ:- በቡድን ውይይቶቻችን ወቅት፤ አሁን ላላችሁ ይሁን ወደ ፊት ልትጀምሩት ላሰባችሁት ቢዝነስ
ዕቅድ ስታወጡ የተማራችኋቸውን አዳዲስ ጽንሰ-ሃሳቦች እባካችሁ ስራ ላይ አውሉ፡፡

ይምሩ:- የቢዝነስ ዕቅድ ማለት፤ያሰብንበት አንድ ቦታ ለመድረስ በየት በየት በኩል አድርገን መሄድ እንዳለብን
በትክክል እንደሚያሳይ የመንገድ ካርታ ነው፡፡

ይምሩ:- በካርታው በትክክል የምንመራ ከሆነ፤በተሳሳተ አቅጣጫ አንሄድም ወይም አደገኛ በሆነ ጎዳና ውስጥ
አንገባም፡፡

ይምሩ:- የቢዝነስ ዕቅድ፤የቢዝነሱ ስም፣የቢዝነሱ ዓይነት፣የተልዕኮ መግለጫ ዝርዝር፣ እና ቢዝነሱን


በትክክለኛው የጊዜ ሠሌዳ መጀመር የሚያስችሉ ጥሩ የድርጊት መርሃ-ግብሮችን ያጠቃልላል፡፡

ይምሩ:- የቢዝነስ ዕቅድ ሌላው የሚያካትታቸው ነገሮች፤ለመጀመር የሚያስችል የገንዘብ መጠን፣የስራ


ማስኬጃ በጀት እንዲሁም የማሳደጊያና የማስፋፊያ መንገዶችን ነው፡፡ በቀጣይ ክፍለ ጊዜያት የምንወያየው
በእነዚህ ዙሪያ ይሆናል፡፡

35
ይምሩ:- ቢዝነሶቻችንን በሚገባ ካደራጀን፤ ደንበኞቻችን የሚፈልጉትን ሆነ የሚያስፈልጋቸውን
ምርት/ቁሳቁስ/ ወይም አገልግሎት በመሸጥ ገቢ ማግኘት እንችላለን፡፡

ይምሩ:- ምርቶች/ቁሳቁሶች/ ማለት፤የሚታዩ፣የሚነኩ ወይም የሚዳሰሱ ዓይነት ዕቃዎች ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- የምርት/ቁሳቁስ/ ምሳሌ ማን ሊሰጠኝ ይችላል? (ምግብ፣ልብስ፣ሞባይል ስልክ፣ወዘተ.)

ይምሩ:- ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆት ጋር ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- አገልግሎቶች ማለት፤የማይነኩ ወይም የማይዳሰሱ ነገር ግን ለደንበኛ የሚሰጥ ሞያዊ ተግባራት
ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- የአገልግሎት ምሳሌስ የሚጠቅስልኝ ማን ነው? (ትምህርት፣ጤና፣ቱሪዝም፣ወዘተ.)

ይምሩ:- ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆት ጋር ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- የውበት ሳሎን፤የምርት/ቁሳቁስ/ ወይስ የአገልግሎት አቅርቦት? (ምርት ወይም አገልግሎት ሊሆን
ይችላል፡፡ ሥራ ፈጣሪዎች ለሰጡት መልስ ማብራሪያ እንዲጨምሩ ያድርጉ፡፡ ፀጉር መስራት፡- አገልግሎት፤
የፀጉር ዊግ፣ጌጣጌጥ፣እና የመሳሰሉት፡- ምርት/ቁሳቁስ/፡፡)

ይምሩ:- ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆት ጋር ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ከዚህ ጊዜ ጀምሮ፤ እያንዳንዳችን እነዚህን አዳዲስ ፅንሰ-ሀሳቦች በቢዝነሶቻችን እና በቢዝነስ


ሀሳቦቻችን ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ምናባዊ ፈጠራዎቻችንን እንጠቀማለን!

ይምሩ:- ቢዝነስ ለመጀመር ወይም ያለንን ለማስፋፋት ስናስብ ጠቃሚው መሣሪያ የተልዕኮ መግለጫ ዝርዝር
መጻፍ ነው፡፡

ይምሩ:- እንዲኖረን ስለምንፈልገው የቢዝነስ ዓይነት ስናስብ፤የተልዕኮ መግለጫ ዝርዝራችን ልናደርገው


የሚገባንን በጣም ጠቃሚ ነገር ያቀርብልናል፡፡ የተልዕኮ መግለጫ ዝርዝር ምን ማለት እንደሆነ ሊነግረኝ
የሚችል ማን ነው?

ይምሩ:- አንድ ሥራ ፈጣሪ፤ የተልዕኮ መግለጫ ዝርዝር ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲያስረዳ ያድርጉ፡-
የቢዝነሶቻችንን ዋንኛ ዓላማ ዘርዝሮ የሚያሳይ ጠቃሚ ዝርዝር መመሪያ ነው፡፡

ይምሩ:- የተልዕኮ መግለጫ ዝርዝር፤የመጀመሪያ ዕቅዳችንን ፈር ወይም የቢዝነሳችንን ዓላማ ሳንስት እንዴት
መሄድ ወደ ፊት መጓዝ እንደምንችል ሊያግዘን ይችላል፡፡

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ለዳቦ መጋገሪያና መሸጫ የተልእኮ መግለጫ ቢያስፈልግ፤ “ከፍተኛ የጥራት ደረጃውን
የጠበቀ፣ትኩስ ዳቦ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ” የሚል ሊሆን ይችላል፡፡

ይምሩ:- በቡድናችሁ ውስጥ እሰቲ ስለ ዚህዳቦ ቤት የተልእኮ መግለጫ ተወያዩ፡፡ ይህንን የተልእኮ መግለጫ
ጥሩ የሚያስብለው ምንድን ነው? 2 ደቂቃ ተጠቀሙ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ2 ደቂቃ ያህል፡፡ ቀለል ያድርጉት፡፡

36
ይምሩ:- ይህንን የተልእኮ መግለጫ ጥሩ የሚያስብለው ምን እንደሆነ ሊያስረዳን የሚችል እስቲ አንድ ሰው
ይኖራል?

ይምሩ:- ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆት ጋር ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- እስቲ እያንዳንዳችሁ የምትወዱትንና አዘውትራችሁ የምትገዙበትን ዳቦ ቤት በምናብ አስቡ (ወይም


ሌላ ተጨባጭ ምሳሌ ይስጡ)፡፡ ይህን የዳቦ መሸጫ እንድትወዱት ያደረጋችሁ ምንድነው?

ይምሩ:- አሁን ደግሞ ያው ዳቦ ቤት ከሶስት ዓመት በኋላ ሻምፖ፣ሳሙና፣ጋዝ እና የእንስሳት ተዋጽኦ መሸጥ
እንደጀመረ አድርጋችሁ በዓይነ-ህሊናችሁ ሳሉት፡፡

ይምሩ:- ያንን ትኩስና ጣፋጭ ዳቦ ለመግዛት ይመጡ የነበሩ ደንበኞች እየተሸጠ ባለው ነገር ግራ ስለተጋቡ
አሁን አይመጡም፡፡ ያ ይፈልጉት የነበረው ዳቦ በሌሎቹ ዕቃዎች ስለተዋጠ ከእንግዲህ ከዚህ ዳቦ ጋጋሪ ምን
እንደሚጠበቅ ማንም አያውቅም።

ይምሩ:- ጥቂት ደቂቃዎችን ይውሰዱና በየቡድኖቻችሁ፤የተልዕኮ መግለጫን መከተል ለዚህ ዳቦ ቤት ባለቤት


የተሻለ ቢዝነስ እንዲኖረው እንዴት ሊጠቅመው ይችል እንደነበር ተውያዩበት፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ3 ደቂቃ ያህል፡፡ ከዚህ ጥያቄ ተነስተው መልሱን ራሳቸው እንዲመልሱ ያድርጉ፡፡ ግልፅ
የተልእኮ መግለጫ መኖር እና ያንን መከተል በማህበረሰቡ ውስጥ ተፈላጊነትን እና አስተማማኝነትን
በመገንባት የደንበኞችን አመኔታ ይጨምራል፡፡

ይምሩ:- እስካሁን ያልተሳተፉ ሁለት ሰዎች፤ ቡድኖቻቸው ስለተወያዩት ነገር እንዲያጋሩን እፈልጋለሁ?
ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆት ጋር ይሸልሙ፡፡

ልምምድ

ይምሩ:- በቡድናችን ውስጥ ለ10 ደቂቃ ያህል፤የየግል ቢዝነስ ተልዕኮ መግለጫዎቻችንን እንዴት
እንደምናወጣ እንለማመዳለን፡፡ የተልዕኮ መግለጫ ማለት፤ በቢዝነሶቻችሁ ውስጥ ምን ማከናወን
እንዳለባችሁ የሚነግራችሁ ማለት መሆኑን አስታውሱ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ10 ደቂቃ ያህል፡፡ ሥራ ፈጣሪ ሰልጣኞቹ የተለያዩ ጽንሰ-ሀሳቦችን እንዲያመነጩ
ያድርጉ፡፡ በሂደቱ ግን ምሪት ይስጧቸው፡፡ ገና ቢዝነስ ካልጀመሩም፤ አዳዲስ ሀሳቦችን እንዲያፈልቁ ወይም
ከአልባሳት መሸጫ ሱቁን ምሳሌ እንዲጠቀሙ ያድርጉ፡፡

ይምሩ:- አስቲ ስለ ቢዝነሶቻቸው እና ስለ ተልዕኮ መግለጫዎቻቸው ሊነግሩን የሚችሉ ፈቃደኞች ካሉ?


ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆት ጋር ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ልናደርጋቸው ስለምናስባቸው ነገሮች መናገር የስራው አንድ አካል ብቻ ነው፡፡ እነዚያን ነገሮች
እንዴት ማከናወን እንደምንችል አሁን እንገልጻለን፡፡

37
ይምሩ:- ተልእኳችንን ለማሳካት የምናደርጋቸው ነገሮች የድርጊት መርሃ-ግብሮች ይባላሉ፡፡

ይምሩ:- ቢዝነሶቻችንን ጀምረን ስናሳድግ፤ ብዙ የድርጊት መርሃ-ግብሮች ይኖሩናል፡፡

ይምሩ:- አንድ የድርጊት መርሃ-ግብር ማለት፤ትልልቅ ግቦቻችን ላይ ለመድረስ የሚረዳን አነስተኛ ግብ ነው፡፡
መርሃ-ግብሮቹም፡-

> በግልጽ ተለይቶ የሚታወቅ(S)፣የሚለካ(M)፣ሊተገበር የሚችል(A)፣ ተጨባጭ(R) እና በጊዜ ሠሌዳ


የተገደበ(T) ወይም (SMART) ሊሆን ይገባል።

ይምሩ:- ስለወደፊት ቢዝነሱ እና እሱን እውን ለማድረግ መውሰድ ስለሚኖርበት አንድ የድርጊት መርሃ-ግብር
ሊያካፍለን የሚችል አንድ በጎ ፈቃደኛ ይኖራል? አንድ ፈቃደኛ ተሳታፊ ወደ መድረክ ይጋብዙ፡፡

ይምሩ:- እባክህ/ሽ፤የቢዝነስ ሃሳብህ/ሽን እና የተልዕኮ መግለጫህ/ሽን ብታካፍለ/ይን? ተሳታፊው ያጋራል፡፡

ይምሩ:- ስላጋራኸ/ሽን እናመሰግናለን!

ይምሩ:- ተልዕኳችሁን ለማሳካት የሚረዱ ጥሩ የድርጊት መርሃ-ግብሮችን ለመቅረጽ አሁን ይህንን የቢዝነስ
ጽንሰ-ሃሳብ እና የተልዕኮ መግለጫ እንጠቀማለን፡፡ ለቢዝነሳችሁ አንድ የድርጊት መርሃ-ግብር እስቲ
ልትገልጹልኝ ትችላላችሁ? በቦርዱ ላይ ይፃፉ።

ይምሩ:- በመጀመሪያ፤የድርጊት መርሃ-ግብሮቻችን (S) በግልጽ ተለይተው የሚታወቁ መሆን አለባቸው።


ይህም ማለት ለውጤት ሲበቁ በግልጽ የሚታዩ መሆን ይኖርባቸዋል ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- እስቲ አንድ የድርጊት መርሃ-ግብር ልጥቀስና ተለይቶ የሚታወቅ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን
እንመልከት? አንድ በጎ ፈቃደኛ ተሳታፊ ምላሽ እንዲሰጥዎት ያድርጉ። እሱ/ሷ መመለስ ካልቻለ/ች፤ሌሎች
እንዲሳተፉ ያድርጉ።

ይምሩ:- “ ______________” ብታከናውን/ኚ ተለይቶ የታወቀ የድርጊት መርሃ-ግብርህ/ሽን አሳካህ/ሽ


ሊባል ይቻላል? በጎ ፈቃደኛውን ይጠይቁ (ከተጠቀሰው ዓላማ ጋር የሚቃረን ወይም የማይዛመድ ነገር
ጠቅሰው ይጠይቁ/ቋት፡፡) ምላሾችን ይቀበሉ

ይምሩ:- ቡድኑን ይጠይቁ፡- ይህ መርሃ-ግብር ተለይቶ የታወቀ ነው? ብዙ ምላሾች ይቀበሉ፤እርስዎም እንዲሁ
ማብራሪያ ወይም ማስተካከያዎች ይስጡ።.

ይምሩ:- በመቀጠልም፤የድርጊት መርሃ-ግብሮቻችን የሚለኩ መሆን አለባቸው።

ይምሩ:- ይህም ማለት፤የድርጊት መርሃ-ግብሮቻችንን ለመመዘን/ለመገምገም/ “ምን ያህል?” ወይም “ስንት?”


የሚሉ ጥያቄዎችን እንጠይቃለን ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- ተሳታፊን ይጠይቁ፡- ይህ መርሃ-ግብር ሊለካ የሚችል ነው? ካልሆነ፤እንዴት ሊቆጠር የሚችል
ልናደርገው እንችላለን? ምላሾችን ይቀበሉ፤ እንዲሁም ግብረ መልስ ይስጡ።

38
ይምሩ:- እነዚህ የድርጊት መርሃ-ግብሮች ተጨባጭ መሆንም ይኖርባቸዋል፡፡ ጠንክረን ሰርተን እውን
ለማድረግ ፈቃደኝነቱና ችሎታው ሊኖረን ይገባል፡፡ ተጨባጭ የድርጊት መርሃ-ግብሮች፤ አሁን ባለንበት ሁኔታ
እና ባሉን ሀብቶች ልንደርስባቸው የምንችላቸው ናቸው ፡፡

ይምሩ:-ተሳታፊን ይጠይቁ፡- የድርጊት መርሃ-ግብርህ/ሽ ተጨባጭ ነው? እንዴት? ይህ የድርጊት መርሃ-ግብር


ለእሱ/ሷ ተጨባጭ መሆን አለመሆኑን እንዲያ/ድታረጋግጥ መሪና ተከታታይ ጥያቄዎችን ይጠይቁ።

ይምሩ:- አንዳንድ የድርጊት መርሃ-ግብሮች ሊደረስባቸው የማይቻል ቢመስሉም፤አሁንም ዝርዝር ዕቅድ


ከወጣላቸው እውን የሚሆኑ ናቸው፡፡

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ ጃክሰን የሚኒባስ ታክሲ ቢዝነስ ለመጀመር ፈለገ፡፡ ነገር ግን ሚኒባስ የመግዛት አቅም
እንደሌለው ገና ከመነሻው ተገነዘበ፡፡ የዚህ ሰው የድርጊት መርሃ-ግብር ተጨባጭ አልነበረም።

ይምሩ:- ጃክሰን በሚኒባስ ፋንታ በሞተር ብስክሌ የትራንስፖርት አገልግሎቱን(ቦዳ (ቦዳ ፣ሞቶ፣ ወዘተ)
ቢጀምር የተሻለ ተጨባጭ ግብ እንደሚሆንለት ሃሳብ መጣለት፡፡

ይምሩ:- እኛም እንደ ጃክሰን፤ቢዝነሱን ለመጀመር አሁንኑ ተግባራዊ/ተጨባጭ ልናደርጋቸው ከምንችላቸው


ትንንሽ መርሃ-ግብሮች ለመነሳት መወሰን ያስፈልገናል፡፡

ይምሩ:- የድርጊት መርሃ-ግብሩ ተጨባጭ ካልሆነ፤ ይጠይቁ፡- ቢዝነስ ያልጀመራችሁና ደንበኛ የሌላችሁም ሆነ
ቢዝነሶቻችሁን ማስፋፋት የምትፈልጉ፤ ግቦቻችሁን ለማሳካት የሚረዷችሁ ትንንሽ እርምጃዎች ምን ምን
ናቸው? ምላሾችን ይቀበሉ፤ እንዲሁም ግብረ መልስ ይስጡ። (ለምሳሌ፡-የክህሎት ስልጠና፣ተግባራዊ
ልምምድ ማድረግ፣ገንዘብ መቆጠብ፣ሰፋ ያለ የሚከራይ ቦታ መፈለግ፣ ወዘተ)

ይምሩ:- በመጨረሻም፤ጥሩ የድርጊት መርሃ-ግብሮች በጊዜ ሠሌዳ የተገደበ ሊሆን ይገባዋል፡፡

ይምሩ:- በጊዜ ሠሌዳ የተገደበ ማለት፤የድርጊት መርሃ-ግብራችንን የምናጠናቅቅበትን ቀን መወሰን ማለት


ነው፡፡

ይምሩ:- በጊዜ ሠሌዳ የተገደበ መሆኑ ወደ ግባችን የምናደርገውን ጉዞ እንድንቀጥልበት ያግዘናል፡፡ በጊዜ ሠሌዳ
ያልተገደበ የድርጊት መርሃ-ግብር በጭራሽ እውን ሊሆን አይችልም፡፡

ይምሩ:-ተሳታፊው ይጠይቁ፡- የድርጊት መርሃ-ግብር በጭራሽህ/ሽ በጊዜ ሠሌዳ የተገደበ ነው? ምላሾችን
ይቀበሉ፤ እንዲሁም ግብረ መልስ ይስጡ። እንዲሁም መሪና ተከታታይ ጥያቄዎችን ይጠይቁ።

ይምሩ:- ስለዚህ፤ከዚህ በኋላ የተሻሻለው የድርጊት መርሃ-ግብራችን የሚሆነው፡- ___________

_________________________________________________________________ ነው፡፡

ይምሩ:- አሁን ጥሩ የድርጊት መርሃ-ግብር ማለትም፡- በግልጽ ተለይቶ የሚታወቅ (S)፣የሚለካ (M)፣
ሊተገበር የሚችል (A)፣ተጨባጭ (R) እና በጊዜ ሠሌዳ የተገደበ (T) ወይም (SMART) አለን ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- ስለ እገዛችሁ በጣም እናመሰግናለን!

39
ልምምድ

ይምሩ:- የተወሰነ ጊዜ ወስዳችሁ፤ ወደፊት የምትጀምሩት ወይም የምሻሽሉት ቢዝነስ ሊኖረው ስለሚገባው
የተልዕኮ መግለጫዎች እና የድርጊት መርሃ-ግብሮች በየቡድናችሁ ተወያዩ፡፡ ከዚያም በሠልጣኞች መጽሐፍ
ገጽ ____ ላይ ባለው ክፍት ቦታ የቢዝነስ ግባችሁን ለማሳካት የሚያስፈልጓችሁን የድርጊት መርሃ-ግብሮች
በጽሁፍ ወይም በሥዕል ግለጹ፡፡ እያንዳንዱ የድርጊት መርሃ-ግብር፤በግልጽ ተለይቶ የሚታወቅ (S)፣የሚለካ
(M)፣ሊተገበር የሚችል (A)፣ተጨባጭ (R) እና በጊዜ ሠሌዳ የተገደበ (T) ወይም (SMART) መሆኑን
ያረጋግጡ! ይህንንም ከጎናችሁ ላለ ጓደኛ ማካፈል ትችላላችሁ፡፡ ከ5-7 ደቂቃዎች ተጠቀሙ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ከ5-7 ደቂቃዎች፡፡ ይህ መረጃ በሠልጣኞች መጽሐፍ ላይ ባለው ክፍት ቦታ


መጻፍ፤ያለዚያም ለጓደኛ ወይም ለአመቻች መንገር ይቻላል፡፡ በዚህ ጉዳይ በቡድኑ ውስጥ ካሉት ከእያንዳንዱ
ሠልጣኝ ጋር ለመወያየት ይሞክሩ፡፡ ጥቂት ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡ የድርጊት መርሃ-ግብሮቻቸው በግልጽ
ተለይቶ የሚታወቅ፣የሚለካ፣ሊተገበር የሚችል፣ተጨባጭ እና በጊዜ ሠሌዳ የተገደበ የሚሉትን መርሆዎች
የተከተሉ መሆናቸውን በመተንተን ያረጋግጡ።

ይምሩ:- እስቲ የድርጊት መርሃ-ግብሮቻቸውን ሊያጋሩን የሚችሉ ሁለት ተሳታፊዎች ይኖራሉ?

ይምሩ:- ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆት ጋር ይሸልሙ፡፡ መስፈርቱን በሚያሟላ መልኩ፤ሠልጣኞቹ ለድርጊት


መርሃ-ግብሮቻቸው የሚየስፈልጓቸውን የተለያዩ ግብዓቶች ለይተው እንዲያውቁ ያግዟቸው፡፡

ይምሩ:- ዛሬ የተማርናቸውን እያንዳንዳቸውን ስንሰበስባቸው፤ለቢዝነስ ዕቅዶቻችን መሠረት የሚሆኑን


ናቸው፡፡ የምንፈልገውን የቢዝነስ ዓይነት መርጠናል፤የቢዝነሳችንን ስም መርጠናል፤የተልእኮ መግለጫ
አዘጋጅተናል እዲሁም ጥሩ የድርጊት መርሃግበሮችን ጽፈናል፡፡

ይምሩ:- ሁላችሁም ጥሩ ሥራ ነው የሰራችሁት! ጥሩ እቅዶችን በጋራ አውጥተናል ብዬ አስባለሁ፡፡

ይምሩ:- ጥሩ እቅዶችን ማዘጋጀት ብልህነት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “የትጉህ ሰው ዕቅድ ወደ
ጥጋብ ያደርሳል፤ችኩል ሰው ግን በፍጥነት ወደ ድህነት ይወርዳል።”

ይምሩ:- ጥቅሱ ከመጽሐፈ ምሳሌ 21÷5 የተወሰደ ነው፡፡ ዕቅድ ለህይወታችንም ሆነ ለቢዝነሳችን መልካም
መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ለምን እንደሆነ እስቲ በየቡድናችሁ ተወያዩበት፡፡

የቡድን አመቻቾች፡- ለ2 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ይህንን ውይይት ይምሩ፤በተሳታፊ ዝምታ ወይም ጥያቄውን
ደጋግመው በማስረዳትዎ አይደናገጡ፡፡

ይምሩ:- ጥንቃቄ የተሞላባቸው ዕቅዶችን እንድናወጣ እግዚአብሔር ለምን እንደሚፈልግ ሁለት ተሳታፊዎች
ልታጋሩን ትችላላችሁ? ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆት ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ከዚህ የትምህርት ክፍል የቀሰሙትን አንድ ዋና ነጥብ ሊነግሩኝ የሚችሉ ሁለት ተሳታፊዎችስ
ይኖራሉ?

ይምሩ:- ሁለት ተሳታፊዎችን ወደ መድረኩ ይጋብዙና አንድ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ ገለጻቸውን እርስዎ
ደግመው በማብራራት ለሃሳባቸው ማረጋገጫ ይስጡ፡፡

40
ይምሩ:- የተልዕኮ መግለጫዎችን እና የድርጊት መርሃ-ግብሮችን ማዘጋጀት፤አስደናቂ ተግባር ነው!
በሚቀጥለው ክፍል፤ ተልዕኳችን ላይ ለመድረስ እንዴት ዕቅድ እንደምናዘጋጅ እናያለን፡፡

41
// ክፍል 5 //

መሠረታዊ የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና 2

የሚወስደው ጊዜ፡- 1 ሠዓት

ግቦች:-
> ተሳታፊዎች ፤ስለ ገቢ እና ወጪ፤እንዲሁም ስለ ትርፍ እና ኪሳራ ስሌት መሠረታዊ ጽንሰ- ሀሳቦች
ግንዛቤ ያገኛሉ፤
> ተሳታፊዎች የአደጋን ጽንሰ-ሀሳብ ይረዳሉ።

አቅርቦቶች፡-
> እስክርቢቶዎች > ነጭ ሠሌዳ
> የሠልጣኞች መጽሐፍ > የነጭ ሰሌዳ ማርከሮች
> የሒሳብ መደመሪያ ካልኩሌተሮች > ጣፋጮች

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


> ትርፍ > ገቢ
> ኪሳራ > ወጪ
> አደጋ /ስጋት/

የሒሳብ ስሌቶች (በነጭ ሰሌዳ ላይ ይፃፉ)፡-


> የተሸጡ ዕቃዎች /አገልግሎቶች/ ብዛት x የመሸጫ ዋጋ = ገቢ
> ገቢ - ወጭ = ሚዛን /ቀሪ ሂሳብ/

ትዕይንቶች (በግድግዳ ወይም በቦርድ ላይ የተለጠፉ ወይም በሠልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ


የተጠቀሱ)
> የንግድ ሱቅ/መደብር/

ዝግጅት:-
> የሴት ሰልቫጅ ልብሶች መሸጫ ሱቅን (ቡቲክ) በምሳሌነት እንጠቀማለን፡፡ ይህ ምሳሌ ለአውዱ ወይም
በተጨባጭ የማይመጥን ከሆነ፤ሌላ የሚመች ምሳሌ ይምረጡ፡፡
> የልብስ መሸጫ ሱቁ የቢዝነሱን ዓይነት የሚገልጽ ስም መኖሩን ያረጋግጡ፡፡

42
> የቡድን አመቻቾች፡- በቡድን ውይይት ወቅት፤በመምሪያው ላይ ከተጠቀሰው የልብስ መሸጫ ሱቅ
/ቡቲክ/ ምሳሌ ውጪ፤ ሥራ ፈጣሪዎች የከፈቱትን ወይም ወደፊት ሊከፍቱ ያሰቧቸውን ቢዝነሶች
ምሳሌ መጠቀምዎን ርግጠኛ ይሁኑ፡፡

> ይህ ትምህርት፤ስለ ትርፍ፣ኪሳራ እና ገቢ በግልጽ ያስረዳል፡፡ በእነዚህ አርዕስተ-ጉዳዮች ዙሪያ


ስልጠናው ይበልጥ የሚያተኩረው ወደ በኋላ ላይ ስለሆነ አሁን በዝርዝር ለማብራራት ከመሞከር
ይቆጠቡ፡፡

> ይህ ስልጠና፤ ሁለት ሥራ ፈጣሪዎች ቀደም ሲል በስራ ሂደት ያጋጠሟቸውን አደጋዎች እና


ውጤቶቻቸውን የማጋራት እድል መስጠትን ያካትታል፡፡ በዚህ ክፍለ ጊዜ፤ ጠቃሚ ተመክሮ
ያላችውና ለማጋራትም ፈቃደኛ የሆኑ ሥራ ፈጣሪዎችን ለማግኘት በንቃት ይከታተሉ።.
> ይህ ክፍል፤ ከሥራ ፈጣሪው ጋር የፊት ለፊት የጥያቄ እና መልስን ያካትታል፡፡ ተከታታይና መሪ
ጥያቄዎችን ሲጠየቅ በነጻነት የሚመልስ እና ሁኔታወችን በፍጥነት ማስተካከል የሚችል አንድ
ተሳታፊ ካለ፤ለዚህ ክፍል ስልጠና መሪ አመቻች መሆኑን ያረጋግጡ፡፡.

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ:-


> መክብብ 11÷4-6

ይምሩ:- በድጋሚ እንኳን በደህና መጣችሁ! ቀደም ሲል ለቢዝነሶቻችሁ የተልዕኮ መግለጫዎችን እና የድርጊት
መርሃ-ግብሮችን በማዘጋጀት ታላቅ ሥራን ሰርታችኋል፡፡

ይምሩ:- አሁን ደግሞ፤የተሻለ ትርፋማ ለመሆን እና ማህበረሰባችንን በተሻለ ለማገልገል እንዴት


ቢዝነሶቻችንን ማሳደግ እንደሚኖርብን እንነጋገራለን፡፡

ይምሩ:- በምሳሌነት ለመጠቀም እንዲረዳን፤ በዚህ ሳምንት መጨረሻ እኛ የሴቶች ልብስ መሸጫ ሱቅ/ቡቲክ/
በመክፈት ሁላችንም በአንድነት ወደ ቢዝነስ እንደገባን አድርገን በምናብ እናስብ።

ይምሩ:- ይህ ምሳሌ ለዚህ ስልጠና ብቻ የሚያገለግል መሆኑን አስታውሱ፡፡ ነገ የምትከፍቱት የቢዝነስ ዓይነት
ከዚህ የተለየ ሊሆን ይችላል፤መሠረታዊ መርሆው ግን ከዚህ ከምንጠቀመው ምሳሌ ጋር አንድ ዓይነት ነው።

ይምሩ:- በትዕይንቱ ላይ ወዳለው የንግድ ሱቅ/መደብር/ ያመላክቷቸው።

ይምሩ:- የልብስ መሸጫ ሱቅ/ቡቲክ/ የምንከፍት ከሆነ፤ስም ያስፈልገዋል፡፡ ይህን ሱቅ ምን ብለን


እንሰይመው?

ይምሩ:- ጥቆማዎችን ይቀበሉ፡፡ የተጠቆመው ስም ምን እየሸጠ እንዳለ (የተቋቋመለትን ዓላማ)


የማያመላክት ከሆነ ተከታታይ ጥያቄዎችን ይጠይቁ፡፡ ስያሜው የአገልግሎቱ መገለጫ መሆን አለበት።
በመጨረሻም የጸደቀውን ስም በትዕይንቱ ላይ ይፃፉት፤ ወይም ተሳታፊዎች በመጽሐፍቶቻቸው ላይ ባለው
ክፍት ቦታ እንዲጽፉት ያድርጉ፡፡

43
ይምሩ:- ___________ የሚለውን የሱቅ ስያሜ፤በዚህ የትምህርት ክፍልም ሆነ በቀጣይ ክፍሎች
ለውይይቶቻችን ምሳሌ አድርገን እንጠቀምበታለን፡፡

ይምሩ:- በቢዝነስ ውስጥ፤ሁላችንም ትርፍ እና ኪሳራ ይገጥመናል፡፡ ከጠቅላላ የሽያጭ ገቢያችን ላይ ሁሉንም
ወጭዎች ከሸፈንን በኋላ የሚቀረን ገንዘብ ትርፍ ይባላል።

ይምሩ:- የወጪያችን መጠን ከገቢያችን ሲበልጥ፤ወይም ያስገባነውን ሁሉ ከፍለን አሁንም ዕዳ ውስጥ


ከሆንን፤ ኪሳራ ገጠመን ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- ለምሳሌ፤___________ የሚባለውን ሰልቫጅ የሴቶች ልብስ መሸጫ ሱቅ በቅርብ ጊዜ ከፍተናል፡፡


በጀመርን በወሩ መጨረሻ ላይ 30 ልብሶች እያንዳንዳቸውን በብር (ለአከባቢው የሚመጥን ዋጋ
ይጠቀሙ)_______ ሸጥን፡፡

ልምምድ

ይምሩ:- በጠረጴዛዎቻችን ላይ የተቀመጡትን የሒሳብ መደመሪያ ካልኩሌተሮች በመጠቀም ከሁሉ


አስቀድሞ ከሽያጭ ምን ያህል ገቢ እንዳገኘን እናስላ፡፡ ይህ የገንዘብ መጠን ገቢ ይባላል። ገቢ ማለት
ከቢዝነሶቻችን የምናገኘው ማንኛውም ገንዘብ ነው።

ቡድን አመቻቾች፡- ለ1 ደቂቃ ያህል፡፡ ተሳታፊዎች ገቢዎቻቸውን እንዲያሰሉ የሚያስችላቸውን የሂሳብ


ቀመር በመጠቀም በሠልጣኝ መጽሐፍቶቻቸው ውስጥ ባለው ቦታ ላይ እንደሰሩ ያድርጉ።

ይምሩ:- በዚህ ወር ምን ያህል ገንዘብ እንዳገኘን ሊነግረኝ የሚችል ሰው ማን ነው? ቁጥሮቹን በዝርዝር
እንዲነግሩዎ ያድርጉ እና “ገቢ” በሚለው አርዕስት ስር በሰሌዳው ላይ ይፃፉ፡፡

ይምሩ:- ትርፋችንን ለማወቅ፤ ወጫችንን ከዚህ ቁጥር ላይ እንቀንሳለን። ወጪ፤ ከቢዝነሳችን ላይ ቀንሰን
ለአንድ ነገር የምናውለው/የምናወጣው/ ማንኛውንም ገንዘብ ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- አሁን አብረን በጋራ የቢዝነሶቻችን ዓይነተኛ ወጪዎችን እናስብ፤ከዚያም በየወሩ ምን ያህል
ሊያስወጡን እንደሚችሉ እንመልከት፡፡

ይምሩ:- ከመካከላችሁ አንድ አንድ ሰው እየመረጥኩ በምሳሌነት ለምንጠቀምበት ቢዝነስ የእያንዳንዱን ዕቃ


ዋጋ እንዲነግረኝ አደርጋለሁ፡፡ እሱ በሚሰጠው ቁጥር ሙሉ በሙሉ ላትስማሙ ትችላላችሁ፤ይህ በምሳሌነት
ብቻ የምንጠቀምበት ስለሆነ አትጨነቁበት፡፡

ይምሩ:- የቢዝነሳችን የወጪ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው፤ ወርሃዊ ወጪያችንስ ምን ያህል ሊሆን ይችላል?

ይምሩ:- ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆት ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡ የወጪ ዓይነት ሲጠቁምዎት፤ያ ወጪ በወር
ምን ያህል እንደሚያስወጣ ይጠይቁት። ውይይቱን አጭር ያድርጉት፡፡ በቁጥሮቹም ሆነ በዋጋዎቹ ላይ
አለመስማማት ከተፈጠረ ምሳሌ ብቻ መሆኑን ያስታውሷቸው፡፡ ወጪዎቹ የቤት
ኪራይ፣የመብራት/ጀነሬተር/፣የጥሬ ዕቃ ግዥ፣የሠራተኛ ደሞዝ፣ እና የሱቅ ቁሳቁስ ግዥ ማካተትዎን
አይርሱ።

ይምሩ:- በዚህ ምሳሌ መሰረት፤የቤት ኪራይ ወጪ __________ ይኖረናል፡፡

44
ይምሩ:- የመብራት/ጀነሬተር/_____________ ይኖረናል፡፡

ይምሩ:- የጥሬ ዕቃ ግዥ ______________ ይኖረናል፡፡

ይምሩ:- የሠራተኛ ደሞዝ ______________ ይኖረናል፡፡

ይምሩ:- የልብስ መስቀያዎች፣ደረሰኝ ወረቀቶች፣እስክሪብቶዎች፣የዕቃ መጠቅለያ እና ፌስታሎች የመሳሰሉ


የሱቅ ቁሳቁስ ግዥዎች ____________ ፈጽመናል፡፡

ይምሩ:- ሌሎች ተጨማሪ ወጪዎች ከነ ዋጋ ዝርዝሮቻቸው ከተሳታፊዎች ከቀረቡልዎ፤ድምጽዎን ከፍ


አድርገው ለሌሎችም በማጋራት በቦርዱ ላይ እየሰሩት ባለው የሂሳብ ስሌትዎ ውስጥ ያካትታሉ፡፡

ይምሩ:- አሁን እነዚህን አጠቃላይ ወጪዎች እንደምራለን። ስንት ይሆናል?

ቡድን አመቻቾች፡- ሠልጣኞች ሒሳቡን እንዲሰሩ ይምሩ ፡፡ ሁሉም በሒሳብ ቀመሩ መሠረት በጋራ እየሠሩ
መሆኑን ያረጋግጡ፡፡

ይምሩ:- ከዚያም ያገኘነውን ይህን ሒሳብ ከጠቅላላ ገቢያችን ላይ እንቀንሰዋለን።

ቡድን አመቻች፡- ሥራ ፈጣሪዎች ይህን የሒሳብ ስሌት እንዲሰሩት ያግዟቸው፡፡ ሁሉም በጋራ በቀመሩ
መሰረት እየሠሩ መሆኑን ያረጋግጡ ፡፡

ይምሩ:- ምን ያህል ገንዘብ ይቀራል? (ምላሾችን ይሰብስቡ)

ይምሩ:- ውጤታችን ትርፍ ሆነ ወይስ ኪሳራ?

ይምሩ:- ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆት ጋር ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ሥራ ፈጣሪዎች እንደመሆናችን መጠን፤ አዲስ ሥራ ስንጀምር ሊፈጠር የሚችለውን ስጋት /አደጋ/
ምን ጊዜም እንጋፈጣለን፡፡

ይምሩ:- አደጋ /ስጋት/ን መጋፈጥ ማለት፤ እኛ በጠበቅነው ልክ ብዙ ገንዘብ ላናገኝ በምንችልበት ቢዝነስ ላይ
ጊዜን በማዋል እና ገንዘብን በመመደብ ዕድልን ለመሞከር መወሰን ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- ዕቅድ በአግባቡ ካላወጣን ወይም በዕቅዳችን መሠረት እንዳንጓዝ የሚያግደን ያልታሰበ ድንገተኛ አደጋ
ከገጠመን፤ቢዝነሱ ሁልጊዜም ላይሳካ የሚችልበት ዕድል አለ፡፡

ይምሩ:- ውድቀትን በመፍራት አዲስ ነገርን ከመሞከር እንዲያግደን መፍቀድ አለብን? (በጭራሽ!)

ይምሩ:- መጽሐፍ ቅዱስ በመክብብ 11÷4-6 ላይ እንዲህ ይላል፡-

“ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ደመናንም የሚከተል አያጭድም፡፡ የንፋስ መንገድ እንዴት እንደሆነች


አጥንትም በእርጉዝ ሆድ እንዴት እንድትዋደድ እንደማታውቅ፤እንዲሁም ሁሉን የሚሰራውን የእግዚአብሄርን
ስራ አታውቅም፡፡ ወይም ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንዲሆኑ አታውቅምና
በማለዳ ዘርህን ዝራ፤ በማታም እጅህን አትተወው፡፡”

45
ይምሩ:- ስጋት /አደጋ/ን ስለመጋፈጥ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስለሚነግረን ነገር ያላችሁን ሃሳብ
በየቡድናችሁ ተነጋገሩበት፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ5 ደቂቃዎች ያህል በምንባቡ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ በተመለከተ አንድ ወይም ሁለት
ተሳታፊዎችን ይጠይቁ፡፡ ከዚያም፤አደጋ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል እያወቁ በድፍረት የገቡበት ወይም
ውጤታማ እንደሚሆኑ እርግጠኛ ያልሆኑበትን ነገር ሞክረው ያውቁ እንደሆን የግል ሕይወታቸውን
እንዲያጋሩ ይጠይቋቸው፡፡ አሁን ላይስ “ስጋቱን መጋፈጥ ነበረብን፤ አሁንም እንደገና ቢገጥመን ያንኑ ደግመን
እናደርገዋለን፤ ወዘተ.” ብለው ያምኑ እንደሆን ይጠይቋቸው፡፡

ይምሩ:- በቢዝነሱ ላይ የሚያሰጋ ነገር እንዳለው እያወቀ ለመጋፈጥ የወሰነ፤ነገር ግን ውጤቱ እንደፈራው
ሳይሆን የቀረ ታሪከ ሊያጋራን የሚችል አንድ ፈቃደኛ ሰው ይኖራል? (ምላሽ ይቀበሉ፤ ለተሰጡ መልሶች
አድናቆትዎን በመግለጽ ጣፋጭ ይሸልሙ።

ይምሩ:- አደጋዎችን የምንወስድባቸው ጊዜያት አሉ ግን እኛ የፈለግነውን ውጤት አናገኝም ፡፡

ይምሩ:- በንግድ ስራ ላይ ስጋት ስላለብዎ እና ውጤቱ እርስዎ የጠበቁት ስለነበረበት ጊዜ አንድ ሰው እንዲናገር
ማድረግ እችላለሁን? (ምላሽ ያግኙ ፤ በጣፋጭ እና በቃላት ውዳሴ ይክፈሉ።)

ይምሩ:- ስጋቶችን ሁሉ ተጋፍጠን ጥሩ ውጤት የምናስመዘግብበት ጊዜያት አሉ፡፡ ዋጋ በመክፈላችን አንድ


ነገር እናገኛለን። መጽሐፈ መክብብ ምንባብ እንደሚነግረን፤ዋጋ የማይከፍሉ ወይም ስጋትን የማይጋፈጡ
ሰዎች ስለማይዘሩና ስለማያጭዱ የሚበሉት ምግብ እንኳ አያገኙም፡፡

ይምሩ:- በሌሎች ጊዜያት ደግሞ፤ስጋቶችን ሁሉ ተጋፍጠን ጥሩ ውጤት አናስመዘግብም፡፡


እንሞክራለን፤ውጤቱ ግን በጠበቅነው መንገድ መሆኑ ይቀርና ኪሳራ ይገጥመናል።

ይምሩ:- አንድ ቢዝነስ በምን ምክንያት ላይሳካ ይችላል? (መልሶችን ከሥራ ፈጣሪዎች ይቀበሉ፡፡)

ይምሩ:- አሁንም፤መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን፤የምንጋፈጣቸው ስጋቶች (አደጋዎች) ስለሚያስከትሉት


ውጤት አስቀድመን መተንበይ አንችልም፤እናም አንዳንድ ጊዜ ውጤታማ ያደርጉናል ብለን ያሰብናቸው
ሳይሆኑ ይቀራሉ፡፡

ይምሩ:- አስተዋዮች ከሆንን፤ለወደፊቱ የተሻሉ እርምጃዎችን/መርሃ-ግብሮችን/ ለመምረጥ እንድንችል


እያንዳንዱን ስጋት እንደ መማሪያ ዕድል እንቆጥረዋለን።

ይምሩ:- ስጋትን ተጋፍጠን ካልተሳካልን፤ ከስህተታችን ተመክሮ በዕቅዳችን ላይ ትንሽ ማሻሻያ በማድረግ እና
እንደገና በመሞከር፤የተሻለ ውጤት ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ይህ ልምምድ፤ህጻን ልጆች በእግሮቻቸው ለመቆም
እና ለመራመድ እንደሚማሩት ዓይነት ነው፡፡ ይነሳሉ እንደገና ተመልሰው ይወድቃሉ፤ነገር ግን ጥረታቸው
እንዲሳካ ያለመታከት መቀጠል አለባቸው፡፡

ይምሩ:- ብዙ ቢዝነሶች ትርፋማ ለመሆን ረጅም ጊዜን ይወስዳሉ።

ይምሩ:- ደንበኞችን መሳብ እና አመኔታቸውን ማትረፍ አለብን፡፡ የምናገኘውን ገንዘብ አዳዲስ የሽያጭ
ምርቶች(ዕቃዎች) መግዣ ማዋል አለብን፡፡ ወደፊት ብዙ ሽያጭ እንዲኖረን ለማስቻል የአገልግሎት ጥራትን
ማሻሻል ይኖርብናል።

ይምሩ:- ትርፋማነት በአንድ ጀንበር አይከሰትም። ይሁን እንጅ፤ ብዙ አነስተኛ ቢዝነሶች ሥራቸውን
የሚጀምሩት በዝቅተኛ ዋጋ ስለሆነ በጣም በፍጥነት ትርፋማ መሆን ይችላሉ፡፡

46
ይምሩ:- በዚህ ክፍል የተማራችሁትን አንድ ነገር ልትነግሩኝ የምትችሉ ሁለት ሰዎች ትኖራላችሁ?

ይምሩ:- ሁለት ሠልጣኞችን ወደ መድረክ ይጥሩና አንድ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ ለመልሶቻቸው ማረጋገጫ
በመስጠት እንደገና ይድገሙት፡፡

ይምሩ:- ዋው!ሁላችሁም ጥሩ መረዳት ነው ያላችሁ፡፡ ዛሬ ስለ ወደፊታችን እና ንግዶቻችን ማለም ብዙ


ተምረናል፤ እንዲሁም ጥሩ እቅዶችን ለራሳችን ማዘጋጀት ጀምረናል! በጥረታችሁ ኮርቻለሁ፡፡ በቀጣይ ክፍል
ደግሞ ስለ ግብይት እንማራለን ::

47
// ክፍል 6 //

ግብይት 1

የሚወስደው ጊዜ፡- 1.5 ሠዓት

ግቦች:-
> ተሳታፊዎች፤ የማርኬቲንግ /ግብይት/ን ጠቀሜታ ይረዳሉ፤ በደንበኞቻቸው ዘንድ ተመራጭ መሆን
የሚችሉባቸውን መንገዶችም ይገነዘባሉ፤
> ተሳታፊዎች ፤የተመረጠ ገበያን ወይም የገበያ ዒላማቸውን ይረዳሉ፤
> ተሳታፊዎች፤ የደንበኞቻቸውን ፍላጎት እንዴት እንደሚረዱ ያውቃሉ፡፡

አቅርቦቶች፡-
> እስክሪብቶዎች > የሠሌዳ ማርከሮች
> የሠልጣኞች መጻሕፍት > ጣፋጮች
> ነጭ ሠሌዳ > የፕላስቲክ ዶሮ ወይም የሞተ እውነተኛ ዶሮ

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


> ምርት ወይም ዕቃ > የገበያ ጥናት ትንተና
> ጥሬ ዕቃ > የዳሰሳ ጥናት
> ጅምላ አከፋፋይ > የተመረጠ ገበያ ወይም የገበያ ዒላማ
> ቸርቻሪ > ሙከራ

ትዕይንቶች፡-
> “በአካባቢየ ያሉ ሰዎች ምን ይፈልጋሉ?” > የገበያ ታርጌት፡- ገበሬ
> “የሌለን የቢዝነስ ዓይነት ምንድን ነው?” > የገበያ ታርጌት፡- እናት
> “ሰዎች ምን መግዛት ይፈልጋሉ?” > የገበያ ታርጌት፡- ነጋዴ /የቢዝነስ ሰው/
> ባዶ መጋዘን ወይም ሱቅ

ዝግጅት:-
> በዶሮው ድራማ ውስጥ ለመሳተፍ ሁለት በጎ ፈቃደኞችን አስቀድመው ይምረጡ (አመቻቾች፣ ቡድን
መሪዎች ወይም ሥራ ፈጣሪ ተሳታፊዎች ሊሆኑ ይችላሉ)፡፡ የትኛውን ገቢር ማንኛው አመቻች
እንደሚተውን በሰልጣኞች መምሪያ ላይ በእርሳስ መጻፍ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ድራማውን
ቀድማችሁ ተለማመዱ፡፡

48
> በዚህ የትምህርት ክፍል ትዕይንቶች ላይ ያሉ አንዳንድ በደማቅ ፊደላት የተጻፉ ስሞች፤ ረዘም ያሉ
ስለሆኑ አያንብቧቸው፡፡ ትዕይንቱ ላይ ተንጋድደው የተጻፉ (ኢታሊሳይዝድ) ስሞችን ግን ድምጽዎን
ከፍ አድርገው ከረቂቁ ላይ ያንብቡ፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ:-


● ፊልጵስዩስ 2÷4

ይምሩ:- በድጋሚ እንኳን ደህና መጣችሁ! አሁን ስለ ማርኬቲንግ እንነጋገራለን፡፡

ይምሩ:- ስኬታማ ቢዝነስ ማለት ምርቶቻችንን ወይም አገልግሎቶቻችንን ለደንበኞቻችን ውጤታማ በሆነ
መንገድ መሸጥ መቻል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን አንድን ምርት ወይም አገልግሎት መሸጥ ከመቻላችን በፊት
ደንበኞቻችን የሚፈልጉትን ወይም የሚያስፈልጋቸውን በትክክል ለመረዳት ጠንክረን መሥራት አለብን።

ይምሩ:- አሁን የማርኬቲንግን /ግብይትን/ ገጽታ ለማሳየት ሁለት በጎ ፈቃደኛ ተሳታፊዎቻችንን ወደ


መድረኩሁለት በጎ ፈቃደኛ ተሳታፊዎቻችን እንዲመጡ መጋበዝ እፈልጋለሁ፡፡

ድራማ

(ቀደም ሲል የተመረጡ) ሁለት በጎ ፈቃደኛ ሠልጣኞች ወደፊት እንዲመጡ ያድርጉ ፡፡ አንደኛው የፕላስቲክ
ዶሮ ይዞ (ከሌለም የሞተ ዶሮ የያዘ በማስመሰል) ይቆማል። ሌላኛው የገበያ ዘንቢል እና የተወሰነ ገንዘብ
ይይዛል ፡፡

ባለ ሱቅ (ድምጹን ከፍ አድርጎ):- “የሚሸጥ ዶሮ፣ ዶሮ እዚህ አለ፡፡”

ደንበኛ (ወደ ባለ ሱቁ በመቅረብ አካባቢውን ይቃኛል):- “እንቁላል የምትጥል ዶሮ እፈልጋለሁ፡፡ ልትሸጥልኝ


ትችላለህ?”

ባለ ሱቅ (የፕላስቲክ ዶሮውን እንደያዘ):- “የታረደ የስጋ ዶሮ ነው ያለኝ፤ማለት ለስጋ የሚሆን፡፡”

ደንበኛ (በተከፋ ስሜት፣ጭንቅላቱን እየነቀነቀ):- “አይ፤የታረደ የስጋ ዶሮ አልፈልግም፡፡ ምንም


አያደርግልኝም። ለቤተሰቦቼ የሚሆን እንቁላል የምትጥል ዶሮ ነው የምፈልገው፡፡

ባለ ሱቅ፡- “የሚገርምህ እነዚህ ዶሮዎች በጣም ጣፋጭ ናቸው፡፡ ግድ የለህም፤ አንዱን ውሰድ?”

ደንበኛ (ጥሎ እየሄደ):- “እኔ የምልህን እየሰማኸኝ አይደለም። ለቤተሰቦቼ የሚሆን እንቁላል የምትጥል እንጅ
የታረደ የስጋ ዶሮ አልፈልግም! ”

ይምሩ:- ፈቃደኛ ተሳታፊዎችን ያመስግኑ እና ወደየቡድኖቻቸው ተመልሰው እንዲቀመጡ ያድርጉ፡፡

49
ይምሩ:- በቢዝነስ ዓለም ስኬታማ ለመሆን የደንበኞቻችንን ፍላጎቶች ማሟላት የሚያስችሉንን ስልቶች
መቀየስ፤ እንዲሁም ሌሎች ለእኛ እንዲያደርጉልን በምንፈልገው መጠን መንከባከብ ይኖርብናል፡፡

ይምሩ:- ባለ ሱቁ የደንበኛውን ፍላጎት አሟልቷል ልንል እንችላለን? (በጭራሽ፡፡)

ይምሩ:- መጽሐፍ ቅዱስ በፊልጵስዩስ 2÷4 ላይ እንዲህ ይላል፡-

“እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፤ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።”

ይምሩ:- ባለ ሱቁ፡ የዕንቁላል ዶሮ ሲጠየቅ የታረደ የስጋ ዶሮ ለመሸጥ መሞክሩ ሲታይ፡ የደንበኛውን ፍላጎት
ግምት ውስጥ ያስገባ ነበር ሊባል ይችላል? (በፍጹም፡፡)

ይምሩ:- ለምን? (ምላሽ ይቀበሉ፤ለተሰጡ መልሶች አድናቆትዎን በመግለጽ ጣፋጭ ይሸልሙ።)

ይምሩ:- ባለ ሱቁ የደንበኛውን ፍላጎት ለማሟላት እንዴት የተሻለ ሥራ ሊሠራ ይችል እንደነበር በየቡድናችሁ
ተወያዩበት፡፡

2 ደቂቃ ያህል ተጠቀሙ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ2 ደቂቃዎች ያህል፡፡ የራሳችንን ብቻ ሳይሆን የሌሎችን ፍላጎት ማሟላትን በተመለከተ
የሚካሄደውን ይህንን ውይይት ይምሩ፡፡

ይምሩ:- ባለ ሱቁ፤ የደንበኛውን ፍላጎት በተሻለ ለማስተናገድ ሊያደርግ ይገባ ነበር የሚሉትን ሊያጋሩ
የሚችሉ ሁለት ተሳታፊዎች ይኖራሉ?

