You are on page 1of 4

*** በኢየሩሳሌም ሰማይ ላይ የታየው ድንቅ ምልክትና የተሰማው የብዙ መለከት ድምጽ የዓለምን ሚዲያ

እያነጋገረ ነው።***

***ከ 500 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ተከፈተ፣ በሰማይም ድንቅ ምልክት
ታየ ክብር ሁሉ ለቤዛችን ለትንሳኤው ጌታ ይሁን።**

**ጽሑፋን በደንብ አንብቡት።**

መ/ር ታሪኩ አበራ

የዓለምን ማኅበረሰብ እጅግ ያስደመመና የኢየሱስ ክርስቶስን ታላቅ አምላክነት ያሳየ ድንቅ ተአምር
በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም ታይቷል። በሰማይ ላይ በግልጽ የተሰማው ድምጽ ባለ ራዕዩ ቅዱስ ዮሐንስ
የሰማው ዓይነት የመለከት ድምጽ ነው።
" በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ትላቅ ድምፅ ሰማሁ፥"
(የዮሐንስ ራእይ 1:10)

ከ 500 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእድሳት የክርስቶስ ሥጋ አርፎበት የነበረው መቃብር ሲከፈት ድንገት
ሳይታሰብ የብዙ መለከትና የእምቢልታ ድምጽ ከሰማይ ተሰምቷል የክብር ደመናም በሰማይ ከብቦ በግልጽ
ታይቷል።

" በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ
ይመጣሉ፥ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ይሰግዳሉ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 27:13)

ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ አርብ ከባዱን ሕማምና ስቃይ ስለ ሰው
ልጆች ሁሉ ተቀብሎ በመስቀል ላይ በፈጸመው የቤዛነት ሥራ በደሙ የዘለዓለም ሥርየትን ሰጥቶ በስሙ ላመኑ
ሁሉ ጽድቅን ያለዋጋ በጸጋ አጎናጽፎ ነፍሱን በገዛ ስልጣኑ ለይቶ ወደ መቃብር ወርዷል።በሦስተኛውም ቀን
መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል የመቃብርና የሲዖል መክፈቻ በእጁ የሁኑ ጌታ በኃይልና በሥልጣን
ሞትን ድል አድርጎ በመቃብር ጀርባ ላይ ቆሞ ትንሳኤውን ገልጿል። ክብር ለስሙ ይሁን።

ይህ ክርስቶስ የተቀበረበትና ትንሳኤውን የገለጸበት ቅዱስ ስፍራ ዛሬ ላይ ታላቅ ቤተመቅደስ ታንጾበት የዓለም
ማኅበረሰብ ወደዚህ ቅዱስ ስፍራ እየሄደ በመጸለይና በመስገድ ለዘመናት በረከትን ሲቀበልበት ኖሯል።
አውሳብዮስ ዘቂሳርያ የተባለው የታሪክ ተመራማሪና የነገረ መለኮት ሊቅ በዚህ ቅዱስ ስፍራ ስለ ታነጸው ቤተ
መቅደስ ሲናገር እንዲህ አለ። "ለመጀመርያ ጊዜ በመቃብሩ ላይ አነስተኛ የጸሎት ቤት የሰራው ሃርድያን
የተባለው የሮም ንጉሠ ነገሥት ነው ይህም በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነበር በኋላ ግን የንግሥት ኅሌኒ ልጅ
ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ለክርስቶስ ካለው ፍቅርና እናቱም ለክርስቶስ ካላት ጥልቅ ፍቅር የተነሳ በ 335 ዓ.ም
ታላቅ ቤተ መቅደስ በከፍተኛ ወጪ አስገንብቷል።" ብሏል።

