You are on page 1of 20

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ መንግስት

የግብርና ሚኒስቴር

የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ አያያዝ፣ አጠቃቀምና ልውውጥን ለመወሠን


የወጣ መመሪያ ቁጥር -----------

መስከረም … ቀን  ዓ.ም.


አዲስ አበባ

1
መግቢያ
በአገራችን ኢትዮጵያ ለግብርና ልማት እየዋለ ባለው የመሬት ሀብት በአርሶ አደሩ፣ በአርብቶ
አደሩና ከፊል አርሶአደሩ ያልተገባ የመሬት አጠቃቀም ምክንያት በአፈር ሀብት ላይ ከጊዜ ወደጊዜ
መጠነ ሰፊ ጉዳት እየደረሰ የሚገኝ መሆኑ፤

ጉዳቱን ለመቀልበስ በመንግስትና በባለድርሻ አካላት በኩል በተበታተነ መልኩ ጥረት እየተደረገ
ቢሆንም የሥራ ድግግሞሽና የሀብት ብክነት ከማስከተሉ ባለፈ በሚፈለገው ልክ ውጤታማ መሆን
ባለመቻሉ፤

የግብርናን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከጊዜ ወደጊዜ ከህዝቡ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ
እያደገ ለመጣው ፍላጎት የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም በአየር ንብረት
ለውጥ የሚከሰተውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመቋቋም የአፈር ጤንነትንና ለምነትን በዘላቂነት መጠበቅ
አስፈላጊ በመሆኑ፤

የአፈር እና ተያያዥ የአግሮኖሚ መረጃ አያያዝ፣ አጠቃቀምና ልውውጥ የአሰራር ሥርዓት


በመዘርጋት፤ መረጃዎችን በማዕከላዊ መረጃ ቋት በየፈርጁ በማደራጀት በዘርፉ የተሰማሩ አካላት
የሚፈልጉትን መረጃ በዓይነት፣ በጥራት፣ በመጠን፣ በጊዜና በቦታ ተደራሽ ማድረግ በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ህገ መንግስት አንቀፅ ፶ ንዑስ ቁጥር ()፤


የፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር
ሺ/ሺ አንቀፅ  ንዑስ አንቀጽ () እና በአንቀጽ  ንዑስ አንቀጽ ()፣ በፊደልተራ
(አ) መሰረት የሚከተለውን መመሪያ ወጥቷል፡፡

2
ክፍል አንድ
ጠቅላላ

. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ “የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ አያያዝ፣ አጠቃቀምና ልውውጥን ለመወሰን የወጣ


መመሪያ ቁጥር ---------/-----------” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

. ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-

/ “መረጃ” ማለት በተለያዩ መረጃ አመንጪ አካላት ከመስክ የተሰበሰበ ጥሬ-መረጃ፣ ከተለያዩ
ምንጮች የተገኘን በማቀናጀት የተቀነባበረ እና የተከማቸ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ነው፤

/ “የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ” ማለት የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና ተፈጥሮ ሀብትን
በዘላቂነት ለመጠቀም የሚያስችል ከአፈር ሀብት አያያዝና አጠቃቀም ጋር የተያያዘ መረጃ ነው፤

/ “ጥሬ-መረጃ” ማለት ከተሰበሰበ በኋላ ጥቅም ላይ ለማዋል ያልተቀነባበረ፣ ያልተተነተነ፣ በወጉ


ያልተደራጀና ትርጉም ያልተሰጠው ቀዳሚ መረጃ ነው፤

/ “ቀዳሚ መረጃ” ማለት በተለያዩ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ የማመንጨት ተልእኮ፡- በአሰሳ ወይም
ምርምርን መሰረት በማድረግ ከመጀመሪያው ምንጭ የተገኘ መረጃ ነው፤ሰ

/ “ውርስ መረጃ” ማለት በተለያዩ ቀደምት መረጃ አመንጪ አካላት- ቀደም ሲል የመነጨና
ለተጠቃሚዎች በግብዓትንት የሚያገለግል ሁለተኛ ደረጃ መረጃ ነው፤

/ “የተቀነባበረ መረጃ” ማለት የተለያዩ መረጃዎችን በግብዓትነት ተጠቅሞ በመተርጎም፣ በቅደም


ተከተል በማስቀመጥ፣ በማሻሻል ወይም በመቀየር ሂደት የተገኘ መረጃ ነው፤

/ “ግልጽ መረጃ” ማለት ማለት ማንኛውም ሰው በቀላሉ ሊያገኘው፣ ሊጠቀመውና ሊያጋራው


እንዲችል ሕጋዊ በሆነ መንገድ ይፋ የተደረገ መረጃ ነው፤

3
/ “በመሳሪያ ተነባቢ መረጃ ” ማለት በተለያየ ፋይል ፎርማት ተዘጋጅቶ በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ፡-
ሊቀናበር፣ ሊተነተንና ሊነበብ የሚችል መረጃ ነው፤

/ “ጂኦስፓሽያል መረጃ” ማለት በገጸ-ምድር፣ ከርሰ-ምድርና በጠፈር የሚገኙ ሰው ሰራሽ እና


ተፈጥሯዊ የመልክዓ-ምድር ስፍራዎችን ባህሪያት በመልክዓ-ምድራዊ መገኛ ማመላከቻ ነጥብ
(ጂኦሪፈረንስ) እና ሽፋን በዝርዝር የሚገልፅ መረጃ ነው፤

/ “ምስጢራዊ መረጃ” ማለት ግልፅነት ያለው የአመዳደብ ብያኔን መሰረት በማድረግ የመረጃ
ልውውጥን ሊገደብ የሚችል የተለየ የመረጃ ዓይነት ነው፤

/ “ሜታዳታ” ማለት የመረጃውን ምንጭ፣የተገኝበትን ግዜ፣ አወቃቀር፣ ጥራት፣ ባለቤትና አመንጪ
አካልን የሚገልፅ ነው፤

/ “መረጃ አመንጪ” ማለት የአፈርና አግሮኖሚ መረጃን ለተለያየ ዓላማ ለመሰብሰብ ወይም
ለመፍጠር የተሰማራ ወይም የሚሳተፍ ሰው ነው፤

