You are on page 1of 13

ክፍል 5

ወጣቶች ለሥራ ያላቸው አመለካከት


ቅርፅ (Format)፡ የሬዲዮ ጭውውት (Drama)

የገፀ ባሕሪያት ቁጥር 3


የፆታ ስብጥር 2 ሴት፣ 1 ወንድ
የገፀ-ባሕሪያትድርሻዎች እናት፣ ወንድ ልጃቸው፣ የቅጥር ሠራተኛ ሴት

ወርቅነሽ ፡

የአብዲ እናት፣ እድሜ 54፣ በጡረታ ምትተዳደር፣ ቤት ውስጥ የባህል ልብስ በመስራት
ተጨማሪ ገቢ ምታገኝ፣ በልጇ ትምህርት ምትኮራ ግን ስራ ባለማግኘቱ የምትጨነቅ እናት

አብዲ

በምህንድስና ትምህርት በዲግሪ የተመረቀ ፣ ስራ አጥ ሆኖ ለአመት ቤት የተቀመጠ፣


የሚመጣለት ስራ ሁሉ አልጥመው የሚል የስራ አመለካከት ችግር ያለበት፣ ቁጭ ብሎ የተሻለ
አድል እንዲመጣለት የሚጠብቅ ሆኖም ስራ አጥ በመሆኑ ችግሩን ከሱ ውጭ አድርጎ የሚናደድ

ጊፍቲ (የጎረቤት ልጅ)

በአካውንቲንግ ተመርቃ ወረዳ የመንግስት ስራ የጤና ጽ/ቤት ሰራተኛ የሆነች፣ በስራ ጉብዝናዋ
ትሁትነቷ ሰው የሚመርቃት፣ ቤተሰቧን በገቢ የምትደግፍ ወጣት ሴት

አፅመ-ታሪክ

እናት ወርቅነሽ ለባህል ልብስ መስሪያ የሚሆን እቃ ለመግዛት ገባያ ውላ ትመጣለች፣ ሰፈራቸው መግቢያ ላይ የተቆፋፈር
መንገድ እግሯን ወለም አድርጓታል፣ ስራ ፈቶ የተቀመጠው ልጇ አብዲ በሙያው ምህንድስና ሰቅሎ የጨረሰ እንመሆኑ ፣
የመንገድ ስራ ጥራትን በመተቸት ጀምራል፣ እናት ለምን አትሰራውም ታዲያ ሀሳብ ታቀርባለች፡ በዚህ ወደ ስራ ለምን
አትፈልግም ጭቅጭቅ ያመራሉ፡፡ እናት እኩያውን የጎረቤት ልጅ ጊፍቲን እያነሳሳች እሷን አታይም ወይ? እያለች እየወቀሰችው
እያለች

ጊፍቲ ለእናት ወለምታ መታሻ መድሀኒት እና የባህል ልብስ ለቤተሰቦችዋ በሙሉ ያሰራችበትን ብር ልብሱንም ልትቀበል
ትመጣለች፡፡

እሲቲ ቡና ይፈላ ተብሎ… የስራ ጉዳይ ወሬ ይጀመርበታል፡፡ ጊፍቲ ከልምዷ የስራ ጥቅም አስረጂ አብዲ አጣጣይ ተከራካሪ
ይሆናሉ። እናት ወርቅነሽ ጊፍቲን አግዛ ስትታይ፣ በስተመጨረሻ አብዲ የስራ አጥነት ችግሩ ከሱ አስተሳሰብ እና ምርጫ
አንደሆን ያምናል፡፡ ጊፍቲም ስራ የሚያገኝበትን በመስሪያ ቤቷ ያለውን የአንድ መስኮት አገልግሎት እንዲያገኝ ሀሳብ
ታቀርባለች፡፡ በዚህ ተስማምተው እናት መርቃቸው ጨዋታቸውን ይቀጥላሉ።
ክፍል 5: ወጣቶች ለሥራ ያላቸው አመለካከት 1

