You are on page 1of 8

ካይዘን ምንድነው?

በ PDF ከፈለጉ በቴሌግራም ቻናሌ ማግኘት ይችላሉ 👇👇👇👇👇


https://t.me/MuhammedComputerTechnology

ካይዘን የጃፓን የአሰራር ፍልስፍና ሆኖ

የአሰራር ልምዶችን፣ ብቃትን ወዘተ

በቀጣይነት ለማሻሻል የሚያስችል የአሰራር

ፍልስፍና ነው፡፡

ካይዘን - “የተሻለ ለውጥ”

· ካይዘን የደንበኛን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማርካትና የምርትና ምርታማነት ማሻሻያ መንገድ ሆኖ

የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ጥራትን ለማሻሻል ተከታታይ የሆነና የማያቋርጥ የፍልስፍና ሂደት ነው:፡

·ካይዘን በምርት ሂደት ውስጥ የሚታዩ

ብክነቶችን በማስወገድ ወይም በመቀነስ

ያለንን ሀብት በቁጠባና እና አዋጭ በሆነ

መንገድ ለመጠቀም በማስቻል ቀጣይና

የማያቋርጥ የምርት ጥራትና

ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል

አሰራር ነው፡፡

· ካይዘን ብክነትን በማስወገድ

ጥራት፣ ወጪና

የማስረከቢያጊዜያችንን በማሻሻል

ቁልፍ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

· ካይዘን የደንበኛን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማርካትና የምርትና ምርታማነት ማሻሻያ መንገድ ሆኖ

የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ጥራትን ለማሻሻል ተከታታይ የሆነና የማያቋርጥ የፍልስፍና ሂደት ነው