/ “መረጃን አስተዳዳሪ” ማለት መረጃን ከአመንጭው አካል ወደ አንድ ማዕከላዊ የመረጃ ቋት
በማሰባሰብ የሚያስተዳር፣ የሚቆጣጠር እና [በሚደረግ ስምምነትም መረጃዎችን ?] ተደራሽ
የሚያደርግ ሰው ነው፤

/ “የመረጃ ደረጃ” ማለት በተፈጥሮ ሰውና በሕግ የሰውነት መብት ባለቸው አካላት መካከል ጥራት
ያላቸውን መረጃዎች ተደራሽ ለማድረግ፣ ለማጋራትና መልሶ ለመጠቀም የሚያግዝ የመረጃ
ጥራት ማረጋገጫ ስምምነት ሰነድ ነው፤

/ “የቴክኒክ ኮሚቴ” ማለት- በግብርና ሚኒስቴርና በሌሎች መረጃ አመንጪ አካላት ወደ መረጃ
ቋት የሚገባ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃን በተመለከተ በሚወጣ ደረጃ መሰረት ጥራትን፣
ወቅታዊነትንና ተደራሽነትን መሰረት በማድረግ መሰራቱን የሚከታተል አካል ነው፤

/ “የመረጃ መብት ባለቤትነት” ማለት በአዕምሮአዊ ንብረት ፈጠራ ባለቤትነት ወይም ከአዕምሮአዊ
ንብረት ፈጣሪው ጋር በሚደረግ ውል የተገኝ መረጃን በባለቤትነት የመቆጣጠር መብት ነው፤

/ “የሶስተኛ ወገን መብቶች” ማለት በሌላ ወገን በባለቤትነት የተያዙ ለግብዓትነት የሚውሉ
መረጃዎችን በመጠቀም የሚገኝ የተቀነባበረ መረጃ ባለቤትንት መብት፤

4
/ “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤

/ በዚህ መመሪያ ውስጥ በወንድ ጾታ የተገለጸ ሁሉ የሴት ጾታንም ይጨምራል፡፡

. ዓላማ

የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ አያያዝ፣ አጠቃቀምና ልዉዉጥ መመሪያ ዓላማ፡-

/ የስራ ድግግሞሽና የሀብት ብክነትን ለመቀነስ አገራዊ ወጥና ጥራቱን የተጠበቀ መረጃ በአንድ
ማዕከል ማደራጀት፤

/ ለፖሊሲ አውጪዎችና ውሳኔ ሰጪዎች ወቅታዊ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ በቀላሉ ተደራሽ
ማድረግ፤

/ ውርስ መረጃዎችን ከተለያዩ መረጃ አመንጪ አካላት በመቀበል በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ
ማድረግ፤

/ አዳዲስ መረጃዎችን የመረጃ ደረጃ ምደባንና አቀራረብን መሰረት በማድረግ በሚፈለገው ጥራትና

ጥልቀት ለማመንጨት ምቹ ሁኔታን መፍጠር፡፡

. የተፈጻሚነት ወሰን

ይህ መመሪያ በመላው ኢትዮጵያ ለግብርና ሚኒስቴር በሕግ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት ወሰን
ልክ፡-

/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃዎችን በሚሰበሰቡ ወይም በሚያመነጩ ወይም በሚያስተዳድሩና


በሚጠብቁ፤ እንዲሁም

/ የጂኦሰፓሻል ቴክኖሎጂንና ሳይንሳዊ ሞዴሎችን በመጠቀም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃዎችን


በመተንተን እሴት በሚጨምሩ፤መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማትና ግለሰቦች ሁሉ ላይ
ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

5
. የመረጃ መርሆዎች

የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ አያያዝ፣ አጠቃቀምና ልውውጥ አሁን ባለንበት ዲጂታል ሥርዓተ-ምኅዳር
ውስጥ ቀጥሎ በዝርዝር የተቀመጡትን መርሆዎች መሰረት አድረጎ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት
አገልግሎት የሚሰጥ መሆን አለበት፤

/ ተገኝነት (Findablity)፡ በማንኛውም መንገድ የሚገኝ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ በማዕከላዊ የመረጃ
ቋት ተደራጅቶ መከማቸትና በመረጃ ተጠቃሚው ሲፈለግ በቀላሉ የሚገኝ መሆን አለበት፤

/ ተደራሽነት (Accessiblity)፡ ማዕከላዊ በሆነው የመረጃ ቋት ውስጥ የተከማቸ የአፈርና አግሮኖሚ


መረጃ ሚስጥራዊ ካልሆነ በቀር ለሁሉም ተጠቃሚ ተደራሽ መሆን አለበት፤

/ ተናባቢነት (Interoperablity)፡ ማንኛውም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ዓለምአቀፍ ወይም


ሀገርአቀፍ የጥራት ደረጃን በማሟላት እርስ-በእርሱ የሚናበብ መሆን አለበት፤

/ እንደገና ጥቅም-ላይ-ዋይነት (Reusablity)፡ ማንኛውም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ የመረጃ


አመንጪውን የባለቤትነት መብትን ባከበረ መልኩ እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል መሆን
አለበት፤

ክፍል ሁለት
የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ተገኝነት
የአፈርና አግሮኖሚ መረጃዎች ተገኝነት ግብ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃን ከመስክ በመሰብሰብ ወይም
የተለያዩ መረጃዎችን በማቀናበር የተገኘ መረጃንና ሜታዳታን በየፈርጁ ተደራጅቶ በቀላሉ መገኘት
እንዲችል ማረጋገጥ ነው፡፡

. መረጃ ማመንጨት

/ መረጃ የሚመነጨው ጥሬ መረጃን ከመስክ ወይም ከተለያዩ ምንጮች በመሰብሰብ፣ በማጠራቀም፣


በተንተን እና ሳይንሳዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሞዴል በማድረግ ነው፤
/ የመረጃ አሰባሰብ ሂደቱ የሚከተሉትን ድንጋጌዎች ተከትሎ መሆን አለበት፡-