ይህ ቤተመቅደስ ከታነጸ በኋላ በርካታ ክርስቲያኖች ከአራቱም መዓዘን እየመጡ አምልኳቸውን ሲፈጽሙና
ክርስትና ከፍ ብሎ ሲታይ በዚህ እጅግ የተበሳጨው የፋርስ ንጉሥ/የዛሬዋ ኢራን/ በ 614 ዓ.ም ኢየሩሳሌምን
በመውረር ቤተመቅደሱ በእሳት እንዲቃጠል አድርጓል ።በዚህ ክርስቲያኖች እጅግ ሲያዝኑና ሲተክዙ በ 630
ዓ.ም ሄራቅሊስ የተባለው የቢዛንታይን ወይም የሮም ምሥራቃዊ ግዛት ገዥ የነበረው ክርስቲያን ንጉሥ ምታ
ነጋሪት ክተት ሠራዊት ብሎ የጦር ኃይሉን ወደ ኢየሩሳሌም አዝምቶ በእግዚአብሔር አጋዥነት የፋርስን
ንጉሥና ኢየሩሳሌምን የወረረውን የአሕዛብ ሠራዊት ሙሉ ለሙሉ አጥፍቶ ቤተመቅደሱን እንደገና
አድሶታል።

ክርስቲያኖች እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ የክርስቶስን ልደትና ትንሳኤ በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት
እና የምሥጋና አምልኮ በየዓመቱ መፈጸማቸውን ቀጥለዋል።

በ 636 ዓ.ም አረቦች ኢየሩሳሌምን ሲገዙ በወቅቱ ቤተመቅደሱን ለመጎብኘት የሄደው የሙስሊሞች መሪ
ከሊፋ ሁመር የህንጻውን ውበትና ታላቅነት ከተመለከተ በኋላ ጉብኝቱን ጨርሶ ሲወጣ በውስተ ውጪ በኩል
ፊቱን አዙሮ ማለትም ለቤተመቅደሱ ጀርባውን ሰጥቶ ሰግዶ ሄዷል።ሲውል ሲያድር ግን ወደ ፊት የሚነሳው
የሙስሊሙ ትውልድ ይህንን ታሪክ ሰምቶ በዚህ ቦታ መስኪድ መሰራት አለበት ብሎ እንዳይጠይቅ ከመስጋቱ
የተነሳ ሁመር ሙስሊሞች እዚህ ቦታ ላይ መጥተው እንጸልይ እንዳይሉ የሚከለክልና ስፍራውም
የክርስቲያኖች መሆኑን የሚገልጽ አዋጅ አውጇል።
Umar wrote a decree prohibiting Muslims from praying at this location.

በ 746 ዓ.ም በኢየሩሳሌም ተነስቶ በነበረ የመሬት መንቀጥቀጥ ህንጻው የመሰነጣጠቅ አደጋ ደርሶበት የነበረ
ሲሆን በ 810 ዓ.ም በቢዛንታይኑ ፓትርያርክ በአቡነ ቶማስ አስተባባሪነት ከፍተኛ እድሳት እና ጥገና
ተደርጎለታል።
የበጎ ነገረ ጠላት የሆነው ዲያብሎስ አሕዛብን በማነሳሳት በ 841 ዓ.ም ቤተ መቅደሱን ለማቃጠል ሙከራ
ቢያደርጉም በእግዚአብሔር ድንቅ ጥበቃ ከእሳት ተርፏል።
በክርስቲያኖች መብዛትና በቦታው የሚፈጸመው አምልኮ እንቅልፍ የነሳቸው ሙስሊሞች በዛ ቦታ ላይ መስኪድ
እንሰራለን ብለው ሲነሱ በ 935 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ባሰሙት ከፍተኛ
ተቃውሞ መስኪድ እንዳይሰራ ተከላክለዋል።በዚህ ክፋኛ የተበሳጩት ሙስሊሞች በ 938 ዓ.ም ቤተ
መቅደሱን በእሳት ለማቃጠል ሙከራ ቢያደርጉም በክርስቲያኖች ርብርብ ከእሳት ተርፏል።