[የመግቢያ ሙዚቃ፤ በድምቀት ጀምሮ እየቀነሰ ይሄዳል]

INT./EXT. ቀን

/አብዲ፣ ወርቅነሽ፣ ጊፍቲ/

እናት ወርቅነሽ ለባህል ልብስ መስሪያ የሚሆን እቃ ለመግዛት ገባያ ውላ ትመጣለች፣ ሰፈራቸው መግቢያ ላይ የተቆፋፈር
መንገድ እግሯን ወለም አድርጓታል፣ ስራ ፈቶ የተቀመጠው ልጇ አብዲ በሙያው ምህንድስና ሰቅሎ የጨረሰ እንመሆኑ ፣
የመንገድ ስራ ጥራትን በመተቸት ጀምራል፣ እናት ለምን አትሰራውም ታዲያ ሀሳብ ታቀራባለች፡ በዚህ ወደ ስራ ለምን
አትፈልግም ጭቅጭቅ ያመራሉ፡፡

አብዲ እናቱ ከገበያ ስትመጣ ለማስደሰት የቡና እቃ እያቀራረበ ሙዚቃ ከፍቶ እየዘፈነ

/ሙዚቃው ይሰማል የጃንቦ ጆቴ፣ አብዲ አብሮት እየዘፈነ/

አብዲ

/ዘፈኑን እየዘፈነ/

ዛሬማ እማዬን ቡና አቀራርቤ ስታይ ደስ ነው የሚላት

/ዘፈኑን እያለ/

እቃ ፍለጋ ላይ እንዳለ .... እቃ የማንኳኳት ድምጽ

አብዲ

ጀበናው ደሞ የት ነው... አዎ ይኸውና /እየዘፈነ/

በመሀል በር በሀይል ይኳኳል

ወርቅነሽ

አብዲ! አብዲ! … አንተ አብዲ!

አብዲ ይሰማና ሙዚቃውን ይቀንሰዋል

አብዲ

አቤት አቤት

በር ይከፍታል /በር የመክፈት ድምጽ/

ወርቅነሽ እና ጊፍቲ በር ላይ አብዲ እናቱ አንደማነከስ ብላ ጊፍቲ ይዛት ይመለከትና ይደነግጣል

ወርቅነሽ
ክፍል 5: ወጣቶች ለሥራ ያላቸው አመለካከት 2

አንተ ልጅ በቃ ይሄ ሙዚቃ እያስጮክ አትሰማም

አብዲ

ይቅርታ እማዬ አልሰማሁሽም... ምን ነው እግርሽን

ምን ሆነሽ ነው፣ ...ጊፍቲ ምን ሆና ነው

ወርቅነሽ

ምንም አልሆንኩም ትንሽ ወለም ብሎኝ ነው

ጊፍቲ

እትዬ መታሻውን ይዤልሽ ልምጣ

አብዲ

መታሻ ምንድን ነው!