6
ማንኛውም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ በምርምር ወይም በፕሮጄክት ድጋፍ ሲመነጭ የመረጃ
መብት ባለቤትነትንና የማስተዳደር ኃላፊነትን ጨምሮ ስለ መረጃው አጠባበቅ በተዘረዘሩት
የተዘጋጀ ቅፅ መሰረት በፅሁፍ ተዘጋጅቶ በስምምነት ውስጥ መካተት አለበት፤

/ ማንኛውም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ሲመነጭ፡-

ሀ/ የመረጃ አሰባሰብ ደረጃን መከተል አለበት፤

ለ/ ጂኦሪፈረንስ መደረግ አለበት፤

/ የቀዳሚ መረጃን ማመንጨት ከመስክ ናሙናዎችን መሰብሰብንና ከዚያም የተሰበሰቡትን


ናሙናዎች በቤተ ሙከራ መመርመርን ያካትታል፤

/ የቀዳሚ መረጃ ሲመነጭ ብሔራዊ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ አሰባሰብን አሰራር ደረጃን የተከተለ
መሆን አለበት፣
/ የተቀነባበረ መረጃን ለማመንጨት የመረጃውን ውጤት ለማግኘት ቀድመው የነበሩት ውርስ
መረጃዎችን የማጠራቀም፣ሳንሳዊ ሞዴሎችን በመጠቀም የመተንተን እና የመተርጎም ስራዎችን
ያካትታል፤
/ የተቀነባበረ መረጃ ሲመነጭ ከአፈር መረጃና ማከማቻ የአሰራ ሂደት ጋር የተጣጣመ መሆን
አለበት፤
/ የተቀነባበረ መረጃ አመንጪዎች ለግብዓት የሚውሉ መረጃዎች ባለቤት ያወጧቸውን የፈቃድ
ግዴታዎች መከተል አለባቸው፤
/ በተቀነባበረ መረጃ ላይ ገደብ ለመጣል የሚፈጠሩት ለግብዓት የሚውሉ ግዴታዎች አስቀድመው
መቃኘትና መረጋገጥ አለባቸው፤

/ የተቀነባበረ መረጃዎች በሚያመነጩበት ጊዜ ሌሎች አካላት መረጃው እንዴት እንደመነጨ


የተከተሏቸውን ዘዴዎች (መንገዶች) በግልፅ መመዝገብ አለባቸው፡፡

. የመረጃ ሜታዳታ
/ ሜታዳታ ከታወቀና ስምምነት ከተደረሰበት ግልጥ ደረጃ ጋር የተጣጣመ መሆን አለበት፤
/ የግብርና ሚኒስቴር ለመረጃ ፍላጋ ቀላል የሆነ ተገቢ ሜታዳታ ቅጽ መኖሩን ወይም መዘጋጀቱን
የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት፤

7
/ ለአዲስም ሆነ ቀድመው ላሉ መረጃዎች ሜታዳታ መመዝገብ አለበት፤
/ የግብርና ሚኒስቴር የሜታዳታ ደረጃ በዓለም አቀፍ ግልጥ ደረጃ መሰረት መዘጋጀቱን እና
ከስምምነት ላይ መደረሱን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት፤
/ የሜታዳታው መዝገብ ቢያንስ የሚከተሉትን መረጃዎች ጨምሮ የያዘ መሆን አለበት፤
ሀ/ የመረጃ መብቶች ባለቤት፤
ለ/. የመረጃ ጠባቂው/አስተዳዳሪው፤
ሐ/ የተፈጠረበት ቀን፤
መ/ የመረጃው መልከዓ ምድራዊ ሽፋን (ተገቢ ከሆነ)፤
ሠ/ ለጂኦስፓሻል መረጃ የጂኦግራፊክ ፕሮጄክሽን፤
ረ/ የመረጃው ዓላማ፤
ሰ/ የመረጃው የፈቃድ አሰጣጥ፤
ሸ/ ለተቀነባበረ መረጃ የመረጃው ምንጭ ማብራሪያ፤
ቀ/ የታተመ ከሆነ የመረጃው ድረ-ገጽ ትስስር/ሊንክ፡፡

ክፍል ሶስት
የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ተደራሽነት
የአፈርና አግሮኖሚ መረጃዎች ተደራሽነት ግቡ በመረጃ አሰተዳዳሪው ከመረጃ አመንጭዎች የተከማቹ
መረጃዎችን የአሰራር ስምምነት በሚፈቅደው መሰረት ለተገልጋዮች ተደራሽ መሆኑን ማረጋገጥ
ነው፡፡

. መረጃን ስለማከማቸት

/ ውርስ ወይም አዲስ የሚሰበሰበሰብ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ እና ሜታዳታ በሚፈለግበት ጊዜ


ሁሉ ለማግኝት መረጃ ለመለዋወጥና ለማሰራጨት የሚያስችል ሥርዓት ተዘርግቶለት በጥብቅ
የመረጃ ቋት መከማቸት አለበት፤

/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ - ከተሰበሰበ ወይም ከመነጨ በኋላ በተቻለ መጠን ወዲያውኑ
ከመረጃው ባለቤት በሚገኝ ፈቃድ ወይም ውል መሰረት በግብርና ሚኒስቴር የመረጃ ቋት
እንዲከማች መደረግ አለበት፤

8
/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ወደ መረጃ ቋት ገብቶ እንዲከማች በመደረጉ ምክንያት የፈጠራ ወይም
የአእምሮአዊ ንብረት መብት አይተላለፍም፤

. የመረጃ ተደራሽነት

/ ማንኛውንም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃን በባለቤትነት የያዘ አካል የሰበሰበውን ወይም ያመነጨውን

መረጃ ለተጠቃሚው ተደራሽ መሆን እንዲችል መረጃውን ካገኘበት ሶስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ወደ