ክርስቲያንና ሚስማር ሲመታ የበለጠ ይጠብቃልና ይህንን የአሕዛብን ጥቃት የተመለከቱ የዓለም ክርስቲያኖች
የበለጠ እየተጠናከሩና ለቦታውም ከፍተኛ ትኩረትና እንክብካቤ መስጠት ጀመሩ።ጠላት ዲያብሎስ በክርስቶስ
ኢየሱስ ድል የተመታበትና የተቀጠቀጠበት ሥፍራ ስለሆነ ይህንን ቦታ ከዓለም ታሪክ ላይ ለማጥፋት በብዙ
ቢታገልም ኃይል የእግዚአብሔር ነውና ከቶውን አልቻለም አይችልምም።

በ 966 ዓ.ም የሙስሊም የጦር ኃይሎች ከየሀገሩ በመሰባሰብ ራሳቸውን በማጠናከር ኢየሩሳሌምን ከከበቡ በኋላ
ቀጥታ ወደ ቤተመቅደሱ በመገስገስ ሙሉ ለሙሉ በእሳት ለማጋየት ቢሞክርሙ ሳይሆንላቸው ቀርቷል
።በብስጭትም በውቅቱ በኢየሩሳሌም የነበሩትን አረጋዊ አባት ፓትርያርክ ዮሐንስ ሰባተኛን በጭካኔ
ገድለዋቸው ሄደዋል፤ ሆኖም ግን ክርስቲያኖች በድጋሚ ቤተመቅደሱን እጅግ ውብ አድርገው አደሱት።

በመጨረሻም ተስፋ ያልቆረጡት ሙስሊሞች ጥቅምት 18 ቀን 1009 ዓ.ም በዋና መሪያቸው በከሊፋ ፋቲምድ
አማካይነት ቤተመቅደሱን ሙሉ ለሙሉ ከቦታው ላይ ለማፍረስ አዋጅ አሰምተው በኃይል ሲዘምቱ በመላው
አውሮፓ ያሉ የክርስቲያን ሀገሮች ሁሉ በታላቅ ተቃውሞ ጦራቸውን አሰልፈው ለውጊያ ተነሱ የመስቀል
ጦርነትም በከፍተኛ ሁኔታ ተፋፋመ በመጨረሻም ለክርስቲያኖች እግዚአብሔር ኃይልና ብርታት ሆኗቸው
ጠላቶቻቸውን ሁሉ አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው ጦርነቱ በድል ተጠናቀቀ።

በ 1048 ዓ.ም በቢዛንታይኑ ንጉሥ በቆስጠንጢኖስ ዘጠነኛ እና በወቅቱ በነበሩት ፓትርያርክ ኒስፎሩስ
አስተባባሪነት የክርስቲያን ሀገራት ሁሉ ተረባርበው ቤተመቅደሱን እጅግ ውብና ማራኪ በሆነ ኪነ ህንጻዊ ጥበብ
በድጋሚ እንዲገነባ አደሩጉ የቤተመቅደሱንም ስያሜ CHURCH OF THE HOLY SEPULCHRE
/CHURCH OF THE RESSURECTION የትንሳኤው መቅደስ ብለው ሰየሙ።ክብርና ምሥጋና አምልኮና
ጌትነት በዙፋኑ ላለው ለትንሳኤው ጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን አሜን።

ኢየሩሳሌም በእኛ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያላት ታላቅ ሀገር ነች እንደ ሃይማኖት የክርስትናችን
መገኛ ፣እንደ ኢትዮጵያዊነት የአባቶቻችን ርስት ስፍራ ነች።

የቀደሙ የኢትዮጵያ ነገሥታትና የቤተክርስቲያን አባቶች በብዙ ወርቅና ብር በዚህ ቅዱስ ስፍራ ርስትን ይዘው
ለእኛ አውርሰውናል የአባቶቻችንን ነፍስ በሰማያዊት ኢየሩሳሌም ከቅዱሳን ሕብረት ይደምርልን።

እባካችሁ ይህንን ድንቅ ተአምርና አኩሪ ታሪክ ለሕዝብና ለአሕዛብ ሁሉ ሼር አድርጉት።

You might also like