ወርቅነሽ

ልጅቷን እቃውን ተቀባላት

እኔንም አታቁመኝ ዞር በል ልግባ

ጊፍቲ

እብዲ እንካ

አብዲ

እሺ እሺ

/እቃ እየተቀበለ መንኳኳት/

ጊፍቲ

መጣሁኝ

ወርቅነሽ

እሺ ሂጂ ሂጂ ልጄ

አብዲ

እዚህ ጋር ወንበሩ ላይ አረፍ በይ.. ቆይ ላስጠጋልሽ

ወርቅነሽ
ክፍል 5: ወጣቶች ለሥራ ያላቸው አመለካከት 3

ወይ አምላኬ ይሄ ሰፈር አንደው መላም የለው

አብዲ

እግርሽን ምን ሆነሽ

ወርቅነሽ

እስኪ ተወኝ! ገበያ ውዬ ለጊፊቲ የምሰፋላትን ልብስ ጨርቁ ጠፍቶ በስንት ፍለጋ

ያውም ዋጋው ጣሪያ ነክቷል፣ ተጨቃጭቄ በስንት መከራ አግኝቼ መጣሁ

አብዲ

እሺ

ወርቅነሽ

እሱን ተሸክሜ ስመጣ፣ እዚህ መግቢያው ላይ መንገዱን ቆፋፍረውት የለ

አብዲ

እህ

ወርቅነሽ

ሸርተት አደረገን እና እግሬ ዞር አለብኝ...ጊፊቲ ደርሳ አገዘችኝ

አብዲ

በጣም ተጎዳሽ

ወርቅነሽ

አይ ብዙም ...ያለው ስታሽ ይለቃኛል፣ ድንጋጤው ነው

አብዲ

ይሄ የተረገመ መንገድ፣ ወይ በስርዓት አልሰሩት፣ ወይ አልጨረሱት፣

ዝም ብለው ያለ ሙያቸው ቆፋፍረውት እኮ ነው

እኔ ኢንጅነሪንግ ተመርቄ ቁጭ ብያለሁ፣ እነሱ ያለሙያ እያስቆፈሩ ሰው ለጉዳት


ይጥላሉ፣

ይኸው አንቺም ላይ ደረሰ

ወርቅነሽ
ክፍል 5: ወጣቶች ለሥራ ያላቸው አመለካከት 4

ሙያዬ ነው ካልክ ወተህ አትሰራው ነበር

አብዲ

ስራውን መች ይሰጡናል፣ እኛን ኢንጅነሮች እያለን የሚቀጥሩት ሌላ ነው

ወርቅነሽ

ወዴት ወዴት! ስራ ማስታወቂያ አውጥተው መቼ አመለከትክ፣

ሰፈር ውስጥ አልርመጠመጥም፣ ገንዘቡ ትንሽ ነው ደረጃዬ አይደለም እያልክ


አልነበር

አብዲ

ታዲያ አምስት አመት ለፍቼ ተምሬ በትንሽ ገንዘብ ያውም

አንደ ቀን ሰራተኛ ያውም ሰፈር ውስጥ ልስራ!

ወርቅነሽ

እንዲህ እያልክ ነው የተገኘውን ስራ ሁሉ ስትንቅ አመት ቤት ቁጭ ያልከው

አብዲ

እማዬ ደግሞ

ወርቅነሽ

እኔ ይከፋሀል እያልኩ ነው ማልናገርህ..

አንጂ አንተ ስራ ቤትህ ድረስ ቢመጣም አትሰራ... ስራ ትንቃለህ

አብዲ

እኔ ስራ አልንቅም! ግን በዲግሪ የተመረኩት

በማእረግ ነጥም የጨረስኩት በሙያዬ የሚመጥነኝ ለመስራት ነው

ወርቅነሽ

አየን እኮ ስንት ነገር መቶ ትመልሳለህ... ስራ መናቅህ ነው

አብዲ

እማዬ ብዙ ግዜ ተነጋግረናል በሙያዬ የሚገባኝን እስካገኝ ብዬ የማይመጥኝን ወርጄ አልሰራም

... ይልቅ ደስ አንዲልሽ ብዬ ቡና አቀራርቤያለሁ


ክፍል 5: ወጣቶች ለሥራ ያላቸው አመለካከት 5

ወርቅነሽ

ሁሌም ስለስራ ሳነሳ ትሸሻለህ እሺ ይሁንል...