መረጃ መሰብሰቢያ ቋት ውስጥ እንዲከማች ማድረግ አለበት፤

/ በሶስት ወር ግዜ ውስጥ የሰበሰበውን መረጃ ወደ መሰብሰቢያ ቋት እንዲከማች ማድረግ ካልተቻለ


የመረጃ ልውውጡ እንዲዘገይ ስለተደረገበት ምክንያት ለመረጃ አስተዳዳሪው ማብራሪያ መሰጠት
አለበት፤

/ በመረጃ መሰብሰቢያ ቋት በኤሌክትሮኒክ መሳሪያ መነበብ በሚችሉበት መልክ በነባሪነት


ተከማችተው የተቀመጡ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ እንደአስፈላጊነቱ በወቅቱ ተደራሽ ማደረግ
በሚችልበት በማንኛውም የመገኛኛ ዘዴ በመጠቀም ለመረጃው ተጠቃሚዎች እንዲደረስ መደረግ
አለበት፤

/ የመረጃ ልውውጥ በግብርና ሚኒስቴር እና ከባለድረሻ አካላት ጋር በሚዘጋጅ ውስጠ ደንብ መሰረት
በመሆን በጋራ ይዘጋጃል፤

. ሚስጥራዊ መረጃን ስለመጠበቅ

/ ምስጢራዊ ነው ተብሎ የተለየ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ተደራሽ እንዳይሆን ሊገደብ ይችላል፤

/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃን ምስጢራዊ ብሎ የመመደብ ስልጣን የግብርና ሚኒስቴር ነው፤

/ የግብርና ሚኒስቴር መረጃን ምስጢራዊ ብሎ ሊመድብ የሚችለው ፡-

ሀ/ በግል ነፃነት ላይ አሉታዊ ውጤት የሚያስከትል ከሆነ፤

9
ለ/ ብሔራዊ ደህንነትን አደጋላይ የሚጥል ሆኖ ሲገኝ ፤
ሐ/ በመረጃው ባለቤት ጥያቄ በበቂ ምክንያት መረጃው እንዳይሰራጭ የጊዜ ገደብ የተጣለበት ሲሆን
ግዜው እስኪ ጠናቀቅ ድረሰ፤ እና
መ/ የሶስተኛ ወገንን መብት የሚጎዳ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡

. እንዳይሰራጭ ስለታገደ መረጃ

/ የታገደ መረጃ ሊሰራጭና ጥቅም ላይ እንዲውል አይደረግም፤


/ በዚህ አንቀፅ ንኡስ ቁጥር / የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በመረጃው ባለቤትና
በአስተዳዳሪው መካከል በሚደረግ ስምምነት ጥቅም ላይ እንዲውል ሊደረግ ይችላል፤

/ በመረጃው ባለቤት ጥያቄ ለተወሰነ ጊዜ እንዳይሰራጭ የታገደ መረጃ ታግዶ ሊቆይ የሚችለው አስከ

ሁለት ዓመት ብቻ ሲሆን በልዩ ምክንያት አስከ አምስት ዓመት ሊራዘም ይችላል፤

/ በመረጃው ባለቤት ጥያቄ ለተወሰነ ጊዜ እንዳይሰራጭ መረጃ ታግዶ ሊቆይ የሚችለው፡-

ሀ/ የመረጃ መሰብሰቢያ ጊዜ ከሶስት ዓመት በላይ ሲወስድ፤


ለ/ መረጃውን ለማሳተም ከሶስት ዓመት በላይ ሲያስፈልግ፤
ሐ/ የመረጃ ሰብሳቢው የፒ.ኤች.ዲ ተማሪ ከሆነ፤
መ/ የፕሮጄክቱ ዘመን ከሶስት ዓመት በላይ ከሆነ ብቻ ነው፤

/ በመረጃው ባለቤት ጥያቄ ለተወሰነ ጊዜ መረጃ ታግዶ እንዳይሰራጭ የጊዜ ገደቡ በመረጃው ባለቤትና
በግብረና ሚኒስቴር በሚወከል የቴክኒክ ኮሚቴ የጋራ ሥምምነት ይወሰናል፤

ክፍል አራት
የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ተናባቢነት
የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ተናባቢነት ግቡ መረጃዎች በዓለም-አቀፍ ስምምነት በተፈረመባቸውና
በሀገር-አቀፍ በወጡ ደረጃዎች መሰረት ጥራታቸውን ጠብቀው መሰራታቸውንና ለመረጃ ልውውጥ
አመችነት በኤሌክትሮኒክ ማሽኖች የሚናበቡ መሆናቸውን ማረጋገጥ ነው፡፡

10
. የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ደረጃ

/ ማንኛዉም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ አመንጭ አካል በዓለም-አቀፍ ደረጃ በስምምነት


የተፈረመባቸዉንና በሀገራችን ደረጃ የወጣላቸዉን የአፈርና አግሮኖሚ መረጃዎች ደረጃ ጋር
የተጣጣመ መሆን አለበት፤

/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ደረጃ ሲዘጋጅ የሚከተሉትን መስፈቶች መሰረት በማድረግ መሆን
አለበት፤

ሀ/ አገራዊና ዓለም-አቀፍ ደረጃዎችን በማገናዘብ፤

ለ/ መረጃው የሚመነጭበትን ቴክኖሎጂ ብቃት ታሰቢ በማደረግ፤

ሐ/ የመረጃውን ታማኒነተ፣ተናባቢነትና ጠቃሜታ ግምት ውስጥ በማስገባት ፣

መ/ የመረጃው መገኛ ቦታ በተጨባጭ መሬት ላይ መመላከቱን በማረጋገጥ ፤

. የመረጃ ልውውጥ

/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃዎችን በተለያዩ አማራጭ መንገዶች ሁሉ የመረጃ ተጠቃሚዎች እንዲጋሩ


ይደረጋል፤

/ በመረጃ ባለቤቶች አማካኝነት ወደ አገር አቀፍ ጥብቅ የመረጃ ቋት እንዲገባ የሚደረግ መረጃ በመረጃ ቋት
አስቀድሞ ከተከማቸና ከተረጋገጠ መረጃ ጋር ተናባቢ መሆን አለበት፤

/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃዎችን ልውውጥ ሲደረግ ምንጭ መጠቀስ አለበት፤

/ በአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ቋት ያልተከማቸ ምንጩ ያልታወቀና ያልተረጋገጠን መረጃ ማጋራትና ጥቅም
ላይ እንዲውል ማድረግ የተከለከለ ነው፤

