You are on page 1of 20

ለሴት ሰራተኞች ከባድ ወይም ለጤና ጎጅ የሆኑ

ወይም የመውለድ ሁኔታ የሚያውኩ ስራዎችን


ለመወሰን የወጣ መመሪያ

ግንቦት 2014 ዓ.ም


አዲስ አበባ
መመሪያ ቁጥር 811/2013
ለሴት ስራተኞች ከባድ ወይም ለጤና ጎጅ የሆኑ ወይም
የመውለድ ሁኔታ የሚያውኩ ስራዎችን እንደገና ለመወሰን
የወጣ መመሪያ፤፤
መግቢያ
 ሴት ሰራተኞች በስራ ላይ ሲሰማሩ ከተለያዩ የስራ ላይ

አደጋዎች እና የጤና ጉዳቶች ለመከላከል በተለይም ከባድ


ወይም ለጤና ጎጅ ከሆኑ ወይም የመውለድ ሁኔታን ከሚያውኩ
ስራዎች ለመጠበቅ ይቻል ዘንድ አስፈላጊ ሁኖ በመገኘቱ ይህ
መመሪያ ወጥቷል፡፡
1. አውጪው ባለስልጣን
 የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒቴስር በአሰሪና

ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ


171/1/መ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህን
መመሪያ አውጥቷል፡፡
2. አጭር ርዕስ
 ይህ መመሪያ ለሴት ሰራተኞች ከባድ ወይም