ደሞ ምኑን አቀረብከው ከሰሉ የታለ፣ ማንደጃውስ ቡናው እራሱ ነው የሚፈላው

አብዲ

ከሰል እኮ አጥቼ ነው፣ በቃ ብር ስጪኝ ከዝቼ መጣለሁ

ወርቅነሽ

አየህ ስራ ብትይዝ ቢያንስ ለቡና ከሰል ትገዛልኝ ነበር

አብዲ

እማዬ ጀመረሽ ደግሞ

INT. ቤት ውስጥ

ቡና እየተፈላ .. እናት ለአብዲ እኩያውን የጎረቤት ልጅ ጊፍቲን እያነሳሳች እሷን አታይም ወይ ትወቅሰዋለች እሷንም ምከሪልኝ
እለች አብዲ ስራ ያጣው በሱ ችግር አንዳልሆነ ለማስረዳ ይሞክራል

ጊፍቲ ለእናት ወለምታ መታሻ መድሀኒት እና የባህል ልብስ ለቤተሰቦችዋ በሙሉ የምታሰራበትን ይዛ ትመጣለች

በር የመከፈት ድምር/

ጊፍቲ

እትዬ ወርቅነሽ ይኸው አመጣሁልሽ

ወርቅነሽ

ጎሽ የኔ ልጅ ተባረኪ

ጊፍቲ

ይሄ የልብሱ ብር ነው 800 አይደል ያሉኝ

ወርቅነሽ

አዎ ትክክል ነሽ...

ወይ ቀኜን ስል ደሞ ግራዬም ይጠዘጥዘኝ ጀመር

ጊፍቲ

እኔ ልሽሎት
ክፍል 5: ወጣቶች ለሥራ ያላቸው አመለካከት 6

ወርቅነሽ

አይ ተይ እኔ ራሴ አደርገዋለሁ፣ አንቺ ስራ አለብሽ ሂጂ

ጊፍቲ

ወይ ቡናውን እኔ ላፍላው ለኔ ብለው ነው እቃ ተሸክመው የተጎዱት..

ወርቅነሽ

እሺ ተባረኪ.. እንደው ግን ይሄ ልጅ ለምን አትመክሪልኝም!

ጊፍቲ

ማንን አብዲን ነው

ወርቅነሽ

ይኸው ከናንት እኩል ተምሮ ስራ የለም፣

አመት ሞላው ለምንድን ነው እንደናንት ስራ ማይሰራው

ጊፍቲ

እሱ እኮ እኔ ያልሆንኩት ካልሆነ ስለሚል ነው

ወርቅነሽ

እኔ ብዬው አልሰማ ብሎኛል እባክሽ ምከሪልኝ እስኪ

ጊፍቲ

ግድ የለም በዘዴ እንነግረዋለን

INT. ቤት ውስጥ

አብዲ ይገባል.../የበር ድምጽ/

አብዲ

ይኸው አማ አግኝቻለሁ… አንዴ ጊፍቲ ቡናውን ተያያሽ አንዴ!

ወርቅነሽ

ና አንተ ቁጭ በል እሷ ታፈላዋለች

አብዲ

ለምን እኔ ነኝ ማድረግ ያለብኝ


ክፍል 5: ወጣቶች ለሥራ ያላቸው አመለካከት 7

ወርቅነሽ

ሙያዬ ኢንጅነሪንጉ ካልሆነ አልሰራም ትል የለ፣

ቡናውንም ሙያ የለህም አትችልበትም ና ቁጭ በል

አብዲ

ዛሬ በቃ ይዘሽናል

ጊፍቲ

እማማ እውነታቸው እኮ ነው

ብዙ ግዜ ሆነ ለምን አንዱ ጋር ስራ አትገባም

አብዲ

እናንተ እኮ አትረዱኝም እኔ ስራ ንቄ አይደለም

ወርቅነሽ

ነው አንጂ አሁን ጊፊቲን እያት አካውንቲንግ ተምራ

መንግስት ቤት ወረዳ አነሰብኝ ሳትል እየሰራች ቤተሰቧን እየረዳች ነው

አብዲ

የሷ እና የኔ ምን አገናኘው

ወርቅነሽ

እንዴት አይገናኝም ተምረሀል ስራ መስራት ነው

ጊፍቲ

ቆይ እማማ ...ብናውን እየጠጣን ይሻላል!