/ የግብርና ሚኒስቴር ከባለድረሻ አካላት ጋር በመመካከር ዝርዝር የመረጃ ልውውጥ የአሰራር ስርዓት
በማዘጋጀት በሥራ ላይ እንዲውል ሊያደረግ ይችላል፤

/ በመረጃ ባለቤቶች አማካኝነት ወደ አገር አቀፍ ጥብቅ የመረጃ ቋት እንዲገባ የሚቀርብ መረጃ በመረጃ ቋት
ውስጥ ካለ ሌላ መረጃ ጋር የማይናበብ ሆኖ ከተገኝ፡- አጠራጣሪ የሆነው መረጃ በሁለት ሳምንት ጊዜ
ውስጥ ተስተካክሎ መቅረብ አለበት፤

11
ክፍል አምስት
የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ እንደገና ጥቅም-ላይ-ዋይነት፤
የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ እንደገና ጥቅም-ላይ-ዋይነት ግቡ መረጃ አመንጪ አካላት ያመነጯቸውን
መረጃዎች ከመረጃ አስተዳሪው ጋር በሚደረግ ስምምነት ወደ መረጃ ማዕከላዊ መረጃ ቋት
መግባታቸውን የባለቤትነት መብት ባከበረ መልክ ጥቅም ላይ መዋላቸውነ ማረጋገጥ ነው፡፡

. የመረጃ አጠቃቀም ስምምነት

/ መረጃ አመንጭ አካላት ማንኛውም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ አቅራቢ አካል ያመነጨውን መረጃ
ለማዕከላዊ መረጃ ቋት የማቅረብ ግዴታ አለበት፤

/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ለተጠቃሚው እንዲደረስ ለማድረግ - ከመረጃ ባለቤቱ ጋር የጥብቅ


መረጃ ቋት አስተዳዳሪው አስቀድሞ ስምምነት በማድረግ ደረጃውን የጠበቀ መረጃ መሰብሰብ
አለበት፤

/ የጥብቅ መረጃ ቋት አስተዳዳሪው (የግብርና ሚኒስቴር) የስምምነት ሰነዱን ቅጽ ያዘጋጃል፤

/ የሚዘጋጀው የስምምነት ሰነድ የሚከተሉትን ዋናዋና ነጥቦች መያዝ ይኖርበታል፡-

ሀ) የመረጃ ሕጋዊነት ማረጋገጫ፤


ለ) ስምምነቱ ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜና መረጃው ለአገልግሎት የሚለቀቅበት
ሐ) ሜታዳታ ገቢ የተደረገበትን ቀን፤
መ) ስምምነት የሚደረግበትን የመረጃ ዓይነት፤
ሠ) የስምምነቱ ጊዜ ሲያልቅ የመረጃው እጣ ፈንታ፤
/ በማንኛውም ጊዜ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ልውውጥ ሲደረግ የመረጃ መብት ባለቤቱ ለመረጃ
አስተዳደሪው ስለሕጋዊነቱ ማረጋገጫ ማቅረብና መረጃው ስራ ላይ እንዲውል ስምምነት መስጠት
አለበት፤

/ በማንኛውም ጊዜ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ልውውጥ ሲደረግ ከመረጃ አስተዳደሪው ለመረጃ


ተጠቃሚው ስለሕጋዊነቱ ማረጋገጫ መሰጠት አለበት፤ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ በመረጃ ባለቤቱ
እና የጥብቅ መረጃ ቋት አስተዳዳሪው መካከል ከተደረገው ስምምነት ውጪ ለሶስተኛ ወገን ተላልፎ
አይሰጥም፤

/ ወደ ጥብቅ የመረጃ ቋት እንዲገባ የተደረገ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ እላይ በአነቀፅ 


እና 
መሰረት በሚስጥር እንዲቆይ ገደብ ካልተጣለበት በስተቀር ለተጠቃሚው ተደራሽይደረጋል፤

12
/ የአፈርና አግሮኖሚን መረጃ መብት ባለቤቶች መረጃቸው ጥቅም ላይ ሲውል እውቅና ሊሰጣቸው
ይገባል፤
/ ጥርጣሬን ለማስወገድ ሲባል ይህ መመሪያ በሌሎች የአእምሯዊ ንብረት መብት ህጎች አፈፃፀም
ላይ ምንም ተፅእኖ የለውም፡፡

. የመረጃ አጠቃቀም ግብረ-መልስ

/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ አስተዳዳሪው አካል ከመረጃ ተጠቃሚዎቻቸው ጋር ተቀራርቦ

በመረጃዎቹ አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ ያሉ ክፍተቶችን ለመለየት እንዲሁም በቀጣይ ውጤታማና


ቀልጣፋ በሆነ መንገድ መረጃ ማጋራት በሚቻልበት ሁኔታ መወያየትና ግብረ-መልስ መሰብሰብ
አለበት፤

/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ አስተዳዳሪው አካል (ግብርና ሚኒስቴር) የአፈርና አግሮኖሚ መረጃን
የሚያመነጩና የሚጠቀሙ አካላት የሚሳተፉበት የተለዩ መድረኮችን ያመቻቻል፤ ከመድረኮቹ
የሚገኙ ምክረ-ሐሳቦችን ለመመሪያው ስኬታማ አተገባበርና ለቀጣይ የግብርና መረጃ ልውውጥ
ፖሊሲ ዝግጅት እንደግብዓት ይጠቀምበታል፡፡

ክፍል ስድስት
የሥራ ኃላፊነት፣ መብትና ግዴታ
. የግብርና ሚኒስቴር ተግባርና ኃለፊነት
/ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ የዚህን መመሪያ ዝርዝር የትግበራ ማንዋል ዝግጅት
ያስተባብራል አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ በአተገባበር ወቅት ክፍተቶች ወይም
ግድፈቶች ሲኖሩ የማስተካከያ እርምጃዎችን ይወስዳል፤

/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃን ለማመንጨት እና ለመጠቀም የሚያስችል ማዕከላዊ የጥብቅ መረጃ


ቋት ይገነባል፣ መረጃ ይሰበስባል፣ ያደራጃል ለመረጃ ተጠቃሚው ተደራሽ እንዲሆን ያደረርጋል፤

/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃን በማመንጨት እና በመጠቀም ዙሪያ የተሰማሩ አካላትን ይለያል፣