· ካይዘን ተከታታይ የሆነ የብቃት ዕድገት የሚያመጣ ስርዓት ሲሆን በተለይም በትኩረት ችግሮችን

ከምንጫቸው እየለየና ምላሽ እየሰጠ የሚሄድ የለውጥ ስርዓት ነው፡፡

የካይዘን አስፈላጊነትና ጠቀሜታው


በምርት ሆነ በአገልሎት አሰጣጥ ወቅት ብክነትንና አላስፈላጊ ወጪዎችን በመቀነስ፤ ሐብትን ከፍ የሚያደርግ

ነው

ምቹ የስራ አካባቢን ይፈጥራል

የደንበኛ እርካታን ያሳድጋል

የድርጅቱን የተቋሙን ዘለቄታነት ያረጋግጣል

የማምረቻ ቦታችንን በአግባ እንድንጠቀም ይረዳናል

ተከታታይ የሆነ ፈጣን ለውጦችን ያስገኛል

ተወዳዳሪነታችን እንዲጨምር ያደርጋል

የስራ እድል ይፈጥራል፤ የሐገርን ገቢ ያሻሽላል

በምርት መምረት/ አገልግሎት አሰጣጥ ወቅት እሴት የሚጨምሩ አሰራሮችን ያሻሽላል፡፡

የመረጃ ግንኙነትን በማጠናከር የአመራሩንና የሰራተኛውን ግንኙነት ያጠናክራል

የካዘን ባህሪያት

የካዘን ባህሪያት

1. ቀጣይነት ያለው መሻሻል

የካይዘን ትግበራ ያልተካሄደባቸው ቢዝነሶች ፤አምራች ድርጅቶች ምርትና ማሻሻያ

ቢኖራቸውም ቀጣይነት የለውም፡፡ በካይዘን የአመራር ፍልስፍና የታጀበ አሰራርን የሚያራምድ

ድርጅት/ተቋም/ የምርት ጥራቱ፣ ምርታማነቱና አገልግሎት አሰጣጡ ቀጣይና በማያቋርጥ ተከታታይ መሻሻል

ሂደት ውስጥ ያልፋል፡፡

2. ሁሉንም የሚያሳትፍ መሆኑ

ካይዘን ተግባራዊ በሚሆንበት ድርጅት (ተቋም) ሁሉም ሰራተኛ ከማኔጅምንቱ እስከ ታች

ሰራተኛ መሳተፍ ይኖርበታል፡፡ የሁሉም ሰራተኞች ተሳትፎ ካልታከለበት ካይዘን

ተግባራዊ ሊሆን አይችልም፡፡ በካይዘን አተገባበር የማሻሻያ ሃሳብ ከከፍተኛ አመራር ደረጃ ወደ

ታች የሚመጣ ሳይሆን በዝቅተኛ እርከን ከሚገኙ ሰራተኞች በማመንጨት ወደ ከፍተኛ

አመራሩ የሚቀርብ ይሆናል፡:በመሆኑም የተጠናከረ የግንኙነትና ሃሳብን በነፃነት

የማቅረቢያ ስርዓትን መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡

3. ብዙ ወጪ የማይጠይቅ መሆኑ
· ያለምንም ወጪ ወይም በትንሽ

ወጪ ካይዘንን መተግበር ይቻላል፡፡

· 5 ቱ ማዎችን በማስቀደም ሌሎች

የካይዘን መሳሪያዎችን ለመተግበር

የሚያስፈልገው የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት

እጅግ አነስተኛ ነው፡፡

· የካይዘንን ትግበራ ፅንሰ ሃሳብ ከግምት ውስጥ ያላስገባ የመዋዕለ-ንዋይ ፍሰት ብክነትን ያስከትላል

4. በሁሉም የዘርፍ ዓይነቶች የሚተገበር መሆኑ

በፋብሪካ፤በኢንተርፕራይዞች፤በህብረት ሰራ ማህበራት፤አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፤በቢሮ፤በቤት፤

በቦርሳችንና በኪሳችንም ሳይቀር ካይዘን ሊተገበር ይገባል፡፡

5. ትንንሽ መሻሻሎች ድምር መሆኑ

ካይዘን በራሱ ትልቅ ውጤትን ለማምጣት ይችላል በማለት የሚተገበር ሳይሆን በሚገኙ ጥቃቅን መሻሻሎች

ጥርቅም ውጤት የሚፈልገውን ግዙፍ ለውጥ የሚያመጣ የአመራር ፍልስፍና ነው፡፡

ካይዘን የትንንሽ መሻሻሎች ድምር ነው፡፡

የካይዘን ችግር አፈታት ዘዴ

ካይዘን እንደ ሌሎች የለውጥ መሳሪያዎች አንድ ጊዜ ተተግብሮ የሚቆም ሳይሆን ሁል ጊዜ ሁሉም ቦታ

ሊተገበር የሚችል የስራ አመራር ፍልስፍና ነው፡፡

· ማቀድ(ማ)

· መስራት(መ)

· አፈጻጸምን መፈተሽና ማስተካከል(መፈ)

· የተስተካከለውን ሃሳብ መተግበር(መተ)

ካይዘን እንደ ሌሎች የለውጥ መሳሪያዎች አንድ ጊዜ ተተግብሮ የሚቆም ሳይሆን ሁል ጊዜ ሁሉም ቦታ

ሊተገበር የሚችል የስራ አመራር ፍልስፍና ነው፡፡

· ማቀድ(ማ)

· መስራት(መ)

· አፈጻጸምን መፈተሽና ማስተካከል(መፈ)


· የተስተካከለውን ሃሳብ መተግበር(መተ)

ካይዘንን ለመተግበር ሚያስችሉ መሰረታዊ/አስፈላጊ አጀንዳዎች

የስራ ዕቅድ፡- የአጭርና የረጅም ጊዜ የምርት ወይም የአገልግሎት መስጠት ዕቅድ ለማዘጋጀትና ለመምራትም

ሆነ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የአመራር ችሎታ ነው፡፡

ወጪዎችን መመዝገብና የስራ መረጃዎችን መያዝ፡-

በካይዘን ትግበራ የአንድን ነጠላ ምርት ወጪ መረጃ በጣም ወሳኙና አስፈላጊ ነው፡፡ይህ ወቅታዊ የሆኑ የምርት

ወይም የአገልግሎት ወጪን ለመተንተን ብቻ ሳይሆን በካይዘን ትግበራ ወቅት ለማሻሻል ከምናስቀምጠው

ግብና የሚገኘውን ውጤት ከምርት ወይም ከአገልግሎት ወጪ አንፃር ለመለካት ያስችላል፡፡ በተጨማሪ

የተለያዩ የስራ መረጃዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡የስራ መረጃዎች ከተለያዩ የስራ አመላካቾች ጋር