አብዲ እንካ ቡናውን አቀብላችው

አብዲ

እሺ

INT. ቤት ውስጥ
ክፍል 5: ወጣቶች ለሥራ ያላቸው አመለካከት 8

ቡና እየተጠጣ … የስራ ጉዳይ መነጋር ይጀምራሉ፡፡ ጊፍቲ ከልምዷ የስራ ጥቅም አስረጂ አብዲ አጣጣይ ተከራካሪ ይሆናሉ
እናት ወርቅነሽ ጊፍቲን አግዛ ስትታይ፣ በስተመጨረሻ አብዲ የስራ አጥነት ችግሩ ከሱ አስተሳሰብ እና ምርጫ አንደሆን
ያምናል፡፡

ወርቅነሽ

ቆንጆ ቡና ነው የኔ ልጅ

ጊፍቲ

አመሰግናለሁ እማማ ... እሺ አብዲ ምንድን ሚሰማህ ንገረን

አብዲ

ምን መሰላችሁ፣ እኔ ስራ ሰርቼ እማዬን መጦር ነው ምኞቴ ስራ ለመፈለግም ሰንፌ


አይደለም ...ግን አስቡት 5 አመት ለፍቼ በኢንጅነሪን ተመርቄ፣ ደህና ክፍያ ያለው
ነገር ነው መስራት ያለብኝ፣ የሚወጣው ማስታወቂያ ሁሉ አነስተኛ ክፍያ ነው በዛ
ላይ ደግሞ የስራ ልምድ ይጠይቃሉ፡

ብዙዎቹ ያገኘኋቸው ስራዎች ደግሞ በሙያ በተመረኩበት የምሰራው አይደሉም፣


ገንዘቡም አንሶ በሙያዬም ካልሆነ ምንድን ነው ጥቅሙ.. እኔ እኮ በመአረግ ነው
የተመረኩት ደህና ቢሮ ኖሮኝ፣ በራሴ በሙያዬ ማገለግለበት እሱ ቢቀር ቢያንስ
ለልብስ እና ለጫማ የማልጨነቅበት ገንዘብ ሊከፈለኝ ይገባል ካሆነ ግዜ ጉልበት
እውቀቴን ማባከን ነው... እኔ ይሄ ነው የሚያናደኝ

ወርቅነሽ

ወይ ጉድ ሰው ያገኘውን ሰርቶ ማደር ነው አንጂ ማንም ከፎቅ የሚጀምር የለም


ሁሉም ቀስ እየተባለ ነው ሚመጣው

ጊፍቲ

እማማ እኔ እሱ ባለው እስማማለሁ...

ማለቴ ሰው በሙያው በተማረበት ለፍቶ ጥሩ ነገር ማግኘት አለበት

አብዲ

እኔም እሱን ነው የምለው...