በአግባቡ መዝግቦ ይይዛል፣ የግንኙነት መድረኮችን ያዘጋጃል፣ አሰራራቸውን ይከታተላል፣
የግንዛቤ ማስጨበጫና የምክክር መድረኮችን እንዲሁም የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን ያካሂዳል፤

13
/ በሀገር-አቀፍ ደረጃ በተለይ በግዙፍ ፕሮጀክቶች ጥናት የመነጨ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ቅጂ
በሚኒስቴሩ መረጃ-ቋት በየፈርጁ ተደራጅቶ እንዲከማች እና የአመንጪውን የባለቤትነት መብት
ባከበረ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤

/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ማመንጨት ሥራ ላይ ለሚሰማሩ ድርጅቶች የሥራ ብቃት ማረጋገጫ


ሰርተፍኬት፤ ለግለሰቦች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣
ይሰርዛል፤

. የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ አመንጪ አካላት ተግባርና ኃለፊነት


/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃን ማመንጨት በሚፈለግበት ቦታ አላስፈላጊ ድግግሞሽን ለማስቀረት
መረጃው ቀድሞ መኖር አለመኖሩን፣ ለታሰበው ዓላማ በቂ መሆን አለመሆኑን ማረጋገጥ፤ የጥናት
ቦታ ሲመረጥ ለግብርና ልማት ሀገራዊ ፋይዳ ያለውን ቦታ ታሳቢ ማድረግ፤

/ የሥራ ድግግሞሽን እና ሀገራዊ የሀብት ብክነትን ለመቀነስ መረጃዎችን በአፈርና አግሮኖሚ መረጃ
አሰባሰብ፣ ምርመራና ትንተና ስታንዳርድ መሰረት ማመንጨት፤

/ በሥራው ላይ በዘርፉ የሰለጠነ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለውን በቂ ባለሙያ


የማሰማራት፤

/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ የሚያመነጩ ድርጅቶች የሥራ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት


የማውጣት፤

/ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ እና ሜታ ዳታው ወደ ጥብቅ


የመረጃ ቋት መከማቻ ማዕከል የማስገባት፤

/ የግብርና ሚኒስቴር በሚያዘጋጃቸው የውይይትና ምክክር መድረኮች በመሳተፍ ሙያዊ አስተዋጽኦ

የማበረከትና ተቀራርቦ ለጋራ ዓላማ በትብብር የመስራት፤

. የአፈርና አግሮኖሚ መረጃዎች ተጠቃሚ አካላት መብትና ግዴታ

/ አንድ መረጃ ተጠቃሚ መረጃ መውስድ የሚችለዉ የመረጃ መውሰጃ መስፈርቶች በድረ-ገጽ ወይም
በአካል ቀርበዉ የተዘጋጁትን ቅጾች ማሟልት ሲችሉ ነው፡፡

14
/ ማንኛዉም በግብርና ምርትና ምርታማነት ልማት ዙሪያ በቀጥታ ልማትና ምርምር ላይ በመሳተፍ
ያሉ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የግል ድርጅቶች እንዲሁም ተመራማሪና ሌሎች ግለሰቦች
የዚህ መረጃ ተጠቃሚዎች ናቸው፤

/ ከመረጃ አስተዳዳሪው በህጋዊ መንግድ የወሰዱትን መረጃ በራሳቸዉ ማስተካከያ ሳያደርጉ ከመረጃ
አመንጨዉ በወረደዉ መሰረት እንደ ግብዓት በመዉሰድ የራሳቸዉን መረጃ ማመንጭት
ወይም ቀጥታ መጠቀም ይችላሉ፤

/ ማንኛዉም የመረጃ ተጠቃሚዎች የወሰዱትን መረጃ ለሌላ ሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት
የተከለከለ ነዉ፤

/ መረጃ ተጠቃሚዎች ስለመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ከመረጃ አስተዳዳሪዉ ማብራሪያዎች ማግኜት


ይችላል፤

. የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አሰጣጥ

/ የስራ ብቃት ማረጋገጫ

ሀ/ ማንኛዉም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ የሚሰበስቡ የሚተነትኑና መረጃ አመንጭ የሆኑ


አካላት ከግብርና ሚኒስቴር የስራ ብቃት ማረጋገጫ ሰርትፊኬት መዉስድ አለባቸዉ፤

ለ/ ማንኛዉም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ የሚሰበስቡ የሚተነትኑና መረጃ አመንጭ የሆኑ


ባለሙያ ከግብርና ሚኒስቴር የስራ ብቃት ማረጋገጫ ሰርትፊኬት ሳወሰወስድ በዚህ ስራ
ላይ መሰማራት አይችልም፣

/ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ

ሀ/ ማንኛዉም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ የሚሰበስቡ የሚተነትኑና መረጃ አመንጭ የሆኑ


ባለሙያ ከግብርና ሚኒስቴር የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርትፊኬት መዉስድ አለባቸዉ፤

ለ/ ማንኛዉም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ የሚሰበስቡ የሚተነትኑና መረጃ አመንጭ የሆኑ


ባለሙያ ከግብርና ሚኒስቴር የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርትፊኬት ሳይሰወስድ በዚህ ስራ
ላይ መሰማራት አይችልም፣

/ ስለብቃት ማረጋገጫ ዕድሳት፤

15
ሀ/ ማንኛዉም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ መረጃ አመንጪ አካላት ለወሰዱት የሙያም ሆነ የስራ
ፈቃድ በየዓመቱ ማሳድስ አለበት፣

ለ/ ካላሳደሰ በመጀመሪያ ምክርና ተግሳጽ በመስጠት እንዲያሰድስ ይደረጋል፤

. የቴክኒክ ኮሚቴ ስለማቋቋም

በግብርና ሚኒስቴር በሌሎች ተቋማትና ግለሰቦች የሚመነጩ መረጃዎች ወደ መረጃ ቋት የሚገቡት


ደረጃቸዉን፣ ጥራትና ወቅታዊነታቸዉን እንዲሁም ተደራሽነት መሆን በሚችሉበት መልኩ መሰራታቸዉን
ለመከታተል የአሰራር ክፍተት ካለ የውሳኔ ሐሳባቸውን ለበላይ ኃላፊ ለማቅረብ ግብርና ሚንስቴር የቴክኒክ
ኮሚቴ ሊያቋቁም ይችላል፡፡