ለጤናቸው ጎጅ የሆኑ ወይም የመውለድን ሁኔታ


የሚውኩ ስራዎችን እንደገና ለመወሰን የወጣ
መመሪያ ቁጥር 811/2013 ተብሎ ሊጠቀስ
ይችላል፡፡
3. ትርጓሜ
ለዚህ መመሪያ አፈጻጸም፡-
1. "አዋጅ" ማለት የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር
1156/2011 ማለት ነው፡፡
2. "ከባድ ስራ " ማለት በደቂቃ ከ7.0 ኪ.ሎ ካሎሪ በላይ የሆነ
ሜታቦሊክ ኢነርጅ ወይም ጉልበት የሚጠይቅ የስራ
እንቅስቃሴ ነው፡፡
3. "ተከታታይነት ያለው ስራ " ማለት የስራውን እንቅስቃሴ
የመቋረጥ ባህሪ የሌለበት እና የድግግሞሽ ሂደት የሚታይበት
ሁኖ አካላዊ ጫና የሚያስከትል ወጥነት ያለው የስራ
እንቅስቃሴ ነው፡፡
4. "ከመሬት በታች የሚካሄድ የቁፋሮ ስራ " ማለት ከመሬት
በታች በመሳሪያና በእጅ ከሚደረጉ ማዕድን ቁፋሮ እና ፍለጋ ጋር
የተያያዙ ስራዎች ማለት ነው፡፡
5. " ነፍሰ-ጡር ሴት " ማለት መጸነሷ በህክምና የተረጋገጠ ሴት
ናት፡፡
6. " ጨረራ " ማለት ማንኛውም የውስጥ አካልና ህዋስን
ሰንጥቆ የማለፍ ሃይል ያለው የኤሌክትሮ ማግኔቲክ ሞገድ ነው፡፡
7. " ለጤና ጎጅ የሆኑ ስራዎች " ማለት ከስራ ጋር ተዛማጅነት
ያላቸው ወይም ከስራ ሂደት የሚመነጩና በሴት ሰራተኞች ላይ
አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት የሚያስከትል ውጤት ያላቸው
ፊዚካል፤ ኬሚካል፣ ስነ ህይዎታዊ፣ ኢርጉኖሚካልና ሳይኮሶሻል
ጠንቆች ያሉባቸው ስራዎች ወይም የስራ እንቅስቃሴዎች
ናቸው፡፡
8. "የመውለድ ሁኔታን የሚያውኩ ስራዎች " ማለት የስነ
ተዋልዶ ጤና ችግር የሚያስከትሉና የጽንስ ተፈጥሯዊ
እድገት የሚያዛቡ ስለመሆናቸው በሳይንሳዊ ምርምር
የተረጋገጠላቸው ካርሲኖጅኒክ ሙታጅኒክና ቴራቶጂኒክ
ንጥረ-ነገሮች ወይም የንጥረ ነገር ውህዶች አገልግሎት
ላይ የሚውልበት የስራ ዘርፍ ነው፡፡
9. በአዋጅ አንቀጽ 2 የተዘረዘሩት ትርጓሜዎች ለዚህ
መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
ማንኛውም በወንድ ጾታ የተገለጸው የሴትንም ጾታ
ይጨምራል፡፡
4. የመመሪያው ተፈጻሚነት
 ይህ
መመሪያ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ
ቁጥር 1156/2011 በሚሸፍናቸው አሰሪና
ሴት ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
5. ሴት ሰራተኞች እንዳይሰማሩባቸው
የተከለከሉ ስራዎች
1. ማንኛውም አሰሪ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ስራዎች ላይ ሴት ሰራተኞችን ቀጥሮ
ማሰራት የተከለከለ ነው፡፡
ሀ. በማዕድን ቁፋሮ እና ከመሬት በታች በሚካሄዱ ጥልቅ ጉድጓድ ወይም የዋሻ ቁፋሮ
ስራዎች
ለ. ጸረ- ተባይና ጸረ-አረም ውህዶችን በመቀመም፣ በመበጥበጥ፣ በመሙላት፣
በማሸግ እና በመርጨት ስራዎች
ሐ. በእርሻ ማሳዎች ውስጥ ጸረ-ተባይና ጸረ-አረም ኬሚካሎች በመርጨት ስራ
ማሰማራት የተከለከለ ነው፡፡
መ. የአስቤስቶ እና የአስቤስቶ ውህድ ንጥረ-ነገሮችን በመፍጨት ፣ በመሞረድ እና
በስራ ላይ እንዲውል በማድረግ ፡፡
ሠ. ጥልቅ ውሃ ወይም በቀላሉ ሊመረዝ የሚችል የፍሳሽ ውሃ ውሥጥ ገብቶ መስራት
6. ልዩ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው
ስራዎች
ማንኛውም አሰሪ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ስራዎች ላይ
ለተሰማሩ ሴት ሰራተኞች ልዩ የሙያ ደህንነት እና ጤንነት
ጥበቃ ሊያደርግ ይገባል፡፡
1. በብረታ ብረት ማቅለጫ፣ በኤሌክትሮ ፕሌቲንግና መካኒካል
ስራዎች በባትሪ ፋብሪካዎች ፣ ጨረር አመንጪ መሳሪያዎችን
በሚጠቀሙ ድርጅቶች የተሰማሩ ሴት ሰራተኞችን በስራ
ሂደት ለሚፈጠሩ አየር ወለድ ንጥረ-ነገሮችና የጨረር
ሞገዶች የመጋለጥ ሁኔታ በአባሪ አንድ ከተዘረዘሩት
የመጋለጫ ጣሪያ ደረጃዎች መብለጥ የለበትም፡፡
2. አሰሪወች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የስራ ዘርፎችና እንቅስቃሴዎች
ውስጥ ለተሰማሩ ሴት ሰራተኞች አመታዊ የጤና ምርመራ ያደርጋሉ፡፡
ሀ. ተስማሚ መቀመጫ በሌለበት ሁኔታ ለረጅም ስዓታት በመቆም
የሚሰሩ ስራዎች
ለ. በጤና አገልግሎት መስጫ ተቋሞች ውስጥ ከደምና ከሰውነት የውስጥ
ፈሳሽ ጋር ቀጥተኛ ግንኑኘት ያላቸው ስራዎች
ሐ. የድንጋይ መፍጮ /ካባ/ እና የድንጋይ ጠረባ ስራዎች
መ. በመንገዶች ስራ ውስጥ አስፋልት /ሬንጅ/ የማፍላትና መርጨት ስራ
ሠ. የመጸዳጃ ጉድጓዶችና የቆሻሻ ማስተላለፊያ ቱቦዎች የማጽዳት ስራ
ረ. በስራ ባህሪያቸው ከፍተኛ ቅዝቃዜ /Cold / እና ከፍተኛ
ሙቀት /Hot / ባላቸው የስራ ዘርፎች
ሰ. የንዝረትና ሰውነትን የማንዘፍዘፍ / Vibration / ባህሪ ያላቸው
ስራዎች፡፡
7. ለነፍሰ ጡርና ለሚያጠቡ ሴት ሰራተኞች የተከለከሉ
ስራዎች