ይምሩ:- ለተሰጡ መልሶች አድናቆትዎን በመግለጽ ጣፋጭ ይሸልሙ።

ይምሩ:- አሁን ደግሞ ስለ አራቱ መሠረታዊ የማርኬቲንግ /ግብይት/ ግብዓቶች (4Ps) ስለሆኑት፤ ስለ
ምርት(P)፣ ዋጋ(P)፣ ቦታ(P) እና ስለማስተዋወቅ(P) እንነጋገራለን፡፡

ይምሩ:- ከምርት እንጀምር፡፡ ምርት ማለት ደንበኛ የሚፈልገውን ወይም የሚያስፈልገውን የሚያሟላ
ማንኛውም ዓይነት አካላዊ ቁስ ወይም አገልግሎት ነው።

ይምሩ:- አንድን ምርት ለማዘጋጀት የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ከብዙ ቦታዎች ሊመጡ ይችላሉ፡፡ እኛ እራሳችንን
ልንሠራቸው ወይም ልናበቅላቸው እንችላለን፤ ያለዚያም ከጅምላ ሻጭ ወይም ከቸርቻሪ ልንገዛቸው
እንችላለን፡፡

ይምሩ:- ጅምላ አከፋፋይ ምን ማለት እንደሆነ ማን ሊነግረኝ ይችላል?

ይምሩ:- ስለ ጅምላ አከፋፋይ ትርጓሜ እንዲሰጡ ተሳታፊዎችን ይጠይቁ፡፡ (ትርጓሜ፡- እጅግ በጣም ብዙ
መጠን ያላቸውን ዕቃዎች ወይም ምርቶች በዝቅተኛ ዋጋ ለችርቻሮ የሚያከፋፍል ሰው ወይም ቢዝነስ
ነው፡፡)

ይምሩ:- በትክክል! ጅምላ አከፋፋይ፤ ስሙ እንደሚያመለክተው፤ ከፍተኛ መጠን ያላቸውን ዕቃዎች ወይም
ምርቶች በዝቅተኛ ዋጋ ለሌሎች የቢዝነስ ሰዎች የሚሸጥ ግለሰብ ወይም ድርጅት ነው፡፡ ፍራፍሬዎችን እና
አትክልቶችን ለአትክልት ቤቶች የሚያቀርብ ገበሬ ጥሩ የጅምላ አከፋፋይ ምሳሌ ሊሆነን ይችላል፡፡

50
ይምሩ:- ቸርቻሪ፤ ለደንበኛ ግለሰቦች የሚሸጥ ሰው ወይም ቢዝነስማን ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ለፍጆታ
የሚውል የህጻናት ምግብ ለእናቶች የሚሸጥ ባለ ሱቅ፤ ቸርቻሪ ይባላል፡፡

ይምሩ:- አሁን በጅምላም ይሁን በችርቻሮ፤ ምርትን ወይም አገልግሎትን ደንበኛ በሚፈልገው መልኩ ለገበያ
ማቅረብ አለብን፡፡ እኛ የእንቁላል ዶሮን ለሚፈልግ ደንበኛ፤ የታረዱ የስጋ ዶሮዎችን መሸጥ አንፈልግም፡፡

ይምሩ:- ስለዚህ ከሁሉ አስቀስሞ፤ በማህበረሰቡ መካከል ገብተን አንዳንድ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማጥናት
ይኖርብናል፡፡ እስቲ መጽሐፍቶቻችሁን ክፈቱና ገጽ ___ን እንመልከት፡፡

ይምሩ:- ቢዝነሶቻችሁን ስታቅዱ፤ ከዚህ በታች የተገለጹት ጥያቄዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው (ወደ
ትዕይንቱ ያመልክቷቸውና ጥያቄዎቹን ያንብቡላቸው)

● በአካባቢዬ ያሉ ሰዎች ምን ይፈልጋሉ?


● የሌለን ቢዝነስ ምንድን ነው?
● ሰዎች ምን መግዛት ይፈልጋሉ?

ይምሩ:- እንደ ቢዝነስ ባለቤት፤ የማህበረሰባችንን ፍላጎቶች መረዳትና ቢዝነሶቻችን ለእነዚህ ፍላጎቶች
ምላሽ የሚሰጡ ማድረግ የእኛ ድርሻ ነው፡፡

ይምሩ:- የገበያ ጥናት ትንተና፤ ማህበረሰባችን የሚፈልገውንና የሚያስፈልገውን ለይቶ ለማወቅ


በአካባቢያችን ካሉ ሰዎች መረጃን የመሰብሰብ ሂደት ነው፡፡

ይምሩ:- ጥሩ የገበያ ጥናት ትንተና ለማካሄድ በርካታ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ፤ በገበያ ላይ ያሉትን ምርቶች
እና አገልግሎቶችን መቃኘት እንችላለን።

ይምሩ:- የሌሉትን እና እኛ ልናቀርብ የምንችላቸውንም መቃኘት እንችላለን ፡፡ በመጀመሪያው ሥዕል ላይ፤


ሴቷ ምን ትፈልጋለች ብላችሁ ታስባላችሁ? (አዲስ ቀሚስ)

ይምሩ:- በዚህ ትዕይንት ላይ እንዳያችኋት ሴት፤ በተመሳሳይ መልኩ ቢዝነሶች ሊያቀርቡላቸው የሚችሏቸው
ፍላጎቶች ማህበረሰባችን አለው፡፡

ይምሩ:- ማህበረሰባችን ይኖረዋል ስለምትሏቸው ፍለጎቶች እና እነዚያን ፍላጎቶች እንዴት መወሰን


እንደምንችል በየቡድናችሁ ተወያዩበት ፡፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እራሳችሁን ጠይቁ፡- የአንተ ማህበረሰብ
በብዛት ምን አለው? ረጅም ርቀት ተጉዘው መጥተው ለመሸመት የሚያስገድዳቸው ምን ዓይነት ምርት
ወይም አገልግሎት አለህ? ማህበረሰብህ ውስጥ የጎደለው/የሌለው/ ምንድነው? በእውነቱ ይህንን በሚገባ
እንፈትሽ፡፡ በዚህ ጉዳይ ለመወያየት 10 ደቂቃዎች ተጠቀሙ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ10 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ስለ ማህበረሰብ ፍላጎቶች በሚኖረው ውይይት ይምሩ። የቢዝነስ
ጽንሰ-ሃሳብ ገና እየፈጠሩ ላሉ ተሳታፊዎች፤ ስኬታማ የሚያደርጋቸውን አማራጭ ለማሰብ ይህ አስፈላጊና
ጠቃሚ ጊዜ ነው፡፡

ይምሩ:- አሁን ቡድናችሁ ከተወያየባቸው ፍላጎቶች ውስጥ አንዱን ሊያጋሩ የሚችሉ ሁለት ሠልጣኞች
ይኖራሉ? ለተሰጡ መልሶች አድናቆትዎን በመግለጽ ጣፋጭ ይሸልሙ።

ይምሩ:- የማህበረሰብን ፍላጎቶች ለይቶ ለማወቅ አንዱ መንገድ፤ በአካባቢው ባሉ የቢዝነስ ተቋማት
ያልተሟሉ ፍላጎቶች መኖር አለመኖራቸውን ለማወቅ ጓደኞቻችንን፣ ጎረቤቶችንን እና የማህበረሰቡን አባላት
መጠየቅ ነው ፡፡

51
ይምሩ:- ሌላው የማህበረሰብ ፍላጎቶች ለይቶ የማወቂያ ስልት የዳሰሳ ጥናት /ቅኝት/ ነው። የዳሰሳ
ጥናት ማለት በቀላል አገላለጽ፤ የሰዎችን ፍላጎቶች ለመረዳት እንዲያግዙን የምንጠይቃቸው ጥያቄዎች
ስብስብ ነው።

ይምሩ:- የዳሰሳ ጥናት /ቅኝት/ በጣም ውጤታማ እንዲሆን፤ ከ25 እስከ 50 የሚደርሱ ሰዎችን ስለ ወል
ፍላጎቶቻቸው መጠየቅ እና ምላሾቻቸውን መመዝገብ ያስፈልጋል፡፡

ይምሩ:- ቀላል ቅኝት /ዳሰሳ/ ለማረግ ከዚህ በታች ያሉ መጠይቆችን እናቀርባለን፡-

1. ሊገዙት እየፈለጉ ግን በአካባቢዎ የማያገኙት ነገር ምንድን ነው?


2. ለመግዛት/ለመሸመት/ ሲፈልጉ በተለምዶ ምን ዓይነት ቦታዎችን ይመርጣሉ?
3. በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ ቢቀርብልን ብለው የሚመኙት አገልግሎት ምንድነው?

ይምሩ:- እነዚህ የዳሰሳ ጥናት መጠይቆች በመጽሐፍቶቻችሁ ገጽ ___ ላይ ተዘርዝረዋል፡፡

ይምሩ:- በመቀጠል የማህበረሰባችንን ፍላጎቶች ለማሟላት እንዴት አንድ ነገር ማድረግ እንደምንችል ማሰብ
ያስፈልገናል፡፡

ይምሩ:- ስለዚህ ጉዳይ ስናስብ፤ ተሰጥኦ እና ክህሎቶቻችን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባትና እነዚህን ገፀ-በረከቶች
በመጠቀም እንዴት ለሌሎች ፋይዳ ያለው ነገር መስራትና የቢዝነስ ዕድሎችን ማሳደግ
እንደምንጠቀምባቸው ማሰብ ይኖርብናል፡፡

ይምሩ:- የተለያዩ የአካል ብልቶች እና ሁሉም እንዴት ለተለያየ ዓላማ እንደሚውሉ መነጋገራችንን
ታስታውሳላችሁ?

ይምሩ:- ለማኅበረሰባችን እንድናበረክት እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ስለቸረን ክህሎቶች ወይም


ተሰጥኦዎች በየቡድኖቻችሁ ወያዩበት። ለዚህ ውይይት 10 ደቂቃ ያህል ጊዜ አላችሁ፡፡ ሁሉም የቡድን አባላት
መሳተፋቸውን አረጋግጡ!

ቡድን አመቻቾች፡- ለ10 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ሁሉም የየቡድን አባላት በዚህ ውይይት ሙሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ
በተቻለ መጠን ጥረት አድርጉ፡፡ ፈቃደኛነት ካላሳዩ፤ የተሻለ ስኬታማ የሚሆኑበት ምን ልዩ ተሰጥኦ
እንዳላቸው፤ ወይም ሌሎች ሰዎች እምብዛም የማያሳኳቸው እነሱ ግን በቀላሉ ማከናወን የሚችሏቸው ምን
ምን ነገሮች እንዳሉ ይጠይቋቸው ፡፡ እነዚህ ሥራ ፈጣሪዎች አሁንም ልዩ ተሰጥኦዎቻቸውን ለመናገር
ከተቸገሩ፤ እርስዎ ራስዎ በእነሱ ላይ ያስተዋሉትን ወይም የሚያውቁትን ክህሎቶቻቸውን በነፃነት
ይጥቀሱላቸው፡፡

ይምሩ:- ልዩ ክህሎቱን ሊያጋራን የሚችል አንድ ፈቃደኛ ሰው ይኖራል?

ይምሩ:- ብዙዎች በመመለስ እንዲሳተፉ ያድርጉ፤ ለመልሶቹ ማረጋገጫ በመስጠት ጣፋጭ ይሸለሙ።

ይምሩ:- “የሌሉን ቢዝነሶች ምንድን ናቸው?” የሚለውን ጥያቄ መጠየቅም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ትዕይንቱ
ላይ ወዳለው፤ “የሌሉን ቢዝነሶች ምንድን ናቸው?” ወደ ሚለው ጽሁፍ ያመልክቷቸው።

ይምሩ:- በአንድ ማህበረሰብ ወይም መንደር ውስጥ እስከ 20 የሚደርስ የዶሮ መሸጫ ሱቅ ሲኖር ፣ አንድም
የልብስ መሸጫ ቡቲክ ግን ላይኖር ይችላል፡፡

52
ይምሩ:- ብዙ ጎረቤቶቻችን የልብስ መሸጫ ሱቅ በቅርበት እንደሚፈልጉ ከተረዳን፣ ይህንን ሱቅ መክፈት
የተሻለ የስኬት እድል እንደሚፈጥርልን አያጠረጥርም። ምክንያቱም ወዲያውኑ ብዙ ደንበኞችን እናፈራለን፡፡

ይምሩ:- የሴቶች የልብስ መሸጫ ሱቃችንን ምሳሌ እንጠቀም፡፡ ትዕይንቱ ላይ ወዳለው ባዶ ሱቅብ
ያመልክቷቸው። ምንም እንኳ ብዙ የሴቶች ልብስ መሸጫ ሱቆች ቢኖሩም፤ እኛ በምንኖርበት አቅራቢያ
በተመጣጣኝ ዋጋ ጥሩ ፋሽን ልብሶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚሸጡ ብዙ ይኖራሉ?

ይምሩ:- ከሌሉ፤ እኛ ልናሟላው የሚገባ የማህበረሰብ ፍላጎት ሊኖር ይችላል ፡፡

ይምሩ:- ሌላው ምሳሌ ምናልባት ጥራት ያለው ምግብ ቤት ሊሆን ይችላል ፡፡ _________ (ባህላዊ ምግብ)
የሚሸጡ ብዙዎች ሊኖሩ ይችላሉ፣ ዶሮ የሚሸጥ ግን የለም፡፡

ይምሩ:- ማህበረሰባችን __________ (ከላይ የተጠቀሱ ተመሳሳይ የምግብ ዓይነቶች) የሚሸጡ ሰባት
ምግብ ቤቶች አያስፈልጉትም።

ይምሩ:- ሰዎች የሚወዱትን ግን በሌሎች ምግብ ቤቶች ውስጥ በቀላሉ ማግኘት የማይችሏቸውን ምግቦች
የሚሸጥ ምግብ ቤት የምንከፍት ከሆነ ብዙ ደንበኞችን መሳብ እንችላለን

53
የስኬት ታሪክ

ይምሩ:- በታሊ ፕሮግራም ውስጥ በጣም ስኬታማ ለመሆን የበቁ ሥራ ፈጣሪዎች፤ በማህበረሰባቸው ውስጥ
የጎደለውን በጥልቀት ለመቃኘት ፈቃደኛ የሆኑት ናቸው፡፡ የቢዝነስ ስኬት፤ በአካባቢው ያሉ ሌሎች ቢዝነሶችን
ከመኮረጅ ያለፈ ነው፡፡

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ ግብፃዊው መሐመድ (በመጽሐፍቶቻችሁ ገጽ ___ ላይ እንደተጠቀሰው) በእርሱ አካባቢ


የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ለየጀነሬተሮቻቸው የሚሆን ነዳጅ ለመግዛት ረዥም ርቀት እንደሚጓዙ አህመድ
አስተዋለ፡፡ ለትራንስፖርት ገንዘብ ለማውጣት፤ ወይም ከገዙት ነዳጅ ላይ ቀንሰው እስከመክፈል ይገደዳሉ፡፡

እናም አህመድ ለአህያው ጋሪ፣ጀሪካን እና ነዳጅ መግዣ የሚሆን ገንዘብ ከታሊ አነስተኛ አበዳሪ ድርጅት
ወሰደ፡፡ ከሌላ ሰፈር ነዳጁን እየገዛ በጋሪው እያመላለሰ ለጎረቤቶቹ መሸጥ ጀመረ፡፡ ተንቀሳቃሽ ነዳጅ ማደያ
ጣቢያ ፈጠረ! ይህ የንግድ ፈጠራ ሃሳቡ በዙሪያው ያለውን ህብረተሰብ ፍላጎት ለማሟላት፤ ለእሱም ጥሩ ገቢ
ማስገኛ ሆነለት፡፡

ይምሩ:- በመጽሐፍቶቻችሁ ገጽ ___ ላይ የታሊ ደንበኞች የፈጠሯቸውን የቢዝነስ ሃሳብ ዝርዝሮች ማየት
ትችላላችሁ፡፡ ስለ እነዚህ የቢዝነስ ፈጠራ ዝርዝሮች ምን ታስባላችሁ?

ይምሩ:- እስቲ ለጥቂት ደቂቃዎች በየቡድኖቻችሁ ተወያዩበት፡፡

ቡድን አመቻች፡- ለ4 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ዝርዝሮቹን ለሁሉም ቡድን ጮክ ብለው ያንብቡላቸው። ውይይቱን
ያመቻቹ ፡፡ ከሁሉ የላቀው የፈጠራ ሀሳብ የትኛው ነው? ከዚህ ዝርዝር፤ ተሳታፊዎችን ምን አዲስ ነገር
እንዲያመነጩ ያደርጋቸዋል?

በታሊ ደንበኞች የተከፈቱ የቢዝነስ ዓይነቶች


● ሥጋ ቤት ● የተማሪ መጻህፍት ● ሻይ ቅጠል ማሸግና መሸጥ
● ፈጣን /ቴክ አወይ/ ምግቦች መሸጫ መደብር ● የማዳበሪያ አቅርቦት ቢዝነስ
● የከብት መኖ መሸጫ ቤት ● ፎቶ ቤት ● ዶሮ ርባታ
● ተረፈ ምርት ● ቀዝቃዛ ምግቦች መሸጫ ● ጁስ እና የወተት ተዋጽኦ
● ከብት ርባታ ● ባህላዊ የጥልፍ ስራ መሸጫ
● ቅመማ ቅመም ንግድ ● ኬክ መጋገሪያ ● የጠረጴዛ ቴኒስ ማጫወቻ
● የእንሰሳት መድኒት ሽያጭ ● የውበት ሳሎን ● የልብስ መሸጫ መደብር
● የሞባይል ቻርጅ አገልግሎት
● የሽንኩርት እርሻ (ቡቲክ)
● ተንቀሳቃሽ ነዳጅ ማደያ
● የግንባታ ዕቃዎች መሸጫ ● አሳ መሸጫ ቤት
መደብር ● ከብት ማደለብ
● ልብስ ስፌት
● መስታወት እና የመስታወት ● ጫማ መሸጫ መደብር
● እህል መሸጫ
ክፈፍ መሸጫ መደብር ● የመዋቢያ ዕቃዎች መሸጫ
● የልብስ ተኩስ አገልግሎት ሱቅ

54
● ሞባይል ጥገና ቤት
● ምግብ ቤት

ይምሩ:- እንደምትመለከቱት፣ የቢዝነስ ሀሳብ በፈጠራ የተደገፈ መሆን ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡
በአካባቢያችሁ እንደምታይዋቸው ነጋዴዎች ተመሳሳይ ቢዝነስ መክፈት በጣም ቀላል እንደሆነ ስለሚታሰብ፤
የፈጠራ ቢዝነስ መጀመሪያ ላይ ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡

ይምሩ:- ከዚህ በፊት የተሞከረ፣ አሠራሩም ሆነ ውጤታማነቱ በግልጽ የታወቀ ቢዝነስን መሞከር የምቾት
እና የእርግጠኝነትን ስሜት ሊፈጥርላችሁ ይችላል። ያ ማለት ግን ስኬታማ ትሆናላችሁ ማለት አይደለም፡፡
በአካባቢው ያሉ የሌሎች ቢዝነሶች ኮፒ የሆነ ቢዝነስ ስኬታማ አይሆንም፡፡

ይምሩ:- በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ ተመሳሳይ ፍላጎቶች እንደሌላቸው ማስታወስም በእጅጉ


አስፈላጊ ነው። በእያንዳንዱ ማህበረሰብ ውስጥ የእኛን አገልግሎት የሚፈልጉ የተለያዩ ሰዎች አሉ፡፡
ደንበኛችን ማን እንደሆነ ለይተን ለማወቅ እራሳችንን የተለያዩ ጥያቄዎች መጠየቅ አለብን።

ይምሩ:- ለምሳሌ፣ “ሴቶችን ነው ማገልገል የምንፈልገው(እናቶችን ወደሚያሳየው ትዕይንት በጥቆማ


ያመልክቷቸው)፣ ልጆችን ወይስ ወንዶችን (የቢዝነስ ሰዎችን ወደ ሚያሳየው ትዕይንት ደግሞ
ይጠቁሟቸው)” በማለት ራሳችሁን ጠይቁ፡፡

ይምሩ:- “የምናገለግለው፤ በከተማ ውስጥ የሚኖሩትን ሰዎች ወይስ በገጠር (ገበሬን ወደ ሚያሳየው
ትዕይንት ይጠቁሟቸው)?”

ይምሩ:- “እነዚህ ሰዎች የአከባቢው ነዋሪዎች ናቸው ወይስ ጎብኝዎች?”

ይምሩ:- “ለሌሎች ሱቆች ጅምላ አከፋፋዮች ነን ወይስ በቀጥታ ለተጠቃሚ ደንበኞች የምንቸረችር?”

ይምሩ:- እነዚህንና መሠል ራሳችንን የምንጠይቃቸው ጥያቄዎች፤ ቢዝነሳችን የትኞች ሰዎች ላይ ማተኮር
እንደሚኖርበት፤ ወይም የገበያ ዒላማችንን /ታርጌት/ ለይተን እንድናውቅ ይረዱናል፡፡

ይምሩ:- የገበያ ዒላማችንን (ታርጌት) የበለጠ ለይተን ባወቅን ቁጥር፤ ለቢዝነሳችን ዕድገት የትኞቹን ምርቶች
እና አገልግሎቶች መሸጥ እንደሚኖርብን የተሻለ የማወቅ ዕድል ይፈጥርልናል፡፡

ይምሩ:- አሁን፤ እያንዳንዱን ቡድን ከሦስቱ የገበያ ዒላማዎች በአንዱ እመድባለሁ፡፡ (እያንዳንዱን ቡድን
በዚህ በትዕይንቱ ላይ በሚታዩት በሦስቱ የገበያ ዒላዎች ላየ ይመድቡ፡፡ በትዕይንቱ ላይ ያሉት ስዕሎች እና
የቡድኖች ቁጥር ካለተመጣጠነ፤ አንዱን ስዕል ከአንድ በላይ ለሆኑ ቡድኖች መመደብ ይኖርብዎታል፡፡)

ይምሩ:- በትዕይንቱ ላይ ለተጠቀሱት የገበያ ዒላማዎች የሚያስፈልጉ የምርት እና አገልግሎት አይነቶች


በየቡድኖቻችሁ ተወያዩበት ፡፡ 5 ደቂቃ ያህል ተጠቀሙ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ5 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ይጠይቁ፡- ስለዚህ ሰው ምን እናውቃለን? ለእነሱ አስፈላጊ የሆነው
ነገር ምንድን ነው? ምን መግዛት ይፈልጉ ይሆን? ለምን ዓይነት አገልግሎቶች ይከፍላሉ?

55
ይምሩ:- ከየቡድኑ አንድ አንድ ሰው እየተነሳ፤ ዒላማ ላደረጓቸው ገበያዎች ሊያቀርቡ የሚችሉትን የዕቃ
ወይም የአገልግሎት ዓይነት ታጋሩናላችሁ?

ይምሩ:- በፈቃደኛነት ላካፈሉ ሠልጣኞች ጣፈጭ ይሸልሙ።

ይምሩ:- በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ በግልጽ የተቀመጠና የገበያ ዒላማ ስላደረገ አንድ ቢዝነስ ማሰብ
እንችላለን? ሊሸጡለት እየሞከሩ ያለ ደንበኛን ባህሪ ለይተው የሚያውቁ ሰዎች፤ ገበያን ዒላማ ያደረገ ምርት
ማቅረብ ይችላሉ? (የሙሽራ ልብስ መሸጫ ሱቅ ለሙሽሮች፣ ፋርማሲ ለበሽተኞች መድሃኒት፣ ወዘተ.
ይሸጣል)፡፡

ይምሩ:- ለዚህ ቢዝነስ የገበያ ዒላማው /ታርጌቱ/ ማን እንደሆነ በቡድኖቻችሁ ውስጥ ተነጋገሩበት፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ5 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ውይይቱን ያመቻቹ፡፡

ይምሩ:- ለቢዝነሶቻችሁ የገበያ ታርጌት ማን እንደሆነ ከእኔ ጋር በመሆን ልታካፍሉን የምትችሉ ሁለት
ሠልጣኞች ትኖራላችሁ?

ይምሩ:- ሠልጣኞቹ ያካፍሉ፡፡ ጣፋጭ ይሸልሟቸው፡፡

ይምሩ:- ስላካፈላችሁን እናመሰግናለን!

ይምሩ:- ዒላማ ያደረግነውን ገበያ አንዴ ከመረጥን በኋላ፤ ስለምንሸጣቸው የምርት ዓይነቶች ማሰብ
እንችላለን ፡፡

ይምሩ:- የሞባይል መሸጫ ሱቅ ለመክፈት ከፈለግን፤ ምን ዓይነት ሞባይሎችን ነው የምንሸጠው? ከሌሎች


ሱቆች የሚለየው እንዴት ነው? ምን ዓይነት መለዋወጫዎች ይገኛሉ? ቻርጀሮች እና ፓወር ባንኮች
እናቀርባለን?

ይምሩ:- ሌላ ቅኝት (ጥናት) ለማካሄድ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል - በተለይ ልንከፍት የወሰንነውን
የቢዝነስ ዓይነት ነጥለን ለማውጣት፡፡

ይምሩ:- ____________ ተብሎ የሚጠራ የልብስ መሸጫ ሱቅ (ቡቲክ) ለመክፈት ከፈለግን፤ የምናደርገው
ቅኝት (ጥናት) ሞባይል መሸጫ ሱቅ ለመክፈት ከምናደርገው ጥናት የተለየ ነው፡፡

ይምሩ:- ለልብስ መሸጫ ሱቅ የዳሰሳ ጥናት ለማድረግ፤ የሚከተሉትን ጥየቄዎች ልናቀርብ እንችላለን፡-

1. በመደበኛነት /አዘውትረው/ የሚለብሱት ምን ዓይነት ልብስ ነው?

2. ልብስ በየስንት ጊዜው ይገዛሉ?

3. በዓመት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ዓይነት ልብሶችን ይለብሳሉ?

4. ተወዳጅ ቀለሞችዎ ምንድናቸው?

5. ለልብስ ምን ያህል ያወጣሉ?

6. ብዙ ጊዜ ልብሶችን የት ነው መግዛት የሚወዱት?

56
ይምሩ:- ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጡት መልሶች ደንበኞቻችን ወደፊት ምን ሊገዙን እንደሚችሉ ግንዛቤ
እንዲኖረን ይረዱናል፡፡

ይምሩ:- ከላይ ከተዘረዘሩት የዳሰሳ ጥናት ጥያቄዎች አንዱን በመጠቀም፤በክፈሉ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ
ተሳታፊዎች ጥያቄውን እንዲመልሱ ያድርጉ፡፡ የመልሶቻቸውን መመሳሰል ልብ ይበሉ፡፡ ከአምስት ወይም
ስድስት ተሳታፊዎች በተሰጡ መልሶች የደረሱበትን የዳሰሳ ጥናት ድምዳሜ ያካፍሉ፡፡

ይምሩ:- ስለዚህ አሁን፤ ወደ ኋላ መለስ እንበልና የቢዝነስ ጽነሰ-ሀሳቦቻችንን ወይም አስቀድመን የጀመርነውን
ቢዝነስ እናስብ፡፡

ይምሩ:- የደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማወቅ እና እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት የሚያስችለንን ምርት ወይም
አገልግሎት የምናቀርብበት አንድ ወይም ሁለት ስልቶች የትኞቹ ናቸው?

ይምሩ:- ጥንድ ጥንድ በመሆን፤ የዳሰሳ ጥናት ጥያቄዎችን እርስ በእርስ እንጠያየቅ እና የሚሰጡ መልሶችን
በመጻፍ ወይም በማስታወስ ለደንበኞቻችን የተሻለ ማቅረብ እንችላለን፡፡

ይምሩ:- እነዚህ ጥያቄዎች፤ ለመጀመር ያቀድናቸው ወይም የጀመርናቸው ቢዝነሶች ላይ ትኩረት ያደረጉ
ሊሆኑ ይገባል፡፡ ያን ጊዜ ለገበያችን ታርጌት የሆኑ ደንበኞችን አይነት እንዲሁም የሚፈልጉትንና
የሚያስፈልጋቸውን ለይተን ለማወቅ ያስችለናል፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ7 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ጥያቄውን ደግመው ይናገሩት፡፡ አስፈላጊ ከሆነ የዳሰሳ ጥናቱን
ሞዴል ያድርጉ፡፡ ከዚያም የቡድን አባላቱን ስለ ገበያ ታርጌቶቻቸው ምን እንደተማሩ ይጠይቋቸው፡፡.

ይምሩ:- ስለ ቢዝነሶቻቸው እና የወደፊት ደንበኞቻቸው ፍላጎት ለመረዳት የሚጠየቅ አንድ ጥያቄ ሊነግሩን
የሚችሉ ከየቡድኑ አንድ አንድ ፈቃደኞች ይኖራሉ?

ይምሩ:- ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆት ጋር ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ግሩም ስራ! ታርጌት ያደረግናቸው ደንበኞች ምን እንደሚፈልጉ ከተረዳን በቢዝነሳችን አማካኝነት
ፍላጎቶቻቸውን ማሟላት እንችላለን፡፡ ይህም እነርሱን ያስደስታል፤ የእኛ ቢዝነስም ያድጋል፡፡

ይምሩ:- ምን እንደምንሸጥ ከወሰንን በኋላ፤ የገበያ ሙከራ ማድረግ ያስፈልገናል፡፡

ይምሩ:- ገበያችንን መሞከር ማለት፤ አዳዲስ ምርቶቻችንን ማስተዋወቅ እና በተመንነው ዋጋ ጥሩ ሽያጭ


መኖሩን ማየት ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- ገበያችንን መሞከር፤ ሊገጥሙ የሚችሉ ችግሮችን መጋፈጥን ይጠይቃል። ደንበኞች ይገዙት ወይም
አይገዙት እንደሆነ ሳናውቅ አዳዲስ ምርቶችን ገዝተን ለመሸጥ ገንዘብ ኢንቨስት እናደርጋለን።

ይምሩ:- እነዚህ አዳዲስ ምርቶች በደንብ ካልተሸጡ፤ ችግሩ ምን ሊሆን ይችላል?

ይምሩ:- ምላሾቹን ይጠብቁ… (የዋጋ መጨመር፣ የምርቱ ትክክለኛ አለመሆን፣ ፍላጎትን የሚያሟላ
አለመሆን፣ የጥራት ችግር፣ መጥፎ አካባቢ)።

ይምሩ:- በትክክል! ከምርቶቻችን ጋር በተያያዘ ያሉትን ችግሮች ለይተን ማውት ከቻልን፤ በቀጣይ ጊዜ
የተሻለ ለመሸጥ አስፈላጊ ለውጦችን ማድረግ እንችላለን!

57
ይምሩ:- አዲስ ምርት በመሸጥ የገበያ ሙከራ የማድረግ አጋጣሚ ባገኘ ጊዜ ስላገኘው ትምህርት /ተመክሮ /
በምሳሌ የሚያስረዳን ወይም ምስክርነቱን የሚያካፍለን አንድ ሰው ይኖራል?

ሥራ ፈጣሪዎች ያጋሩ፡፡ ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆትና ከምስጋና ጋር ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ከዚህ የትምህርት ክፍል የቀሰማችሁትን አንድ ነገር አስመልክቶ ሁለት ሰዎች ልትነግሩኝ
ትችላላችሁ?

ይምሩ:- ሁለት ሰዎችን ይጋብዙ እና አንድ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ አገላለጹን እንደገና በመድገም
መልሶቻቸውን ያስረግጡ፡፡

ይምሩ:- ዋው!ሁላችሁም ጥሩ መረዳት ነው ያላችሁ፡፡ በሚቀጥለው የትምህርት ክፍል ስለ ማርኬቲንግ


የበለጠ እንማራለን፡፡

// ክፍል 7 //
ማርኬቲንግ /ግብይት/ 2

የሚወስደው ጊዜ፡- 1.5 ሠዓት

ግቦች:-
> ሥራ ፈጣሪዎች፤ ስኬታማ የሚሆኑበትን አራቱን የማርኬቲንግ አላባዎች (4 Ps) ይረዳሉ፤ ዝርዝር
ግንዛቤም ይኖራቸዋል፡፡
> ሥራ ፈጣሪዎች፤ ለተለዩ ቢዝነሶቻቸው ስለአግባብ ልዩ ልዩ የማስታወቂያ ዘዴዎች እና እንዴት
ሊተገበሩ እንደሚችሉ ስለሚያመላክቱ አግባብ የሆኑ አላባዎች ግንዛቤን ያዳብራሉ ፡፡

አቅርቦቶች፡-
> እስክሪብቶዎች > ጣፋጮች
> የሒሳብ መደመሪያ ካልኩሌተሮች > የአካባቢው በራሪ ማስታወቂያ ወረቀቶች
> የሠልጣኞች መጻሕፍት > የአከባቢው ጋዜጣ
> ነጭ ሠሌዳ > የአካባቢው ቢዝነስ ካርድ (በትውስት)
> የሠሌዳ ማርከሮች > የቀለም እርሳስ

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


> የዋጋ ተመን > ፕሮሞሽን
> ጥራት > ማስታወቂያ
> ቦታ > የአንድ ለአንድ (የገጽ ለገጽ) ማስተዋወቅ

58
> ቅናሽ > የአፍ ለአፍ ማስታወቂያ

ትዕይንቶች (በግድግዳ ወይም በቦርድ ላይ የተለጠፉ ወይም በሠልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱ)፡-
> ባዶ ሱቅ > የግል ሽያጭ
> መንገድ ዳር ላይ ያለ የባዶ መጋዘን ፎቶ > ቅናሾች
> ማስታወቂያ > የአፍ ቃል

ዝግጅት:-
> ይህ ክፍል ስለ ዋጋ አተማመን በስፋት ይዳስሳል። ከዚህ ክፍል በኋላም በዚህ ርዕሰ-ጉዳይ ዙሪያ
በጥልቀት እንደሚማሩ እባክዎ ልብ ይበሉ፡፡
> ለማስታወቂያው የትምህርት ክፍለ ጊዜ የሚረዱ የአካባቢው በራሪ ማስታወቂያ ወረቀቶችን ፣
የአካባቢው ጋዜጣዎችን እና የአካባቢው ቢዝነስ ካርዶችን ይዘው ይምጡ፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ:-


> 1ጴጥሮስ 4÷9-11
> ምሳሌ 22÷1

ይምሩ:- ወዳጆች ሆይ፤ በድጋሚ እንኳን በደህና መጣችሁ! አሁን ስለ አራቱ የግብይት አዕማድ እንማራለን፡-
ምርት(P)፣ ዋጋ(P)፣ ቦታ(P) እና ፕሮሞሽን(P)። በባለፈው ክፍለ ጊዜ ምርታችንን ለይተን ስለ መወሰን
ተወያይተናል፡፡ አሁን ደግሞ ስለ ቀሪዎች ሦስቱ እንነጋገራለን፡፡

ይምሩ:- ዋጋ በሚለው እንጀምራለን፡፡

ይምሩ:- ከሌሎች ቢዝነሶች ጋር በማነፃፀር ለምርታችን ወይም አገልግሎታችን የምንተምነው ዋጋ


ስኬታችንን በመወሰን ረገድ ጉልህ ሚና አለው፡፡

ይምሩ:- ለምርቶቻችን ዋጋ ስንተምን፤ ወጪያችንን ሸፍኖ፣ ቁጠባችንን የሚያሳድግ እና ቢዝነሳችንን


የሚያስፋፋ ትርፍ ለማግኘት በሚያስችለን መልኩ መሆኑን ማርጋገጥ አለብን፡፡ ነገር ግን ዋጋው ደንበኞቻችን
እኛን ትተው ሌላ ቦታ ሂደው እንዲገዙ የሚያደርግ መሆን የለበትም።

ይምሩ:- ያለ በቂ ምክንያት፤ ከደንበኞቻችን አቅም በላይ ወይም ሌሎች ሱቆች ከሚያስከፍሉት ተመን በላይ
ማስከፈል አንችልም።

ይምሩ:- የምንጠይቀው ዋጋ ከምንሸጠው የምርት ዓይነት ጋር ተመጣጣኝ መሆን አለበት፡፡

ይምሩ:- የልብስ መሸጫ ሱቁን በምሳሌነት ብንወስድ፤ ከሌሎች መሠል ቡቲኮች የበለጠ ክፍያ መጠየቅ
ከሚያስችሉን ምክንያቶች አንዱ፤ ጥራት ያለው ልብስ ካቀረብን ነው፡፡

ይምሩ:- ምናልባትም ሌላኛው ምክንያት፤ ጥሩ የዳሰሳ ጥናት አድርጋችሁ በከፍተኛ ደረጃ ተፈላጊ የሆነ ልብስ
መሆኑን አረጋግጣችሁ ሊሆን ይችላል፡፡

59
ይምሩ:- በመጨረሻም ፣ ሱቃችን ሰዎች ወደሚኖሩበት አካባቢ ለመሄድ፣ ወደ አቅራቢያ ቅርብ ለመሄድ፣
ወይም የተሻለ የደንበኞች አገልግሎት ወይም ማሳያ ካለው፣ በማህበረሰባችን ውስጥ ካሉ ሌሎች ሱቆች በላይ
ማስከፈል እንችል ይሆናል ፡፡

ይምሩ:- የዋጋ ተመን እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው ፡፡ በእርግጥ ሙሉ ክፍለ ጊዜው በእዚህ ርዕስ ዙሪያ
ስለሆነ ብዙም ሳንቆይ ወደዚህ እንመለሳለን፡፡

ይምሩ:- ቀጣዩ የማርኬቲንግ አላባችን ቦታ ነው። “ባዶ ሱቅ”ን ወደሚያመለክተው ትዕይንት


ይጠቁሟቸው።

ይምሩ:- ስለዚህ ጉዳይ ቀደም ሲል መነጋገር ጀምረን ነበር፡፡ ምርቶቻችንን እና አገልግሎቶቻችንን


የምንሸጥበት ቦታ እጅግ በጣም ወሳኝ ነው፡፡

ይምሩ:- በአካባቢው ምርጥ የተባለ ልብስ ቢኖረን እንኳ፤ ከደንበኞቻችን የራቀ ያለዚያም ሱቃችን የቆሸሸ
ወይም የተበላሸ ከሆነ ማንም ሊገዛው አይችልም፡፡

ይምሩ:- እንዲሁም፤ ወደ ቢዝነስ ቦታችን በቀላሉ መጓዝ ወይም ምርቶቻችንን እዚያ ማድረስ ካልቻልን፤
ስፍራው ጥሩ ሊባል አይችልም።

ይምሩ:- ብዙ ጊዜ ለቤተሰቦቻችሁ ምግብ የምትገዙበትን ተወዳጅ መደብር እስቲ ለአንድ አፍታ አስቡ፡፡

ይምሩ:- ከዚያ ቦታ ምኑን እንደምትወዱ እስቲ ንገሩኝ ፡፡ የት ነው? ቅርበት ወይስ የመንገዱ አመችነት? ምን
ምን ይሸጣሉ? እንድትወዱት ያደረጋችሁ ምኑ?

ይምሩ:- ሠልጣኞች እጃቸውን እያወጡ፣ ተነስተው በየተራ መልስ እንዲሰጡ ያድርጉ። ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ከአካባቢ ምቹነት በተጨማሪ፤ ቢዝነሳችን የሰዎችን ፍላጎትና ቀልብ ስቦ የሚያመጣ ሊሆን ይገባዋል፡፡

ይምሩ:- ንጹህ፣ የተደራጁ፣ ጥሩ መስተንግዶ፣ ማራኪ፣ እና ደህንነታቸው የተጠበቁ ቢዝነሶች ብዙ ደንበኞችን


ከመሳባቸውም በተጨማሪ፤ ከሌሎች የተሸለ ዋጋ እንዲከፍሉ ያስችላቸዋል። መስተንግዶ ለሚለው ሌላ
ተመሳሳይ ቃል ፍቺ “መልካም አቀባበል” ሊሆን ይችላል።

ይምሩ:- እግዚአብሔር በእኛ እንዲከብር፤ እርሱ በሰጠን ጸጋ ሁሉ ተጠቅመን ሌሎችን እንድናገለግል ጥሩ


እንግዳ ተቀባዮች መሆን እንዳለብን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡

1ጴጥሮስ 4÷9-11 እንዲህ ይላል፡-

“ያለ ማንጎራጎር እርስ በርሳችሁ እንግድነትን ተቀባበሉ፤ ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ


መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ÷ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ
እርስ በእርሳችሁ አገልግሉ፤ ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፣ እንደ እግዚአብሄር ቃል ይናገር፤
የሚያገለግልም ቢሆን÷ እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን
እስከዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር
ዘንድ፤ አሜን።”

ይምሩ:- መልካም መስተንግዶን የሚያውቁ የቢዝነስ ባለቤቶች መሆን ምን ማለት እንደሆነ በየቡድኖቻችሁ
ተወያዩበት፡፡

60
ይምሩ:- ለጥቂት ደቂቃዎች ውይይት ያድርጉ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ2 ደቂቃዎች ያህል፡፡ “እንግዳ ተቀባይ መሆን የምንፈልገው ለምንድነው? ጥሩ


መስተንግዶ ያላደረገልዎት ሱቅ ሄደው ያውቃሉ? ሁኔታው እንዴት ነበር ነበር?” የሚሉትን ጥያቄዎች
አከታትለው ይጠይቁ፡፡

ልምምድ

ይምሩ:- ጥቂት ደቂቃዎችን ውሰዱና በአከባቢያችሁ ያሉ ማህበረሰቦች ወደ እናነት ሱቅ እንዲመጡ


የሚያደርጋቸውን ልዩ መስተንግዶ የሚያሳዩ ገጽታዎችን በጽሐፍቶቻችሁ ገጽ ____ ላይ ባለው ባዶ
ሱቃችሁ ላይ በስዕል ግለጹ፡፡ ሱቃችሁ የተለየ እንግዳ ተቀባይ መሆኑን የሚያሳይ ቢያንስ አንድ ልዩ ነገር ሳሉ።
ፈጠራ ተጠቀሙ!

ይምሩ:- በጽሐፍቶቻችሁ ገጽ ____ ላይ ባለው ባዶ ቦታ ላይ ለመሳል ጊዜ ይስጧቸው፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ4 ደቂቃዎች ያህል፡፡ የባዶ ሱቁን ግድግዳዎች በቀለም ከማስጌጥ ባሻገርየፈጠራ
ክህሎቶቻቸውን ተተቅመው በስዕል ሐሳቦቻቸውን እንዲገልጹ ያበረታቷቸው።

ይምሩ:- በመጽሐፍቶቻችሁ ላይ ስለ ሳላችኋቸው ነገሮች ሁለት ሰዎች ልታጋሩን ትችላላችሁ?

ይምሩ:- ጣፋጭ ይሸልሟቸው፡፡

ይምሩ:- ሱቃችን ለገበያ ምቹ በሆነ ቦታ ላይ ሊገኝ ይችላል፤ነገር ግን ስያሜ ከሌለው ፣ ሰዎች ጥሩ ልብሶችን
ለመግዛት የት መሄድ እንዳለባቸው ለጓደኞቻቸው ለመንገር /ለመጠቆም/ ሊቸገሩ ይችላሉ፡፡

ይምሩ:- ቀደም ሲል፤ ለልብስ መሸጫ ሱቃችን “_______” የሚል ስያሜ አውጥተንለት ነበር፡፡ በትዕይንቱ
ላይ ወዳለው የባዶ መጋዝን ስዕል ያመልክቷቸው።

ይምሩ:- አሁን ደግሞ የተወሰነ ጊዜ ወስደን፤ በየቡድናችን ላሉት የግል ቢዝነሶች ስያሜ እናውጣላቸው፡፡

ይምሩ:- እነዚህ ስያሜዎች አንደኛው ከሌላኛው የተለየ መሆን አለበት፤ ምክንያቱም በከተማ ውስጥ ያሉት
ሁሉም ሱቆች _____________________ ተብለው ቢጠሩ፤ ሰዎች ሁሉ የትኛው ጋ መሄድ
እንዳለባቸው ግራ ይጋባሉ፡፡ የቢዝነሶቻችሁ ስያሜዎች በሱቆቻችሁ ውስጥ ስለሚሸጡ ነገሮች የሚጠቁሙ
መሆን አለባቸው፡፡

ይምሩ:- ስም ካወጣን በኋላ፤ ሰዎች የት ሊያገኙን እንደሚችሉ የሚጠቁም ስሙን የሚገልጽ ዓርማ
(ምልክት) ያስፈልገናል፡፡ በመጽሐፍቶቻችሁ ገጽ _____ ላይ የሱቃችሁን ስያሜ ፃፉ፡፡ 3 ደቂቃዎችን ያህል
ተጠቀሙ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ3 ደቂቃዎች ያህል፡፡ በተቻለ መጠን የተለያዩ የስም ዝርዝሮችን እንዲጽፉና ከነዚያም
መካከል የሚወዱትን እንዲመርጡ ያበረታቷቸው፡፡ የቢዝነስ ስያሜዎቻቸው ግልጽ ያልሆኑ ወይም አሻሚ
ከሆኑ፤ በተሻለ መንገድ የሚገልጻቸውን ስያሜ እስኪያገኙ ድረስ ተከታታይ ጥያቄዎችን ይጠይቋቸው፡፡ እነዚህ
ስያሜዎች የሚሰሯቸውን የቢዝነስ ዓይነቶች የሚገልጹ መሆናቸውን ያረጋግጡ፡፡ ተሳታፊዎች የቢዝነስ
ስያሜዎቻቸውን በመጽሐፍቶቻቸው ላይ እንዲያሰፍሩ ይንገሯቸው፡፡

61
ይምሩ:- ከዚህ በተጨማሪ፤ ዓርማውን (ምልክቱን) የሚያስቀምጡበት ቦታ ከስሙ ያልተናነሰ ጉልህ ጠቀሜታ
አለው፡፡ ሰዎች በመንገድ ሲመላለሱ በቀላሉ ፊት ለፊት ሊያዩት በሚችሉበት አቅጣጫ ማለትም በህንጻ
ከሚሸፈን ይልቅ ከመንገድ ዳር እና ዳር ቢሆን ይብለጥ ምቹ ያደርገዋል። የዓርማችሁ በግልጽ በሚታይ ቦታ
ላይ መቀመጥ፤ ሽያጫችሁን በአስደናቂ ሁኔታ ሊያሻሽልላችሁ ይችላል!

ይምሩ:- የመጨረሻው የማርኬቲንግ ዓላባ ፕሮሞሽን ነው። ፕሮሞሽን፤ ስለምናቀርባቸው ምርቶች እና


እነዚህን አቅርቦቶች ልዩ ስለሚያደርጋቸው ነገር ለወደፊት ደንበኞቻችን የምንነግርበት መንገድ ማለት ነው፡፡
ይህም ደንበኞች የመግዛት ፍላጎት እንዲኖራቸው ያግዛል።

ይምሩ:- ምርቶቻችንን የምናስተዋውቅበት ብዙ የተለያዩ መንገዶች አሉ ፡፡

ይምሩ:- በፕሮሞሽን እንቅስቃሴያችን፤ ማስታወቂያ፣ የአንድ ለአንድ (የገጽ ለገጽ) እና ቅናሽን


በጥምረት አካትተን መጠቀም እንችላለን፡፡ እያንዳንዱን የፕሮሞሽን ዓይነት በትዕይንቱ ላይ ወይም
በሠልጣኞች መጽሐፍት ውስጥ ያመልክቷቸው።

ይምሩ:- ማስታወቂያ፤ እንደ ባነር፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ማህበራዊ ሚዲያ ወይም ህትመት የመሳሰሉ
የውጭ ሚዲያ ምንጭን በክፍያ በመጠቀም ስለ ቢዝነሳችን አዎንታዊ የሆኑ መስተጋብሮችን መፍጠር ነው፡፡
የህትመት ማስታወቂያ፤ ጋዜጦችን ወይም ቢዝነስ ካርዶችን ያካትታል፡፡ ቢዝነስ ካርድን እና/ወይም ጋዜጣን
ከፍ አድርገው ያሳዩዋቸው፡፡

ይምሩ:- የአንድ ለአንድ /የገጽ ለገጽ/ ማስተዋወቅ፤ ስለ ዕቃዎች /ምርቶች/ እና አገልግሎቶቻችንን


የፊት ለፊት ማስተዋወቅ ማለት ነው። ይህ ዓይነት የማስተዋወቅ ስልት ብዙውን ጊዜ የሚከናወነው፤ አንድ
ደንበኛ ወደ ቢዝነስ ቦታችን መጥተው ሽያጭ ስንፈጽም ነው።

ይምሩ:- ቅናሽ ማለት፤ ደንበኛን ለመጥቀም እና ሽያጭን ለመፋጠን በተወሰኑ ዕቃዎች ላይ ወይም ብዙ
የግዥ ትዕዛዝ ሲኖር ዋጋን ዝቅ አድርጎ መሸጥ ማለት ነው፡፡ ቅናሾች፤ በመቶኛ ተሰልተው በኩፖን መልክ
ሊዘጋጁ ይችላሉ። ቋሚ ደንበኞች፤ የተወሰኑ እቃዎችን ከገዟችሁ ወይም ለረጅም ጊዜ የአገልግሎቶቻችሁ
ተጠቃሚ ከሆኑ ቅናሽ ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፡፡

ይምሩ:- ቢዝነሶቻችንን ለማሳደግ በጣም ውጤታማ ከሚያደርጉ ዓይነተኛ ስልቶች አንዱ የአፍ ለአፍ
ማስታወቂያ ነው ፡፡

ይምሩ:- ትዕይንቱ ላይ ወዳለው የአፍ ለአፍ ማስታወቂያ ያመላክቷቸው፡፡

ይምሩ:- አዎንታዊ የአፍ ለአፍ ማስታወቂያ ማለት፤ አንድ ደንበኛ ከቢዝነሳችን ጋር ጥብቅ ቁርኝት
ሲፈጥርና ከዚያም ጓደኞቹ፣ ጎረቤቶቹ እና ቤተሰቦቹ እኛ ጋ መጥተው ቢዝነስ እንዲሠሩ ሲናገር ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- መጽሐፈ ምሳሌ 22÷1 “መልካም ስም ከብዙ ባለጠግነት ይሻላል፤ መልካምም ሞገስ ከብርና ከወርቅ
ይበልጣል” ይላል፡፡

ይምሩ:- መልካም ስም ከብዙ ባለጠግነት የተሸለው ለምንድን ነው? ይህ ለምን ትክክል ሊሆን እንደሚችል
በየቡድኖቻችሁ በግልጽ ተወያዩበት፡፡

ቡድን አመቻች፡- ለ1 ደቂቃ ያህል፡፡ ይህንን ውይይት ይምሩ፡፡

62
ይምሩ:- መልካም ስም ከወርቅ ለምን እንደሚሻል ከመካከላችሁ አንድ ሰው ሊያጋራን ይችላል?

ይምሩ:- ላጋራው ተሳታፊ ጣፋጭ ይሸልሙት፡፡

ይምሩ:- በአዎንታዊ የአፍ ለአፍ ማስታወቂያ፤ ለቢዝነሳችን መልካም ስምን መገንባት እጅግ ስኬታማው
የፕሮሞሽን ስልት ነው፡፡ ምክንያቱም ሰዎች በምልክት ላይ ከሚያይዋቸው ወይም ከማያውቁት ሰው
ከሚሰሙት ይልቅ ጓደኞቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው የሚነግሯቸውን አምነው የመቀበል ዝንባሌያቸው ከፍተኛ
ነው፡፡

ይምሩ:- በማህበረሰባችሁ ውስጥ እንዲህ ዓይነት መልካም ስምን ዝና ያተረፈ ቢዝነስ በምሳሌነት ሊጠቅስልኝ
የሚችል ሰው አለ?