የማይመጥን ነገር በመስራ ግዜ አላባክን ነው የምለው

ጊፍቲ
ክፍል 5: ወጣቶች ለሥራ ያላቸው አመለካከት 9

ታዲያ የፈለከውን ለማግኘት እኮ ብዙ መንገዶች አሉ መቀጠር አንድ አማራጭ


ነው… ሌላው ደግሞ በራስህ በሙያህ ስራ መፍጠር ይቻላል

አብዲ

አንቺ ደግሞ ተደራጅ ምናምን አንዳትይን..ለሱም እኮ መነሻ ይጠይቃል..ደህና ስራ


ለመቀጠር ደግሞ የስራ ልምድ ይላሉ አንዴት ነው ታዲያ የሚኮነው፣ ለጀማሪ ሁሉ
ነገር የሚከብድ ነው

ጊፍቲ

ይኀውል አብዲ በእርግጥ ያልከው ነገር ይገባኛል፣

የምትፈልገውን ስራ ማግኘቱ አንደምትፈልገው ሊከብድ ይችላል

ግን ከየት ነው መጀመር ያለብኝ ማለት አለብህ

አብዲ

እንሺ ከየት ነው ሚጀመረው

ጊፍቲ

ምን መሰለህ ብዙዎቻችን አመለካከታችንን መጀመሪያ መፈተሽ አለብን፡


አመለካከት ስል ብዙ ወጣት የሚሰራ ስለጠፋ አይደለም ስራ የሚያጣው፣
በዙዎቻችንን ተምረን ስንጨርስ የምንጠብቀው ነገር አለ፣ ጥሩ ገንዝብ በቀላሉ
የሚገኝበት፣ በሙያችን ብቻ የሆነ፣ የተሟላ ቢሮ የስራ ቦታ ያለው ምናልባትም
ብዙ ቦታ የምትነቀሳቀስበት ብቻ ነው ምናስበው ይሄ ደግሞ እውነታ አይሆንም

ወርቅነሽ

ትክክል እስኪ በደንብ ንገሪኝል

ጊፍቲ

አኔ ለምሳሌ ሙያዬ አካውንቲንግም ቢሆን በጀት ላይ ነው ምሰራው ከሙያዬ ጋር


በቀጥታ ባይገናኝም ተቀራራቢ ነው እየሰራሁኝ ልምድ አገኝበታለሁ፣ መጀመሪያ
አንዳንተ በጣም ከብዶኝ ነበር፣ ደሞዙም ትንሽ ነው ብዬ አይመጥኝም ብዬ ነበር
ግን ደሞዝም ስትይዘው ነው በአግባቡ ስትጠቀምበት ነው እየሰራህ ነው
ምታድግበት፣

አብዲ
ክፍል 5: ወጣቶች ለሥራ ያላቸው አመለካከት 10

እሱ ትክክል ነው

ጊፍቲ

እኔ አሁን በስራዬ በቅጥር ሆኖ ሁለት ግዜ ደሞዝ አድጌበታለሁ፡፡ እሱ ብቻ


አይደለም እየሰራሁኝ ስልጠናዎችን አገኛለሁ የመማር እድል አለኝ፡ እኔ ባልኩት
ብቻ ካልሆነ ቤት ብቀመጥ ይሄኔ ምንም አይፈጠረም ይፈጠራል

አብዲ

እሱማ አይፈጠርም

ጊፍቲ

ግን አሁን አነሰም በዛም ደሞዝ ተከፋይ መሆኔ የምፈልገውን እያደረኩበት ነው፣

ግን አሁን አነሰም በዛም ደሞዝ ተከፋይ መሆኔ የምፈልገውን እያደረኩበት ነው።


ቢያንስ ጸጉሬን ለመሰራት ከቤት አልጠይቅም፤ ወጥቼ ምገባበት አነሰብ በሰዛም
በስራቴ አስከብሮኛል፣ ከኔ አልፌ ቤተሰብ ለመርዳት አንዳንድ ነገር ማድረግ
በመቻሌ ደስተና ነኝ፡፡ ከኔ አልፌ ቤተሰብ ለመርዳት አንዳንድ ነገር ማድረግ
በመቻሌ ደስተኛ ነኝ፡፡ ከኔ አልፌ ቤተሰብ ለመርዳት አንዳንድ ነገር ማድረግ
በመቻሌ ደስተና ነኝ፡፡ ደግሞ ደሞዝ መኖሩ በራሱ የሚፈጥረው ነገር አለ፣ ከስራ
አጋሮቼ ጋር እቁብ እጥላለሁ። በስራ አጋጣሚ አበሎች አሉኝ ሌሎች የገንዘብ
አማራጮችም አገኝበታለሁ። ስራ ስንመርጥ ደሞዝ ላይ ብቻ ፣ሙያ ላይ ብቻ
ማተኮር አይገባም ... ስራው ውስጥ ሆነን ወደምንፈልገው መንገድ ሊወሰደን ነው
የሚገባው