የሚገናኙና ለምርት፤ለአገልግሎት ጥራት፤ለምርት ማስረከቢያ ጊዜ፤ለስራ ላይ ደህንነትና ምርት ለማምረት

ወይም አገልግሎት ለመስጠት የሚፈጅበትን ሰዓት፤የተፈጠሩ የምርት ግድፈቶች፤ የአገልግሎት ቅሬታዎችና

የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡

እምነትና ኃላፊነትን መስጠት፡- ካይዘን በከፍተኛ አመራር፤ በመካከለኛ አመራርና ለስራው ቅርብ በሆኑ

ሰራተኞች ቅንጅት የሚተገበር ነው፡፡ ስለዚህ እምነትና ኃላፊነትን መስጠት የካይዘን አመራር ፍልስፍና ሲሆን፤

· ሰራተኞች በስራ ቦታቸው ላይ ያላቸውን ተነሳሽነት መደገፍ

· አስፈላጊውን ኃላፊነት ለአመራር/ሱፐርቫይዘሮች መስጠት

· ለሰራተኞች የስልጠና ዕድል ማመቻቸትና ሰራተኛን ማመን ያስፈልጋል

የካይዘን ህግ/ደንብ

· ለደንበኛ ትኩረት መስጠቱ፤

· ቀጣይና የማያቋርጥ መሻሻል ማምጣቱ፤

· ችግሮችን የሚያሳውቅ መሆኑ፤

· የስራ ቡድኖችን ሚፈጥር መሆኑ

· የተለያየ ዕውቀት ያላቸውን ቡድኖች ውስጥሚካተት መሆኑ፤

· ትክክለኛ ሂደትን የሚከተል መሆኑ፤

· ራስን መግዛት ማሳደጉ፤

· እያንዳንዱ ሰራተኛ መረጃ እንዲያገኝ ማድረጉ


· እያንዳንዱ ሰራተኛ አስፈላጊውን ስልጠና እንዲያገኝ የሚያደርግ መሆኑ

ካይዘን ለመተግበር ምን ያስፈልጋል

· የካይዘን ዕውቀት

· ቀና አስተሳሰብ

· የሁሉም ተሳትፎ

· ፍላጎትና ድጋፍ

· ስለ ካይዘን ማስተማርና መማር

· ካይዘን በቀጣይነት መተግበር

ሊተኮርባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች

ጥራት

ጥራት ማለት አንድን ምርት ወይም አገልግሎት ለመጠቀም ተስማሚ ሆኖ ሲቀርብ ነው፡፡ ምርቱ ወይም

አገልግሎቱ የደንበኛን አጠቃላይ ፍላጎት ማሟላት የሚኖርበት ሲሆን የጥራት ቁጥጥርና የደንበኛ ቅሬታ

የአንድን ምርት ወይም አገልግሎት ጥራት የሚወስኑ ናቸው፡፡

2. ወጪ

ወጪ ማለት አንድን ምርት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት የምናወጣው የግብዓት፤ሰው