ይምሩ:- ምላሾችን ይቀበሉ፡፡ ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆትና ከምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ከዚህ በተቃራኒም እውነትነት አለው፡፡ አንድ ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል በቢዝነሱ ላይ መጥፎ
አመለካከት ካለው - ምናልባትም የተታለሉ ሆኖ ከተሰማቸው፤ ወይም ጥራት የሌለው ዕቃ ከሸመቱ - ሌሎች
እዚያ እንዳይገዙ ይነግራሉ፡፡

ይምሩ:- አሉታዊ የአፍ ለአፍ ማስታወቂያ፤ ቢዝነሳችንን የሚጎዳ አፍራሽ ፕሮሞሽን ስለሆነ አያስፈልገንም፡፡

ይምሩ:- ሱቅ ልንከፍት በዝግጅት ላይ ሆነን ነገር ግን ልንከፍት መሆናችንን ማንም ካላወቀ፤ ለሰዎች
ልናሳውቅ የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች ምን ምን ናቸው? (ምልክት መስቀል፣ ለጓደኞቻችን መንገር፣
ቢዝነስ ካርዶችን ማደል፣ በሬዲዮና በመሳሰሉት ማስተዋወቅ ወዘተ)፡፡

ይምሩ:- ለተሰጡ መልሶች ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- “ማስታወቂያ” ወደሚለው ትዕይንት ያመልክቷቸው፡፡

ይምሩ:- ቢዝነሶቻችንን ውጤታማ በሆነ መንገድ ስማስተዋወቅ ስናስብ ከዚህ የሚከተሉትን ጥያቄዎች
ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፤ “በማስታወቂያዬ የትኛውን የህብረተሰብ ክፍል ታርጌት አድርጌ ለመድረስ
እየሞከርኩ ነው?” እንዲሁም “ምን ያህል ወጪስ ይኖረዋል?”

ይምሩ:- ቢዝነስ ካርዶችን የምንጠቀም ከሆነ፤ ለማን ነው የምንሰጠው፣ እንዴትስ ነው የሚያገኙት፣ ወጪው
ምን ያህል ነው፣ እንዲሁም ደንበኞቻችን እንዲሆኑልን የምንፈልጋቸውን ሰዎች በትክክል ለመሳብ ይረዳናል፣
የሚሉትን መወሰን አለብን፡፡ .

ይምሩ:- ከዚያ በኋላ፤ ለፕሮሞሽኑ የምናወጣው ወጪ ተገቢ መሆኑን መወሰን እንችላለን።

ይምሩ:- እነዚህን የማርኬቲንግ /የግብይት/ ገጽታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ አዲስ ቢዝነስ ወይም
አስቀድማችሁ የከፈታችሁትን ንግድ አስቡ ፡፡

ይምሩ:- ጥቂት ጊዜ ውሰዱና፤ አዲስ ልትጀምሩ ላሰባችሁት ወይም ቀድሞውኑ ለጀመራችሁት ቢዝነስ ሶስት
ወሳኝ ግቦችን በመጽሐፍቶቻችሁ ገጽ ____ ላይ ባለው ባዶ ቦታ በጽሑፍ ወይም በስዕል ግለጹ፡፡ ጥሩ እና
ትክክለኛ መርሃግብር፤ በግልጽ ተለይቶ የሚታወቅ(S)፣የሚለካ(M)፣ሊተገበር የሚችል(A)፣ ተጨባጭ(R)
እናበጊዜ ሠሌዳ የተገደበ(T) ወይም (SMART) መሆኑን አስታውሱ።

63
ይምሩ:- ታርጌት ላደረጋችኋቸው ሰዎች ቢዝነሳችሁን እንዴት እንደምታስተዋውቁ በሚገባ አስቡ፡፡
ቢዝነሳችሁን መክፈት ያሰባችሁት የት ነው? ደንበኞችን ተቀብላችሁ የምታስተናግዱት እንዴት ነው?

ልምምድ

ይምሩ:- በየቡድኖቻችሁ ጥቂት ጊዜ ውሰዱና በገጽ ____ ላይ ያለውን መልመጃ ስሩ፡፡

ይምሩ:- ለዚህ የሚሆን ጊዜ ይፍቀዱላቸው፡፡ ሥራ ፈጣሪዎች ሃሳቦቻቸውን በስዕል በሚገልጹበት ጊዜ እየዞሩ


በማየት ያበረታቷቸው፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ10 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ሥራ ፈጣሪዎቹ ይህንን የማርኬቲንግ መርሃግብር /ዕቅድ/
ጽንሰ-ሀሳብ ተገንዝበው ስራ ላይ የሚያውሏቸው ሦስት ውጤታማ የሚያደርጉ ሦስት ዓላማዎችን
እንዲያሰፍሩ በማድርግ ያግዟቸው፡፡ ተጨማሪ ጊዜ ካላቸው፤ ከዓላማዎቻቸው አንዱን መርጠው
ለቡድኖቻቸው እንዲያጋሩ እና በዚያ ዙሪያ እንዲወያዩ ያድርጉ፡፡

ይምሩ:- ተጨማሪ ጊዜ ካለ፤ በነዚህ አማራጮች ዙሪያ ውይይት ያድርጉ፡፡ ለማርኬቲንግ ዕቅድ የሚረዱ
ተጨማሪ ሀሳቦችን ከፈለጋችሁ በመጽሐፍቶቻችሁ ገጽ ___ ላይ "በቀላሉ ሊተገበሩ የሚችሉ የማርኬቲንግ
እሳቤዎች" የሚለውን ዝርዝር ማየት ትችላላችሁ፡፡ እነዚህ ዝርዝሮች የተበረከቱት የታሊ ደንበኛ እና
የአነስተኛ ቢዝነስ ባለቤት ከሆኑት ሄዘር ብሪግስ ነው፡፡ ሄዘር የምትጋግራቸውን ኬኮች በምትኖርበት ከተማ
ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ በቆሙ የጭነት መኪኖች ላይ የምትሸጥ ሴት ነች፡፡ ጠቅላላ ዝርዝሩን
በተመለከተ በመጽሐፍቶቻችሁ ገጽ ___ ላይ ተመልከቱ፡፡ ይህንን ክፍል ለመሸፈን ጊዜ ከሌለዎት፤ እንደ
ተጨማሪ ምንጭ ከጠቆሟቸው በኋላ ቡድን አመቻቾች ደግሞ ለየቡድኑ ወይም ለግለሰቦች ገለጻ በማድረግ
እንዲያግዙ ሊያልፉ ይችላሉ፡፡

64
በቀላሉ ሊተገበሩ የሚችሉ 15 የማርኬቲንግ እሳቤዎች

1. ደንበኞችን መሸለም:- ለተወሰነ ጊዜ ደጋግመው ከገዙን ወይም አገልግሎታችንን ከተጠቀሙ በኃላ ዕቃ


በነፃ በመስጠት ወይም ነፃ አገልግሎት በመስጠት የታማኝነት ደንበኞች ፕሮግራም በመባልም
ይታወቃል”
2. ከሌሎች የታሊ ደንበኞች ጋር በትብብር መስራት:- ይህም ቢዝነሳቸውን ለማስተዋወቅና እርስ
በእርስ ለመደጋገፍ ይረዳል፡፡
3. የደንበኞችን መረጃ መሰብሰብ:- ማስተዋወቅ ሲፈልጉ፤አዲስ ዕቃ ሲመጣ ለመጠቆም ወይም የተለየ
ክስተት ሲኖር በቀላሉ ለማግኘት እንዲቻል እንደ ስልክ ቁጥር ያለ መረጃ መጠቀም ይጠቅማል፡፡
4. ስልክን በመጠቀም በማህበራዊ ድረ-ገፅ ቢዝነስን ማስተዋወቅ:- የፅሁፍ መልክት߹ፌስቡክ߹ዋትስ
አፕ߹ኢንስታግራም የመሳሰሉ አፕልኬሽኖች ነፃ የማስታወቂያ መንገዶች ናቸው፡፡
5. የፈጠራ ሽርክና ለመፍጠር ከሌሎች ንግዶች ጋር አብረው ይስሩ፡፡ይስሩ፡- ለምሳሌ ዳቦ
ጋጋሪው አንድ ልዩ ሽያጭ በሚኖርበት ጊዜ ለደንበኞች ነፃ ናሙናዎችን የሚያቀርብ
ጠረጴዛ እንዲያዘጋጁ ሊጠይቅ ይችላል፡፡
6. የዕጣ ሽልማት ወይም የዋጋ ቅናሽ ማድረግ ፡- ሰዎች በተፈጥሯቸው በለስ ቀንቷቸው
የሆነ ነገር ማሸነፍ የስደስታቸዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ ለመሸመት ብሎም ለሌሎች ሰዎች
ለመንገርና አድራሻ ሰጥተው ለመላክ ይነሳሳሉ፡፡
7. ስለ ልዩ ልዩ የማስታወቂያ አማራጮች ግንዛቤ ማዳበር፡- ለአካባቢው ሰዎች አና
ለደንበኞች ምቹ የሆነውን በመምረጥ ማለትም አዘውትረው ጊዜ የሚያሳልፉባቸውን
ቦታዎችና መሰል ነገሮችን በማጥናት ማስተዋወቅ፡፡
8. በብዛት ለሚሸምቱ የዋጋ ቅናሽ ማድረግ፡- ትርፋማነትን ግን ርግጠኛ መሆን፡፡
9. ከቢዚነስዎ ጋር የማይገናኝ ተጨማሪ አገልግሎቶችን ለደንበኞች ማበርከት፡- እንደ
በዓላት ባሉ ጊዜያት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ማስተላለፍ ወይም በአካባቢው ልዩ
ዝግጅቶች ሲኖሩ ማሳወቅ።እኛ ሰዎች በተፈጥሯችን ትኩረት የሚሰጡንን ሰዎች
እንወዳለን፡፡እንደነዚህ ዓይነት ትንንሽ የሚመስሉ ተጨማሪ አገልግሎቶች፤ ቢዚነሱን
ከሌሎች ላቅ ብሎ እንዲታይ ያደርጉታል።
10. የመሸጫ ስፍራው፤ሰዎች በቀላሉ የሚያገኙት ይሁን! ከርቀት በቀላሉ የሚለዩ የመንገድ
ዳር ምልክቶች መጠቀም፤ በሩ ክፍት መሆኑን በግልጽ ማሳየት፤ አድራሻ፡የስራ ሠዓትና
ስልክ ቁጥርን ያካተተ ድረ-ገጽ መክፈት፡፡
11. ትሁት መሆን:- የደንበኛን ስም ማስታወስ፡ የግል ቀረቤታ ማዳበር፡ እንክብካቤ ማድረግ፡፡
ይህን መሰል ተግባር ከታሰበው በላይ ወደ በለጠ ቢዚነስ ሊሸጋገር ይችላል፡፡ ሰዎች
ከምንም ነገር በላይ ሰዎችን ይወዳሉ።

65
12. ተጨማሪ አቅርቦቶችን መፍጠር፡- ትንንሽ ዕቃዎችን፤ በገንዘብ መክፈያ ጠረጴዛዎች
ላይ ወይም እንደ ጣፋጭና ፍራፍሬ ያሉትን፤ በምግብ ቤቶች ውስጥ በተጨማሪነት
መሸጥ ቀስ በቀስ ከፍተኛ ለውጥ ይፈጥራል፡፡ በአንድ ደረቅ ኬክ ላይ ትንሽ አይስክሬም
ላዩ ላይ ቀብቶ ምሸጥ ማመን የሚያዳግት ትርፍ ሊያስገኝ ይችላል፡፡ እርስዎስ
ሽያጭዎን ማሳደግ የሚያስችሉ ትንንሽ ተጨማሪአቅርቦቶችን ለደንበኞችዎ
ማመቻቸት ይችላሉ?
13. አንድ ሞያተኛ ቅጠር፡- ስኬታማ የሚያደርጉ ስልቶችን ለሚያቀናብር ሞያተኛ ገንዘብ
ማውጣት ውሎ አድሮ ትልቅ ትርፍ ያመጣል፡፡ የክህሎት ክፍተትዎን (በሶሻል ሚዲያ
አጠቃቀም፡ በሂሳብ አያያዝ፡ በግራፊክ ዲዛይን፡ ወ.ዘ.ተ.) በመፈተሽ ለተወሰኑ ሰዓታት
ለሚያማክርዎ ፐሮፌሽናል ሞያተኛ ስለመክፈል በሚገባ ሊያስቡበት ይገባል፡፡
14. ተጨማሪ ዕቃ መመረቅ፡- አልሸጥ ያል ወይም በቅርቡ ጊዜው የሚያልፍባቸውን
ምርቶች ወደፊት ደንበኞች ይሆናሉ ተብለው ለሚታሰቡ ሰዎች እንደ ናሙና ወስደው
አንዲሞክሩት ወይም ለታማኝ ደንበኞች እንደ ምስጋና ስጦታ ማበርከት፡፡
15. ግብረ-መልስ (አስተያየት) መጠየቅ፡- ቢዚነስን ለማሻሻል ይረዳል። ለዚህም የሚረዳ
አጭር የዳሰሳ ጥናት መጠይቆችን ያዘጋጁ፡፡አዲስ ምርት ወይም አገልግሎት የማቅረብ
ሃሳብ ካለዎት ደንበኞችዎ ይገዙ ወይም አይገዙ እንደሆነ አስቀድመው
ይጠይቁ፡፡ደንበኞችዎ አገልግሎትዎን በማሻሻሉ እንቅስቃሴ ጊዜያቸውን በመሰዋት
የበኩላቸውን እገዛ ስላደረጉ ለማመስገን ልዩ ዕጣ ፕሮግራም ያዘጋጁ፡፡

ይምሩ:- በዚህ ክፍል የተማራችሁትን አንድ ቁም ነገር ልትነግሩኝ የምትችሉ እስቲ ሁለት ሰዎች
ትኖራላችሁ?

Lead: Call on two people and have them share one thing. Validate and reiterate their
answers.

ይምሩ:- ዋው!ሁላችሁም አስደናቂ መረዳት ነው ያላችሁ፡፡ ስንመለስ፤ ስለደንበኞች አገልግሎት እንነጋገራለን!

66
// ክፍል 8 //
የመስተንግዶ አገልግሎት
የሚወስደው ጊዜ፡- 1 ሠዓት
ግቦች:-
> ተሳታፊዎች፤ የመስተንግዶ አገልግሎትን ጥቅሞች ይገነዘባሉ፡፡
> ተሳታፊዎች፤ በነጻነት እና በጥሩ ተግባቦት እርስ በእርስ ውይይት በማካሄድ ልምምድ ያደርጋሉ፡፡

አቅርቦቶች፡-
> እስክሪብቶዎች > የሠሌዳ ማርከሮች
> የሒሳብ መደመሪያ ካልኩሌተሮች > ጣፋጮች
> የሠልጣኞች መጻሕፍት > ስካርፍ
> ነጭ ሠሌዳ

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


> የመስተንግዶ አገልግሎት

ትዕይንቶች (በግድግዳ ወይም በቦርድ ላይ የተለጠፉ ወይም በሠልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱ)፡-
> የመስተንግዶ አገልግሎት ጥቅሞች (1-4) > የደንበኛ ምላሽ
> የደንበኛ እርካታ > የግል እርካታ
> የደንበኛ ታማኝነት

ዝግጅት:-
> ስልጠናው ከመጀመሩ አስቀድሞ፤ የመጀመሪያውን ድራማ የሚለማመዱ ሁለት ፈቃደኛ ሰልጣኞችን
ይምረጡ። የ“ባለ መደብሩ” ድራማ በአካባቢው በሚኖሩ ፈቃደኛ ሠልጣኞች ቢሰራ የበለጠ
ይመረጣል፡፡ ተዋንያኖቹ ድራማውን በጥሩ ሁኔታ ለመተወን እንዲችሉ፤ የመልእክቱን አጠቃላይ
ጭብጥ መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ጀርባቸውን ሰጥተው ሳይሆን ታዳሚውን ፊት ለፊት እያዩ ጮክ
ብለው እንዲናገሩ ያለማምዷቸው።
> የ“ሽያጭ ጥበብ” ድራማን በበቂ ሁኔታ ተለማምደው መተወን በሚችሉ አስተባባሪዎች ቢሰራ
ይመረጣል፡፡

67
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ:-
> ፊልጵስዩስ 2÷3-4
> ማቴዎስ 5÷38-39
> ማቴዎስ 7:12

ይምሩ:- በድጋሚ እንኳን በደህና መጣችሁ! በክፍል ሰባቱ ማርኬቲንግ /ግብይት/ 2 ላይ ሁላችሁም አስደናቂ
መረዳት ነበራችሁ፡፡ በተለይም ____________ (ስሙን ይጥቀሱ) በ ________ ዙሪያ (ያስተዋሉትን
ወይም ሊያበረታቱ የፈለጉበትን ጉዳይ ይግለጹ) የገለጸበትን መንገድ ወድጄዋለሁ!

ይምሩ:- አሁን ደግሞ ከምወዳቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሆነውን “የመስተንግዶ አገልግሎት”ን
እንቃኛለን፡፡

ይምሩ:- በፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2 ላይ ከራሳችን ይልቅ የሌሎችን ፍላጎት እንድናስቀድም ያስተምረናል፡፡


ፊልጵስዩስ 2÷3-4 እንዲህ ይላል፡- “ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ
አታድርጉ÷ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትህትና ይቁጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ
የሚጠቅመውን አይመልከት÷ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።”

ይምሩ:- ጥሩ የመስተንግዶ አገልግሎት ማለት፤ ገንዘብ ከማግኘት የበለጠ ለሰዎች ከፍ ያለ ዋጋ መስጠት


መቻል ነው፡፡

ይምሩ:- የታረደ ዶሮ የሚሸጠውን ሰው ድራማ እስቲ ወደ ኋላ መለስ ብላችሁ ለመቃኘት ሞክሩ፡፡ ያ/ያች
ሰው/ሴት ገንዘብ ከማግኘት የበለጠ ለሰዎች ክብር ይ/ትሰጥ ነበር? (በጭራሽ፡፡)

ይምሩ:- የመስተንግዶ አገልግሎት ማለት፤ ሁል ጊዜም ለደንበኞቻችን እንክብካቤ ማድረግ ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- አንድን ለሽያጭ የሚሆን ምርት ስንመርጥ ወይም ለማምረት ዲዛይን ስናደርግ፤ ቅድሚያ
ትኩረታችን የደንበኞቻችን ፍላጎት እና የሚያስፈልጋቸው ነገር ላይ ሊሆን ይገባል፡፡

ይምሩ:- የደንበኞቻችን ባህሪያት አንዳንድ ጊዜ ጥሩ ላይሆን ይችላል። ምንም ዓይነት ያልተገባ ባህርያት
ቢያሳዩን እንኳ፤ በትህትና እና በአክብሮት አገልግሎት ለመስጠት መወሰን አለብን፡፡ በምንሠራው ስራ
መኩራታችን እንደተጠበቀ ሆኖ፤ መልካምነት ግን አይለየንም፡፡

ይምሩ:- ሰዎች ምንም እንኳ ክፉ ቢሆኑ፤ እኛ ግን መልካም ማድረግ እንዳለብን ኢየሱስ ክርስቶስ
አስተምሯል። በማቴዎስ 5 ÷ 38-39 ላይ እንዲህ ይላል፡- “ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ እንደተባለ
ሰምታችኋል፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ÷ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ
ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት።”

68
ይምሩ:- ይህ በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል! ይሁን እንጅ፤ ይህንን መርህ ኢየሱስ ክርስቶስ በሕይወቱ ብዙ ጊዜ
በተግባር አሳይቷል፡፡ ይህ የእኛ ተፈጥሯዊ ባህርይ ባይሆንም፤ እንደ አንድ ክርስቲያን እና የቢዝነስ ባለቤቶች
እንድንፈጽም ነው ኢየሱስ ያዘዘን፡፡

ይምሩ:- በቢዝነስ ውስጥ፤ በትህትና የማስተናገድን ጠቀሜታ እስቲ በየቡድኖቻችሁ ተወያዩበት፡፡ በአንድ
ወቅት፤ የሆነ ሰው ተገቢ ያልሆነ ባህሪ አሳይቷችሁ እናንተ ግን በምላሹ በትህትና እና በአክብሮት
ያስተናገዳችሁበት አጋጣሚ ካለ አካፍሉ፡፡

ይምሩ:- ጥቂት ደቂቃዎችን ይፍቀዱላቸው፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ2 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ይህ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ጽንሰ-ሃሳቦች አንዱ ነው፡፡ ተሳታፊዎች
በስፋት እንዲወያዩበት ለማድረግ ጥያቄውን ሳያቅማሙ ይድገሙላቸው፡፡ ጊዜ ካለዎት፤ “ይህንን ተግባራዊ
ለማድረግ እንዴት እናስታውሳለን? ሁልጊዜስ ቀላል ይሆንልናል?” በሚሉት ጥያቄዎች ዙሪያ ተወያዩባቸው፡፡

ይምሩ:- ፈቃደኛ ሆነው እስካሁን ያላካፈሉ ወይም ካካፈሉን ቆየት ያሉ ሁለት ሰዎች ተነስተው መልስ
እንዲሰጡኝ እፈልጋለሁ፡፡ በቢዝነሶቻችሁ ውስጥ፤ በትህትና ማስተናገድ ጠቀሜታው የጎላ የሆነው ለምንድን
ነው? (ምላሾቻቸውን ያድምጡ፤ ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆትና ከምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡)

ይምሩ:- ደንበኛን ሁል ጊዜ ምቾት እንዲሰማው ማድረግ፤ የግል ግንኙነትን ማዳበር ብቻ ሳይሆን በቢዝነሳችሁ
እና በደንበኛው ፍላጎት መካከል አመኔታን የሚፈጥር ትስስር እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ደግመው ደጋግመው
መመለስን እንዲመርጡ ያድረጋቸዋል። ደስተኛ ደንበኞች ስለ መልካም ገጠመኞቻቸው ለሌሎች ይናገራሉ!

ይምሩ:- ደንበኛ፤ ስለ ቢዝነሳችሁ መልካም ነገሮችን ለሌሎች ሲናገር ምን ተብሎ እንደሚጠራ የሚያስታውስ
አለ? ማን ነው ሊነግረኝ የሚችል? (አዎንታዊ የአፍ ለአፍ ማስታወቂያ)

ይምሩ:- ጥሩ የመስተንግዶ፤ ከስራ ፈጣረ አገልግሎት ካገኛችሁባቸው ጊዜያት ውስጥ አንዱን ገጠመኝ
አስታውሶ ሊነግረን የሚችል ይኖራል? በዚህ መሠል አገልግሎት ራስዎ ተስተናግደው ወይም ሌላ ሰው
ሲስተናገድ ያዩትን ሊሆን ይችላል።

ይምሩ:- ሁለት ሠልጣኞች እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ ጣፋጭም ይሸልሟቸው፡፡

ይምሩ:- ሥራ ፈጣሪ የመሆን አንዱ እና ዋንኛው መገለጫ፡ ጥሩ የመስተንግዶ አገልግሎት ሰጪነት ነው፡፡
ምክንያቱም ደንበኞች የሚፈልጉትን በሚገባ የማወቅ፤ ከዚህም በተጨማሪ የመከበር እና ሃሳባቸውን
እንደተረዳንላቸው እንዲሰማቸው የሚያደርግ ግንኙነትን የመገንባት ችሎታ አለን ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- እውነተኛ የመተንግዶ አገልግሎት ለቢዝነስ ስኬት በጣም አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ሥራ
ፈጣሪዎች ጥራት በሌለው ዕቃ፣ ተገቢ ባልሆነ ዋጋ፣ በመዋሸት፣ በማጭበርበር፣ በመስረቅ ወይም በንቀት
ሰዎችን ያላግባብ መጠቀሚያ እንዳያደርጓቸው ይከለክላቸዋል፡፡

ይምሩ:- ጥሩ የመተንግዶ አገልግሎት ምን ያህል ያስከፍለናል? (ምንም፡፡)

ይምሩ:- ከፍተኛ የመተንግዶ አገልግሎት የማንሰጥበት ጊዜ ሊኖር ይገባል ብሎ የሚያስብ ሰው አለ?

69
ይምሩ:- ተሳታፊዎች ጊዜ ወስደው እንዲያስቡ እና መልስ እንዲሰጡ ያድርጉ፡፡ (ሁልጊዜም ከፍተኛ
የመተንግዶ አገልግሎት ሊሰጡ እንደሚገባቸው ይንገሯቸው)

ይምሩ:- አይገባም! አንዳንድ ደንበኞቻችን ምንም እንኳን ቁጡና ትህትና የጎደላቸው ቢሆኑ፤ እናንተ ግን
ፊታችሁ በፈገግታ ተሞልቶ እና ተረጋግታችሁ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት የተቻላችሁን ሁሉ ጥረት
ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

ይምሩ:- የሚፈልጉትን አገልግሎት ማቅረብ ካልቻላችሁ፤ “ይቅርታ፤ ጥያቄዎን ማሟላት ባለመቻሌ


አዝናለሁ፡፡ ምናልባት ሌላ ሱቅ እስቲ ይሞክሩ።” በማለት በትህትና መልስ ስጡ፡፡

ይምሩ:- ጥሩ የመተንግዶ አገልግሎት በመስጠታችን ደንበኞቻችን ሆኑ እኛ ምን ምን ጥቅሞችን ልናገኝ


እንችላለን?

ይምሩ:- መልሶችን ይቀበሉ፡፡ ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆትና ከምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡ ለተጠየቀው
ጥያቄ ያልተመለሱትን መልሶች ያንብቡላቸው። ወደ አራቱ ትዕይንቶች በማመላከት መስመር በመስመር
ያንብቡላቸው፡፡

1) የደንበኛ እርካታ - የደንበኛው ፍላጎት ሲሟላ


2) የደንበኛ ታማኝነት - ደንበኞች በግብይታቸው ከተደሰቱ፣ ተመልሰው መጥተው የመግዛት ዕድላቸው
ከፍተኛ ነው
3) የደንበኛው ምላሽ - ደንበኛው በእናንተ ላይ እምነት ከመጣሉ የተነሳ ሊነግርዎት ፈቃደኛ ስለሚሆን፤
ነገሮች ሲበላሹም ሆነ ሲሰምሩ ማወቅ ትችላለችሁ
4) የግል እርካታ - ደንበኞች በምርቱ ወይም በአገልግሎቱ ሲደሰቱ፤ በተግባሮቻችሁ ጥሩ ስሜት
ሊሰማችሁ ይችላል

ይምሩ:- ለጥሩ የመስተንግዶ አገልግሎት ጥሩ ልማዶች በጥቂቱ ከዚህ የሚከተሉትን ይመስላሉ፡-

1) ሁሌም በሠላምታ ጀምራችሁ በስንብት አጠናቅቁ፤ ደንበኛችሁን እንደ ግል ጓደኛ ቁጠሩት።


2) ሠራተኞቻችሁ እናንተንም ሆነ ቢዝነሶቻችሁን ሚወክሉ እንደመሆናቸው መጠን፤ ቅጥር
ስትፈጽሙ ጥበብና ማስተዋል አይለያችሁ።
3) ከደንበኞች ጋር ሊኖር ስለሚገባው ጥሩ መስተጋብር ሠራተኞቻችሁን አሠልጥኗቸው።
4) ጊዜ ወስዳችሁ ከደንበኞቻችሁ ጋር በሚገባ በነጋገር ተግባቦትን ፍጠሩ።
5) በተቻለ መጠን የደንበኞቻችሁን ትዕዛዞች አሰቀድማችሁ በማሟላት ቃላችሁን ጠብቁ። ያኔ
ደንበኞቻችሁ በመደነቅና በደስታ ይሞላሉ።
6) ለደንበኞቻችሁ ያላችሁን ትልቅ ከበሬታ የሚያሳዩ ተጨማሪ ነገሮችን አድርጉላቸው፡፡ ለምሳሌ፤
የሻይ፣ ቡና፣ ወይም የታሸገ ውሃ መስተንግዶ ያለዚያም የታዘዘን ዕቃ ቤት ድረስ በማድረስ ሊሆን
ይችላል፡፡

ይምሩ:- ሌሎች ሰዎች እንዲያደርጉልን በምንፈልግበት መጠን እኛም እንዲሁ እንድናደርግ ማቴዎስ 7÷12
ያስተምረናል፡፡

“እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤” ይላል፡፡

ይምሩ:- ይህን ጠቃሚ የቢዝነስ መርህ መከተል፤ እግዚአብሔር እንዲከብር ከማድረጉም በላይ በከተማው
አንቱ የተባሉ የመስተንግዶ አገልግሎት ባለቤቶች ያደርገናል!

70
ድራማ

ይምሩ:- የመስተንግዶ አገልግሎት ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ድራማ አሁን እንመለከታለን፡፡

ይምሩ:- ሁለት አመቻቾች ወይም አስተርጓሚዎች ድራማውን እንዲሰሩ ያድርጉ፡፡

አንደኛው እንደ ሻጭ (ባለ አትክልት መደብር)፤ ሌላው እንደ ገዥ (ደንበኛ)መስለው እንዲተውኑ ያድርጉ፡፡

ባለ መደብር ሞባይሉን እየነካካ መደብሩ አጠገብ ቆሟል፡፡

ደንበኛ ዙሪያ ገባውን እየቃኜ ወደ መደብሩ ይጠጋል፤ አነዱን እቃ አንስቶ ዋጋውን ያያል፤ ጥራቱን ለማረጋገጥ
ይፈትሻል። ልብ ብሎት እንደሆን ለማረጋገጥ ባለ መደብሩ ደንበኛውን አንጋጥጦ ማየቱን ቀጥሏል።

ባለ መደብር ደንበኛውን ሙሉ በሙሉ ችላ በማለት አሁንም ሞባይሉ ላይ ተመስጦ መመልከቱን እንደቀጠለ


ነው፡፡

ደንበኛ፡- “ይሄ ዋጋው ስንት ነው?” አንድ ምርት ያነሳል፡፡

ባለ መደብር፡- (በተሰላቸ ድምጽ) “_______ ብር፡፡”

ደንበኛ፡- “ሌላ ተጨማሪ ይኖራል?”

ባለ መደብር፡- (በስጨት ብሎ) “ሌላ ተጨማሪ ይታይሃል?!”

ደንበኛ፡- (ወደ ኋላ እያፈገፈገ) “ይቅርታ፣ መጠየቅ ስላለብኝ ነው፡፡”

ባለ መደብር፡- ተመልሶ ሞባይል መነካካቱን ይቀጥላል፡፡

ደንበኛ፡- (ሌላ ምርት እያሳየ) “ይህን መግዛት እችላለሁ?”

ባለ መደብር፡- “ከፈለክ።”

ደንበኛ፡- “ግማሽ ጎኑ የተበላሸ ነው። ዋጋውን ትቀንስልኛለህ?”

ባለ መደብር፡- (በቁጣ) “ያው ነው አይቀንስም! ከፈለግህ ውሰድ ካልፈለግህ ተወው እንጅ ምርቴን
አታጣጥልም!”

ደንበኛ፡- ምርቱን አስቀምጦለት በቁጣ ተሞልቶ በፍጥነት ትቶት ይሄዳል፡፡

ባለ መደብር፡- አሁንም እንደገና ሞባይሉን ያነሳል፡፡

ይምሩ:- ተዋናዮችን በጭብጨባ ያመስግኑ።

71
ይምሩ:- በድራማው ውስጥ የባለ መደብሩ መስተንግዶ ምን ይመስል ነበር? (ጥሩ አልነበረም፤ ወዘተ)

ይምሩ:- ጥሩ ያልነበረው ለምንድን ነው?

ይምሩ:- ምላሽ እንዲሰጡ ያድርጉ፡፡

ይምሩ:- ደንበኛው ምን የተሰማው ይመስላችኋል

ይምሩ:- ምላሽ እንዲሰጡ ያድርጉ፡፡

ይምሩ:- ደንበኛው ተምልሶ ሊመጣ ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ?

ይምሩ:- ምላሽ እንዲሰጡ ያድርጉ፡፡

ይምሩ:- ደንበኛው ስለዚያ መደብር ለሌሎች ሰዎች ምን ሊናገር ይችላል?

ይምሩ:- ምላሽ እንዲሰጡ ያድርጉ፡፡

ይምሩ:- ጥሩ የመስተንግዶ አገልግሎት ሽያጫችንን ከፍ ሊያደርገው ይችላል።

ይምሩ:- ለደንበኞቻችን ግድ እንደሚለን እና እንደምንከባከባቸው እንዲሰማቸው የማድረጊያ ሌሎች ጠቃሚ


የሽያጭ ዘዴዎችም አሉ፡፡ ይህ ዓይነቱ እንክብካቤ ደግሞ እንዲሸምቱ(እንዲገዙ) ያደርጋቸዋል! ከዚህ ቀጥሎ
እንመለከተዋለን!

ድራማ

ይምሩ:- ሁለት አመቻቾች ወደ መድረክ መጥተው የ“ሽያጭ ጥበብ” ድራማን በምልክት እንዲተውኑ ያድርጉ፡፡
በየሐረጎች መካከል ረዘም ያለ ጊዜ አይውሰዱ። የምልክት ተዋንወያኑን እርስዎ ሲያዋሯቸው፤ በእግረ መንገድ
ራሳቸውን ለማዘጋጀት ጊዜ ያገኛሉ።

ትወና አመቻቾች፡- መሪ አመቻቹ እያስተማሩ እያለ ድራማውን ቀስ ብላችሁ በቋንቋ ምልክት ቀጥሉ፡፡
ለድራማው የሚረዱ የአንገት ልብስ /ስካርፍ/ እና Bandanna ስካርፍን ተጠቀሙ።

ይምሩ:- በመጀመሪያ ደረጃ፤ ደንበኞች ወደ መደብራችን ሲገቡ፤ ከሽያጩ በላይ ስለ እነሱ ግድ እንደሚለን
እንዲሰማቸው ያፈልጋል፡፡

ይምሩ:- ስለራሳቸው ጥያቄ በመጠየቅ ወይም አንድ ጥሩ ነገር በመናገር፤ ውይይት መጀመር እንችላለን፡፡

ይምሩ:- ከዚያም፤ ምን ዓይነት ዕቃ እንደሚፈልጉ ማስተዋል እንችላለን፡፡ ቆንጆ ስካርፍ እየፈለጉ ከሆነ፤
ያሉንን ሁሉ በየዓይነቱ እናሳያቸዋለን፡፡

ይምሩ:- ስካርፎቻችንን ቆንጆ የሚያደርጋቸው ምን እንደሆነ ማስረዳት አለብን። የእኛን ስካርፎች ከሌሎች
የተሻለ ተመራጭ የሚያደርጋቸው ምን እንደሆነ በማብራራት የአንድ ለአንድ /የገጽ ለገጽ/ ማስተዋወቅ
እናደርጋለን። ጥራቱ፣ ቀለሙ፣ዲዛይኑ ወይም ዋጋው ሊሆን ይችላል።

72
ይምሩ:- አሁን፤ ደንበኛዋ ስካርፉን አንገቷ ላይ ጠምጥማ ራሷን በመስታውት ማየት እንድትጀምር
እናደርጋለን። ለምሳሌ፤ “ከለበስሺው ልብስ ጋር ማች ያደርጋል፤” ወይም “በክረምት ጥሩ ሙቀት
ይፈጥርልሻል” ማለት እንችላለን፡፡

ይምሩ:- ይህች ደንበኛ ልብሱን ለብሳ ምን እንደምትመስል ራሷን በምናብ መሳል ከጀመረች፤ ልትገዛው
ተቃርባለች ማለት ነው!

ይምሩ:- ሽያጩን ለማጠናቀቅ ሞክረን ደንበኛዋ ዛሬ ሳትገዛን ከሄደች፤ በሌላ ጊዜ ተመልሳ መጥታ የመግዛት
እድሏ የመነመነ ነው፡፡

ይምሩ:- ስለዚህ፤ አሁን ለምን መግዛት እንደሚያስፈልጋት እንድትገነዘብ እናደርጋለን። ለምሳሌ፤ ክረምቱ
እየገባ እንደሆነ፤ ወይም በዚያ ከለር ሌላ እንደሌለን እናስረዳታለን። ምናልባትም ከአንድ በላይ የምትገዛ ከሆነ
መጠነኛ ቅናሽ ልናደርግላት እንችላለን፡፡

ይምሩ:- እንኳን ደስ አላችሁ! ሽያጭ አከናወንን ማለት ነው!

____________________________________________________________________

ይምሩ:- አሁን በየቡድኖቻችሁ ጓደኛ ይምረጡ (ጥንድ ጥንድ ሁኑ)፡፡ አንዱ ሻጭ ሌላኘው ገዥ ትሆናላችሁ፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን የአሻሻጥ ቴክኒኮችን ግንዛቤ ውስጥ በመክተት፤ ካልኩሌተር ወይም በጠረጴዛ ላይ ያሉ
ሌሎች ቁሳቁሶች በመጠቀም ሽያጭ ተለማመዱ፡፡

ይምሩ:- የጥሩ መስተንግዶ አገልግሎት ተግባራዊ ልምምድ ማድረጋችሁን፣ ለእናንተ እንዲደረግላችሁ


የምትፈልጉትን ለደንበኞቻችሁም ያንኑ ማድረግ እንደሚገባችሁ እና የመከበር ስሜት ተሰምቷቸው
እንዲሄዱ ማድረግ እንዳለባችሁ አስታውሱ!

ይምሩ:- ለማስታወስ እገዛ ከፈለጋችሁ በሠልጣኞች መጽሐፍ ገጽ ____ ላይ በስዕል የተደገፉ የሽያጭ
ቴክኒኮችን ተመልከቱ፡፡ 5 ደቂቃ ተጠቀሙ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ5 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ሥራ ፈጣሪዎችን ጥንድ ጥንድ ካደረጉ በኋላ ትወናው በሽያጭ
ሲጠናቀቅ፤ ሚናቸውን ደግሞ ተቀያይረው እንደገና እንዲተውኑ ያግዟቸው፡፡

ይምሩ:- ከእናንተ በጣም ግሩም ሽያጭ ያከናወነ ማን ነው? እስቲ ወደዚህ ኑና ለቡድኑ አሳዩ!

ይምሩ:- ለመልሱ ጣፋጭ ይሸልሟቸው፡፡

ይምሩ:- ከዚህ የትምህርት ክፍል የቀሰማችሁትን አንድ ነገር ልትነግሩኝ የምትችሉ ሁለት ሰዎች አላችሁ?

ይምሩ:- ወጥተው አንድ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ ሃሳባቸውን በመደገፍ ያጋሯቸውን ነጥቦች እንደገና
ያብራሩ፡፡

ይምሩ:- ስለ ዛሬው ተሳተፏችሁ አመሰግናለሁ! ዋው! “ጥሩ የመስተንግዶ አገልግሎት”ን በተግባር በማሳየት
ሁላችሁም አስደናቂ ስራ ሰርታችኋል፡፡

73
// ክፍል 9 //
የዋጋ ተመን

የሚወስደው ጊዜ፡- 2 ሠዓታት


ግቦች:-
> ተሳታፊዎች፤ ከምርቶቻቸው ጋር የተቆራኘውን እሴትን ስለመፈለግ ይማራሉ።
> ተሳታፊዎች፤ ለምርቶቻቸው እንዴት ምክንያታዊ ዋጋ እንደሚያወጡ ይማራሉ።
> ተሳታፊዎች፤ የፍላጎት እና የአቅርቦት መሠረታዊ ነገሮችን ይማራሉ፡፡

አቅርቦቶች፡-
> ነጭ ሠሌዳ እና እስክሪብቶች
> የሒሳብ መደመሪያ ካልኩሌተሮች

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


> እሴት > ጭማሪ /Markup/
> ፍላጎት > መቶኛ /ፐርሰንት/
> አቅርቦት > ቋሚ ዋጋ (-)
> የዕቃ ጠቅላላ ወጪ > ተለዋዋጭ ዋጋ (-)
> ትርፍ ስሌት > Break Even point

የሒሣብ ቀመሮች (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


> ትርፍ ስሌት፡- ከመሸጫ ዋጋ ላይ የዕቃው ጠቅላላ ወጪ ተቀንሶ የሚገኘው ገንዘብ። የሒሣብ ቀመሩ፡-
መሸጫ ዋጋ - የዕቃው ጠቅላላ ወጪ = ትርፍ ስሌት

> ጭማሪ /Markup/፡- ትርፍ ለማግኝት ሲባል በአንድ ዕቃ ጨቅላላ ወጪ ላይ በፐርሰንት/በመቶኛ/


አስልተን የምንጨምረው ክፍያ፡፡ የሒሣብ ቀመሩ፡-
[(መሸጫ ዋጋ÷የዕቃው ጠቅላላወጪ፡-)-1]x100=%ጭማሪ /Markup/
(0.3xየዕቃው ጠቅላላ ወጪ)+የዕቃው ጠቅላላ ወጪ=የ30%ጭማሪ /Markup/
(1 x ትክክለኛው ወጪ)+የዕቃው ጠቅላላ ወጪ= የ100% ጭማሪ /Markup/
> የBreakeven ነጥብ፡- ወርሃዊ ወጪዎቻችንን በሙሉ መሸፈን የሚያስችለን የገቢ መጠን።
ጠቅላላ ወርሃዊ ወጪ÷ትርፍ ስሌት = የBreakeven Point ገቢ

74
ዝግጅት:-
> በአካባቢው የሚገኝ ከፍተኛ አቅርቦት እና ዝቅተኛ ፍላጎት፤ እንዲሁም ዝቅተኛ አቅርቦት እና ከፍተኛ
ፍላጎትን የሚያሳዩ ምሳሌዎችን ይምረጡ። በውይይቶችም መሃል እነዚህን ምሳሌዎች ይጠቀሙ፡፡
> የውሃ፣ የግብር፣ እና ሌሎች መሠል ክፍያዎች ውስን ወይም ተለዋዋጭ መሆናቸውን ከአከባቢው
ባለስልጣን አስቀድመው ይረዱ።
> ምኑ በማድረግ ትምህርቱን ቀለል ያድርጉት።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ:-


> መዝ 106÷3

ይምሩ:- ሁላችሁም በድጋሚ እንኳን ደህና መጣችሁ!

ይምሩ:- ቀደም ሲል በማርኬቲንግ ውይይታችን ላይ እንደምናስታውሰው፤ ትክክለኛ ዋጋን መተመን መቻል


ስኬታማ ቢዝነስን ለመገንባት ወሳኝ ሚናን ይጫወታል፡፡

ይምሩ:- ከፍ ያለ ዋጋ መተመን፤ ወጪያችንን በሙሉ ሸፍነን ትርፍ ማግኘታችንን ያረጋግጥልናል።

ይምሩ:- ይሁን እንጅ፤ የዋጋ ተመናችን ከምርቶቻችን ወይም ከአገልግሎቶቻችን ትክክለኛ ዋጋ በላይ
ማስወደድ አያስፈልገንም። አለበለዚያ፤ ደንበኞች ሌላ ሰው ጋ ሄደው ለመግዛት ይገደዳሉ።

ይምሩ:- መዝሙር 106÷3 እንዲህ ይላል፡-

“ፍርድን የሚጠብቁ፤ ጽድቅንም ሁልጊዜ የሚያደርጉ ምስጉኖች ናቸው።”

ይምሩ:- ትክክለኛ ፍርድን ለሌሎች ማድረግ ወይም ጽድቅን ማድረግ ማለት፤ ለምርቶቻችን እና
አገልግሎቶቻችን ትክክለኛና ሚዛናዊ ዋጋ መተመን ማለትም ጭምር ነው።

ይምሩ:- አንድ ዕቃ ልትገዙ ሄዳችሁ ተመጣጣኝ ያልሆነ ዋጋ ተጠይቃችሁ የምታውቁ ሰዎች ካላችሁ፤ እስቲ
አንድ ሰው ሊያጋራን ይችላል?

ይምሩ:- ምላሽ ይቀበሉና፣ በአድናቆት ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- የአንድን ምርት /ዕቃ/ ወይም አገልግሎት ትክክለኛ ዋጋ ስትተምኑ፤ ጠቀሜታውን በሚገባ መወሰን
አለባችሁ። ጠቀሜታው ከፍተኛ የሆነ ምርት፤ ጥራቱ ከፍ ያለ እና ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ ነው።

ይምሩ:- ደንበኞቻችን የአንድን ምርት ጠቀሜታ በሚወስኑበት ጊዜ፤ ምርቱን ከገዙት በኋላ ስለሚሰጠው
አገልግሎት፣ ከዚያም ጠቀሜታውን ከዋጋው ጋር ያወዳድራሉ። ከዋጋው በላይ እንደሚጠቅማቸው ማረጋገጥ
ይፈልጋሉ።

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ አዲስ ልብስ ልንገዛ ብንፈልግ፣ ለዚያ አዲስ ዕቃ ምን ያህል ገንዘብ ማውጣት እንደሚኖርብን
በጥልቀት እናስባለን፡፡

75
ይምሩ:- ከዚያም በመቀጠል፤ ልናወጣ በወሰንነው የገንዘብ መጠን፡ ጥራት ያለው እቃ ለመግዛት እንፈልጋለን፡፡

ይምሩ:- በዚህ የግዥ ሂደት፤ ተመሳሳይ ዋጋ ያላቸው ሁለት ዕቃዎችን ልናገኝ ስለምንችል የትኛውን
እንደምንገዛ መወሰን ያስፈልገናል፡፡

ይምሩ:- አንደኛው ስፌቱ ጥሩ አይደለም፣ ጨርቁም ጥራት ያለው አይመስልም፣ ከለሩም ደስ አላለንም፡፡
ሌላኛው ግን በጥራት የተሰፋ ሲሆን ከለሩም ይመቻል፡፡

ይምሩ:- ሁላችሁም የመጀመሪያውን ሸሚዝ ለምን መረጣችሁ? (ጨርቁ ጥራት ያለው ስለሆነ፣ ከለሩ ደስ
ስለሚል፣ አዲስ ፋሽን ስለሆነ…)

ይምሩ:- ትክክል። እኛም እንደ ደንበኛው፤ የላቀ ጠቀሜታ ያለው ምርጫችን እንዲሆን እንፈልጋለን፡፡

ይምሩ:- የቢዝነስ ባለቤቶች ብንሆንም፤ እንደ ደንበኞቻችን ሆነን ማሰብ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ደንበኛ
ልናደርጋቸው እንደምንፈልጋቸው ሰዎች ልናስብ ይገባናል፡፡

ይምሩ:- ለደንበኛው ምን አስፈላጊ ነው? ደንበኞቹ ምን ያህል ገንዘብ ሊያገኙ ይችላሉ? ደንበኛው
በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሌላ ሱቅ ተመሳሳይ ምርት ሊያገኝ ይችላል? ሌላኛው የሱቅ ክፍያ ምንድነው?

ይምሩ:- የንግድ ሥራ ባለቤቶች እንደመሆንዎ መጠን ጥራት ያለው እና እጅግ በጣም ጥሩ ዋጋ ያላቸውን
ምርቶች ማቅረብ እንፈልጋለን እንዲሁም ሌላ ሱቅ የማያሟላ ፍላጎታቸውን የሚያሟሉ ፡፡

ይምሩ:- ደንበኞች አንድ የሆነ ምርት ወይም አገልግሎት እንዲቀርብላቸው ሲሹ ፍላጎት ይባላል፡፡

ይምሩ:- እኛ እንደ አንድ የቢዝነስ ባለቤቶች፤ ደንበኞቻችን ምን እንደሚፈልጉ አድምጠን ያንኑ ምርት ወይም
አገልግሎት ማቅረብ የእኛ ድርሻ ነው ፡፡

ይምሩ:- የቀረበው ምርት ወይም አገልግሎት ደግሞ አቅርቦት ይባላል።

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ የሳጠራ ቅርጫት (በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ የሚሰራን ስራ በምሳሌነት መጥቀስ
ይችላሉ) የምታመርቱ ከሆነ፤ ለሽያጭ የተዘጋጁ ብዛት ያላቸው ቅርጫቶች (ወይም የአካባቢው ምርት)
አቅርቦታችሁ ይሆናል ማለት ነው።

ይምሩ:- በአንድ ምርት ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ሲኖርና አቅርቦቱ ግን ዝቅተኛ ሲሆን፤ የዚያ ምርት ዋጋ ከፍ
ይላል።

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ ወርቅ የከበረ ማዕድን ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ፤ ብዙ ሰዎች ወርቅ መግዛት እፈለጉ በብዛት
መገኘት አለመቻሉ፤ የወርቅን ዋጋ በጣም ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል።

ይምሩ:- ከዚህ ተቃራኒው ደግሞ እውነት ነው፡፡ መጠነ ብዙ ምርት ወይም አገልግሎት በገበያ ላይ ሲገኝ እና
ብዙዎች የማይፈልጉት ከሆነ፤ ዋጋው የረከሰ (የወረደ) ይሆናል።

ይምሩ:- በማህበረሰባችሁ ውስጥ በገበያ ላይ በብዛት ከመኖሩ የተነሳ ርካሽ የሆነ ነገር እስቲ በየቡድኖቻችሁ
ሆናችሁ አስቡ - ለምሳሌ በክረምት ወቅት የእህል አቅርቦት ሊሆን ይችላል-

(ወይም ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚመጥን ምሳሌን መጠቀም ይችላሉ)፡፡

76
ቡድን አመቻቾች፡- ለ5 ደቂቃዎች ያህል፡፡ መልሶችን ይጠብቁ፡፡ ተሳታፊዎች መልስ ለመስጠት ከተቸገሩ
ጥቆማ ይስጧቸው፤ ምናልባትም ሁሉም ሰው አምርቶ የሚመገባቸው፣ በተለምዶ የሚታወቁ ጥቂት የምግብ
ዓይነቶችን ጥቆማ ይስጧቸው፡፡

ይምሩ:- ከእያንዳንዱ ቡድን አንድ አንድ ሰው እየተነሳ ሀሳቡን እንዲያካፍል ያድርጉ፡፡ ለምላሾቻቸው ጣፋጭ
ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- እንደ አንድ የቢዝነስ ባለቤት ብዙ ለመሸጥ ከፈለግን፤ በከፍተኛ ደረጃ ተፈላጊና ለየት ያሉ ምርቶችን
ማቅረብ ይጠበቅብናል፡፡

ይምሩ:- ብዙ ሰዎች ሊገዙት የሚፈልጉት ነገር ግን አቅርቦቱ አነስተኛ ከሆነ ምርት የበለጠ ትርፍ እናገኛለን።
ከአካባቢያዊ ምሳሌ እዚህ ላይ ለመጠቀም ይሞክሩ።

ይምሩ:- በቢዝነሶቻችሁ ውስጥ ታርጌት ያደረጋችኋቸው ልዩ ገበያዎች ማለትም በአቅርቦት ዝቅተኛ የሆኑና
ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን ምርቶች ማቅረብ እንደምትችሉ ተወያዩ።

ቡድን አመቻቾች፡- ለ5 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ይህንን ውይይት ያመቻቹ፡፡ ሥራ ፈጣሪዎቹ ለማህበረሰባቸው


ማቅረብ የሚገባቸውን የምርት ዓይነት እንዲያስቡበት የሚያደርግ ተከታታይ ጥያቄዎችን ይጠይቋቸው፡፡

ይምሩ:- በየቢዝነሶቻችሁ በምትሸጧቸው ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ዙሪያ ጠቃሚ ሀሳቦችን እንዳገኛችሁ
ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ይምሩ:- ዋጋን በምንተምንበት ሠዓት ከግምት ውስጥ ልናስገባ የሚገባን ሌላው ጉዳይ፤ የምንጠይቀው ክፍያ
ወጭዎቻችንን ሸፍኖ ለመቆጠብ ወይም ቢዝነሳችንን ለማስፋፋት የሚያስችለን መሆኑን ነው።

ይምሩ:- ትርፍ ለማግኘት፤ ለምርቱ ወይም ለአገልግሎቱ የሚጠይቀውን ወጪ ሁሉ በሚገባ መወሰን አለብን፡፡

ይምሩ:- ጠቅላላ ወጪ ማለት፤ አንድ ዕቃ ወይምአገልግሎት ተመርቶ /ተገዝቶ/ ሸማች እጅ እስኪደርስ


ድረስ የሚጠይቀው ወጪ ነው፡፡

ይምሩ:- በሴቶች የልብስ መሸጫ መደብራችን _________________ (የመደብሩ ስም) ውስጥ ያሉንን
ሰልቫጅ አልባሳት እንመልከት።

ይምሩ:- የመሸጫ ዋጋን መወሰን ያስፈልገናል፡፡ ይህም ቀሚሱ ከጅምላ ሻጩ የተገዛበት፣ የእጥበት ወይም
የጥገና ስፌት፣ ትራንስፖርት፣ የማሳያ /ዲስፕሌይ/ እና የመጠቅለያ ወጪን ያካተተ ይሆናል፡፡

ይምሩ:- በምሳሌያችን ውስጥ የተጠቀሱትን የእያንዳንዱን እቃ ዋጋ እንዲተምን አንድ ሰው መምረጥ


እፈልጋለሁ። ይህ ሰው በሚሰጠው የዋጋ ተመን ሌሎቻችሁ ላትስማሙ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን በምሳሌነት
ብቻ የተጠቀሱ መሆናቸውን ልብ በሉ፡፡

ይምሩ:- ስራ ፈጣሪዎቹ መልስ እንዲሰጡ ይጠይቋቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል የሚጠቀስ ስለሆነ በዋጋዎች ላይ
የሚነሱ ክርክሮችን ይገድቡ፡፡

ይምሩ:- ከሁሉ አስቀድሞ አንድ ነገር እናስብ፤ ያ ቀሚስ ከጅምላ መሸጫ ምን ያህል ያወጣል?
____________

77
ለምላሹ ጥቂት ይጠብቁ እና ሠሌዳው ላይ ይፃፉ፡፡

ይምሩ:- ልብሱን አሳጥቦ ለማስጠገን /ለማሰፋት/ ምን ያህል ያስከፍላል? ___________

ይምሩ:- ለምላሹ ጥቂት ይጠብቁ እና ሠሌዳው ላይ ይፃፉ፡፡

ይምሩ:- ወደ ሱቄ ለማጓጓዝ ምን ያህል ያስከፍለኛል? ___________

ይምሩ:- ለምላሹ ጥቂት ይጠብቁ እና ሠሌዳው ላይ ይፃፉ፡፡

ይምሩ:- በመስቀያ ላይ ለማሳየት /ዲስፕሌይ/ ምን ያህል ወጭ ይጠይቀኛል? ____________

ይምሩ:- ለምላሹ ጥቂት ይጠብቁ እና ሠሌዳው ላይ ይፃፉ፡፡

ይምሩ:- እነዚህ ሁሉ ወጪዎች አንድ ላይ ሲደመሩ የዚህ ቀሚስ ጠቅላላ ወጪ ይሆናሉ።

ይምሩ:- የዚህ ቀሚስ ጠቅላላ ወጪ ስንት ነው? ድምሩን በየቡድኖቻችሁ አስሉ፡፡

ይምሩ:- ለሂሳብ ስሌቱ ጊዜ ይስጧቸው፣ መልሶችን ያሰባስቡ፣ ሁሉም መስማማቱን ያረጋግጡ ከዚያም በቦርዱ
ላይ ቁጥሩን ይፃፉት፡፡

የቡድን አስተባባሪዎች፡- ይህንን ስሌት ምሩ፡፡

ይምሩ:- በቀሚሱ የሽያጭ ዋጋ ላይ ሊካተት የሚገባው ጠቅላላ ወጪ _____________ ብር ነው።


(በዚህ “የዋጋ ተመን” ስልጠና ክፍለ ጊዜ ሁሉ፤ የቀሚስ የመሸጫ ዋጋ ማውጣትን አይርሱ።)

ይምሩ:- ትርፍ ስሌት ማለት፤ ከእያንዳንዱ ምርት ወይም አገልግሎት ላይ የሚገኝ ገንዘብ፤ ወይም ከመሸጫ
ዋጋ ላይ የዕቃው ጠቅላላ ወጪ/Actual Coast/ ተቀንሶ የሚገኘው ገንዘብ ማለት ነው።

ይምሩ:- ትርፍ ለማግኘት፤ ለእያንዳንዱ ዕቃዎቻችሁ የመሸጫ ዋጋ ወይም ለአገልግሎቶቻችሁ የምትጠይቁት


ክፍያ፤ ከዕቃው ወይም ከአገልግሎቱ ጠቅላላ ወጪ ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚገባው አስታውሱ፡፡

ይምሩ:- ከምንሸጠው ከእያንዳንዱ ምርት ወይም አገልግሎት ላይ ትርፍ ስሌት ለመወሰን፤ ከመሸጫ ዋጋው
ላይ ለዚያ ምርት /ዕቃ/ ወይም አገልግሎት ያወጣነውን ጠቅላላ ወጪ እንቀንሳለን፡፡

ይምሩ:- ከዚህ የሚከተለውን የሂሳብ ቀመር በመጠቀም፤ በሂሳብ መደመሪያ ካልኩሌተሮቻችን ትርፋችንን
ማስላት እንለማመድ፡፡

በቦርዱ ላይ ወደ ተጻፈው የትርፍ ስሌት ሒሳባዊ ቀመር ያመልክቷቸው፡፡


(የመሸጫ ዋጋ - ጠቅላላ ወጪ= ትርፍ ስሌት)

ይምሩ:- በመጀመሪያ፤ የምትሸጡበትን ዋጋ ጻፉ። ከዚያም ለዚያ ምርት /ዕቃ/ የወጣውን ወጪ ቀንሱ። ቀሪው
ከዚያ ዕቃ ላይ የምታገኙት ትርፍ ነው።

ይምሩ:- እስቲ አሁን ደግሞ ይህን የሒሳብ ቀመር በመጠቀም የአንድን ዕቃ ወይም አገልግሎት ትርፍ ለማስላት
ዕቃ አንድ ላይ እንለማመድ!