ክፍል ሰባት

የአስተዳደራዊ እርምጃዎች አወሳሰድ

. ማስጠንቀቂያ ስለመስጠት

/ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ አመንጪና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ፡- የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ


አያያዝ፣ አጠቃቀምና ልውውጥ የአሰራርና የአፈጻጸም መመሪያን የጣሰ እንደሆነ - ጥፋቱ
በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱን
የሚያሳግድ፣ የሚያሰርዝ ወይም ሌሎች ከባድ አስተዳራዊ እርምጃዎችን የሚያስወስድ ካልሆነ
በስተቀረ ግብርና ሚኒስቴር እንደአግባቡ የቃል ወይም የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሊሰጥ ይችላል፤

/ በተሰጠዉ ማስጠንቀቂያ መሰረት መረጃ አመንጭዉ ወይም መረጃ ተጠቃሚዉ አስፈላጊዉን


ማስተካከያ ካላደረገ በዚህ መመሪያ አንቀጽ  እና  መሰረት ተገቢዉ ርምጃ ሊወሰድበት
ይችላል፤

. የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ዕገዳ


ማንኛዉም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ አመንጭና ተጠቃሚ ከሚከተሉት ምክንያቶች በአንዱ ጥፋተኛ
ሆኖ ከተገኘ ማሰጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ ጉድለቶቹ ወይም ጥፋቶቹ እስኪስተካከሉ ድርስ የብቃት
ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱን ሊያግድበት ይችላል፤

/ የመረጃ አስተዳዳሪዉን ሳያስፈቅድ ለሶስተኛ ወገን መረጃዉን ያስተላለፈ ከሆነ

16
/ በኢትዮጵያ የወጣዉን ወይንም ሀገሪቷ የተቀበለችዉን የጥራት ደረጃዎች ያላሟል መረጃ
ያመነጨ፤

/ የመረጃ አስተዳሪዉ ያወጣቸዉን መስፈርቶች ያልጠበቀ መረጃ ካመነጨና ወደ ማዕከላዊ መረጃ


ቋት መረጃዎች ገቢ ካደረገ፤

/ በመረጃ አስተዳሪዉ ከሁለት ጊዜ በላይ የጽኁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ካላረመ፤

/ በየአመቱ ፋቀዱን ለማሳደስ ፈቃደኛ ካልሆነ፤

. የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ስለመሰረዝ


የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ አመንጭና ተጠቃሚዎች ከሚከተሉት ምክንያቶች በአንዱ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ
የብቃት ማረጋገጫዉ የምስክር ወረቀት መረጃ አስተዳደሪዉ ሊሰርዝበት ይችላል፤

/ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱ ከመሪያዉ አሰራር ዉጭ በሆነ መንግድ የተገኘ ከሆነ፤

/ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱ በማናቸዉም መንገድ ለሌላ ወገን አስተላለፎ ከተገኘ፤

/ መረጃዉን ሰርዞና ከልሶ አስመስሎ ጥቅም ላይ የዋለ ከሆነ፤

/ በአንቀጽ . የተመለከቱትን ጉድለቶች ያላረመ ከሆነ

. የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሥነ-ሥርዓት


የቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት ቅሬታዎችን የማስተናገጃ ሥርዓት አስፈላጊነት፡-በዚህ መመሪያ ምክንት
ለሚነሱ ማንኛውም ቅሬታዎች አፋጣኝ መፍትሔ በመስጠት፤ለቅሬታዎች መንስዔ ሊሆኑ የሚችሉ
ስህተቶችንና ድክመቶችን በማረም፤ እናሁሉንም የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ ባለቤትነት ባለመብትና የመረጃ
ተጠቃሚዎች በእኩልነት ለማስተናገድ የሚያስችል ፍትሐዊ አሠራር በማስፈን፤ የሰመረ የአፈርና አግሮኖሚ
መረጃ ልውውጥ ሥርዓት ግንኙነት እንዲዳብር ማድረግ ይሆናል፡፡

/ ቅሬታ የማቅረብ መብት


ሀ/ በዚህ መመሪያ አፈጻጸም ምክንያት ሕጋዊ መበቴ ተጓደለብኝ ወይም በደል ተፈጽሞብኛል
በማለት ቅር የተሰኘ - አካለ ቅሬታው እንዲታይለትና የመፍትሄ እርምጃ እንዲወሰድለት
መስሪያቤቱን የመጠየቅ መብት አለው፡፡

17
ለ/ የዘህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ፤

1/ ከመመሪያው አተረጓጎም ወይም አፈጻጸም፤


2/ ከመብቶችና ጥቅሞች አጠባበቅ፤
3/ የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት፤
4/ ሁኔታዎችን ከሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ፤
ጋር በተያያዘ ምክንያት በደል ደረሰብኝ የሚል …… ቅሬተውን ሊያቀርብ ይችላል፡፡
/ የቅሬታ ማመልከቻ
ሀ/ በዚህ መመሪያ አፈጻጸም ምክንያት ሕጋዊ መበቴ ተጓደለብኝ ወይም በደል ተፈጽሞብኛል
በማለት ቅር የተሰኘ - አካለ ቅሬታው እንዲሰማለት የቅሬታ ማመልከቻውን በዚህ መመሪያ
ለተቋቋመው የቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ ለማቅረብ ይችላል፡፡