 በዚህመመሪያ አንቀጽ 5 እና 6 ከተጠቀሱ ስራዎች


በተጨማሪ በአባሪ 2 የተዘረዘሩ ለስነ ተዋልዶ ጤና
ችግር መንስኤ ለሆኑ ንጥረ- ነገሮችና የንጥረ ነገር
ውህዶች በቀጥታ የሚያጋልጡ ማናቸውም የስራ
እንቅስቃሴዎች ለነፍሰ ጡር ሰራተኞችነ ከወሊድ
በኋላ እስከ 6 ወራት ድረስ ለሚያጠቡ ሰራተኞች
የለከለከሉ ናቸው፡፡
8. ለሴት ሰራተኞች የተወሰነ የክብደት መጠን
1. የሴት ሰራተኞችን ጉልበት በመጠቀም የሚካሄድ
ማናቸውም ክብደትን ከቦታ ቦታ የማንቀሳቀስ ፣
የመሸከም፣ የማጓጓዘረ፣ የማንሳት፣ የማውረድ፣
የማውጣት፣ የመጎተት፣ የመሳብ እና የመሳሰሉት
ስራዎች ከዚህ ቀጥሎ የተመለከተውን የክብደት መጠን
ጣሪያ ሳያልፉ ይከናዎናሉ፡፡
ሀ. እንቅስቃሴው ሙሉ በሙሉ በእጅ ሁኖ፡-
1. ተከታታይነት ላለው ስራ እስከ 15 ኪ.ግ
2. ተከታታይነት የሌለው ስራ እስከ 25 ኪ. ግ
ለ. እንቅስቃሴው ሙሉ በሙሉ በእጅ ሁኖ ዳገት
የመውጣትና ቁልቁለት የመውረድ ሁኔታ ባለበት፡-
1. ስራው ተከታታይነት ካለው የእቃው
ክብደት እስከ 10 ኪ. ግ
2. ስራው ተከታታይነት ከሌለው የእቃው ክብደት
እስከ 15 ኪ. ግ
ሐ. እንቅስቃሴው ባለአንድ እግር ጋሪ በመጠቀም ከሆነ
የእቃው ክብደት እስከ 50 ኪ.ግ
9. ስለ ሃላፊነት
ማንኛውም አሰሪ የሚከተሉት ሃላፊነቶች መፈጸም ይኖርበታል፡-
1. ሴት ሰራተኞች ወይም ነፍሰ ጡር ሰራተኞች ወይም የሚያጠቡ
ሰራተኞች የሚሰሩት ስራ ክልከላ የተደረገበት ሁኖ ከተገኘ የስራ
ደረጃቸውና ደመወዛቸው ሳይቀንስ ወደ ሌላ የስራ መደብ አዛውሮ
የማሰራትና በጠንቆቹ ምክንያት የጤና ጉዳት ያለመከሰቱን ማረጋገጥ
2. በዚህ መመሪያ የተጠቀሱትና ክልከላ የተደረገባቸው ወይም ልዩ
የሙያ ደህንነትና ጤንነት ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውን የስራ
እንቅስቃሴዎች አስመልክቶ ሴት ሰራተኞች ሊያደርጉት ስለሚገባው
ጥንቃቄ መረጃና የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መስጠት
3. የመመሪያውን አተገባበር በተመለከተ ሚኒስትሩ ወይም አግባብ
ባለው ባለስልጣን የሚሰጡ ትዕዛዞችን ተፈጻሚ ማድረግ
4. ለሚኒስትሩ ወይም አግባብ ላለው ባለስልጣን በግማሽ ዓመት አንድ
ጊዜ የአፈጻጸም ሪፖርት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
10. የመተባበር ግዴታ

 ማንኛውም የሚመለከተው አካል ወይም


ግለሰብ ይህ መመሪያ ተግባራዊ እንዲሆን
የመተግበር ግዴታ አለበት፡፡
11. ስለ ቅጣት

 ማንኛውም አሰሪ በዚህ መመሪያ


የተዘረዘሩ ድንጋጌዎችን ቢጥስ በአሰሪና
ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር
1156/2011 ስለ ቅጣት የተመለከቱ
ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆኑበታል፡፡
12. መመሪያውን ስለ ማሻሻል
ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የዚህን
መመሪያ አፈጻጸም በየወቅቱ
እየገመገመ ሊያሻሽል ይችላል፡፡
13. የተሻለ መመሪያ

ለሴትሰራተኞች ከባድ ወይም


ለጤናቸው የመውለድን ሁኔታ
ስለሚያውኩ ጎጅ የሆኑ ስራዎችን
ለመወሰን ሚያዝያ 2005 ዓ.ም
የወጣው መመሪያ ተሽሯል

sound industrial relation benefit all 03/01/2023


14. መመሪያው ስለሚጸናበት ጊዜ
 ይህመመሪያ በሚኒስትር ከተፈረመበት ከነሃሴ
12 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡
አመሰግናለሁ!!

You might also like