78
ይምሩ:- በምሳሌነት በምንጠቀመው _________________ በተባለው ልብስ መሸጫ መደብራችን
(የመደብሩ ስም ይጠቀስ)፤ የአንድ ቀሚስን ጠቅላላ ወጪ ___________ ብር አስልተን ነበር (ቀደም ሲል
የተሰላውን ጠቅላላ ወጪ ያስፍሩ)፡፡

ይምሩ:- ይህ ቀሚስ ምን ያህል ያወጣል? መልስ ይቀበሉ እና ሠሌዳው ላይ ይፃፉ።

ይምሩ:- __________ ብር እናስከፍላለን (በቡድን የቀረበ የመሸጫ ዋጋ)፡፡

ይምሩ:- እነዚህን ቁጥሮች በመጠቀም ትርፍ ስሌት እንዴት መስራት እንደሚቻል፤ ማለትም የቀሚሱን
ጠቅላላ ወጪ ከመሸጫ ዋጋው ላይ በመቀነስ በነጭ ሌዳው ላይ ሰርተው ያሳዩ።

ይምሩ:- ከዚህ ቀሚስ ስንት አተረፍን?

ይምሩ:- በመመለስ እንዲሳተፉ ያድርጉ፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ይስጡ። ሁሉም ካልተስማሙ፤
ቡድኑን እንደገና ወደ ስሌቱ ይመልሷቸው።

ይምሩ:- ሁላችም ቆንጆ ተሳትፎ ነው ያደረጋችሁት! በቢዝነሳችን ለእያንዳንዱ ዕቃ ወይም አገልግሎት ምን


ያህል ትርፍ እንደምናገኝ ማወቃችን ለምን አስፈለገ?

ይምሩ:- አንድ ወይም ሁለት ተሳታፊዎች መልስ እንዲሰጡ ያድርጉ፡፡ ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- በአንድ ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ትርፍ ለማግኘት ሲባል በጠቅላላ ወጪ ላይ በመቶኛ /በፐርሰንት/
አስልተን የምንጨምረው ክፍያ፤ ጭማሪ /Markup/ ይባላል፡፡

ይምሩ:- አስታውሱ፤ አንድ ሙሉ የሆነን ነገር በ100ኛ የመከፋፈል ሒሳባዊ ስሌት መቶኛ ወይም ፐርሰንቴጅ
ይባላል።

ይምሩ:- በምንሸጣቸው ምርቶች ሁሉ ላይ ከ30% እስከ 100% ጭማሪ /Markup/ ቢደረግ ይመከራል፡፡ ይህ
ግን እንደ ጥሩ ምክር እንጅ ጥብቅ መመሪያ አይደለም፡፡

ይምሩ:- ከ30% እና 100% መካከል የሆነ ጭማሪን /Markup/ ያካተተ ዋጋን ለማስላት፤ የሚከተሉትን
የሂሳብ ቀመሮች እንጠቀማለን፡- በቦርዱ ላይ ወደ ተጻፉት የጭማሪ /Markup/ ሒሳባዊ ቀመሮች
ያመልክቷቸው፡፡

30% ጭማሪ /Markup/፡- (0.3 x ጠቅላላ ወጪ) + ጠቅላላ ወጪ = የ30% ጭማሪ /Markup/ የታከለበት
መሸጫ ዋጋ

100% ጭማሪ /Markup/፡- (1 x ጠቅላላ ወጪ) + ጠቅላላ ወጪ = የ100% ጭማሪ /Markup/ የታከለበት
መሸጫ ዋጋ

ይምሩ:- የቀደመውን ምሳሌአችንን በመጠቀም፤ ጠቅላላ ወጪው ___________ ብር የሆነን አንድ ቀሚስ
ብንወስድ፡ (ካለፈው ምሳሌ ላይ ጠቅላላ ወጪውን በአብነት ይውሰዱ) የ30% ጭማሪን /Markup/
ለማስላት፤ ጠቅላላ ወጪውን በ 0.3 እናባዛለን፡፡ ከዚያም የ30% ጭማሪ /Markup/ ያለው የመሸጫ ዋጋውን
ለማስላት፤ በጠቅላላ ወጪው ላይ የ30% ጭማሪውን /Markup/ እንደምራለን፡፡ ዋጋው ስንት ይመጣል?

ይምሩ:- ምላሾችን ይቀበሉ፡፡ በመልሱ ትክክለኛነት ሁሉም መስማማቱን ያረጋግጡ፡፡ ከአድናቆት እና ምስጋና
ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

79
ይምሩ:- የ100% ጭማሪን /Markup/ ለማስላት፤ ጠቅላላ ወጪውን በ 1 እናባዛለን፡፡ ወይም በሌላ ቀላል
አገላለጽ፤ ጠቅላላ ወጪውን እጥፍ ማድግ ማለት ነው፡፡ ዋጋው ስንት ሆነ?

ይምሩ:- መልሶችን ይቀበሉ፡፡ በመልሱ ትክክለኛነት ሁሉም መስማማቱን ያረጋግጡ፡፡ ከአድናቆት እና ከምስጋና
ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ስለዚህም፤ ወጪዎቻችንን ሸፍነን ትርፍ ለማግኘት ከብር ____ (የ30% ጭማሪን /Markup/
ያካተተ) እስከ ብር _______ (የ100% ጭማሪን /Markup/ ያካተተ) እናስከፍላለን፡፡

ይምሩ:- ልትሸጡት ላዘጋጃችሁት ምርት /ዕቃ/ ወይም ልታቀርቡት ላሰባችሁት አገልግሎት የወቅቱን ጭማሪ
/Markup/ በፐርሰንት መተመን ከፈለጋችሁ የሚከተለውን ቀመር መጠቀም ትችላላችሁ፡- ቦርዱ ላይ ወደ
ተፃፈው የጭማሪ /Markup/ ሒሳባዊ ቀመር ያመላክቷቸው።

[(የመሸጫ ዋጋ ÷ ጠቅላላ ወጪ) - 1] x 100 =% ጭማሪ /Markup/

ይምሩ:- በአሁኑ ወቅት በቢዝነስ ስራ ላይ ያለ፤ አንድን ምርት ወይም አገልግሎት እንዴት እንደሚሸጥ
ሊያጋራን የሚችል እስቲ አንድ ሰው ይኖራል? (ተሳታፊው የመሸጫ ዋጋውን እንዲናገር ያድርጉ)

ይምሩ:- ምላሽ ይቀበሉ፡፡ በሒሳብ ቀመሩ መሠረት ቦርዱ ላይ ይጻፉ።

ይምሩ:- ያ ምርት /ዕቃ/ ወይም አገልግሎት ጠቅላላ ምን ያህል ያወጣል? (የመጀመሪያው ተሳታፊ ጠቅላላ
ወጪውን ያቀርባል)

ይምሩ:- ምላሽ ይቀበሉ፡፡ በሒሳብ ቀመሩ መሠረት ቦርዱ ላይ ይጻፉ። ከምስጋናና አድናቆት ጋር ጣፋጭ
ይሸልሙ። ስለ ንግድህ ስላጋራኸን እናመሰግናለን!

ይምሩ:- አሁን በሒሳብ ማስያ ካልኩሌተሮቻችን ተጠቅመን የሰውየውን ወቅታዊ ጭማሪ /Markup/
በማስላት ይህን የሂሳብ ቀመር እንጨርስ፡፡ የሒሳብ ቀመሩን ያጠናቅቁ፡፡ ሒሳቡን ተሳታፊዎች በተናጠል
እንዲሰሩ ዕድል ይስጧቸው።

ቡድን አመቻቾች፡- ለ1 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ተሳታፊዎች ይህንን ስሌት በተናጠል በሚሰሩበት ሠዓት ያግዟቸው።

ይምሩ:- የዚህ ምርት /ዕቃ/ ጭማሪ /Markup/ በመቶኛ ስንት ነው? ምላሽ ይቀበሉ፡፡ የሁሉንም ሰው መረዳት
ያረጋግጡ።

ይምሩ:- የጭማሪ /Markup/ን ሥሌት በማስላት ረገድ የተሳካ ሥራ ሰርታችኋል!

ይምሩ:- የጭማሪ /Markup መጠን ከፍ ለማድረግ መወሰን አስፈላጊ ነው፡፡ ጭማሪያችሁ /Markup አሉታዊ
/ነጌቲቭ/ ከሆነ፤ ኪሳራ እየገጠማችሁ ስለሆነ ዋጋውን ከፍ ማድረግ ወይም ወጪዎቻችሁን ዝቅ ማድረግ
ያስፈልጋችኋል፡፡

ይምሩ:- በጥራት መጓደል፣ በጥሬ ዕቃዎች መወደድ፣ በገበያ ዋጋ ወይም በሌላ በማንኛውም ምክንያት
ጭማሪያችሁ /Markup ከ30% መብለጥ የማይችል ከሆነ፤ ምርቱ /ዕቃው/ ላይ ማሻሻያ ማድረግ ወይም ሌላ
ምርት /ዕቃ/ የመሸጥ አማራጭ መንገድ መፈለግ ይኖርባችሁ ይሆናል።

80
ይምሩ:- የምንሸጠው እያንዳንዱ ምርት /ዕቃ/ ወይም አገልግሎት ወጪዎቻችንን ሸፍኖ በቂ ትርፍ በማስገኘት
ንግዱን ለመስፋፋት፣ ለመቆጠብ ወይም ለቤት ወጭ ለማዋል እንዲያስችለን፤ ጭማሪያችን /Markup/
ከ30% እስከ 100% መካከል ባለው ሊሆን እንደሚገባ አስታውሱ!

ይምሩ:- ቢዝነሳችን ስኬታማ እንዲሆን ከፈለግን፤ ወጪያችንን ሸፍኖ ተቀማጭ ገንዘብ እንዲኖረን፤ በየወሩ
ምን ያህል ገቢ ማስገባት እንደሚኖርብን ማወቅ ይገባናል።

ይምሩ:- ይህንን ለማድረግ ደግሞ፤ ከምርታችን ወይም አገልግሎታችን ሽያጭ ጋር የተዛመዱ ሌሎች
ወጪዎችን ሁሉ ለይተን መረዳት ይኖርብናል፡፡

ይምሩ:- ለምሳሌ፣ የምንሸጥበት መደብር /ሱቅ/ ባይኖረን ኖሮ ቀሚሱን መሸጥ አንችልም ነበር፡፡ ስለዚህም
የመደብር ኪራይ ሌላው የቢዝነሳችን ወጪ ነው።

ይምሩ:- በዚህ ምሳሌ አድርገን በምንጠቀመው በሴቶች ሰልቫጅ ልብስ መሸጫ መደብር ውስጥ የሚኖሩንን
ወርሃዊ ወጪዎች በመጠቀም አሁን ልምምድ እናደርጋለን፡፡

ይምሩ:- ምንም እንኳን የክፍያው መጠን የተለያየ ቢሆንም፤ እነዚህ አሁን የምናያቸው የወጪ ዓይነቶች
ወደፊት በምንከፍታችውም ሆነ በከፈትናቸው መደብሮች /ሱቆች/ ሁሉ ላይ ተግባራዊ የሚሆኑ ናቸው፡፡
ምናልባትም የሸቀጣሸቀጥ ሱቅ፣ አትክልት ቤት፣ ፋርማሲ፣ የጥገና መደብር፣ ኢንተርኔት ካፌ፣ ሞባይል ቤት
ወይም ለማኅበረሰባችን አገልግሎት የሚውል ሌላ ማንኛ ዓይነት ሱቅ /መደብር/ ሊሆን ይችላል፡፡

ይምሩ:- እነዚህ ወጪዎች ወርሃዊ ክፍያዎቻችን እንጅ የመነሻ ካፒታል ወጪዎቻችን አለመሆናቸውን
አስታውሱ፡፡

ይምሩ:- አሁን በምሳሌያችን መሠረት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ለእያንዳንዱ ወጪ ዋጋ የሚነግረን

አንድ ሰው እመርጣለሁ፡፡ በሚሰጠው የወጪ መጠን ሙሉ በሙሉ ባትስማሙ እንኳ እንደ ምሳሌ ብቻ
ቁጠሩት፡፡

ይምሩ:- አንድ ሱቅ ብንከፍት፤ በየወሩ ምን ዓይነት ወጭዎች ይኖሩብናል?

ይምሩ:- ለእነዚህ ወጪዎች የሚተመኑ ዋጋዎችን ቦርዱ ላይ በዝርዝር ይፃፉ፡፡ ለክርክር ዕድል ሳይሰጡ ፈጠን
ፈጠን ብለው ይመዝግቡ። የቀሚስ መሸጫ መደብሩን በምሳሌነት መጠቀምን አይርሱ።

> የኪራይ ዋጋ
> የኤሌክትሪክ ወጪ
> የመድን ዋስትና /ኢንሹራንስ/
> ግብር
> አጋዥ ቁሳቁሶች
> የሠራተኛ ደሞዝ
> የትራንስፖርት ወጪ
> እና ሌሎች?

ይምሩ:- ይህን ቢዝነስ ለመስራት የሚጠይቀውን የአንድ ወር አጠቃላይ ወጪ ለማወቅ እነዚህን ሁሉ አንድ
ላይ እንደምራለን፡፡ ሁላችሁም በየግል ስሩት፡፡ ሒሳቡን ለመስራት ጊዜ ይስጧቸው።

ቡድን አመቻቾች፡- ለ2 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ሥራ ፈጣሪዎች የሚያደርጉትን የሂሳብ ስሌት ጥረት ያግዙ፡፡

81
ይምሩ:- የአንድ ወር ጠቅላላ ወጭ ስንት መጣ?

ይምሩ:- ምላሾችን ይቀበሉ፡፡ ሁሉም ሰው መስማማቱን ያረጋግጡ፡፡ ይህ ስሌት በምሳሌያችን መሠረት


የፈጠራ ቁጥሮች መሆናቸውን በድጋሚ አጽንኦት ሰጥተው ይግለጹላቸው።

ይምሩ:- ይህን የወጪ መጠን ማወቃችን እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህን ወርሃዊ ወጪ ለመሸፈን ምን
ያህል ሽያጭ ማከናወን እንደሚያስፈልገን እንድንወስን ይረዳናል፡፡ በዚህ ዙሪያ በቀጣይ የበለጠ እንነጋገራለን፡፡

ይምሩ:- ለወጪዎቻችን በጀት ስንመድብ፤ አንዳንዶች በየወሩ ተመሳሳይ ሲሆኑ ሌሎቹ ግን የተለያዩ ቢሆኑ
ምን እናደርጋለን?

ይምሩ:- ምላሾችን ከየቡድኑ ይቀበሉ፡፡ ከአድናቆት እና ከምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- አብዛኞቹ ወርሃዊ ወጪዎች ተመሳሳይ ናቸው። እነዚህን መሠል ወጪዎች የማይለዋወጡ
ከመሆናቸው የተነሳ ቋሚ ወጪዎች ተብለው ይጠራሉ፡፡ በዚህ በቦርዱ ላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ የትኞቹ
ቋሚ ወጪዎች ናቸው?

ይምሩ:- ምላሾቹን ከየቡድኑ ይሰብስቡ፡፡ እነዚህ ምላሾች እንደየማህበረሰቡ እና እንደ ቢዝነሱ ዓይነት የተለያዩ
ይሆናሉ። የልምምዱ ዋንኛ ዓላማ፤ ስራ ፈጣሪዎች ለመልሶቻቸው አሳማኝ ምክንያት እንዲሰጡ ለማስቻል
ነው፡፡ ከቋሚ ወጭዎች ጎን አግድም መስመር (-) ምልክት ያድርጉ፡፡ አድናቆትዎን ይግለጹ።

ይምሩ:- እንደየምርቱ ሁኔታ፤ አንዳንድ ወጭዎች በየወሩ ይለዋወጣሉ፡፡

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ ግብይት በሚበዛበት ወቅት ሠራተኞችን ጨምረን መቅጠር ስለሚኖርብን የሠራተኛ ወጪ
ከፍ ሊል ይችላል፤ ወይም ለመጪው ዓመት በዓል አዳዲስ እቃዎችን በመግዛት ዝግጅት ማድረግ ሊኖርብን
ይችላል፡፡

ይምሩ:- በየወሩ የሚቀያየሩ ወጭዎች ተለዋዋጭ ወጭዎች ተብለው ይጠራሉ ፡፡ እኛ ምን ያህል ሥራ


እንደያዝን ወይም በሌሎች ነገሮች ላይ ተመስርተን እነዚህ በተለያዩ ወራት ውስጥ ወደ ላይ ይወርዳሉ ፡፡
በቦርዱ ላይ የትኞቹ ወጪዎች ተለዋዋጭ ወጭዎች ናቸው?

ይምሩ:- ምላሾቹን ከየቡድኑ ይሰብስቡ፡፡ ከተለዋዋጭ ወጭዎች ጎን የተጠማዘዘ መስመር (~) ምልክት
ያድርጉ፡፡ እነዚህ ምላሾች እንደየማህበረሰቡ እና እንደ ቢዝነሱ ዓይነት የተለያዩ ይሆናሉ። ለመልሶቻቸው
አሳማኝ ምክንያቶች እንዲሰጡ ተሳታፊዎችን ይጠይቁ፡፡ የልምምዱ ዋንኛ ዓላማ፤ ለመልሶቻቸው አሳማኝ
ምክንያቶች እንዲሰጡ ማስቻል ነው፡፡ ከአድናቆት እና ከምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ትርፋማ ቢዝነስ እንዲኖረን ከተፈለገ፤ የተለያዩ ወጪዎችን በአግባቡ በመረዳት ትክክለኛ የቢዝነስ
በጀት መመደብ ይገባል፡፡

ይምሩ:- ሁሉንም፤ ማለትም ቋሚ እና ተለዋዋጭ ወጪዎቻችንን እንዲሁም ምርቱን /ዕቃውን/ ለማምረት


/ለመግዛት/ እና ለመሸጥ የሚጠይቁ ወጪዎችን በሙሉ ለመሸፈን፤ ብዙ ምርቶችን /ዕቃዎችን/ ወይም
አገልግሎቶችን በከፍተኛ ዋጋ መሸጥ አለብን።

ይምሩ:- እነዚህን ወርሃዊ ወጪዎቻችንን በሙሉ መሸፈን የሚያስችለን የገቢ መጠን ብሬክኢቭን መጠን
/Breakeven point/ ይባላል። በሌላም አገላለጽ፤ ወጪያችንን ለመሸፈን በቂ ገቢ የሚያስገኙ ብዙ ምርቶች
ለሽያጭ ሲዘጋጁ ብሬክኢቭን መጠን /Breakeven point/ ይባላል።

82
ይምሩ:- ከብሬክኢቭን መጠናችን /Breakeven point/ ያለፈ ገንዘብ ማግኘት ካልቻልን ትርፋማ ቢዝነስ
አይኖረንም።

ይምሩ:- በዚህ ረገድ፤ ወጪዎቻችንን የምንቀንስበት ያለዚያም በምርቶች /ዕቃዎች/ ወይም በአገልግሎቶች
ላይ ዋጋ በመጨመር ወይም ብዙ ምርቶች /ዕቃዎች/ ወይም አገልግሎቶች በመሸጥ የበለጠ ገቢ
የምናመጣበትን መንገድ መፈለግ አለብን፡፡

ይምሩ:- በሴቶች የልብስ መሸጫ መደብር ምሳሌያችን ላይ እንደጠቀስነው አጠቃላይ ወርሃዊ ወጪያችን
_______ ብር ነው ብለን ነበር (ከላይ በምሳሌነት የተጠቀሱትን አጠቃላይ ወጭዎች ይጠቀሙ)።
በተጨማሪም፤ በመደብራችን ከሸጥነው ልብስ ትርፍ ስሌት __________ ብር ነው ብለናል (የመሸጫ
ዋጋውን ካለፈው ምሳሌ ይውሰዱ)።

ይምሩ:- የአንድን ምርት ብሬክኢቭን መጠን /Breakeven point/ለማስላት የምንጠቀመው ቀመር፡-

ጠቅላላ ወርሃዊ ወጭዎች ÷ ትርፍ ስሌት = በብሬክኢቭን /Breakeven/ መጠን ሊሸጡ የተዘጋጁ ምርቶች
/ዕቃዎች/ ወይም አገልግሎቶች

ይምሩ:- የሒሳብ መደመሪያ ካልኩሌተሮቻችሁን በመጠቀም፤ በብሬክኢቭን /Breakeven/ መጠን ምን ያህል


ልብሶችን መሸጥ እንደሚያስፈልገን አስሉ።

ይምሩ:- ለዚህ ጊዜ ይስጧቸው፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ2 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ጊዜ ይስጧቸው። መልስ ለመስጠት የሚሞክሩትን አይከልክሏቸው፡፡

ይምሩ:- በብሬክኢቭን /Breakeven/ መጠን፤ በአንድ ወር ምን ያህል ልብሶችን መሸጥ ያስፈልገናል?

ይምሩ:- ምላሾችን ይቀበሉ፡፡ ሁሉም ሰው መስማማቱን ያረጋግጡ፡፡

ይምሩ:- ብሬክኢቭን /Breakeven/ ደረጃ ለመድረስ ወይም ሁሉንም ወጪዎቻችንን ለመሸፈን በየወሩ
_________ ልብሶችን መሸጥ አለብን፡፡ ቢዝነሳችንን ትርፋማ ማድረግ ከፈለግን፤ ብዙ ሽያጮች ማካሄድ
አለብን፡፡

ይምሩ:- ምርቶቻችሁን /ዕቃዎቻችሁን/ በመሸጥ የምታገኙት ገንዘብ ገቢ ይባላል፡፡ ይህ ገንዘብ እንደ ቤት


ኪራይ፣ የሠራተኞች ደመወዝ፣ የመገልገያ ዕቃዎች ግዥ የመሳሰሉ የቢዝነስ ወጪዎቻችንን ለመሸፈን
ያስችለናል፡፡

ይምሩ:- እነዚህን ሁሉ ወጭዎች ከሸፈንን በኋላ የሚቀረን የገንዘብ መጠን፤ አጠቃላይ ትርፋችን ነው።
ለራሳችን በቂ የደሞዝ ክፍያ፣ ለቢዝነሳችን ማስፋፊያ እና ለቁጠባ ልናውለው እንችላለን።

ይምሩ:- በየወሩ መጨረሻ ትርፋችሁን ምን ላይ ማዋል እንደሚኖርባችሁ እንዴት እንደምትወስኑ


በየቡድኖቻችሁ ተወያዩበት፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ4 ደቂቃዎች ያህል፡፡ በዚህ ዙሪያ ሥራ ፈጣሪዎች የሚሉት ካለ ይፍቀዱላቸው፡፡ ትርፍን
መጠቀም የሚችሉባቸው ሶስት ነገሮች አሉ፡- እንደ ደሞዝ ቆጥሮ ወደ ቤት መውሰድ፣ ለቢዝነስ ማስፋፊያ
ማዋል፣ ያለዚያም ቢዝነስ ሲቀዘቅዝ ወይም ለአደጋ ጊዜ መቆጠብ፡፡ ብዙ ሥራ ፈጣሪዎች ከአንድ ቢዝነስ
በተጨማሪ ሌላ የገቢ ምንጭ አላቸው (ለምሳሌ፣ ሁለተኛ ሥራ፣ ሌላ ቢዝነስ፣ ስራ ያላት/ለው የትዳር አጋር)፡፡

83
ልምምድ

ይምሩ:- የአንድን ምርት /ዕቃ/ ወይም አገልግሎት ጠቅላላ ወጪን እንዲሁም ከ30 እስከ 100% ጭማሪ
/Markup/ን ያካተተ የመሸጫ ዋጋ ምጣኔን እንዴት ማስላት እንደምንችል አሁን አውቀናል፡፡ ስለዚህ ልምምድ
የምናደርግበት ሠዓት ነው! በመጽሐፍቶቻችሁ ከገጽ ____ እስከ ____ በመጠቀም፤ ከሶስት እስከ አምስት
የሚደርሱ በቅርብ በገበያ ላይ ያዋላችኋቸውን ወይም ለማዋል ያቀዳችኋቸውን ምርቶች /ዕቃዎች/ ወይም
አገልግሎቶች ጠቅላላ ወጪ እና የመሸጫ ዋጋ ስሩ።

ቡድን አመቻቾች፡- ለ20 ደቂቃዎች ያህል፡፡ በየቡድኖቻቸው ትርፍ ስሌትን እና ከ30% እስከ 100% ጭማሪ
/Markup/ን መፈለግ ይለማመዱ፡፡ ሠዓት ካለም፤ “ሰዎች ያን ያህል ገንዘብ ለዚያ ዓይነቱ ምርት /ዕቃ/ ወይም
አገልግሎት ለመክፈል ፈቃደኛ የሚሆኑ ይመስልሀ/ሻል?” የሚል ጥያቄ ይጠይቋቸው፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- የሚከተሉትን ቀመሮች ይጠቀሙ፡-

ትርፍ ስሌት፡- የመሸጫ ዋጋ - ጠቅላላ ወጪ = ትርፍ ስሌት

30% ጭማሪ /Markup/ (0.3 x ጠቅላላ ወጪ) + ጠቅላላ ወጪ = መሸጫ ዋጋ

100% ጭማሪ /Markup/፡- (1 x ጠቅላላ ወጪ) + ጠቅላላ ወጪ = መሸጫ ዋጋ

ብሬክኢቭን /Breakeven Point/:- አጠቃላይ ወርሃዊ ወጪ ÷ ትርፍ ስሌት = በብሬክኢቭን /Breakeven


የሚሸጡ ምርቶች /ዕቃዎች/ ብዛት

ይምሩ:- ከዚህ የትምህርት ክፍል የቀሰማችሁትን አንድ ነገር ልትነግሩኝ የምትችሉ ሁለት ሰዎች አላችሁ?

ይምሩ:- ወጥተው አንድ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ ሃሳባቸውን በመደገፍ ያጋሯቸውን ነጥቦች እንደገና
ያብራሩ፡፡

ይምሩ:- ይህ ክፍል በዚህ ይጠናቀቃል። ስንመለስ ስለ ተነጻጻሪ ጥቅም እንወያያለን፡፡

// ክፍል 10 //

ተመራጭ አቅርቦት

የሚወስደው ጊዜ፡- 1 ሠዓት

ግቦች:-
> ሁለት ተመሳሳይ ምርቶች በደንበኞች ፍላጎት ላይ ለምን ልዩነት ሊያመጡ እንደሚችሉ ተሳታፊዎች
ግንዛቤን ያገኛሉ፡፡
> ጥራት የመጠበቅን አስፈላጊነት ተሳታፊዎች ይገነዘባሉ።
> ተሳታፊዎች፤ ስለ ገበያ እና ገበያው ስለሚጠይቀው ተከታታይ ማሻሻያዎች እውቀት ያገኛሉ።

84
አቅርቦቶች፡-
> እስክሪብቶዎች > ሁለት ተመሳሳይ ቲ-ሸርቶች (አንድ ንፁህ እና
> የሠልጣኞች መጻሕፍት ቆንጆ፤ሌላኛው የቆሸሸና ተስተካክሎ
> ጣፋጮች ያልተሰፋ)
> ነጭ ሠሌዳ > አንድ በቆንጆ ዲዛይን የተሰራ ቲ-ሸርት
> የሠሌዳ ማርከሮች

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


> የምርት /ዕቃ/ ልዩነት
> ብቃት /ቅልጥፍና/

ትዕይንቶች (በግድግዳ ወይም በቦርድ ላይ የተለጠፉ ወይም በሠልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱ)፡-
> የላቀ ጥራት > የላቀ ዲዛይን እና ምቹ አጠቃቀም
> የላቀ የደንበኞች አገልግሎት > የላቀ ብቃት /ቅልጥፍና/

ዝግጅት:-
> የቡድን አመቻቾችች፡- ይህ ክፍል፤ ማንነትን ጠንቅቆ ለማወቅ፣ ፈጠራን ለማበረታታት እና ሥራ
ፈጣሪዎችን የዚህ ትምህርት ደቀመዛሙርት ለማድረግ ጥሩ ዕድሎችን አካቷል፡፡ ይጠቀሙበት!
> ይህ ክፍል፤ የተመሳሳይ ሸሚዞችን ንፅፅር ያሳያል፡፡ ከየትኛው ሸሚዝ የትኛው እንደሚሻል ሥራ
ፈጣሪዎች እርስ በእርስ ላይስማሙ ይችላሉ፡፡ ለምርጫቸው /ለውሳኔያቸው/ በቂ ምክንያት መስጠት
መቻላቸውን ብቻ ያረጋግጡ፡፡
> ይህ ክፍል፤ ስለ ተሰጥኦዎች እና ክህሎቶች የአነስተኛ ቡድን ውይይቶችን አካቷል፡፡ ጊዜ ወስደው፤
ሥራ ፈጣሪዎች ራሳቸውን መለስ ብለው እንዲፈትሹ እና ያላቸውን ተሰጥኦ እንዲገነዘቡ
ያበረታቷቸው። ሥራ ፈጣሪዎች፤ አንዳቸው ሌላኛውን በመገምገም ግንዛቤ እንዲያገኙ ለማድረግ
ቡድኑን ማበረታታት ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ:-


> መዝ 139÷13-14
> ኤፌ 2÷10
> ምሳሌ 10÷4

ይምሩ:- ሁላችሁም እንደገና እንኳን ደህና መጣችሁ!

85
ይምሩ:- አሁን በተመራጭ አቅርቦት መርህ፤ ምርቶቻችንን /ዕቃዎቻችንን/ እና አገልግሎቶቻችንን
ከተወዳዳሪዎቻችን የተሻለ ተመራጭ እንዲሆኑ ማድረግ ስለሚያስችለን መንገድ እንወያያለን።

ይምሩ:- አንድ ምርት /ዕቃ/ ወይም አገልግሎት ተመራጭ አቅርቦት ሲኖረው፤ ከተመሳሳይ ምርቶች /ዕቃዎች/
እና አገልግሎቶች የተሻለ የሚያደርገው ጥራቶች አሉት።

ይምሩ:- ተመራጭ አቅርቦትን ለማሳደግ አስፈላጊ ነገሮች፡- ወደ አራቱ ተዕይንቶች ያመልክቷቸው

1) የላቀ ጥራት
2) የላቀ የመስተንግዶ አገልግሎት
3) የላቀ ዲዛይን እና ጠቀሜታ
4) የላቀ ቅልጥፍና

ይምሩ:- እነዚህ አራት ወሳኝ ነጥቦች፤ ለደንበኞች የሚቀርብ ምርትን /ዕቃን/ ልዩና የበለጠ ተመራጭ
የሚያደርጉ መሆን አለባቸው፡፡

ይምሩ:- አስታውሱ፤ “ትልቅ ህልም ይኑርህ” በሚለው የትምህርት ክፍል፤ እያንዳንዳችን የፈጠራ እና
የዲዛይን ልዩ ክህሎታችንን አውጥተን እንድንጠቀም እግዚአብሔር በአምሳሉ ድንቅ አድርጎ እንዴት
እንደፈጠረን ተወያይተናል፡፡

ይምሩ:- ስለ እግዚአብሔር ድንቅ የጥበብ ስራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ በመዝሙረ ዳዊት 139÷13-14 እንዲህ
ይላል፡-

“አቤቱ አንተ ኩላሊቴን ፍጥረሃልና÷ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል።ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና


አመሰግንሃለሁ፤ ስራህ ድንቅ ነው÷ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች፡፡”

ይምሩ:- የእግዚአብሔር የእጆቹ ስራ ውጤት ስለሆንን፤ ታላላቅ ነገሮችን የመስራት ክህሎት አለን!

ይምሩ:- በኤፌሶን መልዕክት 2÷10 ላይም እ ንዲሁ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ውጤት ስለመሆናችን
ይናገራል፡፡

“እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ
በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን፡፡”

ይምሩ:- ስለዚህ ጉዳይ በየቡድኖቻችሁ ተነጋገሩበት፡፡ እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን አስቀድሞ ያዘጋጀው


መልካም ሥራ ማለት ምን ማለት ይመስላችኋል? በእነዚህ መልካም ሥራዎች ለደንበኞቻችን እንዴት
መትረፍ እንችላለን? ለ8 ደቂቃዎች ያህል ተወያዩበት፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ8 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ትክክለኛ ደቀ መዛሙርት ለማፍራት ይህን ጊዜ ይጠቀሙበት።


እግዚአብሔር የፈጠራቸው ምን እንዲሆኑ ነው? ልዩ ተሰጥኦዎች እና ክህሎቶቻቸው ምንድን ናቸው?
እግዚአብሔር ምን እንዲያደርጉ ነው የጠራቸው? መጠራታቸውን ማወቃቸው ለደንበኞቻቸው ምርጡን
ምርት /ዕቃ/ ለማምረት /ለማቅረብ/ እንዴት ሊረዳቸው ይችላል? የዚህ አንኳር ነጥብ ስለ መስራት ጉዳይ
ሳይሆን ማንነትን ስለ መገንዘብ እና ከዚህ ግንዛቤ የመነጨ ተፈጥሯዊ መልካም ስራዎችን እየሰሩ መጓዝ
ስለመቻል ነው። ጉዳዩ የመንፈሳዊ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን በሁሉም የቢዝነስ ዘርፎች እና በቤት ውስጥ
ሕይወት ልህቀትን የመምረጥ ጉዳይ መሆኑን እንዲገነዘቡ ያግዟቸው።

86
ይምሩ:- እግዚአብሔር ውብና ድንቅ አድርጎ ፈጥሮናል። እርሱን ስንከተል፤ የተቸሩንን የፈጠራ ገጸበረከቶች
ተጠቅመን ቆንጆ እና ልዩ ምርቶችን /ዕቃዎችን/ ወይም አገልግሎቶችን መፍጠር እንችላለን።

ይምሩ:- በቢዝነሳችን ሆነ በግል ሕይወታችን፤ በምናከናውናቸው ማነኛውም ነገሮች ሁሉ ልህቀትን ማሳየት


እንችላለን፡፡ እናም በተቻለን መጠን ጥሩ ሆነውን ነገር ሁሉ ስናደርግ፤ የእግዚአብሔርን መልካምነት በእኛ
ህይወት ለሌሎች ማሳየት እንችላለን፡፡

ይምሩ:- በተመራጭ አቅርቦት መርህ፤ ደረጃውን የጠበቀና ስኬታማ ሥራን ለመስራት ትርፍ እንዴት ማምረት
እንደምንችል ስናስብ የሁለት የተለያዩ ምርቶች ምሳሌ እንመልከት።

ይምሩ:- ሁለት የተለያዩ የሴቶች ሸሚዝ ይያዙ። አንደኛው ጥራት ያለው እና በጥሩ ዲዛይን የተሰራ ነው፤
ሁለተኛው ተራ ልብስ ነው፤ ምናልባትም የተቀደደና የተጨማደደ ወ.ዘ.ተ. ሊሆን ይችላል- በመስቀያ
የተንጠለጠሉ ሁለት ሸሚዞች፡፡
ይምሩ:- ከሁለቱ ሸሚዞች የትኛው ተመራጭ አቅርቦት አለው? ለምን? ከሌላኛው ይልቅ ይህንን ሸሚዝ
ለመግዛት ያነሳሳችሁ ምክንያት ምንድን ነው?

ይምሩ:- መልስ እንዲሰጡ ያድርጉ፡፡ በሥራ ፈጣሪዎች ያልተመረጠውን ሸሚዝ ያስወግዱ፡፡

ይምሩ:- አሁን ይህ ሸሚዝ ከዛሬ ጀምሮ እስከ አንድ ዓመት ድረስ በገበያ ላይ እየተሸጠ እንዳለ አድርገን
እናስብ፡፡ አሁን ደግሞ አዲስ ሸሚዝ በአዲስ ዲዛይን እና ከለር በገበያ ላይ አለ። ከመጀመሪያው የበለጠ ሌላ
ማራኪ ሸሚዝ ከፍ አድርገው ያሳይዋቸው፡፡ በመስቀያ የተንጠለጠለ ሸሚዝ፡፡

ይምሩ:- ሰዎች የትኛውን ሸሚዝ ወደ መግዛት ያዘነብላሉ?(አብዛኞቹ “አዲሱን” በማለት ይመልሳሉ)፡፡

ይምሩ:- ከዚህ ቀደም፤ በጎረቤቶቻችሁ ወይም በአከባቢያችሁ ያሉ ሱቆች ውስጥ የሚሸጡ ሁለት ተመሳሳይ
ዕቃዎችን እና አንደኛው ስላለው ተመራጭ አቅርቦት በምሳሌነት በማንሳት በየቡድኖቻችሁ ተወያዩበት፡፡
አንዱ ከሌላው በተሻለ እንዴት ሊሸጥ እንደቻለ ተነጋገሩ። ስለዚህ ጉዳይ ለመነጋገር 5 ደቂቃዎች ያህል
ይስጧቸው፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ5 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ስላስተዋሉት የተመራጭ አቅርቦት ግብይትን አስመልክቶ የሚደረጉ
ውይይቶችን ይምሩ፡፡ (ለምሳሌ፡- ሞባይል ስልኮች፣ ሳሙና፣? ላሞች፣ ስኳር፣ ወዘተ.) አስፈላጊ ከሆነ
ምሳሌያዊ ናሙናዎችን በማቅረብ አጉልተው ያሳዩ፡፡

ይምሩ:- በገበያ ላይ የምናቀርባቸውን ምርቶች /ዕቃዎች/ እንዴት ማሻሻል እንደሚያስፈልገን ሁል ጊዜ ማሰብ


ያስፈልገናል ፡፡ ሌሎች ቢዝነሶች የፈጠራ ሥራቸውን በመጠቀም ምርቶቻቸውን ያለማቋረጥ በማሻሻል
በውድድር አሸናፊ ሆነው ለመውጣት ስለሚሞክሩ፤ የተመራጭ አቅርቦት ጠቀሜታው ጊዜያዊ ነው፡፡

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ ሁሉም ሰው እንዳየው ወዲያው ሊገዛው የሚችል አዲስ ቀሚስ አምርተን ቡቲክ ላይ
ልናስቀምጥ እንችላለን፡፡

ይምሩ:- ይሁን እንጅ፤ ያንኑ ቀሚስ ለብዙ ወራት መሸጣችንን ከቀጠልን፤ የገዥዎች /የሸማቾች/ ቁጥር
ይቀንሳል።

ይምሩ:- ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል? (ሰዎች ቀደም ሲል ገዝተውታል፣ አሁን ፋሽኑ አልፏል፣ የሚለበስበት
ወቅት አይደለም (ክረምት፡ በጋ…) ፣ ወዘተ.)

87
ይምሩ:-ምላሽ ይቀበሉና፣ በአድናቆት ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ተመራጭ አቅርቦትን አስጠብቆ ለማስቀጠል፤ ምርቶቻችንን፣ አገልግሎቶቻችንን እና


ዲዛይኖቻችንን ያለማቋረጥ ማሻሻል እና መለወጥ ይኖርብናል።

ልምምድ

ይምሩ:- በሠልጣኞች መጽሐፍ ገጽ ____ ላይ ባለው ባዶ ቦታ፤ በቢዝነሶቻችሁ ልትሸጡት የምትፈልጉትን


ምርት /ዕቃ/ ወይም የምትሰጡትን አገልግሎት በስዕል ግለጹ። ከዚያም ተመራጭ አቅርቦት እንዲኖረው በዚያ
ምርት ላይ አንድ ማሻሻያ ወይም ዲዛይን ጨምራችሁ እንደገና ሌላ ስዕል ሳሉ። ለዚህም 5 ደቂቃዎች
ሰጥቻችኋለሁ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ5 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ተሳታፊዎች አሁን እየሸጧቸው ያሉትን ወይም ወደፊት
የሚሸጧቸውን ነገሮች እንዲያስቡ እና መሳል እንዲጀምሩ ያበረታቷቸው። የፈጠራ ክህሎቶቻቸውን
ተጠቅመው ማሻሻያ ሲያደርጉ ማየት እንፈልጋለን።

ይምሩ:- ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ስለገለጸበት ሥዕል የሚነግረን አንድ ሰው ይኖራል?

ይምሩ:- አንድ ሰው ተነስቶ፤ ስለ ምርቱ ወይም አገልግሎቱ እንዲገልጽ ያድርጉ፡፡

ይምሩ:- ዓለማችን በፍጥነት የምትለዋወጥ እንደመሆኗ መጠን፤ ቢዝነሶቻችሁም እንዲሁ መሻሻል መቻል
አለባቸው።

ይምሩ:- ተመራጭ አቅርቦትን አስጠብቆ የመቀጠያ አንዱ መንገድ፤ በተመሳሳይ ምርት ተወዳዳሪ የሆኑ
ነጋዴዎች ከሚያቀርቧቸው ምርቶች በአዎንታዊ ጎኑ የተለዩ ምርቶችን መሸጥ መቻል ነው።

ይምሩ:- በመንገዳችሁ ላይ ያሉ ሱቆች ________ (ብዙ ጊዜ የሚሸጡ ዕቃዎች፡- ዘይት፣ ስኳር እና ጨው)
የሚሸጡ ከሆኑ እናንተም ተመሳሳይ ዕቃ (በተመሳሳይ መልኩ ብዙ ጊዜ የሚሸጡ ዕቃዎች፡- ዘይት፣ ስኳር እና
ጨው) ለመሸጥ ሱቅ መክፈት አለባችሁ? የለብንም!

ይምሩ:- ለምን የለብንም?

ይምሩ:- ለምን እንደማይኖረባቸው ለሚያስረዱ ሁለት ተሳታፊዎች ዕድል ይስጡ፤ እናም ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- በምንሸጣቸው ነገሮች ላይ ልዩነቶችን መፍጠር፤ የምርት /ዕቃ/ ልዩነት ይባላል፡፡ የምርት /ዕቃ/
ልዩነት፤ ምርቶቻችንን ወይም አገልግሎቶቻችንን ከተፎካካሪዎች አቅርቦት የተሻለ ያደርጋል።

ይምሩ:- ከፍ ያለ ለውጥ በማድረግ ማለትም፤ የደንበኛ አገልግሎት አሠጣጥን በማሻሻል ወይም በላቀ ዲዛይን
በማምጣት፤ በራሳችን ምርት ወይም አገልግሎት ላይ ልዩነትን መፍጠር እንደምንችል ያስታውሱ፡፡

ይምሩ:- ተመራጭ አቅርቦትን ለማግኘት ሌላ ተጨማሪ ስልት አለ ፤ ያም ይበልጥ ቀልጣፋ መሆን ነው።
አንድን ስራ ሠርቶ ለማጠናቀቅ እና ተፈላጊ ውጤት ለማምጣት የምናውለው ጊዜና ጉልበት ቅልጥፍና
ይባላል፡፡

88
ይምሩ:- ለምሳሌ፤ ልብስ ሠፊ ከሆንኩ፤ ቅልጥፍናዬ የሚለካው አንድን ቀሚስ ሰፍቶ ለመጨረስ ምን ያህል
ጊዜ ያህል ሊፈጅብኝ ይችላል በሚል ይሆናል፡፡ ወይም ያንን ቀሚስ ለመሥራት የምጠቀመው የጨርቅ መጠን
ሊሆን ይችላል።

ይምሩ:- መጽሐፈ ምሳሌ 10÷4፤ “የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፤ የትጉ እጅ ግን ባለጠጋ ታደርጋለች”
በማለት ይነግረናል።

ይምሩ:- ክህሎታችንን በማሻሻል ቅልጥፍናን ከፍ ማድረግ እንችላለን፡፡ ይህም ለቢዝነሳችን ተመራጭ


አቅርቦትን ይፈጥርልናል።

ይምሩ:- አንድን ነገር ደግመን ደጋግመን ማድረግ፤ ያንን ስራ በፍጥነት እና በላቀ ክህሎት ለማከናወን
ያስችለናል፡፡ ይህም በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ብዙ ምርቶችን ማምረት እንችላለን። በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ
ብዙ ምርቶችን ማምረት ከቻልን ደግሞ፤ ለዚያ ምርት የምንተምነው የመሸጫ ዋጋ ይቀንሳል።

ይምሩ:- የቅልጥፍና አንዱ መንገድ፤ በዘላቂነት ጥረት ማድረግ እና ታታሪ መሆን ነው። ይህም ጥሩ ትርፍ
ለማግኘት እና ገቢያችንን ለማሳደግ የተሻለ እድል ይፈጥርልናል። ሌላው የቅልጥፍና መንገድ ጊዜን በአግባቡ
መጠቀም መቻል ነው።

ይምሩ:- አንድን ነገር በከፍተኛ ጥረት ደጋግማችሁ በመስራት ስላዳበራችሁት ክህሎት በቡድናችን ውስጥ
እስቲ እንወያይበት። ከዚያም ጊዜያችሁን በአግባቡ በመጠቀም የበለጠ ቀልጣፋ መሆን የሚያስችሉ ሌሎች
መንገዶችን ያጋሩ። ከ 3 እስከ 4 ደቂቃዎች ተጠቀሙ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ5 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ከተግባራዊ ልምምድ ያዳበሯቸውን ክህሎቶች እንዲያጋሩ


ተሳታፊዎችን ይጠይቋቸው፡፡ ከዚያም፤ ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ተግባራት
የከናወኑበትን በምሳሌ እንዲገልጹ ይጠይቋቸው።

ይምሩ:- በተግባራዊ ልምምድ ቀልጣፋ የሆናችሁበትን ክህሎት፤ ከየቡድናችሁ አንድ አንድ ሰው ልትጋሩን
ትችላላችሁ?

ይምሩ:- ምላሾቻቸውን ይቀበሉ፡፡

ይምሩ:- አቅርቦቱ ተመራጭ የሆነ እና በታማኝ ደንበኞቻችን በቋሚነት የሚፈለግን ምርት /ዕቃ/ አንድ ጊዜ
ከፈጠርን፤ ደረጃችንን ጠብቀን መቆየት ይበልጥ ቀላል ይሆንልናል።

ይምሩ:- ጥሩ የደንበኞች እንክብካቤ፣ ጥራት ያ ለው፣ ተመጣጣኝ ዋጋ እና ጥሩ የምርት ልዩነት ላለው ቢዝነስ፤
ደንበኞች በደንበኝነት የመዝለቅ ዕድላቸው ሠፊ ነው፡፡

ልምምድ

ይምሩ:- አሁን የልምምድ ጊዜ ነው! እየሸጣችሁት ስላለው ምርት ወይም እየሰጣችሁት ስላለው አገልግሎት
ያለዚያም ልትከፍቱት ስላቀዳችሁት አዲስ ቢዝነስ አስቡ፡፡ የምርት ወይም አገልግሎት ተመራጭ

89
አቅርቦቶቻችሁን ማሻሻል ስለምትችሉባቸው መንገዶች በመጽሐፍቶቻችሁ መልመጃዎች ላይ በስዕል ወይም
በጽሑፍ ግለጹ።

ይምሩ:- እስከ አሁን ስለ የተወያየንባቸው የተመራጭ አቅርቦት አጠቃላይ ተጽዕኖዎች ግንዛቤ ውስጥ
ማስገባትን አትርሱ፡፡ በአንድነት ከልሷቸው! ለዚህ መልመጃ 5 ደቂቃዎች ያህል ተጠቀሙ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ5 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ይህንን በሚገባ መምራት ያስፈልግዎታል፡፡ ተሳታፊዎች ወደፊተ
በሚኖሯቸው ቢዝነሶች ውስጥ ምርቶቻቸው ምን እንደሚመስሉ በዲዛይን እንዲገልጹ ያድርጉ፡፡ የእያንዳንዱ
ተመራጭ አቅርቦት ገጽታ ምን መምሰል እንደሚኖርበት ሁሉም ሃሳቡን በመግለጽ እንዲሳተፍ ያበረታቱ።
የሚያቀርቧቸውን ምርቶች /ዕቃዎች/ ጥራት፣ ውበት ወዘተ. በስዕል እንዲገልጹ ያድርጉ፡፡

ይምሩ:- እስከ አሁን የቡድን ውይይቶችን አካሂደናል፤ ከምርት ጋር በተያያዘ ቡድኑ የደረሰባቸውን
ድምዳሜዎች ወደ መድረኩ መጥቶ ሊያካፍለን የሚችል አንድ ሰው ይኖራል?