ለ/ የቅሬታ ማመልከቻ የሚከተሉትን መያዝ አለበት፤

1/ የአመልካቹን ስምና አድራሻ፤


2/ የቅሬታውን መንሰዔ፤
3/ ቅሬታው የተፈጸመበት በታና ቀን
4/ ለቅሬታው መንስኤ የሆነውን ተግባር ፈጽሞአል የሚባለውን አካለ፤
5/ ደጋፊ ማስረጃዎች(ካሉ)፤
6/ አመልካቹ የሚሻውን መፍትሔ ወይንም እንዲሰጥለት የሚፈልገውን ውሳኔ፤
7/ ቀንና ፊርማ፤
8/ የቅሬታቸው መንስዔቸው አንድ አይነት የሆኑ ባለጉደዮች የቅሬታ ማመልከቻቸውን
በተወካያቸው አማካይነት በቡድን ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡
/ ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜ ገደብ
ሀ/ ቅር የተሰኘ ባለጉዳይ - ጉዳዩን ለሚመለከተው የሥራ ክፍል አቅርቦ ከተወያበት ቀን ጀምሮ
በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ ማመልከቻውን ለመሥሪያቤቱ የቅሬታ ኮሚቴ ሊያቀርብ
ይችላል፡፡

ለ/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት
የቅሬታውን ማመልከቻ ሊያቀርብ ያልቻለ ቀሬታ አለኘ የሚል አካል ከአቅም በላይ የሆነው
ምክንያት በተወገደ በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ ማመልከቻውን ሊያቀርብ ይችላል፤

/ ቅሬታን ስለማጣራት

18
ሀ/ በዚህ መመሪያ መሰረት የተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ የቅሬታ ማመልከቻ ሲቀርብለት
በዚህ ደንብ አንቀጽ ….. የተደነገገውን አሟልቶ የቀረበ መሆንኑን በማረጋገጥ ተቀብሎ
ይመዘገባል፡፡

ለ/ ኮሚቴው፡-

1/ የቅሬታ ማመልከቻውንና አግባብ ያላቸውን ማስረጃዎች በመመርመር፤


2/ ከአመልከቹ እና ቅሬታ የቀረበበትን ውሳኔ ከሰጠው የሥራ ኃላፊ ጋር በመወያየት፤
እና
3/ አግባብ ያላቸውን ሕጎች ፤ ደንቦች መመሪያዎችና የአሠራር ልምዶች በማገናዘብ፤
የቀረበለትን ቅሬታ ጣራል፡፡
ሐ/ ኮሚቴው የምርመራውን ውጤትና የውሳኔ ሃሳብ የያዘ ሪፖርት ማመልከቻው ከቀረበለት
ቀን ጀምር እጅግ ቢዘገይ ከ15 የሥራ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለመሥሪያ ቤቱ የበላይ
ኃላፊ ያቀርባል፡፡

/ የውሳኔ አሰጣጥ
ሀ/ የመሥሪያቤቱ የበላ ኃላፊ ወይም ወኪሉ የቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት በደረሰው ከአሥር
የሥራ ቀንናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የኮሚቴውን የውሳኔ ሃሳብ ማጽደቅ ወይም በቂ ምክንት
ሲኖረው ፤

1/ በኮሚቴው ከቀረበው የውሳኔ ሃሳብ የተለየ ውሳኔ ለመስጠት፤ ወይም


2/ ኮሚቴው ጉዳዩን እንደገና እንዲመረምር ለማዘዝ ይችላል፡፡
3/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አነቀጽ (1) መሠረት የተሰጠው ውሳኔ ለአመልካቹ በጽሑፍ
እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡
/ ቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ ስለማቋቋም
ሀ/ በዚህ መመሪያ አንቀጽ.. መሰረት የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ተቋቋሟል፤

ለ/ የቅሬታ አጣሪ ኮሚቴው አምስት አባላትና አንድ ፀሐፊ ይኖሩታል፡፡

ሐ/ የኮሚቴው ሰብሳቢ ሁለት አባላትና ፀሐፊው በመስሪያቤቱ የበላይ ኃላፊ ይመደባሉ፤

መ/ ከመረጃ ተጠቃሚዎች አንድ አባል እንዲኖር ይደረጋል፡፡

የቅሬታ ሰሚው

1/ ከመመሪያው አተረጓጎም ወይም አፈጻጸም፤


2/ ከመብቶችና ጥቅሞች አጠባበቅ፤

19
3/ የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት፤
4/ ሁኔታዎችን ከሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ፤ጋር በተያያዘ ምክንያት በደል ደረሰብኝ
የሚል ቅሬተውን ሊያቀርብ ይችላል፡፡
5/ በመስሪያቤቱ የበላይ ኃላፊ የመጨረሻ ውሳኔ ያልረካ ቅሬታ አቅራቢ በመደበኛ
ፍርድቤት ጉዳዩን አቅርቦ እንዲታይለት የማድረግ መብቱ የተጠበቀነው፡፡
/ የቅሬታ አጣሪ ኮሚቴው ተግባር
የቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ፡- ከመመሪያው አተረጓጎም ወይም አፈጻጸም፤ ከመብቶችና ጥቅሞች አጠባበቅ፤
የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት ጋር በተያያዘ የአፈርና አግሮኖሚ መረጃ መብት ባለቤቶችና የመረጃው
ተጠቃሚዎቸ የሚያቀርቡዋቸውን ቅሬታዎች እያጣራ የውሳኔ ሃሳብ ለመስሪያቤቱ የበላይ ኃላፊ የማቅረብ
ኃላፊነት አለበት፡፡

. ለሚፈጠሩ ጥፋቶች የሚወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎች፡-


በመረጃ አስተዳዳሪው መ/ቤት ሠራተኞች በኩል ለሚፈጠሩ ጥፋቶች በፌደራል መንግስት
ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፷፬/፪ሺ፲” እና የዲሲፕሊን አፈፃፀምና የቅሬታ አቀራረብ ሥነሥርዓት
የሚኒስቴሮች ምክርቤትደንብ ቁትር ፸/፻፺ አስተዳደር የዲሲፕሊንና የስነምግባር ደንብ መሰረት
የሚታይ ይሆናል፡፡

. ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸዉ መመሪያዎች


ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛዉም መመሪያ ሆነ የተለመደ አሰራር በዚህ መመሪያ ውስጥ በተጠቀሱ
ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረዉም፤

. መመሪያው የሚጸናበጽ ጊዜ


ይህ መመሪያ ከ--------------------------ቀን ----------- ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

ዑመር ሁሴን

የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር

20

You might also like