ወርቅነሽ

እየሰማህ ነው

አብዲ

እሱማ ትክክል ነሽ ግን የሚገባኝን አለማግኘት ቅር ያሰኛል

ጊፍቲ

ትክክል ነህ ግን ስራ ስትፈልግም አማራጭህን ማስፋት አለብህ ማስታወቂያ ብቻ


በተማርከው ብቻ ተጽፎ ቁጭ ካላል አይሆንም ማለት የለብህም፣ ብዙ አማራጭ
አለው፣
ክፍል 5: ወጣቶች ለሥራ ያላቸው አመለካከት 11

ለምሳሌ እኔ ምሰራበት ወረዳ የአንድ መስኮት የስራ አገልግሎት ሚሰጥበት አለ፣


የሚሆንህን ስራ ከማግኘት በላይ መስራት የምትፈልገው ነገር ላይ የግል ስራ
አማራጮች ያግዛሉ

አብዲ

እውነትሽን ነው

ጊፍቲ

አዎ፣ እንዳውም ከሰሞኑ አብረን ሄደህ ብታናግራቸው ደስ ይለኛል

ወርቅነሽ

ልጄ እስኪ እሺ በል እና ሞክር

አብዲ

እሺ እማ ሞክራሁ

ጊፍቲ

ስማ አንድ ነገር ግን፣ ስራ አለመኖር ብዙዎቻችን ወጣቶች የሚያስጨንቅ ቢሆንም


ዋናው እኛ በምናስበው መልኩ ብቻ ካልተቀመጠ ማለታችን ነው በመቀጠርም
በራስ ስራም እንዳንሳራ የሚያደርገን... ይኔንን ስልህ ኢንጅነሪነግ ተመርቀህ ጽዳት
ስራ ማለቴ አይደለም ግን ጽዳት ውስጥም የኢንጅነሪንግ እውቀት የሚጠይቅ ሙያ
አለ፣ አይተህ አንደሆነ ትልልቅ ድርጅት ሆነው ህንጻ የሚስውቡ በትልቅ በጀት
ሙያ እውቀት ኖሮት ነው የሚሰራው፡፡ ስለዚህ ስራ ስትመርጥ ዋናው የኪስ ገንዘብ
ከማግኘት ጀምሮ ልምድ መያዝም፣ እየተማርክበት ማደግ መቻልህ፣ ስራውን
ስትይዘው አብሮ የሚመጣ ፣ እያሻሻልክ የምትሄድበት የምትሻሻልበት አማራጭ
በእጅህ ማስገባትህ ነው ... ተግባባን

አብዲ

በጣም እንጂ፣ ቁጭ ብሎ እንዲህ ነው አንዲያ ከማለት በምን መልኩ ሊሆን


ይቻላል ብሎ አማራጭ ማየት ነው

ወርቅነሽ

ጎሽ የኔ ልጅ ተባረክ

አብዲ
ክፍል 5: ወጣቶች ለሥራ ያላቸው አመለካከት 12

እሜን ደግሞ ያንቺ ምርቃት ተጨምሮበት ጥሩ ነገር ነው ማገኘው፣

ለአመቱ ሙሉ የባህል ልብስ እኔ ነኝ ከፍዬ ማሰራሽ /ሳቅ/

ወርቅነሽ

ወይ ጉድ ገና ምኑ ተይዞ ያደርግል

ጊፍቲ

እኔ እልጠራጠርም

አብዲ

ንገሪልኝ እሷ እኮ ቡና ማፍላትም አታምነኝም /ሳቅ/

ወርቅነሽ

አይቼ ነዋ ባለፈው ቡናውን አሳርሮ ቆልቶ

እሬት የጠጣው ነበር የመሰለኝ .. ሙች

አብዲ

እቤት ማጋነን

ይሳሳቃሉ

You might also like