ይምሩ:- በጎ ፈቃደኛው ወደ ፊት እንዲመጣ ያድርጉ። ከዚያም ቡድኑ ስለ ምርት ያለውን እሳቤ እንዲያጋራ
ያድርጉ። ጊዜው እንደፈቀደ መጠን የሚከተሉትን ሰፋ ያሉ ጥያቄዎች ይጠይቁ፡፡

ይምሩ:- እነዚህን ምርቶች ተመራጭ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው? ከሌሎቹስ ምን የተሻለ ያደርገዋል?
በገበያ ላይ ካሉ ሌሎች ምርቶችስ በምን ይለያል?

ይምሩ:- ለደንበኞች የምንሰጠው አገልግሎት ምን ይምስላል? ከተፎካካሪዎቻችን ይልቅ የእኛን አገልግሎት


የተሻለ የሚያደርገው ምንድነው?

ይምሩ:- ቅልጥፍናን ለማግኘት ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?

ይምሩ:- ይህ በጥሩ ሁኔታ ከተከናወነ እና ጊዜ ካለዎት፤ ሌላ በጎ ፈቃደኛ ወደ መድረኩ መጥቶ በተጨማሪ


እንዲገልጽ ማድረግ ይችላሉ፡፡

ይምሩ:- ሁለት ተሳታፊዎች፤ ከዚህ የትምህርት ክፍል ስለ ቀሰማችሁት አንድ ነገር ልትነግሩኝ ትችላላችሁ?

ይምሩ:- ሁለት ሰዎችን ይጥሩ እና አንድ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ ሃሳባቸውን በመደገፍ፤ ያጋሯቸውን ነጥቦች
እንደገና ያብራሩ፡፡

ይምሩ:- ዋው! ሁላችሁም አስደናቂ ስራ ሰርታችኋል፡፡ በሚቀጥለው ክፍለ-ጊዜ፤ ስለ ሒሳብ አመዘጋገብ


እንማራለን፡፡

90
// ክፍል 11 //
የሒሳብ መዝገብ አያያዝ

የሚወስደው ጊዜ፡- 1 ሠዓት

ግቦች:-
> ተሳታፊዎች፤ ስለ መሠረታዊ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ አስፈላጊነት ግንዛቤ ያገኛሉ፡፡
> ተሳታፊዎች፤ ሁሉንም ገቢ እና ወጪዎቻቸውን እንዴት መከታተል እንደሚችሉ ያውቃሉ።

አቅርቦቶች፡-
> እስክሪብቶዎች > ነጭ ሠሌዳ
> የሠልጣኞች መጽሐፍት > የነጭ ሠሌዳ ማርከሮች
> እንደ ከረሚላ ያሉ ጣፋጮች ነገሮች > የሒሳብ መደመሪያ ካልኩሌተሮች

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


> በጀት > ወጪ
> የሒሳብ አመዘጋገብ > ገቢ
> ጆርናል > ሚዛን /ባላንስ/

ትዕይንቶች(በግድግዳ ወይም በቦርድ ላይ የተለጠፉ ወይም በሠልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱ)፡-


> የሒሳብ አመዘጋገብ ጆርናል > ደረሰኝ /ናሙና/
> የብር ቦርሳ

ዝግጅት:-
> የሠልጣኞችን መጽሐፍ ይውሰዱና “የሜሪ የሒሳብ መዝገብ፤” የሚለውን (ገቢ እና ወጪ በተናጠል
ያሉበት) ክፍል ፤በኋላ በጋራ ለመሙላት እንዲያመች፤ በነጭ ሠሌዳው ላይ ይጻፉ፡፡
> ከተቻለ እና የሚገኝ ከሆነ፣ ቀላል የሒሳብ መዝገብ፤ ለእያንዳንዱ ሠልጣኝ አድለው በግል
እንዲጠቀሙ ቢያደርጉ እንመክራለን፡፡

91
ይምሩ:- ጤና ይስጥልኝ፤ በድጋሚ ሁላችሁም እንኳን ደህና መጣችሁ! እንደገና በመገናኘታችን ደስ ብሎኛል፡፡

ይምሩ:- አሁን ስለ ሒሳብ አመዘጋገብ እንነጋገራለን፡፡

ይምሩ:- የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ምን ማለት እንደሆነ እና ለምን እንደሚጠቅም ሊነግረኝ የሚችል ሰው
አለ?

ይምሩ:- ለአፍታ ቆም ይበሉ እና ምላሾችን ይቀበሉ፡፡ ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆትና ከምስጋና ጋር ጣፋጭ
ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ከቢዝነሳችን የምናገኘውን ገንዘብ እና ለዚሁ ቢዝነስ የምናወጣውን ብር የማንከታተል ከሆነ


ስኬታማ የቢዝነስ ሰዎች ልንሆን አንችልም፡፡ ማንኛውም ቢዝነስ እነዚህን ሁለት ነገሮች ሁልጊዜ የያዘ ነው፡-
ገቢ እና ወጪ።

ይምሩ:- ወደ ቢዝነሳችን የሚገባ ማንኛውም ገንዘብ ገቢ ይባላል። ለምሳሌ፤ ዳቦ የምንሸጥ ከሆነ፤ ሰዎች
ዳቧችንን ለመግዛት የሚከፍሉን ገንዘብ ገቢ ነው፡፡

ይምሩ:- ከቢዝነሳችን ውስጥ የሚወጣ ማንኛውም ገንዘብ ወጪ ይባላል። ለምሳሌ፤ ዳቦ ለመሸጥ


በመጀመሪያ ዱቄት መግዛት ይኖርብናል፡፡ ዳቦ ለማዘጋጀት ዱቄት መግዣ ያወጣነው ገንዘብ ወጪ ነው፡፡

ይምሩ:- የማንኛውም ቢዝነስ ግብ፤ ከወጪ የበለጠ ገቢ እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡

ይምሩ:- ቢዝነሳችን ትርፋማ መሆኑን የማወቂያ ብቸኛው መንገድ፤ ትክክለኛ የሒሳብ ምዝገባ ማድረግ ነው፡፡
ትክክለኛ የሒሳብ ምዝገባ ማድረግ፤ ወደፊት የበለጠ ትርፋማ መሆን በሚያስችል መልኩ ቢዝነሳችንን
እንዴት እንደምንለውጠው ለማወቅ ይረዳናል፡፡

ይምሩ:- ከቢዝነሳችን ወጪ አድርገን ክፍያ ስንፈጽም ወይም ሽያጭ ባካሄድን ቁጥር፤ የተሸጠበትን ወይም
የተገዛበትን ዝርዝር መግለጫ ከቀን ጋር መመዝገብ ያስፈልገናል፡፡

ይምሩ:- ስለ ሒሳብ መዝገብ አያያዝ በዚህ ሠሌዳ ላይ በምሳሌ እናቀርባለን፡፡ በዚህ ምሳሌ መሠረት፤ “ሜሪ
ምርጥ ዳቦ ቤት” የሚባል ቢዝነስ አለን፡፡ የ ሠልጣኞች መጽሐፍ ገጽ ___ ላይ ክፈቱና ወጪ አመዘጋገብን
አንድ ላይ በተግባር እንለማመድ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- በሠልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘውን የሂሳብ አመዘጋገብ የ“ወጪ” ክፍሉን
በመፈለግ ተሳታፊዎችን ያግዙ፡፡

ይምሩ:- የሒሳብ መዝገብ አያያዙ እንዴት እንደሚሰራ ለማየት የ “ሜሪ ምርጥ ዳቦ ቤት” ን እንጎብኝ፡፡ የቀረፃ
ድራማውን ድራማ ለማከናወን ፈቃደኞች ወደ ግንባር መምጣት የሚጠቁሙ ምልክቶች ፡፡

ድራማ + መልመጃ

ሜሪ፡- ዛሬ ዳቦ ቤቴን ከመከፈቴ በፊት ብዙ ምሠራቸው ነገሮች አሉ፡፡ ዱቄት አልቆብኛል፤ ሁለት አዳዲስ
የዳቦ መጋገሪያ ምጣዶችንም መግዛት አለብኝ፡፡

92
ይምሩ:- ሜሪ የገንዘብ ቦርሳዋን እና የሒሳብ መዝገቧን ይዛ ወደ ገበያ ሄደች።

ሜሪ፡- ዛሬ ከባድ ዝናብ እየዘነበ ስለሆነ ወደ ገበያ ለመሄድ ሚኒባስ መያዝ አለብኝ፡፡

ሚኒባስ ሾፌር፡- ሜሪን አሳፍሮ እየነዳ እነዳለ ያስመስላል፡፡ የተጓዙ በማስመሰል፤ ከአንዱ የክፍል ማዕዘን ወደ
ሌላውኛው ማዕዘን ይንቀሳቀሳሉ፡፡

ሜሪ፡- አመሠግናለሁ! ሒሳቡን ለሾፌሩ ከፍላ፣ ከሚኒባሱ ትወጣና የሒሳብ መዝገቧ ላይ የሆነ ነገር
ትጽፋለች፡፡

ይምሩ:- እሺ፣ አቁሙ! ሜሪ እንቅስቃሴዋን ታቆማለች፡፡ እሺ፤ ሜሪ ምን እየጻፈች እንደሆ ማን ሊነግረኝ


ይችላል? ምላሾችን ይቀበሉ፡፡

ይምሩ:- በትክክል! በሒሳብ መዝገቧ ላይ ያሰፈረችው፤ የታክሲ ወጪዋን ነበር፡፡ ለምን ወጪ ሆነ?

ይምሩ:- ምላሾችን ይቀበሉ፡፡ ከምስጋና እና አድናቆት ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- በትክክል! በሒሳብ መዝገቧ ላይ ያሰፈረችው፤ የታክሲ ወጪዋን ነበር፡፡ ለምን ወጪ ሆነ?

ይምሩ:- ምላሾችን ይቀበሉ፡፡ ከምስጋና እና አድናቆት ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ትክክል! ምክንያቱም፤ ሜሪ ቢዝነሷን ለማካሄድ የምታጠፋው ገንዘብ ስለሆነ ነው፡፡

ይምሩ:- እንደ ቢዝነስ ባለቤቶች፤ ግዥ ለመፈጸም የሚወጡ የትራንስፖርት ክፍያዎችን ጨምሮ፤


ለቢዝነሳችን የምናወጣቸውን እያንዳንዳቸውን ወጪዎች በሒሳብ መዝገብ ላይ መመዝገብ ይኖርብናል፡፡

ይምሩ:- እስቲ የሜሪን የሒሳብ መዝገብ ከእርሷ ጋር አብረን እንሙላ፡፡ በሠልጣኞች መጽሐፍ ገጽ
______________ ላይ ያለውን እንስራ፡፡

ይምሩ:- ትክክለኛ ምዝገባ ማድረግ፤ በዝርዝር መጻፍ ማለት መሆኑን አስታውሱ፡፡ እያንዳንዱን ወጪ
ስንመዘግብ፤ ቀን፣ መግለጫ እና የወጭውን መጠን ማካተት አለብን።

ይምሩ:- ስለዚህ፤ ቀኑን እዚህ ላይ ______________ እንፅፋለን፡፡ ግብይት የተፈጸመበትን ቀን (የዛሬን ቀን


ይጠቀሙ) በሠሌዳው ላይ “ቀን” በሚለው አምድ ስር ይጻፉ። ይህን በሠልጣኞች መጽሐፍ ላይም እንዲሁ
ያስፍሩ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ሁሉም ተሳታፊዎች እየተከታተሉዎት መሆናቸውን እና ትክክለኛውን መረጃ እየሞሉ


መሆናቸውን ያረጋግጡ፡

ይምሩ:- በመቀጠል፤ የወጪውን ምክንያት እንጽፋለን። እናም፤ “የታክሲ ክፍያ” በማለት እናሰፍራለን፡፡
“መግለጫ” በሚለው አምድ ስር “የታክሲ ክፍያ” በማለት ይጻፉ።

ይምሩ:- እና በመጨረሻም፤ የወጪውን መጠን መጻፍ ያስፈልገናል። በመጀመሪያው መስመር ላይ


__________ ይጻፉ (በአካባቢው የዋጋ ተመን መሠረት ይሙሉ)። ሁሉም ይህን አድርጓል? በጣም ጥሩ!
ቀጥሎ፤ ሜሪ ምን እንደምታደርግ እንመልከት።

ይምሩ:- እሺ፤ ጀምሩ!! ተዋንያኖች ካቆሙበት ይቀጥላሉ፡፡

93
ይምሩ:- እና በመጨረሻም፤ የወጪውን መጠን መጻፍ ያስፈልገናል። በመጀመሪያው መስመር ላይ
__________ ይጻፉ ሜሪ፡- የሒሳብ ምዝገባዋን አጠናቅቃ፤ መደብር ውስጥ ሻጭ ወደ ሆነው ወደ ጆርጅ
ትሄዳለች፡፡

ጆርጅ፡- ሠላም፤ ሜሪ! ምን ልርዳሽ?

ሜሪ፡- ሠላም ጆርጅ! የዳቦ ዱቄት አልቆብኛል፡፡ አስር ኪሎ መግዛት እችላለሁ?

ጆርጅ፡- በሚገባ፤ ዋጋው ____ ብር (የአከባቢው የዋጋ ተመን) ነው፡፡.

ሜሪ፡- በጣም አመሰግናለሁ! ክፍያውን ፈጽማ፤ በሒሳብ መዝገቧ ላይ ትመዘግባለች፡፡

ይምሩ:- አሁን ... አቁሙ!! ሜሪ እና የመደብር ሠራተኛው ተውኔታቸውን ያቆማሉ፡፡ እሺ፤ አሁንስ ሜሪ ምን
እየጻፈች ነው?

ይምሩ:- ምላሾችን ይቀበሉ፡፡ ከምስጋና እና አድናቆት ጋርም ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ትክክል! ይህን ሌላ ወጪ በሒሳብ መዝገቧ ላይ እያሰፈረች ነው፡፡

ይምሩ:- ወደ ሒሳብ አመዘጋገባችን እንመለስ እና ቀጥሎ ይህን ወጭ እንሙላ። አሁንም እንደበፊቱ፤ ቀንን
(የዛሬን ቀን) ከማስፈር ጀምሮ፣ በመግለጫ ዓምድ ላይ “ዱቄት” እንዲሁም በወጪ ዓምድ ላይ የአከባቢውን
የዋጋ ተመን በነጭ ሠሌዳው ላይ ያሳዩዋቸው፡፡

ይምሩ:- ይህ ለሁላችሁም ትክክል ነው? እሺ፤ ይህንን በእናንተም የሒሳብ መዝገብ ውስጥ መጻፋችሁን
አረጋግጡ፡፡

ይምሩ:- ሜሪ ከዱቄት በተጨማሪ ሌላ ብትገዛስ? ለምሳሌ፤ ጨው ወይም እርሾ ከገዛች፤ በዚያው መስመር
ላይ ዕቃዎቹን በዝርዝር እናሰፍራቸዋለን፡፡ ከአንድ ሱቅ የተገዙ ሁሉም ወጭዎች፤ በአንድ መስመር ላይ ሊጻፉ
ይችላሉ፡፡

ይምሩ:- እሺ፤ ጀምሩ!! ተዋናዮች ትወናቸውን ይቀጥላሉ።

ሜሪ:- የሒሳብ ምዝገባዋን እንዳጠናቀቀች፤ አን ወደ ተባለችው የቤት ቁሳቁስ ሻጭ ሴት ሄደች፡፡

ሜሪ:- ሠላም፤ አን፡፡ እንዴት ነሽ?

አን:- በጣም ደህና ነኝ ሜሪ! ምን ልስጥሽ?

ሜሪ:- ቢዝነሴ እየሰፋ ስለመጣ፤ ሁለት ተጨማሪ የዳቦ መጋገሪያ ምጣድ መግዛት እፈልጋለሁ! ሒሳቡን ለአን
ትከፍላለች፡፡

አን:- በጣም ጥሩ፤ ሜሪ! ለስራሽ ምቹ የሆኑ ሁለት ምርጥ የዳቦ መጋገሪያ ምጣዶች ይሄው፡፡ ዋጋው
________ ብር (ለአከባቢው የሚመጥን ዋጋ ይሙሉ) ነው። አን ድስቶቹን ለሜሪ ትሰጣለች፡፡ ሜሪ ሒሳቡን
ትከፍላለች፡፡ አን ደረሠኝ ቆርጣ ለሜሪ ትሰጣለች፡፡

94
ሜሪ:- አመሰግናለሁ፤ አን! በየጊዜው ለምገዛቸው ዕቃዎች ሁሉ በጥሩ ዋጋ ስለምትሸጪልኝ በጣም
አመሰግናለሁ፡፡ በሒሳብ መዝገቧ ላይ መዝግባ እንደጨረሰች ደረሰኙን በመዝገቧ ውስጥ በጥንቃቄ ታመዝገቧ
ስቀምጣለች፡፡

ይምሩ:- እሺ፤ አቁሙ!! ሜሪ እና አን ትወናቸውን ያቆማሉ፡፡ እሺ፤ ሜሪ ሌላ ወጪ እየመዘገበች ነው! እኛም


እንዲሁ እንመዝግብ፡፡

ይምሩ:- አሁንም እንደቅድሙ፤ ከቀን (የዛሬን ቀን) ጀምሮ፣ በመግለጫ ዓምዱ ላይ “2 ምጣዶች” እንዲሁም
በወጪ ዓምድ ላይ የአከባቢውን የዋጋ ተመን በነጭ ሠሌዳው ላይ ያሳዩዋቸው፡፡

ይምሩ:- እያንዳንዱ ሰው ይህን ምዝገባ እንዳጠናቀቀ፤ ተዋንያኑን አመስግነው ወደ መቀመጫቸው


እንዲመለሱ ያድርጉ።

ይምሩ:- ስለዚህ አሁን፤ ወጪዎቻችሁን እንዴት መመዝገብ እንደምትችሉ ተገንዝባችኋል፡፡ ሜሪ ሊኖሩባት


የሚችሉ ሌሎች የወጪ ምሳሌዎች ምንድን ናቸው

ይምሩ:- ሶስት ወይም አራት ፈቃደኛ ተሳታፊዎች ምላሽ እንዲሰጡ ያድርጉ፡፡ ከምስጋና እና አድናቆት ጋር
ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- መልካም! እነዚህ ሁሉ ወጭዎች ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ደረሰኝ (ማለትም ለአንድ ለከፈላችሁበት
ነገር የሚያረጋግጥ ወረቀት) ልናገኝ እንችላለን። ሌላ ጊዜ ደግሞ፤ ​በሜሪ ሁኔታ እንደተመለከትነው፤
የማናገኝበት ጊዜ ይኖራል፡፡ ደረሠኝ በምታገኙበት ጊዜ፤ በደረሠኙ ላይ የሰፈሩትን መረጃዎች በትክክል
መመዝገብና ደረሠኙን ለማስረጃ ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው፡፡

ይምሩ:- የሒሳብ መዝገብ አያያዝ፤ ወጪን ተከታትሎ መመዝገብ ብቻ አይደለም። ገቢዎቻችንን


የምንመዘግበውም በዚሁ ነው። ገቢ ምን ማለት እንደሆነ የሚያስታውሰን ማን ነው? ምላሽ ይቀበሉ፡፡

ይምሩ:- ወደ ሜሪ የዳቦ መጋገሪያና መሸጫ ሱቅ እንመለስ እና ገቢ እንዴት እንደሚመዘገብ እንመልከት፡፡


አንድ ደንበኛ ወደ ሱቁ መጥቶ 10 ዳቦ በ _____ ብር ቢገዛ፤ እንዴት እንመዘግበዋለን?

ይምሩ:- አሁንም እንደ ቅድሙ፤ በነጭ ሠሌዳው ላይ ያሳዩዋቸው፡፡ ነገር ግን አዲስ የ “ገቢ” ዝርዝር ያዘጋጁ።
በመጀመሪያ ቀኑን ይጻፉ (የዛሬውን ቀን)፣ ከዚያም በመግለጫ ዓምዱ ላይ “የ10 ዳቦ ሽያጭ”፣ እንዲሁም
በገቢ ዓምድ ላይ በአከባቢው የዋጋ ተመን መሠረት ዋጋውን በነጭ ሠሌዳው ላይ ይጻፉ፡፡

ይምሩ:- ሽያጩ ገንዘብ ያስገኘ እንደመሆኑ መጠን፤ በገቢ ይመዘገባል።

ይምሩ:- በ “ገቢ” አምድ ስር ጠቅላላ ድምሩን ይጻፉ።

ይምሩ:- ሜሪ ዛሬ ለሁለት ተጨማሪ ደንበኞች አምስት አምስት ዳቦ ብትሸጥ፤ እንዴት እንመዘግበዋለን?

ይምሩ:- እያንዳንዱን ተጨማሪ የሽያጭ አመዘጋገብ ያሳዩዋቸው። ሁል ጊዜም ከቀን (ከዛሬ ቀን) ይጀምሩ፤
ከዚያም የመግለጫ ዓምድ እና በአከባቢው ተመን መሠረት ዋጋውን ያስፍሩ።

95
ቡድን አመቻቾች፡- በነጭ ሠሌዳው ላይ የሰፈሩትን ሦስቱንም ሽያጮች ተሳታፊዎች መገልበጣቸውን
ያረጋግጡ፡፡ ለጥረታቸው አድናቆት ይስጡ!

ይምሩ:- በሠልጣኞች መጻሕፍቶቻችሁ ውስጥ፤ በወጪ አምድ ስር ሶስት ዝርዝሮች (የትራንስፖረት ወጪ፣
ዱቄት ግዥ፣ ቤት ኪራይ) እና ሶስት የገቢ ዝርዝሮች (ሶስት የተለያዩ ሽያጮች) ሊኖሯችሁ ይገባል፡፡

ይምሩ:- በገሀዱ የስራ እንቅስቃሴያችሁ ውስጥ ግን በወር ውስጥ የሚኖሯችሁን ወጪ እና ገቢዎች በሙሉ
ተከታትላችሁ ትመዘግባላችሁ፡፡ ስለዚህ ከዚህ የበለጡ ብዙ ዝርዝሮች ይኖሯችኋል ማለት ነው። ለዛሬው ግን
ቀለል እናደርገዋለን፡፡

ልምምድ

ይምሩ:- አሁን በሒሳብ መዝገባችን የያዝናቸውን ገቢ እና ወጪዎች የሂሳብ ባላንስ ወይም ሚዛን መስራት
ይኖርብናል፡፡

ይምሩ:- የሂሳብ ባላንስ ወይም ሚዛን መስራት ማለት፤ በወሩ መጨረሻ ላይ ምን ያህል ገንዘብ እንዳተረፍን
ወይም ምን ያህል እንደከሰርን ለይተን ማወቅ ማለት ነው።

ይምሩ:- ይህን ለማድረግ ደግሞ፤ በመጀመሪያ ሁሉንም ወጪዎቻችንን እንደምራለን፡፡ የእነዚህን ሦስት
የዘረዘሩ ወጪዎች ጠቅላላ ድምር ማን ሊነግረኝ ይችላል?

ይምሩ:- በጣም ጥሩ! ልክ ነው፡፡ ጠቅላላ ወጪያችን __________ ነው።

ይምሩ:- በመቀጠል፤ ሁሉንም ገቢዎቻችንን እንደምራለን። ከነዚህ ሦስት ሽያጮች ያገኘነውን ጠቅላላ ገቢስ
ሊነግርኝ የሚችል ማን ነው?

ይምሩ:- በጣም ጥሩ! ልክ ነው፡፡ ጠቅላላ ገቢያችን __________ ነው።

ይምሩ:- አሁን በቡድኖቻችሁ በመሆን፤ ከጠቅላላው ገቢ ጠቅላላ ወጪን በመቀነስ የሂሳብ ባላንሱን
እንድትሰሩት እፈልጋለሁ ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ2 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ይህን ሒሳብ ለየቡድኖቻችሁ በደንብ ማስረዳት የእናንተ ድርሻ ነው
፡፡

ይምሩ:- የሂሳብ ባላንሳችን ምንድን ነው? ፖዘቲቭ ወይስ ነጌቲቭ?

ይምሩ:- ሁሉም ሰው አንድ ዓይነት ምላሽ ላይ መድረሱን ያረጋግጡ፡፡ የ ካልሆነ፤ ለማብራራት ተጨማሪ ጊዜ
ይውሰዱ እና እንደገና ይሞክሩ።

ይምሩ:- ሁላችሁም በጣም ጥሩ ነው! የሂሳብ ባላንሳችንን በቋሚነት ማወቅ ለምን እንደሚያስፈልገን
የሚነግረኝ ሰው ይኖራል? (ምን ያህል ገንዘብ እንደሚኖረን ስለሚነግረን፤ ለቀጣይ ሳምንት /ወር እቅድ
ለማውጣት ያስችለናል፣ ወዘተ፡፡)

96
ይምሩ:- የሒሳብ መዝገብ አያያዛችን በሂደት ታማኝነትን ያተረፈ ከሆነ፤ የቢዝነሳችን ወጪ እና ገቢ የጉዞ
አቅጣጫን የሚያመላክት መሆን ይጀምራል። እናም ይህ የጉዞ አቅጣጫ፤ ቢዝነሱ ከጊዜ በኋላ እንዴት ሊለወጥ
ወይም ሊያድግ እንደሚችል ያመላክተናል።

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ ሜሪ በበዓላት ሠሞን የተለያዩ የተጋገሩ ነገሮችን የመሸጥ ዕድል እንደሚኖራት ልትገነዘብ
ትችላለች፡፡ የወቅቶች መለዋወጥ ወይም የዋጋ መጨመር በሌሎች ቢዝነሶች ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሊያስከትሉ
ይችላሉ። እነዚህ ሁሉ በጥሩ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ተለይተው የሚታወቁ የጉዞ አቅጣጫ ጠቋሚዎች
ናቸው፡፡

ይምሩ:- የቢዝነስ ባለቤቶች፤ ገበያ በሚበዛበት ወቅት ያለ እጥረት ለመሸጥ የሚያስችል በቂ ቅድመ ክምችት
ለመፍጠር ይህን መረጃ እንደ አቅጣጫ ጠቋሚ ይጠቀማሉ፡፡ እምብዛም ገበያ በማይኖርበት ወቅት ደግሞ
ቢዝነሶቻቸውን ለማስቀጠል ከዚያ ገቢ ላይ ቀንሰው መቆጠብ እንደሚያስፈልጋቸው ያውቃሉ፡፡

ይምሩ:- የተወሰኑ ደቂቃዎች ወስዳችሁ፤ ሰዎች ለግዥ ብዙ ወይም ጥቂት ገንዘብ ስለ ሚያወጡባቸው
ጊዜያትና በዓላት፤ እንዲሁም ይህ በቢዝነሶቻችን ላይ ስለሚኖረው ተጽዕኖ በየቡድኖቻችሁ ተወያዩት።

ቡድን አመቻቾች፡- ለ4 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ቡድንዎ ስለ ተለያዩ የበዓላት ወቅቶች፣ ሰዎች ብዙ ወይም ጥቂት
ገንዘብ የሚያወጡት መቼ እንደሆነ እና በእነዚህ ጊዜያት እንዴት ማቀድ እንደሚገባቸው እንዲያስቡ
ያግዟቸው፣።

ይምሩ:- በዓመት ውስጥ የተሻለ ገበያ ስለሚኖርባቸው ጊዜያት ሊነግረን የሚችል አንድ ሰው ይኖራል?

ይምሩ:- ለመልሱ ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ዝቅተኛ ሽያጭ ስለሚኖርባቸው ጊዜያትስ ሊያጋራን የሚችል ሌላ ሰው አለ?

ይምሩ:- ለመልሱ ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ከዚህ የትምህርት ክፍል ስለ ቀሰማችሁት አንድ ነገር ልትነግሩኝ የምትችሉ ሁለት ተሳታፊዎች
ትኖራላችሁ?

ይምሩ:- ሁለቱም ተሳታፊዎች ወጥተው አንድ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ ሃሳባቸውንም በመደገፍ፤
ያጋሯቸውን ነጥቦች እንደገና ያብራሩ፡፡

ይምሩ:- ዋው! ሁላችሁም ስለ ሒሳብ መዝገብ አያያዝ አስደናቂ መረዳት ነው ያላችሁ፡፡

በሚቀጥለው ክፍል፤ ስለቢዝነስ በጀት ምደባ እንማራለን!

97
// ክፍል 12 //
የቢዝነስ በጀት ምደባ

የሚወስደው ጊዜ፡- 1 ሠዓት

ግቦች:-
> ተሳታፊዎች፤ ለቢዝነሶቻቸው በጀቶችን መመደብ እና ማመጣጠንን ይማራሉ፡፡
> ተሳታፊዎች፤ የቢዝነስ እና የቤት ውስጥ በጀትን ስለመለየት ይማራሉ፡፡

አቅርቦቶች፡-
> እስክሪብቶዎች > ነጭ ሠሌዳ
> የሠልጣኞች መጽሐፍት > የነጭ ሠሌዳ ማርከሮች
> እንደ ከረሚላ ያሉ ጣፋጮች ነገሮች > የሒሳብ መደመሪያ ካልኩሌተሮች

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


> መነሻ ካፒታል > ገቢዎች
> ወጪዎች > ትርፍ

ትዕይንቶች(በግድግዳ ወይም በቦርድ ላይ የተለጠፉ ወይም በሠልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱ)፡-


> የቢዝነስ በጀት

ዝግጅት:-
> ተሳታፊዎችን በቡድን ከመከፋፈልዎ በፊት የሠልጣኞችን መጽሐፍ ይውሰዱና በኋላ ላይ በሚወሰድ
ምሳሌ የሚሞላ የቢዝነስ በጀት ቅጹን በነጭ ሠሌዳው ላይ ይገልብጡ፡፡ በምሳሌው መሠረት
መረጃዎችን ለመሙላት ስድስት ረድፍ ብቻ ያሉት ቅጽ ያስፈልግዎታል፡፡
> ይህ የትምህርት ክፍል ትንሽ ጠጠር /ከበድ/ ስለሚል አንዳንድ ተሳታፊዎች ወደ ኋላ ሊጎተቱ
ይችላሉ፡፡ እናም በቡድንም ሆነ በተናጠል የሚደረጉ ተሳትፎዎችን ያበረታቱ። ይህ ትምህርት
ከሌሎች ስልጠናዎች በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ ክፍል ነው!
> ሥራ ፈጣሪዎች፤ የቤት ውስጥ በጀት እና የቢዝነስ በጀት የመለየትን አስፈላጊነት በሚገባ
መረዳታቸውን ያረጋግጡ፡፡

98
ይምሩ:- በባለፈው ክፍል ላይ ስለ ገቢ እና ወጪ ምዝገባ ሁላችሁም አስደናቂ ስራ ሰርታችኋል፡፡

ይምሩ:- የሒሳብ መዝገብ አያያዝ፤ ምን ያህል ገንዘብ እንዳወጣን፣ ለምርቶቻችን /ዕቃዎቻችን/ እና


ለአገልግሎቶቻችን ዋጋ እንዴት እንደምንተምን፣ ከወጪ ቀሪ ወይም ትርፋችን ምን ያህል እንደሆነ ያሳየናል።

ይምሩ:- ወርሃዊ ገቢ እና ወጪዎቻችንን እንዴት እንደምንመዘግብ ካወቅን፤ ለቢዝነሳችን በጀት መመደብ


እንችላለን።

ይምሩ:- በጀት ምን ማለት እንደሆነ ማን ሊነግረኝ ይችላል?

ይምሩ:- ከሥራ ፈጣሪዎች መካከል አንድ ወይም ከዚያ በላይ ምላሽ እንዲሰጡ ያድርጉ፡፡ ለተሰጡ መልሶች
ከአድናቆትና ከምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- በጀት ማለት፤ ለወደፊቱ ገንዘብ ሳናባክን ወጭዎቻችንን በአግባብ የምንጠቀምበት ዕቅድ ነው፡፡
በጀት፤ ለማንኛውም ቢዝነስ በጣም አስፈላጊ መሣሪያ ነው፡፡

ይምሩ:- ሁለት የተለያዩ በጀቶችን ማዘጋጀት በጣም አስፈላጊ ነው፡- የቢዝነስ በጀት እና የቤት ውስጥ
በጀት፡፡
ይምሩ:- ከሁሉ አስቀድሞ፤ ስለ ቢዝነስ በጀት፤ ከዚያም በመቀጠል ስለ ቤት ውስጥ በጀት እንነጋገራለን፡፡

ይምሩ:- በጀት ምደባን ከመጀመራችን አስቀድሞ፤ ወጪዎቻችን ለይተን ማወቅ ይኖርብናል። በመጀመሪያ፤
መነሻ ካፒታል ይኖረናል፡፡ ይህ፤ ቢዝነሳችንን አሃዱ ብለን ስንጀምር የሚኖሩብንን ወጪዎች ለመክፈል
የሚያስችለን ገንዘብ ነው። መነሻ ካፒታል፤ ቢዝነሱን ለመጀመር፤ ለአንድ ጊዜ ብቻ የምናወጣው ወጪ ነው፡፡

ይምሩ:- ለመነሻ ካፒታል ወጪዎች የራሳቸው የተለዩ የቁጠባ እቅድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ
ወጭዎች ወርሃዊ ሳይሆኑ ቢዝነሱን ስንመሰርት ለአንዴ ብቻ ወጪ የሚደረጉ ናቸው።

ይምሩ:- እስቲ ለአፍታ ቆም ብለን ስለ ታሊ አነስተኛ የብድር አገልግሎት መርሃግብር እንነጋገር፡፡ ታሊ


አነስተኛ የብድር አገልግሎት፤ የኢኮኖሚ አቅም ለሌላቸው ስራ ፈጣሪዎች በልዩ ሁኔታ የመነሻ ካፒታል (ሲድ
መኒ) ለማበደር የተቋቋመ ነው፡፡ እንደምትገኙበት ገሃዳዊ የኑሮ ሁኔታ፤ ከአገልግሎቱ ለመጠቀም የሚገባችሁ
ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ ብድሩ በጥሬ ገንዘብ የሚሰጥ ሳይሆን እንደ መርጃ መሳሪያዎች፣ ዕቃዎች /ሸቀጦች/፣
የቢሮ ዕቃዎች /ሰፕላይስ/ ወይም ሌሎች መሰል ዕቃዎች ላሉ የቢዝነስ መነሻ ካፒታል ወጪን መሸፈን ነው፡፡
ሁሉም ሰው መስፈርቱን ሊያሟላ አይችልም፤ ነገር ግን በዚህ ፕሮግራም የመታቀፍ ፍላጎት ያላችሁ፤ ዛሬ
ከዚህ ስልጠና በኋላ ልታነጋግሩኝ ትችላላችሁ!

ይምሩ:- እስቲ አንድ አዲስ ልብስ ስፌት ቢዝነስ ለመክፈት ቢፈለግ፤ በመነሻ ካፒታል በጀት ሊካተቱ የሚችሉ
ዕቃዎችን በምሳሌነት ሊጠቅስልኝ የሚችል ሰው ይኖራል? (የልብስ ስፌት ማሽን፣ ክር፣ መርፌ፣ ጨርቅ እና
መሰል ቁሳቁስ፡፡) የስራ ፈጣሪዎችን ምላሽ ይቀበሉ፡፡ ለተሰጡ መልሶችም ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ
ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- በመቀጠልም፤ ቢዝነሳችንን ለማካሄድ ወርሃዊ ወይም መደበኛ ወጪዎች ይኖሩናል፡፡

ይምሩ:- የአንድ ቢዝነስ ወርሃዊ ወጪዎችን ምሳሌ ሊሰጠኝ የሚችል ተሳታፊ ይኖራል? (የመብራት እና
የውሃ ክፍያ፣ ቤት ኪራይ፣ ኢንሹራንስ፣ ወዘተ.)

99
ይምሩ:- የስራ ፈጣሪዎችን ምላሽ ይቀበሉ፡፡ ለተሰጡ መልሶችም ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- በመነሻ ካፒታል ወጪ እና በወርሃዊ የቢዝነስ ወጭዎች መካከል ያለውን ልዩነት አሁን የተረዳን
በመሆኑ፤ በወርሃዊ የቢዝነስ ወጪዎቻችን ላይ ብቻ በመመርኮዝ በሠልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ ያለውን
የቢዝነስ በጀት እናዘጋጃለን።

ይምሩ:- እየሰራችሁበት ላለው ወይም አንድ ቀን ልትከፍቱት ላሰባችሁት ማንኛውም ቢዝነስ ወርሃዊ የወጪ
ዝርዝር ለማስፈር፤ በቅድሚያ በዚህ በሠልጣኞች መጽሐፍቶቻችን ላይ ያለውን የበጀት ሠንጠረዥ መጠቀም
ይኖርብናል፡፡ ከዚያም እነዚህን ወጭዎች ለመሸፈን በየወሩ ምን ያህል መመደብ እንዳለብን ልናሰፍር
እንችላለን፡፡ በሠልጣኞች መጽሐፍ ገጽ ____ ላይ ያለውን በየቡድኖቻችሁ ይህንን ሥሩ፡፡ ለዚህም 10
ደቂቃዎችን ያህል ተጠቀሙ።

ይምሩ:- ከመጀመራችሁ በፊት ግን፤ አንድ ነገር መጥቀስ ይኖርብናል፡፡ ቢዝነሳችሁ ከወር ወር ልዩነት እያሳየ
መምጣቱን አንዳንዶቻችሁ አስተውላችሁ ይሆናል። ይህ በተለይ ለአርሶ አደሮች ገሃዳዊ እውነት ነው፡፡ ገበሬ
ከሆናችሁ፤ በተወሰኑ ወራት ውስጥ ማለትም እንደ ዘር ወቅት ባሉ ጊዜያት ብዙ ወጪዎች እንደሚኖሩባችሁ
ታውቃላችሁ፡፡ እንደ መከር ባለ ወቅት ደግሞ እምብዛም ወጭ አይኖርባችሁም።

ይምሩ:- ቢዝነሳችሁ የሚሠራው በዚህ መንገድ ከሆነ፤ አማካይ ወርሃዊ ወጪዎቻችሁን ለማግኘት ዓመታዊ
ወጪያችሁን በሙሉ ደምራችሁ ለ12 ታካፍላላችሁ። ካስቸገራችሁ ቡድን አመቻቾች ሊረዷችሁአመቻቾች
ይችላሉ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ10 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ተሳታፊዎች የቢዝነሶቻቸውን ወጪዎች በሙሉ ዘርዝረው
እንዲጽፉ እና እያንዳንዱ ወጪ በወር ምን ያህል እንደሆነ እንዲወስኑ ያድርጉ። ምናልባትም ከሁሉ አስቀድሞ
ስለ ሳምንታዊ ወጪዎቻቸው እንዲያስቡ እና ከዚያም ወርሃዊ ወጪውን ለመገመት በ4 እንዲያባዙ አንዳንድ
ተሳታፊዎችን በማሠልጠን መርዳት ሊኖርብዎት ይችላል።

የመነሻ ካፒታል ወጪ በዚህ ዝርዝር ውስጥ አለመካተቱን ያረጋግጡ። ጥቂት ምሳሌዎች ከዚህ በተች
ተጠቅሰዋል፡-

1) ጥሬ እቃዎች (ጨርቅ ፣ ክር፣ መርፌ፣ አዝራሮች፣ ወዘተ.)

2) ትራንስፖርት

3) ኪራይ

4) መብራት እና ውሃ

5) የሰራተኛ ደመወዝ

6) የፅዳት ዕቃዎች

7) የልብስ ማንጠልጠያ እና መስቀያ አሻንጉሊት

8) ደረሰኝ፣ እስክሪብቶዎች፣ ማህተም፣ ወዘተ.

100
9) የታሊ ብድር ወለድ ክፍያ እና አመላለስ

10) ከምፒዩተር፣ ካልኩሌተር፣ እና ሌሎች ሜካኒካል መሣሪያዎች

** ይህንን እውቀት በየግል ቢዝነሶቻቸው በስራ ላይ ለማዋል ጥሩ አጋጣሚ ስለሆነ፤ ከእነዚህ ምሳሌዎች
በመነሳት ስለ ቢዝነሶቻቸው እንዲያስቡ ተሳታፊዎችን ያበረታቱ፡፡ ሆኖም ይህ የሚያስቸግር ከሆነ፤
ከትምህርቱ መጀመሪያ ጀምሮ ምሳሌ ያደረግነውን የሴቶች ልብስ መሸጫ ሱቅ በመጠቀም በቡድን ሆነው
መስራትን አማራጭ ማድረግ ይችላሉ፡፡

በየጠረጴዛዎቻቸው ለተሳታፊዎች እገዛ የሚያደርጉ ቡድን አመቻቾች፡- አሁን እያንዳንዳችሁ እየሰራችሁት


ስላለው ወይም ወደፊት እንዲኖራችሁ ስለምትፈልጉት ቢዝነስ እንድታስቡ እፈልጋለሁ፡፡ ምርቶቻችሁን
ወይም አገልግሎታችሁን ከመሸጥ ጋር በተያያዘ የሚያስፈልጉ ወጭዎችን በሙሉ አስቡ እና የእያንዳንዱን
ወርሃዊ የወጭ ተመን ግምት በሠልጣኞች መጽሐፍ ገጽ ___ ላይ አስፍሩ፡፡ እነዚህ ወጪዎች ከወር ወር
ሊለያዩ ይችላሉ፤ ለአሁኑ ግን አማካይ የሆነውን ተመን እናስቀምጣለን፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- እያንዳንዱ ተሳታፊ በወጪው ዙሪያ እንዲያስብ በማድረግ ረገድ እገዛዎን ይቀጥሉ፡፡
ሳምንታዊ ወጪዎችን ወደ ወርሃዊ አማካኝ በማምጣት ላይ እገዛ ያድርጉ።

ይምሩ:- አንድ ሰው ወደ መድረክ መጥቶ ስለ እያንዳንዱ ወርሃዊ የቢዝነስ ወጪው ሊነግረን ይችላል?

ይምሩ:- ሠሌዳው ላይ ጻፍ፡፡

ይምሩ:- _____________________ (የተሳታፊው ስም) ሁሉንም ወጪዎች ዳስሷል? ምንም የተረሳ


የለም? የተረሱትን ይፃፉ፤ ተሳታፊውንም ከአድናቆት ጋር ያመስግኑ።

ይምሩ:- ተጨማሪ ሁለት ደቂቃዎችን በመውሰድ፤ በየቡድናችን ያልተቀሱ የወጪ ዝርዝሮችን አጠናቅቀን
ሁሉንም በመደመር የአንድ ወር አጠቃላይ ወጪያችንን እናሰላለን፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ2 ደቂቃዎች ያህል፡፡ የረሷቸውን ወጪዎች ሁሉ አስታውሰው እንዲዘረዝሩ፣ በየወሩ


ምን ያህል ማውጣት እንደሚፈልጉ እንዲጽፉ፣ እና አጠቃላይ ድምር እንዲያሰፍሩ ተሳታፊዎቻችሁ
ተሳታፊዎቻችሁን ያግዙ።

ይምሩ:- የወጪዎቻችን አጠቃላይ ድምር፤ በየወሩ ምን ያህል ገንዘብ እንደምናወጣ ያሳየናል።

ይምሩ:- ትርፍ ለማግኘት ወይም ትርፋማ ለመሆን፤ አማካይ ወርሃዊ ሽያጫችን ከወጪያችን መብለጥ
አለበት።

ይምሩ:- አሁን ደግሞ፤ ሁሉንም ወርሃዊ ገቢዎቻችንን ማለትም ቢዝነሳችን ያስገኝልናል ብላችሁ
የምትጠብቁትን ገንዘብ እንመዘግባለን፡፡

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ የዶሮ ሽያጭ ቢዝነስ ቢኖራችሁ፤ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ስንት ዶሮዎችን

ልትሸጡ እንደምትችሉ፣ እያንዳንዳቸው ምን ያህል እንደሚያወጡ ትመዘግቡና ከዚያም ጠቅላላ ገቢውን


ታሰላላችሁ፡፡

101
ይምሩ:- ወይም እንደ ፀጉር ቤት ያሉ አገልግሎቶችን የምትሰጡ ከሆነ፤ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የስንት ሰው
ፀጉር ለመቁረጥ እንዳቀዳችሁ እና ለእያንዳንዱ ምን ያህል እንደምታስከፍሉ ትመዘግባላችሁ፣ ከዚያም
በማባዛት ጠቅላላ ገቢውን ትውስናላችሁ።

ይምሩ:- ገበሬ ከሆናችሁ ወይም ወቅትን የሚጠይቅ ሌላ ዓይነት ቢዝነስ ከሆነ ያላችሁ፤ ገቢያችሁ ከወር ወደ
ወር በእጅጉ እንደሚለያይ ልብ በሉ ፡፡ ስለዚህ አማካኝ ወርሃዊ ገቢያችሁን ለማወቅ፤ የዓመቱን ጠቅላላ ገቢ
በመደመር ለ12 ማካፈል ያስፈልጋችኋል።

ይምሩ:- ይኖረናል ብለን የምናስበውን ገቢ ለማወቅ እንዲሁ መገመት አለብን? በጭራሽ!

ይምሩ:- እስካሁን በተማርነው መሠረት፤ ወርሃዊ ገቢና ወጪያችንን በትክክል እንዴት እንደምናቅድ
የሚያሳውቀን መሳሪያ ምን ይባላል? ምላሾችን ይቀበሉ። (የሒሳብ መዝገብ አያያዝ)፡፡

ይምሩ:- (“የሒሳብ መዝገብ አያያዝ” የሚል መልስ ማንም ካልሰጠ) ወርሃዊ ገቢ እና ወጪን በአግባቡ
ለመከታተል ይህ ነገር በጣም አስፈላጊ መሆኑን ያስታውሷቸው፡፡

ይምሩ:- በየወሩ ምን ያህል ገቢ ሊኖረን እንደሚገባ ወስነን ከዚያም አጠቃላይ ገቢውን ደምረን “ጠቅላላ
ወርሃዊ ገቢ” በሚለው ሣጥን ውስጥ ለማስፈር በየቡድናችን ጥቂት ጊዜ እንውሰድ፡፡

ይምሩ:- በቡድን እንዲሰሩ ጊዜ ይስጧቸው፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ6 ደቂቃዎች ያህል፡፡ በዚህ ሂደት እያንዳንዱን ተሳታፊ ያግዙ። አንድ ተሳታፊ ገና ቢዝነስ
ያልጀመረ ከሆነ፤ ያ ሰው የበጀት ረቂቅ እንዲያወጣ ያድርጉት፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ2 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ገቢን በመመዝገብ እንዲሁም ደምሮ በባዶ ሣጥን ውስጥ
በማስቀመጥ ተግባር ቡድንዎን ያግዙ።

ይምሩ:- አንድ ሰው ወደዚህ መጥቶ፤ የአንድ ወር የቢዝነስ ገቢውን ሊነግረን ይችላል?

ይምሩ:- ምላሹን በሠሌዳው ላይ ይመዝግቡ፡፡

ይምሩ:- (የተሳታፊውን ስም ይጥቀሱ) ________________ ሁሉንም ገቢዎቹን አስታውሷል?


ያልጠቀሳቸው የገቢ ምንጮች ይኖራሉ?

ይምሩ:- ተሳታፊውን ከአድናቆት ጋር ያመስግኑ እና ያልተጠቀሱ የሚሏቸውን ማንኛውንም የገቢ ምንጭ


በዝርዝር ይጻፉ።

ይምሩ:- አጠቃላይ ወርሃዊ ወጪያችንን ከምናገኘው ወርሃዊ ገቢ በመቀነስ፤ ገንዘብ እንዳገኘን ወይም
እንዳጣን መወሰን እንችላለን፡፡ ገንዘብ ስናገኝ፤ ትርፋችን ይባላል።

ይምሩ:- ትርፍ ወይም ኪሳራን ማወቅ፤ በጀቶቻችንን ማመጣጠን ተብሎ ይጠራል። የበጀቶቻችንን ሚዛን
ካስተካከልን፤ ካወጣነው የበለጠ ገንዘብ ማግኘት አለማግኘታችንን እናረጋግጣለን።

ይምሩ:- ይህን ከቡድኖቻችን ጋር እንስራው፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ1 ደቂቃ ያህል፡፡ የቡድንዎ አባላት በሠልጣኞች መጽሐፍቶቻቸው ላይ ያሉትን ገቢ ከገቢ
ወጭዎች እንዲያቀናንሱ ያግዟቸው።

102
ይምሩ:- የአንድ ወር በጀታችሁን አስልታችሁ ትርፍ ያሳያችሁ እጃችሁን አንሱ፡፡

ይምሩ:- በጣም ጥሩ! ይህ ማለት፤ በዚህ ወር ካወጣችሁት የበለጠ ገቢ አግኝታችኋል ማለት ነው!

ይምሩ:- አሁን ደግሞ ኪሳራ ያሳየባችሁ እጃችሁን አውጡ፡፡ መልካም፤ ይህም ማለት ከገቢያችሁ በላይ
እያወጣችሁ ነው ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- ወጪያችን ከገቢያችን ከፍ ያለ ከሆነ፤ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? (የምናወጣውን መቀነስ፣


የምናስገባውን መጨመር፣ ወዘተ.)

ይምሩ:- ለተሰጡ መልሶች ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ትክክል ነው! ወርሃዊ በጀታችን ኪሳራ ካሳየን፤ የተወሰኑ ወጭዎቻችችንን እንቀንሳለን ያለዚያም
ተጨማሪ ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን በመሸጥ ገቢን የሚጨምር የማርኬቲንግ እቅድ ወይም
ማስታወቂያ መፍጠር ያስፈልገናል።

ይምሩ:- እናም፣ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ እጅግ ጠቃሚ የሆነው ለዚህ ነው፡፡ በቀጣይ ወራት በጀቶቻችንን
ለማቀድ ይረዳናል፡፡ መዝገቦችን ካልጠበቅን ፣ ታዲያ እኛ ለመቀጠል መለወጥ ያለብንን ነገሮች ለመለወጥ
የሚያስችል መንገድ የለንም፡፡

ይምሩ:- ከዚህ የትምህርት ክፍል ስለ ቀሰማችሁት አንድ ነገር ልትነግሩኝ የምትችሉ ሁለት ሰዎች አላችሁ?