ኃይል፤የመሳሪያና ሌሎች ወጪዎች ማለት ነው፡፡ የአንድ ዕቃ ዋጋ የሚወሰነው በወጪ መርህ ሳይሆን በገበያ

ፍላጎት መሆን ይኖርበታል፡፡

በተለምዶአዊ ወይም በወጪ መርህ ዋጋ የሚወሰነው ፡- ዋጋ = ወጪ + ትርፍ

በገበያ መርህ ወይም በካይዘን ዋጋ የሚወሰነው ፡- ትርፍ = ዋጋ - ወጪ ነው፡፡

3. ምርታማነት

ምርታማነት ማለት አንድን ምርት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት

ሚያስፈልጉትን እንደ ግብዓት፤የሰው ኃይል፤መሳሪያና ሌሎች ወጪዎች በተቻለ

መጠን በዝቅተኛ ወጪ ከፍተኛ ምርት ወይም አገልግሎት ማግኘት ነው፡

የማቅረቢያ ጊዜ

የማቅረቢያ ጊዜ ማለት አንድን ምርት አምርቶ ለደንበኛ ማስረከብ የሚቻልበት

ጊዜ ነው፡፡
የስራ ቦታ ደህንነት

ምርት ወይም አገልግሎት በሚሰጥበት አካባቢ የሠራተኛውን ደህንነት

የሚጎዱትን ዕቃዎች ወይም አሰራሮች ማስተካከል ነው፡፡

የስራ ተነሳሽነት

ሰራተኛው ከዚህ በፊት ከነበረው ሁኔታ በተለየ ምርትን በጥራት በማምረት

ወይም አገልግሎትን በተሸለ መንገድ ለመስጠት ሲነሳ ነው፡፡

አካባቢያችን - የውሃ አጠቃቀም፣ የአየር መበከል፣

የድምጽ ሁኔታ፣ተረፈ ምርት……

እሴት የሚጨምርና የማይጨምር ስራ

1. እሴት የሚጨምር ስራ

· ደንበኛው በምርቱ ላይ እሴት እንደተጨመረ ሲያድርበት

· የምርቱ ዋጋ ወይም እሴት ሲጨምር

· እሴት ሲጨምር ሶስት ዳይሜንሽን አለው ፡፡እነሱም

- የሰው ኃይል፤መሳሪያ

- መረጃ

- ግብዓት ናቸው

2. እሴት የማይጨምር

እሴት የማይቸምሩ ስራዎች ብክነቶች ናቸው፡፡ስለሆነም ለምርት፤ለአገልግሎት ወይም ለሁለቱም ሂደት

ምንም አስተዋጽዖ ስለሌላቸው መወገድ አለባቸው፡፡

እሴት የማይጨምሩ ስራዎችን በማስወገድና በመቀነስ እንዲሁም እሴት ያላቸውን ስራዎች ከፍ በማድረግ

ብክነትን ማሻሻል ይቻላል፡፡

ሰባቱ የችግር አፈታት ዘዴዎች

1) የጋራ ግንዛቤ ማግኘት

ከማንኛውም ቦታ ማንኛውንም ነጥብ በማንሳት፤ አንቀሳቃሾች ለምን? ወይም ትክክል ነውን? የሚለውን

ማሰብ አለባቸው፡፡ ይህ ለካይዘን ተግባራት የመጀመሪያው ቁልፍ ነው፡፡

2) ነባራዊ ሁኔታን መረዳት


ለማንኛውም ችግር፣ የቻሉትን ያህል መረጃዎችን በማሰባሰብ ትክክለኛ የሆኑ መንስኤዎች መለየት፡፡

3) በአሃዛዊ መረጃዎች ማጣራት

አሃዛዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ እና የመመደብ ሥራ የዋና ተግባራችን አካል መሆን አለበት፤ ምን እቃ? የምን

ማሽን?፣ ማ?፣ መቼ? እና እንዴት? የሚሉት መረጃዎች የሚሞሉበት የማረጋገጫ ቅጽ ማዘጋጀት፡፡ እነዚህን

መረጃዎች በመከፋፈል በቁጥር በመመደብ የችግሩ መንስኤ በቀላሉ እንዲለይ ማስቻል፡፡

4) ዕቅዳችንን ማረጋገጥ

የተግባሮቻችን ትኩረት በሚገባ ግልጽ ማድረግ፡፡

5) መደገፍ

የሌሎች ሰዎች ድጋፍን ማበረታታት፤ ብዙ ሃሳቦች ከተለያዩ አቅጣጫ እንዲፈልቁ ማድረግ፡፡

6) የሌሎችን ሃሳብ መቀበል

የማነቃቂያ ሃሳቦችን በመጠቀም ብዙ አማራጭ ሃሳቦች እና የመፍትሄ አማራጮች ማስገኘት አለበት፡፡

7) ማስቀጠል/ማዝለቅ

ውጤቱን ካረጋገጥን ብኋላ፣ ደረጃ በማውጣት የማረጋገጫ ስርዓት በመዘርጋት ችግሩ እንዳይደገም መከላከል

አለብን፡፡

1. እሴት የሚጨምር ስራ

· ደንበኛው በምርቱ ላይ እሴት እንደተጨመረ ሲያድርበት

· የምርቱ ዋጋ ወይም እሴት ሲጨምር

· እሴት ሲጨምር ሶስት ዳይሜንሽን አለው ፡፡እነሱም

- የሰው ኃይል፤መሳሪያ

- መረጃ

- ግብዓት ናቸው

2. እሴት የማይጨምር

እሴት የማይቸምሩ ስራዎች ብክነቶች ናቸው፡፡ስለሆነም ለምርት፤ለአገልግሎት ወይም ለሁለቱም ሂደት

ምንም አስተዋጽዖ ስለሌላቸው መወገድ አለባቸው፡፡

እሴት የማይጨምሩ ስራዎችን በማስወገድና በመቀነስ እንዲሁም እሴት ያላቸውን ስራዎች ከፍ በማድረግ

ብክነትን ማሻሻል ይቻላል፡፡


ሰባቱ የችግር አፈታት ዘዴዎች

1) የጋራ ግንዛቤ ማግኘት

ከማንኛውም ቦታ ማንኛውንም ነጥብ በማንሳት፤ አንቀሳቃሾች ለምን? ወይም ትክክል ነውን? የሚለውን

ማሰብ አለባቸው፡፡ ይህ ለካይዘን ተግባራት የመጀመሪያው ቁልፍ ነው፡፡

2) ነባራዊ ሁኔታን መረዳት

ለማንኛውም ችግር፣ የቻሉትን ያህል መረጃዎችን በማሰባሰብ ትክክለኛ የሆኑ መንስኤዎች መለየት፡

You might also like