ይምሩ:- ሁለት ሠልጣኞች ወደ መድረክ ወጥተው አንድ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ ሃሳባቸውን በመደገፍ፤
ያጋሯቸውን ነጥቦች እንደገና ያብራሩ፡፡

ይምሩ:- ዋው! ሁላችሁም ስለ ቢዝነስ በጀት ምደባ አስደናቂ መረዳት ነው ያላችሁ፡፡በሚቀጥለው ክፍልም
ከዚህ ተመሳሳይ የሆነ ጽ ንሰ ሃሳብ፤ ስለ “ቤት ወጪ በጀት ምደባ” እናያለን፡፡

103
// ክፍል 13 //
የ ቤት ወጪ በጀት ምደባ

የሚወስደው ጊዜ፡- 1 ሠዓት


ግቦች:-
> ተሳታፊዎች፤ ለቤት ወጪዎቻቸው በጀትን መመደብና እና ማመጣጠንን ይማራሉ።
> ተሳታፊዎች፤ የቢዝነስን እና የቤት ወጪ በጀትን መለየት ይማራሉ፡፡

አቅርቦቶች፡-
> እስክሪብቶዎች > ነጭ ሠሌዳ
> የሠልጣኞች መጽሐፍት > የነጭ ሠሌዳ ማርከሮች
> ጣፋጮች > የሒሳብ መደመሪያ ካልኩሌተር

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


> የቤት ወጪ በጀት

ዝግጅት:-
> ተሳታፊዎች በቡድን ከመከፋፈላቸው በፊት፤ የተሳታፊዎችን የማሠልጠኛ መጽሐፍ ይዋሱና
የተወሰኑ ምሳሌዎችን ለመሙላት “የቤት ወጪ በጀት” የሚለውን ቅጽ በነጭ ሠሌዳው ላይ
ይገልብጡ፡፡ የናሙናውን መረጃ ለመሙላት ስድስት ረድፍ ብቻ ይበቃል፡፡
> ይህ የስልጠና ክፍል ትንሽ ፈታኝ ከመሆኑ የተነሳ ለአንዳንድ ተሳታፊዎች ወደኋላ መቅረት ምክንያት
ሊሆን ይችላል። ተሳታፊዎች በተናጠልም ሆነ በቡድን የሚያደርጉትን ተሳትፎ ማበረታታትዎን
አጠናክረው ይቀጥሉ። ይህ ሥልጠና በጣም ወሳኝ ከሆኑት የሥልጠና ክፍሎች ውስጥ አንዱና ዋንኛው
ነው!
> እርግጠኛ ይሁኑ ተሳታፊዎች የቤት ወጪ በጀትና የቢዝነስ በጀትን በትክክል ለያይተው ማየት
መቻላቸውን ያረጋግጡ፡፡
> መደበኛ የስልጠና ፕሮግራሙ ከመጀመሩ አስቀድመው ፈቃደኛ ሠልጣኞች ድራማውን
እንዲለማመዱ እና ከተቻለም የባህል “አልባሳት” እንዲለብሱ ያድርጉ፡፡

ይምሩ:- የቢዝነስ በጀትን በመመደብ ረገድ ሁላችሁም አስደናቂ ሥራ ሠርታችኋል! እነዚህን የተማርናቸውን
ትምህርቶች ተጠቅመን የቤት ወጪ በጀት ምደባን ተግባራዊ እናደርጋለን፡፡

104
ይምሩ:- በመጀመሪያ፤ እንደ እናት እና ልጅ ሆነው ስለ ቤታቸው ወጪ በጀት በመወያየት የሚተውኑ ሁለት
ጓደኞቻችንን እንመልከት፡

105
ልምምድ

ድራማ:- ቅድመ ዝግጅት ያደረጉ ሁለት ፈቃደኛ ሠልጣኞች ወይም አመቻቾች ወደ መድረኩ እንዲመጡ
ያድርጉ፡፡ ይህ ድራማ አንዲት ሴት ልጅ ከእናቷ ጋር በገንዘብ (ፋይናንስ) ጉዳይ ስትከራከር ያሳያል፡፡ ከስልጠናው
አውድ ጋር እስከተስማማ ድረስ፤ የቤተሰቡ ግንኙነት የግድ እናትና ልጅ መሆን ስለሌለበት መቀየር ይችላሉ፡፡

ልጅ፡- እማማ፤ ዛሬ ወደ ከተማ ወጣ ብዬ ልመጣ ስለሆነ፤ ለትራንስፖርት የሚሆን __________ ብር


እፈልጋለሁ፡፡

እናት:- ለትራንስፖርት የሚውል ገንዘብ የለኝም፤ የኔ ልጅ! ትናንት ከተማ የሄድሽ ጊዜ ሁሉንም ብር ጨርሰሽ
ነው የመጣሽው፡፡

ልጅ፡- ምን ማለትሽ ነው? ለእኔ የሚሆን ምንም ገንዘብ የለሽም? የሚሸጡ ዶሮዎች የሉም?

እናት:- ዶሮዎች አሉኝ፡፡ ነገር ግን ዛሬ አነሱን ከሸጥሁ፤ ነገ የምንሸጠው ምንም እንቁላል አይኖረንም፡፡

ልጅ፡- ስለ ነገ ምን አገባኝ! ዛሬ ወደ ከተማ መሄድ አለብኝ! እነዚያን ዶሮዎች ሽጠሽ ለምን አትሰጪኝም?

እናት:- ለመሆኑ ከተማ ምን ዓይነት ወሳኝ ነገር ቢኖርብሽ ነው?

ልጅ፡- ጓደኞቼን ማግኜት እፈልጋለሁ!

እናት:- ይሁን እንጅ፤ ነገ ለመብላት ዶሮዎቹን ማቆየቱ በእርግጠኝነት የተሻለ ነው?

ልጅ፡- እሺ፤ የአሳማ ግልገሉን ሺጪው፡፡

እናት:- የአሳማ ግልገሉን?! እሱን’ማ ማድረግ አንችልም፡፡ የአሳማ ግልገሉን በሶስት ወራት ውስጥ አደልበን
ሺጠን የወንድም እና የእህትሽን የትምህርት ቤት ክፍያ እንሸፍናለን!

ልጅ፡- እና እኔ በምን ልሂድ!?

እናት:- የወሩን የትራንስፖርት ገንዘብሽን ትናንት ጨርሰሻል፡፡ ስለዚህ የሆነ ስራ ሰርተሸ ገንዘብ ካላገኘሽ
በቀር፤ ዛሬ ወደ ከተማ መሄድ አትችይም፡፡

ልጅ፡- ሥራ? ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት አልፈልግም፡፡ ከተማ ሄጄ ጓደኞቼን መጎብኘት ብቻ ነው


ምፈልገው፡፡

እናት:- መልካም፤ እኛም እንስሳቶቻችንን መሸጥ ስለማንችል፤ ሥራ ካልሰራሽ የትራንስፖርት ገንዘብ


አታገኝም፡፡ እነዚህ እንስሳት ቢዝነሶቻችን ናቸው፡፡ እነሱን የምንሸጥ ከሆነ፤ ሌላ ቢዝነስ አይኖረንም፡፡ ቢዝነስ
ከሌለን ደግሞ በሕይወት መኖር አንችልም፡፡ ገንዘብን እንዴት እንደምናወጣ በጥበብ ማሰብ አለብን፡፡

ልጅ፡- እሺ ማሚዬ፡፡ ስለ ቤተሰባችን የወደፊት ሕይወት ማሰብሽ ትክክል እንደሆነ አሁን ገብቶኛል፡፡
በሚቀጥለው ወር የተሻለ ማቀድ እንድችል፤ በጀት እንዴት መመደብ እንደሚኖርብኝ ታስተምሪኛለሽ?

እናት:- በሚገባ ነዋ፤ የኔ ውድ፡፡ እንዲህ እንዳሁኑ በየጊዜው ላለመጨቃጨቅ፤ አብረን በጀቱን እናውጣ፡፡

106
________________________________________________________________

ይምሩ:- ዋው፤ ግሩም ትወና!!!!

ይምሩ:- በዚህ ድራማ ውስጥ ምን አስተዋላችሁ?

ይምሩ:- ብዙዎች አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ይፍቀዱላቸው።

ይምሩ:- ስለ እናትየዋ ምን ትላላችሁ? ልጇስ?

ይምሩ:- ስለ ቤት በጀት ምደባ አስፈላጊነት ምን ተማራችሁ?

ይምሩ:- ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ቤት እና ቤተሰቦቻችንን በሚገባ ለማስተዳደር ወርሃዊ ወጪዎቻችን ምን ምን ናቸው? (ዝርዝሮችን


በሠሌዳው ላይ ይጻፉ)

1)አስቬዛ

2) የትምህርት ቤት ክፍያ

3) መብራት እና ውሃ

4) ነዳጅ/ጋዝ

5) ሳሙና / ልብስ እና የገላ/

6) አልባሳት እና ጫማ

7) መድሃኒት

8) ስጦታዎች

9) አስራት

10)

ይምሩ:- ከነዚህ ወጪዎች መካከል የተወሰኑት ቋሚ ወጪዎች ናቸው፤ ምንም ይሁን ምን ከወር ወር ዘላቂ
ናቸው ማለት ነው። አሁን ከቋሚ ወጪዎች ጎን የኮከብ ምልክት እናደርጋለን። መልስ ከተሳታፊዎች ይቀበሉ፤
ለምሳሌ የትምህርት ቤት ክፍያ፣ መብራት እና ውሃ፣ ወዘተ።

ይምሩ:- በተመሳሳይ ሁኔታ፤ ከነዚህ ወጭዎች ውስጥ የተወሰኑት ተለዋዋጭ ወጪዎች ናቸው፤ ይህም
ማለት እንደ በጀቱ መጠን ሊለዋወጥ የሚችል ነው፡፡ ወጪዎች በእኛ ፍላጎት ወይም የበጀት አቅም ላይ
የመሠረቱ ወጭዎችን ደግሞ ለመለየት እናክብብ። ሃሳቦችን ከተሳታፊዎች ይቀበሉ፤ ለምሳሌ አልባሳት፣
አስቬዛ፣ ነዳጅ/ጋዝ፣ ወዘተ፣ ናቸው ፡፡ ተለዋዋጭ ወጪዎች፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሊቀነሱ የሚችሉ ናቸው፡፡

107
ትክክለኛ ቋሚ ወጪ የትኛው እንደሆነ እና እንዳልሆነ አለመስማማት ሊኖር ይችላል። ዋናው ጉዳይ፤
ተሳታፊዎች ትኩረቶቻቸውን በጀታቸው ላይ እስካደረጉ ድረስ የተወሰኑ ወጭዎችን መቆጣጠር እንደሚችሉ
እንዲገነዘቡ መርዳት ነው፡፡

ይምሩ:- ወርሃዊ የቤት ገቢያችን ምን ያህል ነው? ምንጩስ ከየት ነው? (የሚሰጡ ጥቆማዎችን በሠሌዳው
ላይ ይፃፉ)። የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፡-

1. ደመወዝ
2. ከሠብል ወይም ከእንስሳት ወይም ከሌሎች ቁሳቁስ ሽያጭ
3. ከቢዝነስ ትርፍ
4. የቤተሰብ አባል ደመወዝ

ይምሩ:- አንድ ተሳታፊ “ከሠብል ወይም ከእንስሳት ወይም ከሌሎች ቁሳቁስ ሽያጭ” ወይም ሌላ በወቅት ላይ
የተመሠረተ የገቢ ምንጭ ጠቅሶ መልስ ከሰጠዎ፤ ይህን ጥያቄ አስከትለው ይጠይቁት፡-የገቢያችን ምንጭ
የእንስሳት ወይንም የሰብል ሽያጭ ከሆነ፤ ያንኑ የገቢ መጠን በየወሩ እናገኛለን? (አናገኝም፡፡)

ይምሩ:- የገቢዎቻችን መጠን በዓመቱ ወራት ሁሉ የተለያዩ ሲሆኑ ወርሃዊ በጀቶቻችንን እንዴት መመደብ
እንችላለን?

ይምሩ:- ምላሾችን ይቀበሉ፡፡ ለተሰጡ መልሶችም ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡ በወር ውስጥ
ያሉትን ትርፍዎች እንዲከፋፍሉ እና ሁሉንም ገንዘብ ወዲያውኑ እንዳያወጡ ያበረታቷቸው።

ልምምድ

ይምሩ:- አሁን፤ የቤት በጀትን በየቡድናችን ማዘጋጀት እንጀምር፡፡ ምንም እንኳን እያንዳንዱ ቤት የተለያየ
ቢሆንም፤ በሠሌዳው ላይ ያሉት ዝርዝሮች ሀሳብ ለማመንጨት ሊያግዟችሁ ይችላሉ፡፡ የአንድ ወር ወጪ እና
ገቢዎቻችሁን በሠልጣኞች መጽሐፍ ገጽ ____ ላይ አስፍሩ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ይህን የሠልጣኞቹን እንቅስቃሴ በመምራት ያግዙ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ዝርዝሮች፤
የራሳቸውን ለመጀመር እንደመነሻ ሊረዳቸው ይችላል፡፡

ይምሩ:- ጠቅላላ ወርሃዊ ወጪዎቻችሁን ደምሩና ሒሳቡን በሠልጣኞች መጽሐፍ ‘ጠቅላላ ወጪ’ በሚለው
ሳጥን ውስጥ ያስገቡ።

ይምሩ:- በቂ የማጠናቀቂያ ጊዜ ይስጧቸው፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ይህን ሒሳባዊ ስሌት ለመስራት በሚደረግ ጥረት ተጨማሪ እገዛ የሚፈልጉ ሊኖሩ
ስለሚችሉ በንቃት በመከታተል ይምሯቸው፡፡

ይምሩ:- ጠቅላላ ወርሃዊ ገቢዎቻችሁን ደምሩና ሒሳቡን በሠልጣኞች መጽሐፍ ‘ጠቅላላ ገቢ’ በሚለው
ሳጥን ውስጥ ያስገቡ።

ቡድን አመቻቾች፡- ይህን ሒሳባዊ ስሌት ለመስራት በሚደረግ ጥረት ተጨማሪ እገዛ የሚፈልጉ ሊኖሩ
ስለሚችሉ በንቃት በመከታተል ይምሯቸው፡፡

108
ይምሩ:- አሁን፤ በሠልጣኞች መጽሐፍቶቻችሁ ውስጥ እንደተጠቀሰው አጠቃላይ ወጪዎቻችሁን
ከአጠቃላይ ገቢዎቻችሁ ቀንሱ።

ቡድን አመቻቾች፡- ይህንን ስሌት ይምሩ፤ እንዲሁም ድጋፍ የሚፈልግ ማንኛውንም ሰው ይርዱ።

ይምሩ:- ወርሃዊ ወጪዎቻችሁ ከገቢዎቻችሁ ከበለጡ፤ ወጪ መቀነስ የሚያስችሉ ዕድሎችን መፍጠር


ያለዚያም በቢዝነሶቻችሁ ወይም በሌሎች ዕድሎች አማካኝነት ገቢን ማሳደግ ያስፈልጋችኋል፡፡

ይምሩ:- ወጪዎቻችሁን ለመቀነስ ከፈለጋችሁ፤ ከሁሉ አስቀድሞ፤ መጀመሪያ የተነጋገርንባቸውን ተለዋዋጭ


ወጭዎችን መፈተሸ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ወጪዎች፤ በአኗኗር ዘይቤያችን፣በምርጫዎቻችን፣ በግዥ
ድግግሞሽ ላይ ለውጦች በማድረግ መቀነስ የምንችላቸውን ወጪዎች ናቸው፡፡

ይምሩ:- በሠሌዳው ላይ ወደ ተጻፉት የወጪ ዝርዝሮች እንመለስ፡፡ ያከበብናቸውን ተለዋዋጭ ወጪዎች


ተመልከቱ፡፡ የወሩን በጀት ጠብቆ ለመቀጠል፤ ከነዚህ ወጪዎች ውስጥ አንዱን የምንቀንስበትን አንድ መንገድ
ሊጠቁም የሚችል ሰው አለ? አንድ ወይም ሁለት ተሳታፊዎች በዚህ ጉዳይ ሀሳባቸውን እንዲሰጡ ያድርጉ
(ስጦታ ከመግዛት ይልቅ በእጅ ሠርቶ መስጠት፣ ውድ ያልሆነ ምግብ መምረጥ፣ ወዘተ፡፡) ለተሰጡ መልሶች
ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ለቤት ውስጥም እንዲሁ ጠቃሚ እንደሆነ ማየት ትችላላችሁ፡፡
ምክንያቱም በትክክል መዝግበን የማንይዝ ከሆነ፤ ለወጪ ከተመደበ ገንዘብ ውስጥ ምን ያህል እንደቀረን
እንኳ የምናውቀው በግምት ይሆናል ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- ገቢ እና ወጪዎቻችን የሚለዋወጡ ቢሆኑ እንኳ፤ በየወሩ እውነተኛ እና ተጨባጭ የሆነ የቤት ውስጥ
በጀት ለመመደብ ምን ማድረግ እንዳለብን የተወሰነ ጊዜ ወስዳችሁ በየቡድኖቻችሁ ተወያዩበት።

ቡድን አመቻቾች፡- ለ5 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ውይይቱን ይምሩ፡፡ ይህንን ጥያቄ ይጠይቁ እና ሥራ ፈጣሪዎች
ፈጠራ አዘል መልሶችን እንዲሰነዝሩ ያድርጉ፡፡

ይምሩ:- ወጪያችንን በዕቅድ ለመምራት፤ በጀትን እንዴት በአግባብ መጠቀም እንችላለን?

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ በየወሩ ለአስቬዛ ምን ያህል ገንዘብ እንደምናወጣ በጀት መድበናል፡፡ ለቤተሰቦቻችን አስቬዛ
በወር አንድ ጊዜ ብቻ ስለማንገዛ፤ ወደ ገበያ በሄድን ቁጥር የስንት እንደምንሸምት እንዴት እንወስናለን?

ይምሩ:- ወርሃዊ አስቬዛ ስንት እንደመደበ የሚነግረኝ አለ? ለአንድ ሠልጣኝ ዕድል ይስጡና የገንዘቡን መጠን
በሠሌዳው ላይ ይፃፉት፡፡ በወር ውስጥ ስንት ጊዜ ነው ለቤተሰቡ አስቬዛ የምትገዛው? የዚህንም መልስ
በሠሌዳው ላይ ይፃፉት፡፡

ይምሩ:- አሁን፤ ወርሃዊ የአስቬዛ በጀትህን ገቢያ በምትሄድበት ወይም በምትመላለስበት ቁጥር ልክ
እናካፋለን፡፡ ሒሳባዊ ስሌቱን ሠሌዳው ላይ ያስሉት እና ውጤቱን ያክብቡት። ገንዘቡን ከወር ወር
ለማብቃቃት እና የገንዘብ እጥረት እንዳይገጥመን ለማድረግ፤ ወደ ገበያ በሄድን ቁጥር መጠቀም የሚገባንን
የወጪ መጠን እንዲህ እንወስናለን። ይህም በገንዘባችን፤ ጥበብ የተሞላበት ውሳኔዎችን እንድንወስን
ይረዳናል፡፡

ይምሩ:- የቢዝነስ በጀትን ከቤት ወጪ በጀታችን መለየት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ለቢዝነስ
ማስፋፊያ የታሰበውን ገንዘብ በድንገት ለቤት ወጪ እንዳንውለው ያደርገናል፡፡

109
ይምሩ:- የቢዝነስ ገንዘባችንን ለቤት ወጪ የምናውል ከሆነ፤ ቢዝነሳችንን በሕይወት ለማቆየት /ለማስቀጠል/
ገንዘብ ልናጣ እንችላለን፡፡ ቢዝነሳችን ከወደቀ ደግሞ፤ በቀጣይ ወር ለቤት ወጪ የምንከፍለው ገንዘብ
አይኖረንም፡፡

ይምሩ:- ይህንን ክፍለ ጊዜ ከማጠናቀቃችን በፊት፤ ስለ ሒሳብ መዝገብ አያያዝ እና ስለ በጀት አመዳደብ ምን
ያህል እንደገባን ለማረጋገጥ ጥቂት ጊዜ ወስደን በየቡድናችን ጥያቄዎችን እንጠይቅ!

ቡድን አመቻቾች፡- ለ8 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ሁሉም የቡድን አባላት እስኪገባቸው ድረስ ወደ ቀጣይ ክፍል
አይሂዱ፡፡

ይምሩ:- ከዚህ ሥልጠናም በኋላ፤ እንዲጠቅማችሁ ታስቦ ተጨማሪ የሒሳብበ መዝገብ አያያዝ እና የበጀት
ቅጾች በሠልጣኞች መጽሐፍ የመጨረሻ ገጾች ላይ እንዳሉ አስታውሱ፡፡

ይምሩ:- ከዚህ የትምህርት ክፍል ስለ ቀሰማችሁት አንድ ነገር ልትነግሩኝ የምትችሉ ሁለት ሰዎች አላችሁ?

ይምሩ:- ሁለት ሠልጣኞች ወደ መድረክ ወጥተው አንድ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ ሃሳባቸውን በመደገፍ፤
ያጋሯቸውን ነጥቦች እንደገና ያብራሩ፡፡

ይምሩ:- ዋው! ሁላችሁም ጥሩ መረዳት ነው ያላችሁ፡፡ አሁን ጥቂት እረፍት ወስደን ስንመለስ፤ ከምወዳቸው
የስልጠና አርዕስቶች መካከል አንዱ የሆነውን እንወያያለን፡- ስለ ቁጠባ!

110
// ክፍል 14 //
የቢዝነስ ቁጠባ

የሚወስደው ጊዜ፡- 1 ሠዓት

ግቦች:-
> ተሳታፊዎች፤ ለቢዝነሶቻቸው መቆጠብ ለምን እንደሚያስፈልጋቸው ይገነዘባሉ፡፡
> ተሳታፊዎች፤ ጥቂት በጥቂት እንዴት እንደሚቆጥቡ እና የቢዝነስ ቁጠባ ዕቅዶችን እንዴት
እንደሚያዘጋጁ ይማራሉ።
> ተሳታፊዎች፤ በቁጠባ እና ኢንቨስትመንትን በመጠቀም ቢዝነሶቻቸውን የማሳደግን ጠቀሜታ
ይማራሉ።

አቅርቦቶች፡-
> እስክሪብቶዎች > የሰሌዳ ማርከሮች
> የሠልጣኞች መጽሐፍት > ጣፋጮች
> ነጭ ሠሌዳ > የሒሳብ መደመሪያ ካልኩሌተሮች

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ) ፡-


> የታቀደ ቁጠባ > የወደፊት ግቦች
> ድንገተኛ እና ያልታቀዱ ፍላጎቶች > ገቢ አመንጪ ኢንቨስትመንቶች
> መነሻ ካፒታል

ትዕይንቶች (በግድግዳ ወይም በቦርድ ላይ የተለጠፉ ወይም በሠልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱ)፡-
> ድንገተኛ እና ያልታቀዱ ፍላጎቶች
> የወደፊት ግቦች

ዝግጅት:-
> የቁጠባ መሠናክል ከሆኑት መካከል አንዱና ዋንኛው፤ ያላቸው ለሌላቸው ማካፈል እንዳለባቸው
ተደርጎ የመታመኑ ጉዳይ ነው፡፡ ምንም እንኳን ይህ ጥሩ ሀሳብ ቢሆንም፤ ብዙ ተረጂዎችን የመርዳት
ግዴታ እንዳለባቸው ስለሚሰማቸው ብዙዎችን ስኬታማ እንዳይሆኑ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ በዚህ
የስልጠና ክፍል፤ ይህንን ጉዳይ በጥንቃቄ ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡
> ይህ የስልጠና ክፍል፤ የዱላ ቅብብል ሩጫን ያካትታል። የዝግጅት መመሪያውን በገጽ _____ ላይ
ይመልከቱ።

111
> በዓመት ውስጥ በዳቦ መጋገሪያ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የድንገተኛ አደጋ ምሳሌዎች ሲቀርቡልዎት፤
እንደ “እሳት ቃጠሎ” ያሉ አውዳሚ አደጋዎችን አይቀበሉ፡፡ ምክንያቱም የሚጠይቀው ወጪ ከባድ
ስለሆነ ምሳሌውን ያበላሽብዎታል፡፡ እንደ “ምጣድ ጥገና” እና የመሳሰሉ ቀላል ወጪዎች ላይ ትኩረት
ያድርጉ።
> ተሳታፊዎች የቁጠባ ሒሳባቸውን ሲያሰሉ፤ ጠቅላላውን ለ12 በማካፈል ወርሃዊ፣ ከዚያም ለ4
በማካፈል ሳምንታዊ የቁጠባ መጠናቸውን እንዲያውቁ ይደረጋሉ፡፡ ይህ ዘዴ፤ በ48 ሳምንታት ቁጠባ
ዓመታዊ እቅዳችንን እንደምናሳካ ያስገነዝባል፡፡ ስልቱ የተዘየደው ቁጠባውን ለማቅለል ማለትም፤
በዓመት ወይም በወር በአንዴ መክፈል ለሚከብዳቸው ስዎች ታስቦ ነው፡፡
> የዱላ ቅብብል ሩጫ ድጋፍን ለመግለጽ ሃይ ፋይቭን (የአንድን ሰው የእጅ መዳፍ ከሌላ ሰው የእጅ
መዳፍ ጋር በማጋጨት) ይጠቀማል፡፡ ይህ በባህሉ ተቀባይነት ከሌለው፤ ሌላ አማራጭ ይጠቀሙ።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ:-


> ምሳሌ 13÷11
> ምሳሌ 21÷20

ይምሩ:- እንኳን በደህና መጣችሁ! አሁን፤ ለቢዝነስም ሆነ ለግል ስኬት ዓይነተኛ መሣሪያ ስለሆነው ስለ ቁጠባ
እንነጋገራለን፡፡

ይምሩ:- የታቀደ ቁጠባ ማለት፤ ወደፊት እንዳስፈላጊነቱ ለመጠቀም ሆን ተብሎና ታስቦ ገንዘብ የመቆጠብ
ዕቅድ ነው፡፡ የታቀደ ቁጠባ በሚዘጋጅበት ጊዜ፤ ከጠቀሜታቸው አንጻር፤ ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ቁጠባዎች
በቅደም ተከተል ማስቀመጥ ወሳኝ ነው፡፡

ይምሩ:- አብዛኛዎቹ የታቀዱ ቁጠባዎች፤ በአንድ ወይም በሁለት ጀንበር አይከሰቱም። ቁጠባ የሚመሰረተው
በረዥም ጊዜ ሂደት ቀስ በቀስ ነው፡፡

ይምሩ:- መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ገንዘብ ብዙ የሚለው አለው። መጽሐፈ ምሳሌ 13÷11 ቁጠባን አስመልክቶ
እንዲህ ይላል:- “በችኮላ የምትከማች ሀብት ትጎድላለች፤ ጥቂት በጥቂት ጠተከማቸች ግንትበዛለች።”

ይምሩ:- በአንድ ወቅት፤ ገንዘብ በፍጥነት አግኝቶ ብዙም ሳይቆይ የጠፋበትን ገጠመኝ ሊነግረን የሚችል ሰው
አለ? መልስ ይቀበሉ፡፡

ይምሩ:- ገንዘቡን ጥቂት በጥቂት እየቆጠበ በጊዜ ሂደት ማደግ የቻለ አንድ ሰው ራሱን ምሳሌ አድርጎ
ሊያጋራን ይችላል? መልስ ይቀበሉ፡፡

ይምሩ:- መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ገንዘብ ብዙ የሚለው አለው። መጽሐፈ ምሳሌ 13÷11 ቁጠባን አስመልክቶ
እንዲህ ይላል:- “በችኮላ የምትከማች ሀብት ትጎድላለች፤ ጥቂት በጥቂት ጠተከማቸች ግንትበዛለች።”

ይምሩ:- በአንድ ወቅት፤ ገንዘብ በፍጥነት አግኝቶ ብዙም ሳይቆይ የጠፋበትን ገጠመኝ ሊነግረን የሚችል ሰው
አለ? መልስ ይቀበሉ፡፡

ይምሩ:- ገንዘቡን ጥቂት በጥቂት እየቆጠበ በጊዜ ሂደት ማደግ የቻለ አንድ ሰው ራሱን ምሳሌ አድርጎ
ሊያጋራን ይችላል? መልስ ይቀበሉ፡፡

112
ይምሩ:- ከዚህም በተጨማሪ፤ ገንዘብን ለወደፊት ለማስቀመጥ በጥበብ መቆጠብን አስመልክቶ እግዚአብሔር
በምሳሌ 21÷20 ጥሩ መመሪያ ሰጥቶናል፡፡ “የከበረ መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል፤ አዕምሮ
የሌለው ሰው ግን ይውጠዋል፡፡”

ይምሩ:- ብዙ ሰዎች ድሃ ስለሆኑ ገንዘብ መቆጠብ እንደማይችሉ ያምናሉ። ለዛሬ የሚያስፈልጋቸውን በቂ


ገንዘብ ሳያገኙ፤ ለነገ ብለው የሚየስቀምጡት ነገር እንደማይኖር ያምናሉ፡፡

ይምሩ:- ይህ እውነት አይደለም፡፡ የገቢው መጠን ምንም ይሁን ምን፤ ማንም ሰው ገንዘብ መቆጠብ ይችላል፡፡

ይምሩ:- አሁን ጥቂት ደቂቃ ውሰዱና፤ ገንዘብን መቆጠብ ብልህነት መሆኑን በየቡድኖቻችሁ ተውያዩበት፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ4 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ጥያቄውን ያብራሩላቸው፡፡ መልስ አይስጡ፡፡

ይምሩ:- ምነው በቆጠብን ኖሮ ብለን የምንቆጭበት ደረጃ ላይ እስክንደርስ ድረስ፤ ገንዘብ መቆጠብን
ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ አይሆንም፡፡

ይምሩ:- ዓሳ የመሸጥ ትንሽ ቢዝነስ እንዳለችን አድርገን እናስብ፡፡ ዓሳውን ለመግዛት፣ በጭስ ለማድረቅ፣ እና
ለመጓጓዣ ወጪን የሚሸፍን ብቻ አጠራቅመናል። ሌላ ጭማሪ ገንዘብ የለንም፡፡

ይምሩ:- ይሁን እንጂ፤ አንድ ቀን ዓሳውን ለመግዛት በጉዞ ላይ እያለን ብስክሌታችን በአንድ ሞተር ብስክሌት
ቢገጭ እና የኋላ ጎማው ከጥቅም ውጪ ቢሆንስ? ዓሳችንን ገዝተን ለመሸጥ ወደ ሐይቁ የምንኄድበት
መጓጓዣ የለንም፡፡ በዚህ ሳቢያ ቢዝነሳችንን ማካሄድ አንችልም።

ይምሩ:- የታቀደ ቁጠባ ቢኖረን ኖሮ ግን ካስቀመጥነው ገንዘብ አውጥተን ብስክሌታችንን አስጠግነን፤ ጎማውን
አስቀይረን ቢዝነሳችንን ማስቀጠል እንችል ነበር።

ይምሩ:- በጀቶቻችንን ስናወጣ፤ ለቢዝነሳችንም ሆነ ለቤት የወጪና የገቢዎቻችን ዕቅድ እናወጣለን፡፡ የታቀደ
ቁጠባም እንዲሁ ተመሳሳይ ነው።

ይምሩ:- ድንገተኛ ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ስኬታማ ለመሆን፤ ለነዚህ ድንገተኛ ክስተቶች ማቀድ አለብን፡፡
ያለበለዚያ ሁል ጊዜም ህይዎታችን በትግል የተሞላ ስለሚሆን በፍፁም ወደ ፊት አንጓዝም፡፡

ይምሩ:- ያዘጋጀናቸው ሁለቱ የበጀት ዓይነቶች ምን ምን ናቸው? (የቢዝነስ እና የቤት ውስጥ በጀት)

ይምሩ:- ስለዚህ፤ ለቢዝነስም ሆነ ለቤታችን የተለያዩ የቁጠባ ዕቅዶችን ማዘጋጀት አለብን፡፡

ይምሩ:- ለቢዝነሳችን የታቀደ ቁጠባ በማዘጋጀት እንጀምራለን፡፡ የታቀደ ቁጠባ፤ ሁለት ቅድሚያ
የሚሰጣቸውን ነገሮች ከግምት ውስጥ ያስገባል፡-

1. ድንገተኛ እና ያልታቀዱ ፍላጎቶች

2. የወደፊት ግቦች እና ገቢ-አመንጪ ኢንቨስትመንቶች

ይምሩ:- ቢዝነስ ገና ያልከፈትን ከሆነ፤ ሦስተኛ የቁጠባ ዘርፍ ያስፈልገን ይሆናል፡፡ ይህም የመነሻ ካፒታል
ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ስለዚሁ ጉዳይ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በድጋሚ እንነጋገርበታለን፡፡

113
ይምሩ:- ድንገተኛ እና ያልታቀዱ ፍላጎቶች፤ በቢዝነሶቻችን ላይ ተጽዕኖ የሚያሳርፉ እንደ ጎርፍ ወይም
እሳት ቃጠሎ ላሉ የተፈጥሮ አደጋዎች የሚውሉ ናቸው፡፡ የብስክሌት ወይም የመኪና ጎማ መፈንዳት
ስራችንን በአግባቡ እንዳናከናውን መሠናክል ሊሆንብን ይችላል። ዝርፊያ/ውንብድና ወይም በሽታ ሌላው
እንቅፋት ነው፡፡

ይምሩ:- በአንድ ወቅት፤ በቢዝነሱ ላይ የተከሰተበትን አደጋ ምሳሌ አድርጎ ሊያካፍለን የሚችል ሰው አለ?

ይምሩ:- ምላሾችን ይቀበሉ፡፡ ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- የወደፊት ግቦች እና ገቢ-አመንጪ ኢንቨስትመንቶች፤ ቢዝነሶቻችንን ለማሻሻል ወይም


ለማስፋፋት የምንቆጥባቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ቁጠባዎች፤ ለሱቅ፣ ኮምፒዩተር ወይም ሞባይል ስልክ፣
ብስክሌት፣ የቤት ጣሪያ ማደሻም ሆነ አዲስ መቀየሪያ፣ እንዲሁም ተጨማሪ የሽያጭ ምርቶች መግዣ፤
ወይም ተጨማሪ ቢዝነስ ለመክፈት ሊውሉ ይችላሉ፡፡

ይምሩ:- ገቢ ማለት ከቢዝነሳችን የምናገኘው ገንዘብ ነው፡፡ ማመንጨት ማለት አንድ ነገር እንዲያድግ
ማድረግ ማለት ነው፡፡

ይምሩ:- ገቢ-አመንጪ ኢንቨስትመንቶች ማለት፤ ቢዝነሳችንን ይበልጥ ለማሳደግ (ለማስፋፋት) ከትርፋችን


ቀንሰን እንደገና መልሰን የምንጨምርበት ስልት ነው፡፡

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ የአናጺነት ቢዝነስ ብከፍት፤ የኤሌክትሪክ መጋዝ ለመግዛት ቁጠባዬን በገቢ-አመንጪ እና
በወደፊት ግቦች ላይ ላደረግ እችላለሁ፡፡ የኤሌክትሪክ መጋዙ፤ እንጨትን በፍጥነት በመቁረጥ ሥራዎችን
አፋጥኖ እንድጨስ በማድረግና ብዙ ደንበኞችን በማፍራት ቢዝነሴን ለማሳደግ ይረዳኛል፡፡

ይምሩ:- ከገቢ-አመንጪ የኢንቨስትመንት ዓይነቶች አንዱ፤ ቢዝነስ ከመጀመራችን አስቀድሞ የሚከሰት ነው፡፡
ይህም ቀደም ሲል ስለ በጀት በተማርነው ክፍል ላይ ያየነው መነሻካፒታል ነው፡፡

ይምሩ:- መነሻ ካፒታል ምን ማለት እንደሆነ በድጋሚ ማን ሊነግረን ይችላል?

ይምሩ:- ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡ (ቢዝነሶቻችሁን ስትጀምሩ


የሚያስፈልጓችሁ ዕቃዎች ወይም የምታወጡት ገንዘብ፡፡)

ይምሩ:- በጣም ጥሩ! መነሻ ካፒታል፤ ቢዝነሳችንን ስንጀምር የምናወጣቸው ወጪዎች ናቸው። እነዚህ
ወጪዎች የሚከናወኑት አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ቢዝነስን ለመጀመሪያ ጊዜ ለማቋቋም አስቀድመን በጀት
መመደብና መቆጠብ አለብን፡፡

ይምሩ:- መነሻ ካፒታል፤ እንደ ልብስ ስፌት ማሽን፣ የሽያጭ ምርት ክምችት፣ እንሰሳት፣ የሒሳብ
መመዝገቢያ ማሽን፣ ካልኩሌተር፣ ወዘተ ያሉ ነገሮችን ሁሉ ሊያካትት ይችላል፡፡

ይምሩ:- አንዳንድ ጊዜ፤ ንግድ ለመጀመር ብዙ ገንዘብ ሊኖረን እና መላው ሱቃችን በዕቃ ጢም ብሎ ሊሞላ
ይገባል ብለን እናስባለን።

ይምሩ:- ነገር ግን፤ አብዛኛዎቹ ስኬታማ ቢዝነሶች ከትንሽ ተነስተው ደረጃ በደረጃ የሚያድጉ ናቸው፡፡

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ ሪስቶራንት የምንከፍት ከሆነ ብዙ ዓይነት ምግቦች፣ ብዙ ጠረጴዛ እና ወንበሮች እንዲሁም
ብዙ አስተናጋጅ ሠራተኞች ሊኖሩን ይገባል ብለን እናስብ ይሆናል፡፡

114
ይምሩ:- ይሁን እንጅ፤ እነዚያን ሁሉ ነገሮች አሟልቶ የሚያስጀምር ገንዘብ ከሌለን፤ በትንሹ መጀመር
ይኖርብን ይሆናል።

ይምሩ:- ምናልባትም፤ በሶስት ጠረጴዛዎች፣ በደንብ ማዘጋጀት በምንችላቸውና በምናውቃቸው አምስት


የምግብ ዓይነቶች ብቻ ልንጀምር እንችላለን፡፡ ምናልባትም ሪስቶራንቱን ትተን በትንሽ ምግብ ቤት መጀመር
ያስፈልገን ይሆናል። ከዚያም ስለዚያ ትንሽ ምግብ ቤት የምግብ መጣፈጥ ወሬው እየተስፋፋ፣ ደንበኞች
ሲበዙ እና ቢዝነሳችን እያደገ ሲሄድ በምንቆጥበው ገንዘብ ሪስቶራንት መክፈት እንችላለን፡፡

115
የስኬት ታሪክ

ይምሩ:- ያለዚያም ቁጠባን፤ አዳዲስ ምርቶች ለደንበኞች በማቅረብ ለማስፋፋፊያ ማዋያ አድርጋችሁ
ልታስቡት ትችላላችሁ፡፡ በሠልጣኞች መጽሐፍ ገጽ ___ ላይ የቀረበችው የታሊ ደንበኛ ሳራ እንዲሁ አድርጋ
ነበር፡፡ በታሊ አነስተኛ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆን የሴቶች ጫማ ሽያጭ ቢዝነስ ሥራ ጀመረች፡፡
በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ የጫማ ማሳያ /ዲስፕሌይ/ ከፈተችች፤ ሞባይሏን ደግሞ አዳዲስ ምርቶች
ማስተዋወቂያ እና ትዕዛዞች መቀበያ አድርጋ ተጠቀመችበት፡፡

ይምሩ:- ሳራ፤ ከትርፍዋ የተወሰነውን በመቆጠብ አዳዲስ የሽያጭ ምርቶችን ለመግዛት እና ቢዝነሷን
ለማስፋፋት አስቀድማ ወስና ነበር፡፡ እናም የወንድ ጫማዎችን ሳይቀር ጨምራ መግዛት በመቻሏ የዕቃ
ክምችቷም ሆነ ሽያጯ በከፍተኛ ደረጃ አደገ፤ ትርፍዋም ጨመረ:: ሳራ በተመሳሳይ መልኩ ለሌሎችም ነገሮች
እንዴት ትቆጥብ እንደነበረ በሚቀጥለው ክፍልም እናያለን!

ይምሩ:- አንድን ትንሽ ምግብ ቤት ወደፊት የሰፋ እና የተሻለ ለማድረግ፤ ትርፋችንን በመቆጠብ መልሰን
ገቢ-አመንጪ ኢንቨስትመንቶች ላይ የምናውልበትን መንገዶች በተመለከተ በየቡድኖቻችሁ ተወያዩበት፡፡

ይምሩ:- ለዚህ የተወሰኑ ደቂቃዎችን ይፍቀዱላቸው፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ5 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ሀሳቦችን እንዲያመነጩ እና በማስታወሻዎቻቸው እንዲመዘግቡ


ያግዟቸው። እነዚህ ኢንቨስትመንቶች የሽያጭ ዕቃዎችን /ሸቀጣሸቀጦችን/ ከማብዛት ያለፉ ሊሆኑ ይገባል፡፡
አንድ የሱቅ ሠራተኛ ትልቁ መሻቱ ገቢን ማሳደግ ነው፡፡ ለሽያጭ የሚቀርቡ ብዙ ምርቶችን ዝም ብሎ
ከመግዛት ይልቅ፤ ምናልባትም አይነቶቻቸው የተለያዩ ዕቃዎችን ይግዙ ወይም ተጨማሪ ምርቶችን እንዲይዝ
ሱቁን ያስፋፉ።

ይምሩ:- ምን ምን ሀሳቦችን አመነጫችሁ?

ይምሩ:- ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- አሁን፤ ለየግል ቢዝነሶቻችን የመነሻ ካፒታሎቻችን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ በየቡድኖቻችን


እንወያይና እነዚህን ወጭዎች በሠልጣኞች መጽሐፍ በገጽ ____ ላይ እንጻፍ፡፡ ይህንን ለማድረግ 10
ደቂቃዎች ያህል ውሰዱ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ10 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ለውይይት ጊዜ ይስጡ፡፡ ተሳታፊዎቹ፤ በመነሻ ካፒታል እና
በገቢ-አመንጪ ኢንቨስትመንቶች መካከል ስላለው ልዩነት እንዲገነዘቡ ያግዟቸው። ለአሁኑ የመነሻ ካፒታል
ወጪ ዝርዝሮችን ብቻ ያስፍሩ።

ይምሩ:- ምን ዓይነት ቢዝነስ እንዳላችሁ እና የዚህ ቢዝነስ የመነሻ ካፒታል ወጪዎች ምን ምን ሊሆኑ
እንደሚችሉ የምታጋሩን ትኖራላችሁ? ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

116
ይምሩ:- አንዳንዶቻችሁ፤ ለቢዝነሳችሁ መነሻ ካፒታል የሚሆን ወጪ እንዲሸፈንላችሁ ለታሊ አነስተኛ
የብድር አገልግሎት ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ ምናልባትም አንዳንዶቻችሁ፤ ቀድሞውኑ ይህን ብድር
አግኝታችሁ ይሆናል፡፡ ወይም ሌሎቻችሁ፤ ከዚሁ ከታሊ አነስተኛ የብድር አገልግሎት የወሰዳችሁትን መነሻ
ካፒታል በመመለስ እና በመቆጠብ ላይ ልትሆኑ ትችላላችሁ።

ይምሩ:- የአነስተኛ ብድር መልሶ ክፍያ፤ ወጪ እንጂ የታቀደ ቁጠባ አይደለም፡፡

ይምሩ:- ምንም እንኳን ለመነሻ ካፒታል እንዲያግዝ ጥቃቅን እና አነስተኛ ብድር የመውሰድ ፍላጎት ካላችሁ
በዚያ ካፒታል ላይ ለመጨመር አስቀድማችሁ ከራሳችሁ ገንዘብ የተወሰነ እንድትቆጥቡ እናበረታታችኋለን፡፡
ገንዘብ የመቆጠብ ችሎታ እንዳላችሁ እና ቢዝነስ ለመጀመር የራሳችሁን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደምትችሉ
መረዳታችሁ አስፈላጊ ነው ብለን እናስባለን፡፡

ልምምድ

ይምሩ:- ቀጣዩ ጨዋታ በክፍል ውስጥ ወይም ከክፍል ውጪ የሚደረግ የቅብብሎሽ ውድድር ነው፡፡ የሩጫ
ቦታውን ትልቅ ወይም ትንሽ ያድርጉት። የመወዳደሪያ ቦታውን እንደፈለጉ ሊያሰፉት ወይም ሊያጠብቡት
ይችላሉ፡፡ ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት ቡድኖቹ ዝግጁ ሆነው መሰለፋቸውን ያረጋግጡ፡፡ እርስዎ ማብራሪያ
በሚሰጡበት ወቅት፤ ቡድን አመቻቾች ከፊት ሆነው ራሳቸውን ምሳሌ እርገው ያሳዩ፡፡

ይምሩ:- አሁን ጨዋታው የሚጀመርበት ጊዜ ነው- የቅብብሎሽ ውድድር! ሁለት ቡድኖች ይኖሩናል፡፡
እያንዳንዱ ቡድን በመስመር ይሰለፋል፡፡ አንደኛው ቡድን፤ “ድንገተኛ እና ያልታቀዱ ፍላጎቶች” ሌላኛው
ቡድን ደግሞ “የወደፊት ግቦች እና ገቢ-አመንጪ ኢንቨስትመንቶች” የሚሉ አርዕስቶችን ይወክላሉ፡፡

ይምሩ:- አንድ ረዳት በሰልፉ ትይዩ ከጎን ይቆማል፡፡ እኔ “ቀጥል” ስል፤ ከእያንዳንዱ ረድፍ ፊት ላይ ያሉት ወደ
ረዳቱ በመሮጥ በተሰጣቸው አርዕስት ስር የሚያስታውሱትን ቃል በጆሮው ሹክ ይሉታል፡፡

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ “ድንገተኛ እና ያልታቀዱ ፍላጎቶች” በሚለው አርዕስት ስር የተሰለፈ ሰው፤ “የሚያፈስ
ጣሪያ” ማለት ይችላል፡፡ በ“ወደፊት ግቦች እና ገቢ-አመንጪ ኢንቨስትመንቶች” ስር የሆነ ደግሞ፤ “አዲስ
ሠራተኛ መቅጠር” ሊል ይችላል፡፡

ይምሩ:- የመጀመሪያው ሰው መልስ እንደሰጠ፤ በፍጥነት ወደ ነበረበት ሠልፍ ይመለስና ከእርሱ ቀጥሎ
ለተሰለፈው ጓደኛው “ግጭ!” በማለት መዳፉን በመዳፉ ገጭቶ ከፍተኛ ሞራል ይሰጠዋል፡፡ “ግጭ!” የሚለውን
የሞራል መስጫ ስልት በተግባር ያሳዩዋቸው፡፡

ይምሩ:- “ግጭ!” ሞራል እንዳገኘህ ወደ ረዳቱ በፍጥነት በመሮጥ፤ በተሰጠህ አርዕስት ስር ሌላ


የምታስታውሰውን ቃል በማንሾካሾክ ትነግራለህ፡፡ (የቡድኑ ሠልጣኝ አባላት ቁጥር አነስተኛ ከሆኑ፤ሁሉም
በየተራ አንድ አንድ ነገር እንዲናገሩ ያድርጓቸው ፡፡) ቀደም ሲል የተባለውን ደግማችሁ ከተናገራችሁ ወደ
ቦታችሁ ሮጣችሁ ከመመለሳችሁ በፊት፤ ረዳቱ ሌላ እንድትናገሩ ያደርጋችኋል፡፡ እያንዳንዱ የቡድን አባል
በየተራ መሳተፍ አለበት።

ይምሩ:- በአንደኛነት የሚያጠናቅቅ ቡድን የጣፋጭ ሽልማት ያገኛል!

ይምሩ:- ወደ ቡድን 1 ያመልክቱ፡- ይህ ቡድን “ድንገተኛ እና ያልታቀዱ ፍላጎቶች” የሚል ርዕስ ይይዛል፡፡

117
ይምሩ:- ወደ ቡድን 2 ያመልክቱ፡- ይህ ቡድን የ“ወደፊት ግቦች እና ገቢ-አመንጪ ኢንቨስትመንቶች” የሚል
ርዕስ ይይዛል፡፡

ይምሩ:- ዝግጁ ናችሁ? በየርዕሶቻችሁ ስር ሁኑ፤ ተዘጋጁ፤ ጀምሩ!

መሪው እና ቡድን አመቻቾች፡- መስመሮቻቸውን ጠብቀው እንዲንቀሳቀሱ ያድጉ፡፡ ውድድሩ ሲጠናቀቅ


ለአሸናፊው ቡድን አድናቆትዎን በጭብጨባ ይግለጹ፡፡ ሁሉምንም ካስቀመጡ በኋላ ጣፋጭ ይሸልሟቸው፡፡

ይምሩ:- ሁላችሁም ቆንጆ ተሳትፎ ነው ያደረጋችሁት! በጣም ደስ የሚል ነበር! አሁን ወደ ውስጥ ተመልሰን
እንግባ፡፡

ይምሩ:- እሺ፤ እያንዳንዱ ቡድን አሁን ምን ያስባል?

ይምሩ:- ከአንደኛው ምድብ ይጀምሩ እና ወደ 10 የሚጠጉ መልሶችን ያጋሩ፤ በሠሌዳውም ላይ ያስፍሩ፡፡


ለሌላኛው ምድብም እንዲሁ ያድርጉ። እነዚህ የጠቀሷቸው ሁሉ የቢዝነስ እንጅ የግል ወይም የቤት ጉዳዮች
አለመሆናቸውን ርግጠኛ ይሁኑ፡፡

ይምሩ:- ዋው፤ ለብዙ ነገሮች መቆጠብ እንችላለን ማለት ነው!

ይምሩ:- በቢዝነሶቻችን ውስጥ ቁጠባ ስለሚጠይቁ የተለያዩ ነገሮች ስናስብ ቆይተናል፤ ለእያንዳንዱ ጉዳይ
በተናጠል ለመቆጠብና በጊዜ ሂደት በቂ ገንዘብ ለማግኜት የቁጠባ በጀት ማዘጋጀት ያስፈልገናል፡፡

ይምሩ:- ለነዚህ ለምንፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ በየወሩ መቆጠብ ይቻላል? (አይቻልም)፡፡

ይምሩ:- እነዚህ ሁሉ ክስተቶች እና ድንገተኛ አደጋዎችስ በወር ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ ይከሰታሉ?
(ብዙውን ጊዜ አይከሰቱም)።

ይምሩ:- ለዚህ ነው በአስራ ሁለቱም ወራት የቁጠባ ዕቅድ ማውጣት እና በየሳምንቱ አነስተኛ ገንዘብ
መቆጠብ አስፈላጊ የሆነው። በየጊዜው ትንሽ ትንሽ ስለመቆጠብ የሚነገር ምሳሌያዊ አባባል
ታስታውሳላችሁ? መልካም ጥበብ ነው!

ይምሩ:- የዳቦ መጋገሪያ ሱቅን ምሳሌ አድርገን በመውሰድ፤ የቁጠባ ዕቅድ እናውጣ፡፡

ይምሩ:- በውድድሩ ላይ እንዳየነው፤ በአንድ ዓመት ውስጥ በዳቦ መጋገሪያችን ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ሁለት
ድንገተኛ ክስተቶች ________________ እና ________________ ናቸው፡፡ (በአንድ ዓመት ጊዜ
ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ ሁለት ምሳሌዎችን ይምረጡ እና በሠሌዳው ላይ ይፃፉ፡፡ “በቃጠሎ ሙሉ በሙሉ
መውደም” እና መሠል ድንገተኛ አደጋዎችን በምሳሌነት አይጠቀሙ፡፡ ምክንያቱም ወጪው ከባድ ስለሆነ
ምሳሌውን ያበላሸዋል፡፡ እንደ ምጣድ ጥገና ያሉ ቀላል ወጪዎች ላይ ትኩረት ያድርጉ፡፡)

ይምሩ:- እነዚህ ድንገተኛ ክስተቶች ምን ያህል ያስወጣሉ?

ይምሩ:- ሁለቱንም የድንገተኛ አደጋዎች ክፍል አካትቱና የእያንዳንዱን ግምታዊ ዋጋ ይጠይቋቸው። እናም
ከዝርዝሩ ጎን ይመዝግቡ።

ይምሩ:- ከጨዋታው እንደተገነዘብነው፤ ቢዝነሳችንን ለማስፋፋት የሚረዱን ሁለቱ የወደፊት ግቦች እና


ገቢ-አመንጪ ኢንቨስትመንቶች _____________ እና ____________ ናቸው፡፡ (በጨዋታው ወቅት

118
ከተሰጡት መልሶችውስጥ ሁለቱን በምሳሌነት ከጨዋታው እንደተገነዘብነው፤ ቢዝነሳችንን ለማስፋፋት
የሚረዱን ሁለቱ የወደፊት ግቦች እና ገቢ-አመንጪ ኢንቨስትመንቶች _____________ እና
____________ ናቸው፡፡ ይምረጡ።)

ይምሩ:- እነዚህ ግቦች ምን ያህል ያስወጣሉ?መልሱን በሠሌዳው ላይ ያስፍሩ፡፡

ይምሩ:- አሁን፤ በሠሌዳው ላይ ባሰፈርነው የአካባቢው ዋጋ ላይ በመመርኮዝ ለእያንዳንዱ ምድብ /ክፍል/


በየሳምንት ምን ያህል ገንዘብ መቆጠብ እንደሚኖርብን ማወቅ ያስፈልገናል፡፡ ካልኩሌተሮቻችሁን በመጠቀም
ጠቅላላ ሒሳቡን ደምሩ፣ አካፍሉ፣ ከዚም ሳምንታዊ የቁጠባ ሂሳቡን መጠን ይወቁ።

ይምሩ:- እያንዳንዱን ምድብ ጠቅላላ ከደመሩ በኋላ በ12 ያካፍላሉ፤ ከዚያም እንደገና በ4 ያካፍላሉ፡፡
እያንዳንዱን ስሌት ደረጃ በደረጃ ሠሌዳው ላይ ይጻፉ እና ምን እያደረጉ እንደሆነ ያስረዷቸው፡፡

ይምሩ:- የቁጠባ ግቦቻችንን ለማሳካት፤ ከሳምንታዊ ሽያጫችን ላይ ልንቆጥብ የሚያስፈልገን አጠቃላይ


የገንዘብ መጠን ይህ ነው።

ይምሩ:- አሁን ለቢዝነሶቻችን የቁጠባ እቅድ ማውጣት በየቡድናችን እንለማመድ፡፡

ይምሩ:- በዚህ ​ዓመት ለመቆጠብ ግብ አድርጋችሁ ለመያዝ የምትፈልጓቸውን ሁለት ግቦች ከእያንዳንዱ
ምድብ ምረጡ፤ የሚጠይቀውን የእያንዳንዱን ዋጋ አስተውሉና ሳምንታዊ የቁጠባ እቅዶችን አዘጋጁ ፡፡ ይህን
ለመስራት ከ10 እስከ 15 ደቂቃዎች ውሰዱ፤ ስለሆነም ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቅማችሁ አስቡ፡፡

ይምሩ:- በጣም አስፈላጊ ነጥብ ስለሆነ፤በቂ ጊዜ ይስጧቸው፡፡ ከየቡድኑ ጋር ያላቸውን መስተጋብር ለማየት
ቡድን አመቻቾችን ዞረው ይጎብኟቸው፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ከ10-15 ደቂቃዎች ያህል፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ከእያንዳንዱ ሠልጣኝ ጋር በተናጠል
መወያየት ይፈልጉ ይሆናል፡፡ ለቢዝነስ ብቻ የቁጠባ ዕቅድ ያዘጋጁ። የዚህ ስልጠና ዋንኛ ግብ፤ እያንዳንዱ
ሠልጣኝ ዕቅድ (ቀለል ያለም ቢሆን) እንዲያዘጋጅ፣ የተወሰኑትን ለይቶ በማውጣት የቁጠባ ግብ
እንዲያስቀምጥ፣ እንዲሁም ለእነዚያ ለተቀመጡ ግቦች ገንዘብ እንዲተምን ነው። ከሠልጣኞች መካከል
ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ካሉ፤ ከቡድናቸው ውስጥ ላለ ሌላ ሰው እቅዳቸውን እንዲጽፍላቸው ሊነግሩ
ይችላሉ፡፡ በስዕል መግለጽም አንድ አማራጭ ነው፡፡ ስራ ፈጣሪዎቹ በወር እና በሳምንት የሚቆጥቡትን
የሒሳብ መጠን ለማወቅ የሚያደርጓቸውን ስሌቶች ይምሩ፡፡

ይምሩ:- የቢዝነስ ቁጠባ ዕቅድ በማውጣት ሁላችሁም ድንቅ ሥራ ሰርታችኋል! የዓመቱን የቁጠባ ግብ
ለማሳካት በየሳምንቱ ምን ያህል ገንዘብ በአስተማማኝ ቦታ ማስቀመጥ እንደሚያስፈልግ ከመካከላችሁ
ተነስተው ሊያጋሩን የሚችሉ ይኖራሉ?

ይምሩ:- እስከ ሶስት የሚደርሱ ተሳታፊዎች እንዲያጋሩ ይፍቀዱ፤ ለእያንዳንዳቸው አድናቆትዎን ይለግሱ፡፡

ይምሩ:- አሁን ደግሞ ስለ አንዳንድ ቢዝነስ ቁጠባ መሠናክሎች እንነጋገራለን፡፡

ይምሩ:- በየሳምንቱ ወይም በየወሩ ገንዘብ መቆጠብን አስቸጋሪ የሚያደርጉ ነገሮች ምንድን ናቸው?
(የቤተሰብ አባላት ፍላጎት መብዛት፣ በቂ ገቢ አለማግኜት፣ የምርት ወቅት አለመሆን ወይም ገበያ
የሚቀዘቅዝበት ጊዜ፣ ወዘተ፡፡)

119
ይምሩ:- የቤተሰባችን አባል ተቸግሮ፤ ምናልባትም ቢታመም፣ የቀብር ማስፈጸሚያ ገንዘብ ቢያጣ፣ ወይም
የትምህርት ቤት ክፍያ ባይኖረው፣ ወዘተ. የመሳሰሉ ችግሮች እንዳጋጠሙት እያወቅን እኛ ግን ይህን ሁሉ ችላ
ብለን ገንዘብ ማስቀመጥ አንዳንድ ጊዜ ከባድ ሊሆንብን ይችላል፡፡

ይምሩ:- ያም ሆኖ ለፍተን የምናገኘውን ገንዘብ ሁሉ የምናጠፋ ከሆነ ቢዝነሳችን ምን ይሆናል? (ቢዝነሳችን


ይወድቃልል፤ ወይም ሌላው ቢቀር ሊያድግ እና ሊስፋፋ አይችልም)።

ይምሩ:- ምላሾችን ይቀበሉ፡፡

ይምሩ:- ሰዎች ሲቸገሩ መርዳት አስፈላጊ ነው፡፡ ስለ ቤት ወጪ የቁጠባ እቅዶች ስንነጋገር፤ ለዚህ ​የተመደበ
የወጪ በጀት ሳይቀር እንዳለን እናያለን፡፡

ይምሩ:- ነገር ግን ከቢዝነስ የምናስገባውን ገንዘብ ሁሉ ወዲያው የምናጠፋ ወይም የምንሰጥ ከሆነ፤
ቢዝነሳችን ይወድቃል። ቢዝነሳችን ዛሬ ከወደቀ ደግሞ ነገ ቤተሰብን ሆነ ጓደኞቻችንን በጭራሽ የምንረዳበት
ዕድል አይኖረንም፡፡

ይምሩ:- ቤተሰባችንን ወደፊት በአስተማማኝ ሁኔታ መርዳት የምንችልበት ተመራጩ ዘዴ፤ ዛሬ ቢዝነሳችንን
ተንከባክቦ በማሳደግ ነው የምንለው ለዚህ ነው፡፡

ይምሩ:- ፍላጎቶቻችንን ለማሟላት ሁኔታዎችን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ የቁጠባ ዕቅድ ማዘጋጀት ጠቃሚ ነው፡፡
ለምሳሌ፤ ጉልህ ወጪዎቻችንን ለመሸፈን፤ የቢዝነሳችን ገቢ ዝቅተኛ በሚሆንበት ወቅት አነስተኛ ገንዘብ
መቆጠብ፣ እንዲሁም ከፍተኛ ገቢ በሚኖርበት ወቅት ተጨማሪ ገንዘብ መቆጠብ ሊኖርብን ይችላል።

ይምሩ:- ከዚህ የትምህርት ክፍል ስለ ቀሰማችሁት አንድ ነገር ልትነግሩኝ የምትችሉ ሁለት ሰዎች አላችሁ?

ይምሩ:- ሁለት ሠልጣኞች ወደ መድረክ ወጥተው አንድ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ ሃሳባቸውን በመደገፍ፤
ያጋሯቸውን ነጥቦች ደግመው ያብራሩ፡፡

ይምሩ:- የገንዘቡ መጠን ምንም ያህል እዚህ ግባ የማይባል ቢሆንም እንኳን፤ ዋናው ነጥብ በየሳምንቱ
ያለማቋረጥ መቆጠባችን ነው። ሁሉም የቢዝነስ ቁጠባ ዕቅዶችን የማውጣት ድንቅ ተግባር! ሁላችሁም
ጥሩ መረዳት ነው ያላችሁ፡፡ በሚቀጥለው ክፍል፤ ስለ ቤት ወጪ የቁጠባ ዕቅድ እንማራለን!

120
// ክፍል 15 //
የቤት ወጪ ቁጠባ

የሚወስደው ጊዜ፡- 1 ሠዓት

ግቦች:-
1. ተሳታፊዎች፤ የቤት ወጪ ቁጠባ ለምን እንደሚያስፈልጋቸው ግንዛቤ ያገኛሉ፡፡
2. ተሳታፊዎች፤ ትንሽ በትንሽ መቆጠብን እና በግል ህይወታቸው ውስጥ ለየትኛው መቆጠብ
እንደሚችሉ ይማራሉ፡፡
3. ተሳታፊዎች፤ የቤት ወጪ ቁጠባ ዕቅድን ያወጣሉ፡፡

አቅርቦቶች፡-
> እስክሪብቶች > የነጭ ሰሌዳ ማርከሮችች
> የሠልጣኞች መጽሐፍት > ጣፋጮች
> ነጭ ሠሌዳ > የሒሳብ መደመሪያ ካልኩሌተር

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


> የቤተሰብ ፍላጎቶች > ክብረ-በዓላት እና ልዩ ዝግጅቶች
> ድንገተኛ እና ያልታሰቡ /ያልታቀዱ/ > የወደፊት ግቦች
ፍላጎቶች

ትዕይንቶች(በግድግዳ ወይም በቦርድ ላይ የተለጠፉ ወይም በሠልጣኞች መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱ)፡-


> የቤተሰብ ፍላጎቶች > ክብረ-በዓላት እና ልዩ ዝግጅቶች
> ድንገተኛ እና ያልታሰቡ /ያልታቀዱ/ > የወደፊት ግቦች
ፍላጎቶች

ዝግጅት:-
> ስኬታማ ስላደረጋቸው ቁጠባ ምስክርነትን እንዲያጋሩ ለተሳታፊዎች ዕድል ይሰጣል፡፡ ይህንን
ለማድረግ ፈቃደኛ ከሆኑ፤ ተሳታፊዎቹን አስቀድመው ያዘጋጇቸው፡፡
> ቁጠባን አስመልክቶ ለሚዘጋጀው ድራማ አራት ፈቃደኛ ሰዎችን አስቀድመው ያሰባስቡ እና ያዘጋጁ።
> ተሳታፊዎች ቁጠባን ሲያሰሉ፤ በወር የሚደርሰውን ለማወቅ በ12፤ ከዚያም ሳምንታዊውን ለማስላት
በ4 እንዲያካፍሉ እናደርጋለን፡፡ በዚህም ስሌት በ48 ሳምንታት፤ ዓመታዊ ቁጠባዎችን ማወቅ
እንደሚቻል እንገነዘባለን፡፡ ነገር ግን ይህንን የምናደርገው፤ ነገሮችን በማቅለል ገንዘብ ከወር እስከ ወር
ለማይበቃቸው ሠልጣኝ አባላት ሁሉ ቁጠባን ተደራሽ ለማድረግ ነው።

121
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ:-
> መጽሐፈ ምሳሌ 30÷25
> መጽሐፈ ምሳሌ 13÷11

ይምሩ:- በእውነቱ የቢዝነስ ቁጠባ ዕቅድ አወጣጥን በሚገባ ሠርታችኋል!

ይምሩ:- አሁን ደግሞ፤ ምናልባትም ከጠቀሜታ አኳያ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነውን፤ የቤት ወጪ ዕቅድ
እናወጣለን፡፡

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ የምናገኘው ገቢ ለምግብ ለልጆቻችን የትምህርት ቤት ክፍያ እና ተያያዥ ወጪዎችን


ብቻ የሚሸፍን እንደሆነ አድርገን እናስብ፡፡ ሌላ ተጨማሪ ገንዘብ የለንም፡፡

ይምሩ:- ይሁን እንጅ፤ ከእለታት አንድ ቀን አንዱ ልጃችን በጣም ታምሞ ብናገኘውስ? እንዲያውም
ተገቢውን ህክምና ካላገኘ፤ በጥቂት ወራት ውስጥ እንደሚሞት ቢነገረን፡፡

ይምሩ:- የቁጠባ ዕቅድ ቢኖረን ኖሮ፤ ያጠራቀምነውን ገንዘብ አውጥተን አስፈላጊውን የህክምና ወጪ
መሸፈን እንችል ነበር።

ይምሩ:- ስለ ቢዝነስ ቁጠባ በተወያየንበት ጊዜ፣ ​በሁለት ምድብ ከፍለን የመቆጠብ ዕቅድ አውጥተናል፡፡
የቤተሰብ ወጪ ቁጠባን ስናቅድ ደግሞ በአራት ምድቦች ከፍለን ነው! በሠሌዳው ላይ ወደ ተዘረዘሩት ምድቦች
ያመልክቷቸው፡፡

● የቤተሰብ ፍላጎቶች
● ድንገተኛ እና ያልታሰቡ /ያልታቀዱ/ ፍላጎቶች
● ክብረ-በዓላት እና ልዩ ዝግጅቶች
● የወደፊት ግቦች

ይምሩ:- የቤተሰብ ፍላጎቶች የሚባሉት እንደ ትምህርት ቤት ክፍያዎች እና ለቤተሰብ የሚያስፈልጉን


የቤት ዕቃዎችና መሠል ነገሮች ናቸው።

ይምሩ:- ስለ ድንገተኛ እና ያልታሰቡ /ያልታቀዱ/ ፍላጎቶች ምንነት በቢዝነስ ቁጠባ ዙሪያ


ተረድተናል፤ ከቤት ወጪ ጋር በተያያዘ ግን የተለዩ ናቸው፡፡

ይምሩ:- በቤተሰብ ውስጥ፤ ድንገተኛ ወይም ያልታሰበ /ያልታቀደ/ ፍላጎት ምን ሊሆን እንደሚችል የሚነግረኝ
አለ? (ህመም፣ የቀብር ማስፈጸሚያ ወጪ፣ የቤት ቃጠሎ፣ የተበላሸ ጣሪያ፣ ወዘተ፡፡)

ይምሩ:- በጣም ጥሩ ምሳሌዎች! ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ክብረ-በዓላት እና ልዩ ዝግጅቶች፤ ለመታደም የምትጓዙበት፣ ወይም ስጦታን የምትገዙበት እንደ


ሠርግ እና የምረቃ ስነ-ስርዓት ያሉ ናቸው፡፡

122
ይምሩ:- በመጨረሻም፤ የወደፊት ግቦች የምንላቸው፤ ቤቶቻችንን ለማሻሻል ወይም ለማስፋፋት
የሚያስፈልጉን ነገሮች እንዲሁም የቤተሰብን የወደፊት ጥቅም የሚያረጋግጡ ግቦች ናቸው፡፡ እነዚህም፤
ለቤታችን መሻሻል ወይም ጭማሪ፣ ብስክሌት ወይም አዲስ ጣሪያ መቀየር፣ ወይም ለቀጣይ ትምህርት ክፍያ
መቆጠብ ሊሆኑ ይችላሉ።

ይምሩ:- የቤት ወጪ ቁጠባ ልምድ ያለው እና ስለ ጠቀሜታውም ምስክርነት ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ስራ
ፈጣሪ ካለ በየመሃሉ ዕድል ይስጡ፡፡

የስኬት ታሪክ

ይምሩ:- ካለፈው ምዕራፍ፤ ስለ ሳራ ታሪክ ታስታውሳላችሁ? በማስተዋልና በጥበብ መቆጠብ በመቻሏ፤


ከሴት ጫማ ሌላ የወንድ ጫማ በመጨመር የአቅርቦት መጠኗን ከፍ በማድረግ ሽያጯን አሳድጋለች፡፡

ይምሩ:- ከዚህም በላይ ከሳራ ብዙ መማር እንችላለን! አያችሁ፤ ለቤት ወጪ ፍላጎቶቿም እንዲሁ በጥንቃቄ
ትቆጥብ ነበር፡፡

ይምሩ:- ሳራ ብድሯን ከፍላ ከጨረሰች በኋላ፤ “ሴት ልጄን ኮሌጅ ማስተማርን ጨምሮ በህይዎቴ
አከናውናቸዋለሁ ብየ አስቤያቸው የማላውቃቸውን ነገሮች ማሳካት ችያለሁ” በማለት ነበር ለታሊ ማህበራዊ
ሠራተኛ ያጫወተችው፡፡

ይምሩ:- በሳራ ጥበብ የተሞላበት ቁጠባ ሳቢያ፤ ልጇ የኮሌጅ ትምህርት የመከታተል ዕድል አገኘች፤ እንዲሁም
የመላ ቤተሰቧ የወደፊት ሕይወት ተለወጠ።

ይምሩ:- እንዴት ልታሳካው ቻለች? ዕቅድ በማውጣት፣ በትንሽ በትንሹ በመቆጠብ እና ከዚህ ውሳኔዋ ዝንፍ
ሳትል ተግባራዊ በማድረጓ!

ይምሩ:- አሁን፤ ስለ ቤት ወጪ ቁጠባ ዕቅድ አወጣጥ በጋራ እንሰራለን፡፡

ይምሩ:- በዓመት ውስጥ በግል ሕይወታችን ሊከሰቱብን የሚችሉ ሁለት ድንገተኛ አደጋዎች ምን ምን
ናቸው?

ይምሩ:- ምሳሌዎቹን ከተሳታፊዎች ይቀበሉና በሠሌዳው ላይ ይፃፉ፡፡

ይምሩ:- እነዚህ ሁለት ድንገተኛ አደጋዎች በአጠቃላይ _______ ብር ያስወጡናል ብለን እናስባለን፡፡ በወጪ
የዋጋ አተማመን በሚፈጠር አላስፈላጊ ክርክር ከስልጠናው መስመር ላለመውጣት የእነዚህንም ሆነ የቀጣይ
ምሳሌዎችን ወጪ በሠሌዳው ላይ ያስፍሩ፡፡

ይምሩ:- ሁለት የምናከብራቸው በዓላት እና ልዩ ዝግጅቶች ምን ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

ይምሩ:- ሁለት የቤተሰብ ፍላጎቶችስ ምን ሊኖሩብን ይችላሉ?

ይምሩ:- ምሳሌዎችን ይጠብቁ እና በቦርዱ ላይ ይፃፉ ፡፡ አንድ ሰው “ምግብ” ቢል፤ “ይህ የቁጠባ ዕቅዳችን አካል
መሆን አለበት ወይስ የቤት ወጪ በጀት?” በማለት ይጠይቁ። (የቤት ወጪ በጀት፡፡) ለእያንዳንዱ የተወሰነ
የገንዘብ መጠን ይመድቡ፡፡

123
ይምሩ:- በቤት ወጪያችን ውስጥ ሁለት የወደፊት ግቦቻችን ምንድን ናቸው?

ይምሩ:- ምሳሌዎቹን ይፃፉ፡፡ለእያንዳንዱ የዋጋ ተመሆን አለበትመን ይመድቡ።

ይምሩ:- ሁላችንም ቡየድኖቻችን፤ እነዚህን የአንድ ዓመት የቁጠባ በጀት ምድቦች እንደምርና በ12 ወራት
በማካፈል ወርሃዊ ቁጠባ ስንት መሆን እንዳለበት እንገነዘባለን፡፡ ይህን ቁጥር ካገኘን በኋላ እንደገና በ4 አካፍለን
በየሳምንቱ ምን ያህል መቆጠብ እንዳለበት እናውቃለን፡፡

ይምሩ:- ለዚህ በቂ ጊዜ ይፍቀዱላቸው፡፡ ወደ ቀጣይ ክፍል ከመሻገርዎ በፊት፤ እያንዳንዱን ቡድን ዞረው
ያረጋግጡ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ2 ደቂቃዎች ያህል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ምሪት እየሰጡ፤ ተሳታፊዎች በራሳቸው
ይህን እንዲሰሩት ይፍቀዱላቸው፡፡ ተሳተፊ ያልሆነ ሰው ካጋጠመዎት፤ መደመሪያ ካልኩሌተር ይስጡት እና
እንዲለማመድ ያ ግዙት።

ይምሩ:- ለቤተሰብ ፍላጎቶች ማሟያ በየሳምንቱ ምን ያህል ገንዘብ መቆጠብ እንደሚያስፈልገን የትኛው
ቡድን ሊነግረኝ ይችላል?

ይምሩ:- ትክክለኛውን መልስ ለሚያጋራ ለእያንዳንዱ ቡድን አድናቆትዎን ይግለጹ፡፡ መልሱን ለማመሳከር
እርስዎ አስቀድመው መስራት ይኖርብዎታል፡፡

ይምሩ:- ለድንገተኛ እና ላልታሰቡ /ላልታቀዱ/ ፍላጎቶች በየሳምንቱ ምን ያህል ገንዘብ መቆጠብ


እንደሚያስፈልገንስ ማን ሊነግርኝ ይችላል?

ይምሩ:- ምላሽ ይቀበሉ፡፡

ይምሩ:- አሁን ደግሞ የክብረ-በዓላት እና ልዩ ዝግጅቶች ሳምንታዊ ቁጠባ ምን ያህል መቆጠብ


እንደሚያስፈልገንስ የትኛው ቡድን ይነግረኛል?

ይምሩ:- ምላሽ ይቀበሉ፡፡

ይምሩ:- ለወደፊት ግቦችስ?

ይምሩ:- ምላሽ ይቀበሉ፡፡

ይምሩ:- ለአንድ ወር ያህል እንደቆጠብን አድርገን እናስብ፡፡

ይምሩ:- አሁን፤ አራቱን ፈቃደኛ ተዋንያኖቼን እፈልጋለሁ! (አስቀድሞ የሠለጠኑና የተዘጋጁ በጎ ፈቃደኞች
ወይም አመቻቾችን ይጠቀሙ፡፡)

ይምሩ:- የመጀመሪያው ተዋናይ እንዲህ እያለ ይገባል፡-

ተዋናይ 1፡- “ዛሬ የጓደኛዬ የልደት ቀን ስለሆነ ስጦታ መግዛት እፈልጋለሁ፡፡ አንድ የሆነ ቆንጆ ነገር ገዝቼ
ልሰጣት እፈልጋለሁ፡፡ ለዚህ ስጦታ ስንት ብር ሊያስወጣኝ ይችላል?”

ይምሩ:- ወደየቡድኑ ዞረው እነዲህ በማለት ይጠይቁ፡-

ይምሩ:- ከየትኛው የቁጠባ ምድብ /ክፍል/ ነው ገንዘብ ማውጣት ያለብኝ? (ክብረ-በዓላት እና ልዩ ዝግጅቶች)

124
ይምሩ:- ለጓደኛህ የልደት ስጦታ ምን ያህል ወጪ የጠይቃል?

ይምሩ:- ይህን ያህል የገንዘብ መጠን ከጠቅላላው ላይ ይቀንሱ እና ብሩን ቆጥረው ለተዋናዩ እየሰጡት እንዳለ
አድርገው ያስመስሉ።

ይምሩ:- በቂ ገንዘብ ካለ፡- ለጓደኛህ ስጦታ መግዣ _____ ብር (የስጦታው ዋጋ) አግኝተሀል።

ተዋናይ 1፡- ከክፍል ይወጣል።

ይምሩ:- ሁለተኛው ተዋናይ እየተነጫነጨ በፍጥነት ይገባል:-

ተዋናይ 2፡- “ትናንት ማታ ወደ ቤት ስመጣ፤ ሞባይሌ ከኪሴ ወድቆ ተሰበረ።”

ይምሩ:- ለአዲስ ስልክ መቀየሪያ ከየትኛው የቁጠባ ምድብ /ክፍል/ ማውጣት ይኖርብናል? ምላሽ ይቀበሉ።
(ድንገተኛ እና ያልታቀዱ ፍላጎቶች)

ይምሩ:- ስልኩ ዋጋው ስንት ይሆናል? በቂ ገንዘብ አለን? (አዎ፡፡)

ይምሩ:- በቂ ገንዘብ ካለ፤ አዲስ ስልክ ለመቀየር ______ ብር (የስልኩ ዋጋ) አግኝተሀል።

ይምሩ:- የወሰነውን የገንዘብ መጠን ለተዋናዩ ይስጡ እና ከጠቅላላው ቁጠባ ላይ ይቀንሱ።

ተዋናይ 2፡- ከክፍል ይወጣል።

ተዋናይ 3፡- ወደ ክፍል በመግባት እንዲህ ይላል፤ “የልጄ ጫማ ስለጠበባት ስትረግጥ እያመማት ነው፡፡ ሠፋ ያለ
ጫማ ልገዛላት እፈልጋለሁ፡፡

ይምሩ:- ይህ ወጪ በየትኛው የቁጠባ ምድብ /ክፍል/ የሚመደብ ነው? (የቤተሰብ ፍላጎቶች)

ይምሩ:- አዲሱ ጫማ ስንት ብር ያወጣል? ምላሾችን ይቀበሉ።

ይምሩ:- በቂ ገንዘብ ካለ፤ ለልጅህ አዲስ ጫማ መግዣ_______ (የጫማው ዋጋ) አግኝተሀል።

ይምሩ:- የተወሰነውን የገንዘብ መጠን ለተዋናዩ ይስጡት እና ከጠቅላላው ቁጠባ ላይ ይቀንሱ።

ተዋናይ 3፡- ከክፍል ይወጣል።

ተዋናይ 4፡- ገብቶ እንዲህ ይላል፤ “በፍጥነት ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ የ_________ (ሞተር ሳይክል
ወይም ብስክሌት… በ ወደፊቱ ግቦች ምድብ እንደቆጠብነው መጠን) መግዣ ገንዘብ እፈልጋለሁ፡፡ ለዚህ
የሚሆን በቂ ብር ይኖራል?”

ይምሩ:- ገንዘቡ ከየትኛው ምድብ ነው መገኘት ያለበት? (የወደፊት ግቦች)

ይምሩ:- ____________ (ሞተር ሳይክል ወይም ብስክሌት) ዋጋው ስንት ነው? (አካባቢያዊ የዋጋ ተመን
መረጃ ይሰብስቡ። ይህ ወጪ፤ ለአንድ ወር ከቆጠብነው የገንዘብ መጠን የበለጠ መሆን አለበት።)

125
ይምሩ:- ለዚህ የሚበቃ ብር አለን? (የለንም፡፡)

ይምሩ:- ይሄን ሞተር ብስክሌት ወይም ሳይክል ለመግዛት፤ ከሌሎች የወጪ ምድቦች /አካውንቶች/ የተራረፉ
ሂሳቦችን ከዚህ ምድብ ጋር ጨምረን መግዛት ይኖርብናል? (አይኖርብንም ማለት አለባቸው፡፡)

ይምሩ:- ለምን? (የተቆጠበ በቂ ገንዘብ ከሌለን፤ መጠበቅ ይኖርብናል፤ ወዘተ)፡፡

ይምሩ:- በቂ ለመቆጠብ ለምን ያህል ጊዜ መጠበቅ አለባቸው? (ከተሳታፊ ምላሽ ይጠብቁ፤ ያለዚያም
ችግሩን በሠሌዳው ላይ ያስፍሩ)፡፡

ይምሩ:- (ለተዋናይ 4) ይቅርታ፤ በአሁኑ ወቅት፤ በቁጠባችን ውስጥ በቂ ገንዘብ እንደሌለን ቡድኑ ወስኗል፡፡

ይምሩ:- ሞተር ብስክሌት ወይም ሳይክሉን መግዛት የሚያስችል በቂ ገንዘብ ለማግኜት፤ ስንት ወራት
መቆጠብ እንደሚያስፈልገን ሒሳቡን አስሉ። (የብስክሌቱ/ሳይክሉን ዋጋ በወደፊት ግቦች ምድብ ወርሃዊ
ቁጠባ ማካፈል)።

ቡድን አመቻቾች፡- ለ2 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ተሳታፊዎች ይህን ሒሳብ እንዲሰሩ ይምሯቸው፡፡

ይምሩ:- ለብስክሌትህ በቂ ቁጠባ እሰክናደርግ ድረስ _______ (የወራት ቁጥር) ወራትን መጠበቅ
ያስፈልገናል።

ተዋናይ 4፡- ከክፍል ይወጣል።

ይምሩ:- ሁላችሁም ድንቅ ሥራ ሠርታችኋል! ለተዋንያኖቹ ጣፋጮች ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ለጠየቁት ብስክሌት መግዣ የሚሆን ገንዘብ እንደሌላችሁ ለልጆቻችሁ መንገር ከባድ ነው?

ይምሩ:- አዎ፤ በጣም ከባድ ነው፡፡ ገንዘብን በተመለከተ የወደፊት ዕቅድ ማውጣት በጣም አስፈላጊ
የሚሆነውም ለዚሁ ነው።

ይምሩ:- መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ነፍሳት የሚነግረን ነገር አለው፡፡ ምንም እንኳ በአካል ትናንሽ እና ደካማዎች
ቢሆኑም፤ ለወደፊት አስበው እንዴት ማከማቸት እንደሚችሉ ይተርክልናል፡፡ መጽሐፈ ምሳሌ 30÷25
እንዲህ ይላል፡- “ገብረ ጉንዳን ኃይል የሌላቸው ህዝቦች ናቸው፤ ነገር ግን በበጋ መኗቸውን ይሰበስባሉ”፡፡

ይምሩ:- መጽሐፈ ምሳሌ 13÷11 ንም አስታውሱ፡- “በችኮላ የምትከማች ሀብት ትጎድላለች፤ ጥቂት በጥቂት
የተከማቸች ግን ትበዛለች፡፡”

ይምሩ:- ምንም እንኳን ብዙ የሚባል ነገር ባይኖረን፤ ጥቂት በጥቂቱ መቆጠብ የሚያስችል አቅም አለን፡፡ የሆነ
ነገር ባገኘን ቁጥር፤ የተወሰነውን ደህንነቱ በተጠበቀ ስፍራ አስቀምጠን የመቆጠብ ልምድ በማዳበር የወደፊት
ግቦቻችንን ማሳካት እንችላለን።

ልምምድ

ይምሩ:- አሁን፤ ለየቤታችን ወጪ የቁጠባ ዕቅዶች የማውጣት ልምምድ እናደርጋለን፡፡

126
ይምሩ:- በሚቀጥለው ዓመት ልትቆጠቧቸው የምትፈልጓቸውን ሁለት የወደፊት ግቦች በሠልጣኞች
መጽሐፍ ገጽ ____ ላይ በየቡድኖቻችሁ ጻፉ፡፡ እነዚህ ግቦች፤ በበበጀቶቻችን ዝርዝር ውስጥ የሌሉ መሆን
አለባቸው፡፡

ይምሩ:- በበጀት እና በቁጠባ ዕቅድ መካከል ያለውን ልዩነት በድጋሚ ሊያስታውሰን የሚችል ሰው አለ?

ይምሩ:- ምላሽ ይቀበሉ፡፡

ይምሩ:- ለመቆጠብ የምትፈልጉትን ነገር ከእያንዳንዱ ዝርዝር አጠገብ የዋጋ ተመን አስስቀምጡ፤ ከዚያም
እያንዳንዱን ምድብ ጠቅላላ ድምር አስፍሩ።

ይምሩ:- በመቀጠልም፤ ጠቅላላ ድምሩን ለ12 በማካፈል በየወሩ ምን ያህል ገንዘብ መቆጠብ
እንደሚያስፈልጋችሁ ወስኑ። ከዚያም፤ ሳምንታዊ ቁጠባችሁን ለማወቅ እንደገና በ4 አካፍሉ።

ይምሩ:- ለወደፊት ግቦቻችሁ የቁጠባ ዕቅዶችን፤ በሠልጣኞች መጽሐፍ ገጽ ____ ላይ አሁን ፃፉ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ8 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ከእያንዳንዱ ምድብ ሁለት ሁለት ግቦችን በሠልጣኞች መጽሐፍ
ገጽ ____ ላይ በጽሁፍ ወይም በስዕል እነዲገልጹ ያበረታቷቸው፡፡ የእያንዳንዱን ምድብ ዓመታዊ የቁጠባ
ግቦች መወሰናቸውን፤ ከዚያም በወርሃዊ እና ሳምንታዊ ግቦች መከፋፈላቸውን ርግጠኛ ይሁኑ፡፡ የቤት ወጪ
ብቻ መሆኑንም ያረጋግጡ!

ይምሩ:- ስላዘጋጀው የቁጠባ ዕቅድ ሊያጋራን የሚፈልግ ሰው አለ?

ይምሩ:- ጊዜ ሰጥተው፤ ተሳታፊዎች ሃሳባቸውን እንዲያጋሩ ያበረታቱ፡፡

ይምሩ:- ድንቅ ሥራ!

ይምሩ:- ሁላችሁም በሚገባ ተረድታችሁታል! ዛሬ ማታ የቤት ስራችሁ የሚሆነው፤ የቤት ቁጠባ እቅዳችሁን
መጨረስ እና እቅዳችሁን እውን ለማድረግ ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ ነው።

ይምሩ:- ይህ ከአንዳንድ የቤተሰቦቻችሁ አባላት ጋር መወያየትን ወይም የባንክ ሂሳብ መክፈትን ወይም
የተወሰነ ገንዘብ አስተማማኝ ቦታ ማስቀመጥን (መቆጠብን) ሊያካትት ይችላል።

ይምሩ:- ከዚህ የትምህርት ክፍል ስለ ቀሰማችሁት አንድ ነገር ልትነግሩኝ የምትችሉ ሁለት ሰዎች አላችሁ?

ይምሩ:- ሁለት ሠልጣኞች ወደ መድረክ ወጥተው አንድ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ ሃሳባቸውን በመደገፍ፤
ያጋሯቸውን ነጥቦች ደግመው ያብራሩ፡፡

ይምሩ:- ስለተሳትፏችሁ አመሰግናለሁ! በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ እንገናኝ፡፡

127
// ክፍል 16 //
ሥነ ምግባር

የሚወስደው ጊዜ፡- 1 ሠዓት

ግቦች:-
> ተሳታፊዎች፤ ሥነ ምግባርን የተላበሰ ቢዝነስ ጠቀሜታው ምን ያህል አዎንታዊ እንደሆነ ይገነዘባሉ፡፡
> ተሳታፊዎች፤ ለእነርሱ እንዲደረግላቸው የሚፈልጉትን ለሌሎችም የማድረግን ጠቀሜታ ይረዳሉ፡፡

አቅርቦቶች፡-
> እስክሪብቶዎች > የሠሌዳ ማርከሮች
> የሠልጣኞች መጽሐፍት > በአከባቢው የሚሸጥ የልጆች ልብስ
> ጣፋጮች > ቀሚስ ወይም ሌላ እቃ
> ነጭ ሠሌዳ > ገንዘብ (ብር)

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


> ሥነ ምግባር
> የሥነ ምግባር ደንብ

ዝግጅት:-
> ሊባል የታሰበውን ግልጽ ለማድረግ ሲባል በዚህ ክፍል ውስጥ ያሉ ድራማዎችን ከመደበኛ ክፍለ
ጊዜው አስቀድመው በቂ ልምምድ ማድረግዎን ርግጠኛ ይሁኑ፡፡ ድራማዎቹ ረዘም ያሉ ስለሆኑ ጊዜ
ይወስዳሉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ:-


> ማቴዎስ 22÷37-40

128
ይምሩ:- በዚህ የስልጠና ክፍል፤ ሥነ ምግባራዊ እና ጥበባዊ ምርጫዎችን በማድረግ በማህበረሰባችን ውስጥ
መሪ መሆን እንዴት እንደሚቻል እንወያያለን፡፡

ይምሩ:- ከዚህ የሥነ ምግባር ስልጠና በኋላ፤ የተማርናቸውን ትምህርቶች በሙሉ አሁን ባሉን ሆነ ወደፊት
በሚኖሩን ቢዝነሶች ላይ ተግባራዊ እናደርጋለን፡፡

ይምሩ:- ሥነ ምግባር፤ የአንድን ሰው ባህሪ የሚገዙ የሞራል መርሆዎች ናቸው፡፡

ይምሩ:- እነዚህን መሠረታዊ መርሆዎች በአብዛኛው የምንቀስማቸው፤ በልጅነት ከወላጆቻችን፣ ከዚያም


በሀገራችን ካሉት ሕጎች እና ደንቦች፣ ወይም ከምንከተለው ሃይማኖት ሊሆን ይችላል፡፡

ይምሩ:- እርስዎ ሥነ ምግባርን የት እና እንዴት እንደ ተማሩ ለተሳታፊዎች ያጋሩ፡፡

ይምሩ:- ሥነ ምግባር፤ የእያንዳንዳችንን የአኗኗር ዘይቤ እንዲመሩ የምንፈቅድላቸውን እሴቶች ይወክላል፡፡

ይምሩ:- የሃይማኖት ህግ አስተማሪዎች ኢየሱስ ክርስቶስን “ከህግ ማናይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት?” ብለው
እንደጠየቁት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፡-

“ታላቂቱ ተዕዛዝ እንዲህ የምትል ናት፡- ‘እስራኤል ሆይ÷ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው÷ አንተም
በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህም በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ’ የምትል
ናት። ፊተኛይቱ ትዕዛዝ ይህች ናት፡፡ ሁለተኛይቱም፡- ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” የምትል እርስዋን
የምትመስል የህች ናት፡፡ ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።”

ይምሩ:- እንደ ክርስቲያን፤ ይህ የእምነታችን መሠረት ነው፡፡ በቢዝነሶቻችን ይሁን በግል ህይዎታችን፤
ሌሎችን እንዴት መያዝ እንዳለብን በምናደርጋቸው ውሳኔዎች ሁሉ ይህን አስተማህሮ ተግባራዊ ልናደርገው
እንችላለን፡፡

ይምሩ:- እግዚአብሔር አምላክን በፍጹም ልባችን መውደድ እና ባልንጀራችንን እንደራሳችን መውደድ፤ ሁለቱ
እጅግ በጣም አስፈላጊ ትዕዛዛት ለምን እንደሆኑ በየቡድኖቻችሁ ተወያዩ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ4 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ይህን ውይይት በመምራት ያግዟቸው፡፡

ይምሩ:- በየቡድኖቻችሁ ስለ ተወያያችሁበት ጉዳይ ማካፈል የምትፈልጉ አላችሁ ?

ይምሩ:- በጣም አስፈላጊ እና መሠረታዊ የሆኑ መርሆዎች እና እሴቶች በአኗኗራችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ
የማሳደር አቅም ይኖራቸዋል ፡፡ ይህንንም የሥነ ምግባር ደንብ ብለን ልንጠራው እንችላለን፡፡

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ የአንድ ሰው ሥነ ምግባር ህይወቱን ሙሉ በሀቀኝነት እንዲኖር ሊያደርገው ይችላል፡፡

ይምሩ:- የሌላኛው ሰው ሥነ ምግባር ደግሞ፤ ለተቸገሩ ሁሉ ለጋስ እንዲሆን ሊያደርገው ይችላል ፡፡

129
ይምሩ:- የሥነ-ምግባር ደንቦች ስለሆኑት መሠረታዊ መርሆዎች እና እሴቶች በየቡድኖቻችሁ ተወያዩበት፡፡
ለእናንተ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ምንድን ናቸው? ግልጽ ሁኑ። ሰዎች እንዴት ሊያስተናግዷችሁ
እንደሚገባ አስቡ፡፡ ለምን? ስለዚህ ጉዳይ ለመወያየት 8 ደቂቃዎችን ያህል እሰጣችኋለሁ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ8 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ተለይተው ስለ ታወቁ እሴቶች እንዲናገሩ ያግዟቸው። ሌሎች
ሰዎች እንዲያደርጉልን የምንፈልገውን፤ እኛም ለሌሎች እንዲሁ ማድረግ ጥሩ ነው የሚሉ ከሆነ፤ ይህንን
በተጨባጭ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችሉ ግልጽ ምሳሌዎችን እንዲሰጡ ያድርጉ፡፡

ይምሩ:- አለኝ ስለሚለው አንድ መርህ ወይም እሴት ሊያጋራን የሚችል ሰው ይኖራል? ምላሾችን ይቀበሉ፤
ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ከተለያዩ ባህሎች፣ አስተዳደግ ወይም ሀይማኖቶች በመጡ ሁለት ሰዎች መካከል፤ የአንደኛው
ስነምግባር ከሌላኛው የተለየ የሞራል ድምዳሜ እንዲኖረው ሊያደርገው ይችላል፡፡

ይምሩ:- በሌላ መልኩ፤ አንድ ሰው ከምንም በላይ ለሐቀኝነት ቅድሚያ ሲሰጥ፡ ሌላው ደግሞ ለደግነት ከፍተኛ
ቦታ ሊሰጥ ይችላል።

ይምሩ:- ለደግነት ከፍተኛ ቦታ የሚሰጡ ሰዎች፤ የጎረቤቶቻቸውን ስሜት የሚጎዳ ከሆነ፡ ሙሉ በሙሉ ሐቀኛ
ሆኖ ለመገኘት ይቸግራቸዋል፡፡

ይምሩ:- ለሐቀኝነት ከፍተኛ ቦታ የሚሰጡ ሰዎች ደግሞ፤ ጎረቤቶቻቸውን የሚያበሳጭ እንኳ ቢሆን፡ ሁል
ጊዜም እውነትን መናገር በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

ድራማ

ይምሩ:- ሁለት ፈቃደኛ ተዋንያን፤ ከዚህ የሚከተሉትን ድራማዎች እንዲያቀርቡ ያድርጉ፡፡ አስቀድመው
ልምምድ ያደረጉ ሊሆኑ ይገባል፡፡

ባለ ሱቅ፡- “እንደምን አለሽ፤ እመቤቴ፡፡ ምን ልታዘዝ?”

ደንበኛ:- “እንደምን ዋልህ፤ ወዳጄ፡፡ ለአጎቴ ልጅ ሠርግ የምለብሰው አንድ ጥሩ ቀሚስ እፈልጋለሁ፡፡”

ባለ ሱቅ፡- “በጣም ጥሩ፤ ይህቺ የምታምር ቀሚስ ትመችሻለች?”

ደንበኛ:- “አዎ፤ እሱ ቆንጆ ነው፡፡ ከለሩ ግን ምርጫዬ አይደለም፡፡ በሠማያዊ ይኖርሃል?”

ባለ ሱቅ፡- “በሚገባ እንጂ! ይሄስ? እንዲያውም ከፀጉርሽ ጋር ይሄዳል።”

ደንበኛ:- “ዋው፤ ያምራል! እወስድዋለሁ፡፡ ዋጋው ስንት ነው?"

ባለ ሱቅ፡- ______ ብር።

ደንበኛ:- “ይሄ’ማ ውድ ነው፡፡ ምናልባት _______ ብር ከሸጥህልኝ እገዛዋለሁ፡፡”

ባለ ሱቅ፡- ለማስጨመር ይሞክራል፡፡ ከተወሰነ ክርክር /ደርድር/ በኋላም ይስማማል፡፡

130
ደንበኛ:- ገንዘቧን አውጥታ ከፍላ፤ ባለ ሱቁን አመስግና ትሄዳለች፡፡

ባለ ሱቅ፡- የሰጠችውን የብር መጠን እየተመለከተ፤ “ከተስማማንበት ዋጋ በላይ ነው የከፈለችኝ፡፡”


ይላል፡፡

ይምሩ:- ፈቃደኛ ተዋንያኖቹን ያመስግኑ እና ወደ ተሳታፊዎቹ ዞረው እንዲህ በማለት ይጠይቁ፡-

ይምሩ:- በዚህ ሠዓት ባለ ሱቁ ምን ማድረግ አለበት? (ሮጦ ሄዶ ጭማሪውን ገንዘብ ለደንበኛው ለመመለስ
ይሞክራል? ወይስ ደንበኛው ሆን ብላ እሱን ለመጥቀም፤ ጭማሪውን ገንዘብ ሰጥታው እንደ ሄደች አድርጎ
ያስባል? ወይስ ቀድሞውኑም ተከራክራ በማይሆን ዋጋ እንደወሰደችው በማሰብ፤ ይሄ ምንም ማለት
እንዳልሆነ ቆጥሮ ራሱን ያሳምናል?)

ይምሩ:- ይህ ወሳኝ የሥነ-ምግባር ድርጊት የሆነው ለምንድን ነው? (እንዳንሰርቅ፣ ጎረቤታችንን እንደራሳችን
እንድንወድድ፣ ወዘተ. መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያዝዘን)፡፡

ይምሩ:- አሁን ደግሞ፤ ሌላ የባለ ሱቅ እና የደንበኛን ገጸ-ባህሪ የሚጫወቱ ሁለት ፈቃደኛ ተዋንያንን ወደ
መድረኩ ይጥሩ፡፡

ደንበኛ:- “ሠላም ለአንተ ይሁን፤ ወዳጄ! እንዴት ነህ?"

ባለ ሱቅ፡- “ሠላም ለአንተ ይሁን፤ ወንድሜ! እግዚአብሔር ይመስገን፤ በጣም ደህና ነኝ፡፡ ቤተሰብ ደህና
ነው?”

ደንበኛ:- “ሁሉ ሠላም ነው፡፡ ልጆችህስ እንዴት ናቸው?”

ባለ ሱቅ፡- “ደህና ናቸው፤ አመሰግናለሁ፡፡ ምን ልታዘዝ?”

ደንበኛ:- “ለልጄ ቆንጆ ቀሚስ ፈልጌ ነበር፡፡ እንዴት እንዳደገች ብታይ፡፡”

ባለ ሱቅ፡- “ዋው! ደስ ይላል፡፡ ጥሩ ቀሚስ እሰጥሃለሁ፡፡”

ደንበኛ:- “ቤተሰብ ስለሆንን፤ መቼም ልዩ ቅናሽ እንደምታደርግልኝ እርግጠኛ ነኝ?”

ባለ ሱቅ፡- “በሚገባ እንጂ፤ ወዳጄ፡፡”

ደንበኛ:- “አመሰግናለሁ፡፡ ይሄ ምን ያህል ነው?”

ባለ ሱቅ፡- “መደበኛ ዋጋው ______ ብር ነው ፡፡ ለአንተ ግን ______ ብር እሸጥልሃለሁ።”

ሁለተኛው ደንበኛ:- ገብቶ፤ “እንደምን ዋልህ” ይላል፡፡

ባለ ሱቅ፡- አዲስ ወደ ገባው ደንበኛ ፊቱን እያዞረ፤ “እግዚአብሄር ይመስገን፤ ሠላም ነው! ምን
ልታዘዝ?" ይለዋል፡፡

ሁለተኛው ደንበኛ:- “ለልጄ ቀሚስ ፈልጌ ነበር፡፡ ያኛው ስንት ነው?” የመጀመሪያው ደንበኛ ወደ
ያዘው ቀሚስ እየጠቆመ።

131
ባለ ሱቅ፡- ከመጀመሪያው ደንበኛ እጅ ቀሚሱን ተቀብሎ፤ “ኦው፤ ይሄን ነው? ይሄ _______ ብር
ነው፡፡ (ከመደበኛ ዋጋው ከፍ ያለ አድርጎ ይጠራል)።.

ሁለተኛው ደንበኛ:- “በጣም ጥሩ፤ እወስደዋለሁ፡፡”

ባለ ሱቅ፡- ገንዘቡን ተቀብሎ በፍጥነት መጠቅለል ይጀምራል፡፡

የመጀመሪያው ደንበኛ፡- “እኔ ልገዛው የፈለግሁት ቀሚስ’ኮ ነበር!” ይላል ግራ በተጋባ ስሜት፡፡

ባለ ሱቅ፡- “ኦው ይቅርታ ወንድሜ፤ በእርግጠኝነት ትረዳኛለህ ብየ አምናለሁ፡፡ እንዳየከው፤ ያ ደንበኛ


ከመደበኛ ዋጋው በላይ ነው ጨምሮ የከፈለው! ለልጅህ ሌላ ቀሚስ እሰጥሃለሁ፡፡”

የመጀመሪያው ደንበኛ፡- “ከዚያ የተለየ፤ ሌላ ቀሚስ እመርጣለሁ ብየ አላስብም፡፡ ሌላ ሱቅ መሄድ


ይኖርብኛል።”

የመጀመሪያው ደንበኛ፡- በንዴት ጥሎ ይወጣል።

ባለ ሱቅ፡- ግራ ተጋብቶ እንደቆመ ይቀራል፡፡

ይምሩ:- ፈቃደኛ ተዋንያኖቹን ያመስግኑ።

ይምሩ:- እዚህ ላይ፤ ከሥነ-ምግባር ብዥታ ወይም ጥያቄ ጋር ተያይዞ ምን ታስባላችሁ? የሱቁ ሠራተኛ
እንዴት ማስተናገድ ነበረበት?

ይምሩ:- ለመልሶቹ ጊዜ ይስጡ፡፡

ይምሩ:- የመጀመሪያው ደንበኛ ምን ማድረግ ነበረበት ብለን እናስባለን?

ይምሩ:- ለመልሶቹ ጊዜ ይስጡ፡፡

ይምሩ:- በቢዝነስ ስራ ላይ ወይም እንደ ደንበኛ ሆነን፤ ሥነ-ምግባርን የተላበሰ ውሳኔን የሚጠይቅ ጉዳይ
ጋጠማችሁ ጊዜ ካለ በየቡድኖቻችሁ ተወያዩበት፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ4 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ቢያንስ አንድ ገጠመኙን ሊያጋራ የሚችል ሰው ለማግኘት
ይሞክሩ። ከ1 እስከ 15 ቁጥር ቆጥረው ፈቃደኛ ሰው ከሌለ፤ የራስዎን ታሪክ ለቡድኑ ያጋሩ፡፡

ይምሩ:- በህይወቱ የሥነ ምግባር ውሳኔን የሚጠይቅ ክስተት ያጋጠመውን ጊዜ ሊያጋራን የሚችል አንድ ሰው
ይኖራል? ምላሾችን ይቀበሉ፤ ለተሰጡ መልሶች ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ሥነ-ምግባር፤ በማንኛውም ጊዜ ለሁሉም ሰው ይሠራል፡፡ ሥነ-ምግባርን የተላበሰና ሐቀኛ ሕይወት


ላለመኖር፤ ወይም ቢዝነስን በመልካም ሥነ-ምግባር እና በሐቀኝነት ላለመስራት ምንም ዓይነት አሳማኝ
ምክንያት ሊኖር አይችልም።

ይምሩ:- ተግባራችን ሥነ ምግባር የጎደለው መሆን አለመሆኑን ለማወቅ እራሳችንን መጠየቅ የምንችላቸው
ጥያቄዎች አሉ ፡፡ በሠልጣኞች መጽሐፍ ገጽ ____ ላይ ተዘርዝረዋል ፡፡

132
1. ይህ ማድረግ የምፈልገው ነገር ሕጋዊ (በህግ የተፈቀደ) ነው?

2. ፍትሃዊ ነኝ? የማደርገው በእኔም ላይ እንዲደረግ የምፈልገውን ነገር ነው?

3. ይህ ተግባር ስለራሴ ምን እንዲሰማኝ ያደርጋል?

4. ይህ ተግባር እግዚአብሔርን ያስደስተዋል?

ይምሩ:- ሥነ-ምግባር ከሕጋዊ ነገር ይለያል፤ ምክንያቱም ህጎች እንደየሃገሩ፣ ማህበረሰቡ፣ እና ግለሰቡ ሊለያዩ
ይችላሉ፡፡ የህሊናችን መስፈርቶች ግን አንድ ዓይነት እንደሆኑ ይኖራሉ፡፡

ይምሩ:- እውነተኛውን ሞራላዊ ኑሮ የምንኖር ከሆነ፤ የሰው ልጆች ሁሉ በዘር፣ መደብ፣ ሀይማኖት ወይም
በጾታ ልዩነት ሳይደረግባቸው እኩል ለማስተናገድ ጥረት እናደርጋለን፡፡

ይምሩ:- ሌሎች እንዲደርጉልን በምንፈልገው ልክ፤ እኛም ማንኛውንም ሰብዓዊ ፍጡር በትህትና እና
በአክብሮት ማስተናገድን እንመርጣለን፡፡

133
ልምምድ

ይምሩ:- አሁን፤ በሠልጣኞች መጽሐፍ ገጽ ____ ላይ፤ በሕይወት ዘመናችሁ ሰዎች እንዴት እንዲያይዋችሁ
እና እንዲያስተናግዳችሁ እንደምትፈልጉ በስዕል ግለጹ፡፡ ስዕሉን ካጠናቀቃችኁ በኋላ በጠረጴዛችሁ ዙሪያ
ላሉት ጓደዮቻችሁ አጋሩ፡፡

ይምሩ:- አጭር እና ግልጽ ይሁን። ከፈለጋችሁም፤ እንዴት እንዲያስተናግዷችሁ እንደምትፈልጉ ለመግለጽ


በጽሁፍ መጠቀምም ትችላላችሁ፡፡ 4 ደቂቃዎች ያህል ተጠቀሙ፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ4 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ሁሉም ተሳታፊ የሠልጣኝኞችን መጽሐፍ ገጽ ___ከፍተው


መልመጃውን በሚገባ መረዳታቸውን ያረጋግጡ። ያበረታቷቸው፣ ያበረታቷቸው፣ ያበረታቷቸው! አንዳንዶች
ከጎናቸው ካለ ጓደኛቸው ለመኮረጅ አስከማሰብ ይደርሳሉ፤ ነገር ግን የየራሳቸው ለየት ያሉ ጽንሰ ሀሳቦች ዋጋ
ያላቸው መሆኑን እንዲገነዘቡ ያግዟቸው! ሃሳባቸውን በስዕል አስፍረው ከጨረሱ በኋላ፤ እነዚህ ሥራ
ፈጣሪዎች እንዴት እንዲታዩ እና እንዲስተናገዱ እንደሚፈልጉ የሚደረገውን ውይይት ይመሩ፡፡

ይምሩ:- ሰዎች እንዴት እንዲያስተናግዷችሁ እንደምትፈልጉ ስለሚያሳዩት ስዕሎቻችሁ ልታስረዱን ፈቃደኛ


የሆናችሁ ሁለት ተሳታፊዎችን እፈልጋለሁ፡፡

ይምሩ:- ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ሌሎች እንዲሆኑልን እና እንዲስተናግዱን በምንፈልገው ልክ፤ እኛም በአካባቢያችን ያሉ ሰዎችን


በተመሳሳይ መልኩ ልንይዝ እና ልንንከባከብ ግድ ይለናል፡፡ ሁላችንም በእግዚአብሔር ድንቅ ሆነን የተፈጠርን
እና የተወደድን ስለሆንን፤ እያንዳንዳችን ትልቅ ዋጋ ያለን፤በትህትን እና በአክብሮት ልንያዝ ይገባናል፡፡

ይምሩ:- ከዚህ የትምህርት ክፍል ስለ ቀሰማችሁት አንድ ነገር ልትነግሩኝ የምትችሉ ሁለት ሰዎች አላችሁ?

ይምሩ:- ሁለት ሠልጣኞች ወደ መድረክ ወጥተው አንድ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ ሃሳባቸውን በመደገፍ፤
ያጋሯቸውን ነጥቦች ደግመው ያብራሩ፡፡

ይምሩ:- ስለ ዛሬ ተሳትፏችሁ ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ፤ በቀጣይ ክፍል እስክንገናኝ ሠላም ሁኑ፡፡

134
// ክፍል 17 //

አመራር

የሚወስደው ጊዜ፡- 1 ሠዓት

ግቦች:-
1. ተሳታፊዎች፤ በሥራ ቦታቸው የአመራር መርሆዎችን ያውቃሉ፡፡
2. ተሳታፊዎች፤ በማህበረሰቦቻቸው ውስጥ መሪ እንዲሆኑ ይበረታታሉ፡፡

አቅርቦቶች፡-
● እስክሪብቶዎች ● የወለል ምንጣፍ፣ ብርድ ልብስ፣ ወይም
● የሠልጣኞች መጽሐፍት መሸፈኛ ጨርቅ (ለአስማተኛ ምንጣፍ
● ጣፋጮች ጨዋታ /ለማጂክ ካርፔት ጨዋ)
● ነጭ ሠሌዳ
● የሠሌዳ ማርከር
● የእግር ማስታጠቢያ ገበታ
● ልብስ /ስካርፍ

ቁልፍ ቃላት (በሠሌዳው ላይ ይፃፉ)፡-


> መሪ
> ግልጽነት

ዝግጅት:-
● የዮሐንስ ወንጌል 13÷3-5, 12-15 ድራማን የሚተውኑ፤ ማለትም ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
እንደሚያነብቡ አድርገው የሚተውኑ ሁለት አመቻቾችን ይምረጡ፡፡ የከናፍርት እንቅስቃሴዎቻቸው
ከጥቅሱ ምንባብ ጋር መጣጣም ይኖርበታል፡፡ የእግር መታጠብ ስነ-ስርዓትን አስመስሎ ለመተወን
የሚያስፈልጉ፤ ወንበር፣ ጨርቅ ወይም ፎጣ፣ እና የእግር ማስታጠቢያ ገንዳ ያዘጋጁ፡፡ ውሃ በአካል
አያስፈልግዎትም፡፡
● ይህ ክፍለ ጊዜ፤ ለአመራር ጭውውት ሁለት የተለያዩ አማራጮችን ያካትታል፡፡ በእርስዎ አውድ
መሠረት የተሻለ የሚሠራልዎትን፤ ከሚከተሉት አንዱን ይምረጡ፡-
● የመቆላለፍ ጨዋታ:- መደበኛ ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብለው፤ የትስስር ጨዋታውን
ለቡድን አመቻቾች ያስተምሯቸው። ተሳታፊዎች ተግባራዊ ከማድረጋቸው በፊት እንቅስቃሴውን
በሞዴልነት እንዲያሳዩ ያዘጋጇቸው፡፡ ወንዶችም እና ሴቶች በአንድ ክፍል ውስጥ የሚሠለጥኑ ከሆነ፤

135
ቡድኖችን ከመመስረትዎ በፊት እጅ ለእጅ መያያዝ እና ተጠጋግቶ መቆም የሚቻል መሆኑን
ያረጋግጡ፡፡
● ምትሃታዊ የምንጣፍ ጨዋታ:- መደበኛ ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብለው፤ ምትሃታዊ
የምንጣፍ ጨዋታውን ለቡድን አመቻቾች ያስተምሯቸው። ተሳታፊዎች ተግባራዊ ከማድረጋቸው
በፊት እንቅስቃሴውን በሞዴልነት እንዲያሳዩ ያዘጋጇቸው፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ:-


● ዮሐንስ 13÷3-5 &12-15
● መዝ 37÷1-3 &16-19

136
ይምሩ:- ስነ-ምግባርን ወይም ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ ሌሎችን እንዴት ማስተናገድ እንዳለብን አሁን
ተገንዝበናል፤ ስኬታማ መሪ ስለ መሆንስ እንዴት እንማራለን?

ይምሩ:- መሪ፤ ተፅእኖ ፈጣሪ የሆነ ሰው ነው፡፡ በቃ ይሄው ነው፡፡ ሁሉም ሰው ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው፡፡ ምንም
ያህል ከፍ ወይም ዝቅ ያላችሁ ብትሆኑ፤ ከሌሎች ጋር ግንኙነት እስካለን ድረስ ተጽዕኖ ማሳደራችን አይቀሬ
ነው፡፡ እራሳችሁን እንደ መሪ አስባችሁ ላታውቁ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን ናችሁ፡፡

ይምሩ:- የልጅ እናት ወይም አባት ከሆናችሁ፤ መሪዎች ናችሁ፡፡ የሰዎች ጎረቤት ወይም ዘመድ ከሆናችሁ፤
መሪዎች ናችሁ። ለአንዳንዶች ጓደኛ ወይም የስራ ባልደረባ ልትሆኑ ትችላላችሁ - እናም መሪ ናችሁ። አዎ፤
የአንድ ሰው አለቃ ብትሆኑ እንኳ እናንተ መሪዎች ናችሁ።

ይምሩ:- ስለዚህ አሁን የምንነጋገረው፤ በጎ ተጽዕኖ በማሳደር እንዴት ጥሩ መሪ መሆን እንደሚችሉ ነው፡፡

ይምሩ:- እንደ መሪ፤ አራት ነገሮች ስኬቶቻችንን ሊወስኑ ይችላሉ ፡፡ እነዚህም፡-

● የማቀድ
● የማደራጀት
● የመምራት እና
● ራስን ምሳሌ አድርጎ ተጽዕኖ የመፍጠር ክህሎቶቻችን ናቸው፡፡

ይምሩ:- ጥሩ መሪ፤ እነዚህን ሁሉ ነገሮች በሚገባ ማከናወን ይጠበቅበታል።

ይምሩ:- አንድ ጥሩ መሪ የሆነ ሰው ምሳሌ ማን ሊሰጠኝ ይችላል፤ ምክንያቱስ?

ይምሩ:- ምላሾችን ይሰብስቡ፡፡ ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ኢየሱስ ክርስቶስ የጥሩ አገልጋይ መሪ ዋና ምሳሌ ነው። ምንም እንኳን ኢየሱስ ኃይሉን ተጠቅሞ
ሰዎችን መቆጣጠር የሚያስችለው ቢሆንም፤ እርሱ ግን ሰዎችን ማገልገል መርጧል፡፡

ይምሩ:- በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 13፤ ከቁጥር 3 እስከ 5 እና ከቁጥር 12 እስከ 15 ላይ ያለውን የመጽሐፍ
ቅዱስ ክፍል በጋራ እናነባለን፡፡ እኛ ይህን ክፍል ጮክ ብለን ስናነብ፤ ሁለት ፈቃደኛ ሠልጣኞች አንዱ የሌላውን
እግር የማጠብ ትዕይንት አስመስለው እንዲሰሩ እናደርጋለን፡፡ ሁለቱ ፈቃደኛ ተዋንያኖቼ ወደ መድረክ
ልትመጡልኝ ትችላላችሁ?

ይምሩ:- ይህንን ድራማ አስመስሎ ለመስራት የሚረዱ የእግር ማስታጠቢያ ገበታ እና/ወይም ፎጣ
አስቀድመው ያዘጋጁ፡፡ ለዚህ ድራማ ውሃ አያስፈልግም፡፡ እርስዎ ራስዎ ወይም ሌላ ፈቃደኛ ተሳታፊ
መጽሐፍ ቅዱሱን ሲያነቡ፤ ሁለቱ ፈቃደኛ ተዋንያኖች ወደ መድረክ መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡

ይምሩ:- ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 13፤ ከቁጥር 3 እስከ 5 እና ከቁጥር 12 እስከ 15 እንዲህ ይነበባል፡-

“ኢየሱስ አብ ሁሉን በእጁ እንደሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ


አውቆ÷ከእራት ተነሳ ልብሱንም አኖረ÷ ማበሻም ጨርቅሽዶ ታጠቀ። በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ÷
የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ፡፡” “… እግራቸውንም
አጥቦ ልብሱንም አንስቶ ዳግመኛ ተቀመጠ÷ እንዲህም አላቸው፡- ‘ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?’

137
እናንተ መምህር እና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ፡፡ እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር
ሰስሆን እግራችሁን ካጠብኩ÷ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል፡፡ እኔ
ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና፡፡”

ይምሩ:- አመሰግናለሁ፤ ተዋንያኖቼ! ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን ለማገልገል እንደመረጠ እና እነርሱም


ለሌሎቹ እንዲሁ እንዲያደርጉ እንደጠየቃቸው በዚህ ጥቅስ ውስጥ እናያለን ፡፡ አገልጋይ መሪ ምን
እንደሚመስል ለእኛም ለእያንዳንዳችን ምሳሌን ሰጥቶናል፡፡

ይምሩ:- በዚህ አሁን በተረዳሁበት መንገድ የመራኝ አገልጋይነትን የተላበሰ መሪ በህይወቴ አጋጥሞኛል፤ የሚል
አንድ ፈቃደኛ ተነስቶ ሊያጋራን የሚችል አለ? ፈቃደኛ ከሆኑት መካከል አንዱን ይምረጡ።

ይምሩ:- ስላጋራኸን በጣም እናመሰግናለን!

የስኬት ታሪክ

ይምሩ:- የዚህ ዓይነት የአገልጋይ አመራር አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ፡፡ የታሊ ደንበኛ የሆነችው

ግብፃዊቷ ሶኸር ገና በወጣትነቷ የአራት ልጆች እናት ለመሆን በቃች፡፡ የዚህችን ሴት ታሪክ

በሠልጣኞች መጽሐፍ ገጽ ___ ላይ ማግኜት ትችላላችሁ፡፡

ይምሩ:- ከታሊ ብድር በመውሰድ የተበላሹ ዕቃዎችን መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል (ሪሳይክሊንግ) ቢዚነስ
ጀመረች፡፡ በዚህ ቢዚነስ ገቢዋ እያደገና የቤተሰቧ ሕይወት እየተለወጠ ሲመጣ፤ ሶኸር ብደሯን በጊዜው
በመመለስ ሌሎች የአካባቢዋን ሰዎች ለመርዳት በሚደረገው የታሊ ፕሮግራም የበኩሏን አስተዋጾ ለማበርከት
ቻለች፡፡ ከታሊ ብዙ ደንበኞች ጋርም በመተዋወቅ የምክር አገልግሎት በመስጠትና ልምድ በማጋራት
ታግዛቸው ነበር፡፡

ይምሩ:- የሶኸር አመራር፤ ልክ እንደ እርሷ ያሉ ሌሎች ብዙ ሴቶችንም ረድቷል፡፡ ሶኸር የራሷን ቤተሰብ ብቻ
ለመንከባከብ ምርጫ ነበራት፤ ይሁን እንጅ ክህሎቷን እና ልቧን ሌሎችን በመምራት ለማገልገል
ተጠቀመችበት።

ይምሩ:- ማንም ሁኑ ማን፤ አገልጋይነት የተላበሰ መሪነትን በተግባር ማሳየት ትችላላችሁ፡፡ ሌሎችን
ማስቀደም እና እነሱም እንዲሁ እንዲሰሩ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ይህንንም በቤተሰቦቻችሁ፣ በማህበረሰቡ፣
ወይም በቤተክርስቲያኖቻችሁ እውን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

ይምሩ:- አሁን ተነስተን፤ ለአጭር ጊዜ በየቡድናችን በመሆን ሁላችንም እንደ ቡድን ለመስራት እና የተለያዩ
የአመራር ክህሎቶቻችንን ለማዳበር የሚረዳንን ፈጣን ጨዋታ እንጫወታለን፡፡

ልምምድ

ይምሩ:- ከዚህ በታች ያሉትን ሁለት ልምምዶች አስቀድመው ያንብቡ እና ለአድማጮችዎ የተሻለ ሊሠራ
የሚችልውን ይምረጡ፡፡ ቁልፍልፍ ጨዋታ ለማድረግ አካላዊ ንክኪን ይጠይቃል፡፡ ምትሃታዊ የምንጣፍ
ላይ ጨዋታ ለማድረግ ደግሞ ምንጣፍ ወይም ብርድ ልብስ ያስፈልጋል። ሁለቱም ጨዋታዎች፤ ተግባራዊ

138
እንቅስቃሴ እና ሠፋ ያለ የወለል ቦታን ይፈልጋሉ። የመረጡትን የጨዋታ ዓይነት ለቡድን አመቻቾች
አስቀድመው ያብራሩላቸው፡፡

አማራጭ 1 - ቁልፍልፍ ጨዋታ

ይምሩ:- ሁላችንም እንነሳ እና ከመጫወቻ ወለሉ ጥቂት ራቅ ብለን እንቁም፡፡

ይምሩ:- ይህን ጨዋታ ለመጫወት፤በየቡድኖቻችን ሆነን ክብ ሰርተን እንቁም፡፡ ሁላችንም እጆቻችንን


እንዘረጋና ከፊት ለፊታችን ያሉትን እጆች እንይዛለን፡፡ አንድ ሰው የሁለት ሰዎችን እጆች መያዙን አረጋግጡ፡፡
አጥብቃችሁ ተያያዙ!

ይምሩ:- ሁሉም ሰው ከተያያዘበት ሳይላቀቅ፤ “ቁልፍልፉን” መፍታት ያስፈልገዋል፡፡ የያዛችሁትን እጅ በፍጹም


እንዳትለቅቁ፡፡

ይምሩ:- ቡድን አመቻቾች “ቁልፍልፉ”ን የመፍታት እንቅስቃሴን በተግባራዊ ገለጻ ለሠልጣኞች እንዲያሳዩ
ጊዜ ይስጧቸው፡፡ በዚህ ጨዋታ፤ ሁሉም ሰው ከቁልፍልፉ እስኪፈታ ድረስ፤ አንዱን እጅ በሌላው እጅ ላይ
ማሳለፍን እና አንዱን በአንዱ ስር ማሾለክን ያካትታል፡፡

ይምሩ:- አሁን ደግሞ የእናንተ ተራ ነው!

ቡድን አመቻቾች፡- ለ7 ደቂቃዎች ያህል፡፡ የራስዎን ቡድን ይዘው ግልጽ ወደሆነ ቦታ ይሂዱ እና ቁልፍልፍ
ጨዋታውን ይጀምሩ፡፡ የአንድ ቡድን አባላት ቁጥር 8 ቢሆን ተመራጭ ነው፡፡ የእርስዎ ቡድን አባላት ከዚህ
የሚያንሱ ከሆነ ከሌላ ቡድን ጋር ይቀላቅሏቸው፤ የሚበልጡም ከሆነ ይክፈሏቸው፡፡ እርስዎ አብረው ሊሳተፉ
ይችላሉ፤ ነገር ግን አፈታቱን አያሳይዋቸውም፡፡

ይምሩ:- የተወሰነ ጊዜ ይስጧቸው፤ ለሚያደርጉት ለእያንዳንዱ ጥረት ድጋፍዎን ይገለጡላቸው፡፡ ሁሉም


ተመልሰው እንዲቀመጡ ያድርጉ፡፡

አማራጭ 2 - ምትሃታዊ የምንጣፍ ላይ ጨዋታ

ይምሩ:- ለዚህ ጨዋታው የሚያስፈልጉዎት፤ ምንጣፍ፣ ብርድ ልብስ እና ቡድኑ የሚቆምበት ሠፊ የፕላስቲክ
ንጣፍ ናቸው፡፡ ወለሉ ላይ ይዘርጉት፡፡

ይምሩ:- ሁላችንም እንነሳና ከመጫወቻ ስፍራው ጥቂት ራቅ ብለን እንቁም፡፡ ለዚህ ጨዋታ ብዙ ፈቃደኞችን
እንፈልጋለን፡፡ በምንጣፉ (በብርድ ልብሱ ወይም በፕላስቲክ ንጣፉ) ዙሪያ እንዲሰባሰቡ ያድርጉና ከ4 እስከ 6
የሚደርሱ ፍቃደኞችን ይጋብዙ፤ የተሳታፊዎች ቁጥር እንደ ምንጣፉ ስፋት የሚወሰን ነው፡፡ያስታውሱ፡- ብዙ
ምንጣፎች ወይም ብርድ ልብሶች ካለዎት፤ ጨዋታውን በሁለት እና ከዚያ በላይ በሆኑ ቡድኖች ሊያከናውኑት
ይችላሉ፡፡

ይምሩ:- ምትሃታዊ የምንጣፍ ላይ ጨዋታውን ለመጫወት፤ ፈቃደኛ የቡድኑ አባላት በሙሉ ተነስታችሁ
በዚህ ምንጣፍ ላይ ትቆማላችሁ፡፡ ማንም ሰው ወለሉን እንዲነካ አይፈቀድለትም፡፡ እሺ; ዝግጁ?

ይምሩ:- አሁን ፈተናው ምን እንደሚመስል እነግራችኋለሁ፡- ማንም ከምንጣፉ ሳይወጣ፤ ምንጣፉን በጋራ
መገልበጥ! አንድ ሰው እንኳ ከምንጣፉ ቢወጣ፤ ጨዋታው እንደገና ይጀመራል! ይህ ስራ በሚገባ ማሰብ፣ ጥሩ
ተግባቦት፣ እና የቡድን ስራን ይጠይቃል፡፡ ዝግጁ? ቀጥሉ!

139
ይምሩ/ቡድን አመቻቾች፡- ለ7 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ታዳሚው እየታዘበ፤ ቡድኑ የተሰጠውን ግዳጅ ለመወጣት
የተወሰነ ጊዜ ይፍቀዱ፡፡ ቡድኑ ይህን ለማከናወን ከተቸገረ፤ ስራው እስኪሠራ ድረስ ሌሎች ፈቃደኞችን
በመጠየቅ እንዲቀጥሉ ያድርጉ፡፡ ጨዋታው እንደተጠናቀቀ፤ ታዛቢዎች ሁሉ በጭብጨባ እና በጩኸት ሞራል
እንዲሰጡ ያበረታቱ፡፡ ከዚያም፤ ሁሉም ተመልሰው እንዲቀመጡ ያድርጉ፡፡

ይምሩ:- ስለ ጨዋታው ምን ትላላችሁ? ከባድ ነበር ወይስ ቀላል?

ይምሩ:- ስራውን አስቀድሞ አቅዶ በአግባብ ለመከወን የቻለው፤ ወይም በማስተባበር ከፍተኛውን ድርሻ
የተውጣው ማን እንደሆነ በየቡድኖቻችሁ ውሳኔ ስጡ፡፡

ይምሩ:- ቡድኑን በመምራት እና ሰዎቹ እንዲከተሏቸው በማስተባበር ክፍተኛ ጥረት ያደረጉ ሁለት ሰዎች
እነማን ነበሩ?

ይምሩ:- ማን ምን ዓይነት ሚና እንደተጫወተ ቡድኖቹ ለይተው እስኪያወጡ ድረስ ጊዜ ይስጧቸው፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ3 ደቂቃዎች ያህል፡፡ እያንዳንዱን ድርሻ በመወጣት ረገድ ከሌሎች የላቀ አስተዋጽኦ
ያደረገውን ቡድኑ ለይቶ እንዲያወጣ ይጠይቁ፡፡ በመምራትና በማስተባበር የተለየ ሚና ተጫውቷል
ያስባላቸውንም ምክንያት እንዲገልጹ ያድርጉ፡፡ ስራ ፈጣሪዎቹን ያበረታቱ፤ የመሪነት ክህሎቶቻቸውንም
ያድንቁ፡፡

ይምሩ:- የጥሩ መሪ ተግባራት ስናከናውን፤ እነዚህን ክህሎቶች ሁሉ መጠቀም ያስፈልገናል፡፡

ይምሩ:- በቡድኑ ውስጥ፤ ጥሩ የመሪነት ተግባር ማን እንደ ተወጣ እና ለምን እንደሆነ አንድ ሰው ተነስቶ
ሊነግረኝ ይችላል?

ይምሩ:- ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ስለ ወደፊቱ ማቀድ፣ በሚገባ መደራጀት፣ ሰዎችን እና ሁኔታዎችን እንዴት መምራት እንዳለብን
ማወቅ፣ እና ምሪታችንን ሌሎች እንዲከተሉ ተጽዕኖ መፍጠር ይኖርብናል፡፡

ይምሩ:- እንደ ቡድን አባላት፤ ጥሩ የአመራር ክህሎት ያሳየ ሰው ማን እንደሆነ ጊዜ ወስዳችሁ ተነጋገሩበት፡፡
አንድን መሪ፤ መስፈርት ያሟላ መሪ የሚያስብለው ምንድን ነው? ሰዎች የሰውየውን አመራር የመከተል
ፍላጎት እንዲያድርባቸው የሚያደርጋቸው ምንድን ነው?

ይምሩ:- ለዚህ ጊዜ ይስጧቸው፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ4 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ሁሉም ሠልጣኝ በውይይቱ እየተሳተፈ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡

ይምሩ:- አንድ ጥሩ መሪ በምሳሌነት በመጥቀስ፤ ይህን ሰው ለምን ጥሩ መሪ ሊለው እንደ ቻለ ሊያጋራን


የሚፈልግ ሰው አለ?

ይምሩ:- ከአድናቆትና ምስጋና ጋር ጣፋጭ ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- በቢዝነስ፤ አመራር ማለት ከእኛ ጋር ወይም ለእኛ የሚሰሩ ሰዎች እንዲማሩ፣ እንዲያድጉ፣ እና
እንዲለወጡ ማገዝ ማለት ነው፡፡

140
ይምሩ:- አንድን ስራ ብቻችንን ማጠናቀቅ ብንችል እንኳ፤ እንሰራዋለን ማለት አይደለም፡፡

ይምሩ:- ሠራተኞቻችን ያለ እኛ እገዛ ስራውን እንዲያከናውኑት በመፍቀድ፤ አዲስ ክህሎት ወይም የበለጠ
በራስ መተማመን እንዲያዳብሩ ማድረግ ተመራጭ ነው፡፡

ይምሩ:- አንዳንድ ጊዜ፤ ሠራተኞቻችን አንድን ስራ በግላቸው ለመስራት የሚያስችል በራስ መተማመን
እስኪያዳብሩ ድረስ ምናልባትም አሠራሩን ድጋግመን ማሳየት ሊያስፈልገን ይችል ይሆናል፡፡

ይምሩ:- በአጠቃላይ ሲታይ ግን፤ በዙሪያችን ላሉ ሠራተኞች ሀላፊነትን መስጠት መልካም ነው፡፡

ይምሩ:- ጥሩ ማኔጀር፣ መሪ፣ ወይም አለቃ፤ ሠራተኞቹም እንዲሁ ጥሩ መሪ እንዲሆኑ ያበረታታል ፡፡

ይምሩ:- አንዳንድ ጊዜ፤ ቢዝነስ ጥሩ የመሪነት ብቃት ያለው አለቃ ብቻ ያስፈልገዋል ብለን ልናስብ እንችል
ይሆናል፡፡ እውነታው ግን ይህ አይደለም፡፡ ስኬታማ ቢዝነሶች፤ ብዙውን ጊዜ በተለያዩ መንገዶች የሚመሩ ብዙ
ጥሩ መሪዎች አሏቸው፡፡

ይምሩ:- ሠራተኞቻችን እና ባልደረቦቻችን እንደተበረታታቱ ሲሰማቸው፤ የግል እርካታ ያገኛሉ።

ይምሩ:- ሠራተኞች በስራቸው ጥሩ ክንውን ሲያስመዘግቡ፤ የበለጠ ኃላፊነት፣ የደመወዝ ጭማሪ፣ ምስጋናና
አድናቆት ወይም የሥራ እድገት ሊሰጧቸው ይችላሉ!

ይምሩ:- ለምሳሌ፤ ____________(በአካቢው የሚታወቅ ስም) የተባለ በጣም ትጉህ ራተኛ በየቡድናችን
እንዳለን አድርገን እንቁጠር፡፡ ይሁን እንጅ፤ ይህ ሠራተኛ ደንበኞችን የሚፈራ እና ዓይናፋር ይመስላል። እኛ
እንደ መሪ፤ ይህ ሠራተኛ ደንበኞችን በራስ የመተማመን መንፈስ እንዲቀርብ የምናበረታታባቸው ሁለት
መንገዶች ምንድን ናቸው?

ቡድን አመቻቾች፡- ለ7 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ይህንን ጥያቄ እንደአስፈላጊነቱ ይድገሙላቸው፡፡ ምንም ዓይነት
ምላሽ መስጠት ካልቻሉ፤ ለመነሻ የሚሆን ፍንጭ ይስጧቸው፡፡

ይምሩ:- ከእያንዳንዱ ቡድን አንድ አንድ ሰው ያላቸውን ሀሳብ እንዲያካፍሉ ይጠይቁ፡፡ ምላሻቸውንም
ከምስጋና እና አድናቆት ጋር ይቀበሉ፡፡

ይምሩ:- ለመልካም ሥነ ምግባር እና ለጥሩ አመራር ሌላው አስፈላጊ ነገር ግልጽነት ነው።

ይምሩ:- “ግልጽነት” የሚለው ቃል አካላዊ ትርጓሜው፤ ብርሃንን በውስጡ የሚያስተላልፍ እና ከበስተጀርባው


ያሉ ነገሮችን በግልጽ ማሳየት የሚያስችል (ብርሃን አስተላላፊ) ቁስ የሚል ነው።

ይምሩ:- ከብርሃን አስተላላፊ ፕላስቲክ የተሰራውን የሠልጣኞችን መጽሐፍ የውጪ ሽፋን ለናሙናነት
በመውሰድ ከፊት ለፊትዎ በማድረግ ያሳይዋቸው፤ ያለዚያም ወደ መስኮቱ ወይም በአቅራቢያ ወዳለ
መስታውት ጀርባ ሄደው ራስዎን ያሳይዋቸው፡፡

ይምሩ:- ሌላው የግልፅነት ትርጓሜ ደግሞ፤ ያላሰለሰ ሐቀኝነት እና ተዓማኒነትን የተላበሰ የሚል ነው ፡፡

ይምሩ:- ግልጽነትን የተላበሰ የቢዝነስ ባለቤቶች ስንሆን፤ የምናስከፍላቸው ዋጋዎች ሚዛናዊ ፣ጥራታችን
ተመራጭ፣ እንዲሁም ወጥነት ያለው የደንበኞች አገልግሎት እንደምንሰጥ በደንበኞቻችን ዘንድ አመኔታን
እናገኛለን፡፡

141
ይምሩ:- እሴቶቻችን በግልጽ የሚታዩ ስለሚሆኑ፤ ደንበኞቻችን ይህንን ያውቃሉ።

ይምሩ:- ከእነርሱ ሆነ ከሌሎች ጋር የሚኖረንን የቢዝነስ እንቅስቃሴ በግልፅ ማየት ሲችሉ፤ ከሌሎች
ተወዳዳሪዎቻችን በተሻለ እኛን እንዲመርጡ ያደርጋቸዋል፡፡ ምክንያቱም ግንኙነታችን፤ የሐቀኝነት እና
ግልጸኝነት መንፈስ የተሞላበት ነውና፡፡

ይምሩ:- ግልጸኝነትን የተሞሉ የቢዝነስ ባለቤቶች መሆን የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች ምንድን
ናቸው? ስለዚህ ጉዳይ በየቡድኖቻችሁ ተወያዩበት፡፡

ቡድን አመቻቾች፡- ለ4 ደቂቃዎች ያህል፡፡ ውይይቱን ያመቻቹ፡፡

ይምሩ:- ነገር ግን ሌሎች የቢዝነስ ተፎካካሪዎቻችን ተገቢ ባልሆነ መንገድ የተሻለ ገቢ ሲያስገቡ ብናይስ?
መጽሐፍ ቅዱስ በመዝሙረ ዳዊት 37 ላይ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ይናገራል፡፡

ይምሩ:- በራስዎ ሕይወት ውስጥ ይህን መሰል ክስተት ተፈጥሮ ከነበረ፤ አሁን ለማጋራት ዕድሉ አለዎት፡፡

ይምሩ:- መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 37፤ ከቁጥር 1 እስከ 3 እና ከ16 እስከ 19 እንዲህ ይላል፡-

“በክፉዎች ላይ አትቅና÷ አመጻንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፤ እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና÷ እንደ


ለመለመ ቅጠልም ይረግፋሉና፡፡ በእግዚአብሔር ታመን÷ መልካምንም አድርግ÷ በምድርም ተቀመጥ÷
ታምነህም ተሰማራ፡፡” ……..“ለጻድቅ ያለው ጥቂት ከብዙ ከሃጢያተኞች ሃብት ይበልጣል፡፡ የኃጥዓን
ክንድ ትሰበራለችና፤ እግዚአብሔርን ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል፡፡ የንጹሐንን መንገድ እግዚአብሔር
ያውቃል÷ ርስታቸውም ለዘላለም ነው፤ በክፉ ዘመንም አያፍሩም÷ በረሀብ ዘመንም ይጠግባሉ፡፡”

ይምሩ:- የሚዋሹ እና የሚያጭበረብሩ ሁሉ ለጊዜው ያደጉ፣ ከፍ ያሉ ሊመስሉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ዘለቄታ


የላቸውም፡፡

ይምሩ:- መልካም ሥነ ምግባርን የተላበሰ መሪ፤ ጠንከራ መሠረት ያለው ቢዝነስ ይገነባል፣ እንዲሁም ለስኬት
እና ለእድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ የሌሎችን አመኔታና አክብሮት ያስገኛል፡፡

ይምሩ:- በክፉ ምግባር ሀብታም ከመሆን፤ በመልካም ሥነ ምግባር ጥቂት ማግኜት እንደሚሻል መዝሙረ
ዳዊት 37 ይመክረናል።

ይምሩ:- ከዚህ የትምህርት ክፍል ስለ ቀሰማችሁት አንድ ነገር ልትነግሩኝ የምትችሉ ሁለት ሰዎች አላችሁ?

ይምሩ:- ሁለት ሠልጣኞች ወደ መድረክ ወጥተው አንድ ነገር እንዲያጋሩ ያድርጉ፡፡ ሃሳባቸውን በመደገፍ፤
ያጋሯቸውን ነጥቦች ደግመው ያብራሩ፡፡

ይምሩ:- ስንመለስ፤ እስካሁን በጋራ የተማርናቸውን ትምህርቶች ሁሉ በሥራ ላይ ስለ ማዋል እንወያያለን!

142
143
// ክፍል 18 //
ክለሳ፣ የድርጊት መርሃ ግብር እና ምረቃ
የሚወስደው ጊዜ፡- ከ30 ደቂቃ እስከ 1 ሠዓት + የምረቃ ስነ ስርዓት

ግቦች:-
> ተሳታፊዎች፤ የተማሩትን ትምህርት ሁሉ በአንድነት የማቀናበር ዕድል ይኖራቸዋል፡፡
> ተሳታፊዎች፤ እያንዳንዱ የሥልጠና ክፍል ከአንዱ ወደ ቀጣዩ እንዴት እንደሚያመራ እና ስለ
እያንዳንዱ አስፈላጊነትና ጠቀሜታእንዴት እንደሚወስድ ይገነዘባሉ፡፡
> ተሳታፊዎች፤ ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ፤ ባልገባቸው ጉዳይ ዙሪያ በጥልቀት ያስባሉ፡፡
> ተሳታፊዎች፤ ዓላማ እና የሥልጠና ግብረ-መልሶቻቸውን ከአመቻቾች ጋር የመጋራት ዕድል
ይኖራቸዋል ፡፡ እነዚህ ምላሾች ለወደፊት መሻሻል እና ተጠያቂነት እንዲረዱ ፤ ተመዝግበው መቀመጥ
ይኖርባቸዋል።

አቅርቦቶች፡-
> እስክሪብቶዎች > ነጭ ሠሌዳ
> የሠልጣኞች መጻሕፍት > የሠሌዳ ማርከሮች
> ጣፋጮች

ዝግጅት:-
> በክለሳው ወቅት፤ ተሳታፊዎች የሠልጣኞችን መጽሐፍ አይጠቀሙም። ይህ ስለ ስልጠናው በቡድን
በሚደረጉ ውይይቶች ምን ያህል እንደሚያስታውሱ ራሳቸውን የሚፈትኑበት ነው፡፡
> ከዚህ የክለሳ ክፍለ ጊዜ በኋላ፤ ተሳታፊዎች ለቢዝነሶቻቸው ሆነ ለግል ህይወታቸው ዕቅድና ግቦችን
የመፃፍ እድል ይኖራቸዋል፡፡
> ከዚህ የሥልጠና ክፍለ ጊዜ በኋላ፤ ስለ ምረቃው ቀን እና ሠዓት ለሁሉም ተሳታፊዎች ማስታወስን
አይርሱ።
> በዚህ የመጨረሻ የስልጠና ክፍለ ጊዜ ወይም በሚቀጥሉት ሳምንታት፤ ለተወሰኑ ሠልጣኞች ተጨማሪ
ምክር ወይም የስልጠና ድጋፍ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

144
የክለሳ ክፍለ ጊዜ
ይምሩ:- እስካሁን ድረስ ብዙ ነገሮችን በጋራ ተምረናል። እስከ ዛሬ ድረስ የተነጋገርንባቸውን ነገሮች ሁሉ
ለማስታወስ እንዲያግዘን፤ አሁን አንድ የመጨረሻ ጨዋታ እንጫወታለን! የማስታወስ ጨዋታ ነው፡፡ እናም
እያንዳንዱ እንደ አንድ ሆኖ ይሰራል፡፡

ይምሩ:- ለሁሉም ተሳታፊ አንድ ጥያቄ እጠይቃለሁ፤ እናም መልሱን የኔ ቡድን ያውቀዋል ብሎ ካሰበ ተነስቶ
ይቆማል! ዕድሉ ሊያመልጠን አይገባም ብሎ ያሰበ ሰው ከሌሎች ቡድኖች በተሻለ ፈጥኖ መነሳት ይኖርበታል!

ይምሩ:- አንድ ሰው ቀድሞ በመቆም የመጀመሪያ ከሆነ፤ በቡድኑ ውስጥ ያለ ሌላ ሰው መልሱን ሊናገር
ይችላል፡፡

ይምሩ:- በትክክል የመለሰ፤ 10 ነጥቦችን ያገኛል፡፡ ከተሳሳተ 5 ነጥብ ይቀነስበታል፤ ከዚያም ሌላ ቡድን
በፍጥነት ተነስቶ ሊመልስ ይችላል። ትክክለኛውን መልስ ከመለሰ፤ 5 ነጥብ ያገኛል፡፡

ይምሩ:- አስታውሱ፤ መመለስ ከፈለጋችሁ ተነስታችሁ መቆም ይኖርባችኋል - እንደተቀመጣችሁ መልስ


በመስጠት፤ ነጥብ ማግኜት አትችሉም!

ይምሩ:- እስቲ ልምምድ እናድርግ! ስሜ ማነው?

ይምሩ:- ፈጥኖ ተነስቶ የቆመውን እንዲመልስ ያድርጉ።

ይምሩ:- በጣም ጎበዝ! 10 ነጥብ አግኝታችኋል!

ይምሩ:- ሌላ ሙከራ እናድርግ፡፡ የት ነው የምትኖረው?

ይምሩ:- ጎበዝ! በትክክል መልሰኸዋል።

ይምሩ:- አሁን ለመጀመር ዝግጁ ናችሁ?

ይምሩ:- ጥያቄዎቹን በራስዎ መንገድ /ሥልት/ ማሻሻል ይችላሉ። ጨዋታውን ለማራዘም ወይም
ተሳታፊዎች ተጨማሪ ነጥቦች እንዲያገኙ ከፈለጉ፤ ጥያቄ መጨመር ይችላሉ።

1) ሕልም የማለም አስፈላጊነት እና ጠቃሜታ ምንድን ነው? ((በብዙ መልክ ሊገለጽ ይችላል)

2) ግቦቻችንን ለይተን ለማስቀመጥ ወሳኝ ከሆኑት ነገሮች ውስጥ ሁለቱን ጥቀሱ፡፡ (በግልጽ ተለይቶ
የሚታወቅ(S)፣የሚለካ(M)፣ሊተገበር የሚችል(A)፣ ተጨባጭ(R) እና በጊዜ ሠሌዳ የተገደበ(T) ወይም
(SMART))

3) እያንዳንዱ የቢዝነስ ባለቤት ሊኖረው የሚገባ አንድ ግብ ምንድን ነው? (የማህበረሰቡን ፍላጎት ማሟላት)

4) ለቢዝነሶቻችን የፋይናንስ ዕቅድ ስናዘጋጅ ምን ተብሎ ይጠራል? (በጀት)

5) የገበያ ትኩረት /ዒላማችን ምን እንደሆነ እንዴት ማወቅ ይኖርብናል? (በማስተዋል መመልከት፣ የዳሰሳ
ጥናት ማድረግ፣ ጥያቄዎችን መጠየቅ)

145
6) ደንበኞች ስለቢዝነሶቻችን በእርግጠኝነት እንዲያውቁ የምናደርግባቸው መንገዶች ምን ምን ናቸው?
(ፕሮሞሽን፣ ማስታወቂያ)

7) ምርቶቻችን በአንፃራዊነት ከሌሎች የተሻለ ጠቀሜታ እንዲኖራቸው ከሚያደርጋቸው ነገሮች ሁለቱን


ጥቀሱ፡፡ (ጥራት ፣ውጤታማነት፣ እሴት፣ ወዘተ.)

8) ምን ዓይነት Mark-up ማግኘት እንፈልጋለን? (30-100%)

9) ሁለት የፕሮሞሽን ዓይነቶች ምን ምን ናቸው? (ማስታወቂያ፣ የገጽ ለገጽ ማስተዋወቅ፣ በራሪ


ወረቀቶች፣ የአፍ ማስተዋወቅ፣ ቅናሽ)

10) ለቢዝነሳችን ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ምን ምን ያስፈልጉናል? (ቦታ፣ ምቾት እና ደህንነት፣ ቅርበት፣


ወዘተ)

11) ለቢዝነሳችን ስም መሠየም ለምን ያስፈልገናል? (ለዕውቅና፣ ለገጽ በገጽ ማስተዋወቅ)

12) በቂ ገንዘብ እያገኘን መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? (የሒሳብ መዝገብ በመጠቀም፣ የበጀት
ዕቅድን በማመጣጠን፣ ትርፍ እና ኪሳራን በማስላት)

13) ከአራቱ የቁጠባ ምድቦች ውስጥ ሦስቱ ምን እና ምን ናቸው? (ለድንገተኛ እና ላልታሰቡ /ላልታቀዱ/
ፍላጎቶች፡-፣ ​ለቤተሰብ ፍላጎቶች ፣ለልዩ ዝግጅቶች ፣ለወደፊት ግቦች)

14) ግቦቻችን ላይ ለመድረስ የምንወስዳቸው መለስተኛ ርምጃዎችን ምን ብለን እንጠራዋለን?


(ግቦች/ዓላማዎች)

15) ሥነ ምግባርን የተላበሰ የቢዝነስ ባለቤት መሆን አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? (በብዙ መልክ ሊገለጽ
ይችላል)

16) በጀት ማውጣት ለምን ያስፈልጋል? (ስሜት የሚሰጥ ማንኛውም ዓይነት መልስ)

17) በመልካም መስተንግዶ የሚታወቅ የቢዝነስ ባለቤት ለመባል መገለጫዎች ምንድን ናቸው? (ውሃ
ማቅረብ፣ ሠላምታን ማስቀደም)

18) አንድን መሪ፤ ጥሩ መሪ የሚያስብለው ምንድን ነው? (ሐቀኝነት እና ግልጽነት፣ ለሌሎች የሚኖር
ትህትና፣ የማስተባበር እና የማደራጀት ብቃት)

19) የቁጠባ ዕቅድ እንዲኖረን የምንፈልገው ለምንድን ነው? (ያልታሰበና ድንገተኛ ሁኔታ ቢከሰት፣ ወደፊት
ለምናስበው ነገር)

20) መነሻ ካፒታል ምንድነው? (ቢዝነሳችንን ለመጀመር የምናጠራቅመው እና ለአንድ ጊዜ /ዙር/ ብቻ


የምንከፍለው ገንዘብ)

21) የገቢ ማስገኛ /ገቢ አመንጪ/ ኢንቨስትመንት ምሳሌ ምንድ ነው? (ስሜት የሚሰጥ ማንኛውም ዓይነት
መልስ)

22) አዲስ ቢዝነስ ለመጀመር፤ ቅድሚያ ምን ርምጃ ለወስዱ ይችላሉ? (ስሜት የሚሰጥ ማንኛውም ዓይነት
መልስ)

146
23) በዚህ ሳምንት የተማሩት በጣም አስፈላጊ ነገር ምንድነው? (ስሜት የሚሰጥ ማንኛውም ዓይነት
መልስ)

24) እስካሁን ያላችሁን ቢዝነስ ለየት ባለ መልክ መስራት የምትፈልጉት ነገር ምንድን ነው? (ስሜት የሚሰጥ
ማንኛውም ዓይነት መልስ

25) እስካሁን ከተማሩት ውስጥ ለሌላ ሰው ማካፈል /ማጋራት/ የሚፈልጉት አንድ ነገር ምንድን ነው?
(ስሜት የሚሰጥ ማንኛውም ዓይነት መልስ)

ይምሩ:- ከፈለጉ ተጨማሪ ጥያቄዎችን ያክሉ!

ይምሩ:- የተሰጡ ነጥቦችን በዝርዝር ይጻፉ፣ ይደምሩ፣ አሸናፊ ቡድኑን ይለዩ፣ በመጨረሻም፤ ከረሜላ
ይሸልሙ፡፡

ይምሩ:- ሁሉም ቡድን ቆንጆ ተሳትፎ ነው ያደረገው! በእውነቱ፤ ሁላችንም ብዙ ተምረናል!

የድርጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት


ይምሩ:- እስካሁን የገበየናቸውን እነዚህን ቆንጆ የቢዝነስ ጽንሰ ሀሳቦች ተጠቅመን፤ ተግባራዊ የሚሆን
የድርጊት መርሃ ግብር ለማዘጋጀት ጊዜው አሁን ነው!

ይምሩ:- የቢዝነሳችሁን የመጨረሻ ተልእኮ በመጻፍ ትጀምራላችሁ፡፡ መጀመሪያ ወደ ጻፋችሁት ወደ ክፍል 4፤


ማለትም (መሠረታዊ የቢዝነስ ክህሎት ሥልጠና) ተመልሳችሁ ማጣቀስ ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን እንደገና
ለማሻሻል ጊዜው አሁን ነው! ምን ተማራችሁ? ምን ዓይነት ልዩ ክህሎቶቻችሁን ለይታችሁ አወቃችሁ?
ማህበረሰባችሁ ምን ዓይነት ምርት ወይም አገልግሎት ይፈልጋል? በአንፃራዊነት በአካባቢው ካሉ ሌሎች
ቢዝነሶች የተሻሉ አገልግሎቶች እንዴት ትሰጣላችሁ?

ይምሩ:- በመቀጠልም፤ ይህንን ቢዝነስ ለመጀመር ወይም የጀመራችሁትን ለማሻሻል የምትፈልጉበትን የጊዜ
ሠሌዳ ታዘጋጃላችሁ፡፡

ይምሩ:- ከዚያም፤ ሶስት የግል ህይወት እና ሶስት የቢዝነስ ግቦችን ፃፉ፡፡ እስካሁን የለያችኋቸውን ግቦች
ለማስታወስ ቀደም ሲል የሠለጠናችሁበትን የትምህርት ክፍል መለስ ብላችሁ ቃኙ፡፡

ይምሩ:- በመጨረሻም፤ እነዚህ የቢዝነስ ግቦች ላይ ለመድረስ የሚረዳችሁን ጥሩ የድርጊት መርሃ ግብሮችን
እንድትጽፉ እንፈልጋለን፡፡ አስታውሱ፤ የድርጊት መርሃ ግብሮቻችሁ፡- ______________
_________________________________________________ ሊሆኑ ይገባል፡፡ (በግልጽ ተለይቶ
የሚታወቅ(S)፣የሚለካ(M)፣ሊተገበር የሚችል(A)፣ ተጨባጭ(R) እና በጊዜ ሠሌዳ የተገደበ(T) ወይም
(SMART))

147
ይምሩ:- ይህንን መልመጃ ለመጨረስ፤ የሠልጣኞች መጽሐፍ ገጽ ____ን ክፈቱ፡፡ ለ15 ደቂቃ ያህል
እንሰራለለን፡፡ በአጠገባቸው እየተንቀሳቀሱ አስፈላጊውን ግብረ መልስ፣ ማበረታቻ እና ድጋፍ ይስጧቸው።

ቡድን አመቻቾች፡- ለተሳታፊዎች በየቡድኑ እገዛ አድርጉላቸው፡፡ በዚህ የመጨረሻ ክፍል፤ የተማሯቸውን ሁሉ
በሥራ ላይ ለማዋል ለሚያደርጓቸው ጥረቶች አበረታቷቸው እንዲሁም አመስግኗቸው፡፡

ይምሩ:- ስለ ቢዝነስ ግቡ፣ የድርጊት መርሃ ግብሩ፣ እና ስለ ጊዜ ሠሌዳው ሊያጋራን የሚፈልግ አንድ ሰው
ይኖራል?

ይምሩ:- ጊዜ እንደፈቀደልዎት መጠን፤ ብዙዎች እንዲሞክሩ ይፍቀዱ። ከቻሉ መልሶቹን ሁሉ በሠሌዳው ላይ


ያስፍሩ - ይህ አስደሳችና አዝነዘኝ ከመሆኑም በተጨማሪ፤ የሚመኙትን የድርጊት መርሃ ግብር እንደወሰዱና
እንዳልወሰዱ ለመገምገም ይረዳዎታል፡፡

ጥያቄ እና መልስ
ይምሩ:- ጊዜ ካለዎት፣ ተሳታፊዎች እንደገና ሊወያዩባቸው በሚፈልጓቸው ማንኛውም ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ
በማወያየት ይህን ጊዜ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡

የስልጠናው ማጠናቀቂያ ቅኝት


ይምሩ:- ከማጠናቀቃችን በፊት፤ የተወሰነ መረጃ ከእናንተ መቀበል እንፈልጋለን፡፡ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ
ወስዳችሁ፤ ሁላችሁም እንድትሞሉት የምንፈልገው አጭር የዳሰሳ ጥናት አለን። ይህ ስልጠና ምን ያህል እገዛ
እንዳደረገላችሁ እና እኛ ማሻሻል የሚገባንን ማወቅ ለእኛ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

ይምሩ እና ቡድን አመቻቾች፡- ከእያንዳንዱ ተሳታፊ ጋር የተናጠል ውይይት በማካሄድ፤ ስለ ስልጠናው


የማጠናቀቂያ ቅኝት ያድርጉ። ቅኝቱን እንዲህ በተናጠል ማካሄድ፤ የመረጃው ሚስጥራዊነት እንዲጠበቅ
ስለሚያደርግ፤ ተመራጭ ነው፡፡ ማብራሪ የሚጠይቁ ጥያቄዎችን በማቅረብ፤ ምላሾችን ቃል በቃል እና
በጥንቃቄ ይመዝግቡ።

ማጠቃለያ
ይምሩ:- በዚህ የስልጠና ቆይታ፤ ስለነበራችሁ ተሳትፎ እና ከእኛ ጋር ቆይታ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን።
በፕሮገራሙ መሠረት በስልጠና ቦታ ላይ በሠዓቱ በመገኘት፣ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ እና በጓደኝነት መንፈስ
አክብራችሁናል።

ይምሩ:- ለምረቃ ዝግጅታችን በጣም ጓጉተናል! የሠልጣኝ መጻሕፍቶቻችሁን ወደ ቤታችሁ መውሰድን


አትርሱ፡፡ ምክንያቱም ቢዝነሳችሁን ስትጀምሩ ወይም ያላችሁን ቢዝነስ ስታሻሽሉ ተመልሳችሁ ለመከለስ
እና ለማስታወስ ያግዛችኋል፡፡

148
ይምሩ:- ለምረቃ እንገናኝ!

ይምሩ:- የምረቃ ፕሮግራሙ መቼ እንደሚሆን እና ቤተሰቦቻቸው ተጋባዥ እንደሚሆኑ ወይም እንደማይሆኑ


ይግለጹላቸው። የሠልጣኝ መጻሕፍቶቻቸውን ወደ ቤት ወስደው እንዲጠቀሙባቸው በድጋሚ
ያስታውሷቸው!

የምረቃ ሥነ ሥርዓት
ስልጠናው ተጠናቅቋል፤ ይሁ እንጅ፤ ይህንን ወሳኝ ስኬት ለማክበር በቂ ዝግጅት ያድርጉ! ተሳታፊዎቹ
ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን መስዋዕት አድርገዋል፤ ከለመዱት የህይወት ዘይቤ ወጥተው ለመለወጥ ብዙ
ጥረት አድርገዋል። ለዚህ ብርቱ ጥረታቸው እውቅና በመስጠት እና የምረቃ ሥነ ሥርዓት የሸልሟቸው!

በሁሉም የምረቃ ሥነ ሥርዓቶች ላይ፤ የምስክር ወረቀት፣ የግል እና የቡድን ፎቶዎች፣ እንዲሁም
የሥልጠናው የዳሰሳ ጥናቶች አይቀሬ ናቸው፡፡ የመስተንግዶው መጠን በዚህ የሚወሰን በመሆኑ፤ የሠልጣኝ
ቤተሰቦች ወይም የማህበረሰቡ አባላት የሥነ ሥርዓቱ ታዳሚዎች መሆን አለመሆናቸውን አስቀድመው
ያረጋግጡ።

የምረቃ ፕሮግራሙ ጽንሰ ሃሳቦች፡-

● ስለ ስልጠናውም ሆነ በስልጠናው ወቅት ስላስተዋሉት ገጠመኞች እንዲያጋሩ ተሳታፊዎችን


ያበረታቱ፤
● አመቻቾችም አጭር የምስጋና እና የአድናቆት ንግግር ሊያደርጉ ይችላሉ፤
● ለተመራቂዎቹ የምስክር ወረቀት ይስጡ፤
● ከእያንዳንዱ ተመራቂ እንዲሁም ከአንድ ወይም ሁለት አመቻቾች ጋር ፎቶ ይነሱ፤
● ከመላ ተመራቂዎች እና ከተወሰኑ ተጋባዦች ጋር በአንድነት ፎቶ ይነሱ፤
● ለስልጠናው ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ የጣቢያው አስተናጋጆች ስጦታዎችን ያበርክቱ፤
● በመክሰስ /ስናክ/ እና በሻይ መስተንግዶው ይደሰቱ!
● ከተሳታፊዎች ለሚበረከትልዎ ስጦታ ዝግጁ ይሁኑ፡፡

149
// መረጃዎች //
ቅጾች ፣ የምስክር ወረቀቶች እና ማጣቀሻዎች

1. የመመዝገቢያ ቅፅ / የስልጠናው ማጠናቀቂያ ቅኝት

2. የሠልጣኞች ማስታወሻ ዝርዝር

3. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ ቁልፍ

4. የቃላት መፍቻ ቁልፍ

5. የተመራቂዎች ምስክር ወረቀት

150

You might also like